cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Abu mahir lbnu kedir

የዚህ ቻናል አላማው ኢስላማወዊ ትምህርቶችን በቁርኣንና በሀዲስ ማስረጃ ተደግፎ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ስለዚህ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶቻቹን አድ በማድረግ ተባበሩን ጀዛኩም አሏሁ ኸይር

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 518
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+17 kunlar
+3030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ለዒድ አል-አድሃ በዓል የሀገር ቤት ጉዞ —————ክፍል 1 ለሙስሊሞች መደሰቻ ሁለት ታላላቅ በዓላትንና የጁምዓ እለትን ለደነገገው ለዓለማቱ ጌታ አላህ የላቀ ምስጋና ይገባው!!። እንደሚታወቀው ከነዚህ ውጪ ሌላ በሸሪዓ የተደነገገ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ያለው ኢስላማዊ በዓል የሚባል ነገር የለም!!። እነዚህ በዓላትም መለኮታዊና ከአምልኮ የተያያዙ ናቸው። በዚህ በተከበረው የዚል-ሒጃ ወር አቅማቸው የፈቀደላቸው ሰዎች፣ የጉዞውን ጣጣ የቻሉ ሰዎች የተከበረውንና መጎብኘቱ ግዴታ የሆነውን ብሎም መጎብኘቱ ከአምስቱ የእስልምና ማእዘናት የሆነውን የአላህን ቤት ለመጎብኘት የሚጓዙት በርካቶች ናቸው። ይህን ያልቻሉ ደግሞ ቤተሰባቸው የተለያየ ክ/ሀገራትና ገጠር ያሉ ወገኖች ከቤተሰባቸው ለማሳለፍ ወደተለያዩ ክ/ሀገር ከተሞችና ገጠር ይጓዛሉ። ይህ ጉዞ አላህን ማመፅ ካልተቀላቀለበትና እስከ ፍፃሜው አላህን መታዘዝ ከሆነ ምንኛ ያማረ ጉዞ ነው!። ይህ ጉዞ ለመልካም ነገርና ለቤተሰብ ዚያራ በመሆኑ የሚያስደስትና እጅግ የሚወደድ ቢሆንም፣ ተጓዦች አላህ (ይጠብቀንና) አላህን አያምፁበትም ፍፁም የሆነ ጉዞ ነው ማለት ግን አይደለም። በመሆኑም ተጓዦች ከእነዚህ አላህን በእጅጉ ከሚያስቆጡ ስህተቶች እንዲቆጠቡ ማስታወሱ ግድ ነው። » እንዲያውም ገና ጉዞው ሲጀመር በተከበረው ዘጠነኛው ቀን፣ ያንን (የዚል-ሂጃ 9ኛ) ቀን መፆሙ ያለፈውንና የሚቀጥለውን ዓመት ወንጀል ያስምራል በተባለው የተከበረ ታላቅ ቀን፣ አላህ ሀራም ያደረገውን የከበደ ወንጀል አደንዛዥ እፅ የሆነውን ጫት እየበላ የሚጓዘው ህዝብ ከተጓዦች አብዘሃኛው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም!። ጥቂት አላህ ያዘነላቸው ባሪያዎቹ ሲቀሩ አብዘሃኛው ተጓዥ ይህን አደገኛና አላህ ሀራም ያደረገውን አደንዛዥ እፅ እየበላ መጓዝ የተለመደ እየሆነ ነው። በዚሁ አጋጣሚ ጫትን ለማይቅሙትና የዲን እውቀት ላላቸው ለጥቂቶች አንድ መልእክት አለኝ:- (ከሚቅሙ ሰዎች ጋር ተቀላቅላችሁ የምትሔዱ ካላችሁ በራሳችሁ ላይ አንድ ግዴታ ነገር ጥላችኋል፣ እሱም:- የተወገዘን ነገር ማውገዝ ነው!። አላህ ሀራም ያደረገውን ነገር ሲተገበር ዝም ካላችሁ እንደ ዲዳ ሸይጧን መሆናችሁን አትዘንጉ!፣ ማውገዝ ወይም መከልከልና ደዕዋ ማድረግ ካልቻላችሁ ጫት ከማይቅሙና ዘፈን ከማይከፍቱ ከቢጤዎቻችሁ ነው መሄድ ያለባችሁ።) ታዲያ በጥቅሉ ጫትን በየተኛውም ጊዜ የምትቅሙ ሰዎች አላህን ልትፈሩ ይገባል!! ምንም ጥቅም የሌለውን አካልን የሚጎዳ፣ ገንዘብን የሚያባክን፣ አደንዛዥ የሆነን ነገር ሸሪዓችን እርም አድርጓል። ↪️ ጫት አካልን ጎጂ መሆኑን ታምኑበታላችሁ! እራስን የሚጎዳ ነገር መጠቀም ደግሞ አላህ ሀራም አድርጓል!! ↪️ ጫት ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለውና ገንዘብን እንደሚያባክን ታውቃላችሁ!! አባካኞች የሸይጧን ጓዶች መሆናቸውን ደግሞ አላህ በቁርኣኑ ተናግሯል። ↪️ ጫት አዕምሮን እንደሚቀይር ታምናላችሁ! አዕምሮን የሚቀይር ነገር ደግሞ ከአስካሪ መጠጥ ነው። አስካሪ መጠጥ በእስልምና ሀራምነቱ ደግሞ እንኳን ለሙስሊሞች ለከሀዲውም ግልፅ ነው!! እነዚህን ጥቂት ጫትን ሀራም የሚያደርጉ ነጥቦች አብዘሃኛው ጫት ቃሚ "ለእውነት ሲባል" ብሎ ያመነባቸውና የጤና ባለ ሞያዎች ያረጋገጡት እውነተኛ ጫት የሚያስከትላቸው አደጋዎች እንጂ ከራሴ የሆኑ ፈጠራዎች አይደሉም!። ከላይ ለጠቀስኳቸው ነገሮች ማስረጃን ያልጠቀስኩት ከምንም በላይ ማስረጃው ግልፅና የሚታወቅ ከመሆኑ አንፃር ፅሁፉ እንዳይረዝም ብዬ ነው። ➡️ ከዚህ ጉዞ ሌላው ጥፋትና ከባድ ወንጀል ዘፈን፣ ነሺዳና መንዙማ እየተደመጠ መጓዙ ነው!!። ዘፈን አንዳንዶች ዘንድ ባህላዊ (በቋንቋቸው) ሲሆን ልክ እንደ ሙሃደራ (ሀዲስ) የሚቆጥሩት አሉ፣ ይህ ደግሞ በጥፋት ላይ ሌላ ጥፋት ነው።  በዘፈን ሀራምነት ሙስሊም ሆኖ የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም። አውቆ ማጣመም ፈልጎ ካልሆነ በስተቀር!፣  ምናልባትም ከአንዳንድ ጠሞ አጥማሚዎች ብዥታ የሚወድቅበት ሊኖር ስለሚችል እስቲ በጥቂቱ የሚከተሉትን ማስረጃዎችን እንመልከት፣ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏል:- {وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ} الإسراء ٦٤ “ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል።” አል-ኢስራእ 64 “በድምፅህ አታል” የሚለውን በዘፈንና በአሎባልታ ጫወታ በዛዛታ ማለት ነው ተብሏል። ኢብን ከሢር የተሰኘው የቁርኣን ማብራሪያ ላይ ይህን አንቀፅ በሚያብራራው ቦታ ይመልከቱ። አላህ የመልካም ባሪያዎችን ባህሪ ሲገልፅ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:- {وَالَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ الزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا بِاللَّغْوِ مَرُّوا كِرَامًا} الفرقان ٧٢ “እነዚያም በውሸት የማይመሰክሩ፣ በውድቅ ቃልም ተናጋሪ አጠገብ ባለፉ ጊዜ የከበሩ ሆነው የሚያልፉ ናቸው።” አል-ፉርቃን 72 “ውድቅ ቃል” በማለት የተጠቀሰው ዘፈን ነው ተብሏል። ኢብን ከሢርን ይህን የቁርኣን አንቀፅ በሚያብራሩበት ቦታ ይመልከቱ። አላህ በተቀደሰው ቃሉ ሙሽሪኮች ቁርኣን ከመስማት እንቢተኛ መሆናቸውንና ለቁርኣን ጀርባ መስጠታቸውን ሲያወግዝ እንዲህ ብሏል:- {أَفَمِنْ هٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ{٥٩}وَتَضْحَكُونَ وَلَا تَبْكُون {٦٠}وَأَنتُمْ سٰمِدُونَ} النجم ٥٩–٦١ «ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?፣ ትስቃላችሁምን?፣ አታለቅሱምን? እናንተ ዘንጊዎች ናችሁ።» አን-ነጅም 59-61 “እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ” የሚለውን ታላቁ ሷሃባ ዐብደላህ ኢብን ዐባስ እና ሱፍያን አስሰውሪ…የመሳሰሉ ሌሎችም “እናንተ ዘፋኞች ናችሁ” ማለት ነው የተፈለገበት በማለት ተናግረዋል። ኢብን ከሢር የቁርኣን ተፍሲርን ይመልከቱ። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ በጠንካራ ሰነድ “ዘፈን በልብ ውስጥ ንፋቅን እንደሚያበቅል” መናገራቸውም ተዘግቧል። ስለ ዘፈን ሀራምነት ከቁርኣን አንቀፆች ባሻገር የተለያዩ እጅግ በርካታ ሶሂህ (ትክክለኛ) ሀዲሶች አሉ! ጊዜን ለመቆጠብና ፅሁፉ እንዳይረዝም ከሀዲስ ምንም አልጠቀስኩም። ዘፈንና ነሺዳን በተመለከተ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎችን በሰፊው ማንበብ የፈለገ የሚከተለውን ሊንክ ተጭኖ pdf ን አውርዶ ያንብብ። ስለ ነሺዳና ዘፈን ⤵️ pdf https://t.me/IbnShifa/933 ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Hammasini ko'rsatish...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

ነሺዳ የሱፊዮች እና የኢኽዋኖች ዘፈን እንጂ ኢስላማዊ አይደለም!! PDF """"""" በኢብን ሽፋ ከ 4አመት በፊት 1439 ዓ.ሂ ላይ ነሺዳን በተመለከተ ከኢኽዋኖችና ሱፊዮች ዘንድ ለሚነሱ ብዥታዎች አንድ በአንድ በቁርኣንና በሀዲስ የተሰጠ መልስ #share #ሼር_አድርጉት! የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ

https://telegram.me/IbnShifa

https://telegram.me/IbnShifa

ይህ የወንድም አቡ ዘከሪያ ሙሐመድ አል-ወልቂጢይ በብሎክ ሁለት አይን ለከፈቱ ጀማሪዎች ቻናል ላይ የተለቀቁ የተጠናቀቁ ዱሩሶች በቅደም ተከተል ያለበት ሊንክ ነው። 1ኛ, ኪታቡ ተውሒድ ፈውዛን ➴➴➘➴➴➘➴➴ https://t.me/Muhammed_al_wolkite/35 2ኛ, ሙዕተቀዱ ሶሒህ ➴➴➘➴➴➘➴➴ https://t.me/Muhammed_al_wolkite/112 3ኛ, አዱረቱል በሒያ ➴➴➘➴➴➘➴➴ https://t.me/Muhammed_al_wolkite/205
Hammasini ko'rsatish...
✅ #አዲስ_ሙሐደራ ↙️عنوان ➘➘➘ ↩️ ««فضائل وأعمال عشر ذي الحجة» ↘️ ርዕስ➘➘➘ ↪️ «የ አስሮቹ የዙል-ሂጃ ቀናቶች ትሩፋትና ስራዎች» 🎙 للأستاذ أبي البخاري مبارك بن إبراهيم «حَفِظَهُ اللَّهُ» 🎙በኡስታዝ ሙባረክ ኢብራሂም አቡል ቡኻሪ (ሀፊዘሁላህ) ✅ትምህርቱን ለመከታተል ቻናሉን #join በማድረግ ይቀላቀሉ👇👇 t.me/mubarekabulbukhary t.me/mubarekabulbukhary
Hammasini ko'rsatish...
የ_አስሩ_ዙል_ሂጃ_ቀናት_ትሩፋትና_ስራዎች.mp39.23 MB
Photo unavailableShow in Telegram
በዚህ የአላህ እዝነት በተከፈተበት ወቅት የሆነ ትልቅ የኸይር በር ልጠቁማችሁ ወደድኩ https://t.me/Abdurhman_oumer/8365?single 👆 ዳሩ ሱና አሁን ያለበትን ቦታ የራሱ ለማድረግ እኔ እበቃለሁ ብሎ ዱንያ ላይ የአላህን ቤት በመገንባት ጀነት ላይ ቤት እንዲገነባለት በቁርጠኝነት የሚነሳ ጀግና ካለ ላስታውሰው ወደድኩ ለዚህ ትልቅ ኸይር ስራ እኔ አለሁ የሚል በሚተሉት የአካውንት ባለቤቶች በእነ (ሙስጠፋ… ) ማስገባት ይችላል። ንግድ ባንክ 1000542222682 ዘምዘም ባንክ  0024246020101 ጁሙዓን በዳሩ ሱና ሰግጀ ገደም ብየ ሳለ ይሄን ኸይር ስራ ጠቁሜ ከአጅሩ ተቋዳሽ ብሆን ብየ ነው ያካፈልኳችሁ ሌሎቻችሁም ሼር በማድረግ ከአጅሩ ተቋዳሽ ለመሆን ተጣደፉ
Hammasini ko'rsatish...
👉 አዲስ ኪታብ pdf عنوان:- لزوم السنة في شرح أصول السنة ሱናን አጥብቆ መያዝ በሚል ርእስ የተዘጋጀ የኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሀንበል (ረሂመሁላህ) ኡሱል አስ-ሱንና ኪታብ ማብራሪያ للشيخ الفاضل الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي حفظه الله ✍🏻አዘጋጅ:- የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ እና የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ ኣደም ተማሪ የሆኑት ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ) ከሳዑዲ ዐረቢያ መከተ'ል መከረመህ 🔸በዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም ቻናል በonline ጁምዓ፣ ቅዳሜና እሁድ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በሸይኹ በራሳቸው እየተቀራ ነው በአማርኛ ስለሚብራራ ሁሉም መከታተል ይችላል ቴሌግራም ቻናል ⤵️ https://t.me/HussinAssilty https://t.me/HussinAssilty (ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት) የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
Hammasini ko'rsatish...
شرح أصول السنة.pdf2.17 MB
الشيخ الألباني يحكي حال المميعة قال العلامة الألباني -رحمه الله-: " على طالب العلم أن يقف عند قوله الله عز وجل: { ولا تقف ما ليس لك به علم إن السمع والبصر والفؤاد كل أولئك كان عنه مسؤولا } فعلى طلاب العلم أن يعرفوا حدَّهم وأن يقفوا عند ما عرفوا من أنفسهم، وقد قيل قديما: من عرف نفسه فقد عرف ربه ولا يجوز لطلاب العلم أن يدخلوا فيما لا قِبَل لهم به، فإن ذلك يحملهم على المدابرات والمقاطعات والمكاتبات، التي لا تأتي إلا بالشر ". 📚الهدى والنور ٨٦
Hammasini ko'rsatish...
Repost from Abdusomed Muhamed
ምንድነው አላማህ የምትለፋበት? መቀላቀል ሆነ የሌለው መሰረት እሳትን ከውሃ ካልቀላቀልኩ ማለት ምንድነው አላማህ የምትለፋበት ምንድነው መሮጡ ከርስህን ለሞምላት ንቃ እንጂ ወንድሜ ዱንያኮ ጠፊ ናት ተውሂድና ሱናን አትነግድበት ለሚጠፋ ነገር ለማትዘዎትርበት የሱና ወንድሜ ፅና ባለህበት አላህ ይጠብቀህ እስክንሰናበት ✏️አቡ ፊርደውስ https://t.me/abdu_somed https://t.me/abdu_somed
Hammasini ko'rsatish...
Abdusomed Muhamed

دروس وفوائد أبي فردوس

https://t.me/abdu_somed

"منهاج الفرقة الناجية والطاءفة المنصورة " ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ለሚንሃጁል ፊርቀቲን ናጂየቲ ወጥጥጧኢፈቲል መንሱረቲ" ➴➴➴➴➴ ==================== በሸይኽ ሙሐመድ ብን ጀማል ዘይኑ ረሂመሁሏህ ተዘጋጅቶ ➴➴➴➴➴ ==================== ትርጉም:‐ አቡ ዓብዲልዓዚዝ/ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ በቻልነው ሁሉ ለሌሎች እንዲደርስ የበኩላችንን እናበርክት ➴➴➴➴➴ ==================== የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ كن على بصيرة https://t.me/alateriqilhaq
Hammasini ko'rsatish...
منهج_الفرقة_الناجية_والطائفة_المنصورة_2.pdf1.71 MB
ቀጣይ   በያኑ ማፊ ነሲሀቲ ኢብራሂም…የሚለው ኪታብ ደርስ ተጀምሯል ገባ ገባ በሉ👇👇👇👇 https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=b0dfa2ef81cdf4141a
Hammasini ko'rsatish...
ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel

ይህ የዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው مركز دار السنة لتعليم الشريعة الإسلامية Dar As-Sunnah Sharia Knowledge Center አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን። ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

Hammasini ko'rsatish...
ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel

ይህ የዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው مركز دار السنة لتعليم الشريعة الإسلامية Dar As-Sunnah Sharia Knowledge Center አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን። ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031