cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የግጥም ረመጥ✍️

የግጥም ረመጥ አንዴ join ካሉ ሱስ የሚያስይዙ ግጥሞች የሚያገኙበት ስለፍቅር ስለሀገር ስለቤተሰብ ስለሁሉም ጉዳዮች የተገጠሙ ግጥሞችን የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል ከግጥም ቻናሉ ያልተስሞሟት ነገር ካለ እንዲስተካከል አስተያየት ይስጡን እናስተካክላለን። ለአስተያየቶች @SUNMAN111 👈👈 ይህን ይጠቀሙ። @Abelaaaaam @Abelaaaaam @Abelaaaaam

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
536
Obunachilar
-124 soatlar
-47 kunlar
-1130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ደካማ መሆንን አትፍራ ጠንካራ በመሆንህ አትኩራ ማንም ምንም አለም ያሻዉን ይበል ዕራስህን ሁን መንገድህን ተከተል ዕድልህን ተጠቀምበት እንጂ አትልቀቀዉ ወደ ገርነት መመለስን አትተዉ
Hammasini ko'rsatish...
3
ብሔር ና ክልል _ ዘር ቀለም አልመርጥም ፣ ሁሉም የሰዉ ልጅ ነዉ _ አላበላልጥም ፣ በፍቅር ጎዳና _ ካገኘኋት ጓዴን እድሌን ልሞክር _ ልጀምር መንገዴን ። nahom
Hammasini ko'rsatish...
1
ኢትዮጵያዊነት ነዉ አሸንድዬን ላከብር ትግራይ ተሻግሬ መጣሁ ወደ ደቡብ አክሱም ላይ አድሬ ቀናት ቆጥሬ ... የማከብርበትን ደማቅ በዓል ፍቼ ጨምበላላ ሲሉ ዝናዉን ሰምቼ ሸገር ላይ አድሬ ሲነጋ ሲዳማ ወግና ባህሉን ለዓለም ላሰማ ፤ ለምን እቀራለሁ ኦሮሞስ መጓዜን ልሻገረዉ እንጂ ሸካክፌ ጓዜን ለማክበር ኢሬቻን ። መስቀል ደረሰና ሄድኩኝ ከጉራጌ ኢትዮጵያዊነት ነዉ ባህልና ወጌ ገና ' ን ላሊበላ ጥምቀትን በጎንደር አማራ ተጉዤ በአላቱን ሳከብር ትዝ አለኝ በድንገት ቁልቢ ገብርኤል አሁን ደሞ ሀረር ጉዞዬን ልቀጥል እሄዳለሁ አፋር ቤንሻጉል ሶማሌ ኢትዮጵያዊነት ነዉ ወግና ባህሌ ናዝሬት ድሬ ደዋ ወላይታ ጋምቤላ ከሀበሻ ምድር ... የሚወደድ እንጂ የለም የሚጠላ በነጻነት ምድር በሰሜን በደቡብ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ በምስራቅ በምዕራብ ሁሉንም አያለሁ ኢትዮጵያን በሙሉ መገለጫዬ ነዉ ወግና ባህሉ ። ናሆም
Hammasini ko'rsatish...
2
የእናት _ ፈገግታዋ አንቺ ስትከፊ _ ጨረቃም ተከፋች ንፋስ አልነፈሰ ፀሀይ እንኳን ጠፋች አንቺ ስትከፊ _ ሰማይ ተቆጣ ደመና አልዳመነ ዝናብም አልመጣም አንቺ ስትከፊ _ አለም ጎዶሎ ናት ኑሮ ኑሮ አይደል ህይወትም ጣ ' ም ' የላት አንቺ ስትከፊ _ ቀኑ ይጨልማል ጨለማዉ ያስፈራል እናማ እናቴ ችግርሽ ይቸገር ማጣትሽም ይጣ ደመናዉ ይገፈፍ ፀሀይሽም ትዉጣ መከፋትሽ ይክፋዉ ሐዘንሽም ይዘን እንባሽ የሳቅ ይሁን ጥርስሽ አይከደን ጎዶሎ ቀን አትይ ሁሉ ይሁን ተድላ አንቺ ስትስቂ ነዉ የኔ ቀን ' ሚሞላ
Hammasini ko'rsatish...
4
ሰላም እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜን እንኳን አደረሳችሁ
Hammasini ko'rsatish...
1
ለእኛ ተሰቃየ ተንገላታ እግዚአብሔር ያሰቃዩትን ያንገላቱትን አባት ሆይ የሚያረጉትን አያቁም እና ይቅር በላቸዉ ብሏል እሱ እንኳን ጌታ የአለም መድሀኒት የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ እንኳን ያሰቃዩትን ያንገላቱትን ይቅር ብሏቸዋል እኛስ ይኸዉ ዛሬም ቂም ይዘን ቁርሾ ይዘን በቀል ይዘን ይኸዉ ወንድም ወንድሙን እህት እህቷን እየተጋደልን እየ ገደልን ነዉ እራሳችንን እየገደልን መሆኑን እረስተን ያለፈ ነገር ይዘን ቂም ቁርሾ በቀል ይዘን ይኸዉ ይቅር መባባል አቃተን ለልጅ ልጆቻችን ምንድነዉ ምናወርሳቸዉ እነሱም ይቅር መባባል ያቅታቸዉ ለልጆቻችን ለልጅ ልጆቻችን ለትዉልዱ መገዳደል ነዉ ምናስተምራቸዉ መገዳደልን ነዉ ምንተዉላቸዉ እነሱም ነገ አድገዉ ወንድም እና እህቶቻቸዉን በአንድ አምሳል የተፈጠሩትን ይግደሉ አድገዉ እነሱም እንደኛ መሆን ይፈልጋሉ ልጆች የእናት እና የአባታቸዉን ድርጊት ይዘዉ ነዉ የሚያድጉት ምክንያቱም እነሱ ብለዉ ሚያስቡት እማዬ ትክክል ናት ጥፋት የለባትም አባዬ ትክክል ነዉ ጥፋት የለበትም ብለዉ ነዉ ሚያስቡት ስለዚ እኛ ለዚች አለም እንግዳ ነን ወደ ማይቀረዉ ቤታችን እንሄዳለን በኋላላይ ከሚፀፅተን አሁኑኑ ቆም ብለን እናስብ እናት እና አባቶቻቸዉ ሲሞቱ በነሱ ስም ነዉ ሚጠሩት ይሄ የከሌ ልጅ ነዉ ሰዉ ሚገለዉ ነዉ የሚባለዉ ስለዚ ቆም ብለን እናስብ ለልጅ ልጆቻችን ትተነዉ ምንሄደዉ ጠለንላቸዉ ምንሄደዉ ጥላቻን መገዳደል ሳይሆን ዛሬ ስንገድል ለልጅ ልጆቻችን መግደልን እያስተማራቸዉ ነዉ ጥላቻን እያስተማራቸዉ ነዉ ስለዚ ቆም ብለን እናስብ ጥላቻን መገዳደል ሳይሆን ፍቅርን ይቅርታን ትተን እንለፍ ሞት እንደ ጥላችን እየ ተከተለን ነዉ ዛሬ እንሙት ነገ በእንቅፋትም እንሞታለን በትንታም እንሞታለን ቁጭ ብለን እንሞታለን ከእንቅልፋችን ላንነቃ እንችላለን በዛዉ መቅረት አለና ለልጅ ልጆቻችን እናስብ ለትዉልዱ እናስብ ይቅር እንባባል ብናጠፋም ባናጠፋም ይቅር እንባባል ቂም ቁርሾ በቀል ክፋት እንተዉ አባት ባጠፋዉ ልጅ አይወቀስም ፍቅር ያሸንፋል በፍቅር በይቅርታ እንራመድ
Hammasini ko'rsatish...
3
ሆሳዕና በአርያም ልበል ቆሜ ከበራፍህ እንደ እኔ ዓይነት ኃጥያተኛ ባይመጥንም ለደጃፍህ ሆሳዕና ልበል እንደ ደቂቅ ህፃናቱ አኑረኛል እያልኩ ልቀኝ ሁሉን ችሎ በምህረቱ ዘንባባዬን ልቅጠፍ ላንጥፋ ተንበርክኬ ወልደ ዳዊት ጌታ እያልኩኝ አምላኬ የቢታንያ ድንጋይ ልሳኑ ተፈቶ ለክብርህ ተቀኝቷልና ጌታዉን ለይቶ እኔም ልቀኝልህ ኃጥያቴ ቢበዛም ፈጥረኸኛል እና ምንም ብበድልህ ልጅህን አትረሳም ! አምናለዉ ድናለዉ ዘንባባክን ይዤ ጥፋቶቼን ሳይሆን አንተን ተመርኩዤ ኪሩቤል አሰፋ
Hammasini ko'rsatish...
👍 2 1
" ለመልካም ነገሮች ዝቅ ስትል በፈጣሪክ ከፍ ትላለክ "
Hammasini ko'rsatish...
3
በልጅነታችን ንፁህ ልብ እንጂ ንፁህ ልብስ አልነበረንም ... ዛሬ ግን ልብሳችን ፀድቶ ልባችን ቆሸሸ ...
Hammasini ko'rsatish...
6👍 2
አባት እንደሌለዉ ድሃ አደግ ሆነናል ፤ በደላችን በዝቶ እጅግ ጎስቁለናል ፤ ከዉድቀት አንስተህ እንባችንን አብስ ፤ ወዳንተ እንድንቀርብ ልባችንን መልስ ፤ እንደ ቀድሞ ሁሉ ዘመናችን አድስ ፤ ከእርኩሰት አንፅተህ ነፍሳችንን ቀድስ ። ዔደን ታደሰ
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 1