cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ብሩህ ተስፋ

Gefa ወደላይ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
11 872
Obunachilar
-1424 soatlar
-1047 kunlar
-48530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
ያለማነቱ እግዚአብሔር በባህርዩ ከፊት የሚመራ መሪ እንጂ ከኋላ የሚከተል ተመሪ አይደለም፤ ሁሉን የፈጠረ ሃያል አምላክ እንጂ ማንም እጁን የሚጠመዘዘው ደካማ ፍጡር አይደለም፤ የነገሥታት ልብ በእጁ ነው፣ እንደ ፈሳሽ ውሃ እንደወደደ ወዲህ ወዲያ ያደርጋል* እንጂ ከማንም ምንም ትእዛዝ የሚቀበል አይደለም፤ የሚከተሉትን በጎች በመልካም የሚመራ ደግ እረኛ እንጂ ለህልውናው እረኛ የሚያሻው በግ አይደለም። ሆኖም የዛሬ 2000 ዓመት ይህ እግዚአብሔር ማንነቱን ትቶ 'የእግዚአብሔር በግ' ሆኖ የሰው ስጋ ለብሶ ወደ ምድር መጣ። አምላክ ሆኖ ሳለ ጲላጦስ ዳኝነት በተሰየምበት እየሱስ ደግሞ ተከሳሽ ሆኖ በቆመበት ሸንጎ "ልሰቅልህ ወይም ልፈታህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም?"** እስከሚባል ድረስ 'ሃያል' ማንነቱን ለእኔና ለእናንተ ሲል ተወ። እኛን ለማዳን ሲል ክብሩን ትቶ ስለመጣ የአባቱን ፈቃድ እስከ መስቀል ሞት ድረስ እንኳን ሊታዘዝ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። ሆኖም ግን በመስቀል ላይ ሳለ 'የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እስቲ ውረድ' ብለው እንዳላገጡበት ሰዎች አንተም 'አምላክ እንዴት ይሞታል' እያልክ በባዶ እንድትመራመር ሳይሆን ይኼ ጌታ የሆነውን የሆነው ለእኔ ነው እንድትል ነው። ጌታ እየሱስን እንደ ግል አዳኝ አድርጎ መቀበል ማለት ይኸው ነው። *ምሳሌ 21፣:1 **ዮሐንስ 19:10 ጥያቄ ቢኖርዎ ይላኩልን!
Hammasini ko'rsatish...
6👍 2
ሰው ከሸመገለ በኋላ ሊወለድ እንደሚችል ያውቃሉ? እንዴት ካሉ፣ ከእርሶ በፊት ይህ እንዴት ይቻላል ብሎ ጠይቆ ስለነበረው ሰው ታሪክና ለጥያቄው የተሰጠውን መልስ ያንብቡ። ይሄ መወለድ በደግም ሆነ በክፉ ዘላለምን የሚወስን በጣም ቁልፉ ጉዳይ ነውና በዮሐንስ ወንጌል ምዕ3 ላይ እንዴት መወለድ እንደሚቻል የተጻፈውን ያንብቡና ያንኑ ያድርጉ። አንብበው ጥያቄ ካለዎም ያገኙን።
Hammasini ko'rsatish...
9👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሰው ቤት አታበላሽ! በጥንት ዘመን ሰዎች ወደ መቅደስ ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው የመስዋዕት እንስሳ ወይም የአስራት ስጦታ ነበር። ሆኖም የየራሳቸውን ከቤታቸው ድረስ ይዘው ሲመጡ ያለውን ድካም ለማቅለል በሚል ሌሎች "ለእግዚአብሔር የሚቀርብ" የሚል ታርጋ የተለጠፈባቸውን እንስሶች ሰብስበው በመቅደስ ግቢ ውስጥ ገበያ አቆሙ። ዮሐንስ ወንጌል 2:13 ጀምሮ ይህንን የተመለከተው ኢየሱስ ጅራፍ አበጅቶ ከብቶቹን በሙሉ አስወጣ፣ የነጋዴዎችንም ገበታ ገለባበጠና "የአባቴን ቤት የንግድ ቤት (የወንበዴዎች ዋሻ ማቴ21:13) አታድርጉት አለ። ከዚህ ታሪክ ዝቅ ብሎ ዮሐ2:21 ላይ ስለ መቅደስ ሲናገር "መቅደስ" የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነው ሰውነታችን መሆኑን ኢየሱስ ገልጿል። 'ለእግዚአብሔር' በሚል፣ ለሃይማኖት ባለ ቅንዓት፣ ኑሮን ቀለል ለማድረግ ወይም በሌላ ምክንያት የሰውነት መቅደሳችንን የሚያረክሱ ነገሮችን በልባችን ሰብስበን ከሆነ የመቅደሱና የቤቱ ባለቤት አይወደውምና ጅራፍ ሳያነሳ በፊት እኛው ቤቱን እናጽዳለት። ጥያቄ ቢኖርዎ ያግኙን።
Hammasini ko'rsatish...
👏 5 2
Photo unavailableShow in Telegram
የቶዮታ መኪና መስራች የሆኑት Mr Toyoda የመጀመሪያዋን መኪና በ1936 ሲፈበርኩ በመኪናው ላይ እንዲሁ ያለ ሥራ/ዓላማ የፈጠሩት አንድም የመኪና አካል የለም። Mr Toyoda እንኳን እንዲህ ባለ ጥንቃቄ እያንዳንዱን የመኪና አካል በዓላማ የሚገጥሙ ከሆነ በመልኩ የሰራህ እግዚአብሔር አንተን እንዴት ያለ ዓላማ እንዲሁ በምድር ላይ ያስቀምጣል፣ እንዴትስ የአንተ በሕይወት መኖር የአጋጣሚ ጉዳይ ነው ብለህ ታስባለህ? ደግሞም በመኪናው ላይ ያሉት አካላት ለራሳቸው ጥቅምና ደስታ የተፈጠሩ ሳይሆን መኪናው የተሰራበት ዋና ዓላማ ዕውን እንዲሆን የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ታስበው የተሰሩ ናቸው። እግዚአብሔር በእኛ ተጠቅሞ የልቡን ሃሳብና ፈቃድ ሲፈጽም የሚሆንልን ደስታና በረከት መኖሩ እውነት ነው፣ እንጂ የተፈጠርንበት ዓላማ በእኛ ደስታ ጀምሮ በእኛ ደስታ ላይ እንዲያበቃ አይደለም። የተፈጠርክበትን ዓላማ እወቅ፣ የተፈጠርክበትን ዓላማ ለመጨበጥ ትጋ፣ ለተፈጠርክበት ኑር። "በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ..." ዕብራውያን 13:21
Hammasini ko'rsatish...
6
Photo unavailableShow in Telegram
የመንግስት ትዕዛዝ ሆኖባት እንጂ ሴት ልጅ ወሯ ከገባ በኋላ በእንስሳ ጀርባ ላይ ተቀመጣ ረጅም መንገድ ለመሄድ የምትወጣበት ጊዜ አልነበረም። ነገር ግን የማርያም ጉዞዋ ራሱ የጀመረው በእሺታ ስለነበር አቅሟ ባይፈቅድም ለህዝብ ቆጠራ ከዮሴፍ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ልትሄድ ተነሳች። አመሻሽተው ከተማ ሲደርሱ ለእንግዶች ማረፊያ የሚሆኑ ቦታዎች ሁሉ ቀድመው ስለተያዙ የሚያርፉበት አላገኙም። በዚህ መሃል እርሷ ደግሞ ቀኗ ደርሶ ምጥ እያፋፋማት ነበር። ምጥ ይዟት የምታቃስትን ሴት ሊያስጠጋ የሚፈቅድ በሌለበት አንድ እሺ ባይ ተገኘ፣ የበረት ባለቤት። ህፃን ለመቀበል የሚሆን ጽዱና ንጹህ ቦታ ባይኖረውም እሺ ፈቃድ ግን ተገኝቶበታልና ማርያምና ዮሴፍ በዚያ አርፈው ጌታ የሆነው አዳኝ በዛ የበረት ስፍራ ተወለደ። ከኢየሱስ በዚያ መወለድ የተነሳ ያ በረት እስካሁን የሚጎበኝ የተከበረ ስፍራ ሊሆን በቅቷል። ጌታ ልብህን ወይንም እሺ ፍቃድህን ስጠኝ ሲልህ ንጹህና ፍፁም የሆነ ነገር ስላለብህ ሳይሆን ያንኑ ማንነትህን ቀድሶና ቀይሮ የከበረ ማንነትን ከውስጥ ሊያወጣ ነውና አንድ እሺን አትንፈገው። ጥያቄ ቢኖርዎ ይላኩልን!
Hammasini ko'rsatish...
6👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
በተሸነፈው አትሸነፍ በዳዊትና በጎልያድ መካከል ፍልሚያ ከመደረጉ በፊት አንድ ውል ነበራቸው። ያውም ጎልያድ ካሸነፈ፣ ከዳዊት ጀርባ ያለው ህዝብ ሁሉ ለጎልያድ ህዝብ ባሪያ ሊሆን፤ ዳዊት ካሸነፈም እንዲሁ በተቃራኒው ከጎልያድ ጀርባ ያለው ህዝብ ለዳዊት ህዝብ ባሪያ ሊሆን ተስማምተው ነበር። በውጤቱም በእግዚአብሔር ስም የወጣው ዳዊት ጎልያድን ስላሸነፈ ድሉ የህዝቡ ሁሉ ድል ሆኖ ጠላቶቻቸውን አሳደዷቸው። እኛም በየቀኑ ከፊታችን የሚቆሙ ዓለም፣ ሥጋና ሰይጣን የሚባሉ ጠላቶች አሉብን። ዋነኛ የጦር መሳሪያቸው ደግሞ ኃጥያት ነው። የምስራቹ ግን መሪያችን ኢየሱስ ሁሉንም በመስቀሉ ስላሸነፋቸው፣ የእርሱ ድል ደግሞ የእኛም ድል ነውና በስሙ እየረገጥናቸው ሄደን በፍጻሜውም ከእርሱ ጋር በሰማይ ለዘላለም እንኖራለን። ሆኖም ሰልፋችን ከአሸነፈው ጌታ ጋር ካልሆነ በተሸነፈው ተሸንፈን የዘላለም ፍጻሜአችንም ከተሸነፈው ጋር በሲኦል እንዳይሆንብን ከወዲሁ ሰልፋችንን እናስተካክል። "ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።" 1ኛ ዮሐንስ ምዕ1:4 ጥያቄ ቢኖርዎ ይላኩልን!
Hammasini ko'rsatish...
8🔥 2👍 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዕድለኛ ነዎት በዚህ በአዲስኪዳን የምህረት ዘመን መኖር እንዴት ታላቅ ዕድል እንደሆነ አስተውለው ያውቃሉ? እግዚአብሔር ፍጹም ፃድቅ ስለሆነና የህግ መተላለፍን ስለማይታገስ የኃጥያትን ዋጋ እጅ በእጅ የሚከፍልበት ዓይን ለዓይን፣ ጥርስ ለጥርስ ፍርድ የሚሰጥበት 'ብሉይኪዳን' የሚባል የህግ ዘመን ነበር። ዛሬስ? እግዚአብሔር ዛሬም የጽድቅና የቅድስና ደረጃ ለውጥ ወይም የህግ ማሻሻያ አላደረገም። እንደ ድሮው ዛሬም ደም ሳይፈስ ስርየት የለም፣ ኃጢአትንም ደግሞ በሞት ይቀጣል። በአዲስኪዳን የሆነልን እድሳት ነገር ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ የኃጥያታችንን ዕዳ በመስቀል ላይ ስለከፈለልን ዛሬ በኛ ላይ ዓይን ለዓይን ፍርድ አይሆንብንም፤ በእኛ ፋንታ በሞተልን በኢየሱስ ከእግዚአብሔር ምህረትን የምንጠይቅበት የንስሐ ዕድል ተሰጥቶናልና። ንስሐ ማለት ግን ለበደላችን ምህረትን ማግኘት ብቻ ሳይሆን "የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ ነገር ግን... በገዛ እጆቹ መልካምን እየሰራ ይድከም" እንደሚል የህይወት አቅጣጫ ለውጥንም ይጠይቃል። ኤፌሶን ምዕ 4ን ያንብቡ። ሆኖም ግን ይህንን በአዲስኪዳን በኢየሱስ ያገኘነውን የንስሐ ዕድል አለመጠቀም ምህረት የሌለውና የዘላለም ሞት ፍርድ ያለበት እንደሆነም ማወቅ ተገቢ ነው። ጥያቄ ቢኖረዎ ያገኙን።
Hammasini ko'rsatish...
👍 12 3
Photo unavailableShow in Telegram
ስኬት ምንድነው? ስኬት አብዛኛው ሰው የፈለገውን ሲያገኝ፣ ከአሰበበት ሲደርስ፣ ህልሙን ሲጨብጥ ተሳክቶለታል ይባላል። በዚህ ትርጉም ከሄድን፣ የልቡን ምኞት ያገኘው ሎጥ እጅግ የተሳካለት ሰው ሊባል ነው። እውነታው ግን ለዓይኑ ያማረውንና የተመኘውንም አግኝቶ ሕይወቱ የኪሳራ እንደነበረና ከዓመታት ድካም በኋላ ነፍሱን ሊያድን ባዶ እጁን እንደወጣ ታሪኩን እናውቃለን። ምክንያቱም እውነተኛ ስኬት ሰው የተመኘውን ገንዘብ፣ ቁሳቁስ፣ ኑሮ... ሲያገኝ ሳይሆን እግዚአብሔር ካሰበለት ሲደርስና ያሰበውን ስራ ሲፈጽም ብቻ ነው። መጽ/ቅ "ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም" እንደሚል ተሳካ የሚባለው እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን አስቀድሞ ካሰበልንና ከተፈጠርንበት ዓላማ ላይ ስንደርስ ነው። ኤርምያስ 29:11 ችግሩ ግን የፈጠረን ለምን እንደፈጠረን ካልተገለጠልን፣ እኛ ደግሞ ያለ ዓላማ መኖር የማንችል ፍጡራን ስለሆንን ሌላ የራሳችንን ሰው ሰራሽ/አርተፊሻል ዓላማ ልንፈጥርን እሞክራለን። "እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።" ኤፌሶን 2:10 ይህንን እንወቅ! እግዚአብሔር እኛን የፈጠረውም ሆነ አስቀድሞ ያሰበውን መልካም ስራ በእኛ የሚሰራው በክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ኢየሱስን ሳንይዝ እግዚአብሔር ያሰበውን መልካም ስራ በእኛ ይሰራል ብሎ ማለት የሚታሰብ አይደለም።
Hammasini ko'rsatish...
4👍 1🔥 1
በአጋጣሚ ከከተማ ውጪ ለስራ ስለወጣን የባለፈውን ጥያቄ ማበረታቻ በተባለው ቀን ባለማድረጋችን ይቅርታ እንጠይቃለን። በሳምንቱ መጨረሻ ከመስክ እንደተመለስን እንልካለን።
Hammasini ko'rsatish...