cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Mekedonia-መቄዶንያ

ይህ የቴሌግራም ቻናል ዓላማው ጎዳና ላይ ወድቀው የሚሰቃዩ አረጋውያኖችንና አዕምሮ ሕሙማንን በተለይም የአልጋ ቁራኛዎችን ለመርዳት ነው። መቄዶንያ በአዲስ አበባ፣ ደሴ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ ጎሬ፣ አደዋ እና ሐረር ቅርንጫፎችን በመክፈት ሰዎችን እየረዳ ነው። ወደዚህ ቴሌግራም ቻናል ወዳጆቻችንን "Add" በማድረግ መልካም ነገር አብረን እንስራ! 8161 ላይ OK ብለው ቴክስት ያድርጉ!

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
369
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

እናመሰግናለን........ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 የኢፌዴሪ የግል ድርጅት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባተ ምትኩ እና የአስተዳደር ክፍል በሙሉ አረጋውያን እና የአዕምሮ ህማማንን ለመጠየቅ አዲስ አበባ ዋናው ማዕከል አያት ፀበል መድሀኒአለም ፊትለፊት ተገኝተው ጎብኝተዋል እናመሰግናለን። በዕለቱም ለአረጋውያን የሚሆን በብር 500,000 ሺህ ብር የሚያወጣ የፅዳት ቁሳቁስ እና የምግብ ፍጆታ እርዳታ እንዲሁም ብር በቼክ 500,000 በድምሩ አንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገውልናል። በቀጣይም ከማዕከላችን ጎን በመሆን ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ስራ አስፈፃሚው የተናገሩ ሲሆን ድጋፉን የተረከቡት ክቡር ዶክተር ብንያም በለጠ እርዳታው ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀው መጎብኘታቸው እጅግ ከበቂ በላይ ነው ያሉ ሲሆን! የዚህ እርዳታ ልዩ የሚያደርገው በራሳቸው ተነሳሽነት ደውለው ጠይቀውን ለአረጋውያን አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል በማለት አመስግነዋል! በመጨረሻም አዲስ ዩቱዩብ አካውንት ከፍተናል subscribe በማድረግ አባል እንድትሆኑ መልዕክት አስተላልፈዋል🙏🙏🙏 Mekedonia-መቄዶንያ የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ https://youtube.com/@Mekedonia Mekedonia-መቄዶንያ የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/Mekedonia7979 Mekedonia-መቄዶንያ ፌስ ቡክ ገጽችን ነው share,like ያድርጉ https://www.facebook.com
Hammasini ko'rsatish...
Follow the mekedonia-መቄዶንያ channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaMYOBI1NCrLszK5gM1U
Hammasini ko'rsatish...
mekedonia-መቄዶንያ

WhatsApp Channel Invite

ሰው ከሀብት የተነሣ የገዛ ወገኑንና ዘመዱን ሁሉ ይጠላል፡፡ መደሰት የሚቻለው ሰውን ሲወዱና ለሰው መልካም ሲያደርጉ  ነው፡፡ እኛስ በምንድን ነው ደስ የሚለን? በሀብት ፣ በሥልጣን ፣ በዕውቀት ፣ በወገን መመካት ነው ደስ የሚለን ወይንስ መልካም በመስራት ፣ የተቸገረን በመርዳት ፣ የታመመን በመጠየቅ ...? ደስታ ፣ ተድላ ፣ ፍስሓ እርሱ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ቄራዎች ጅርጅት ዛሬ በማዕከላችን ጉብኝት አደረጉ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት  የሥራ ሀላፊዎችና ሠራተኞች በጉብኝታቸሁ እጅግ መደሰታቸሁን ገልፀው ሌሎችም  ግለሰቦች ፤ ድርጅቶች ፤ ማህበራት ፤ የሃይማኖት ተቋማት እና ሌሎችም ልዮ ልዮ ሰዎች መጥተው እንዲጎበኙ ጥሪ አስተላልፈዋል ። በመጨረሻም ለበጎ አድራጎት ማህበሩ ያመጡትን የምግብ ዘይት ፤ የተፈጨ ዱቄት እና ሌሎችም ልገሳዎች አድርገውልናል ። እናመሰግናለን !! 👉አዲሱን youtube channel subscribe  በማድረግ  የዩቲዩብ  ቻናሉን subscribers   እናሳድግ !! 👉ይህን  ሊንክ በመጫን subscribe አድርጉ 👇👇👇 https://youtube.com/@Mekedonia?si=iUp-u1RPsvWC2wcg
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
እኔ ሊቀ ዲያቆናት ንዋይ  አበበ ነኝ!!!!! በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ሊቀ ዲያቆናት ንዋይ  አበበ  ከአባቱ አቶ አበበ ፈንቴ እና ከእናቱ ከወ/ሮ ሰብለ አጋየ በ1982  ተወለደ ሊቀ ዲያቆናት ንዋይ  እድሜየ ለትምህርት እንደደረሰ ዳግማዊ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመዘግቦ ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ተምሬ  መስከረም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ 10ኛ ክፍል ተምሪያለሁ፡፡ 10ኛ ክፍል ማትሪክ ውጤት ዝቅ ስላለብኘ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ከዚያም ሜትሪፓሪታል  ዩንቨርሲቲ  ገብቼ የ2ኛ ዓመት ተማሪ እያለሁ ነበር ድንገት የአዕምሮ ህመም ያጋጠመኝ  ከዚያም አማኑኤል ሆስፒታል ገብቼ ህክምና ስከታተል ከቆየሁ በኃላ ሽንቁሩ ሚካኤል፣ ፃድቃኔ ማሪያም ፀበል፣ በድቁናና በዝማሪ ባገለገልኩበት የመንበረ ፀባኦት ካቴድራል ፀበል  ገብቼ ተጠምቄ መድሃኒአለም ክርስቶስ አባቴ  እናቴ አማላጄ ድንግል ማሪያም ቅዱሳን ሁሉ ክብር ይግባቸው ከእኔ አልተለዩኝም፡፡ በመጨረሻ   የሚቀበለኝ ቤተሰብ ስላልነበረ የመቄዶንያ ሰዎች በደረሳቸው ጥቆማ ወደ ማዕከሉ አመጡኝ፤ ሊቀ ዲያቆናት ንዋይ  አበበ እንዲህ ይላል በመንፈሳዊውም በአለማዊውም ብዙ ትምህርት ቤት ተመላልሻለው ነገር ግን መቄዶንያን የሚያክል እውነተኛ ትምህርት ቤት አላገኘውም አባቴ ብንያም በለጠ እና  እናቴ እሌኒ ገ/እየሱስን በምን ቃል አመሰግናቸዋለሁ ብቻ እግዚአብሄር በእነሱ ላይ አድሮ የእኔን አልጋ አንጥፎልኛል  ፡፡ በአሁ ሰዓትም በመቄዶንያ ግቢ አባቶችን በመንፈሳዊ አገልግሎት እያገዝኩ እገኛለሁ!! ከእኔ ላልተለየኝ የአለማት ፈጣሪ የሆነው ልዑል እግዚአብሄር በህይወት ዘመኔ አልተለየኝም፤ ወላዲት አምላክ ረዳቴ ድንግል ማሪያም አልተለየችኝም፤ ቅዱሳኑ ሁሉ ረድተውኛል ክብር ምስጋና ይድረሳቸው፡፡ እግዚአብሄር ከሁላችን ጋር ይሁን  አሜን!!!!
Hammasini ko'rsatish...
የአቶ አስፋው ሰማ 1ኛ ዓመት መታሰቢያውን ምክንያት በማድረግ በርካታ አረጋውያንን ምሳ ስለጋበዙልን ቤተሰቡ እግዚአብሄር ይስጥልን! የአባታችንም ነብስ በአፀደ ገነት ያሳርፍልን! ነብስ ይማርልን! ነብስ ይማርልን! ነብስ ይማርልን!
Hammasini ko'rsatish...
👏 2
መቄዶንያ ቀን ለጨለመባቸውና ጧሪ፣ ቀባሪ፣ ደጋፊ ለሌላቸው የሀገር ባለውለታ አረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን ፈጥኖ ደራሽ በመሆን መጠጊያ፣   መጠለያ ፣ የህክምና ከምንም በላይ ቤተሰባዊ የሆነ ፍቅርና እንክብካቤን እንዲሁም ሌላ ተጨማሪ ፍላጎታቸውን በመለገስ ከሀዘናቸው ወጥተው ሕህወታቸውን ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲመሩ መስራቱን ቀጥሎበታል ። የዛሬ ባለታሪካችን ! አስር አለቃ ደምሴ ይርጉ ይባላሉ !! በግንቦት ወር 1941 ዓ/ም በደብረ ብርሃን ከተማ ከአባታቸው ይርጉ መኩሪያ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አበባ ሺበሺ ተወለዱ ። እድሚያቸሁ ለትምህርት ሲደር የቄስ ትምህርታቸውን እዛው ደብርሃን የተማሩ ሲሆን 1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት መርካቶ ልዑል ወሰን ሰገድ ት/ቤት ከ1--6 ክፍል ተምረዋል ። ከ 6 --12 ክፍል ትምህርታቸውን ደሞ አዲስ ከተማ አጠቃላይ ት/ቤት የተማሩ ሲሆን ። በ19 64 ዓ/ም የ12 ክፍል ተማሪ እያሉ አባታቸሁ  አቶ ይርጉ መኩሪያ በሞት ሲያጡ የሚረዳቸው ሰው ባለመኖሩ ትምህርታቸውን አቋርጠው ሲቪል አቪሽን በእሳት አደጋ ተከላካይነት ተቀጥረው በአዲስ አበባ ለ2 ዓመት እንዲሁም በድሬዳዋ ለ4 ዓመት ሰርተዋል ። ከዚህ በኃላ ከ 1971 ዓ/ም እስከ 1977 ዓ/ም ለ 6 ዓመታት በደርግ መንግሥት ተመልምለው በውትድርና ሀገራቸውን አገልግለዋል ። በር 1983 ዓ/ም ወያኔ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር የ ደርግ ወታደር የነበሩትን ተሀድሶ በሚል ወደ ዴዴሳ ተወስደው ከሰኔ እስከ ህዳር ድረስ ቆይተው ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ መጡ ። የሚረዳቸሁ ሲያጡ 2 ዓመት እህታቸው ጋር ተቀምጠው የቆዩ ቢሆኑም እህታቸው በህመም ምክንያት ሲያርፉ ወደ ክፍለ ሀገር ሄደው ከ3 ዓመት በላይ ቆይተው ሲታመሙ አንድ ዘመዳቸሁ ምኒልክ ሆስፒታል አስገብታቸው እየታከሙ እያሉ ህክምናቸውን ጨርሰው ሲወጡ የሚገቡበት ቤት ፤ የሚጠጉት ቤተሰብ ዘመድ ስላልነበራቸው ወደ መቄዶንያ እዛ ባሉ ሰዎች ምክንያት ተደውሎ ይጠቆማል ። በዚህ ጊዜ 2010 ዓ/ም ጥቅምት ወር ላይ የመቄዶንያ ሰራተኞች በደረሳቸሁ ጥቆማ መሠረት ከምኒሊክ ሆስፒታል አስር አለቃ ደምሴ ይርጉ ወደ ማዕከሉ በማምጣት ህክምናቸውን እንዲከታተሉ ተደረገ አስር አለቃ ደምሴም በነበራቸሁ የውስጥ ደዌ በሽታ ምክንያት እረጅም አመት ሲሰቃዩ የቆዩ ሲሆን ወደ ማዕከሉ ገብተው በተደረገላቸሁ ህክምና እና ቤተሰባዊ እንክብካቤ  ሳይንቀሳቀሱ ከተኙበት አልጋ ላይ ድነው ተነስተዋል በአሁን ሰዓት በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን አሁን ላይ የ75 ዓ/ም የእድሜ ባለፀጋ አስር አለቃ  ደምሴ ይርጉ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ። ከዚህ በላይ በጤና እረጅም አመት እንዲኖሩ እንመኛለን ። በሌላ አስተማሪ ታሪክ እስክንገናኝ በሁልጊዜ ቤተሰብነታችን ያቆየን ቸር ቆዩን እስከዛው Share               Like                              Commente 👍 እናድርግ !! 👉አዲሱን youtube channel subscribe  በማድረግ  የዩቲዩብ  ቻናሉን subscribers   እናሳድግ !! 👉ይህን  ሊንክ በመጫን subscribe አድርጉ 👇👇👇 https://youtube.com/@Mekedonia?si=iUp-u1RPsvWC2wcg
Hammasini ko'rsatish...
አቶ ማህሪ እና ወ/ሮ አለም እሸት እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ! 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 አቶ ማህሪ እና ወ/ሮ አለም እሸት በዛሬው እለት ሰርጋቸውን ምክንያት በማድረግ ለ700 አረጋውያን ምሳ ጋብዘውልናል እጅግ በጣም እናመሰግናለን!!! ጋብቻችሁን የአብርሃምና የሰሃራ ያድርጉላችሁ?
Hammasini ko'rsatish...
1
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለአለም አቀፍ የበጎ ፈቀደኞች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!!! 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ወድ የመቄዶንያ ቤተሰቦች እንኳን ለዛሬዋ ቀን አደረሳችሁመቄዶንያ ላለፉት 10ት ዓመታት ከተመሰተበት ጀምሮ ከጎናችን በመሆን በተለያዩ ስራ መስኮች ጉልበታችሁን፣ ሀሳባችሁን፣ ገንዘባችሁ እና ሙያችሁን ሳትሰስቱ በመለገስ አረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ከወደቁበት ጎዳና እንዲነሱ ምክንያት ለሆናችሁ ሁሉ፣ አዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ቤታችሁን ለአረጋውያን  መጦሪያ  በመለገስ  ባለ ወርቅ ልቦች እና ደግ ቤተሰቦቻችን፣ ሰርግ፣ልደት፣ ክርስትና፣ ሰደቃ፣ ኒካህ፣ ሙትዓመት እና ሌሎች ዝግጅቶችን በመቄዶንያ በማድረግ አረጋውያንን ምሳ የጋበዛችሁ ፣ ካላችሁ ላይ ለማካፈል የተለያዩ ቁሳቁሶችን አልባሳት፣ ጫማ፣ የፅዳት ቁሳቁስ ሌሎችን የለገሳችሁ እውነተኛ በጎ ፈቃደኞች እናንተ ናችሁ እና እንኳን አደረሳችሁ፡፡ መቄዶንያ በአሁኑ ሰዓት መቄዶንያ በአሁኑ ወቅት 7,500 በላይ የሚሆኑ ወገኖቻችንን በተለይም እራሳቸውን ችለው መንቀሰሳቀስ፣ መመገብ እና መፀዳዳት የማይችሉ አረጋውያንንና አዕምሮ ሕሙማንን ከተለያዩ የሀገራችን ከተማ ጎዳናዎች ላይ በማንሳት  አዲስ አበባን ጨምሮ በ26 ቅርንጫፎች የበጎ አድራጎት ስራውን እየሰራ ይገኛል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
👍 18