cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አመለካከት TUBE

የዚህ ቻናል አላማ ሰዎች ራዕያቸውንና አላማቸውን ለይተው በማወቅ ለተፈጠሩበት መልካም ስራ ማዋልን እንዲሁም አስተሳሰባቸውን በመለወጥ የሚፈልጉትን ህልም እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ ፣ የአሸናፊነት ልማድ እንዴት እንደሚገነባ እንዲሁም የአእምሯችንን ሚስጥራዊ አሰራር የምናውቅበት እና የስኬታማ ሰዎች ተሞክሮም እናቀርባለን። ለአስተያየትዎ https://t.me/attitudep

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
146
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Hammasini ko'rsatish...
Ethiopia || #ትኩረታችን እንዴት እናዳብር? || #Howto develop focusing

#AmharicMotivationalVideos#yourFocusIsyourResults#Focus#HowToDevelopFocus#በመጀመሪያ እንኳን በሰላም በፍቅር በደስታ ወደ ቻናላችን መጡ።ስለጎበኙን እናመሰግናለን ።ከተመቾት LIKE, SHARE ,COMMENTS...

የተግባራዊ እውቀት ቁልፍ! (“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮበ ማሞ የተወሰደ) “መረጃ ማለት እውቀት ማለት አይደለም” – Albert Einstein የታወቀው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን አንድ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ጥቃቅን ጥያቄዎች እንዳደከሙት ይነገራል፡፡ ከጥያቄዎቹ አንዱ፣ “አንድ ማይል ስንት ጫማ ነው” (በአገራችን አቆጣጠር አንድ ኪሎ ሜትር ስንት ሜትር ነው እንደ ማለት ነው) የሚል ነበር፡፡ የአልበርት መልስ እንዲህ የሚል ነበር፣ “በአንዲት ትንሽ መጽሐፍ ውስጥ በቀላሉ የማገኘውን ቀላል መረጃ በቃሌ ለመያዝ በመሞከር አእምሮዬን ለምን አጨናንቀዋለሁ?”፡፡ ሄንሪ ፎርድ የተሰኘው የፎርድ መኪናዎች ድርጅት ባለቤትና ባለሃብትም በተመሳሳይ ሁኔታ ጋዜጠኞች በጥያቄ ሲያደክሙት የመለሰው መልስ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ጠያቂዎቹ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎችን ስም እየጠቀሱ “እከሌን ታውቀዋለህ? … እከሌስ ማን ነው? … ይህና ያኛው ጦርነት የተካሄደው በስንት አመተ ምህረት ነው? … ” በማለት አደከሙት፡፡ መልሱ እዲህ የሚል ነበር፣ “የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ በቃሌ አላውቅም፡፡ ነገር ግን መልሱን የሚነግራችሁ ሰው በአንድ ጊዜ ልጠቁማችሁ እችላለሁ”፡፡ አእምሮህን የሞላው መረጃ ነው ወይስ ተግባራዊ እውቀት? የምታውቀው እውቀት ምን ያህል ተግባራዊ ነው? ብዙውን ጊዜህን በማጥፋት የምታጠናቸው የእውቀት አይነቶች ምንድን ናቸው? አንዳንድ ሰዎች ያላቸው የእውቀት ብዛት አስገራሚ ነው፣ የእውቀቱ አይነት ግን መረጃ ከማቀበል ወይም የአጠቃላይ እውቀት ውድድርን ከማሸነፍ ውጪ ለምንም ጥቅም አይውልም፡፡ የአንዳንድ ሰዎችን አእምሮ የሞላው መረጃና እውቀት ከጊዜአዊ ደስታና በማኪያቶ ጊዜ በሚደረግ ክርክር በልጦ ከመገኘት አያልፍም፡፡ በሃገሩ ውስጥ ያለ ሃብታም ስም ከነአያት፣ ባለሃብቱ ስንት ብር ባንክ ውስጥ እንዳለው፣ በዚህ አመት ስንት እንዳተረፈ፣ ስንቴና መቼ እንደተዘረፈ፣ ስንቴ አግብቶ እንደፈታ … ይተረትሩታል፡፡ በከተማው ውስጥ የሚነዳው የመኪናውን አይነትና ዋጋ … የሰፈሩ ሰው ሁሉ የፍቅር ሕይወት ታሪክ … የእንግሊዝ ቡድን ተጫዋቾችን ስም ከነሕይወት ታሪካቸው … መረጃዊ-እውቀቱ ብዙ ነው፣ ተግባራዊነቱ ግን ጥቂት ነው፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች ማወቅ ክፋት ኖሮት ሳይሆን አንድ ሰው የግሉን ሕይወት የሚያሻሽልበትን እውቀት ለማግኘት ብቃቱም ሆነ ፍላጎቱ እንደሌለው እየተናገረ ይህን ያህል መረጃ በአእምው ለማከማቸት መቻሉ አንድ የተዛባ ነገር እንዳለ አመላካች ነው፡፡ ከመረጃ ማሽንነት ውጣ፣ ወደ ተግባራዊ እውቀትና እድገት ዘልቀህ ግባ፡፡ በነገራችን ላይ፣ ተግባራዊ እውቀት ማለት ተጠቅመህበት ሕይወትህን የምታሻሽልበትና የገቢ ምንጭ ሊያመጣልህ የሚችል እውቀት ማለት ነው፡፡ https://t.me/Attitudeplc https://m.youtube.com/user/MrGgg2004 https://www.facebook.com/attitudease
Hammasini ko'rsatish...
Asfaw_Motivation

የዚህ ቻናል አላማ ሰዎች ራዕያቸውንና አላማቸውን ለይተው በማወቅ ለተፈጠሩበት መልካም ስራ ማዋልን እንዲሁም አስተሳሰባቸውን በመለወጥ የሚፈልጉትን ህልም እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ ፣ የአሸናፊነት ልማድ እንዴት እንደሚገነባ እንዲሁም የአእምሯችንን ሚስጥራዊ አሰራር የምናውቅበት እና የስኬታማ ሰዎች ተሞክሮም እናቀርባለን። ለአስተያየትዎ

https://t.me/attitudep

Hammasini ko'rsatish...
#ETHIOPIAN | #ሰብሮ_መውጣት | #breaking #throughout #Motivational

#ATTITUDE_አመለካከት#በመጀመሪያ እንኳን በሰላም በፍቅር በደስታ ወደ ቻናላችን መጡ። ስለጎበኙን እናመሰግናለን ።ከተመቾት 𝙇𝙄𝙆𝙀, 𝙎𝙃𝘼𝙍𝙀 ,𝘾𝙊𝙈𝙈𝙀𝙉𝙏𝙎, 𝙨𝙪𝙗𝙨𝙘𝙧𝙞𝙗𝙚𝙧 ሳብስክራብ በማድረግና የደ...

Hammasini ko'rsatish...
ETHIOPIA| ጓደኛን እንዴት መምረጥ እንችላለን|| How to Choose Friends Amharic Motivations by Asfaw

ጓደኞችዎን እንዴት እንደሚመርጡ ማወቅ ለምን አስፈላጊ ነው?ጓደኞችዎን በተሻለ መንገድ እንዴት እንደሚመርጡ1. ርህራሄ መኖር አለበት2. ስለፍላጎቶችዎ ይናገሩ3. የተለያዩ ቦታዎችን በመደበኛነት ያዘወትራል4. መቻቻል መኖር አለበት5. ሰዎች ሌሎችን እን...

Hammasini ko'rsatish...
https://youtu.be/850ljsaMAtQ የጊዜ አጠቃቀም ዘይቤአችን ሲቃኝ! ዛሬ የምኖረው ኑሮዬ የብዙ ነገር ድምር ነው፡፡ በአንድ ጎኑ የግሌ ጸባይና ዝንባሌ ጠብታ ሲኖርበት በሌላ ጎኑ ደግሞ በልጅነቴ በምሳሌነት ከመሩኝ ቤተሰቦቼና አስተማሪዎቼ አይቼና ቀስሜ ያደኩትም ጠብታ አለበት፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ እነዚህ ሁኔታዎች ተደምረው የዛሬውን በጊዜ ላይ ያለኝን ግንዛቤ ወደመኖር አምጥተውታል፡፡ ስለዚህም ካለፈው ሕይወቴ ተጽእኖ የተነሳ የጨበጥኩትን የጊዜ አያያዝ ሁኔታ ለመገንዘብ ራሴን ማየት መልካም ጅማሬ ነው፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ የሚከተሉትን የተለመዱ የጊዜ አያያዝ ዝንባሌዎች እናጢን፡፡ “አቶ የአደጋ ጊዜ ተጠሪ” ልክ የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች ተግባራቸው በየቦታው እየበረሩ የተነሳን እሳት ማጥፋት እንደሆነ “አቶ የአደጋ ጊዜ ተጠሪ” እዚህና እዚያ ብቅ ለሚሉ ሁኔታዎች ምላሽ በመስጠት ጊዜውን የሚያሳልፍሰው ነው፡፡ ለተለያዩ ችግሮች ምላሽ በመስጠት ከመሯሯጡ የተነሳ ቁጭ ብሎ ጊዜውን በሚገባ ለመጠቀም የሚረዳውን እቅድ ለማውጣት “ጊዜ” የለውም፡፡ ልክ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ከዚህኛው ወደዚያኛው እሳት እንደሚጣደፉ፣ እንዲህ አይነቱ ሰው ብዙውን ጊዜ ከስፍራ ወደ ስፍራ በፍጥነት ሲዘዋወርና በወቅቱ ሃሳቡን ለሳበው ችግር ምላሽ ለመስጠት ሲሯሯጥ ይታያል፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ ይህ አይነቱ ዝንባሌ አብዛኛውን ጊዜ ምንጩ የአስተዳደግ ሁኔታ ነው፡፡ አንድ ሰው ለተደወለው ስልክና ተከሰተ ለተባለው ችግር ሁሉ በድንገት ብድግ በማለት በሚሮጡ ቤተሰቦች መካከል ካደገ ያንንው ተምሮ ነው የሚያድገው፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ “አቶ አስደሳች” የ“አቶ አስደሳች” ችግር “እምቢ” ለማለት ያለመቻል ችግር ነው፡፡ አንድ ሰው አንድን ነገር እንዲያደርግለት ከጠየቀው፣ ጊዜ ባይኖረው እንኳ “እሺ” በማለት ቃል ይገባል፡፡ ሰውን ሁሉ የመሸኘቱ፣ ለቸገረው ሁሉ ገንዘብ አበዳሪነቱ፣ ከአቅሙ በላይ ቢሆንም እንኳ የተጠየቀውን ስራ ሁሉ በእሺታ የመቀበሉ ዝንባሌ ጊዜ አጠቃሙን ከመስመር አውጥቶበታል፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ “አቶ አስደሳች” በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ከሁለትና ከሶስት ሰዎች ጋር ቀጠሮ ሊይዝ ይችላል - በመዘንጋት ሳይሆን እምቢ የማለት የፈቃድ ጉልበት በማጣት፡፡ እንዲህ አይነት ሰው ከአምስትና ከስድስት ኮሚቴዎች በላይ አባል ሆኖ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡እንዲህ አይነቱ ዝንባሌ ከዝቅተኝነት ስሜትና ተቀባይነት ለማግኘት ከሚኖር የውስጥ ምኞት ወይም ደግሞ የሰውን ስሜት ላለመጉዳት ካለ ጽኑ ፍላጎት ሊመነጭ ይችላል፡፡ “አቶ አስደሳች” ብዙ ጊዜ ከሰዎች ሲደበቅ ይታያል - ይህንን አድርግልኝ ተብሎ ተጠይቆ እምቢ ከሚል መደበቁን ይመርጣል፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ “አቶ ጊዜ አለኝ” “አቶ ጊዜ አለኝ” አንድን ነገር የሚተገብረው ሲመቸው ወይም “ሙዱን” ሲያገኝ ነው፡፡ ዘና ያለ፣ መጨናነቅ የማይወድና ብዙውን ጊዜ እግሩን ጠረጴዛ ላይ ሰቅሎ የሚታይ ሰው ነው፡፡ ተግባሮቹን ቅደም ተከተል የማስያዝ ልማድ ባይኖረውም በውስጥ ታዋቂነት ግን ማድረግ ደስ ከሚለው ተግባር መጀመር እንደሚወድ እውቅ ነው፡፡ አንድ ነገር ደስ የሚለው ከሆነ ጊዜ አያጣለትም፡፡ በመቀጠልም ለማድረግ ቀለል ያለውን የመምረጥ ዝንባሌ አለው፡፡ አንድ የጀመረውን ነገር ለማስተላለፍ ወይም ለማቆም ትንሽ “እንቅፋት” በቂ ነው፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ “አቶ ጊዜ አለኝ” የኑሮው መፈክር፣ “ስደርስ እደርስበታለሁ” ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በጊዜው ያልተከናወነ ተግባር ሊያደርስ የሚችለውን መዘዝም ሆነ ሊጎዳ የሚችለውን ሰው የማየት ብቃት የለውም፡፡ እንዲሁ በመላ-ምት ስለሚኖር ከራሱ አልፎ ቤተሰቡንም ሆነ መስሪያ ቤቱን የሚጎትት ታላቅ የስኬት ጠንቅ ነው፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ “ወ/ሪት ማሕበረሰብ” “ወ/ሪት ማሕበረሰብ” የተወለደችው ከሰዎች ጋር ለመሰባሰብ እንደሆነ የሚያስመስልባት ማንነት አላት፡፡ የንግግር ችሎታዋና የመግባባት ፍጥነቷ አስገራሚ ነው፡፡ ከሰዎች ጋር ለመገናኘትና ለማሳለፍ ከምታገኘው አጋጣሚ አንዱም አያመልጣትም፡፡ የሚያስደንቀው ነገር ለማሕበራዊ ሕይወት በምታደርገው የዚህና የዚያ ሩጫ በፍጹም አለመድከሟ ነው፡፡ “ወ/ሪት ማሕበረሰብ” “ጓደኞቼ” ብላ የምትጠራቸው ሰዎች ቁጥር ስፍር የላቸውም፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ አብዛኛዎቹን በቀን ውስጥ በአካል ካላገኘቻቸው በስልክ ረዘም ላለ ጊዜ ታነጋግራቸዋለች፡፡ ለመስራት ያልፈለገችው ስራ ካለ ያንን ስራ የምታስተላልፈው ከሰዎች ጋር በመገናኘትና ይህና ያንን በማድረግ ነው፡፡ “ወ/ሪት ማሕበረሰብ” ከስራዋ አካባቢ በፍጹም ሰው አይጠፋም፡፡ ከአንድ ቦታ ወደሌላኛው፣ ወይም ደግሞ ከስራ ቦታ ወደቤቷ ስትሄድ በመንገድ ላይ ሰዎችን ቀጥሮ ሻይ መጠጣትም ሆነ መጨዋወት የተለመደ ተግባሯ ነው፡፡ የአንድን ስራ የቀን ገደብ ከሰዎች ጋር ለማሳለፍ ስትል ማስተላለፍ እንደ ችግር አይታያትም፡፡ https://youtu.be/850ljsaMAtQ ከላይ ከተዘረዘሩት ዝንባሌዎች መካከል ራስህን በየትኛው አገኘኸው? ጊዜን በጥበብ በመጠቀም ወደ ተሻለ ስኬታማ ሕይወት ለመግባት “የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” የተሰኘውን መጽሐፍ እንዲያነቡ እጋብዛለሁ፡፡ == በቅንነት ለሌሎች ሼር ያድርጉ == http://t.me//attitudeplc
Hammasini ko'rsatish...

ከገንዘብ የሚበልጡ ነገሮች https://youtu.be/cOI9i9Zj4EM አንድ አሜሪካዊ ነጋዴ በአንዲት የሜክሲኮ የወደብ ከተማ ዳር ቆሞ ሳለ አንዲት ትንሽ ጀልባ አንድ አሳ አጥማጅ ይዛ ወደ ወደቡ ተጠጋች፡፡ በጀልባ ውስጥ አንድ የሜክሲኮ ተወላጅ አሳ አጥማጅ ያጠመዳቸው ቁጥራቸው ከመጠን ያለፈ ትናንሽ አሳዎች አሉ፡፡ አሜሪካዊው ሜክሲኮአዊውን ስለአሳ ማጥመድ ችሎታው ካደነቀው በኋላ አንድን ጥያቄ አቀረበለት፣ “እነዚህን አሳዎች ለማጥመድ ስንት ጊዜ ፈጀብህ?” “በጣም አጭር ጊዜ” ብሎ መለሰ፣ ሜክሲኮአዊው፡፡ አሜሪካዊው፣ “ይህንን ያህል አሳ በአጭር ጊዜ ማጥመድ ከቻልክ ለምን ቀኑን ሙሉ ውለህ ብዙ አሳ ለማጥመድ አትሞክርም” ብሎ ጠየቀው፡፡ https://youtu.be/cOI9i9Zj4EM ሜክሲኮአዊው፣ “አሁን በምሰራበት ሁኔታ ለቤተሰቤ በቂ አቅርቦትን ይዤ እገባለሁ” ብሎ መለሰ፡፡ አሜሪካዊው ጥያቄውን በመቀጠል፣ “በቀረህ ጊዜ ምን ታደርጋለህ?” አለው፡፡ ሜክሲኮአዊው ገበሬ፣ “ጠዋት በቂ እረፍት እወስዳለሁ፣ በቂ አሳ ካጠመድኩ በኋላ ልጆቼ ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ከእነሱ ጋር እጫወታለሁ፣ ከዚያም ከባለቤቴ ከማሪያ ጋር ጣፋጭና አጭር የቀን እንቅልፍ እንወስዳለን፣ ከዚያም ወደ ከተማ ወጣ እልና ከጓደኞቼ ጋር ሻይ እየጠጣን ጊታሬን መታ መታ አደርጋለሁ፤ ቀኔ በእነዚህ ሁኔታዎች ሙሉ ነው”፡፡ https://youtu.be/cOI9i9Zj4EM አሜሪካዊው በመገረምና በማሾፍ፣ “እኔ የታዋቂው የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ተመራቂ ነኝ፡፡ ልምከርህ! ከጠዋት እስከማታ አሳ ማጥመድ አለብህ፡፡ ከዚያም ተለቅ ያለ ጀልባ መግዛት ትችላለህ፡፡ ከዚያ በአሳ ጠመዳ የምታሳልፈውን ጊዜህን ትንሽ ጨመር በማድረግ በርካታ ጀልባዎችን ትገዛለህ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብዙ ጀልባዎች ይኖሩሃል፡፡ ከዚያም ዋና አከፋፋይ መሆን ትጀምርና ለአሳ ጠመዳ በምትወስደው ጊዜህ ላይ ጥቂት ጨመር በማድረግ የራስህን ፋብሪካ ትከፍታለህ፡፡ ከዚያም ከዚህች መንደር ትወጣና ወደ ሜክሲኮ ዋና ከተማ ትገባለህ፣ ከዚያ ወደ ሎስ አንጀለስ፣ ቀስ በቀስም የአለም የገበያ ማእከል ወደሆነችው ወደ ኒውዮርክ በመግባት ታላቅ ሰውና ሚሊየነር ትሆናለህ፡፡” ሜክሲኮአዊው በመገረም፣ “ይህ የምትለው ጉዳይ ስንት ጊዜ ይፈጃል?” አለው፡፡ አሜሪካዊውም፣ “ከ20 እስከ 25 ዓመታት ይፈጃል” አለው፡፡ https://youtu.be/cOI9i9Zj4EM ሜክሲኮአዊውም መልሶ፣ “ከ25 ዓመታት በኋላ እዚያ ደረጃ ከደረስኩ በኋላስ?” አለው በፍጥነት፡፡ አሜሪካዊው በመሳቅ፣ “ያን ጊዜማ የሚያጓጓ ነገር ውስጥ ትገባለህ፡፡ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቀህ ይህንን የገነባኸውን ንግድ ለሕዝብ በማቅረብ አክሲዮን ትሸጥና ብዙ ቢልየን ብር በማግኘት እጅግ ባለጠጋ ትሆናለህ፡፡” https://youtu.be/cOI9i9Zj4EM አሁንም ሜክሲኮአዊው መልሶ፣ “በቢልየን የሚቆጠር ብር ካገኘሁ በኋላስ” አለው፡፡ “ከዚያማ ጡረታ ትወጣና ወደነበርክበት የባህር ወደብ ከተማ ትመለሳለህ፡፡ አሁን እንደምታደርገው ጠዋት በቂ እረፍት ትወስዳለህ፣ በቂ አሳ ካጠመድ በኋላ ከልጅ ልጆችህ ጋር ትጫወታለህ፣ ከዚያም ከባለቤትህ ከማሪያ ጋር ጣፋጭና አጭር የቀን እንቅልፍ ትወስዳለህ፣ ከዚያም ወደ ከተማ ወጣ ትልና ከጓደኞች ጋር ሻይ እየጠጣህ ጊታርህን መታ መታ ታደርጋለህ”፡፡ ሜክሲኮአዊው ተገረመ፡፡ በሃሳቡ፣ “አሁን የምኖረውን የተረጋጋ የሕይወት ሁኔታ ከ25 ዓመታት ልፋት በኋላ ለማግኘት ምን አስሮጠኝ” ብሎ በማሰብና በአሜሪካዊው ሃሳብ ስቆ መንገዱን ቀጠለ፡፡ https://youtu.be/cOI9i9Zj4EM ራስንና ቤተሰብን ለማሻሻል ለተወሰ ጊዜ ብዙ መስራት አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ የመኖሩ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እዚህና እዚያ ደረጃ ለመድረስ የምንሮጠውን ሩጫ ቆም ብለን ማየት የሚገባን ወቅት ነው፡፡ ለእድገትና ለመሻሻል ስንል ግን መስዋእት ልናደርጋቸው የማንችላቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ https://youtu.be/cOI9i9Zj4EM • ለገንዘብ ስትል በፍጹም ለቤተሰብህ የምትሰጠውን ትኩረት፣ ፍቅርና ጊዜ አትሰዋ !!! • ለገንዘብ ስትል በፍጹም ጤንነትህን አታቃውስ !!! • ለገንዘብ ስትል በፍጹም ህሊናህን አትሽጥ !!! • ለገንዘብ ስትል በፍጹም መልካም ስምህን አትጣል !!! • ለገንዘብ ስትል በፍጹም እምነትህን አትካድ !!! • ለገንዘብ ስትል በፍጹም ሕዝብህን፣ ወገንህንና ሃገርህን አሳልፈህ አትስጥ !!! https://t.me/attitudeplc
Hammasini ko'rsatish...

Watch "#Ethiopia//ምርጥ የእመቤታችን መዝሙር የበላዬሰብ የተለመነች እኛንም ትለመነን" on YouTube https://youtu.be/tSP5qMIU3mc
Hammasini ko'rsatish...
#Ethiopia//ምርጥ የእመቤታችን መዝሙር የበላዬሰብ የተለመነች እኛንም ትለመነን

አመለካከት TUBE: እጅግ መሳጭ የአንድ ገበሬ ታሪክ! በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ገበሬ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የዚህ ገበሬ ፈረስ ይጠፋል። የመንደሩ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ ሃዘናቸውን ይገልጹለታል። https://youtu.be/GowcmXpPWto እንዲህ ሲሉ ” ፈረስህ በመጥፋቱ አዝነናል፤ እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” ሲሉት። ገበሬው መልሶ “መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ብሎ መለሰላቸው። በበነጋታው የጠፋው ፈረስ ሌሎች ሰባት ፈረሶችን አስከትሎ መጣ። ይህንን የተመለከቱ የሰፈሩ ሰዎች ወሬውን ይሰሙና ወደ ገበሬው ቤት በመሄድ እንዲህ ይሉታል።” የሚገርም እኮ ነው፤ አንድ ፈረስ ነበረህ አሁን ስምንት ፈረሶች ሆኑልህ። እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬውም ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይ ሆንም ይችላል” ሲል መለሰላቸው። https://youtu.be/GowcmXpPWto ሲነጋ የገበሬው ልጅ ከስምንቱ ፈረሶች አንዱን ሰርቆ ሊጋልብ ሲሞክር ፈረሱ አሽቀንጥሮ ይጥለውና ልጁ እግሩን ይሰበራል። ወሬውም በሰፈሩ ሁሉ ተሰማ። እንደ ልማዳቸው የሰፈሩ ሰዎች ተሰባስበው ” ውይ የልጅህ መሰበር እንዴት ያሳዝናል ባክህ? እንደው ምን አይነት መጥፎ እድል ነው?” አሉት። ገበሬውም መልሶ ” መጥፎ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ሲል እንደልማዱ በእርጋታ መለሰላቸው። በቀጣዩ ቀን የመንደሩ የጦር ተቆጣጣሪ፤ ወጣቶችን ለጦር ሜዳ ሊመለምል ወደ መንደሩ ይዘልቃል። የሁሉንም ቤት ወጣት ወንዶች ለጦርነት ሲመለምል ከፈረስ ላይ የወደቀውን የገበሬውን ልጅ ግን እግሩ ስለተሰበረ ሳይወስዱት ቀሩ። ይሄኔ የመንደሩ ሰዎች ተሰባስበው ወደ ገበሬው በመሄድ እንዲህ አሉት “አየህ ልጅህ እግሩን በመሰበሩ ወደጦር ሜዳ ሳይወሰድ ቀረ፤ እንደው ምን አይነት ጥሩ እድል ነው?” ገበሬው ግን አሁንም እንዲህ አላቸው ” ጥሩ እድል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል” ============//============== ምን ለማለት ፈልጌ ነው : ብዙን ጊዜ በኑሮዋችን ውስጥ አንድ ነገር ሲከሰት በችኮላ “መጥፎ” ወይም “ጥሩ” እድል በማለት እንፈርጃለን። መልካም ያልነው ነገር መጥፎ ነገር ይዞ ሲመጣ፤ መጥፎ ያልነው ነገር ደግሞ መልካም ነገር ይዞ ብቅ ሲል፤ ዳኝነታችን መሰረት የሌለው እንደሆነ እንረዳለን። ወደ ኋላ መለስ ብለን የመጣንበትን ብንቃኝ፤ በእርግጠኝነት በአንድ ወቅት መጥፎ እድል ናቸው ብለን የፈረጅናቸው በኋላ ላይ ግን መልካም ነገር ይዘውልን የመጡ የህይወት አጋጣሚዎችን እናገኛለን። እኛ ግን ቀድመን “መጥፎ” እና “ጥሩ” እድል እያልን ነገሮችን ስንከፋፍል፤ አይምሮዋችን አስቀድሞ ነገሮችን ስለሚዳኝ ጭንቀት በጊዜው ከሚሆነው ነገር ጋር እንዳንስማማ ያደርገናል። የገበሬው አመለካከት ግን እጅግ የሚደንቅ ነው። የሚገጥሙት ነገሮች ምን ይዘው እንደሚመጡ ስለማያውቅ “መልካም” እና “መጥፎ” እድል እያለ እራሱን ላልተጠበቀ ሃዘን አያዘጋጅም። የፈረሱ መጥፋት መጥፎ እድል ነው ብሎ ለማለት አልደፈረም። ምክንያቱም የሆነው ነገር ምን ይዞ እንደሚመጣ ስላላወቀ። ፈረሱ ሌሎች ፈረሶችን ይዞ ሲመጣም “መልካም እድል” ብሎ ሊደመድም አልወደደም፤ እንደሰወኛ ብናስብ እነዛ ፈረሶች ባይኖሩ ልጁ አይሰበርም ነበር። የልጁን መሰበርም እንደ መጥፎ እድል ሊወስደው አልፈለገም፤ እንደሰወኛ ግን ልጁ እግሩ ባይሰበር ኖሮ፤ እንደሌሎቹ የሰፈር ወጣቶች ከአባቱ ተነጥሎ ወደ ጦር ሜዳ በተወሰደ ነበር። እንዲህ አይነት አመለካከት ከአልታሰበ የስሜት መናወጥ ያድናል፤ እርግጥ ነው ቀላል አይደለም። ነገር ግን በህይወት መንገድ ላይ ስንጓዝ የሚገጥሙን ሁኔታዎች ጊዜ ብቻ የሚፈታው ሚስጥር በውስጣቸው አለ። ነገሮች ሁሉ ወደ በጎ እየተቀየሩልን እግዚአብሔርን ባማረርንበት አፋችን እንድናመሰግነው ያደረገን አጋጣሚ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለ። በአንጻሩ በስንት ልመና ያገኘነውን ነገር ምነው ባትሰጠኝ ኖሮ ብለን ያማረርንበትም ጊዜ ይኖራል። በዚህ አለም ላይ ያለምክንያት የሚሆን ምንም ነገር የለም። ምናልባት አሁን እያለፍነበት ያለው ፈተና እና የኑሮ ጦርነት እድላችንንን እንድንማረር እያረገን ይሆናል፤ ነገ የሚመጣውን ግን አናውቅም። የእኛ ድርሻ መሆን ያለበት ሁሉንም እንደአመጣጡ መቀበልና ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ብለን ለእግዚአብሔር መተው ነው። መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላል “ሁሉም ነገር ለበጎ ነው” https://youtu.be/GowcmXpPWto https://telegram.me/Attitudeplc
Hammasini ko'rsatish...
Ethiopian |#ፍርሐትን #የማሸነፍ #ቁልፍ| #the #key To #Winning #FEAR

እምነት ዘርን ትመስላለች ፣ራሷን ታበቅላለችና። መልካም ዘርን (ሐሳብን) በአእምሮህ ውስጥ ዘርተህ በቅን ሐሳብ እየተንከባከብካት ጠብቃት።#ATTITUDE_አመለካከት YouTubeቻናላችን ስለጎበኙ እናመሰግናለን፡፡ ተመሳሳይ ቪዲዮችን ለመመልከት ሊንኩን ...

Hammasini ko'rsatish...
Ethiopia || #ትኩረታችን እንዴት እናዳብር? || #Howto develop focusing

#AmharicMotivationalVideos#yourFocusIsyourResults#Focus#HowToDevelopFocus#በመጀመሪያ እንኳን በሰላም በፍቅር በደስታ ወደ ቻናላችን መጡ።ስለጎበኙን እናመሰግናለን ።ከተመቾት LIKE, SHARE ,COMMENTS...