ሊያና ኬር Liyana Care 7755
Kanalga Telegram’da o‘tish
➮ የጤና ምክሮች 👨⚕️ ➮ ሀኪምዎን ያማክሩ7755 ➮ ቴሌሜዲስን 💉 ➮ በአይነቱ ለየት ያለ ሀክምና📱📲
Ko'proq ko'rsatish6 259
Obunachilar
-324 soatlar
-237 kunlar
-15030 kunlar
Postlar arxiv
⚠️ ስለ አጥንት መሳሳት (Osteoporosis) ምን ያውቃሉ?
🔅የአጥንት መሳሳት (Osteoporosis) የሚከሰተው የአጥንታችን ክብደት (bone mass) ሲቀንስ እና የውስጠኛው የአጥንት መዋቅር ሲደክም ነው። ይህም አጥንት በቀላሉ እንዲሰበር ያደርገዋል።
👉ይህ በሽታ አጥንት እስኪሰበር ድረስ ምንም ዓይነት ግልጽ ምልክት ሳያሳይ በሰውነታችን ውስጥ ሊቆይ ይችላል፡፡
🚨 ለአጥንት መሳሳት (Osteoporosis) የሚያጋልጡ ዋና ዋና ነገሮች ምንድን ናቸው?
✨የአጥንት መሳሳት ችግር በማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰት ቢችልም፥ የሚከተሉት ሁኔታዎች ግን ለአደጋው የመጋለጥ እድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ፦
🔻የእድሜ መግፋት
🔻ሴቶች ላይ የወር አበባ ቀድሞ መቋረጥ
🔻ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት እና ካፌይን (ቡና እና ሻይ) ማብዛት
🔻የትምባሆ/ሲጋራ አጠቃቀም
🔺የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ
🔺በጣም ዝቅተኛ የሰውነት ክብደት መኖር
🔺የቫይታሚን ዲ (Vitamin D) ወይም የካልሲየም (Calcium) እጥረት
🔺የመውደቅ ወይም ቀደም ሲል የአጥንት መሰበር ታሪክ መኖር
🔺በቤተሰብ ውስጥ የአጥንት መሰበር ታሪክ (Family History) መኖር
❇️ በሌሎች የጤና እክሎች ሳቢያ የሚመጣ የአጥንት መሳሳት (Secondary Osteoporosis)
የአጥንት መሳሳት በሽታ አንዳንድ ጊዜ በቀጥታ ሳይሆን በሌሎች ህመሞች ወይም በሚወሰዱ መድኃኒቶች ምክንያት ሊከሰት ይችላል። ዋና ዋናዎቹ መንስኤዎች የሚከተሉት ናቸው፦
1. የካንሰር ህመሞች
3. ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም (Chronic kidney disease)
4. የሆርሞን መዛባቶች (Endocrine disorders)
5. ስር የሰደዱ የማበጥ/የመቆጣት ባህሪ ያላቸው ህመሞች (Chronic inflammatory diseases)
6. ለአምስት ዓመት እና ከዚያ በላይ ለረጅም ጊዜ የሚወሰዱ መድኃኒቶች (Medications)
7. የተመጣጠነ ምግብ እጥረት(Malnutrition)
🔷 የህመሙ ምልክቶችና መገለጫዎች ሙሉ በሙሉ ከሚያጋጥሙ የአጥንት ስብራቶች ጋር የተያያዙ ናቸው።
🔘ከስብራት ጋር የተያያዙ ምልክቶች፦ ህመም፣ የመንቀሳቀስ ችግር፣ የመተንፈስ ችግርና የአካል ቅርጽ ማጣት።
🔘ከስብራት መኖር ጋር የተያያዙ ምልክቶች፦ የቁመት ማጠር፣ የጀርባ ጎባጣነት፣ የደረት ቅርጽ መለወጥ፣ የጎድንና የዳሌ አጥንት መደራረብ ይታያሉ።
🔔ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ስለ አጥንት መሳሳት (Osteoporosis) የነበረው ግንዛቤ ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል። ቀደም ሲል በሽታው "ከእድሜ መግፋት ጋር አብሮ የሚመጣ የማይቀር ነገር" ተደርጎ ይታይ ነበር። ዛሬ ግን አጥንት መሳሳት ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ከባድ የጤና እክል መሆኑ ተለይቷል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ ሙሉ በሙሉ መከላከል እና በአግባቡ ማከም የሚቻል በሽታ መሆኑ ተረጋግጧል።
⚔️ መከላከያ መንገዶች
🔍 የአጥንት መሳሳት ችግርን ለመከላከልና ለማከም መድኃኒት መውሰድ ብቻውን በቂ አይደለም። የሚከተሉት የዕለት ተዕለት የኑሮ ዘይቤ ለውጦች አጥንትን በመጠበቅ ረገድ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው፦
🧎የመውደቅ አደጋዎችን መቀነስ (Prevention of falls)
💪የጡንቻ ጥንካሬ እና የሰውነት ሚዛን መጠበቂያ ስፖርቶች
🥗የተመጣጠነ ምግብ
🍷የአልኮል መጠጥን መቀነስ
☕️ካፌይን መቀነስ
🚬ሲጋራ ማጨስን ማቆም
🌞ፀሐይ መሞቅ
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
👨👩👧👦 ማህበራዊ ግንኙነት እና የቤተሰብ ጊዜ ለአእምሮ ጤና ያለው ጥቅሞች
👩👩👧ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ ለአእምሯችን ምርጡ ፈውስ እንደሆነ ያውቃሉ?
⚠️ከሰዎች ጋር መገናኘት (Socializing) ለአእምሮ ጤና የሚሰጠው ዋና ዋና ጥቅሞች፦
1. 📉 የጭንቀት ሆርሞንን ወዲያውኑ ይቀንሳል
ከሰዎች ጋር ስንገናኝ፣ ስንጫወት ወይም አብረን ስንቆይ አእምሯችን ኦክሲቶሲን (Oxytocin) የተባለውን "የደስታ እና የፍቅር ሆርሞን" ያመርታል።
ይህ ሆርሞን የጭንቀት ሆርሞኖችን (Cortisol) ወዲያውኑ የማውረድ አቅም አለው።
2. 🛡 የብቸኝነት እና የድብርት ስሜትን ይከላከላል
ብቸኝነት ለአእምሮ ጤና ትልቅ ጠላት ነው። ከቤተሰብ ጋር መሆን ወይም ከሚያምኑት ጓደኛ ጋር ማውራት "በዚህ ዓለም ላይ ብቻዬን አይደለሁም፣ የሚወደኝ እና የሚደግፈኝ ሰው አለ" የሚል የደህንነት ስሜት (Belongingness) ይሰጠናል።
3. 🧠 የማስተዋል እና የማሰብ ብቃትን ያሳድጋል
ማውራት፣ መከራከር፣ አብሮ መጫወት እና የሰዎችን ታሪክ መስማት አእምሯችን ንቁ እንዲሆን ያደርገዋል።
ማህበራዊ ግንኙነታቸው ጠንካራ የሆኑ ሰዎች በዕድሜ መግፋት የሚመጣውን የመርሳት ችግር (Dementia) የመከላከል ዕድላቸው ሰፊ ነው።
4. 🗣 ስሜትን አውጥቶ ለመተንፈስ ይረዳል
ሃሳብን በውስጥ አምቆ መያዝ አእምሮን ያደክማል። ለሚቀርቡት የቤተሰብ አባል ወይም ወዳጅ የውስጥን ስሜት አካፍሎ ማውራት፣ ምንም መፍትሄ ባይገኝለት እንኳ አእምሮን 70% ቀለል ያደርገዋል።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🎀 ጡት ካንሰር
🔅የጡት ካንሰር በዓለም ዙሪያ በሴቶች ላይ በስፋት የሚያጋጥም እና ለህልፈተ ህይወት የሚዳርግ የካንሰር አይነት ነው።
📌 በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታ፦
👉እንደ ቅርብ ጊዜ መረጃዎች (ለምሳሌ የግሎቦካን የቅርብ ሪፖርቶች) በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ 16,900 በላይ አዳዲስ የጡት ካንሰር ታካሚዎች ይመዘገባሉ።
👉የጡት ካንሰር በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች 32% (አንድ ሦስተኛ ያህሉን) በመያዝ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። እንዲሁም ከካንሰር ጋር በተያያዘ ለሚከሰት ህልፈተ ህይወት 17.6% የሚሆነውን ድርሻ በመያዝ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
🌍 የዓለም አቀፍ ሁኔታ፦
በሰሜን አሜሪካ በቅድመ ምርመራ እና በሽታውን አስቀድሞ ማወቅ በመቻሉ ምክንያት በሽታው የመያዝ ምጣኔ እየቀነሰ ቢሆንም፣ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ግን እየጨመረ ይገኛል።
⚠️ ለበሽታው የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
🔸የእድሜ መግፋት እና ሴት መሆን
🔸የመጀመሪያ የወር አበባን በለጋ እድሜ ማየት (Early menarche)
🔸የወር አበባ መቋረጫ እድሜ መዘግየት (Late menopause)
🔸የመጀመሪያ እርግዝና በእድሜ መግፋት መሆን ወይም በጭራሽ አለመውለድ
🔸ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን ማዘውተር እና ከመጠን በላይ መወፈር
🔸የሆርሞን ምትክ ህክምና (Hormone replacement therapy) መውሰድ
🔸በአፍላ የዕድሜ ክልል ለጨረር መጋለጥ።
🩺 የጡት ካንሰር ምልክቶች
የጡት ካንሰር ምልክቶች እንደ በሽታው ደረጃ ሊለያዩ ይችላሉ። በሽታው መጀመሪያ ላይ ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል ወይም ምልክት እያሳየ ሊመጣ ይችላል።
ምልክት የሚያሳይበት ደረጃ ፦
-ህመም የሌለው የጡት እብጠት፦ አብዛኛውን ጊዜ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ምልክት ነው።
-ከጡት ጫፍ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ መውጣት
-ከጡት ጫፍ ዙሪያ ያለው የቆዳ ቀለም ወይም ገጽታ መለወጥ
-በብብት ስር ያሉ እጢዎች ማበጥ
⚠️ በሽታው ሳይታከም ሲቆይ እና ደረጃው ሲገፋ የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፦
🩹የጡት መቁሰል፣ ከቁስሉ ደም መፍሰስ ወይም በቁስሉ ላይ ተጨማሪ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን መከሰት (Ulceration & Super infection)
🍊የብርቱካን ልጣጭ የሚመስል የጡት ገጽታ፦ የጡት በከፍተኛ ሁኔታ ማበጥ፣ መቅላት እና በጡት ቆዳ ላይ ትንንሽ ጉድጓዶች መፈጠር።
😮💨የሳል ወይም የጀርባ ህመም፦ ካንሰሩ ከጡት አልፎ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል (ለምሳሌ ወደ ሳንባ ወይም አጥንት) መሰራጨቱን (Distant metastases) የሚያሳይ ምልክት ሊሆን ይችላል።
⚠️የጡት ካንሰርን አስቀድሞ ማወቅ ህይወትን ለመታደግ እና ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ለመዳን ቁልፉ መንገድ ነው።
❇️ የራስን ጡት አዘውትሮ መመርመር (Regular Self-Breast Examination)፦ እያንዳንዱ ሴት በየወሩ በቤቷ ውስጥ የራሷን ጡት እና ብብት በትክክለኛው መንገድ በመዳሰስ ምንም አይነት አዲስ ለውጥ ወይም እብጠት አለመኖሩን እንድታረጋግጥ ይመከራል።
❇️ለማንኛውም እብጠት ትኩረት መስጠት፦ በጡት ላይ የሚገኝ ማንኛውም አይነት እብጠት (Lump) ችላ ሊባል አይገባም፤ ተገቢው የህክምና ክትትል እና ምርመራ (Workup) ሊደረግለት ይገባል።
📋 የሚገኙ የህክምና አማራጮች
በሽታውን ለማከም እንደ አስፈላጊነቱ ብቻቸውን ወይም ተጣምረው ሊሰጡ የሚችሉ የህክምና አይነቶች፦
ቀዶ ጥገና
የኬሞቴራፒ ህክምና
የሆርሞን ህክምና
የጨረር ህክምና
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🥱 ለምን እናዛጋለን?
❇️ አሁን ይህንን ርዕስ ሲያነቡ እንኳ ሊያዛጉ እንደሚችሉ ያውቃሉ😀? ማዛጋት በዓለማችን ላይ ካሉ እጅግ ሚስጥራዊ የሰውነት ተግባራት አንዱ ነው፡፡ እስቲ ስለዚህ አስገራሚ ድርጊት ሳይንሳዊ እውነታዎችን እንመልከት፡፡
📌 ማዛጋት ምንድን ነው? ማዛጋት ጥልቅ አየር ወደ ውስጥ የምናስገባበት፣ የጆሮ ታምቡርን የምንወጥርበት እና አጠር ያለ አየር ወደ ውጭ የምናወጣበት ሂደት ነው። ይህ በሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ከአንበሳ እስከ አሳ ባሉ አብዛኛዎቹ የጀርባ አጥንት ባላቸው እንስሳት ላይም ይታያል።
😲 አስገራሚ እውነታዎች
👥 ተላላፊነቱ፡ አንድ ሰው ሲያዛጋ ካዩ፣ በሚቀጥሉት 5 ደቂቃዎች ውስጥ እርስዎም የማዛጋት እድልዎ 50% ነው!
🤰🏻ከማህፀን ጀምሮ፡ ፅንሶች ገና በ11ኛው ሳምንት የእርግዝና ጊዜ ውስጥ ማዛጋት ይጀምራሉ።
⏰ ጊዜው፡ በአማካይ አንድ ጊዜ ማዛጋት 6 ሰከንዶች ይወስዳል።
💡ለምን እናዛጋለን? (ጥቅሞቹ)
⚡️ሳይንቲስቶች ቀደም ሲል ማዛጋት ኦክስጅንን ለመጨመር ነው ብለው ያስቡ ነበር፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ የሚከተሉት ምክንያቶች ይበልጥ ተቀባይነት አግኝተዋል::
1️⃣ አንጎልን ማቀዝቀዝ፡ ማዛጋትን እንደ ጭንቅላትዎ "ማቀዝቀዣ (Fan)" አድርገው ያስቡት። ቀዝቃዛ አየር ወደ ውስጥ በጥልቀት መሳብ የአንጎልን ሙቀት ለማስተካከል ይረዳል።
2️⃣ ንቁ መሆን፡ አሰልቺ ስራዎች በሚሰሩበት ጊዜ የፊት ጡንቻዎችን በመለጠጥ እና የደም ዝውውርን በመጨመር ንቁ ሆነው እንዲቆዩ ይረዳል።
3️⃣ የጆሮ ግፊትን ማስተካከል፡ በአውሮፕላን ሲበሩ ወይም ከፍታ ቦታ ላይ ሲሆኑ በጆሮዎ ላይ የሚሰማውን የ"ፖፕ" (pop) ድምፅና ግፊት ለማስተካከል ይረዳል።
⚙️ ማዛጋትን የሚቀሰቅሱ ነገሮች
🙁መሰላቸት፡ አንጎል አዲስ ነገር ሲያጣ የሙቀት መጠኑ ይጨምራል፤ ማዛጋት ደግሞ "ለመነቃቃት" የሚደረግ ጥረት ነው።
ድካም፡ እንቅልፍ ሲመጣ የአንጎል ማቀዝቀዣ ስርዓት ስለሚቀንስ ማዛጋት ይከሰታል።
😨ጭንቀት (Anxiety)፡ ብዙ አትሌቶችና ንግግር አቅራቢዎች ትልቅ ክስተት ከመጀመሩ በፊት ጭንቀትን ለማስታገስ ያዛጋሉ።
👥 አንድ ሰው ሲያዛጋ እርሶ የሚያዛጉትን ማዛጋት ተላላፊ ማዛጋት እንለዋለን። ይህ ድርጊት በህብረት ውስጥ ንቁ ሆኖ ለመቆየትና ተግባቦትን ለማሳለጥ ይረዳል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ተላላፊ ማዛጋት ከሌሎች ስሜት ጋር ከመረዳዳት (Empathy) ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በተለይም በጣም የሚቀርቡት ሰው ሲያዛጋ እርስዎም የማዛጋት እድልዎ ከፍተኛ ነው!
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🌪ጄነራላይዝድ አንዛይቲ ዲሰኦርደር(Generalized Anxiety Disorder - GAD)
ጭንቀቱ ለረጅም ጊዜ (ከ6 ወር በላይ) የሚቆይ፣ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ላይ እንቅፋት የሚፈጥር እና ለመቆጣጠር የሚያስቸግር ሲሆን GAD ይባላል።
⚠️ይህ ሁኔታ ከክስተቱ በላይ የሆነ ከፍተኛ ስጋትን ያካትታል።
🚩 ምልክቶች (Symptoms)
😟 የማያቋርጥ ስጋት፦ ሁልጊዜ "መጥፎ ነገር ይከሰታል" በሚል ስጋት እና አእምሮ በሃሳብ መወጠር።
😣 የጡንቻ መወጠር፦ የሰውነት መቆረጣጠም፣ የራስ ምታት ወይም በጡንቻዎች ላይ ከፍተኛ ጥንካሬ መሰማት።
😴 የእንቅልፍ መዛባት፦ እንቅልፍ መተኛት መቸገር፣ ቶሎ ቶሎ መንቃት ወይም በድካም ስሜት መንቃት።
😤 ቶሎ መበሳጨት፦ በትንሽ ነገር መናደድ ወይም ትዕግስት ማጣት ቶሎ መቆጣት።
🧠 ትኩረት ማጣት፦ በጭንቀት ሃሳቦች ምክንያት በአንድ ነገር ላይ ማተኮር መቸገር (አእምሮ ባዶ እንደሆነ መሰማት)።
🏥 ሕክምና
🗣የንግግር ሕክምና (CBT)
💊የመድኃኒት ሕክምና፦ የነርቭ ሥርዓትን ለማረጋጋት በሀኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
የስክሪን ጊዜ በህጻናት አእምሮ ላይ ያለው ተጽዕኖ 🧠
✨ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ፈጣን ይዘት ያላቸውን የስክሪን መረጃዎች(fast-paced digital content) መመልከታቸው በአእምሮ እድገታቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መምጣቱን ማየት ከጀመርን ሰነባብተናል፡፡ የቢቢሲ ዜና (BBC News) ሰሞኑን ስለ ስክሪን ጊዜ አጠቃቅም የወጡ አዳዲስ መመሪያዎችን ይዞ ብቅ ብሏል፡፡
👶 ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት አዲሱ የስክሪን ጊዜ መመሪያ
🔹ከ 2 ዓመት በታች፡ በህብረት ለሚደረግ እንቅስቃሴ ካልሆነ በስተቀር (ለምሳሌ ለዘመዶቻቸው በቪዲዮ መደወል) ጠቅላላውኑ የስክሪን ጊዜን ያስወግዱ።
🔹ከ 2 እስከ 5 ዓመት፡ የስክሪን ጊዜን በቀን ከአንድ ሰዓት በላይ አይጠቀሙ።
🔹የተከለከሉ ጊዜያት፡ በምግብ ሰዓት ምንም ዓይነት ስክሪን አይጠቀሙ ወይም ከመተኛት አንድ ሰዓት በፊት ስክሪን አይጠቀሙ።
🔹የይዘት ምርጫ፡ ዝግተኛ ፍጥነት(slow-paced) ያላቸውን ይዘቶች ይምረጡ፤ ፈጣን የሶሻል ሚዲያ ቪዲዮዎችን ወይም AI መጫወቻዎችን ያስወግዱ።
🚨 ፈጣን ይዘቶች ለምን ያሳስባሉ?
🔸የህፃናት አእምሮ ከአዋቂዎች አእምሮ እስከ 10 እጥፍ በሚዘገይ ፍጥነት መረጃዎችን ያዘጋጃል፡፡ ህጻናት ዝም ብለው ቢቀመጡም፤ ፈጣን የሆነ ይዘትን በሚያዩበት ጊዜ "fight or flight" (ተጋፈጥ ወይም ሽሽ) የተሰኘውን የጭንቀት ስርዓት ይቀሰቅሳል እናም ልባቸው ይመታል፣ ሀይል ወደ ጡንቻዎቻቸው ይለቀቃል ልክ አደጋ ውስጥ እንዳሉ ዓይነት፡፡
🔸የባህሪ ችግር፡ በልጅነት ጊዜ ከልክ ያለፈ ስክሪን መመልከት ለወደፊት የባህሪ መዛባት እና ቁጣ (tantrums) ያጋልጣል።
🔸 ቁጣን ለማረጋጋት ስክሪን መጠቀም ከጊዜ በኋላ ችግሩን ይበልጥ ያባብሰዋል።
👨👩👧👦 ተግባራዊ ተግዳሮቶች፡
🔻ወላጆች ስራ ሲበዛባቸው ለልጆቻቸው ስክሪንን እንደ መያዣ ይጠቀማሉ።
🔻ስክሪኑን ከልጆች መውሰድ ለከፍተኛ ብስጭት (meltdown) ምክንያት ሊሆን ይችላል።
🔻ቴክኖሎጂን ሙሉ በሙሉ ከማስወገድ ይልቅ የቤተሰብ ህይወት አዎንታዊ አካል ማድረግ ላይ ማተኮር ይመከራል። -------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🏘 አጎራፎቢያ (Agoraphobia)
አጎራፎቢያ ማለት "ለማምለጥ አስቸጋሪ በሆኑ ወይም እርዳታ በማይገኝባቸው ቦታዎች ላይ መገኘትን መፍራት" ማለት ነው።
🚩 የአጎራፎቢያ ምልክቶች
አንድ ግለሰብ አጎራፎቢያ ካለበት በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ከፍተኛ ጭንቀት ይሰማዋል :-
🔍ክፍት ቦታዎች ላይ መሆን
👥ሰፊ ህዝብ ያለበት ቦታ ላይ መሆን
🚌የህዝብ ትራንስፖርት ላይ መሆን
🏘ከቤት መውጣት
አካላዊ ምልክቶች፦
❣️የልብ ምት መጨመር፣
😰ማላብ፣
🥶መንቀጥቀጥ፣
😮💨የትንፋሽ ማጠር
😵💫ማዞር
💡 ህክምናው
የንግግር ሕክምና
የመድኃኒት ሕክምና -------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🧠 ፎሊክ አሲድ (Folic Acid)፣ (ቫይታሚን B9) "የእርግዝና ቫይታሚን" ከመሆንም በላይ ነው። ለዲኤንኤ (DNA) እና ለአጠቃላይ ጤንነትዎ መሠረታዊ ግብዓት ነው።
🧬 ጥቅሞቹ (ዋና ዋና ጉዳዮች)
🔻ዲኤንኤ (DNA) እና ለእድገት፡ ለዘረመል ውህደት (genetic integration) እና ለፈጣን የሴል ክፍፍል (rapid cell division) ወሳኝ ነው።
🔻ለደም ጤንነት፡ ከቫይታሚን B12 ጋር በመሆን ቀይ የደም ሴሎችን (RBCs)፣ ነጭ የደም ሴሎችን እና ፕሌትሌቶችን (platelets) ለመስራት ይረዳል።
🔻ለነርቭ፡ ጤናማ የነርቭ ስርዓትን ለመጠበቅ ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
🔻የበሽታ መከላከያ፡ የሰውነትን በሽታ መከላከያ ስርዓት ጠንካራ እና ንቁ ያደርጋል።
🤰 ለእርግዝና ጊዜ እጅግ ወሳኝ
❇️ ፎሊክ አሲድ ለነፍሰ ጡር እናቶች የግድ አስፈላጊ ነው፦
🔺በፅንሱ ላይ የሚከሰትን የነርቭ ቱቦ ችግሮች (Neural Tube Defects) ይከላከላል።
🔺የህፃኑን የአእምሮ እና የአከርካሪ አጥንት እድገት ይደግፋል።
🔅በእርግዝና ጊዜ የፎሊክ አሲድ ፍላጎት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።
🥬 ዋና ዋና የምግብ ምንጮች
🔸አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች፡ ቆስጣ ፣ ብሮኮሊ እና አተር።
🔸ፍራፍሬዎች፡ ሎሚ፣ ብርቱካን
🔸ፕሮቲኖች፡ ጉበት፣ ባቄላ እና ምስር።
⚠️ ጠቃሚ ምክር፡ ፎሊክ አሲድ በውሃ ውስጥ የሚሟሟ እና በከፍተኛ ሙቀት (overcooking) በቀላሉ የሚጠፋ ነው። ጠቃሚ ንጥረ ነገሮቹን ላለማጣት አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎችን በትንሹ ማብሰል
🚩 የእጥረት ምልክቶች
የፎሊክ አሲድ ማነስ ለ ሜጋሎብላስቲክ አኒሚያ (Megaloblastic Anemia) ሊያጋልጥ ይችላል፣ ምልክቶቹም፦
🔹ከፍተኛ ድካም እና የሰውነት መድከም።
🔹ትንፋሽ ማጠር።
🔹የበሽታ መከላከያ አቅም መቀነስ።
🔔ማስታወሻ፡ አልኮል መጠጣት በትናንሽ አንጀት ውስጥ የሚኖረውን የፎሊክ አሲድ ውህደት (absorption) በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። -------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
ለመላው የ ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ!እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳቹ!
በዓሉ የሰላም፣ የጤና ፣ የፍቅር ፣ እና የመተሳሰብ ይሁንልዎ።
መልካም የትንሳኤ በዓል።
Endi mavjud! Telegram Tadqiqoti 2025 — yilning asosiy insaytlari 
