cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የቃል ኪዳን እናት ኪዳነ ምህረት

⛪ ⛪ ⛪በተቻለ መጠን ጊዜውን ያማከሉ መዝሙር ስነ ግጥም ብሒለ አበው የቅዱሳን ስዕል እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ አሰተማረ የሆኑ ነገሮችን ለማቅረብ እንደ ዝ|ሐ|ኖ|ቅ|ኪ|ም|ገ|ሰ|ት|ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ ቻናል ነው⛪ ⛪ ⛪⛪🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #channal creater ☞☞ . . . ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን ለመደገፍ @KIDUS019 ላይ ላኩ!

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
179
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Hammasini ko'rsatish...
ትልቁ ፈተና መሞት አይደለም አለመኖር እንጂ! ትልቁ ፈተና መፀለይ አይደለም አለማመን እንጂ! ትልቁ ፈተና ማፍቀር አይደለም አለመፅናት እንጂ! ትልቁ ፈተና መደመር አይደለም አለማካፈል እንጂ ትልቁ ፈተና ማጣት አይደለም ተስፋ መቁረጥ እንጂ! ትልቁ ፈተና ማግባት አይደለም አለመግባባት እንጂ! ትልቁ ፈተና መደሰት አይደለም ደስታን አለመቆጣጠር እንጂ! ትልቁ ፈተና ማሰብ አይደለም የሚያስቡትን አለማጤን እንጂ! ትልቁ ፈተና ችግር አይደለም ትዕግስት ማጣት እንጂ! ትልቁ ፈተና ማዘን አይደለም ማማረር እንጂ! ትልቁ ፈተና ሃይማኖተኛ መሆን አይደለም መንፈሳዊ መሆን እንጂ! ትልቁ ፈተና ስልጣን አይደለም አጠቃቀሙን አለማወቅ እንጂ! ትልቁ ፈተና እውቀት አይደለም እያወቁ መሳሳት እንጂ! ትልቁ ፈተና ስደት አይደለም የተሰደዱለትን አላማ መርሳት እንጂ! ትልቁ ፈተና ወደ ራስ ማየት አይደለም ዘረኝነት እንጂ! ትልቁ ፈተና ስኬታማ መሆን አይደለም ራዕዩን መርሳት እንጂ! ትልቁ ፈተና የፀለዩትን ማግኘት አይደለም ያላገኙትን አለማማረር እንጂ! ትልቁ ፈተና ዝምተኛ መሆን መቻል አይደለም በዝምታ ውስጥ መረጋጋት ማጣት እንጂ! ትልቁ ፈተና ቤተክርስትያን መሄድ አይደለም የሚሄዱበት ምክንያት መዛባት እንጂ! ትልቁ ፈተና ገንዘብ አይደለም በገንዘቡ የምናደርግበትን ነገር አለማስተዋል እንጂ! ትልቁ ፈተና ልጅ መውለድ አይደለም ልጅን መቅረፅ እንጂ! ትልቁ ፈተና ዜግነት መቀየር አይደለም ማንነትን መርሳት እንጂ! ትልቁ ፈተና መጣላት አይደለም ለበቀል ማቀድ እንጂ! ትልቁ ፈተና ይቅርታ ማድረግ አይደለም ይቅርታውን ማመን እንጂ! ትልቁ ፈተና ፈጣሪን ማሰብ አይደለም ፈጣሪን ማመን እንጂ! ትልቁ ፈተና ተሰሚነትን መጨመር አይደለም ለሚሰሙን መልካም አርአያ መሆን እንጂ! ትልቁ ፈተና ስራ መጀመር አይደለም ስራውን መፈፀም እንጂ! ትልቁ ፈተና ማቀድ አይደለም አቅዶ መፈፀም እንጂ! ትልቁ ፈተና ሞክሮ መበላሸት አይደለም ድጋሚ አለመሞከር እንጂ! ትልቁ ፈተና ጓደኛ ማጣት አይደለም ወዳጅ ማግኘት እንጂ! ትልቁ ፈተና ማሸነፍ መቻል አይደለም አሸንፎ መፅናት እንጂ! ትልቁ ፈተና ተመስገን ማለት አይደለም አመስግኖ መርካት እንጂ! ትልቁ ፈተና መደንገጥ አይደለም ግራ መጋባት እንጂ! ትልቁ ፈተና መሸነፍ አይደለም ተሸንፎ መቅረት እንጂ! ትልቁ ፈተና እንደ እዮብ መውደቅ አይደለም እንደ እዮብ መፅናት እንጂ! ትልቁ ፈተና ከልብ ማልቀስ አይደለም ተሰብሮ መቅረት እንጂ! ትልቁ ፈተና ሰው ሆኖ መፈጠር አይደለም ሰው ሆኖ መኖር እንጂ! 🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
💕ማርያም ሆይ💕 👉እነሆ የፍቅርሽ መንፈስ አነሣሣኝ፡፡ በዕንጨቶች እመስልሽ ዘንድ፡፡ 👉 በእንኮይ ዕንጨት እመስልሻለሁ ወድጄ ከጥላሽ አርፊአለሁና፡፡ 👉 የኅቱም ድንግልናሽም አበባ ላፍንጫዬ ሸተተው፡፡ የንጽሕናሽ ፍሬም ለጐሮሮየ ጣመው ፡፡ ከናቱ ከልያ እርሻ ሮቤል እንዳገባው እንኮይ ዋጋ (ዘፍጥ፣ ፴፬ ፡፡) 👉 የያዕቆብ ልጅ ይሳኮር ተጸነሰ፡፡ የሥሳኮር ስሙ ግን ትርጓሜው የእንኮይ ዋጋ ማለት ነው፡፡ 👉 እንዲሁም ሊቶስጥራ በሚባል ስፍራ አይሁድ በጠመቁት በማኀፀንሽ ፍሬ ደም ዋጋ ጌታችን መድኃኒታችን ልጅሽ ከተሞሸረባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሃይምናን ተፀነሱ፡፡ 👉 እንግዲህ ደግሞ የዘይት ዕንጨት እልሻለሁ ያቋቋምሽ ደም ግባት አማረኝ ካንቺ የፈሰሰው በለሳን ቅቤም የፊቴ መቀቢያ ሆነ፡፡ 👉 የበለስ ዕንጨት ብዬ እጠራሻለሁ አዳም ሰፍቶ መከለያ እድርጐ ዕርቃኑን ስለሠወረበት የበለስ ቅጠል እንዲሁ እኔም ከልጅሽ ጐን ከፈሰሰው ጥምቀት ውሀ ሙሽርነትን ተከደንሁ፡፡ (ዘፍጥ ፫-፯ ፡፡) 👉 የነቢዩም የኤርምያስ ደቀ መዝሙር ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ስለ ለቀመው የበለስ ቅንጣት፡፡  👉 ከመሶብ ውስጥ አኖረው፡፡ ጥቂትም ፈቀቅ ብሎ ከዕንጨት ጥላ ስር ፷፮ ዓመት ተኛ ቢነቃም ዛሬውን ተኝቶ ዛሬውን የነቃ መሰለው። የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን !!! 🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Hammasini ko'rsatish...
#ወምድርኒ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ(፪) ምድርም ፀዳች ሐሴት አደረገች በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች(፪) 🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Hammasini ko'rsatish...
ወምድርኒ.mp37.75 KB
እንቋዕ አብጽሐክሙ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም በፍቅር ወበጥዒና። ሠናይ በዓል ይኩን ለኲልክሙ ሕዝበ ክርስቲያን! BAGA AYYAANA DU'AA KA'UU GOOFTAA KENYAA IYAASUS KIRISTOOSIN NAGAAN ISINIIN GAHE "ኢሀሎ ፡ ዝየ ፡ ተንሥአ ፡ በከመ ፡ ይቤ ፤ እንደተናገረ ተነስቷልና በዚህ የለም" ''AKKA JEDHEETI KA'EERA ASI HIN JIRU'' ማቴ ፳፰ ፥ ፮ "እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም በፍቅርና በጤና አደረሳችሁ።" ✝️ ለሁሉም የክርስቲያን ሕዝብ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁን 🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Hammasini ko'rsatish...
“ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።” ሉቃስ 24፥5 🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Hammasini ko'rsatish...
​​👉ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ ⚡⚡⚡ሰኞ⚡⚡⚡ 👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ⚡⚡⚡ማክሰኞ⚡⚡⚡ 👉ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 ⚡⚡⚡ረቡዕ⚡⚡⚡ 👉አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ⚡⚡⚡ሐሙስ⚡⚡⚡ 👉አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ⚡⚡⚡ዓርብ⚡⚡⚡ 👉ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ ⚡⚡⚡ቅዳሜ⚡⚡⚡ 👉ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ⚡⚡⚡እሁድ⚡⚡⚡ 👉ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ 🤗በትንሳኤ ወቅት ሰላምታችን🤗 #ክርስቶስ_ተንስአ_እሙታን #በዐቢይ_ኃይል_ወስልጣን #አሠሮ_ለሠይጣን #አግዓዞ_ለአዳም #ሰላም #እምይእዜሰ #ኮነ_ፍስሐ_ወሰላም •➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 🇪🇹ኢትዮጵ🇪🇹 @KIDUS017
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.