uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

طــــريــقــة الــنــجــاح

طــــريــقــة الــنــجــاح

Kanalga Telegram’da o‘tish

من أحب أن لا ينقطع عمله بعد موته فلينشر العلم {ابن الجوذي رحمه الله /التذكرة(٥٥)

Ko'proq ko'rsatish
2 335
Obunachilar
-324 soatlar
+237 kun
+5830 kun
Postlar arxiv
📌ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «ለማንኛውም ፀጋ ምቀኛ እንዳለው ሁሉ ለማንኛውም ሀቅ ደግሞ አስተባባይና ተእቢተኛ አለው።» 📚 ۞ مفتــاح دار الـســعادة【1/216】۞

ወንድማችን ሸይኽ ሙሐመድ አረብ ወለጋ ወደ አኺራ ሂደዋል በዓለም ላይ ያላቹህ ሙስሊሞች ዱዓ አድርጉላቸው ማረፊያቸውን ፊርደውስ አሏህ ያርግላቸው ልባችን ቢያዝንም አሏህ የማይወደውን አንናገርም إن لله ما أخذ وله ما أعطى وكل شيء عنده بأجل مسمى إنا لله وإنا إليه راجعون ! إن العين تدمع والقلب يحزن ولا نقول إلا ما يرضي ربنا وإنا بفراقك يا شيخنا لمحزونون. 👉   ውድ ሰለፍዮች አላህ ሶብር ይስጣችሁ ! ዉዱ ሸይኻችን ሸይኽ ሙሐመድ ዐረብ ቱሉ ጋና ዛሬ መግሪብ አካባቢ በተነሳ ጦርነት ተባራሪ ጥይት መቷቸው ወደ አኼራ ሄደዋል ። አላህ ከሙቀረቦቹ ጋር ያድርጋቸው ። ቤተሰቦቻቸውና ዘመድ አዝማድ እንዲሁም መላው ሰለፍይ ማህበረብ አላህ ፅናቱን ይሰጠው ። https://t.me/bahruteka/7901

👉 የቡኻሪ ሞትና የሚስክ ሽታ ! " كان البخاري يحفظ أكثر من ست مائة ألف حديثا لما مات – رحمه الله – فاحت رائحة المسك من قبره " سير أعلام النبلاء (12/466) " ኢማሙል ቡኻርይ ከ600 ሺህ በላይ ሐዲስ ሐፍዞ ነበር ። በሞተ ጊዜ ከቀብሩ የሚስክ ሽቶ መአዛ ይነፍስ ነበር "። http://t.me/bahruteka

🌹....በሐላል መንገድ ሴትን ለማግኘት የሚጥር ወንድ ልብን የሚስብ ነገር አለው፤ እርሱም በሕይወቱ ውስጥ በስውር መሆንዋን ሳይሆን፣ በሕይወቱ ውስጥ ቦታ ሊሰጣት እንደሚፈልግ፣ እና አንድ ቀን ሁልጊ
🌹....በሐላል መንገድ ሴትን ለማግኘት የሚጥር ወንድ ልብን የሚስብ ነገር አለው፤ እርሱም በሕይወቱ ውስጥ በስውር መሆንዋን ሳይሆን፣ በሕይወቱ ውስጥ ቦታ ሊሰጣት እንደሚፈልግ፣ እና አንድ ቀን ሁልጊዜ ሊከፈትለት ይመኘው ከነበረው በር በኩል ወደ እርሷ መምጣት እንደሚፈልግ ነው...

#ስለ_ሰዎች_እውነታ 👇👇 (وَإِن تُطِعۡ أَكۡثَرَ مَن فِی ٱلۡأَرۡضِ یُضِلُّوكَ عَن سَبِیلِ ٱللَّهِۚ إِن یَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ هُمۡ إِلَّا یَخۡرُصُونَ) በምድርም ካሉት ሰዎች አብዛኞቹን ብትከተል ከአላህ መንገድ ያሳስቱሃል፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡ [አል_አንዐም 116] ╭┈──── ••⇣⇣🌸🍃 ╰┈➢https://t.me/sehih_hadith🌹

#የማለዳ_ግብዣ💦🌹 🍂ከሱረት_አል_መርየም🎧💐 አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ { ቁርአን 33፡35}🌹📖 ╭┈──── ••⇣⇣🌸🍃 ╰┈➢https://t.me/sehih_hadith🌹

📌ሷሊሕ አል-ዲማሽቂ (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፡- «ልጄ ሆይ! ሃይማኖትህ፣ አካልህ፣ ሀብትህ እና ቤተሰብህ ሰላም እና ደህንነታቸው የተጠበቀ ሆኖ አንድ ቀንና ሌሊት ካለፈህ፤ አላህ (ተባረከ ወተዓላን) እጅግ በጣም አመስግነው። በዚያች ቀን በደህንነትና በሰላም ባለህበት ሰዓት ሃይማኖታቸውን ያጡ፣ ወይም ሀብታቸው የተዘረፈባቸው፣ ወይም ስውርነታቸው (መከለያቸው) የተገለጠባቸው፣ ወይም ደግሞ አከርካሪቸው የተሰበረ (ከባድ ድብርትና ውድቀት የገጠማቸው) ስንቶች አሉ!» 📚 ታሪኽ ዲማሽቅ 23/325

Repost from N/a
─── 🌸 ─── ✨ የዲን እውቀትዎን የሚያዳብሩበት ምርጥ ስፍራ! • ✍️ አስተማሪ ጽሑፎች • ❓ ኢስላማዊ ጥያቄዎች • 💡 ድንቅ ጥበቦች 👉 አሁኑኑ ይቀላቀሉን፤ የኸይር ተካፋይ ይሁኑ! ───────────

سُورَةُ #الكهف📖🌸👈 || 🎙️طارق مُحمد 💦ሱረቱል #ካህፍ 👉 የቻለ ይቅራ 📖ያልቻለ ያዳምጥ 🎧 💐 Join And Share ⤵️⤵️ ┈••••••••✿❒🌹https://t.me/sehih_hadith🌹✿❒•••••••┈ ┈••••••••✿❒🌹https://t.me/sehih_hadith🌹❒✿••••••••

ለማስታወስ ያክል ↪️#ጁመዓ!! 🌹🕌 🍃እናንተ ያመናችሁ ሆይ በአርብ ቀን ወደ ስግደት በተጠራ ግዜ አላህን ወደ ማውሣት ሂዱ መሸጥንም ተው ይህ የምታውቁ ከሆነ ለናንተ በላጭ ነው። , 《ሡረቱል ፦ አል ጁሙአህ》 በላጭ ቀናቹ የጁመዐ ቀን ነው ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም "ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዐ ቀን ነው ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም , ~ከላይ ያለፋት መለኮታዊ ንግግሮች በኢስላም ከሌሎች ቀናቶች ለይቶ ለጁመአ ለት የሠጠውን ደረጃ ያሣዩናል ይህን የተከበረ ቀን በምን መልኩ ማሣለፍ እንዳለብን ከነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ዘንድ የመጡት በማውሣት እንተዋወስ ወደ መልካም ነገር ያመላከተ እንደሠሪው ያክል መንዳ ያገኝበታል ። , =•የጁመአ ለት ሡብሒ ሠላት ያለው ደረጃ ,አላህ ዘንድ በላጩ ሠላት የጁመአ ቀን ሡብሒ በጀመአ መስገድ ነው።] 《📚ሢልሢለቱ ሰሒህ》 ~ጁመአ ለት ሡብሒ ሠላት ላይ ምንምን ሡራ ይቀሩ ነበር ? , ~የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለምበጁመአ ሡብሒ ላይ 《አሊፍ ላም ሚም ተንዚሉ: ሠጅዳ》 እና 「ሀል አታ አለል ኢንሣኒ」 ይቀሩ ነበር። 《📚ቡኻሪና ሙስሊም》 , 🔺 በጁመአ ቀን ሠለዋት ማውረድ ያለው ጥቅም ፦ ~የጁመአ ቀን እና ማታ በኔ ላይ ሠለዋትን አብዙ,በይሀቅይ ~በላጭ ቀናቹ የጁመአ ቀን ነው የዛ ቀን: "አደም ተፈጠረ "ሞተ "ጡሩንባ ይነፋል "በህይወት ያለ ሁሉ ይሞታል በኔ ላይ ሠለዋትን አብዙ ሠለዋታቹ በኔ ላይ የምትቀረብ ናት " ~አስሀቡ ሡነንነወውይ 📚ሰሒህ ብለውታል , 🚿የጁመዓ ቀን ገላን መታጠብ አንደኛቹ ወደ መስጂድ ሢመጣ ገላውን ይታጠብ ። 《📚ቡኻሪና ሙስሊም 》 , የጁመአ ቀን ሽቶ መቀባት ፣ ጥሩውን መልበስ ፣ረጋ ብሎ ሣይጣደፍ ወደ መስጂድ መሔድ በሁጥባ ወቅት ዝም ብሎ ማዳመጥ ያለው ጥቅም ~የጂመአ ቀን የታጠበ, ሽቶ ካለውና ከተቀባ (ለወንድ ማለት ነው),ጥሩ ልብስ የለበሰ , ወደ መስጂድ ሢሔድ በተረጋጋ መንፈስ ከሔደ ,ከተመቸውና ከሠገደ ,አንድንም ሠው ካላስቸገረ , ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣበት እስኪሠገድ ድረስ ዝም ያለ በሁለት ጁመአዎች መሀል ያለውን ወንጀል ይማርለታል " , 🕐በግዜ መስጂድ መሔድ,የጁመአ ቀን መላይካዎች የመስጂድ በር ላይ ይቆማሉ ከዛ መጀመርያ ቀድሞ የሚገባውን ይፅፋሉ : መጀመርያ መስጊድ የሚገባው ግመል እንደሠጠ ከሱ ቀጥሎ ከብት ከሡ ቀጥሎ በግ ከዛም ዶሮ ከዛም እንቁላል ኢማሙ ሚንበር ላይ ሢወጣ መዝገቡን ዘግተው ሊያዳምጡ ይገባሉ " 《📚ቡኻሪና ሙስሊም 》 🚫 የጁመአ ቀን የተከለከሉ ነገሮች ❗️ #ኢማሙ ሁጥባ ሢያደርግ ማንኛውም አይነት ንግግር ክልክል ነው በመልካም ማዘዝም ከመጥፎ መከልከልም ቢሆን "ለጎደኛህ የጁመአ ቀን ኢማሙ ሁጥባ እያደረገ ዝም በል ካልከው ውድቅ የሆነ ነገር ሠርተሀል "ቡሀርና ሙስሊም አህመድ "ውድቅን ነገር የሠራ ከጁመአው ምንም ነገር የለውም " የሚል ጨምረው ዘግበዋል , ~ዘግይቶ መስጂድ መምጣት እና ሠዎች አዛ ማድረግ "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሁጥባ እያደረጉ አንድ ሠው በሠዎች ጀርባ ላይ እየተረማመደ ሢመጣ "ተቀመጥ! ሠዎችን አስቸገርክ" አሉትኝ , አላህ የተጠየቀውን ነገር የማይመ ልስባት አንድ ወቅት አለች። #በጁምአእለት አንድ ሠአት አለች እሧን ሠአት አንድ ሙስሊም የሆነ ባርያ አያገኛትም እሡ የሚሠግድ ሢሆን አላህን አንዳች ነገር አይጠይቀውም የሠጠው ቢሆን እንጂ " 《 ቡኻሪ እና ሙስሊም 》📚 , ~ ያቺ ሠአት መቼ ናት? በዚህ ዙርያ ኡለሞች የተለያየ አመለካከት ሠንዝረዋል ከሙስሊም በተዘገበ ሀዲስ ኢማሙ ሁጥባ ከጨረሰበት ሠላት እስኪሰገድ ያለው ክፍተት ነው "አቡ ዳውድ እና ነሳእይ በዚህ መልኩ ዘግበዋል , ~ከጁመአ የመጨረሻው ወቅት ላይ ፈልጓት "በሌላ ዘገባ "ከአስር ቡሀላ የሚል ነው። ኢብኑ አልቀዪም፦(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ የጁምዐ ዕለት የዒባዳ ዕለት ነው፣ ከቀናት አንፃር እንደ ወርሃ ረመዳን ዒባዳ የሚወደድበት ዕለት ሲሆን በዕለቱ ልክ እንደ ለይለቱ አልቀድር ዱዓ ተቀባይነት የሚያሆንበት ሰዓት አለ። 【ዛዱል ሚዓድ 1/198】 Join And Share ⤵️⤵️ ┈••••••••✿❒🌹https://t.me/sehih_hadith      🌹✿❒•••••••┈ ┈••••••••✿❒🌹https://t.me/sehih_hadith ❒✿••••••••

አዝካሩ ሰባህ(የጥዋት ዚክር) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ أَصْبَحْنَا وَأَصْبَحَ الْمُلْكُ لِلَّهِ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرُ. رَبِّ أَسْأَلُكَ خَيْرَ مَا فِيْ هَذَا الْيَوْمِ وَخَيْرَ مَا بَعْدَهُ، وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِيْ هَذَا الْيَوْمِ وَشَرِّ مَا بَعْدَهُ، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنَ الْكَسَلِ وَسُوْءِ الْكِبَرِ، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ فِي النَّارِ وَعَذَابٍ فِي الْقَبْرِ. ‎ ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ ‘አሰባሕና ወአሰበሐል መልኩ ሊልላህ ወልሐምዱ ሊልላህ ላኢላሀ ኢልለሏሀ ወሕደሁ ላሸሪክ ለሁ ለሁል መል ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲይር፤ ረብቢ አስአሉከ ኸይረ ማፊ ሃዝል የውመ ወኸይረ ማባዕደሁ ወአዑዙ ቢከ ሚንሸርሪ ማፊ ሐዘል የውመ ወሸርሪ ማ በዕደሁ፤ ረብቢ አዑዙ ቢከሚነል ከስሊ ወሱኢል ኪበር፤ ረብቢ አዑዙ ቢከ ሚን ዐዛቢን ፈንናር ወዐዛቢን ፊል ቀብር ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ ማለዳ ላይ ለመድረስ ነቅተናል፡፡ በዚህ ሰዓት ሉዓላልነት የዓላማት ጌታ የሆነው አላህ ነው፡፡ ምስጋና ከአላህ ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አገር የለውም፡፡ ሉዓላዊነት የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም የርሱ ብቻ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ የዚህን ቅና የቀጠዩን /የሌሊቱን/ መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፡፡ ከዚህ ቀንና ከቀጣዩ /ከሌሊቱ/ ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ ከእሳት ቅጣት ከቀብር ውስጥ ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ┈┈•••✿❒🌹❒✿•• اَللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّيْ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ، خَلَقْتَنِيْ وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوْءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوْءُ بِذَنْبِيْ فَاغْفِرْ لِيْ فَإِنَّهُ لاَ يَغْفِرُ الذُّنُوْبَ إِلاَّ أَنْتَ.‎ ‘አልሏሁምመ አንተ ረብቢ ላኢላህ ኢልላ አንተ፤ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱከ ወአነ ዐለ ዐሕዲከ ወወዐዲከ መስተጠዕቱ አዑዙ ቢከሚን ሸርሪ ማስነዐቱ አቡዑ ለከ ቢኒዐመቲክ ዐለይየ ወአቡኡ ቢዘንቢ ፈግፈርሊ ፈኢንነሁ ላየግፈሩ ዙኑበ ኢልላ አንተ አላህ ሆይ አንተ አምላኬ ነህ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ፈጥረህኛል፡፡ እኔ ባሪያህ ነኝ፡፡ እኔ የቻልኩትን ያክል ያንተን ቃልዳኪን ለመሙላት እሞክራለሁ፡፡ ከስራሀው ነገር ከክፉው በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ በኔ ላይ ለዋልከው ጸጋህ እውቅና እሰጣለሁ፡፡ ሐጢአቴም እናዘዛለሁ፡፡ ማረኝ፡፡ ከአንተ ውጭ ሐጢአትን የሚምር የለም፡፡’ اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَصْبَحْتُ أُشْهِدُ وَأُشْهِدُ حَمَلَةَ عَرْشِكَ، وَمَلاَئِكَتَكَ وَجَمِيْعَ خَلْقِكَ، أَنَّكَ أَنْتَ اللهُ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ وَحْدَكَ لاَ شَرِيْكَ لَكَ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُكَ وَرَسُوْلُكَ. (4×)‎ አልሏሁምመ ኢንኒ አሰበሕቱ ኡሽሒዱከ ወኡሸሒዱ ሐመለተ ዐርሺክ፤ ወመላኢከተከ ወጀሚዓ ኀልቂከ፤ አንከ አንተአሏህ ላኢላሃ ኢለላ አንተ ወሕደክ ላሸሪከ ለከ፤ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱከ ወረሱሉከ] አንተነህና ዙፋንህን የተሸከሙ /መላዕክትን/ ስመሰክር አንግቻለሁ፡፡አንተ አላህ መሆንህንና ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ እንደሌለ አንድነትህ አጋር እንደሌለህም፤ ሙሐመድም ባሪያህና መልዕክተኛህ መሆናቸውንም፡፡ አራት ጊዜ፡፡ /አቡዳውና ቡኻሪ/✍ 373

🪶ዛሬ ላይ ሁሉም መልካም ስራህ አደባባይ ላይ ነው። ዑምራው፣ ሰደቃው፣ ፆሞ፣ ሶላቱ እንደዚህ ማድረጉ (በአደባባይ መታየቱ) በራሱ ባያስኮንንም ነገር ግን መልካም ሥራዎች በሰዎች ፊት ሲከናወኑ የሪአ (የዝና ወይም የውዳሴ ፍላጎት) ስሜት የመቀላቀል ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። በሰው ዓይን ሳይታይ፣ በይፋ ሳይነገር፣ ከሰው እይታ ተደብቆ በብቸኝነት ከፈጣሪ (አላህ) ጋር ብቻ የሚደረግ መልካም ሥራን መከውን አላህ ዘንድ ለመወደድም ተቀባይነት እንዲኖረው ወሳኝ ተግባር ነው! ረሱል (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مَنِ استطاعَ منكم أنْ يكونَ لَهُ خَبْءٌ [خَبِيءٌ] مِنْ عمَلٍ صالِحٍ فلْيَفْعَلْ﴾ “ከእናንተ መካከል ከሰዎች የተሰወረ (የተደበቀ) መልካም ሥራ መፈጸም የቻለ ሰው፣ ይሥራው።” 📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 6018 አል۔ኢማሙ ዘሀቢ እንዲህ ይላሉ፦ {كانوا - أي: السلف - يستحبُّون أن يكون للرجل خبيئةٌ من عملٍ صالحٍ، لا تعلم به زوجته ولا غيرها} “ሰለፎች ሰውዬው ሚስቱም ሆነች ወይም ሌላ ማንም ሰው የማያውቀው (የተደበቀ) መልካም ስራ እንዲኖረው ይወዱ ነበር (ያዘውትሩ) ነበር።” 📕 ሲየር አዕላሙ ኑበላ፡ 9/349 ©Sahih bukhari&Muslim

🔷ይሄ አፕ ስልካቹ ላይ የሌለ ሰዎች Ok ሚለውን ተጭናቹ የሰለፊዮች ቻናል ይቀላቀሉ
🔷ይሄ አፕ ስልካቹ ላይ የሌለ ሰዎች Ok ሚለውን ተጭናቹ የሰለፊዮች ቻናል ይቀላቀሉ

🌸#አላህ_አይተወዉም 🥀...«ሰዎችን በጥቃቅን ነገሮች ሳይቀር አላህን የሚፈራው፣ ቁጣውን የሚውጠው፣ መልሱን የሚገታው፣ ልቤን ይጎዳኛል በማለት ዓይኑን ከማዞር የሚቆጠበው፣ የሰውን ስሜት የማያዋርደው፣ በባለቤቱ ዓይን ትልቅ የሆነን ነገር የማይተች፣ ቅሬታ ይዞ የመጣ ሰው ከእርሱ ሲመለስ ልቡ ሰላም አግኝቶ የሚወጣ፣ የልብ ፍቅር እንዲቀጥል ሲባል ስህተትን ይቅር የሚለው (የሚያልፈው) ያ ሰው አላህ ፈጽሞ አይተወውም!» ⛈ ┈••••••••✿❒🌹https://t.me/sehih_hadith🌹❒✿••••••••

{قَد نَرَى تَقَلُّبَ وَجهِكَ فِي السَّمَاء} 👌...ወደ ሰማይ የሚደረጉ ዝም ያሉ፣ ያለ ቃል በምልጃ የተሞሉ አሻንጉሊት-አልባ እይታዎች፤ አሏህ ዝርዝራቸውን አወቀ፣ በነብዩም ልብ ውስጥ የነበሩትን አንደበቱ ከመናገሩ በፊት አንበባቸው:: {فَلنُوَليَنكَ قِبلَةً تَرضَاهَا} የመጠባበቅን ፍርሃትና ብቸኝነት የሚያስቀር፣ ልብን የሚጠግን የአላህ ውበትና እርካታ መፍሰስ!!። ከዚህ ሁሉ በኋላ ልብህ አይረጋጋምን?..... ┈••••••••✿❒🌹https://t.me/sehih_hadith🌹❒✿••••••••

أذكار الصباح. #የጠዋት_ዚክር 📖🌹 وَٱذۡكُرِ ٱسۡمَ رَبِّكَ بُكۡرَةٗ وَأَصِيلٗا የጌታህንም ስም በጧትና ከቀትር በላይ አውሳ፡፡ [አል_ኢንሳን ፡ 25]

#ሐጢአት_በግልጽ_እና_በስውር የሚፈጸሙ አላህ በሱረቱል አንዓም ላይ አማኞችን እንዲህ በማለት ያዘዛቸዋል፡ (وَذَرُوا۟ ظَـٰهِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَبَاطِنَهُۥۤۚ إِنَّ ٱلَّذِینَ یَكۡسِبُونَ ٱلۡإِثۡمَ سَیُجۡزَوۡنَ بِمَا كَانُوا۟ یَقۡتَرِفُونَ) የኃጢአትንም ግልጹንም ድብቁንም ተውዉ፡፡ እነዚያ ኃጢአትን የሚሠሩ፤ ይሠሩት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣሉ፡፡ [ሱረቱል አንዓም፡ 6:120] 👉...አል-ሻውካኒ በዚህ አንቀጽ ዙሪያ አስተያየታቸውን ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል፡ «የግልጽ ሐጢአት» ማለት እንደ የሰውነት ክፍሎች ተግባራት ያሉ የሚታዩት (የሚገለጡት) ሲሆኑ፣ «ስውር ሐጢአት» ማለት ደግሞ እንደ ልብ ተግባራት ያሉ የማይታዩት (የማይገለጡት) ናቸው። ሌሎችም በይፋ (በግልጽ) የምትሠሯቸውን እና በስውር (በሚስጥር) የምትሠሯቸውን ሐጢአቶች ይመለከታል አሉ። [ፈትሑል ቃዲር፡ 445] ┈••••••••✿❒🌹https://t.me/sehih_hadith🌹❒✿••••••••

👉..."ከሀራም መራቅ ላይ ታገስ፣ አላህ ይረዳሃል። ነገር ግን በስሜት ፊት ራስህን አቅልለህ ከላላህ፤ ስሜቱ ሁልጊዜ ያሸንፍሃል። በእርግጥም ሰው ከተከለከሉ ነገሮች መራቅ አለበት፣ ራሱን ለማስገደድ ከሞከረም አላህ ይታገሰዋል (ጽናቱን ይሰጠዋል)።"
ኢብኑ ዑሠይሚን📚🌹

💦የጧት አዝካር🌸📖 💦አስባህና ወ አስባሃ አልሙልኩ ሊላህ ወልሃምዱሊላህ ላ ኢላህ ኢለላህ ዋህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁልሃዱ ወሁወ ዓላ ኩሊሼኢን ቀዲር ፡፡ ረቢ አስአሉካ ከይሪ ማፊ ሃዘል የውም ወከይር ማባእደሁ ፡፡ ወዐኡዙ ቢካ ሚን ሸሪ ሃዘል የውም ወሸሪ ማባዕደሁ ፡፡ ረቢ አዑዙ ቢከ ሚነል ከሰል ወ ሱኢል ኪበር ፡፡ ረቢ አዑዙ ቢከ ሚን ዓዛብ ፊ ናር ወ ዓዛብ ፊልቀብር፡፡ ማለዳ ላይ ለመድረስ ነቅተናል፡፡)በዚህ ሰዓት ሉአላዊነት የለዓማት ጌታ የሆነው የአላህ ነው፡፡ምስጋና ለአላህ ይግባው፡፡ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡አንድ ነው፤ አጋር የለውም፡፡ሉአላዊነት የእርሱ ብቻ ነው፡፡እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡ጌታዬ ሆይ! የዚህን ቀንና (የምሽቱን) መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፡፡ ከዚህ ቀንና ከቀጣዩ (ከምሽቱ) ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ከስንፍናና መጥፎ ከሆነ እርጅና (ከመጃጀት) በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ከእሳት ቅጣት ከቀብር ውስጥ ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ አላሁመ ቢከ አስባህና ወቢከ አምሰይና ወቢካ ናህያ ወ ቢከ ነሙት ወኢለይከኑሹር። አላህ ሆይ ! በአንተ ለማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተም ለምሽት እንበቃለን፡፡በአንተ ህያው እንሆናለን፤ በአንተም እንሞታለን፤መሰብሰባችን ወደ አንተ ነው፡፡ አላሁመ ዓሊሚል ገይቢ ወሸሃዳ ፋጢሩ ሰማዋቲ ወልአርድ ረቢወዓን ኩሊሸይ ወመሊኪህ ፡፡አሽሃዱ አን ላ ኢላሃኢላ አንተ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ነፍሲ ወሚን ሸሪ ሸይጣን ወ ሺርኪህ፤ አቅተሪፉ ዓላ ነፍሲ ሱአን አው አጁሩሁ ኢላ ሙስልም፡፡ የሰማያትና የሩቅንም የቅርብንም የምታውቅ፤ የምድር ፈጣሪ የሆንክ አላህ ሆይ! የሁሉም ነገር ጌታ ነህ፤ የሁሉም ነገር የበላይ ተቆጣጣሪ ነህ፤ከአንተ ሌላ የሚመለክ አምላክ የለም ብዬ እመሰክራለሁ፡፡ከነፍሴ ክፉ ነገር ፣ ለሸይጣንና ከአጋሮቹ ተንኮል፣በራሴ ወይም በአንድ ሙስሊም ላይ ክፉ ነገር እንዳልፈፅምም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡* አላሁመ ኢኒ አስአሉከ አልዓፍው ወልዓፊያ ፊ ዱንያ ወልአኪራ ፤ አላሁማ ኢኒ አስአሉከ አልዓፍው ወልዓፊያ ፊ ዲኒ ወዱንያይ ፣ ወአህሊ ወማሊ ፤ አላሁማ እስቱር ዓውራቲ ወአሚን ረውዓቲ ፤ አላሁማ አህፈዝኒ ሚን በይኒ የደይ፣ ወሚን ከልፊ ፣ ወዓን የሚኒ ወዓን ሺማሊ ፣ ወሚን ፈውቂ ፣ ወአዑዙ ቢከ ቢዐዘመቲካ አን ኡግታል ሚን ታኽቲ፡፡ አላህ ሆይ! በዚህችም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ይቅርታና ጤንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! በሃይማኖቴ በዚህች ዓለም ህይወቴም ፣ በቤተሰቦቼም፣ በንብረቴም፣ ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ነውሬን ሸፍንልኝ፡፡አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴ ፣ከኋላዬም፣ከቀኜም ፣ ከግራዬም፣ከበላዬም ጠብቀኝ፡፡ከበታቼም እንዳልጠቃ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ላኢሃ ኢለላህ ዋህዱ ላሸሪከ ለሁ፤ ለሁልሙልክ ወለሁ ሃምድ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፡ ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡አንድ ነው፤ አጋር የለውም፡፡ንግሥና ምስጋና ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ በሁሉም ነገር ላይ ፍፁም ቻይ ነው፡፡ አስባህና ዓላ ፊጥረቲል ኢስላም ወዓ ከሊመቲል ኢኽላስ ወዓላ ዲኒ ነቢዩና ሙሐመድ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወዓላ ሚለቲ አቢና ኢብራሂመ ሃኒፈን ሙስሊመን ወማካነ ሚነል ሙሽሪኪን። በኢስላማዊ ተፈጥሯችን፣ በመልካም ንግግር(ከሊመተል ኢኽላስ)፣በነቢያችን በሙሐመድ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)ሃይማኖት ፣ቀጥ ያለ ሙስሊም በነበረውና ከሙሽሪኮች (ከሚያጋሩት) ባልነበረው በአባታችን በኢብራሂም ጎዳና ላይ እንደፀናን አነጋን፡፡ ያሃዩ ያቀዩም ቢራህመቲከ አስተጊስ ፤ አስሊህሊ ሻእኒ ኩሊህ ወላ ተኪልኒ ኢላ ነፍሲ ጠርፈተ ዓይኒን፡፡ አንተ ህያው የሆንክ አምላክ ሆይ! አንተ ራስክን የቻልክ አምላክ ሆይ! በእዝነትህ እታገዛለሁ፡፡ጉዳዬን ሁሉ የተስተካከለና መልካም አድርግልኝ፡፡ለቅፅበት እንኳን እኔን ለራሴ ብቻ አትተወኝ፡፡ አላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላህ ኢላ አንተ ኸለቅተኒ ወአና ዐብዱክ ፣ ወአና ዓላ ዓህዲከ፣ ወዋዕዱከ መስተጣዕቱ ፣ ዓኡዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሰዓዕቱ፣ አቡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዓለይ፤ ወ አቡኡ ቢዘንቢ ፈግፊርሊ ፈኢነሁ ላየግፊሩ ዙኑብ ኢላ አንተ፡፡ አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፣ከአንተ ሌላ የሚመለክ የለም፣አንተ ፈጠርከኝ፣እኔ ባርያህ ነኝ፡፡ በቃልኪዳኔና በገባሁት ቃል በምችለው አቅም አሟላለሁ፡፡በሰራሁት ሃጢአት ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡በእኔ ላይ ለዋልከው ጸጋህ እውቅናን እሰጣለሁ፡፡ ሐጢአቴንም አምኛለሁ፤ማረኝ፡፡ከአንተ ውጭ ሐጢአትን የሚምር የለም፡፡ ሱብሃነላህ ወቢሃምዲሂ፡፡ ለአላህ ጥራት እና ምስጋና ይግባው። •••••••••🌹••••••••🌅•••••🌴 ╭┈──── ••⇣⇣🌸🍃 ╰┈➢      https://t.me/sehih_hadith