cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት - ሐረር

ይህ በኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ የምሥ/ሐ/ሀ/ስ ጥንተ አድባራት ወገዳማት አቦከር ደብረ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ እና ሐኪም ጋራ ደብረ አድኅኖ ቅ/ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ገጽ ነው። ፨ ለመቀላቀል፡ 👉https://t.me/frehaymano ሀሳብ እንዲሁም አስተያየት ካሎት : 👉 @Frehaymanot1923 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "አገልግሎት ሕይወቴ ካልሆነ ፤ መኖር ለእኔ ሞቴ ነው"

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
608
Obunachilar
+224 soatlar
+87 kunlar
+3430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
🌾🍇ፍሬ ሃይማኖት ምርጫ ፳፻፲፮ ዓ.ም ፨፨፨ አሁን በአገልግሎት የሚገኘውን አመራር የአገልግሎት ጊዜ መጠናቀቅ አስመልክቶ ፤ ለቀጣይ 3ት ዓመታት ሰ/ት/ቤቱን ወክለው የሚመሩ ስራ አመራር የፊታችን እሑድ (ሰኔ 30/2016) ጠቅላላ ምርጫ ይካሄዳል ። ስለሆነም የሰ/ት/ቤቱ አካል የሆናችሁ ሁላችሁ 📌የወጣት እና የሰራተኛ ጉባዔ ቋሚ አባላት፣ 📌በቅርብም በሩቅም ያላችሁ የሰ/ት/ቤቱ ነባር አባላት፣ 📌የሰ/ት/ቤቱ አጋር የሆናችሁ ማኅበራት፣ እሑድ ሰኔ 30 / 2016 ዓ/ም በሰ/ት/ቤቱ ትምህርተ ወንጌል አዳራሽ አባቶች ካህናት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ⌚ ከቀኑ 8:30 ጀምሮ የምርጫው ሂደት ላይ እንድትሳተፉ ስንል በአክብሮት ጠርተንዎታል። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን🙏
Hammasini ko'rsatish...
👍 4 1
Photo unavailableShow in Telegram
🎉 ውድ የ 2015 ዓ.ም የ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና (Entrance) ተፈታኞች ፨፨፨ እንኳን የ 12 ዓመት ፍሬያችሁን ለምታዩበት ቀን በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እያልን የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት አባላት እና ግንኙነት ክፍል ባዘጋጀው የምህላ ጸሎት እና ኦረንቴሽን (Orientation) ቀን ተገኝታችሁ ለነፍሳችሁም ሆነ ለሥጋችሁም የሚሆን ስንቅ ትሰንቁ ዘንድ በክርስቶስ ፍቅር ጋብዘንዎታል! ፨፨፨ 🍇 የምህላ ጸሎት፡ ከሰኔ 26 – 28 ሰርክ 11፡00 – 12፡30 🌾 Orientation: ሐምሌ 14 ሰርክ 11፡00 – 12፡30 ፨፨፨ ይህን መልዕክት ቢያንስ ለ 5 ተፈታኝ ያድርሱልን! ፨፨፨ ተፈታኝ የሆናችሁ ሁላችሁ ተጋብዛችኋል!!! ፨፨፨ ፨፨፨
Editing Credit #ቤተ_ቃል (+251920892776) Contact Us
፨፨፨ https://t.me/frehaymano
Hammasini ko'rsatish...
4👍 2
Repost from Mahibere Kidusan
Hammasini ko'rsatish...
MK TV || የተመረጡ ገጾች || እንደ ሶሻል ሚዲያ የፈተነኝ የለም - ኢዩኤል ደረጀ

Subscribe and share

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK

https://www.facebook.com/eotcmkidusan/

4👏 1
👍 7 5
12👍 6🙏 2👏 1
✞ ማርያም እንወድሻለን ✞ "ኦ ማርያም በእነተዝ ናፈቅረኪ ወለዐብየኪ እስመ ወለድኪለነ መብልዐፅድቅ ዘበዐማን ወስቴሕይወት ዘበዐማን" ማርያም እንወድሻለን/፪/ ስለወለድሽ የሕይወት ምግብን ማርያም እንወድሻለን           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ድክመቴን አትይ…………ማርያም በሀጢያት መወደቄን……..ማርያም ተስፋዬ አንቺ ነሽ ……….ማርያም እስከለተሞቴ …………….ማርያም ላልከዳሽ ምያለሁ ………..ማርያም ከስርሽ ላልጠፋ ………….ማርያም ገፀ በረከቴ ……………….ማርያም የሕይወቴ ዋስትና ………..ማርያም           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► የምእመናን ውበት ……....ማርያም ዘውድ አክሊላቸው ………ማርያም ድንግል አንቺ እኮ ነሽ …….ማርያም የመንገድ ስንቃቸው ……...ማርያም ምስክር ነኝ ለአንቺ ………ማርያም እንደነብያቱ ………………ማርያም ስጦታ መሆንሽን …………ማርያም ለአዳም ልጆች ሁሉ ………ማርያም           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ሞገስና ፀጋ ……………ማርያም በጌታ ፊት ያለሽ ………ማርያም ከሰይጣን መሸሻ ...... ማርያም ዋስ ጠበቃችን ነሽ….….ማርያም እንዴት ነበር ያኔ …….ማርያም ጌታን ስትወልጂ ……..ማርያም የእረኞቹ ደስታ ………ማርያም የመላእክት ዝማሬ ……ማርያም                መዝሙር|       ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥            ፍሬ-መዝሙር
Hammasini ko'rsatish...
✞ ጋሜል - ዘ ኦርቶዶክስ የመዝሙር ግጥሞች ✞

✟ የኦርቶዶክሳውያን የመንፈሳዊ ምስጋና ቤት ✟ ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ 💿 የተዋሕዶ የመዝሙር ግጥሞች 💿    ✍ / ትምህርቶችን ለማግኘት ✍ 👇👇👇

https://t.me/maedot_ze_orthodox

| ለማስታወቂያ ስራዎች ➢ @EOTC24bot

4👍 1
ወላዲተ አምላክ 👉እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "ወላዲተ አምላክ" ትባላለችን? ለምን? * "ወላዲተ አምላክ" የቃሉ ትርጉም * የቃሉ ነገረ መለኮታዊ ፋይዳ * የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት በመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት * የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት-በቀደምት አበው ትምህርት +++++++++~~~+++++++ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስ “ወላዲተ አምላክ” የሚለውን መቃወሙ በነገረ ክርስቶስና በነገረ ድኅነት ላይ የሚያስከትለው ነገር መሠረታዊ የሆነ ኑፋቄ መሆኑን በሚገባ አስረድቷል፡፡ እነዚህን ነገሮችም እንደሚከተለው በሚገባ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡- ከድንግል ማርያም የተወለደው አካላዊ ቃል የእኛን ባሕርይ ነሥቶ (ተዋሕዶ) ሥግው ቃል ካልሆነና ሰው ብቻ (ዕሩቅ ብእሲ) ከሆነ መዳናችን አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ የተቀበላቸው ሕማማትና መከራዎች የሥግው ቃል (ሥጋን የተዋሐደውና የእኛን ባሕርይ ባሕርዩ አድርጎ ሰው ሆኖ በሥጋ የተገለጠው አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል) ሕማማትና መከራዎች ሳይሆኑ የዕሩቅ ብእሲ (የስው ብቻ) ይሆናሉና፡፡ ፍጡር በሆነ በሰው ብቻ መዳን አይቻልምና ስለዚህ ድነናል ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ወላዲተ አምላክ የሚለውን ቃል መካድ የአምላክን ሰው የመሆን ምሥጢር (ምሥጢረ ሥጋዌን) እና የሰውን መዳን መካድ ነው፡፡ እንደዚሁም አካላዊ ቃል አዲሱን ሰው ዳግማዊ አዳምን ለመፍጠር አካላዊ ቃል ከእኛ ባሕርይ ጋር ሊያደርግ የሚያስፈልገው ተዋሕዶ፡ ንስጥሮስ እንዳለው ዓይነት አፍኣዊና የጉርብትና ዓይነት ዝምድና ሳይሆን፣ ውሳጣዊና ባሕርያዊ የሆነ ጥብቅ እና አማናዊ የሆነ ተዋሕዶ ያስፈልገው ነበር፡፡ ይህ አይደለም ከተባለ የባሕርያችን መታደስ፡ በሐዲስ ተፈጥሮ የመዳናችን ነገር ሁሉ ከንቱ ይሆናል፡፡ #መድሎተ_ጽድቅ ሀይለ ገብርኤል
Hammasini ko'rsatish...
2👍 1
🌷👉 ጸጥ ማለት የነፍስን ሰላም ከሚያውኩ ነገሮች መራቅ ነው። ይለናል     ቅዱስ/ ዮሐንስ/ ዘሰዋሰው 🌷👉 ቅዱስ/ ዮሐንስ/ አፈወርቅ / በቅዳሴው ስለ ጌታችን ህመም እንዲህ አለ - "አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነገሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነገሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት።" ብሎ ስለ ጌታ ሕማም እንዲህ ነግሮናል! 🌷👉 አባ/ ገብርኤል/ ያዕቆን ስለ እመቤታችን እንዲህ አለ፦ "እመቤታችን ለኛ ያላት ፍጹም ፍላጎት በቃላቶቻችን ብቻ እንድናከብራት ሳይሆን ልጇን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንመስል ነው።" ብሎ እንዲህ ይነግረናል! 🌷👉 ቅዱስ/ አውግስጢኖስ እንዲህ ይላል፦ "ከፍ ማለት ትፈልጋለህ? በመውረድ ጀምር።ዐደመናን የሚሻገር ግንብ ለመገንባት አቅደሃል? አስቀድመህ የትሕትናን መሠረት ጣል።" ይላል!
Hammasini ko'rsatish...
👍 4 1
👋 ሰላም እንደምን አመሻችሁ ውድ የፍሬ ሃይማኖት ቤተሰብ እንኳን ለሊቀ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወርሀዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏 ነገ እግዚአብሔር ቢፈቅድና ቢረዳን ብንኖር ስማችሁ ከዚህ በታች የተጠቀስን አባላት የልማት ክፍል አገልጋይ አባላት ነን ጠዋት 12:00 በጊዜ እንገኝ🙏ሰላም እደሩ 1.ዲ/ን አይናማው ሽመልስ 2.ዲ/ን ናትናኤል መርሻ 3.ፍፁም ጌታቸው 4.እስክንድር ገ/ሚካኤል 5.ኤደን ተስፋዬ 6.እድላዊት ሁሴን 7.ኤደን አብደላ 8.ቃልኪዳን ሙሉጌታ 9.ምህረት ጥላሁን
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.