cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

#አል ሒከም / AL HIKEM

በአላህ ተማመን - በሰው አትመካ ሰው ሌጣ ፈረስ ነው - ይጥልሀል ጫካ !

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
166
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

" ኩሉ ኡመቲ የድኹሉነል ጀናህ ኢላ መን አባ : ወመን ያአባ ያረሱለላህ ? መን ዓጣአኒ ደኸለል ጀናህ : ወመን ዓሳኒ ፈቀድ አባ " ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ሁሉም የኔ ኡመት - ሀቁ ነው ጀነቱ እምቢ ያለው ሲቀር - ተነግሮት መስፈርቱ ማነው እምቢተኛው - ጀነትን ሊገባ አሻፈረኝ የሚል - ቢጠይቅ ሰሀባ እኔን የታዘዘኝ - ቃል ህጌን የሞላ ጀነት ሀላሉ ናት - ይቸራል ከመውላ መንገዴን የተወዉ - ያልጣመው ስሌቱ ወደ ኋላ ያለ - የረታው ስሜቱ ኒዕማም ወደ ኋላ - ከሱ መጎተቱ ብሎም ሀራሙ ናት - ቀረበት ጀነቱ !! @Al_HikemIslamicpoims
Hammasini ko'rsatish...
ባል ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብለው ያወጋሉ፤ በባል ፊት ላይ የሚታየው የፈገግታ ውበት የጨረቃ ብርሀን ምንጭ ይመስላል። ሚስት በስስት እየተመለከተች፦"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ዱዓ አድርጉልኝ እስቲ!" ትላለች። ባልም እጃቸውን ከፍ አድርገው፦" ያ አላህ! የዓኢሻን ያለፈውንም፣ የሚመጣውንም፣ የደበቀችውንም፣ ይፋ ያደረገችውንም ወንጀሏን ይቅር በላት" አሉ። ዱኣው ማይስተው ባል ዱዓ ሲያደርግ ሚስት ደስታዋን መቋቋም አቅቷት ከስሜቷ ፈንቅሎ የወጣው ሳቅ ጭንቅላቷን በባለቤቷ ታፋዎች ላይ ደፍታ እንድትስቅ አስገደዳት። ማመን አልቻለችም... ባል ሚስቱን እየተመለከተ፦"ዱኣዬ ደስ ብሎሽ ነው?" ሲል ጠየቀ። ሚስት ባሏን በቅርበት እየተመለከተች፦"እንዴት አያስደስተኝም አንቱ የአላህ መልዕክተኛ!!!" አለች። ባል ሩቅ በትዝታ ተጓዙ፣ ወዳልደረሱበት መጪ ትውልድ በምናብ ዋለሉ፣ ወዳላይዋቸው ትውልዶች በናፍቆት ነጎዱ...፦"ወላሂ ይህን ዱዓ በያንደንዱ ሰላቴ ለኡመቴ አደርገዋለሁ'ኮ" አሉ። ------------------------ የሚመጥንዎት ሰላዋት በርሶ ላይ ይውረድ (ሰ.ዓ.ወ) @Al_HikemIslamicpoims
Hammasini ko'rsatish...
ሹክር :- የፍጥረተ ዓለሙ - ረቢ አንዱ ጌታ ይድረስህ ገለታ - ለቀኑም ለማታ አልሀምዱሊላሂ - በቀን በማታ አላ ኩሊ ሀሊን - ስለ ሁሉም ኒዕማ ሸካሪ መሆኑ - ግድ ነው ለኔማ ሁሉንም አሟልቶ - ከቸረኝ ቡሀላ ከምስጋና ሚልቅ - ምን አለኝ ለመውላ ይበልጥ የሚያጅበኝ - ከዓለመ ረቡ ለአመስጋኝ ጭማሪ - የሚለው ጥበቡ የምስጋና ከላም - ለምላሱ የገራ እልፍ አዕላፍ ያተርፋል - ለዱንያም አኺራ ያልቀናው አንደበት - አማራሪ ደርሶ ማስተንተን ማይሻ - ከኒዕማው ተላብሶ እሳት ይማግዳል - ከከፍታው ወርዶ እያደር ዝቅታ - ጉዞው ሁሉ መርዶ አዛቢ ለሸዲድ - ቅጣቴም በረታ የካድከኝ እንደሆን - ብሎ ካለህ ጌታ አመስግን ክብሩ ነው - ለዋለልህ ፀጋ ላልዋለልህ ጭምር - ሚስጥሩ እሱጋ እናም አስምርበት - ከስጦታው ድልቡ ለአመስጋኝ ጭማሪ - የሚለው ጥበቡ '' አልሀምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን '' @Al_HikemIslamicpoims
Hammasini ko'rsatish...
قَالَ تَعَالَى: {إِنَّمَا المُؤْمِنُونَ إخْوَةٌ} [الحجرات: 10].
Hammasini ko'rsatish...
«181» فالأول: عن أَبي رُقَيَّةَ تَمِيم بن أوس الداريِّ رضي الله عنه: أنَّ النَّبيّ صلى الله عليه وسلم، قَالَ: ((الدِّينُ النَّصِيحةُ)) قلنا: لِمَنْ؟ قَالَ: ((لِلهِ وَلِكِتَابِهِ وَلِرَسُولِهِ وَلأئِمَّةِ المُسْلِمِينَ وَعَامَّتِهِمْ)). رواه مسلم.
Hammasini ko'rsatish...
"ዋዕተሲሙ...." ወንድም እህቶቼ  -  ከናንተ ባላውቅም በአደባባይ ላይ  -  እኛን ለሚያየንም አንዱን ዓሊም ከላይ -  ከፊሉን ከትቢያ ሌላኛውን ኢማም  -  ሲያጣው በነብስያ ምርጫም ግራ ገባኝ  -  የቱ ነው መንገዴ እኔንስ ማን ይምራኝ  -  የት ይግባ ዘመዴ የቀራው በየ ጎጥ  -  ሲቧደን እያየው በመሀል ቤት ሁኜ  -  እኔስ ተሰቃየው ቀርቼ ከነሱ  -  ከሆነ መድረሴ ሳያውቁ መኖሩን  -  ትመርጣለች ነብሴ ቁርዓኑ የአላህ ቃል  -  ምዕመናን ሊመራ ሀዲሱም ከረሱል  -  ከአምቢዮቹ አውራ አራቱም ኸሊፋ  -  በዚህ ከተመራ ሰሀባው ታቢዒይ  -  አስሀበሰለፉ ያአላህን ጌትነት  -  የረሱሉን መንገድ ----------  አድምቀው ካፃፉ ታድያ የኛ ደርሶ  -  ኡስታዜን ካልያዝከው አንተ ጥመት ላይ ነህ  -  ብለን የምንፈርደው እኛ መቼ ፀድቀን  -  ማን ነፃ ብሎን ነው ያንተም የኔም ቁርዓን  -  ምናውቀው ሀዲሱ ባንተም በኔም ኪታብ  -  አንድ ነው ርዕሱ ዋዕተሲሙ ብሎ  -  ከዚያም ቢሀብሊላህ ወላ ተፈረቁ  -  ሁሉም ዒባደላህ በአንቀፁ ማብቂያ  -  ሲናገር ጀሊሉ ወንድማማች ሁኑ  -  አዞናል በቃሉ የዱንያ አኺራ -  ወንድም እህቶቼ እናንተም አትጡኝ  -  እኔንም አይክፋኝ ------------  እናንተን አጥቼ በማህበራዊ ገፅ  -  ፌስቡክ ላይ በገሀድ ምንፈጥረው ሽኩቻ  -  ዲኑን ስለሚንድ ብንችል አንድነትን  -  እንስበክ በጋራ ይህ ነው ፅዱ መንገድ  -  ትውልድ የሚያፈራ ዲን መመካከር ነው  -  ተብሏል በነቢ ታድያ የኛ ችግር   -   ከጎረቤት ግቢ የኛ አለመግባባት  -  ሌላው አከባቢ ለምን ርዕስ ይሁን   -  ለምን አፍ እንግባ በትንሽ ትልቁ   -   አንፍጠር ወከባ ዞረን ልንሰግድ   -   ወደ አንድ ካዕባ የቤታችን ችግር  -  ገብተን ወደ ጓዳ ለሁሉም ወለምታ   -  መፍትሄ እናሰንዳ አቃቂር ማውጣቱ  -  በሌላው ዓቂዳ የኛ ስራ አይደለም  -  ይሄን እንረዳ እንጂማ ከደጁ  -  ወተን ወደ ሜዳ ያልተግባባንበት  -  ፈንጂ ሲፈነዳ ብዙ አካል ይጠፋል  -  ከሊቁም ደቂቁ ቢያንስ ይሄን እናስብ  -  ወገኖቼ ንቁ !                   ወላሁ አዕለም ! #share_your_frends @Al_HikemIslamicpoims
Hammasini ko'rsatish...
ሙፍቲን መሳደብም ሆነ አይነኬ ማድረግ ስህተት ነው! ————————— . ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ትልቅ ዓሊም ናቸው። የዕድሜ ባለጸጋ ናቸው። ብዙ መልካም ውለታም አላቸው። እሳቸውን መስደብም ሆነ መዝለፍ በፍጹም ተገቢ አይደለም። የሚሳደብ እና የሚዛለፍ ከድርጊቱ ሊቆጠብ ይገባል። . ነገር ግን ያሉበት ቦታ መጅሊስ ነው። መጅሊስ የመላውን ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ዕጣ ፈንታ የሚመለከት ተቋም ነው። አገራዊ አንድምታዎችም አሉት። በመሆኑም በዚህ ተቋም ውስጥም ሆነ በሌላ ሕዝባዊ ሚናዎቻቸው እሳቸውን አግባብ እና ክብር በጠበቀ መልኩ መተቸት፣ መሐየስ፣ የአካሄድ ስህተቶቻቸውን መጠቆምም ሆነ በጉዳዩ ላይ ሕዝባዊ ግንዛቤ መፍጠር ተገቢም ነው። ግዴታም ነው። . ዑለማን ማክበር ተገቢ እንደሆነ ሁሉ በሕዝባዊ ጉዳዮች ዙሪያ ችግሮችን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠርም ማኅበረሰባዊ ኃላፊነት ነው። እሳቸውን መዝለፍም ሆነ አይነኬ ማድረግ ሁለቱም ስህተት ነው። ሁለቱም ጽንፍ ነው። . ሙፍቲን «በመተቸት ስም» ድንበር የሚያልፍ እና ጋጠወጥ ስድቦችን የሚሳደብ እንዳለ ሁሉ «ሊሰደቡ አይገባም» በሚል እንዳይተቹ የሚከላከል እና ተቺን ለማሸማቀቅ የሚሞክርም አለ። ይህንን በደንብ አስተውያለሁ። ግን ሁለቱም አይጠቅሙንም። ግለሰቦችን አይነኬ ማድረግ እኛው ላይ መልሶ የሚያርፍ ፈተና መፍጠር ነው። ተገቢው መንገድ ከዘለፋ እና ስድብ በመቆጠብ ስህተቶችን መጠቆም ነው። አንብቤ ስላመንኩበት አካፈልኳችሁ አላሁ አዕለም !
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.