cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Meant to Be

fiction,poem & other

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
144
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Meek1one .mp34.31 MB
ይርዳው ጤናው(1).mp35.28 MB
ሳምኤል #ክፍል5 ረጅም ጥቁር ፀጉሯ ስትራመድ ከወዲያ ከወዲህ እያለ ወገቧን ያጅባል። የፊቷ ጥራት ቀልብ ይስባል። ቀይ ወፍራም ከንፈሯ ተመልካች ያሳስታል። ኮራ ባለ አራማመድ አፉን ከፍቶ ሚያያትን ሁሉ እያለፈች ወደ መሰብሰቢያው ክፍል ገባች። የበጎ አድራጎት ክበብ መቋቋሙን የሰማችው ኤልዳና ስብሰባ መኖሩ ሲወራ ጊዜ ሳታጠፋ ነበር የመጣችው። ተመዝግባ ብዙ መስራት ትፈልጋለች። ምናልባትም የሷን እርዳታ የሚሹ እልፍ አእላፍ ነፍሶች ናቸው። እጇን ለመዘርጋት ደግሞ ዝግጁ ነች። የክበቡ ተጠሪ የሆነው ልጅ እግር የኬሚስትሪ መምህር አዳነ አጀንዳውን ይዞ ከተማሪዎቹ ፊት ተሰየመ። ሰላምታ ከሰጠ በኋላ ስለ ክበቡ አስፈላጊነት እንዲህ በማለት የመግቢያ ንግግር አደረገ። " ልጆች በዚህ ክበብ ውስጥ ለማገልገል ሰው ሁኖ መወለድ ብቻ በቂ ነው። የግዴታ የገንዘብ መዋጮ ተሰብስቦ መዝናኛ ጉብኝት ምናምን መሄድ አያስፈልግም። እኛ ምንዝናናው የረዳናቸው ህፃናት፣ ወጣቶችና አረጋውያን ደስተኛ ሲሆኑ ነው። እናንተ ምትበሉት፣ ምትጠጡት፣ ምትማሩበት፣ ምትኖሩበት አላጣችሁም። ይሄን ሁሉ ያጡ ህፃናት ግን አይደለም አለም ላይ እኛ ሀገር ብቻ ራሱ መዓት ናቸው። ለምን እንደዚህ ሆኑ? ሌላ ጥያቄ ነው። ሰው በምክንያት ማንንም ሊረዳ አይገባም። መርዳት ስላለበትና ሰው ስለሆነ እንጂ። ስለዚህ ተሰባስበን በገንዘብም በእውቀትም በአይነትም ምናግዛቸው ምንደግፋቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ብዙ ስራ አለብን።" በመቀጠል የክበቡን ሰብሳቢ፣ ፀሀፊና ገንዘብ ያዥ ከመጣው ወደ 30 ሚጠጋ ተማሪ መሀል ለመምረጥ እጩዎች መመልመል ተጀመረ። ለሰብሳቢነት በባስኬት ቦል ሚታወቀው የአስራ ሁለተኛ ክፍል ቁንጮው ናታን በከፍተኛ የድምፅ ብልጫ ተመረጠ። የግቢው ቆንጆ ምትባለው አስረኛ ክፍሏ ማርታ የፀሀፊነት ቦታውን ያዘች። የአስራ አንደኛ ክፍል የባቹ ሰቃይ ሚባልለት ግሩም ደግሞ የገንዘብ ያዥነት ስልጣኑን ተረከበ። አዲስ ገቢ አይመረጥም ተብሎ የተከለከለ ይመስል ከሲኒየሮቹ ከእያንዳንዱ ክፍል አንዳንድ ከተመረጠ በኋላ ወርሀዊ መዋጮ በየወሩ አምስት አምስት ብር እንዲሆን ተወስኖ ስብሰባው ተበተነ። ስብሰባው የእረፍት ሰዓቱን እንዳቃጠለው ከተማሪው ክላስ መግባት የተረዳችው ኤልዳና ፈጠን ፈጠን እያለች በመራመድ ላይ ናት። ከኋላዋ የነካት ሰው ያለ ስለመሰላት ዞር አለች። "ሀይ" በግራ እጁ ፀጉሩን ቆፈር ቆፈር እያደረገ ቀኙን ለሰላምታ ዘረጋላት። ቸኩላ ስለ ነበር በአፏ ብቻ "ሰላም ነው" ብላው እንደ መሮጥ አለች። የባስኬቱ ኮኮብ እየተከተለ "ናታን እባላለሁ" አላት። "ኤልዳና" "እሺ ኤል ስኖጣ በር ላይ እጠብቅሻለሁ" ፈገግ አለ። "ኧ.."ገልምጣው እየሮጠች ሄደች። "ማርያምን" እየጮኸ እሱም ወደ ክፍሉ ተገነጠለ። ********************************* ሳሙናና ውሀ ቸግሮት እንኳን እንደ ብርቱካን ቀይ የነበረው ፊቷ ከቆዳዋ በቀሉ ቀያይና ጥቋቁር ጠባሳዎች ተሸፍኗል። መስመር መስመር ሰርቶ ደርቋል። ከአይኗና ከከንፈሯ በስተቀር አፍንጫዋ ሳይቀር በልዞ ለአይን ይከብዳል። በመስታወቱ ውስጥ መልኳን እንደዚህ ተበላሽቶ ያየችው ሊያ ነጩን ፋሻ ተመኘች። እናቷና ጓደኞቿ አይናቸውን ጨፈኑ። ነርሶቹም በፍርሀት አይን አይኗን ያያሉ። ሊያ እንባዋን ዋጥ አድርጋ ምንም ሳትናገር መስታወቱን አስቀምጣ ለመሄድ ተነሳች። ባለ ኮፍያውን ትልቁን ጃኬቷን ደርባ ጫማዋን መልበስ ስትጀመር አሜን ሄዳ እግሯ ስር ወደቀች። ተንበርክካ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ትለምናት ጀመር። "ሊያዬ እባክሽ እንደዚህ ሆነሽ አትሂጂ ገና አልዳንሽም እኮ እኔ ጋር ቆይና ሲሻልሽ የፈለግሽበት ትሄጃለሽ። የኔ ቆንጆ እባክሽን ጥለሽኝ አትሂጂ?! ቆይ ለኔስ ሌላ ማን አለኝ?! ካላንቺ ማን አለኝ ሊያዬ?! አንድ ልጄ እኮ ነሽ! እባክሽን አትጨክኝብኝ..." ደንዳናው ሳምሶን ሳይቀር አንጀቱ ተላወሰበት። "ተነሺልኝ" ከሊያ አፍ የወጣው ቃል ግን ይሄ ብቻ ነበር። "ተነሺ" ደገመችው። "ሊያ ባክሽን ተይ እሷስ አታሳዝንሽም?" ቤዛና ሀሴት እየተቀባበሉ ሊያስቆሟት ሞከሩ። እነ ዶልም አገዟቸው። ሳምሶን ብቻ ነበር ምንም ያላለው። ብቻ ቆሞ ይመለከታቸዋል። እነዛን በድሀ አቅማቸው ደፋ ቀና ብለው ያሳዳጉትን እናትና አባቱን አስታውሶ እንባው ቅርር አለ። በደከመ ጉልበት አርሶ ያበላቸው የነበረው አባቱ፣ ባንድ እጇ እሱን ተሸክማ በሌላው ቂጣ ጋግራ ታበላው የነበረችውን እናቱ፣ ፊቱ ላይ ድቅን አሉበት። ያ የልጅነት ጉልበታቸው በርክቶ አብሯቸው ትንሽ መቆየት ቢችል ደስ ይለው ነበር። ከአይናቸው አርቆ እንዲህ ያሉበትን እስከማያውቅ አጥፍቶ ሊያስቀረው ፈጣሪ እያክለፈለፈ አመጣው። እዚሁ ቀረ። የቤተሰብ ፍቅር፣ ልጅ መሆን አበቃ። ካደገበት ቀዬ እንባውን እየዘራ እንደመጣ አሁንም በልቡ እንዳነባ አለ። "ኧረ ሳም አንድ ነገር በላት" የበረከት ሽክሹክታ ከገባበት ሀሳብ አባነነው። ወደ አልጋው ሄደና አሜንን ደግፎ ከልጇ እግር ስር አነሳትና ሊያን እጇን ያዛት። ቀጥ ብላ አየችው። "አስተዋይ ሁኚ። እኛን ተመልከቺን እስኪ? እነ ቤዛን እያቸው? ሚሄዱበት፣ ሚጠጉት ዘመድ አላቸው? እኔስ አለኝ? ከዚህ ከጨቀየና ምስቅልቅሉ ከወጣ ህይወት ሚያወጣን አለ? ከስቃያችን አድኖ ሚያስጠጋን አለ? ከሱስ አላቆ ሚቀበለን ፣ ሚረዳን አለ? አንቺ ግን አለሽ ሊያ። ለዛውም የአለም ምርጥ አጋር፣ የምድር ምርጥ ዘብ እናት አለችሽ። አንዳንዴ አንቺ ያለሽን ሌሎች ግን የሌላቸውን ነገሮች ተመልከች። በዛ ላይ ገና ልጅ ነሽ። ገና ብዙ ነገር ይጠብቅሻል። መጠንከር አለብሽ። በይ አሁን ትንሽ አረፍ በይና ተረጋግተሽ ከናትሽ ጋር ወደ ቤት ትሄዳላችሁ። ትምህርትሽን ትቀጥያለሽ። ለናትሽስ ማን አላት? በይ ተቀመጪ።" ግንባሯን ሳም አደረጋት። ....................ይቀጥላል.................. ✍ረቂቅ @yan_semon
Hammasini ko'rsatish...
ሳምኤል #ክፍል4 መንገድ ዳር የሚገኝ የቆርቆሮ አጥር ግቢ ውስጥ ያለች ትንሽዬ አንድ ክፍል ቤት ለታመመችው ጓደኛቸው መጠየቂያ ሰርቶ ለመውሰድ ሀሴትና ቤዛ ባለቻቸው ጉድ ጉድ ይላሉ። ዶልና በረከት ቤቷን በሲጋራ ጭስ አፍነዋታል። ሳምሶን ብቻውን በሩ ጋር ተቀምጦ ሰሞኑን የሰረቃቸውን ስልኮች ለመሸጥ እየፈታታ ይመረምራል። ሁሉም ከራሱ ጋር ያወራል። ጠብታ ዘይት በቤቱ አለመኖሩን ያየችው ቤዛ ሀሴትን ባዘነ አስተያየት አይን አይኗን ታያታለች። እሷም ብትፈልግ አጣች። "እ ....ሴቶች ቆማችሁሳ ....ምነው አስራሩ ጠፋችሁ እንዴ? ሀሀ" ዶል ሁሉንም ፈገግ ሊያስብል አስቦ መቀለዱ ነው። ቀልዱ ያበሳጫት ቤዛ ግን ሄዳ ፊቱ አፈጠጠችበት። "ብር ስጠኝ እስኪ ዘይት መግዣ¡ እ ? የኔ አንበሳ? በቤቱ እኮ ምንም የለም! ባዶ ነው! ባዶ! ከሲጋራ ጭስ እና ከጫት ቅጠል ከቢራ ጠርሙስ ሌላ ምን አለ?!እ...ሰርቆ ለ ሱስ... አንድ ሚላስ ሚቀመስ ነገር የለም እኮ! እስኪ ንገረኝ ከበላህ ስንት ጊዜ ሆነህ? እ...ተናገራ ምን ይዘጋሀል!! ይስቃል እንዴ ደሞ ጥርሳም" አምባረቀችበት። "እና ምን ይሁን እ ምን ይሁን ታዲያ? እኔ አይደለሁም እኮ ወደዚህ ህይወት ገትቼ ያስገባሁሽ!ምንድን ነው ያዙኝ ልቀቁኝ ምትይው?! አፍሽን ዝጊ !" ከተቀመጠበት ተነሳ። "ልትማታ ነው?! ምታኛ! በላ ምታኝ! በል እንጂ" መጯጯህ ጀመሩ። "አቦ ምንድን ነው!" ደምፃቸው ረብሾት ሳምሶን ወደ ውስጥ ገብቶ አፈጠጠባቸው። ሁሉም ስለሚፈሩት ዝም አሉ። "ምን ይዘጋችኋል!" አምባረቀባቸው። "አይደለም እኮ ሳም..." "አትቅለስለሺ ተናገሪ ምንድን ነው?!" አቋረጣት። "ዘ...ዘይት ፈልገን እኮ..." ሀሴት ጣልቃ ገባች። "እና እኔ ዘይት ልሁን! እናንተ የትም ጥላችሁት የመጣችሁት ሴትነት አማራችሁና እኛ መበጥበጥ አለብን?! " "እንደሱ አይደለም እኮ ሳም..." "በቃ በቃ ሁልሽም ወደ እዚህ ስትመጪ ምንም እንደሌለ እያወቃሽ ነው። ዘይት ወጥ ምናምን እያልሽ አትቃዢ!" አፋ አፋቸውን ብሏቸው ወጣ። ቤዛ እንባዋ ፈንቅሏት ማልቀስ ጀመረች። "ቤዝ ደግሞ እሱን እያወቅሽው?" የቀሩት ከበው ያባብሏት ጀመር። ሳምሶን ሁሌም በንግግሩ እንዳስከፋቸው ነው። መናገር የፈለገውን ሁሉ ይናገራል። ስሜቱን በቃላት ከመግለፅ በስተቀር ለሰው ስሜት አይጨነቅም። ራሱን ብቻ ሚሰማ እሱ ብቻ ትክክል እንደሆነ ሚያስብ ግልፍተኛ ልጅ ነው። አብረውት ካሉት ሌሎቹ ተለቅ ያለ መሆኑም ለዚህ ባህሪው ሳያግዘው አልቀረም። ት/ቱን ቢቀጥል እስካሁን ካምፓስ ይገባ ነበር። ያቋረጠው ከ9ነኛ ክፍል ነው። እኛ አቅቶናል ከተማ ግባና ራስህን አድን ብለው መርቀው እናትና አባቱ ከክፍለ ሀገር ከሸኙት ብዙ አመት ሆኖታል። የስራ ማጣት ፣ የተገኘውም አለመሙላት፣ የሚያገኛቸው ሰዎችም ባህሪ ብቻ ሚያስከፉትና ተስፋ ሚያስቆርጡት ብዙ ነገሮች ተደማምረው ዱርዬ የዱርዬ ሰብሳቢ ሱሰኛ ሌባ አደረጉት። ግልፍተኛነቱ አብሮት የተፈጠረ ቢሆንም አሁን ያለበት ህይወት ግን የባሰ ጨካኝ አድርጎታል። ይሄን ሁሉ ጊዜ እናትና አባቱን ጠይቆ አያውቅም። ይኖሩ ይሙቱ ግድ ሚሰጠው አይመስልም። ይሰርቃል። ቅጥ ከጠፋው ኑሮው ራሱን በሱስ ይደብቃል። ተይዞ ታስሮ አያውቅም። ቢነቀባት እንኳን ራሱን እንዴት ማዳን እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። ተፈጥሮ ብልጠትን አድላዋለች። ባጭሩ ሳምሶን ለሰው አስቸጋሪ የሆነ ባህሪ ያለው ውስብስብ ሰው ነው። ከራሱ ከሳምሶን በስተቀር ሳምሶንን የሚረዳ ሌላ ማንም የለም። "እንኪ ያውልሽ በዚህ ስሪ!" አንድ ሊትር ገዝቶ ወረወረላቸው። አንደበቱ ያስቀይማል እንጂ ልቡ ንፅህ ነው። ሴት ልጅ ተከፍታ ማየት ስለማይችል ወዲያው አንዱን ስልክ ሽጦ ገዝቶ አመጣላቸው። እንስቶቹ ፊታቸው በደስታ እያበራ ተቀበሉት። ቶሎ ሚከፋት ቤዛ ዘላ ተነስታ ተጠመጠመችበት። "በይ በይ እሺ ሂጂ ስሪ" በደስታቸው መደሰቱን ላለማሳየት እየታገለ ከቅፏ አምልጦ ወንዶቹ ጋር ቁጭ አለ። " እስኪ ሙያ ልናይ ነው"በረከት እጁን እያሟሟቀ መጓጓቱን አሳየ። ትንሽዬ ቤታቸውን የሞላው እቃ ሁሉ የተሰረቀ ነውና ከዚህ በፊት ተዘርግቶ ከሚሸጡ የፕላስቲክ የቤት እቃዎች ከሰረቋቸው ሰሀኖች መሀል ተለቅ ባለው ለሊያ አጠቀሱ። የተረፈውን አብረው እየተጎራርሱ በሉ። ጓደኝነታችው ፈረሰ ሲሉት መልሶ ሚገነባ እንደነሱ እየወደቀ ሚነሳ አይነት ነው። ጠንካራ ትስስር አላቸው። በችግር ጊዜ ሚደጋገፉ አሳልፈው ማይሰጣጡ ህይወት ያዛመደቻቸው ወንድምና እህቶች ናቸው። ************************ ሊያ ከተኛችበት መነሳት መንቀሳቀስ ጀመራለች። ምግብም ትወስዳለች። ፊቷ ላይ ያለው ፋሻም ሊነሳላት ነው። አሜንም ስራ ስቴድ ካልሆነ ተለይታት አታውቅም። በመጠኑም ቢሆን እናቷን ማውራት ጀምራለች። ሆዷን እስኪያማት ስለሚያስቃት ዶል ፣ ስለነቤዛ ታጫውታታለች። ማታ ማታም እዛው ሆስፒታሉ ግቢ እሷም እንድትንቀሳቀስ ንፋስ እየተቀበሉ ይራመዳሉ። ዛሬ ፋሻው ይነሳላታል። እሷ ግን ብዙም የጓጓች አትመስልም። ቶሎ ከዚህ መሄድ ትፈልጋለች። አንድ አይነት ቦታ፣ ተመሳሳይ ሰው፣ አንድ አይነት አየር ሰልችቷታል። አሜን ግን ፊቷ እንደ ተበላሸ ቀርቶ ልጇ እንድታዝንባት በጣም ፈርታለች። እነ ሳምሶንም ተሰባስበው መተዋል። ዶክተሩ ብቻ ነው የሚጠበቀው። ...................ይቀጥላል.................. ✍ረቂቅ @yan_semon
Hammasini ko'rsatish...
እዮም መኮነን - የእውነቷን 16k.m4a5.84 KB
እዮም መኮነን - የምድር ድርሻዬ 16k.m4a7.53 KB
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.