cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የብዕር እንባ

ደብዳቤዎች ወጎች አጫጭር ድርሰቶች እና የተለያዩ ፅሁፎች እንዲሁም ከዚህም ከዚያም የተቀነጨቡ ፅሁፎች እዚህ ያገኛሉ። መውደቅህን ሳይሆን እንደገና መነሳት መጣርህን አስብ 💪 ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት @kbig_13 ላይ ያድርሱኝ

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
224
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ሠው በሠውኛ ሠዋሠው ምንም ማሠሪያ አንቀፅ የለውም።
Hammasini ko'rsatish...
አንድ የሆነ ቦታ አንድ የሆነ ቦታ ቤተመቅደስ አይነት፡ የሚታመን ታቦት የሚቀመጥበት፡ አንድ የሆነ ቦታ ቤተመንግስት አይነት፡ የሚፈራ ዙፋን የሚጎለትበት አንድ የሆነ ቦታ የሰውን ልብ አይነት፡ የዘላለም ፍቅር የሚታተምበት አንድ የሆነ ቦታ የሆነ ቦታ አይነት የአደባባይ ሚስጥር የሚዋረድበት፡ አንድ የሆነ ቦታ--- አንቺ ለኔ እንዲያ ነሽ ከሆነው ሰውሬ ሆነ ላይ ያኖርኩሽ። Hagi Beyu
Hammasini ko'rsatish...
🔹ቃላት የማይገልጿቸው ስሜቶች አሉ፤ ከቃላት በላይ ግን ድርጊት ይገልፃቸዋል። ህልምህን፣ ፍቅርህን እና ማንነትህ ከቃላት በላይ ተግባር እንዲገልፃቸው ከጣርክ ትክክለኛው መስመር ላይ ነህ።
Hammasini ko'rsatish...
እንኳን ለጌታችን ለአምላችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ከዘጠኙ ዐበይት በዓል ለአንዱ ለሆነው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ለሙሴ ለኤልያስ ለሐዋርያት ለጴጥሮስ ለያዕቆብና ለዮሐንስ ብርሃነ መለኮቱ ለገለጠበት በዓል በሰላም አደረሰን። መልካም በዓል ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን🙏🙏🙏 ቡሄን በትዝታ ቀናቱ ተዳርሶ ቡሄ መጣ ሲባል ከልጅነት አለም ትዝታ ይነግሳል * * * ሆያ ሆዬ ስንል በ 'ሆ' ሲቀበሉን በጭፈራ መሀል ሁሉን አሞግሰን ሙልሙል ተከፋፍሎ ..ምርቃት ታድሎ በደስታ ሲሸኙን .....እኛም በምስጋና እንመለሳለን * * * ............በዳቦ መአዛ ሰፈሩ ታጥኖ ሆዬ በሚል ዜማ ቀኑ ተሽሞንሙኖ ........ ሳይ ውስጤ በትውስታ ኀላውን ይቃኛል ከወደኔ አለም ቡሄን በትዝታ ከኀላ ተገኝቶ ካለፈው ጨዋታ ........... ደስታን ይታደላል ዛሬን ከእናንተ ጋር ቡሄውን ልካፈል እኔም በተራዬ እንዲህ ሆዬ ልበል ሆያ ሆዬ .. .. .. .. .. .. .. ሆ ሆያ ሆዬ .. .. .. .. .. .. .. ሆ እዛ ማዶ .. .. .. .. .. .. .. ሆ ጅራፍ ይጮሀል እዚህ ማዶ .. .. .. .. .. .. ሆ ጅራፍ ይጮሀል ቀኑ በድምቀት አሸበራርቋል የጅራፉ ጩኸት ፍቅርን ሲያበስር የጥላቻው ዜማ ቅላጼው ሲከስር ፍቅር የዋለበት ደስታን ታድለናል ነገን ከዛሬ ጋር ለአንድነት ታጭተናል መልካም ቡሄ 🙏
Hammasini ko'rsatish...
"የራስህን ህይወት ስታስተካክል የሌሎችን እያበላሸህ መሆን የለበትም! የራስህን መንገድ ምትጠርገው የሌሎችን እየቆፈርክ መሆን የለበትም! የራስህን እንጀራ ለማብሰል የሌሎችን ሊጥ አትድፋ! በራስህ መንገድ ጣልቃ እንዲገቡ እንደማትፈቅደው ሁሉ የሊሎችንም መንገድ አትዝጋ!" 💞 መልካም ቀን ❤️
Hammasini ko'rsatish...
ዝም ብለህ ወደ ራስህ በልክ አምጣቸው ።።።።። 1. ይሰለቹሃል አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ! 2. 'ሼም ነው' ነው የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ! 3. አይባልም "... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም። 4. ክፈል አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ። 5. ነውር ነው ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ። 6. አታቋርጥ ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው። 7. አታብሽቅ ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ። 8. አመሥግን ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን። 9. ያለስስት አድንቅ ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው። 10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ። 11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል። 12. ስነ ስርዓት ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው። 13. ክብር ለሁሉም ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም። 14. ስልክህን አስቀምጥ ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው። 15. አድብ ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው። 16. ተቆጠብ ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ። 17. መነጽርህን አውልቅ ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው! 18. አትሳሳት በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ። 19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው። 20. ዕቃ መልስ የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ። 21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ! ።።።።። በዶ/ር ምህረት ደበበ
Hammasini ko'rsatish...
እስኪ ይቺን ነገር ተጋበዙልኝ😏😜😂 እስኪ አንድ አማተርና አንድ ፕሮፌሽናል አራዳ ስለ አራዳነት ይጨዋወቱ፡፡ ፕሮፌሽናል፦ ሃይ ፒስ ነው ጀለሴ? አማተር፦ አባቴ እንዴት ነሽ የአራዳ ልጅ! አራዳ ትመስያለሽ ሲያዩሽ፤ ወዴት እየቆሰቆስሽው ነው? ፕሮፌሽናል፦ እዚህ አካባቢ የሆነ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አለ ብለውኝ ነበር፤ ይቅርታ ታሳየኛለህ? አማተር፦ ባክህ እኔ አላውቅልህም! ሙዴን ከለብከው፤ እኔ እኮ በርጫ ቤት የሚፈልግ አራዳ መስለኸኝ ነበር፡፡ ለፋራ ቦታ የለንም ወደዚያ ሂድ! ፕሮፌሽናል፦ ሃሃሃሃሃ! አባቱ ሰሞኑን ነው ከገጠር የመጣሽው? አማተር፦ ምን ማለት ነው? አንተ እኔ የጨስኩ የአራዳ ልጅ ነኝ፡፡ የሆንክ ባላገር ነገር ነህ እንዴ? ፕሮፌሽናል፦ ጀለሴ ከተመቸሽ እዚያች ካፌዋ ጋ ቁጭ ብለን እንጫወት? አማተር፦ እሺ እናቀጣጥነው ቀጥል፡፡ ፕሮፌሽናል፦ እዚህ ጋ ቁጭ በል እና እስኪ ስለ አንዳንድ ነገሮች እንጨዋወት ብየ ነው፡፡ አማተር፦ አባቴ የአራዳ ልጅ ይመችሽ! ፕሮፌሽናል፦ ሃሃሃሃ! ምነው ቅድም ባላገር ስትለኝ አልነበር እንዴ? አማተር፦ ምን መሰለሽ! አሁን ሰዓቱ የበርጫ ነው፡፡ አንቺ ቤተ መጻሕፍት ትጠይቂያለሽ፤ የአራዳ ልጅ እንዲህ አያደርግም፡፡ አሁን ግን ሙድሽ ተመችቶኛል፡፡ ፕሮፌሽናል፦ አሁን ቁጭ ብለን እንድንጫወት የፈለኩት ስለ አራዳነት እንድትነግረኝ ነው፡፡ አራዳ ማለት ምንድነው፣ ምን ዓይነት ሰው ነው? አማተር፦ ኧረ ጀለሴ እንዲህ እንዲህ ዓይነት «ኩዌሽን» አይጠየቅም፡፡ አንቺ የአራዳ ልጅ አይደለሽ እንዴ! ሙድ የገባው ሰው እኮ ያስታውቃል፡፡ ፕሮፌሽናል፦ እኔ አራዳ ልሁንም አልሁንም ለአንተ አራዳነት ምንድነው ነው ያልኩህ? አማተር፦ የአራዳ ልጅ ማለት ለምንም ነገር ጭንቅ የሌለው ነው፡፡ ውሎው ከባላገር ልጆች ጋር ሳይሆን ከከተማ ልጆች ጋር ብቻ ነው፡፡ የአራዳ ልጅ አነጋገሩ ሁሉ ያስታውቃል፡፡ የባላገር ቋንቋ አይጠቀምም፡፡ አራዳ የሚታወቀው በቋንቋው ነው፡፡ ፕሮፌሽናል፦ ይቅርታ ግን ስምህን አልነገር ከኝም፡፡ አማተር፦ ፍላዎር ፕሮፌሽናል፦ ማን ነበር የቀድሞው ስምህ? አማተር፦ አቦ ዛሬ ደግሞ ምን ዓይነቱን ጌጃ ነው ያጋጠመኝ፤ ሙዴን አትከይተዋ! ፕሮፌሽናል፦ ረጋ በዪ ጀለሴ ሲታወቅብሽማ እንዲህ አትንጨርጨሪ! ይልቅ ከየትኛው የገጠር አካባቢ እንደመጣህ ንገረኝ? አበባው የነበረውን ስምህን ነው አይደል እዚህ መጥተህ ፍላዎር ነኝ የምትል? አማተር፦ ኧረ አባቱ አይሞድም! ምነው ወርክ ኔፕ ነሽ እንዴ? እኔ እኮ ዱቅ እንበል ስትይ እንደውል ትያለሽ ብየ ነበር፡፡ ፕሮፌሽናል፡- አዳምጠኝ! አሁን የፈለኩህ በቁም ነገር ነው፡፡ አራዳ ማለት እንደዚህ አንተ እንደምትለው መደናቆር ማለት አይደለም፡፡ በስመ አራዳ የእኛን ስም ያስጠፋችሁት እናንተ ከገጠር የምትመጡት ናችሁ፡፡ ትሰማኛለህ? አሁን የምነግርህን የፋራነት ምልክቶች ጠንቅቀህ አዳምጠኝ፡፡ አሥር ጊዜ እየደጋገሙ አራዳ ነኝ ማለት፣ ሌሎችን ባላገር እያሉ መሳደብ፣ ራሳቸው የማያውቁትን ቃላት እየፈለጉ ግራ መጋባት፣ ፋራ የሚል ስድብ መደጋገም... እነዚህ የነገርኩህ ሁሉ የጥሬ መሃይም ምልክቶች እንጂ የአራዳነት ምልክቶች አይደሉም እሺ? አማተር፡- እሺ የትክክለኛ አራዳነት ምልክቶችን ንገረኝ ፕሮፌሽናል፦ ትክክለኛ አራዳ ማለት በትክክል ስሜቱን የሚያውቅ፣ ለሚያደርገው ነገር ራሱን ማስወሰን የሚችል፣ የገጠር ልጅ የከተማ ልጅ የሚለው ነገር የማያስጨንቀው፣ አራዳነቱን የሚለካው ንግግሩን በማወላገድና ግራ በማጋባት ሳይሆን ለሰዎች ግልጽ በመሆኑ፣ ተናግሮ ማሳመን በመቻሉ፣ በሰው ፊት ስለየትኛውም ጉዳይ ሲያወራ የማይሳቀቅና ሀሳብ የማያጣ ማለት ነው፡፡ ሰው የመሆን ምልክት ጫትና ሲጋራ ሳይሆን በማንበብ ሙሉ ሰው መሆኑን የሚያምን፡፡ በቃ በሰው ፊት ስለአገሩ አፉን ሞልቶ መናገር የሚችል ነው፡፡ አማተር፦ የገጠር ልጅ የከተማ ልጅ የሚለው ነገር የማያስጨንቀው አልከኝ፡፡ ቅድም ከገጠር ነው ወይ የመጣኸው አላልከኝም ነበር እንዴ? ፕሮፌሽናል፦ አዎ! ብዬሃለሁ፡፡ ለምን መሰለህ? ከገጠር እንደመጣህ እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው፡፡ ብዙ ከገጠር የሚመጡ ልጆች ናቸው ለእንዲህ ዓይነት ዝርክርክነት የሚጋለጡት፡፡ የገጠር ልጅ መሆናቸው ውርደት ይመስላቸዋል፡፡ የገጠሩ ባህል የሚያሳፍር ይመስላቸዋል፡፡ የከተማ ልጆችን ብትመስሉም እኮ ጥሩ ነበር፡፡ የምታሳዛኑት ግን ከገጠር እንደመጣችሁ ድርጊታችሁ ይናገራል፡፡ በእርግጥ ብዙ ሰዎች አራዳ ሆኖ ነው ሊሏችሁ ይችላሉ፡፡ ልብ ብሎ ነገሩን ላጤነው ሰው ግን ጀማሪ አራዳ ያስታውቃል፡፡ አራዳ መሆን ሳይሆን አራዳ መምሰል ነው የሚፈልገው፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች ‹‹የገጠር ልጅ መሰልኩህ እንዴ?›› በማለት የገጠር ልጅ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ልብ ብለሃቸው ከሆነ ትንሽ ትልቁን ያካብዳሉ፡፡ አንድ ሰው አለባበሱ ወይም የሆነ ነገሩ ቢበላሽበት፣ በንግግር ቢሳሳት በዚያ ሰው መሳቅና ሙድ መያዝ የግድ ይመስላቸዋል፡፡ አንዴ የያዙትን ነገር ሙጭጭ ብለው ይደጋግሙታል፡፡ እነርሱ የሚያውቁት አራዳ ማለት የከተማ ልጅ መምሰል እንጂ አስተዋይና ንቁ መሆኑን አይደለም፡፡ ለዚያ ነው ከገጠር ነው የመጣኸው ያልኩህ? አማተር፦ ይህ ያልከኝ ችግር የከተማ ልጆች ላይ አይታይም? ፕሮፌሽናል፦ የከተማ ልጅ ፋራ የለውም እያልኩህ አይደለም፡፡ እንዲያውም እነርሱ ጋ ደግሞ የከፋው ችግር ምን መሰለህ? መሃል አዲስ አበባ መወለድ ብቻውን አራዳ የሚያደርግ ይመስላቸዋል፡፡ ሁሉ ነገር ልክ ስለሚመስላቸው ለመስተካከል እንኳን አይሞክሩም፡፡ ስለዚህ አራዳነት ከተማ መወለድ ብቻ አይደለም፡፡ አማተር፦ የከተሞችንም የገጠሮችንም አጣጣልካቸው፤ ታዲያ ማነው አራዳ? ፕሮፌሽናል፦ ቀደም ሲል እንዳልኩህ ነዋ! አራዳ ማለት በቃ የነቃ፣ አስተዋይ የሆነ፣ በትንሽ በትልቁ የማያካብድ ነው፡፡ በአለባበስ፣ በአነጋገር፣ በየትኛውም ነገር ስህተት እንኳን ቢያስተውል የሚያስረዳ እንጂ አቃቂር የማያወጣ ነው። አንዳንዴ ያየውን ነገር እንኳን አይቶ እንዳላየ ነው የሚያልፈው፤ ምክንያቱም ያ ነገር በባለቤቱ ላይ ምን ዓይነት የስነ ልቦና ቀውስ እንደሚያመጣ ይገባዋል፡፡ ፋራ ግን ይህ አይገባውም፡፡ አማተር፦ በእውነት ዛሬ በጣም ትልቅ ነገር ነው ያስተማርከኝ፤ ይህን ሁሉ ልብ ብየው አላውቅም ነበር፡፡ ፕሮፌሽናል፦ ሃሃሃሃ! በነገራችን ላይ አንተ ገና ስንጀምር የነበረውና አሁን የነበረህ አነጋገር ራሱ በጣም የተለያየ ነው፡፡ የአሁኑን አነጋገርህን እኮ ማንም መረዳት ይችላል፡፡😂😂😂
Hammasini ko'rsatish...
ፍቅር እና ሳቅ™

ያፈቀረን ማሳቅ ለኛ ኖርማል ነው አያሳስብም😉 #Join ያርጉና የትም ባልተሰሙ ቀልዶቻችን ፈታ እያሉ በውብ የፍቅር ቃላቶች ይደመሙ😍 ዘፈን ግጥም ጠቃሚ ምክሮች... ከቻልክ❤ ፍቅርን ተናገር፣ አስተምር፣ ኑር! . . . ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን 👉0916157728 or @atSUPERIOR & @luestar . . . Please😊Don't Leave ችግር ካለ አናግሩን

ጊዜን እንጠቀመው አብዛኛዎቻችንን ጊዜ ይጠቀምብናል እንጅ ጊዜን እኛ ስንጠቀመው ብዙም አይስተዋልም፡፡ ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም እራሱን ያዘጋጀ ሰው ሁለም አሸናፍና ወዳሰበበት ለመድረስ አቅም ያለው ነው፡፡ ጊዜ ውስጥ ወጣትነት፣ እርጅና እና ሞት አለ፡፡ ወጣትነታችን ወደ እርጅና ሳያመራ መሆን የሚንፈልገውን አሁን እንወስን፡፡ መሆን የሚንፈልገው ጊዜ ውስጥ ስላለ ምንም ለመሆን ከፈለግን ምንም ለመሆን የሚያግተን ምንም ነገር የለም፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው መሆን የሚንፈልገውን ወስነን ጊዜን በአግባብ መጠቀምና መጠቀም ብቻ ነው፡፡ ጊዜ ከተጠቀሙት ቀን ነው፡፡ ካልተጠቀሙበት ምሽትና ምንም ለመስራት የማይመች ጨለማ ነው፡፡ ወስን መሆን የሚትፈልገው በእጅህ ነው፡፡ ቶሎ መስንና ጊዜ ሳያሸንፍህ ጊዜን አሸንፈህ አሸናፍ ሁን፡፡
Hammasini ko'rsatish...
"#ይህን_አስብ!" ☝️ከጭንቀትህ የተነሣ በምሽት ለመተኛት ትቸገራለህ ? 👉ራሳቸውን የሚያሳርፉበት ቀርቶ የሚያስጠጉበት እንኳን የሌላቸውን አስብ ፡፡ ☝️በሥራህ ደስ የማይል ቀን ያጋጥምሃል? ፤ 👉ላለፉት ዘመናት ዛሬንም ጨምሮ እንኳን ሥራ አጥቶ የተቀመጠውን ሰው አስብ ፡፡ ☝️ወዳጅነትህ ወደ ከፋ ጎዳና እያመራ ስለሆነ ተስፋ ቆርጠሃል? 👉ማፍቀርና በምላሹ ደግሞ መፈቀር ምን ዓይነት እንደሆነ ጭራሹኑ የማያውቁትን ሰዎች አስብ ፡፡ ☝️የምትወደውን አንድ ሰው በሞት ስላጣህ ቀኑ ጨልሞብሃል? ፤ 👉ሙሉ ቤተሰቡን አንድ ቀን የቀበረውን ብቸኝነት እንደ ሳማ ቅጠል የሚለበልበውን እርሱን አስብ ፡፡ ☝️በሕይወትህ ባጋጠሙህ ጭንቀቶችና በገጠምካቸው ፈተናዎች ትማረራለህ ፤ ሁሉም የሆነው ስለኖርክ ነው ፡፡ 👉በመቃብር ሥፍራ ካሉት አንዱ እንኳን እንደ አንተ ደስታና ሐዘንን ፣ ከፍታና ውድቀትን የማየትም ሆነ የማስተዋል አቅሙም አጋጣሚውም የለውምና ይህንኑም አስብ ፡፡ 🙏ስለዚህ በምትኖርበት ጊዜ ሁሉ ላለፈው ለሚመጣውና እየሆነ ላለ መጨነቅን አቁምና ፈጣሪን አመስግን መልካምና የተቀደሰ ቀን ይሁንላችሁ! 🙏🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
#ሽማግሌው ሲጠባበቁት የነበረው አውቶብስ ስለመጣላቸው ለመሳፈር ተጠግተዋል፡፡ እግራቸውን አንስተው  ወደ ውስጥ ሲገቡ በአጋጣሚ የአንድ እግር ጫማቸው ተንሸራቶ ውጭ ይቀራል፡፡  መልሰው ጫማቸውን ማግኘት ሳይችሉ አውቶብሱ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ሽማግሌው ምንም አይነት የብስጭት ቃላት ሳያሰሙ የቀሪ እግራቸውን ጫማ ያወልቁና በመስኮት በኩል አሾልከው ወደ ውጭ ይጥሉታል፡፡ የሽማግሌውን ድርጊት ውስጥ ሁኖ ይመለከት የነበረ ወጣት ተሳፋሪ ለሽማግሌው እንዲህ ሲል ጥያቄውን አቀረበላቸው፡፡ “አባት ሲያደርጉ የነበሩትን ነገር እያየሁ ነበር፡፡ ለምንድን ነው ቀሪውን ጫማ የወረወሩት?” አላቸው፡፡ ሽማግሌውም ወዲያውኑ እንዲህ ሲሉ መለሱለት “እየውልህ ልጄ ሾልኮ የቀረውን ጫማ ሊጠቀሙበት የሚችሉት ይሄኛውም አብሮ ሲኖር ነው፡፡ እናም ለማንኛውም ያገኘው አካል ጥቅም እነዲሰጠው ወይም ዋጋ እንዲኖረው ስል ነው ይሄኛውን ጨምሬ መወርወሬ” አሉት፡፡ ደራሲ እንዳለጌታ እንዳለው “የማትጠቀምበት ነገር ሁሉ ያንተ አይደለም!” #መልእክታችን፦ እኛስ የማንጠቀምባቸው ንብረቶች ይኖሩ ይሆን? በተለይ በዚህ የክረምት ብርድ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ብንለግሳቸው እኛ ከምናገኘው የህሊና እርካታ ባለፈ ፈጣሪን ማስደሰት ነው
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.