cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

ሰላም ውድ የግሩፖችን አባላት ይሄ ግሩፕ አላማው ንባብን የሚወድና የራሱን ማንነት ያልዘነጋ ትውልድን መፍጠር ነው #ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል #ማንበብ እይታን ያሳድጋል #ማንበብ ንግግርን ያስተካክላል ያሳምራልም ኑ አብረን እናንብ ትውልድ እንገንባ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
444
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-27 kunlar
-630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የሀብት_መንገድ_በሮበርት_ኪዮላኪ_@shuktus_books.pdf15.49 MB
“ሁሉም የእጁን ያገኛል” ✍ መሳፍንት ተፈራ ~~~ አንዲት እናት ሁልጊዜም ዳቦ ስትጋግር የዳቦው ቁጥር ለቤተሰቡ ሁሉ አዳርሶ አንድ ተጨማሪ እንዲተርፍ አድርጋ ነበር። እናም አንዱን ትርፍ ዳቦ በቤታቸው አቅራቢያ የሚያልፍ የተራበ ሰው እንዲወስደው በሚል በዳንቴል ጠቅልላ በር ላይ ታስቀምጠዋለች። አንድ ጀርባው የጎበጠ ሰውም ዘወትር እየሄደ ዳቦውን ወስዶ ይበላ ነበር። ለብዙ ወራት ያቺ ሴት ዳቦ ማስቀመጧን፣ ሰውዬም ወስዶ መብላቱን ቀጠሉ። የሚገርመው ነገር ያ ዳቦውን የሚወስደው ሰው አንድም ቀን ምስጋና አቅርቦላት ስለማያውቅ ሴትዬዋ ትበሳጭ ጀመር። ይባስ ብሎ ሰውዬው በማመስገን ፋንታ “ሁሉም ሰው የእጁን ያገኛል” ማለትን ያዘወትር ነበር። ይሄን ሲል ሴትዬዋ “ምናባቱ ለማለት ፈልጎ ነው?” እያለች መበሳጨቷ አልቀረም። “ይሄ ውለታ ቢስ፣ ማመስገን ሲገባው ጭራሽ ‹የእጇን ይስጣት› እያለ ያሟርትብኛል? ቆይ ልኩን ባላሳየው…” እያለች ትዝት ጀመር። በንዴት ስሜት ውስጥ ሆናም በቀጣዩ ቀን ዳቦ ስታስቀምጥ በውስጡ መርዝ ልትነሰንስበት ትወስናለች። እንዳይነጋ የለም ቀጣዩ ማለዳ ሲመጣ የጋገረችው አንደኛው ዳቦ ውስጥ መርዝ አድርጋበት ልታስቀምጥ ስትል እጇ መንቀጥቀጥ ጀመረ። ራሷን እንደምንም ልታደፋፍር ብትታገልም አልቻለችም። ከዚያም “ምን ማድረጌ ነው” እያለች ለጥቂት ደቂቃዎች ራሷን ወቀሰች። ወዲያው ከጋገረቻቸው ዳቦዎች መካከል የራሷን ፋንታ አንስታ እንደተለመደው በዳንቴል አድርጋ በሩ ላይ አስቀመጠችው። መርዝ ተደርጎበት የነበረውን ዳቦም ማንም እንዳይደርስበት ብላ ወስዳ ሽንት ቤት ከተተችው። የዚያን እለት የገዛ ቁርሷን ለዚያ ተመጽዋች ስላስረከበት ጾሟን መዋል ግድ ሆኖባት ነበር። እንደዚያው ባዶ ሆዷን እንዳለች ልክ ዘወትር እንደምታደርገው ጸሎት ቤቷ ገብታ ለወንድ ልጇ ጸሎት አደረገች። ልጇ ወደ ጦር ግንባር ከዘመተ ረጅም ዘመን አስቆጥሯል። ፈጣሪ ልጇን በሕይወት ይመለስላትም ዘንድ የእናት አንጀቷ ስፍስፍ እስኪል እያለቀሰች ጸለየች። የዚያን እለት ማታ ግን ያለወትሮው የቤቱ በር ተንኳኳ። እርሷም ግር እየተሰኘች ሄዳ ስትከፍተው ጦር ሜዳ የሄደው ልጇ በሩ ላይ ቆሟል። ስታየው በጣም ተደሰተች። እልልታዋንም አቀለጠችው። ትከሻው ላይ ተጠምጥማ ደስታ እንባ እያነባች አገላብጣ ስትስመው ቆየች። ልጇ በጣም ከስቶ ነበር። የጉንጩ አጥንት ፈጥጦ፣ ሰውነቱ መንምኖ ሲታይ ምግብ ከቀመሰ ወር ያለፈው ይመስላል። ቤት ገብቶ ራት ከተበላ በሁዋላ ስላሳለፈው ታሪክ ለእናቱ ተረከላት። በትረካውም መሀል እንዲህ አለ። “መቸም ተዓምር ነው! ወደዚህ ከተማ በእግሬ እየመጣሁ ሳለ መንገድ ላይ አቅም አንሶኝ ወድቄ ነበር። ቦታው ምናልባት ከዚህ ስድስትና ሰባት ኪሎ ሜትር ቢርቅ ነው። ዐቅሜን ስገምተው እዚህ ቤት የሚያደርሰኝ መስሎኝ ነበር፤ ነገር ግን ጥቂት ሲቀረኝ ርሀብ አዝለፍልፎ ጣለኝ። እናም ከጦርነት ተርፌ በርሀብ ስለመሞቴ እርግጠኛ ወደመሆን ደረጃ ስሸጋገር በድንገት አንድ አልፎ ሂያጅ ደረሰልኝ። ጀርባው ላይ ጎበጥ ያለ ደግ ሰው ዳቦ ይዞ መጥቶ ሲያበላኝ ነብሴ መለስ አለችልኝ። ታዲያ ዳቦውን ሲሰጠኝ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ?” እናት እንባዋ በጉንጯ ኮለል ብሎ እየፈሰሰ “ምን አለህ ልጄ? እኔ ምን አውቃለሁ አንተው ንገረኝ!” አለች። ልጁም እንዲህ ሲል መለሰ። “‹በየቀኑ አንድ ዳቦ እየበላሁ ነው የምኖረው። አሁን እንደምታየው እጄ ላይ አንድ ዳቦ ነው ያለው። ግዴለም ለዛሬ እኔ ሳልበላ ልቅር፤ ጦሜን አድራለሁ። ከእኔ የበለጠ ይሄ ዳቦ ላንተ ያስፈልግሃል› አለና ቅንጣት ታህል ቅር ሳይለው ሰጠኝ። ይሄው እኔም በእሱ ደግነት ከሞት ዳንኩ።**
Hammasini ko'rsatish...
ቴሌግራም ከ ጠዋት ጀምሮ መዘጋቱ ይታወቃል እና ከዚህ በታች ያለውን  proxy በመጠቀም በጥራት እንዲሰራ ማረግ ትችላላችሁ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/proxy?server=rwdc.ir.drroshanimplant.com.copydvd.ir.fanavadc.com.abginefilm.ir.hamyartruck.ir.ava-sigas.com.windowtranslation.com.dedna.ir.post-alirezaix.ir.4-so.ir.metisclinic.ir.raisin377.com.atresabz.one.tiget.ir.all-anti-are-bega-and-you-come-to-changer-lol.cyou.&port=443&secret=eeda411655b684fe87abf58ec2235e28167765622e62616c652e6972
Hammasini ko'rsatish...
🎂🎂🎂አስደሳች ዜና🎂🎂🎂 YouTube Telegram Tiktok የመሳሰሉ Application ያለ VPN በስልክ  በ ሪሲቨር & በ Tv መስራት ጀምረዋል።
Hammasini ko'rsatish...
🤟
ቢትኮይን .. የዘመናዩ ዓለም ተስፋ? (ወይስ ዳፋ?) ይሄ "ቢትኮይን" የሚሉት የኢንተርኔት ገንዘብ ቀልቤን ከሳበው ጥቂት ዓመታት ተቆጥረዋል። እንደ ቀልድ የዛሬ 15 ዓመት በጥቂት የሚተዋወቁ ሰዎች መካከል እንደመገበያያ እንዲያገለግል ተብሎ የተጀመረ ነው። በአንድ ስምየለሽ የኮምፒውተር ፕሮግራመር የተፈጠረ። "ዲጂታል ካሽ" ወይም "ዲጂታል ከረንሲ"። ነው ቢትኮይን። ግን መንግሥታት አይቆጣጠሩትም። ፖለቲከኞች ምን ያህል ገንዘብ ይታተም፣ ብለው የሚወስኑበት ቀዳዳ የለም በቢትኮይን። ድንበር አይገድበውም። ብሔራዊ ባንኮች አያውቁትም። ኢንሹራንስ አልተገባለትም። ግን ዛሬ በዓለም ዙሪያ ሚሊየኖች የሚገበያዩበት፣ የሚሸጡ የሚለውጡት፣ የሚጫረቱበት፣ በአየር ላይ የሚዛቅ የኢንተርኔት ወርቅ ሆኗል። ቢትኮይን! ለወንጀለኞች ጥቁር ገበያ ለማጧጧፍ የተመቸ አይደለም ወይ? ማነው የሚዘውረው? ሰው ግን ማንን አምኖ ነው በቢትኮይን ላይ ጥሪቱን እያፈሰሰ ያለው? እውን ቢትኮይን የዓለም ሕዝብ ሀብት ነው? ሁሉም ሰው የመንግሥትን ገንዘብ ትቶ በቢትኮይን መገበያየት ቢጀምርስ? ምን ይፈጠራል? ግን ይሄ ቢትኮይን ምንድነው? ከየት መጣ? ወደየትስ ይሄዳል? የወደፊቱ የዓለማቀፍ የዲጂታል ንግድ በቢትኮይን የሚንቀሳቀስ ይሆናል? ቢትኮይን የወደፊቱ የዓለም ገንዘብ ነው? ወይስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንክትክቱ ወጥቶ አሁን የተነከሩበትን በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ሀብት ንብረት ይዞ ጠፊ፣ በኪሣራ የሚደመደም፣ መዓት ሕዝብን ጨርቅ የሚያስጥል፣ የቁጭት ቤርሙዳ ነው? በምንስ ያስታውቃል? በታሪክ ሂደትና በሕዝብ ትግል ሐይማኖትና መንግሥት ተለያይተዋል (ይባላል)። የግል ሕይወትና መንግሥትም ተለያይተዋል (ይባላል)። በዘመናዊው ዓለም መንግሥትና ሴክስ እና ጀንደርም ተለያይተዋል (ይባላል)። በዜጎች የወሲብ ሕይወት ውስጥ ገብቶ አገባህ፣ ፈታህ፣ ወሰለትክ፣ ፆታ ቀየርክ፣ ሴተኛአዳሪ ሆንክ፣ ፍናፍንት ሆንክ፣ መነንክ፣ ወዘተ እያለ የሚገባ መንግሥት ከናካቴው ይጠፋል ወደፊት ነው የሚሉት። በዚህ ዘመን መንግሥትና ሚዲያም እየተለያዩ ነው። የመንግሥት አፍ የሆነ የሕዝብ ሚዲያ በወደፊቷ ዓለም አይገኝም (ይባላል)። ብቻ "ዘመናዊ"ው የሰው ልጅ ታሪክ "መንግሥት" የሚባለውን በጥቂት ፖለቲከኞች የሚዘወር ዳምጠው መኪና ከሕይወታችን ውስጥ መንጭቆ የማውጣት (ወይም ከመንግሥትና ጣጣዎቹ የመገላገል) ጉዞ ነው ብሎ ባጭሩ መግለጽ ይቻላል የሚሉ አሉ። ዛሬ ዛሬ መንግሥት ሌላ ቀርቶ ጦርሠራዊቱን ራሱ መቆጣጠር ያልቻለበት ጊዜ ነው። ቅጥር ሠራዊቶች የመንግሥታትን ድንበር እየተሻገሩ ለከፈላቸው አካል ወታደራዊ አገልግሎታቸውን የሚሰጡበት ጊዜ ላይ ነን። ዛሬ ዋግነር ግሩፕን ሰብሰብ ብሎ ወደ አፍሪካ ዘልቀህ የማሊን መንግሥት እንደምንም ብለህ አፈራርስልንና፣ ስትመለስ ደሞ እግረመንገድህን የኢትዮጵያንም መንግሥት አሣሩን አብልተህልን ና ብሎ ቀብድ የሚከፍለው አካል ካገኘ፣ ዓይኑን ሳያሽ ታጣቂዎቹንና ድሮኖቹን አንጋግቶ ይዘምትብናል። እና ዘመኑ ገንዘብ ሊገዛው የሚችል ጥሩ ጦርሠራዊት ከገበያ አማርጠህ መሸመት የምትችልበት፣ መንግሥቶች በሠራዊቶች ላይ የነበራቸውን ታሪካዊ የሞኖፖሊ (በብቸኝነት ጠቅልሎ የማዘዝ) ሥልጣን ያጡበት ዘመን ላይ ነን። ባጠቃላይ በብዙ የህይወት ፈርጆች ሲታይ.. ይህ የሰው ልጆች ነፃነት እየተረጋገጠ የመጣበት ዘመን... ዋና መገለጫው መንግሥት የሚባለውን አካል ከሕዝብ ጫንቃ ላይ እየመነጨቀ.. በጥሎ ማለፍና በዝረራ ከጨዋታ ውጭ እያደረገ መጓዝ ነው። እና... ይህ የዓለም ሕዝብ የነፃነት ጉዞ ፀረ-መንግሥት ግስጋሴውን ቀጥሎ... በመጨረሻም... በዚህ ባለንበት ዘመን... መንግሥት በገንዘቦች ሕትመት፣ በገንዘቦች ምንዛሪና፣ በገንዘቦች ዝውውር ላይ የነበረውን የብቸኛ አድራጊ-ፈጣሪነት ሥልጣን.... መንጭቆ የሚወስድበት ዘመን ይሆን ወይ? የቢትኮይን ባለቤትና ተቆጣጣሪ የለሽ የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ በዓለም ዙሪያ ድንበሮችን እየተሻገረ እየተስፋፋ የመምጣት ነገር... መንግሥት የቀረውን የመጨረሻ ሞኖፖሊ ፓወር የመነጠቁ ዜና ብሥራት ነው ወይ? ቢትኮይን የየሀገሩን ብሔራዊ ባንክ በጡረታ የሚያሰናብት የሕዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ውጤት ነው? ወይስ... ወንጀለኞች ከመንግሥታት ተሸሽገው ለመነገድ የፈጠሩት ... ነገር ግን መዓት የዋሃንን ወደራሱ ስቦ ያማለለ... የኢንተርኔት ጥቁርገበያ የቤትስም ነው? ምንድነው ቢትኮይን በትክክል? መንግሥቶች ለምን ፈሩት? ጥቅሙና ጉዳቱስ ምንድነው? ቢትኮይን የወደፊቱ ዓለም ነፃነት ወዳድ የዓለም ሕዝብ ተስፋ ነው? ወይስ ዳፋ? ምንድነው ይሄ ቢትኮይን? ጥያቄዎቻችን ብዙ ናቸው። ይሄ የሊባኖስ-አሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰርና፣ የኮለምቢያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ማዕከል አባልና ተባባሪ ተመራማሪ የሆነው ፣ በገንዘብና ግብይት ታሪክ ላይ ፒኤች ዲውን ያነገበው... ይሄ ሰይፈዲን አሙስ የተሰኘ አስደማሚ የኢኮኖሚክስ ምሁር... ብዙ ትንታኔዎችና አተያዮች አሉት። መሳጭ ነው። መስጦኛል። ሰይፉን (ሰይፈዲንን) በዝግታ እያነበብኩት ነው። ግን መች ነው ስለዚህ ቢትኮይን የሚባል ነገር ጥርት ያለ ስዕል የማገኘው? እውነቱ የሚገለፅልኝ? መች ነው?... አላውቀውም! በአንድ አሳቻ ቀን ላይ ግን ይሄ ቢትኮይን የተባለ በመንግሥት ዓይን ሥር ሽው እልም የሚል የአየር ላይ ሾተላይ ገንዘብ... ግልፅ፣ ግልፅልፅ፣ ፍርጥ-ርጥርጥ ማለት አይቀርለትም!!! እስከዚያስ...? እስከዚያማ... ማንበባችንን አጠናክረን እንቀጥላለን! Everything was difficult before it's easy! ሁሉም ቀላል ነገር፣ ሲጀመር፣ ከባድ ነበር። ቢትኮይንም ጭምር! ለዛሬ አበቃሁ። ቻው!
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ይኸው እየታገልን ነው
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ጥያቄ በመመለስ የሚከፍለን ምርጥ Web https://quit2.xyz/90967108584814302/ Do quizzes to earn US dollars, easily earn 1 US dollars in 1 minute, and anyone who logs in to our website will get 10 US dollars.
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
Forex trading መማር ለምትፈልጉ በአጠቃላይ ጀማሪ ለሆናቹ ወይም ለመጀመር ያሰባቹ ሰዎች አስፈላጊው መጽሐፍ እጄ ገብቷል መግዛት የምትፈልጉ እኔ ጋር በርካሽ ዋጋ ማግኘት ትችላላቹ
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.