cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አስገራሚ እውነታዎች

ምርጥ ምርጥ አስገራሚ እውነታዎች 👉የመሬት መልክዐ ምድር አቀማመጥ 👉ስለ ጠፈርና ጠፈርተኞች 👉መላው የአለም ህዘብ አሉ ወይስ የሉም ብሎ ስለሚጠይቃቸው ባዕድ ፍጡራን (ALIYNS)

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
200
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የዓመት ዝናብ በ3 ቀናት በቻይና ዘነበ፤ ቢሊየን የባሕር ፍጥረታት ሐምሌ ላይ ሞተዋል"
Hammasini ko'rsatish...
🤔30 ለማመን የሚከብዱ የአለም እውነታዎች🤔 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 1🤔 ወፎች አይሸኑም 2🤔 ጉንዳኖች ፈፅሞ አይተኙም፤ሳንባ የላቸውም፤ሰራተኛ ጉንዳን እስከ 7 ዓመት ሊኖር ይችላል ንግስቶ ግን እስከ 15 ዓመት ልትኖር ትችላለች:: 3🤔 ሻርክ ብቸኛው የማይታመም እንሰሳ ነው ምንም አይነት በሽታ አያጠቃውም ካንሰርን ጨምሮ:: 4🤔 ፈረሶች እና ላሞች ቁመው ነው እሚያንቀላፉት:: 5🤔 የማር ንብ ሁለት ሆድ ሲኖራቸው አንዱ ለማር ሲሆን ሁለተኛው ለሚመገቡት ምግብ ማስቀመጫ ያገለግላቸዋል:: 6🤔 ትልቁ ነጭ ሻርክ ከሶስት ወር በላይ ሳይበላ መጎዝ ይችላል:: 7🤔 አብዛኞቹ ዝሆኖች በክብደት ከስማያዊ አሳነባሪ(Blue whale) ምላስ ያንሳሉ:: 8🤔 በረሮ በርሀብ እስኪሞት ድረስ ለሳምንት ያህል ጭንቅላቱ ተቆርጦ በሂወት መቆየት ይችላል:: 9🤔 የአህያ አይን አቀማመጥ በአንድ ግዜ አራቱንም እግሮች ማይት ያስችሉታል:: 10🤔 ዶልፊን ውሀ ውስጥ ከ24ኪ.ሚ ርቀት ያለ ድምፅ በቀላሉ መስማት ይችላል:: 11🤔 የወባ ትንኝ(Mosquito) 47 ጥርስ አላት:: 12🤔 ማንኛውም ሁለት የሚዳ አህያ(zebra) እንድ አይነት መስመር አይኖራቸውም:: 13🤔 ቢራቢሮ የሚቀምሱት(taste) በሆላ እግራቸው ነው:: 14🤔 የወንድ ሸረሪት የወሲብ አካል በአንዱ የእግሩ ጫፍ ላይ ይገኛል:: 15🤔 ንቦች አምስት አይን አላቸው:: 16🤔 አሳማ በተፈጥሮ(physical) ወደ ሰማይ ማየት አያስችለውም:: 17🤔 አይጥ ከተራበች የራሶን ጅራት ትበላለች 18🤔 ለሚስቱ ታማኝ የሆነ እንስሳ ቀበሮ ብቻ ነው 19🤔 ሰማያዊ አሳነባሪ (Blue whale) በመጠን እስካሁን በአለማችን ከነበሩ እና ካሉ እንሰሳዎች ትልቁ ነው:: 20🤔 የለሌት ወፍ ብቸኛዋ ከአጥቢዎች መብረር የምትችል ሲሆን የእግር አጥንቶቾ ከመቅጠናቸው የተነሳ መብረር እንጂ መራመድ አትችልም:: 21🤔 የለሌት ወፍ ምንግዚም ከዋሻ ሲወጡ ወደ ግራ ይበራሉ:: 22🤔 እባብ አይኖቹ ቢከደኑም በአይኖቹ ቆብ ማየት ይችላል:: 23🤔 ወንድ የወባ ትንኝ አይናደፍም ሴቶ ብቻ ናት መናደፍ የምትችለው:: [femal Anofiles mosqto] 24🤔 የዱር አይጥ (Rat) በፍጥነት መራባት የሚችሉ ሲሆን በ18 ወራት ብቻ 2 አይጦች 1 ሚሊዮን ዘመዶችን ማፍራት ይችላሉ:: 25🤔 አንድ ንብ አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ለማዘጋጀት ከ 4000 በላይ አበቦችን መጎብኝት አለባት :: 26🤔 ቀንድ አውጣ ለ3 አመት መተኛት ይችላል:: 27🤔 አንድ ላይ የተያያዘ የሸረሪት ድር ተመሳሳይ ወፍረት ካለው አንድ ላይ ከተያያዘ የብረት ሺቦ ይጠነክራል:: 28🤔 ዝሆኖች ከ3ማይል ላይ ያለ ውሀ ማሺተት ይችላሉ:: 29🤔 ኦይሰትር(Oyster) የተባለ የአሳ ዝርያ ከአንዱ ፆታ ወደ ሊላኛው እንዲሁም ወደ ነበረበት ለወሲብ በሚመቸው ፆታውን መቀየር ይችላል:: 30🤔 በየአመቱ 1/3 የሚሆነው የአለማችን ሰብል በተባይ/ነብሳት ይወድማል።
Hammasini ko'rsatish...
ይህንን ያውቁ ኑሯል ❓❓❓🤔 1. አይጥና ፈረስ አያስመልሳቸውም 2. የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ከክብሪት ቀድሞ ነው የተፈጠረው 3. አዞ ምላሱን ማውጣትም ሆነ ምግብ ማኘክ አይችልም 4. በሰውነታችን ውስጥ ካሉት አተሞች ውስጥ 98 በመቶዎቹ በየአመቱራሳቸውን ይተካሉ 5. ድምፅ ከአየር ይልቅ በብረት ውስጥ በ15 እጥፍ ይጓዛል 6. ጎሪላዎች በቀን ለ14 ሰዓታት ይተኛሉ 7. የአንድ ሰው ልብ በቀን 100ሺህ ጊዜ ይመታል 8. ወሲብን ለመደሰቻ የሚጠቀሙበት የሰው ልጅና ዶልፊን ብቻ ናቸው 9. የእጅ ጥፍራችን ከእግር ጥፍራችን በአራት እጥፍ ያድጋል 10.ልክ እንደ እጅ አሻራ ሁሉ የእያንዳንዳችን የምላስ አሻራ የተለያየ ነው 🙄 ©
Hammasini ko'rsatish...
🖊EthioTelecom እየሰጠ ስለነበረው Free Internet አንዳድ ነገር ልበላቹ ባልታወቀ መንገድ እኔን ጨምሮ ብዙ ሰወች 4GB Internet Package ወስደዋል ባለኝ መረጃ መሰረት ከ ጥዋቱ 12:00 ሰአት ጀምሮ ይሄ Free Package ሲሰራና ወደ 2:00 አከባቢ ቆምዋል. በርግጥ EthioTelecom *999# USSD Server Optimised አድርገው ነበር በጣም Busy ና ቀርፋፋ ስለ ነበር ለ Costumer ቀልጣፋ ለማድረግ. እናም ስለ 4GBው Free Package ብዙ ወሬወች እተናፈሱ ነው ከዛም ውስጥ 📍 ሃክ ተደርጎ ነው 📍Negative ነው ማለትም Card ስንሞላ ይቆርጣል 📍System ላይ Bug ተፈጥሮ የሚሉ ናቸው. ፩ኛ ሃክ ሲጀመር ቴሌኮም በአፍሪካ ወስጥ ካሉት ቁጥር ትልቅ ድርጅት ውስጥ ይመደባል ስለዚህ አለ የተባለ ትልቅ ድርጅት ከሆነ በዛው ልክ Securityው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም የራሳቸው ጥቃት ተከላካይ Ethical Hacker አሉዋቸው Systemሙን በየግዜው Update ይደርጋል እናም እኛ እንደምናስበው ቴሌኮም መጥለፍ ቀላል ና ተራ አይደለም. ፪ Negative ነው ማለትም Card ስንሞላ ይቆርጣል እንግዲህ እኔ በገባልኝ TxT መሰረት 4GB Internet Package Gift🎁 ነዉ የሚለው ተመልከቱ👇 Internet Package 4GB for 30 days is 4096.000 MB with expiry date on 2021-09-21 at 08:10:35;from gift Mobile እዚህጋር Dismatch ያደርጋል Gift ተብሎ እንዴት Negative ሊቆጥርብን ይችላል እኔ እስከማውቀው Gift ነፃ እንደሆነ ነው ሰቶ መቀበልም ከሆነም አብረን እናያለን እስከዛ ግን ማናችንም L8tr እንደሚቆርጡ እርግጠኛ ሆነን መናገር አንችልም. ምናልባት ለፆም ፍቺ ም ይሆናል😊 ፫ System ላይ Bug ተፈጥሮ ይሄ በመጠኑም ያስኬዳል + እስማማለሁ አይደለም EthioTelecom ላይ Facebook Twitter What's App ላይ የሚከሰት ነው ስለዚህ ቢፈጠር አያስገርምም Debug ይደረጋል 📍በዚህ አጋጣሚ 📌Bug ማለት በProgramming System ላይ የሚፈጠር ስህተት ሲሆን 📌Debug ማለት ደግሞ የፈጠረውን የስህተት Re- Program በማድረግ ማስተካከል ነው የኔ ሀሳብ🤔 ማንኛውም ድርጅቶች ላይ እንደሚፈጠረው የSystem ችግር ገጥሙዋቸው ወይም ተፈጥሮ አሊያም ከ ቁጥጥር ውጭ (Out Of Control) ሆኖባቸዋል ሊሆን ይችላል Internet ራሱ እንደ በፊቱ በስትክክል እየሰራ አይደለም አንዳድ ጀለሶቼ ጋር ጭራሽ አይሰራም ይሄ Bug እንዳለ አንዱ ማሳያ ይመስለኛል. በሌላ በኩል እንደምታውቁት የውጪ የቴሌኮም ድርጀቶች በቀጣይ ጥር ወር ሊገብ ስለሆነ የማቆያ ዘዴ ( አኩምፓቸር) ሊሆን ይችላል ለገባው 🤣 ስለ ነገሩ 994 ደውዬ ለማጣራት ሞክሬ ነበር አልተሳካም Official ፔጃቸውንም እየተከታተልኩ ነው አዲስ ነገር የለም ካለ አሳውቃቹዋለው በመጨረሻም ስለተፈጠረው ችግር እርግጠኛ ለመሆን ፍርዬ መግለጫ እስክትሰጥ ድረስ ብንጠብቅ አይሻልም ቤተሰቦች 😆 📍አንዳንዶቻቹ በ inbox በ Bot እና በ Offical Groupችን ላይ ብድር ነው + ዉሸት ነው ያልሆነ ነገረ አትፖስት እያላቹኝ ነው እንደ አስተያየት እቀበለዋለሁ. ነገርግን እኔ እዚህ ቻነል ላይ ምለቀው ዝምብዬ አይደለም ከተለያዩ EthioTelecomምን ጨምሮ ከሌሎችም Website Information Gather አድርጌ ነው ቢያንስ የለቀኩበትን 3ምከንያት ከላይ ገልጫለሁ More Refer ለማድረግ ሞክሩ ደግሞ ማንንም💁‍♀️አላስገደድኩም መጠቀም አለመጠቀም የናንተ ፍላጎት ነው.
Hammasini ko'rsatish...
Ethiopian Astronomy 🇪🇹 🌎🌎"ከዋክብት"🌎🌎 ጥርት ባለው ሰማይ ላይ ተረጭተው የሚታዩትን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት በምሽት ስትመለከት የአድናቆት ስሜት አድሮብህ ያውቃል? ከዋክብት፣ በሚፈነጥቁት ብርሃን ድምቀት ብቻ ሳይሆን በቀለማቸውም አንዳቸው ከሌላው እንደሚለዩ አስተውለህ ይሆናል። የከዋክብት ክብር ወይም የብርሃናቸው ድምቀት የሚለያየው ለምንድን ነው? ለምሳሌ አንዳንዶቹ ከዋክብት ነጭ ሌሎቹ ሰማያዊ፣ ቢጫ ወይም ቀይ ቀለም እንዳላቸው ሆነው የሚታዩን ለምንድን ነው? ብልጭ ድርግም የሚሉ የሚመስሉትስ ለምንድን ነው? ከዋክብት፣ በውስጣቸው እጅግ በጣም ከፍተኛ መጠን ያለው ኃይል የሚያመነጭ የኑክሌር ማብለያ አላቸው ማለት ይቻላል። ይህ ኃይል ወደ ኮከቡ ውጨኛ ክፍል ይሄድና በአብዛኛው በኢንፍራሬድ ጨረርና በዓይን በሚታይ ብርሃን መልክ ወደ ሕዋ ይሰራጫል። የሚገርመው ነገር በጣም ከፍተኛ ሙቀት ያላቸው ከዋክብት ሰማያዊ ሲሆኑ ቀዝቀዝ የሚሉት ደግሞ ቀይ ቀለም አላቸው። እንዲህ ያለ የቀለም ልዩነት ሊኖር የቻለው ለምንድን ነው? ብርሃንን ፎቶን የሚባሉ ቅንጣቶች ጅረት እንደሆነ አድርገን ልናስበው እንችላለን፤ እነዚህ ቅንጣቶች የኃይል ሞገድ የሚያሳየው ዓይነት ባሕርይ አላቸው። ከፍተኛ የሙቀት መጠን ያላቸው ከዋክብት ከፍተኛ ኃይል ያላቸውን ፎቶኖች የሚለቁ ሲሆን እነዚህ ደግሞ አጭር የሞገድ ርዝመት አላቸው፤ አጭር የሞገድ ርዝመት ያለው የብርሃን ክፍል ሰማያዊ ቀለም አለው። በአንጻሩ ደግሞ ቀዝቀዝ የሚሉት ከዋክብት አነስተኛ ኃይል ያላቸውን ፎቶኖች የሚለቁ ሲሆን እነዚህ ፎቶኖች ደግሞ ቀይ ቀለም ካላቸው ሞገዶች ይመደባሉ። ለእኛ ብርሃን የምትሰጠን ኮከብ ማለትም ፀሐይ የምትፈነጥቀው ብርሃን ከአረንጓዴ እስከ ቢጫ ባለው ክልል ውስጥ ይገኛል። ታዲያ ፀሐይ አረንጓዴ ሆና የማትታየው ለምንድን ነው? በዓይን መታየት በሚችለው የብርሃን ክልል ውስጥ ባሉት የሞገድ ርዝመቶች ሁሉ ከፍተኛ ብርሃን ስለምታመነጭ ነው። በመሆኑም ፀሐይ ከሕዋ ስትታይ ነጭ ትመስላለች። የምድር ከባቢ አየር የፀሐይን ቀለም “ይለውጠዋል” የፀሐይ ብርሃን ወደ እኛ የሚደርሰው በከባቢ አየር በኩል አልፎ ነው፤ ይህም የፀሐይን መልክ በተወሰነ መጠን ስለሚለውጠው ፀሐይ በቀን ውስጥ በተለያየ ሰዓት የተለያየ ቀለም ያላት ትመስላለች። ለምሳሌ እኩለ ቀን ላይ ፀሐይ በአብዛኛው ደማቅ ቢጫ ሆና ትታያለች። ይሁንና ፀሐይ በምትወጣበትና በምትጠልቅበት ጊዜ ብርቱካንማ ወይም ቀይ ሆና ትታያለች። እንዲህ ያለ የቀለም ለውጥ ሊኖር የቻለው በምድር ከባቢ አየር ውስጥ በሚገኘው ተን፣ የጋዝ ሞለኪውሎች እንዲሁም በዓይን የማይታዩ ጥቃቅን ቅንጣቶች ምክንያት ነው። ከባቢ አየር በውስጡ ባሉት ነገሮች የተነሳ ወደ ምድር ከሚመጣው የፀሐይ ብርሃን ውስጥ ሰማያዊና ሐምራዊ የሆነውን ቀለም ስለሚበትነው ደመና በሌለበት ቀን ሰማዩ ውብ የሆነ ሰማያዊ ቀለም ይኖረዋል። ፀሐይ ከምትፈነጥቀው ብርሃን ውስጥ ሰማያዊውና ሐምራዊው ቀለም በዚህ መንገድ ስለሚቀነስ እኩለ ቀን ላይ ፀሐይ ቢጫ ቀለም ይኖራታል። ጀምበሯ ወደ አድማስ በምትጠጋበት ጊዜ ግን ብርሃኗ ከባቢ አየሩን በአግድሞሽ ስለሚያቋርጥ በምድር ከባቢ አየር ውስጥ ረጅም ርቀት ይጓዛል፤ በዚህ ጊዜ የምድር ከባቢ አየር ሰማያዊውንና አረንጓዴውን ብርሃን ይበልጥ ይበትነዋል። ስለሆነም የምትጠልቀው ፀሐይ በጣም የምታምር ቀይ ኳስ ሆና ትታያለች። የቻናላችንን ሊንክ share በማድረግ አጋርነታችሁን አሳዩን👇👇👇👇👇👇 @asgrami_ewnetawoche @asgrami_ewnetawoche
Hammasini ko'rsatish...
👉ጉንዳኖች የአልኮል መጠጥ ሲርከፈከፍባቸው ይሰክራሉ ፤ ሰክረውም ይወድቃሉ፡፡ የሚገርመው ጉዳይ ደሞ ያልሰከረው ጉንዳን የሰከረውን ጉንዳን ደግፎ ደጋግፎ ወይም እቅፍ ድግፍ አድርጎ ሰፈሩ ወይም እቤቱ መውሰዱ ነው
Hammasini ko'rsatish...
Ethiopian Astronomy🇪🇹 የጳጒሜን 5 ፤ 6 እና 7 አመጣጧ ሲተነተን 🌏ጳጒሜን የተባለችው 13ኛዋ ወር በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል፡፡ የ5 ቀናትን የጳጉሜንን አመጣጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጠንቅቀው ቀምረው በባሕረ ሐሳብ ብራናቸው ላይ ጽፈውልናል፡፡ 🌏ይኸውም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ያሉት 12ቱ ወራት ያላቸው ዕለታት በአጠቃላይ 360 ናቸው፡፡ በቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ትንተና 1 ዕለት የሚባለው 24 ሰዓት ከ52 ካልዒት ከ31 ሳልሲት ነው፡፡ 🌏1 ካልዒት ማለት 24 ሰከንድ ሲኾን 52 ካልዒት ማለት 1248 ሰከንድ ነው፤ 31 ሣልሲት ማለት 12.4 ሰከንድ (ቅጽበት) ይኾናል፡፡ በመኾኑም በአንድ ቀን ውስጥ 1 ደቂቃ ከ0.4 ሰከንድ ትርፍ መኖሩን ያስረዳል፡፡ 🌏በመኾኑም ከመስከረም 1 እስከ ነሐሴ 30 ባሉት 360 ቀናት ያሉትን 52 ካልዒት ወይም 1248 ሰከንድ እንዲኽ እናባዛቸዋለን፤ 52 ካልዒት X 360 ዕለታት= 18720 ካልዒት ወይም (449, 280 ሰከንድ) ይኾናል፤ ወደ ደቂቃ ስንለውጠው 7488 ደቂቃ ወይም 5 ዕለት ይኾናልና የጳጒሜን አመጣጥ ይቺ ናት፡፡ 🇪🇹የጳጉሜን 5 ምስጢር 👉አራቱ የዓመት ወቅቶች ማለትም መፀው፣ ሐጋይ፣ ጸደይና ክረምት 91, 91 ቀናት የሚኾኑት ከጳጒሜን 1 አንድ ዕለት እየተሰጣቸው ሲኾን በአጠቃላይ 364 ዕለታት ወይም 52 ሳምንት ኾኖ አንዲት ዕለት ትተርፋለች፤ ይቺም ጳጒሜን 5 ስትኾን በኢትዮጵያ ቀደምት የዘመን ቀመር ሊቃውንት “ዕለተ ምርያ፣ አዕዋዲት” ትባላለች፡፡ 🌏ዕለተ ምርያ ማለት ዕለተ መድኀኒት ማለት ነው፤ ምክንያቱም ጳጒሜን 5 የመድኀኒታችን ክርስቶስ ልደትን የምናውቅባት ስለኾነች ነው፤ ይኸውም ጳጒሜን 5 በዋለችበት ዕለት የክርስቶስ ልደት ዕለት በተመሳሳይ መልኩ ይውላል፡፡ 🌏ለምሳሌ የዚኽ ዘመን ጳጉሜን 5 ዕለት ሰኞ ናት፤ በተመሳሳይ መልኩ የ2011 የጌታችን የልደት በዓል ታኅሣሥ 29 ሰኞ ይውላል፡፡ በዚህ ምክንያት ዕለተ ምርያ የሚል ሥያሜ ሊሰጣት ችሏል፡፡ 🌏በተጨማሪም ጳጒሜን 5 የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የዐዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደኾነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመኾኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ መዋሉ በእጅጉ ይደንቃል፡፡ 🇪🇹ጳጉሜን 6 ምስጢር 🌏የ6ተኛዋ ጳጒሜን አመጣጥን ስናይ፡- በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ስሌት 1 ዓመት የምንለው 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው፡፡ ይህን የየዓመቱን 6 ሰዓት ስንቈጥር የኹለት ዓመት 12 ሰዓት፤ የሦስት ዓመት 18 ሰዓት፤ የአራተኛው ዓመት 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ሲሆን ይኸውም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መጀመሪያ ሲኾን ይኸውም በቀደምት የአቡሻክር ሊቃውንት “መጠነ ራብዒት፣ ሠግረ ዮሐንስ” ትባላለች። ዘመነ ዮሐንስ ተራምዶ የሚያልፍባት ለማለት ነው፡፡ 🌏እኛ ጳጒሜን 6 ስናደርግ ምዕራባውያኑ ግን የጳጒሜን ወራትን በማጥፋታቸው ኹሌ ለእነርሱ 28 የኾነችው የካቲትን በአራት ዓመት አንዴ 29 ያደርጋሉ፤ Leap Year ብለው ይጠሯታል፡፡ 🇪🇹ጳጒሜን 7 እና አመጣጧ 🌏የኢትዮጵያን ቀደምት ሊቃውንትን በእጅጉ እንድናደንቅ ከሚያደርገን አንዱ የጳጒሜን 7ትን ስሌት ጠንቅቀው አስልተው በብራና የአቡሻክር መጽሐፍ ላይ ጽፈውልን ስሌቱን አስልተው ማለፋቸው ሲኾን፤ የስሌቱም መጠሪያ “ዕሪና መዓልት ዕሪና ሌሊት” በመባል ይታወቃል፡፡ ይኸውም 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይም 365 ዕለት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ የኾነው የፀሓይ ዐውደ ዓመት የ6 ካልዒት ወይም የ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ጥርቅም ወይም ከላይ ያየናት የአንዷ ዕለት 0.4 ሰከንድ ጥርቅም ነው ፡፡ 🌏ስናሰላውም የ5 ዓመቱ 30 ካልዒት፤ የ10ሩ ዓመት 60 ካልዒት (1 ኬክሮስ ወይም 24 ደቂቃ) ይሆናል፡፡ የ100 ዓመት (10 ኬክሮስ) ወይም 240 ደቂቃ (4 ሰዓት) ይኾናል፡፡ የ200 ዓመት 20፤ የ300 ዓመት 30፤ የ400 ዓመት 40 ኬክሮስ፤ የ500 ዓመት 50 ኬክሮስ፤ የ600 ዓመት 60 ኬክሮስ ሲሆን 60 ኬክሮስ ማለት 1440 ደቂቃ ወይም 24 ሰዓት ወይም 7 ተኛዪቱ ጳጉሜን ናት፡፡ 👉ሆኖም ግን የአቡሻሕርና የባሕረ ሐሳብ መምህራን ጳጕሜን 7 የተገኘችው ከጥቃቅን መስፈርት ወገን ከሆነችው ከካልዒት በመሆኑ ሒሳቧ ብቻ ታስባ ድቁቅ ደቃይቅ ተብላ ብቻ እንድትተው በማዘዝ ዕለቷ ግን በኅሊና ብቻ እንድትታሰብ እንጂ ተቆጥራ እንዳትከበር አዘዋል፡፡ በመሆኑም በማሰብ ብቻ እንጂ በዕለትነት ተቆጥራ አትውልም፡፡ 👉በአቡሻሕሩ ስሌት መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ 12 ዕሪና መዓልት 12 ዕሪና ሌሊት (ጳጉሜን 7) ተመላልሶ በ1700 ዓ.ም. ወይም በ7800 ዓመተ ዓለም ኾኖ 13ኛው ከተጀመረ 313 ሆኖ በዘመነ ሉቃስ ይኸው ሊፈጸም በ2013 ዓ.ም ካሰላነው 287 ዓመት ይቀራል ወይም በ2300 ዓ.ም. ላይ ይሆናል ማለት ነው፡፡ 🌏ይህ በሚሆን ጊዜ ዐቀድ የሚባል ኮከብ አለ፤ ሰሌዳው በፀሓይ ልክ፤ ባሕርዩ ጽሉም ነው፤ ርሱ በ600 ዓመት መጥቶ ፀሓይን ይጋርዳታል፤ ያን ጊዜ ሌሊቱና መዓልቱ ጨለማ ኹኖ ይውላል ያድራል፤ ይኸውም የመከራ ፊት አውራሪ አጫሪ ነው፤ ይኸውም በዐጤ ኢያሱ ወይም ፀሓይ ሰገድ በተባለ በዐጤ ዮስጦስ ጊዜ ተደርጓል ብለው መዝግበውልናል፡፡ ይህን ስናይ የቀደምት ኢትዮጵያውያንን ዕውቀት ሁሌም እንድናደንቅ ያደርገናል:: Source:-አንድሮሜዳ ቁ.1 For any comment 👇👇 @Eyuelaliant Share and stay tuned 👇👇 @asgrami_ewnetawoche
Hammasini ko'rsatish...
the diamond world(የዳይመንዱ አለም) ሳይንቲፊክ ስሙ "55 Cancri e" ይባላል የሚዞረው ኮከብ ደግሞ "55 Cancri A" ይባላል ፕላኔቱ ኤክሶፕላኔት(exoplanet) ወይም ከኛ ሶላር ሲስትመ ውጭ ነው የሚገኘው ይሄም ከኛ መሬት 40 የብርሃን አመተ ይርቃል ይሄ ፕላኔት የተገኘው በውጮቹ 2004 አከባቢ ሲሆን ሰለ ፕላኔቱ በውቅቱ ብዙ መረጃወች አልተገኘም ነበረ። በ2010 እና 2012 አከባቢ በተጠና ጥናት ፕላኔቱ የተሰራው ከካርበነ(carbon) ንጥረ ነገረ ሲሆን እንደሚታወቀው ዳይመንድ እና ግራፍይት የሚሰሩት ከካርበነ ስብስብ ነው። ይሄም እንደሳይንቲስቶች ግምት ይሄ ፕላኔት አንድ ሶስተኛው ክፍል የተሰራው ከዳይመንድ ነው ቀሪው ክፍል የተሰራው ከግራፍይት እና ሌሎችም ማእድናት ነው ፕላኔቱ ስፍቱ የኛን መሬት ሁለተ እጥፍ ሲሆን ክብደቱ ግን ስምንት እጥፍ ነው ፕላኔቱ የራሱ ኮከበ ያለው ሲሆን ኮከቡን የሚዞረው በጣም ተጠግቶ ነው ከመሬት አንፃር ይሄም ፕላኔቱ ሱፐርኤርዝ(super earth) ያስብለዋል። ፕላኔቱ የራሱን ፀሐይ ዙሮ ለመጨረስ 2.4 የመሬት ቀን ይፈጅበታል ፕላኔቱ እጅግ ሞቃት ከሚባሉ ፕላኔቶቹ አንዱ ነው ሙቀቱ 1,700° ድግሪሴልሴሽ ነው ይሄ ሙቀቱ ብረትን የማቅለጠ አቅም አለው ፕላኔቱ ልክ እንደመሬት የራሱ የሆነ ከባቢ አየረ አለው ይሄም የታወቀው በ 2016 ነበር ይሄም የራሱ ከባቢ አየረ ያለው ኤክሶፕላኔት(exoplanet) ሲታወቀ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር የዚህ ፕላኔት ዳይመንድ አውነ ላይ ባለው በኛ ምድር ዋጋ ቢሸጠ "$26.9 nonillion" ያወጣል ይሄ ማለተ ሰላሳ ዜሮ ያለው ቁጥር ነው ይሄም ሲፃፍ 26.9*10^30 ነው እንደሚታወቀው ቢልዬን የሚባለው ቁጥር 9ኝ ዜሮ አለው share share 🙏👇👇👇
Hammasini ko'rsatish...
#የቶማስ_ኤዲሰን_እናት! ⭐️ታዳጊው ቶማስ ኤዲሰን ከዕለታት አንድ ቀን ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲሄድ አንድ ወረቀት ለእናቱ ሰጣት። ''እማዬ መምህራችን ይህን ወረቀት ሰጠኝና ለእናትህ ብቻ ስጣት አለኝ'' አላት። እናቱም ደብዳቤውን አንብባ በፍርሃት ተሸብባ፤ ዕንባ 😢😢በዓይኖችዋ ዙሪያ ግጥም አለ። ነገርግን ድምጽዋን ከፍ አድርጋ ለልጅዋ ደብዳቤውን አነበችለት። 📌''ልጅሽ የሚገርም ክህሎት ያለው ብልህ ልጅ ነው። አሁን የሚማርበት ትምህርት ቤት ለእሱ በጭራሽ አይመጥነውም ያንሰዋል። የተሻሉ ጎበዝ መምህራን ያሉበት ትምህርት ቤት ቢገባ ይሻለዋል። ምክንያቱም እሱን የሚመጥነው ትምህርት ማግኝት ስለማይችል እባክሽ እራስሽ ልጅሽን ቤት ውስጥ አስተምሪው...!'' ይላል አለችው። #እናቱ ከሞተች ከብዙ ዓመታት በኋላ ቶማስ ኤዲሰን በአሜሪካ ታላቁ የክፈለ ዘመኑ የፈጠራ ሰው ሆነ። ከእለታት አንድ ቀን የድሮ የቤተሰቡን ቁምሳጥን ሲከፍተው አንድ ተጣጥፎ የተቀመጠ ደብዳቤ አገኘ። ከፍቶ ሲያየው መምህሩ ልጅ እያለ ለእናቱ ብቻ እንዲሰጥ ያዘዘው ደብዳቤ ነበር። ወዲያውኑ ደብዳቤውን ከፍቶ ማንበብ ጀመረ '' #ልጅሽ_የዓእምሮ_በሽተኛ_ነው። ለማንኛውም እዚህ ትምህርት ቤት እንዲማር አንፈቅድለትም። ስለዚህ ካሁን በኋላ ከትምህርት ቤቱ ተሰናብቷል።'' ይላል መልእክቱ። ✔️ቶማስ ኤዲሰን በስሜት ተመስጦ ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ በኋላ የግል ማስታወሻ ደብተሩ ላይ እንዲህ ብሎ አሰፈረ። ''ቶማስ አልቫ ኤዲሰን የዓእምሮ ህመምተኛ ታዳጊ ሕጻን ነበር። እናቱ ግን የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ሊቅ እንዲሆን አስቻለችው።'' 📌ግብረገብ - የእናቶች ፍቅርና ማበረታታት ለልጆች መጻኢ ስኬታማ ሕይወት መሰረት ነው። በተፈጥሮዋቸው በተለይ እናቶች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸው ቅርበታቸው ከፍተኛ ነውና ሕጻናትን በሞራል በመደገፍ ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለአገራቸው እና ለዓለም የሚበጅ ስራዎችን ትተው የሚያልፍ ፍሬዎች እንዲሆኑ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው። አትችልም፣ አትሞክሪ፣ የኔ ልጅ እኮ አይሆንለትም ወዘተ... መሰል ሞራል ገዳይ አሉታዊ ስሜት ንግግሮች ከማድረግ ይታቀቡ። በአንፃሩ ልጆችን ስሜታቸውን መረዳት፣ በእንክብካቤ መያዝ፣ ሳይታክቱ ምላሽ መስጠት፣ ትኩረት ሰጥቶ ማዳመጥ ይገባል። ስወዳችሁ በብዛት!😍 😘😘 #ክብር ለእናቶች ሁሉ ይሁን!
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.