uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ETHIO-ቴክ-TIPS

ETHIO-ቴክ-TIPS

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan

📈 Telegram kanali ETHIO-ቴክ-TIPS analitikasi

ETHIO-ቴክ-TIPS (@ethiotechtipss) kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 16 131 obunachidan iborat bo'lib, Boshqa toifasida -o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 16 131 obunachiga ega bo‘ldi.

27 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -3 665 ga, so‘nggi 24 soatda esa -65 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 13.65% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 6.40% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 2 202 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 033 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 16 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Kanal uchun tavsif kiritilmagan.

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 28 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Boshqa toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

16 131
Obunachilar
-6524 soatlar
-3767 kun
-3 66530 kun
Postlar arxiv
​🛑 ቴሌግራም ላይ ወደ ማይፈለጉ ግሩፖች በሰው እንዳይጨመሩ የማገጃ ዘዴ ​ሳያውቁት በተለያዩ ያልታወቁ የቴሌግራም ግሩፖች እና ቻናሎች ውስጥ በየቀኑ እየተጨመሩ ከተቸገሩ፦ ​የሚገኝበት ቦታ፦ ቴሌግራ
​🛑 ቴሌግራም ላይ ወደ ማይፈለጉ ግሩፖች በሰው እንዳይጨመሩ የማገጃ ዘዴ ​ሳያውቁት በተለያዩ ያልታወቁ የቴሌግራም ግሩፖች እና ቻናሎች ውስጥ በየቀኑ እየተጨመሩ ከተቸገሩ፦ ​የሚገኝበት ቦታ፦ ቴሌግራም ከፍተው Settings > Privacy and Security > Groups & Channels ውስጥ ይግቡ። ​ቅንብሩን ማስተካከል፦ "Who can add me" የሚለው ላይ Everybody ከሚለው ወደ My Contacts ይቀይሩት። ​ጥቅሙ፦ በስልክ ቁጥርዎ የተመዘገቡ የቅርብ ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር ማንም የማያውቁት ሰው ወይም ቦት ወደ የትኛውም ግሩፕ መክተት አይችልም። ​#TelegramSecurity #PrivacyTips #OnlineSafety #TelegramHacks ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

🚀 ስልክዎን ፈጣን ለማድረግ የሚረዳው ሚስጥራዊ የDeveloper Options ብልሃት ​አንድሮይድ ስልክዎ አፖችን ሲከፍት እና ሲዘጋ የሚታየው አኒሜሽን (Animation) እንዲቀንስ በማድረግ ስልኩ
🚀 ስልክዎን ፈጣን ለማድረግ የሚረዳው ሚስጥራዊ የDeveloper Options ብልሃት ​አንድሮይድ ስልክዎ አፖችን ሲከፍት እና ሲዘጋ የሚታየው አኒሜሽን (Animation) እንዲቀንስ በማድረግ ስልኩ እጅግ ፈጣን እንዲመስል ማድረግ ይቻላል። ​Developer Options ማብራት፦ Settings > About phone > Software information ውስጥ ገብተው Build number የሚለውን 7 ጊዜ በተደጋጋሚ ይጫኑት። ​አኒሜሽኖችን መቀነስ፦ ወደ ዋናው ሴቲንግ ተመልሰው Developer options ውስጥ ይግቡና ወደ ታች ወርደው የሚከተሉትን 3 አማራጮች ያግኙ፦ ​Window animation scale ​Transition animation scale ​Animator duration scale ​ቅንብሩን መቀየር፦ ሶስቱንም ከ 1x ወደ 0.5x ይቀይሯቸው (ወይም ሙሉ ለሙሉ Off ያድርጓቸው)። ​ውጤቱ፦ ስልክዎ አፖችን ሲከፍትም ሆነ በመካከላቸው ሲዘዋወር ያለምንም መዘግየት በቅጽበት ይከፍታል። ​#AndroidTips #PhoneSpeed #TechTricks #SmartphoneHacks ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​🌐 በስልክ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ የዳታ ፍጆታን በግማሽ የሚቀንስ ብልሃት ​ጎግል ክሮም (Chrome) ሲጠቀሙ ሜጋባይት እንዳይበላ ይህን ቅንብር ያብሩ፦ ​Chrome Lite/Data Saver፦ የጎግል
​🌐 በስልክ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ የዳታ ፍጆታን በግማሽ የሚቀንስ ብልሃት ​ጎግል ክሮም (Chrome) ሲጠቀሙ ሜጋባይት እንዳይበላ ይህን ቅንብር ያብሩ፦ ​Chrome Lite/Data Saver፦ የጎግል ክሮም አፕሊኬሽን ከፍተው ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ይጫኑ። ​ቅንብሩን ማስተካከል፦ Settings > Lite mode (ወይም በቅርብ ስሪቶች Settings > Privacy and security) ውስጥ ገብተው የድረ-ገጽ ዳታ ቆጣቢን ያብሩት። ​ውጤቱ፦ ድረ-ገጾች ከመከፈታቸው በፊት መጠናቸው እንዲቀንስ ስለሚደረግ ኢንተርኔት በከፍተኛ ፍጥነት ይከፍታል፣ የሞባይል ዳታ ፍጆታንም በ30% እስከ 50% ይቀንሳል። ​#ChromeTips #DataSaving #MobileHacks #InternetTips ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

🔊 የስልክ ስፒከር ድምፅ ሲቀንስ በድምፅ ሞገድ የማጽጃ ዘዴ ​ስልክዎ አቧራ ከገባበት ወይም ውሃ ነክቶት የስፒከሩ ድምፅ ከቀነሰ ያለ መርፌና እቃ በቀላሉ ማጽዳት ይቻላል። ​አሰራሩ፦ ብራውዘር ላይ
🔊 የስልክ ስፒከር ድምፅ ሲቀንስ በድምፅ ሞገድ የማጽጃ ዘዴ ​ስልክዎ አቧራ ከገባበት ወይም ውሃ ነክቶት የስፒከሩ ድምፅ ከቀነሰ ያለ መርፌና እቃ በቀላሉ ማጽዳት ይቻላል። ​አሰራሩ፦ ብራውዘር ላይ ገብተው fixmyspeakers.com የሚለውን ድረ-ገጽ ይክፈቱ፤ ወይም ዩቲዩብ ላይ "water eject sound" ብለው ይፈልጉ። ​እንዴት ይሰራል?፦ ድረ-ገጹ የተለየ የድምፅ ድግግሞሽ (Sound Frequency) ያጫውታል፤ ይህ ኃይለኛ ንዝረት በስፒከሩ ቀዳዳ ውስጥ የተጣበቀውን ውሃ ወይም አቧራ ወደ ውጭ ይገፈትረዋል። ​ጥንቃቄ፦ ድምፁ በሚጫወትበት ጊዜ የስልኩን ድምፅ (Volume) እስከ መጨረሻው ይጨምሩት እና ስፒከሩን ወደ ታች አዙረው ይያዙት። ​#MobileHacks #SpeakerFix #TechTips #SmartphoneHacks ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​🔒 የቴሌግራም መለያዎ በሌላ ስልክ እንዳይከፈት የማረጋገጫ መንገድ ​አካውንትዎ በሌላ ኮምፒውተር ወይም ስልክ ላይ ክፍት ሆኖ መልዕክቶችዎ እየተነበቡ እንዳልሆነ በየጊዜው ይፈትሹ፦ ​የሚገኝበት ቦታ
​🔒 የቴሌግራም መለያዎ በሌላ ስልክ እንዳይከፈት የማረጋገጫ መንገድ ​አካውንትዎ በሌላ ኮምፒውተር ወይም ስልክ ላይ ክፍት ሆኖ መልዕክቶችዎ እየተነበቡ እንዳልሆነ በየጊዜው ይፈትሹ፦ ​የሚገኝበት ቦታ፦ ቴሌግራም ከፍተው Settings > Devices ውስጥ ይግቡ። ​ምን ያሳያል?፦ የእርስዎ ቴሌግራም በአሁን ሰዓት በየትኞቹ ስልኮች፣ ላፕቶፖች ወይም ብራውዘሮች ላይ ክፍት እንደሆነ በዝርዝር ከነቦታው ያሳያል። ​እርምጃ፦ እርስዎ የማያውቁት ወይም የማይጠቀሙበት መሳሪያ ካለ "Terminate Session" የሚለውን በመጫን ወዲያውኑ ዘግተው ያስወጡት። ​#TelegramSecurity #PrivacyTips #OnlineSafety #AccountProtection ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​⌨️ ኮምፒውተር በድንገት ስክሪኑ ሲቆም (Freeze ሲያደርግ) ፈጣን መፍትሄ ​ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ስራ ላይ እያሉ አይጥ (Mouse) ካልተንቀሳቀሰች እና ስክሪኑ ከቆመ በቀጥታ ከማጥፋት ይህን
​⌨️ ኮምፒውተር በድንገት ስክሪኑ ሲቆም (Freeze ሲያደርግ) ፈጣን መፍትሄ ​ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ስራ ላይ እያሉ አይጥ (Mouse) ካልተንቀሳቀሰች እና ስክሪኑ ከቆመ በቀጥታ ከማጥፋት ይህን ይሞክሩ፦ ​የግራፊክስ ድራይቨር ሪሴት ማድረጊያ፦ በኪቦርዱ ላይ Win + Ctrl + Shift + B ቁልፎችን በአንድ ላይ ይጫኑ። ​ምልክቱ፦ ስክሪኑ ለአንድ ቅጽበት ጥቁር ሆኖ ድምፅ (Beep) ካሰማ በኋላ ወዲያውኑ ተመልሶ ይነሳል። ​ጥቅሙ፦ ኮምፒውተሩ የግራፊክስ ሲስተሙን እንደ አዲስ ስለሚቀሰቅሰው የሰሩትን ፋይል ሳያጡ ስራዎን መቀጠል ያስችልዎታል። ​#WindowsHacks #PCShortcuts #ComputerTroubleshoot #TechBasics ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​📶 የWi-Fi ይለፍ ቃል (Password) ሲረሳ በስልክ በቀላሉ ማግኛ ዘዴ ​የተገናኘንበትን የቤት ወይም የቢሮ ዋይፋይ ፓስወርድ ረስትን ለሌላ ሰው ማጋራት ስንፈልግ፦ ​QR Code ማውጣት፦ የስ
​📶 የWi-Fi ይለፍ ቃል (Password) ሲረሳ በስልክ በቀላሉ ማግኛ ዘዴ ​የተገናኘንበትን የቤት ወይም የቢሮ ዋይፋይ ፓስወርድ ረስትን ለሌላ ሰው ማጋራት ስንፈልግ፦ ​QR Code ማውጣት፦ የስልክዎን Settings > Wi-Fi ውስጥ ገብተው የተገናኙበትን ኔትወርክ ስም ሲጫኑ QR Code ያመጣላችኋል። ​ለሌላ ሰው ለማጋራት፦ ሁለተኛው ስልክ የካሜራውን ስካነር ከፍቶ ይሄንን QR Code ሲያነበው ያለምንም ፓስወርድ በቀጥታ ይገናኛል። ​ፓስወርዱን ጽሑፍ ለማየት፦ የQR ኮዱን ስክሪንሾት በማንሳት በ Google Lens ወይም በማንኛውም QR Scanner ስካን ሲያደርጉት ትክክለኛውን የይለፍ ቃል ከስር ጽፎ ያሳያል። ​#WiFiHacks #AndroidTips #TechTricks #InternetTips ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​🔒 ብሉቱዝ (Bluetooth) ሁልጊዜ ክፍት መተው የሚያመጣው አደጋ ​ብሉቱዝን ሳንጠቀምበት ክፍት ትተን በህዝብ መሃል ስንንቀሳቀስ ስልካችን በቀላሉ ሊጠለፍ ይችላል። ​Bluebugging ጥቃት፦
​🔒 ብሉቱዝ (Bluetooth) ሁልጊዜ ክፍት መተው የሚያመጣው አደጋ ​ብሉቱዝን ሳንጠቀምበት ክፍት ትተን በህዝብ መሃል ስንንቀሳቀስ ስልካችን በቀላሉ ሊጠለፍ ይችላል። ​Bluebugging ጥቃት፦ ሀከሮች በክፍት ብሉቱዝ በኩል ወደ ስልክዎ ሰርገው በመግባት የደዋይ ዝርዝርዎን፣ መልዕክቶችዎን አልፎ ተርፎም የስልኩን ጥሪዎች ማዳመጥ ይችላሉ። ​ባትሪ ማባከን፦ ክፍት የሆነ ብሉቱዝ በአካባቢው ያሉ ሌሎች መሳሪያዎችን ያለማቋረጥ ስለሚፈልግ ባትሪን በፍጥነት ይጨርሳል። ​መፍትሄው፦ ከጆሮ ማዳመጫ ወይም ከስፒከር ጋር ተጠቅመው ሲጨርሱ ወዲያውኑ ብሉቱዝን የማጥፋት ልምድ ይኑርዎት። ​#MobileSecurity #BluetoothHacks #CyberSafety #TechTips ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​🕵️ የካሜራ እና ማይክሮፎን ፈቃድ (App Permissions) መፈተሽ ​የሚያወርዷቸው ቀላል ጨዋታዎች ወይም የፎቶ አፖች ከጀርባ ድምጽዎን እንዳይቀዱ ጥንቃቄ ያድርጉ። ​የችግሩ መነሻ፦ ለምሳሌ ቀ
​🕵️ የካሜራ እና ማይክሮፎን ፈቃድ (App Permissions) መፈተሽ ​የሚያወርዷቸው ቀላል ጨዋታዎች ወይም የፎቶ አፖች ከጀርባ ድምጽዎን እንዳይቀዱ ጥንቃቄ ያድርጉ። ​የችግሩ መነሻ፦ ለምሳሌ ቀላል የፍላሽ (Torch) አፕሊኬሽን የእርስዎን ካሜራ፣ ማይክሮፎን እና የስልክ አድራሻ (Contacts) መጠቀም ለምን አስፈለገው? ​እንዴት ይፈተሻል?፦ የስልክዎ Settings > Privacy > Permission Manager ውስጥ ይግቡ። ​ማጣራት፦ ማይክሮፎን እና ካሜራ የሚጠቀሙ አፖችን ዝርዝር ይመልከቱ፤ የማያስፈልጋቸውን "Don't allow" የሚለውን በመጫን ፈቃዳቸውን ይንፈጓቸው። ​#PrivacyProtection #AndroidSecurity #DataPrivacy #CyberSecurity ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

🖼️ የፎቶዎችን የጀርባ ገጽታ (Background) ያለ ምንም አፕሊኬሽን የማጥፊያ ዘዴ ​የመታወቂያ ፎቶ ለመስራት ወይም ለግራፊክስ ስራ የፎቶን የጀርባ ክፍል ለማጥፋት ምንም አይነት አፕሊኬሽን መጫ
🖼️ የፎቶዎችን የጀርባ ገጽታ (Background) ያለ ምንም አፕሊኬሽን የማጥፊያ ዘዴ ​የመታወቂያ ፎቶ ለመስራት ወይም ለግራፊክስ ስራ የፎቶን የጀርባ ክፍል ለማጥፋት ምንም አይነት አፕሊኬሽን መጫን አያስፈልግዎትም። ​ቀላሉ መንገድ፦ ስልክዎ ወይም ኮምፒውተርዎ ላይ ብራውዘር ከፍተው remove.bg የሚለውን ድረ-ገጽ ይክፈቱ። ​አሰራሩ፦ "Upload Image" የሚለውን ነክተው ፎቶዎን ሲያስገቡ ድረ-ገጹ በ AI ታግዞ በ 5 ሰከንድ ውስጥ ጀርባውን አጥፍቶ ንጹህ PNG ፎቶ ያዘጋጅልዎታል። ​ጥቅሙ፦ ምንም ክፍያ አይጠይቅም፤ የፎቶውን ጥራት ሳይቀንስ በቀጥታ ዳውንሎድ ማድረግ ያስችላል። ​#TechHacks #PhotoEditing #GraphicDesign #OnlineTools ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​🔐 ስልክዎን ለህፃናት ሲሰጡ አላስፈላጊ ነገሮች እንዳይነኩ የማገጃ ዘዴ (Guided Access / Guest Mode) ​ህፃናት ዩቲዩብ ወይም ጨዋታ እንዲጫወቱ ስልክዎን ሲሰጡ ፋይል እንዳያጠፉ ወይ
​🔐 ስልክዎን ለህፃናት ሲሰጡ አላስፈላጊ ነገሮች እንዳይነኩ የማገጃ ዘዴ (Guided Access / Guest Mode) ​ህፃናት ዩቲዩብ ወይም ጨዋታ እንዲጫወቱ ስልክዎን ሲሰጡ ፋይል እንዳያጠፉ ወይም ወደ ሌላ ቦታ እንዳይገቡ ይህን ያድርጉ፦ ​Samsung ስልኮች ላይ፦ Settings > Modes and Routines ወይም Samsung Kids የሚለውን ያብሩ፤ የተወሰኑ ጨዋታዎችን ብቻ እንዲጫወቱ ይፈቅዳል። ​ሌሎች አንድሮይድ ስልኮች፦ Settings > Users & accounts > Multiple users ገብተው "Guest" የሚለውን መርጠው ይስጧቸው። ​ጥቅሙ፦ በእንግዳ (Guest) ገጽ ላይ የእርስዎ ፎቶዎች፣ የባንክ አፖች እና መልዕክቶች በሙሉ ስለሚደበቁ ስልክዎ ፍጹም ደህንነቱ የተጠበቀ ይሆናል። ​#AndroidTips #ParentalControl #MobileSecurity #TechTips ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​🌐 የድረ-ገጾች ይለፍ ቃል (Password) በኮምፒውተር ላይ ሲረሳ በቀላሉ ማግኛ ዘዴ ​ቀደም ሲል ክሮም (Chrome) ላይ ያስገቧቸውን ነገር ግን የረሷቸውን የፌስቡክ ወይም የኢሜይል የይለፍ ቃ
​🌐 የድረ-ገጾች ይለፍ ቃል (Password) በኮምፒውተር ላይ ሲረሳ በቀላሉ ማግኛ ዘዴ ​ቀደም ሲል ክሮም (Chrome) ላይ ያስገቧቸውን ነገር ግን የረሷቸውን የፌስቡክ ወይም የኢሜይል የይለፍ ቃላት ለማየት፦ ​የሚገኝበት ቦታ፦ ጎግል ክሮም ከፍተው ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ይጫኑ፤ ከዚያም Settings > Autofill and passwords > Password Manager ውስጥ ይግቡ። ​ማየት፦ የረሱትን ድረ-ገጽ ስም ፈልገው ሲጫኑ ከፓስወርዱ ጎን ያለችውን የአይን ምልክት (Eye icon) ይጫኑ። ​ማረጋገጫ፦ የኮምፒውተርዎን የከፈቱበትን ፒን (Windows PIN) ሲያስገቡ የተደበቀውን ፓስወርድ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ​#ChromeTips #PasswordManager #PCBasics #TechHacks ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​⚡ የስልክ ቻርጀር ገመድ ቶሎ እንዳይበጠስ የሚረዳ ቀላል ብልሃት ​የአብዛኛው ሰው ቻርጀር የሚበላሸው ጫፉ አካባቢ በመታጠፍ እና ሽቦው በመላጥ ነው። ​የችግሩ መነሻ፦ ስልኩ ቻርጅ እያደረገ ገመዱን
​⚡ የስልክ ቻርጀር ገመድ ቶሎ እንዳይበጠስ የሚረዳ ቀላል ብልሃት ​የአብዛኛው ሰው ቻርጀር የሚበላሸው ጫፉ አካባቢ በመታጠፍ እና ሽቦው በመላጥ ነው። ​የችግሩ መነሻ፦ ስልኩ ቻርጅ እያደረገ ገመዱን አጥፎ መጠቀም ወይም ገመዱን ሲነቅሉ ከጭንቅላቱ ይልቅ ከሽቦው ጎትቶ ማውጣት ነው። ​ቀላል መከላከያ፦ ያገለገለ እስክሪብቶ ውስጥ የሚገኘውን ትንሽ ጸደይ (Spring) አውጥተው በቻርጀሩ ጫፍ ሽቦ ላይ ይጠምጥሙት። ​ውጤቱ፦ ጸደዩ ገመዱ እንዳይታጠፍ እና እንዳይሰበር አጥብቆ ስለሚይዘው የቻርጀሩን እድሜ ለረጅም ጊዜ ያራዝመዋል። ​#TechHacks #LifeHacks #SmartphoneCare #HardwareTips ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​🔋 ስልክዎ ሳያውቁት ቶሎ ቶሎ እንዲሞቅ የሚያደርጉ 3 ስህተቶች ​ስልክ ከመጠን በላይ መሞቅ የሲፒዩ (Processor) እና የባትሪን እድሜ በከፍተኛ ፍጥነት ይቀንሳል። ​ከነሽፋኑ ቻርጅ ማድረግ፦
​🔋 ስልክዎ ሳያውቁት ቶሎ ቶሎ እንዲሞቅ የሚያደርጉ 3 ስህተቶች ​ስልክ ከመጠን በላይ መሞቅ የሲፒዩ (Processor) እና የባትሪን እድሜ በከፍተኛ ፍጥነት ይቀንሳል። ​ከነሽፋኑ ቻርጅ ማድረግ፦ ወፍራም የላስቲክ ወይም የቆዳ ከቨር (Cover) ሙቀቱ ወደ ውጭ እንዳይወጣ አፍኖ ስለሚይዘው ቻርጅ ሲያደርጉ አውልቀው ማስቀመጥ ይመረጣል። ​ደካማ ኔትወርክ ባለበት ቦታ ዳታ ማብራት፦ ስልኩ ደካማ ሲግናል ሲያገኝ አንቴናው በሙሉ አቅሙ ኔትወርክ ለማደን ስለሚሞክር ከፍተኛ ሙቀት ያመነጫል። ​ፀሐይ ላይ ማስቀመጥ፦ በተለይ በመኪና ዳሽቦርድ ላይ ወይም መስኮት አጠገብ ቀጥታ ፀሐይ የሚያርፍበት ቦታ ስልክን መተው ውስጣዊ ሰርከቱን ሊያበላሽ ይችላል። ​#SmartphoneTips #Overheating #MobileCare #AndroidTips ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​🛑 Wi-Fi እየተጠቀሙ "No Internet Access" ካለዎት ፈጣን መፍትሄ ​ዋይፋይ ተገናኝቶ ነገር ግን ቢጫ አጋኖ አሳይቶ ኢንተርኔት ካልሰራ ችግሩን በኮምፒውተር በሰከንዶች ውስጥ ማስተካከል
​🛑 Wi-Fi እየተጠቀሙ "No Internet Access" ካለዎት ፈጣን መፍትሄ ​ዋይፋይ ተገናኝቶ ነገር ግን ቢጫ አጋኖ አሳይቶ ኢንተርኔት ካልሰራ ችግሩን በኮምፒውተር በሰከንዶች ውስጥ ማስተካከል ይቻላል፦ ​Command Prompt መክፈት፦ ዊንዶውስ ሰርች ላይ cmd ብለው ፈልገው "Run as administrator" በማለት ይክፈቱት። ​DNS ማጽዳት፦ ipconfig /flushdns ብለው ጽፈው Enter ይበሉ፤ የተጨናነቀውን የድሮ የኔትወርክ አድራሻ ያጸዳል። ​IP ሪሴት ማድረግ፦ በመቀጠል netsh winsock reset ብለው አስገብተው ኮምፒውተሩን Restart ያድርጉት፤ የኔትወርክ ሲስተሙን ሙሉ ለሙሉ አድሶ ኢንተርኔቱን ያስጀምረዋል። ​#Networking #WiFiTroubleshoot #WindowsHacks #ITSupport ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​🔐 ስልክዎ ሳይከፈት (Locked ሆኖ) ሚስጥራዊ መልዕክቶች ስክሪን ላይ እንዳይታዩ ማድረጊያ ​ስልክዎ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ ሳለ የሚላኩልዎ የቴሌግራም፣ የዋትስአፕ ወይም የባንክ መልዕክቶች ማንም
​🔐 ስልክዎ ሳይከፈት (Locked ሆኖ) ሚስጥራዊ መልዕክቶች ስክሪን ላይ እንዳይታዩ ማድረጊያ ​ስልክዎ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ ሳለ የሚላኩልዎ የቴሌግራም፣ የዋትስአፕ ወይም የባንክ መልዕክቶች ማንም ሰው እንዳያነብባቸው፦ ​አሰራሩ፦ የስልክዎ Settings > Notifications > Lock screen notifications ውስጥ ይግቡ። ​ቅንብሩን መቀየር፦ "Show content" ከሚለው ይልቅ "Hide content" የሚለውን ይምረጡ። ​ውጤቱ፦ ስልኩ ሲቆለፍ ማሳወቂያው ብቻ ይመጣል እንጂ በውስጡ የተጻፈው ጽሑፍ ወይም መልዕክት የሚታየው እርስዎ ስልኩን በጣት አሻራ ወይም በይለፍ ቃል ሲከፍቱት ብቻ ይሆናል። ​#PrivacyTips #AndroidSecurity #MobileHacks #TechSafety ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

​⌨️ ኮምፒውተር ላይ የኢሞጂ (Emoji) ሰሌዳ በቀላሉ ማምጫ መንገድ ​በኮምፒውተር እየጻፉ ቴሌግራም ወይም ፌስቡክ ላይ እንዳለው በቀላሉ ኢሞጂዎችን መጠቀም ይፈልጋሉ? ​አቋራጭ ቁልፍ (Shortcu
​⌨️ ኮምፒውተር ላይ የኢሞጂ (Emoji) ሰሌዳ በቀላሉ ማምጫ መንገድ ​በኮምፒውተር እየጻፉ ቴሌግራም ወይም ፌስቡክ ላይ እንዳለው በቀላሉ ኢሞጂዎችን መጠቀም ይፈልጋሉ? ​አቋራጭ ቁልፍ (Shortcut)፦ በኪቦርዱ ላይ Windows Key + . (ነጥብ) ወይም Windows Key + ; በአንድ ላይ ይጫኑ። ​የሚመጣው አማራጭ፦ በሰከንዶች ውስጥ የኢሞጂ፣ የGIF እንዲሁም የተለያዩ የሂሳብ እና የቋንቋ ምልክቶች (Symbols) ዝርዝር ይመጣላችኋል። ​ጥቅሙ፦ ጽሑፍ በምትጽፉበት በማንኛውም ቦታ (Word፣ Browser፣ Telegram) ላይ በቀጥታ ይሰራል፤ ኮፒ ፔስት ማድረግ አይጠበቅባችሁም። ​#WindowsTips #PCShortcuts #TechHacks #ComputerTips ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

🔍 Google ላይ የፈለጉትን መረጃ በቀጥታ የማግኛ 3 የፍለጋ ዘዴዎች ​ጎግል ላይ የሆነ ነገር ሲፈልጉ አላስፈላጊ ገጾች እንዳይመጡ እና ጊዜ እንዳይባክን እነዚህን ምልክቶች ይጠቀሙ፦ ​ጥቅስ ምልክ
🔍 Google ላይ የፈለጉትን መረጃ በቀጥታ የማግኛ 3 የፍለጋ ዘዴዎች ​ጎግል ላይ የሆነ ነገር ሲፈልጉ አላስፈላጊ ገጾች እንዳይመጡ እና ጊዜ እንዳይባክን እነዚህን ምልክቶች ይጠቀሙ፦ ​ጥቅስ ምልክት (" ")፦ የተወሰነ ቃል ወይም ሀረግ ልክ እንዳለ እንዲፈልግልዎት በጥቅስ ውስጥ ያስገቡት፤ ለምሳሌ "cyber security ethiopia" ብለው ከጻፉ ሁለቱ ቃላት ተከታትለው ያሉበትን ገጽ ብቻ ያመጣል። ​ፋይል አይነት (filetype:pdf)፦ መጽሐፍት ወይም ጥናታዊ ጽሑፎችን በቀጥታ ለማውረድ ከፈለጉ ከርዕሱ ቀጥሎ filetype:pdf ብለው ይጻፉ፤ ድረ-ገጾችን ዘሎ የወረደ የ PDF ፋይል ብቻ ያመጣል። ​የተወሰነ ድረ-ገጽ ውስጥ ብቻ ለመፈለግ (site:)፦ ለምሳሌ ቴሌግራም ላይ የተጻፈ ነገር ለመፈለግ ከፈለጉ site:t.me networking ብለው በመጻፍ ከቴሌግራም ውጭ ያሉትን ድረ-ገጾች በሙሉ ማግለል ይቻላል። ​#GoogleSearch #SearchTricks #ProductivityTips #TechHacks ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

📲 ስልክ ውሃ ውስጥ ከገባ ሩዝ ውስጥ መክተት ትክክል ነው? ​ብዙ ሰዎች ስልካቸው ውሃ ሲገባ ወዲያው ሩዝ ውስጥ ይከቱታል፤ ይህ ግን የሚጠቅመው ሳይሆን የሚጎዳው ያመዝናል። ​እውነታው፦ ሩዝ እርጥበ
📲 ስልክ ውሃ ውስጥ ከገባ ሩዝ ውስጥ መክተት ትክክል ነው? ​ብዙ ሰዎች ስልካቸው ውሃ ሲገባ ወዲያው ሩዝ ውስጥ ይከቱታል፤ ይህ ግን የሚጠቅመው ሳይሆን የሚጎዳው ያመዝናል። ​እውነታው፦ ሩዝ እርጥበትን የመምጠጥ አቅሙ በጣም አዝጋሚ ነው። በተጨማሪም የሩዙ ዱቄት እና ትናንሽ ፍርፋሪዎች በስልኩ ቻርጀር እና ስፒከር ቀዳዳዎች ውስጥ ገብተው ተጨማሪ ብልሽት ይፈጥራሉ። ​ትክክለኛው እርምጃ፦ ስልኩን ወዲያውኑ ማጥፋት (Turn off) እና ቻርጀር ላይ በፍጹም አለመስካት። ​መፍትሄው፦ በንጹህ ጨርቅ ውጩን በደንብ አድርቆ አየር በሚገባበት ቦታ ወይም በሲሊካ ጄል (Silica Gel - አዳዲስ ጫማዎች ውስጥ ከሚገኘው ነጭ ፓኬት ጋር) ማስቀመጥ። ​#MobileTips #TechMyths #SmartphoneRepair #AndroidTips ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss

⚠️ ስልክዎ ላይ አላስፈላጊ ማስታወቂያዎች (Pop-up Ads) አስቸግረውዎታል? ​ብዙ ጊዜ አፕሊኬሽን ስንከፍት ወይም ኢንተርኔት ስንጠቀም ስክሪኑን የሚሞሉ ማስታወቂያዎች የሚመጡት አደገኛ አፖችን (
⚠️ ስልክዎ ላይ አላስፈላጊ ማስታወቂያዎች (Pop-up Ads) አስቸግረውዎታል? ​ብዙ ጊዜ አፕሊኬሽን ስንከፍት ወይም ኢንተርኔት ስንጠቀም ስክሪኑን የሚሞሉ ማስታወቂያዎች የሚመጡት አደገኛ አፖችን (Adware) በስህተት ስላወረድን ነው። ​Chrome Setting ያጥፉ፦ ጎግል ክሮም ከፍተው Settings > Site Settings > Pop-ups and redirects ገብተው Block ማድረጋቸውን ያረጋግጡ። ​ያልታወቁ አፖችን ያጥፉ፦ Settings > Apps ውስጥ በመግባት ስም የሌላቸውን ወይም አርማቸው (icon) ነጭ የሆነ አጠራጣሪ አፖችን ፈልገው Uninstall ያድርጉ። ​የማይታወቁ ምንጮችን ይገድቡ፦ ከPlay Store ውጭ አፖችን በቀጥታ የሚያወርዱበትን (Install Unknown Apps) ፍቃድ ዝጉ። ​#AndroidTips #TechHacks #MobileSecurity ከተመቻቹ like and share🙏 join us @EthioTechTipss