uz
Feedback
HiTech

HiTech

Kanalga Telegram’da o‘tish

HiTech | Learn. Fix. Create. 📱💻🎨 Your Ethiopian tech hub! We teach: ✅ Smartphone Repair ✅ Laptop & Chip-Level Repair ✅ Graphics & Motion Design ✅ Coding & Web Development ✅ Tools, Tips & Tech Reviews Join the HiTech family — grow your skills & build

Ko'proq ko'rsatish
1 636
Obunachilar
+124 soatlar
+117 kunlar
+2630 kunlar
Postlar arxiv
HiTech
1 635
በኢ-ሜይል አማካኝነት የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን እንዴት መከላከል እንችላለን? የኢ-ሜይል-ፊሺንግ(email phishing) አንዱ የሳይበር ጥቃት መፈጸሚያ ዘዴ ሲሆን ፥ የመረጃ በርባሪዎች ኢላማ ያደረጉትን ሰዉ መረጃ ለመመንተፍ የተለያዩ ይዘት ኖሯቸዉ ለመክፈት የሚያጓጉ አገናኞች(ሊንኮችን)፣ አባሪዎች (attachments) የያዙ መልእክቶች ወደ ተጠቂዉ በመላክ እና እንዲክፍተ በማድርግ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ናቸዉ። ለምሳሌ ትልቅ ሽልማት እንዳሸነፉ የሚገልፁ መልእክቶች ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ይህም የሚከሰተው አንድ አጥቂ የታመነ አካል በመምሰል የተጠቂውን ኢ-ሜይል ፈጣን መልእክት ወይም የጽሑፍ መልእክት እንዲከፍት በማድረግ የሚፈጸሙ ናቸው። ቀጥሎም በከፈተው ኢ-ሜይል ላይ አጥፊ ተልእኮ ባዘሉ አገናኞች አማካኝነት ወደሚፈልጉት አደገኛ ገጽ እንዲገቡ በማድረግ ጠቃሚ ወይም ሚስጥራዊ መረጃ ለአደጋ ይጋለጣል። የፊሺንግ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ ይገባል፡- ✅ ኢንተርኔት ከፍተን ያለፍቃዳችን ብቅ እያሉ እንድንጭናቸዉ የሚጠይቁ ማስታውቂያዎች ዉስጥ በመግባት ሚስጥራዊ መረጃዎችን ከማስገባት መቆጠብ፤ ✅ የግል እና ሚስጥራዊ መረጃዎን እንዲሁም የገንዘብ ነክ መረጃን በበይነመረብ ላይ በጭራሽ አለማጋራት ፤ ✅ የመረጃዎቻችንን መጠባበቂያ (backup) መያዝ መረጃዉ ቢጠፋ ወይም ቢውደም መረጃዎቹን መተካት የሚያስችል ምትክ መጠባበቂያ መያዝ፤ ✅ የሚጠቀሙትን የድረ-ገጽ ደህንነት ማረጋገጥ በመርጃ ማፈላለጊያዉ (browsers) የአድራሻ ባር ላይ (HTTPS) መኖሩን በማየት ማረጋገጥ፤ ✅ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ፋየርዎልን (firewall) መጫን ኮምፒዉተር ላይ አጥፊ ተልእኮ ያላቸዉ ሶፍትዌሮች እንዳይገቡ መከላከላል፤ ✅ የባለብዙ ደረጃ የደህንነት ማረጋገጫ መጠቀም ለምሳሌ የአንድ ጊዜ የይለፍ-ቃል በኤስኤምኤስ መልእክት በኩል የሚገባ፣ physical token፣ የባዮሜትሪክ አይዲ/ID ተግራዊ ማድረግ። ✅ የኦንላይን ላይ መለያዎችዎን በመደበኛነት ይመልከቱ ወይም ያረጋግጡ ለምሳሌ ፡- የይለፍ-ቃሎችን በመደበኛነት መቀየር፣ ✅ የእርስዎን የባንክ ሂሳብ መግለጫዎች/statements/በመደበኛነት ያረጋግጡ ✅ የመርጃ ማፈላለጊያዎን(web browser) ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፤ ✅ አላስፈላጊ የሆኑ የኢሜይል መልዕክትን ማጣራት /Filter Spam/ ✅ የማይታወቁ ወይም አስፋላጊ ያልሆኑ የኢ-ሜይል መልእክቶች ወደ ግልዎ ወይም የድርጅትዎ የመልእክት ሳጥን እንዳይገቡ ማገድ ✅ ሰዋሰዋዊ ስህተቶች እና የፊደል ግድፈቶች ያሉባቸው ድረ-ገፆችን ሁልጊዜ በትኩረት ማየት እና አለመጠቀም። ✅ ያለዎትን ማንኛውንም ሚስጥራዊነት ያለው የግል መረጃ መስጥሮ መያዝ እና ሌሎች መሰል ጥንቃቄዎችን መውሰድ እንደሚገባ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህነንት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ════❁✿❁ ═══════ 📌Telegram channel https://t.me/cellphonetechnology

HiTech
1 635
✍ ከF1 እስከ F12 ያሉ የዊንዶውስ ቁልፎች አገልግሎት በኮምፒውተራችን ኪይቦርደ ከላይ ተደርድረው የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function Key እንላቸዋለን፡፡ በዋናነትም ከሌሎች ቁልፎች ጋር በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡ ━━━━━━━━━━━━━━━━ 📢: @cellphonetechnology ━━━━━━━━━━━━━━━━ ✍ ውድ እና የተከበራችሁ የቻናላችን ተከታታዮች በዛሬው ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡ ➘F1 ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡ ➘F2 የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt + Ctrl + F2 መጫን የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡ ➘F3 ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift + F3 መጫን የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡ ➘F4 አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 መጫን ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡Alt + F4 መጫን አክቲቭ የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4 ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt + F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት ነው፡፡ ➘F5 አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5 መጫን Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡ ➘F6 በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን አቅጣጫ መጠቆሚያ(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን ወደቀጣዩ የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡ ➘F7 ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡ ➘F8 ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ Startup menu ለመግባት የጠቅማል፡፡ ➘F9 በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን CTRL + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { } ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ ለማጥፋት ➘F10 አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን ራይት ክሊክ እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡ ➘F11 በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን ስክሪን ይሞላዋል (Full screen)፡፡ ➘F12 ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ የ Save as መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡ ✍ ⚠️ ሁላችሁም ለጓደኛዎ #share ማድረጎን አይርሱ። ©━━━━━━━👇🏽👇🏽━━━━━━© 📢: @cellphonetechnology

HiTech
1 635
Repost from HiTech
All mobile phone flash file available for only 1500 birr Samsung Tecno Infinix Nokia Huawei Itel Iphone and others More than 1.2 TB file 0922888396

HiTech
1 635
Repost from HiTech
1 TB transcend hard disk With full flash file / firmware Samsung Huawei Itel Tecno Infinix Iphone and others 4500 birr Inbox
1 TB transcend hard disk With full flash file / firmware Samsung Huawei Itel Tecno Infinix Iphone and others 4500 birr Inbox @Tekle21

HiTech
1 635
🔒ፓስዋርድ ሲጠፋን ኮምፒውተራችንን መክፈቻ ዘዴ ================== ✏️የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ መፍትሄ አለው ። ✅የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ወይም "isee password Windows password Recovery pro" ሲሆኑ ሁለትም ከ internet ላይ ማውረድ ትችላላችሁ ነገር ግን isee password windows password recovery pro የሚለውን ገዝታችሁ የምታገኙት ስለሆነ እኛ የገዛንውን ለውድ የቻናላችን ተከታታዮች sofrwarun ከላይ ለቀንላችኋል። 🔒በ "Spotmou Bootsuit.iso ሶፍትዌር ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ:- 🔘ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡ 🔸Step1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን 🔸Step2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡ 🔸Step3: ፍላሹን /ሲዲውን/ ኮመፒዩተሩን ጋር አገናኝተን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) (ለHp ላፕቶፕ F9) መንካት፡፡ 🔸Step4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለውን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡ 🔸Step5: ኮምፒዩተሩ ከተከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡ 🔸Step6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለውን “Menu” እንመርጣለን፡፡ 🔸Step7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡ 🔸Step8: “Please select the target widows” ከሚለው ሼር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/ 10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሼር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለውን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለውን እንጫናለን፡፡ 🔸Step9: መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡ 🔸Step10: ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot). በትክክል 100% ይሰራል። 🔒በ "iSee password windows password recovery Pro" ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ ሶፍትዌሩን ቻናላችን ላይ ለቀንዋል Registered የሆነውን የሚከተለውን step ይከተሉ። 1⃣ ሶፍትዌሩን Download ያድርጉ ። 2⃣ ሌላ Computer ላይ install ያደርጉት 3⃣ ሶፍትዌሩን ስከፍቱት ከላይ በምስል እንደምታዩት ያመጣላችኋል። 4⃣ ባዶ Flash or CD ትከቱና 🔘ፍላሽ ከሆነ የከተታችሁት Create password Reset Usb Flash drive ከሚለው ሾር የፍላሹን ስም መርጣችሁ "Burn Usb" የሚለውን ስነኩት Burn አድጎ ሲጨርስ flashun ትነቅላላችሁ። 5⃣ከዛ በፓስዎርድ የተዘጋብንን ኮምፒዩትራችንን Turn OFF ማድረግ 6⃣ፍላሹን/ሲዲውን/ ከኮምፒዩተራችን ጋር አገናኝተን Turn On ማድረግ ከዛም (F12 ለቶሽባ/ዴል) F9 ለHp Computer (Boot key) መንካት 7⃣ " Boot sequence" የሚል ሲመጣልን " USB" የሚለውን መርጠን "Enter"ን በመንካት ትዕዛዙን መከተል። 8⃣ ኮምፒዩተራችን ከተከፈተ ብኋላ "isee password Windows recover pro" ይከፍትልናል ከአፕልኬሽኑ ላይ ካሉት አማራጭች(Option) ውስጥ "Admin Password Resetter" የሚለውን መንካት ከዛም "yes" የሚለውን እንጫናለን። 9⃣ ትንሽ ከቆየ ብኋላ(max. 2mint) "password is reset Successfully" የሚል መልዕክት ያሳየናል። 🔟 ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot) 👽ፓስዎርዳችሁ ምንም አይነት file/data ሳይጠፋ ተከፈተ ማለት ነው አሁን የሚፈልጉትን password ማድረግ ትችላላችሁ። ❗️ Proof 100% ይሰራል። 🇪🇹 #ኢትዮጵያዊነት_መልካምነት ነው። #እባኮትን #ለ10 ጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈         🗣➹share &Join Us                      👇🏾👇🏾👇🏾 ☄ @cellphoneTechnology       ━ ••• ━ ••• ━━•••━━━

HiTech
1 635
✴️ ኮምፒዩተራችንን በ schedule እንዴት መዝጋት እንችላለን? 🎈አንዳንዴ ትልቅ መጠን ያለውን ፋይል እንዲያወርድ አዘነው አልያም ትልቅ ሶፍትዌር install እያደረግን ከተወሰነ ሰአት በኻላ ኮ
✴️ ኮምፒዩተራችንን በ schedule እንዴት መዝጋት እንችላለን? 🎈አንዳንዴ ትልቅ መጠን ያለውን ፋይል እንዲያወርድ አዘነው አልያም ትልቅ ሶፍትዌር install እያደረግን ከተወሰነ ሰአት በኻላ ኮምፒዩተራችን እንዲዘጋ እንፈልግ ይሆናል። ለምሳሌ ማታ ላይ የሆነ ፋይል ብናዝ እና ከ ሁለት ሰአት በኻላ ፋይሉን አውርዶ ቢጨርስ ከዛ በኻላ እስኪነጋ ሳንዘጋው ብንተወው ለኮምፒዩተር ጤንነት አይመከርም። 🎈ይሄን ችግር ለመቅረፍ ኪይቦርዳችን ላይ የ window + R አንድ ላይ ስንጫን ከሚመጣልን መስኮት ላይ የሚከተለውን ኮማንድ እንጽፋለን። shutdown –s –t number 🎈Number ቦታ ላይ የምንፈልገውን ሰከንድ እንጽፍለታለን። 🎈ለምሳሌ:- shutdown –s –t 3600 ብለን enter ብንለው ከ 1 ሰአት በኻላ ኮምፒተራችን በራሱ ይዘጋል ማለት ነው። 🎈 ሌላው ሀሳባችንን ብንቀይር እና ያዘዝነውን ለማጥፋት ብንፈልግ window + R ተጭነን የሚከተለውን ኮማንድ እንጽፋለን። shutdown –a 🏳️ ከላይ ያለው በዋነኛነት ለ window 10 የሚሰራ ሲሆን በሌሎች window OS ላይም ሊሰራ ይችላል። ════❁✿❁ ═══════

HiTech
1 635
Repost from HiTech
All mobile phone flash file available for only 1500 birr Samsung Tecno Infinix Nokia Huawei Itel Iphone and others More than 1.2 TB file 0922888396

HiTech
1 635
Repost from HiTech
1 TB transcend hard disk With full flash file / firmware Samsung Huawei Itel Tecno Infinix Iphone and others 4500 birr Inbox
1 TB transcend hard disk With full flash file / firmware Samsung Huawei Itel Tecno Infinix Iphone and others 4500 birr Inbox @Tekle21

HiTech
1 635
@cellphoneTechnology ሀይ ጋይስ ዛሬ እምንማማረው በቀላል መንገድ original ስልኮችን እንዴት መለየት እንደምንችል ነው 1. setting ውስጥ መግባት 2. display የሚለውን መምረ
@cellphoneTechnology ሀይ ጋይስ ዛሬ እምንማማረው በቀላል መንገድ original ስልኮችን እንዴት መለየት እንደምንችል ነው 1. setting ውስጥ መግባት 2. display የሚለውን መምረጥ 3. font style እና font size ሁለቱንም በየተራ በመምረጥ የሚቀያይሩ ከሆነ ስልካችሁ በትክክል orignal ነው ከተመቻችሁ like

HiTech
1 635
ብዙ ሰዉ የማያዉቃቸው የጂኤስኤም ሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች! ETHIO ICT 1. ስልክዎ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋቹ! ወደ *21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ! ለምሳሌ ስልክ ቁጥርዎ 0910654321 ከሆነ ወደ *21*091065432# ይደውሉ ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ! ከላይ የተገለጸው በ900 ቦታ የፈለጉት ሌላ ትክክለኛ የስልክ ቁጥር ያልሆነም ማድረግ ይችላሉ! ➜ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ለማድረግ ሲልጉ *21*0144123456# በ0144123456 ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ ስልክ ቁጥር ያስገቡ ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል *#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል 2. ስልክዎ ብዚ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *67*የፈለጉትቁጥር# ብለው ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ 3. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ 4. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ! 5. ኮል ወይቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል ወይቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮልወይቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል 6 ሲደውሉ ስልክ ቁጥርዎ እንዳይታይ ወይም በሌላ ቁጥር ተክተው ለመደወል ሲፈልጉ #31#የሚደውሉት ቁጥር ከዛ መደወል ☞አንዳንድ ስልኮች # 31# ከተደወለ በኀላ የምንደውለውን ቁጥር እናስገባለን በእኛ አገር ኔትዎርክ ላይሰራ ይችላል የሰራላችሁ comment ላይ ንገሩን share ,like በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉ

HiTech
1 635
የብርሀን /ላይት/ ጥገና የብርሃን ችግር በአራት ዋና ዋና ክፍሎች እንከፍለዋለንከፍለዋለን:- 1ኛ ችግር ምንም ብርሀን የሌለው ፣ 2ኛ ችግር ብርሀን ቀኑን ሙሉ የሚያበራ ወይም ምንም የማይጠፍ፣ 3ኛ ችግር ስክሪን ላይ ብርሀን የሌለው ሲሆን፣ 4ኛ ችግር ኪፓድ ላይ ብርሀን የሌለው ስልክ ነዉ፡፡ 1.ምንም ብርሃን የሌለው – በዚህ ጊዜ መጀመሪያ የስልካችንን መቼት /ሴቲንግ/ እናያለን፡፡ ባክላይት ኦፍ ከሆነ ወደ ኖርማል እንመልሰዋለን ፡፡ በመቀጠል ኪፓድ ኮኔክተርን እናያለን እግሮቹ ታጥፈዉ ወይም ተሰብረው ከሆነ ተገቢውን ማስተካከያ እናደርጋለን፡፡ ኮኔክተሮቹ ከቆሸሹ እናጸዳቸዋለን፡፡ ችግሮቹን ለመፍታት እንዲመቸን ዲሲቲ 3 እና ሌሎቹን እንለያቸዉ፡፡ ዲሲቲ 3:- የዲሲቲ 3 ስልኮች ብርሀን ቁጥጥር የሚደረገው በዩአይ አይሲ ነዉ፡፡ ዩአይ አይሲ ሃያ እግሮች አሉት ፡፡ አንደኛው እግር ዩአይ አይሲ ላይ ከሚገኘው ትንሽ ነጥብ አጠገብ ይገኛል፡፡ የዩአይ አይሲ 9ኛዉ እግር የእስክሪናችንን ብርሀን ይቆጣጠራል፡፡ 13ኛዉ እግሩ ደግሞ የኪፓድ ብርሃንን ይቆጣጠራል፡፡ የብርሃን ሰጪ ዳዮዶች / LEDs/ ፓዘቲቭ እግር የዩአይ አይሲ አንደኛ እግር ከባትሪ ፓዘቲቭ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸዉ ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ግንኙነቶች በመልቲ ሜትር ፈልገን የተቋረጡ መንገዶች ካሉት በጃፐር እናገናኛቸዋለን፡፡ ይህንን አድርገን ችግሩ የማይፈታ ከሆነ ችግሩ ያለዉ ዩአይ አይሲ ላይ ስለሆነ ለመቀየር እንገደዳለን ማለት ነዉ፡፡ ዲሲቲ ፎር፣ ደብሊው ዲቱ እና ቢቢ ፍይቭ:- እነዚህ ስልኮች የራሳቸው የሆነ ላይት ድራይቨር አይሲ / ላይት አይሲ/ አላቸው ፡፡ ላይት አይሲ የስልካችንን የብርሃን እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል፡፡ የላይት አይሲን ቦታ ለማግኘት አጠገቡ የሚገኘውን ጥቅል ሽቦ/ ቡስተር ኮይል/ ማየት አለብን፡፡ ይህ ጥቅል ሽቦ ለላይት አይሲ ተገቢውን ቀጥተኛና የማይቀየር ሀይል ለመስጠት ያገለግላል፡፡ ሁለት አይነት ላይት አይሲዎች አሉ ፡፡ 1ኛዉ የአይሲ አይነት እግሮቹ ወደ ዉጪ የመጡ እና በአይናችን ልናያቸዉ የምንችላቸው ናቸዉ፡፡ 2ኛዉ የአይሲ አይነት ደግሞ እግሮቹ ቦርዱ ዉስጥ ሆነዉ ሊታዩ የማይችሉ ናቸዉ፡፡ ሁለቱም የአይሲ አይነቶች 8 እግር አላቸው ፡፡ የአንደኛው አይነት አይሲ እግሮች እና ቡስተር ኮይል ግንኙነት በኮንቲኒቲ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ የአይሲዉ ሁለተኛ እና ሶስተኛ እግር ከቡስተር ኮይል ጋር የተያያዙ ናቸው ፡፡ የአይሲዉ አንደኛው እግር ደግሞ ከባትሪ ፓዘቲቭ ጋር ግንኙነት አላቸው ፡፡ 2.መብራቱ በጭራሽ የማይጠፍ ስልክ የዚህ ችግር ምክኒያት የሚሆነዉ ላይት አይሲዉ ዉስጥ ሾርት ስርኪዉት /ሁለት መገናኘት የሌለባቸው / መስመሮች ሲገናኙ ነዉ፡፡ ስልኩ ዲሲቲ ስሪ ከሆነ ዩአይ አይሲ ይቀየራል፡፡ ስልኩ ዲሲቲ ፎር፣ ደብሊው ዲቱ ወይም ቢቢ ፍይቭ ከሆነ ላይት አይሲዉን መቀየር ብቸኛዉ መፍትሔ ይሆናል፡፡ 3.ስክሪኑ ላይ ብርሃን የሌለው ነገር ግን ኪፓዱ ላይ ብርሃን ያለዉ ስልክ የዚህ ስልክ ችግር ላይት ወይም ቡስተር ኮይል የሚሆንበት አጋጣሚ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ከሁለቱ አንዱ እንኳን መስራት ቢያቆምሌላ ችግር ቢኖርበበት ኪፓዱ ላይ ብርሀን ማየት አንችልም ነበር፡፡ ስለዚህ ችግሩ የሚሆነዉ ከላይ አይሲ እና ከቡስተር ኮይል ወደ ስክሪን የሚወስደው መንገድ ላይ የተቋረጠ መስመር አለ ማለት ነዉ፡፡ ለዚህ ችግር መፍትሔ ሊሆን የሚችለው :- 1. ስክሪኑን በመቀየር መሞከር 1. የተጣመመ ወይም የተሰበረ እግር ካለዉ ማስተካከል 2. ስክሪን ኮኔክተሩን መቀየር @cellphoneTechnology

HiTech
1 635
ተደጋጋሚ የሞባይል ስልክ ችግሮች እና መፍትሔዎች 1. ለሌላ ሰዉ ድምጽ ይሰማል፡፡ ነገር ግን በጣም አነስተኛ ሲሆን ወይም የራቀ ድምጽ ሲሆን 909 ወይም 904 መደወል ♥ጥሪዉ ሲጀምር የድምፅ መጨመሪያ ቁልፍን በመጫን ድምጥን መጨመር ♥ችግሩ ካልተፈታ ስፒከር ቀዳዳን ማፅዳት ♥ከላይ የተገለጡት መንገዶች ካልተፈታ ስፒከሩን መቀየር ይኖርብናል፡፡ 2. የስልካችን ጥሪ ከተወሰኑ ሰከንዶች ወይም ደቂቃዎች በሆአላ ይቋረጣል፡፡ የስልካችን የጥሪ መቼት ላይ የጥሪ ገደብ /ኮል ታይም ሊሚት/Call time limit/ የሚለውን ማጥፍት በተለይ ቻይና ስልክ ላይ auto quick end የሚል መቼትን ማጥፍት፡፡ call record General call setting More Auto quick -end Off 5. የቻይና ስልኮች ላይ ኪፓዱ ላይ ያለዉ ብርሀን ይታያል፣ በተጨማሪም ስክሪኑ ላይ ምስሎች ይታያሉ፡፡ ነገር ግን የስክሪኑ ብርሀን የማይታይ ከሆነ ሁሉም የቻይና ስልኮች ስክሪናቸዉ ላይ ሶስት፣ አራት ወይም አምስት የስክሪን ዳዩድ መስመሮች ይገኛሉ፡፡ እነኝህ መስመሮች ከስክሪኑ ጋር የተበየዱበት ሊድ ሊለቅ ወይም ስክሪኑ ከቦርዱ ጋር የተበየደበት ቦታ ላይ የስክሪን ብርሀን መስመሮች ተላቀዉ ከሆነ በድጋሜ ፔስትና ሊድ በመጠቀም እያንዳንዱን እግር በአግባቡ መበየድ፡፡ 6.Insert SIM የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ሲም ካርዱ የሚሰራ መሆን አለመሆኑን የሚሰራ ስልክ በመጠቀም ማየት የሲም መርገጫ ብረቱን በእጃችን መጫን ሲም ኮኔክተሩን በቲነር ማጠብ 7.እንደ 1110,6030,2600,2610,2310,1600 ያሉ ኖኪያ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲም ተጠቅመን Insert Sim የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ቻርጅ ኮኔክተሩን ማፅዳት ወይም መቀየር ቻርጅ ኢንተርፌስ አካባቢ በቲነር ማፅዳት 8. ባትሪ ሲገባበት ቫይብሬተር የሚያደርግ ከሆነ / ስልኩን ሳናበራዉ ልክ ባትሪ እንደገባበት በራሱ ቫይብሬት የሚያደርግ ከሆነ/ DCT3 ስልክ ከሆነ ዩአይ አይሲን መቀየር ሌሎች ስልኮች ላይ ፓወር አይሲ መቀየር 9.ኔት ወርክ የሌለው ስልክ አንቴና ኢንተርፌስ ወይም ከቦርዱ ጋር በአግባቡ መግጠሙን ማረጋገጥ ቦርዱን በቲነር ማጠብ አንቴና ስዊቹን ማሞቅ ኔትወርኩ አሁንም ካልተስተካከለ ደግሞ አንቴና ስዊች መቀየር 10. እኔ የምናገረው ይሰማል ሌላ ሰዉ የሚናገረዉ አይሰማኝም ስፒከሩን መቀየር 11.ሰዉ የሚያወራው የሚሰማ ከሆነ ነገር ግን እኛ የምናወራው የማይሰማ ከሆነ ማይኩን መቀየር 12.ወጭ ጥሪ ያደርጋል ነገር ግን አይቀበልም ኮል ዳይቨርት በርቶ ከሆነ ማጥፍት 13.ከቁጥሮቹ መካከል አንዱ ብቻ ተነጥሎ የማይሰራ ከሆነ ቁጥሩ ላይ የሚያርፈዉን አልሙኒየም ማፅዳት 14.ተንሸራታች ስልክ ላይ ያሉት ቁልፎች አይሰሩም ፣ከታች ያሉት ቁጥሮች በሙሉ ይሰራሉ ኬብል መቀየር 15.የምን ሰማዉ ድምጽ ይንጫጫል/ ከሌላ ሰዉ ጋር ስንነጋገር/ ስፒከር መቀየር 16.ቁጥሮች መደዳ የማይሰሩ ከሆነ ኪፓድ አይሲን ምሞቅ ወይም መቀየር 17.ስልኩ ክፍለሃገር ሲሄድ ኔትወርኩ አይሰራም ኔትወርክ ፊልተሩን መቀየር 18.ይሰራ የነበረ ሳምሰንግ ስልክ ኔትወርኩ ሲጠፋ ወይም ያልተለመደ ባህሪ ሲአሳይ ( ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት ፣ ሳይወድቅ እና ዉሀ ሳይገባበት)፡፡ *2767*2878# በመጫን ስልኩን ፎርማት ማድረግ ይቻላል፡፡ 19.ስልክ ስናወራ የቁልፍ መጫን ድምፅ ይሰማናል/ ሳንነካዉ በራሱ ቁጥር ይደረድራል/ ኪፓድ አይሲን መቀየር 20.ኔትወርክ ሙሉ ሁኖ ልክ ስንደዉል ኔትወርኩ ዜሮ ይሆናል ፓወር አምፕሊፋየሩን ማሞቅ ወይም መቀየር @cellphoneTechnology

HiTech
1 635
📌 አልፎ አልፎ አሪፍ የሚባሉ የቴሌግራም ቦቶችን/bot/ እለቅላችኋለው። ❖ 6 ምርጥ ቦቶች/bots/ ① @AppFollowBot ►የምትፈልጉትን ለ"iphone" የሚሆን አፕልኬሽን በቴሌግራም ለማወረድ ከፈለጉ Appstore ከመፈለግ... ② @LinkToFilesBot ►ቪዶ/video,ሶፍቴር/Software የምትፈልጉትን ነገር ከቴሌግራም ላይ ወስደው በምትፈልጉት የዳውንሎ መተግበሪያ ማውረድ ከፈለጉ ለምሳሌ በ (IDM - Internet Download Manager) ③ @apkdl_bot ►የምትፈልጉትን ለ"Android" የሚሆን አፕልኬሽን በቴሌግራም ለማወረድ ከፈለጉ playstore አልሰራ ላላችሁ... ④ @BotListBot ►የምትፈልጉትን ቦት ለማግኘት ቴሌግራም ላይ ያሉትን ከ>60% ከነጥቅማችው ያገኛሉ። ⑤ @TextMagicBot ►በሚያምር ሁኔታ የቻናላችሁን ስም ወይም ስማችሁን በተለያየ ፎንት (🅕🅞🅝🅣,ʇuoɟ,𝓕𝓸𝓷𝓽..) ለመፃፍ ከፈለጉ ⑥ ►እኛን ለማግኘት እና ጥያቄ ካሎት ይህን ይጠቀሙ። 🇪🇹 #ኢትዮጵያዊነት_መልካምነት ነው። #እባኮትን #ለ10 ጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈         🗣➹share &Join Us                      👇🏾👇🏾👇🏾 ☄ @cellphoneTechnology       ┗━ ••• ━ ••• ━━•••━━━┛

HiTech
1 635
📲 ብቅ የሚሉ ማስታወቂያዎችን እንዴት ነው ልናስቆማቸው የምንችለው? 💢ቀለል ያሉ #ሁለት(2) መንገዶችን ልጠቁማቹ #1ኛው_መንገድ: 1⃣. Chrome ብራውዘራችሁን ክፈቱ እና #Settings መግባት 2⃣. Settings ውስጥ ስትገቡ ከሚመጡ አማራጮች መካከል Site Settings የሚለውን መምረጥ 3⃣. Site Settings ውስጥ ስትገቡ ከሚመጡ አማራጮች መካከል Pop-ups and redirects የሚለውን ክሊክ ማድረግ 4⃣. Pop-ups and redirects የሚለው ሲመጣ ሁለት አማራጮች ይመጣሉ እነሱም -ON እና OFF 5⃣. OFF የሚለውን መምረጥ፡፡በቃ ካሁን በሃላ አስሬ ብቅ እያሉ የሚበጠብጣችሁ ማስታወቂያዎች ይጠፋሉ።👍 🔆2ኛው_መንገድ:- Turn On the Data Saver - እዚያው የምትጠቀሙበት ክሮም ብራውዘር ላይ ዳታ ሴቨር (Data Saver) #On ለማድረግ፦ 1⃣. Chrome ብራውዘራችሁን ክፈቱ እና Settings ውስጥ መግባት 2⃣. Settings ውስጥ ስትገቡ ከሚመጡ አማራጮች መካከል Data Saver የሚለውን መምረጥ 3⃣. Data Saver የሚለው ሲመጣ ሁለት አማራጮች ይመጣሉ እነሱም -ON እና OFF 4⃣. -ON የሚለውን መምረጥ በቃ አለቀ፡፡👍 🌍🌍🌍🌎🌎🌏🌎🌏🌎🌏🌏🌍🌍🌍 📌መረጃዎችን ለወዳጅዎ 🗣👥 ያጋሩ። 📥መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #MUTE(🔇🔕) ያደረጋችሁት #UNMUTE(🔊🔔) በማድረግ ተባበሩን ®⌚️📱💻⌨🖥🖨💽📀🖨🖥⌨💻📲⌚️® 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 🖥 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

HiTech
1 635
1 TB transcend hard disk With full flash file / firmware Samsung Huawei Itel Tecno Infinix Iphone and others 4500 birr Inbox
1 TB transcend hard disk With full flash file / firmware Samsung Huawei Itel Tecno Infinix Iphone and others 4500 birr Inbox @Tekle21

HiTech
1 635
እንዴት ከሌላ ስልክ📲 ላይ ቻርጅ #ማስተላለፍ እንደሚቻል ያውቃሉ! ስልካችንን📲 እንዴት ከሌላ ስልክ ላይ ቻርጅ ማድረግ እንችላለን? #አስፈላጊ ነገሮች⬇️⬇️⬇️ ✅ሌላኛው ስልክ ✅OTG ✅data cable 1⃣. አሰራር፦ ኬብሉን #OTG ላይ ይሰኩና በቀላሉ #OTG ያለበትን ጫፍ ቻርጅ ሰጪው ስልክ📲 ላይ ይሰኩት። 2⃣. ሌላኛውን ጫፍ ቻርጅ ማድረግ የሚፈልጉት ስልክ ላይ ይሰኩት።

HiTech
1 635
All mobile phone flash file available for only 1500 birr Samsung Tecno Infinix Nokia Huawei Itel Iphone and others More than 1.2 TB file 0922888396

HiTech
1 635
blower used in a good condition with sildering iron 6500 birr

HiTech
1 635
photo content

HiTech
1 635
photo content