cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የኛ ጤና

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ይህ የቴሌግራም ቻላን የተከፈተበት አላማ ጤና ነክ የሆነ መረጃ የሚዳስስ የምንወያይበት ክፍት መድረክ መሆኑን ስገልፅላችሁ በደስታ ነው ጥያቄ መጠየቅና ያልገባዎት ማብራሪያ የሚጠይቁበት ክፍት መሆኑን እገልፃለሁ። https://t.me/+-chQVGVC8mRmYTE0

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
21 252
Obunachilar
-1124 soatlar
-677 kunlar
-32230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Repost from N/a
እርግዝና ሊፈጠር የሚችልባቸውን ቀኖች ታውቂያለሽ? ሰላም ውድ የገፃችን ተከታታዮች ዛሬ ይዘን ለመቅረብ የሞከርነው የወር አበባን መሠረት ያደረገ እርግዝና ሊፈጠርና ላይፈጠር የሚችሉባቸውን ቀናቶች ለይተን ለማወቅ የሚረዳ ግንዛቤ ለመፍጠር ሲሆን ይህ መረጃ በማወቅ ደረጃ ብቻ ቢሆንና ወደ ተግባሩ ለመሄድ አደጋ እንዳለው ከወዲሁ እንድትገነዘቡ ስንል መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ በትክክል እርግዝና ሊፈጠርበት የሚችሉት ቀናቶች ኦቪውሌሽን በሚከናወንበት ቀናቶች ናቸው፡፡ ኦቪውሌሽን (Ovulation) የሚከሰትበት ቀን አንዲት ሴት ልጅ የወር አበባ ካየችበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ14ኛው ቀን አካባቢ ይከሰታል፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ የማርገዝ ዕድል የሚኖርባቸው ቀኖች ከወር አበባ በኋላ ባሉ ከ8-10 ቀኖች ነው (የወር አበባዎ ለመቆም ከ4-6 ቀኖች የሚፈጅበት ከሆነ)፡፡ ነገር ግን ረዘም ያለ የወር አበባ ጊዜ ካለሽ ኦቪውሌሽን የሚከሰትበት ጊዜ ስለሚረዝም የወር አበባሽን የጊዜ ቆይታ ማወቅ አለብሽ። ☑️ የሚከተለው መረጃ ከወር አበባ በኋላ እርግዝና የሚፈጠርባቸውን ቀኖች የሚያሳይ ሲሆን መሰረት ያደረገው በየ 28 ቀን የወር አበባዋን ለምታይ ሴት ብቻ ነው፡፡ 🔸 ከቀን 1-5 (የወር አበባ ከፈሰሰበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ አምስተኛው ቀን) = የወር አበባ መፍሰሻ ጊዜ ነው፡፡ (Menstrual Bleeding) 🔸 ከቀን 6-9 = በንጽጽር እርግዝና የማይፈጠርበት ጊዜ ነው፡፡ (Relatively Infertile) 🔸 ከቀን 10-12 = በንጽጽር በነዚህ ቀኖች እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ (Relatively Fertile) 🔸 ከቀን 13-15 = በነዚህ ቀኖች በእርግጠኝነት እርግዝና ይፈጠራል፡፡ (Most Fertile) 🔸 ከቀን 16-19 = በንጽጽር በነዚህ ቀኖች እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፡፡ (Relatively Fertile) 🔸 ከቀን 20-28 = በነዚህ ቀኖች እርግዝና አይፈጠርም፡፡ (Infertile) ☑️ ማስታወሻ ትክክለኛው የኦቪውሌሽን ጊዜ የሴት እንቁላል የወንድ የዘር ፍሬን ዝግጁ ሁኖ የሚጠብቅበት ጊዜ ሲሆን ይህም ጊዜ ከ 12 – 24 ሠዓት ብቻ ይረዝማል፡፡ ምክንያቱም የወንድ የዘር ፍሬ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ በሴት ሰውነት ውስጥ ከሶስት (3) እስከ አምስት (5) ቀናቶች መቆየት ይችላል የሴቶች ዕንቁላል ደግሞ ለተጨማሪ ቀናቶች ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ልታረግዢ የምትችይው ከ አምስት(5) እስከ ሰባት (7) የሚደርሱ ቀኖች አሉሽ ማለት ነው፡፡ መልካም ጤንነት!! https://t.me/+9-8fYhrqMelmZTRk
Hammasini ko'rsatish...
Health

Happiness is the highest form of health.

👍 13
👍 5
#በበረሮ የተቸገራቹሁ በሙሉ ፍቱን የተቀመመ የበረሮ ማጥፊያ እኔጋ ይገኛል እስከነእንቁላሉ ጠራርጎ ያጠፋል ግልግል ብለዉ ይመሰክሩለታል delivery በነፃ እንቀራረባለን በ 09 38 48 34 22 ደውሉልኝ ወስደዉ አስተያየት ከሰጡት በጥቂቱ
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
#በበረሮ የተቸገራቹሁ በሙሉ ፍቱን የተቀመመ የበረሮ ማጥፊያ እኔጋ ይገኛል እስከነእንቁላሉ ጠራርጎ ያጠፋል ግልግል ብለዉ ይመሰክሩለታል delivery በነፃ እንቀራረባለን በ 09 38 48 34 22 ደውሉልኝ ወስደዉ አስተያየት ከሰጡት በጥቂቱ
Hammasini ko'rsatish...
Repost from N/a
የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠርበዎት 1. በቂ ውሀ ይጠጡ። 2. የጨው መጠን ይቀንሱ። 3. የሶድየም መጠን የበዛባቸውን የምግብ አይነቶች ይቀንሱ። 4. አሳ አዘውትረው ይጠቀሙ። 5. በቂ ሎሚና ብርቱካን ይጠቀሙ። 6. አቾሎኒ፣ ብስኩት፣ ከረሚላና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን ይቀንሱ። 7. የካልሽየም መጠን ያመጣጥኑ። 8. ብዙ ስጋ አይጠቀሙ። 9. የታሸጉና የተቀነባበሩ ምግቦችን አብዝተው አይጠቀሙ። 10. አትክልትና ፍራፍሬ ያዘውትሩ። https://t.me/+9-8fYhrqMelmZTRk
Hammasini ko'rsatish...
Health

Happiness is the highest form of health.

🥰 4👍 3 2
Repost from N/a
የደም ማነስ የደም ማነስ ቀላል በሽታ ሊመስለን ይችላል!!! ይህም አብዛኞቻችን ወደ ህክምና ተቋም መሄድ አንፈልግም ነገር ግን የደም ማነስ በራሱ የሚያስከትልብን የጤና ችግርች አሉ ለምሳሌ፡-የልብ ህመምን ያስከትልብናል ስለዚህ በምን ምክንያት እንደሚከሰት እና ምን ማድረግ እንዳለብን አብረን እንመለከታለን የደም ማነስ የምንለው ቀይ የደም ሴል ማለትም ለሰውነት አካላችን ኦክስጅን ያለው ደም የሚያደርሰው እጥረት ሲያጋጥም የሚፈጠር ነው፡፡ መነሻው 📌 በቂ ቀይ የደም ሴል በማይመረትበት ጊዜ 📌 አደጋ ወይም መድማት ካለ 📌 ቀይ የደም ሴል በሚያመርተው መቅኔ ላይ ጉዳት በሚደርስበት ወቅት 📌 በአይረን ንጥረ ነገር እጥረት ምልክቶቱ 📌 ድካም 📌 አቅም ማነስ 📌 የነጣ ወይም ወደ ቢጫነት ያደላ ቆዳ መኖር 📌 ጤናማ ያልሆነ የልብ ምት 📌 የትንፋሽ ማጠር 📌 ድንዛዜ 📌 የደረት ህመም 📌 ቀዝቃዛ እጅ እና እግር 📌 የራስ ምታት 📌 የፀጉር መሳሳት 📌 የድፍረት መቀነስ 📌 ትኩረትን ማጣት መፍትሄው 📌 ፈሳሽ መውሰድ 📌 ቫይታሚን ሲ መውሰድ 📌 እንደ አስፈላጊነቱ የደም ልገሳ ማድረግ https://t.me/+9-8fYhrqMelmZTRk
Hammasini ko'rsatish...
Health

Happiness is the highest form of health.

👍 20
Repost from N/a
ስለ ማር ማወቅ ያለብዎ ነገሮች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹            #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን ⏩ ንቦች እንዴት ነው ማር የሚሰሩት? 🔺 አጀማመሩ ንብ ከአበባ ኔክታር ስትመጥ ነው። ኔክታሩን ሃኒኮምብ ወደሚባል ክፍል ወስዳ ታጠራቅማለች። እዛው በተቀመጠበት ዙሪያ ሌሎች ንቦች ሲበሩ የሚፈጥሩት የመርገብገብ ነፋስ ኔክታሩን በማድረቅ ወደ ማር ይቀይረዋል። ኔክታሩ ወደ ማር እንደተቀየረ የተቀመጠበት ሴል በሰም ይደፈናል። ንቦች አንድ ፓውንድ ማር ለማምረት 2ሚልየን አበባ መቅሰም አለባቸው። ⏩ ማር ወይስ ስኳር? 🔺 ማር ይሻላል ወይስ ስኳር አከራካሪ ርእስ ነው። ነገር ግን ማር ከስኳር የሚሻልባቸው ገጽታዎች አሉት። ማር በውስጡ ጸረኦክሲዳንቶች፣ አሚኖ አሲዶች እና ቫይታሚኖችን ይይዛል። አንድ የሻይ ማንኪያ ማር 21 ካሎሪ ሲኖረው አንድ ሻይ ማንኪያ ስኳር 16 ካሎሪ ይይዛል። ⏩ማር ሳይበላሽ ምን ያህል ግዜ ይቆያል? 🔺 ማር ረጅም ህይወት አለው። ሳይንቲስቶች ቢበላ ችግር የማያመጣ ለሺህ አመታት የተቀመጠ ማር ማግኘት ችለዋል። ማር በተዘጋ እቃ ውስጥ ከተቀመጠ በቀላሉ አይበላሽም። ማር በተፈጥሮ እርጥበቱ ዝቅተኛ ነው፣ ጠንካራ አሲዳማ ይዘት አለው፣ እንዲሁም ጸረ ባክቴሪያ ንጥረነገሮችን የያዘ ነው። በተዘጋ እቃ ደረቅ ቦታ ውስጥ በማስቀመጥ ከመበላሸት መከላከል ይቻላል። ⏩ ማር ምን ምን የጤና ጥቅሞች አሉት? 🔺 የብርድ ስሜትን ያጠፋል፡- የተለያዩ ጥናቶች እንደሚናገሩት ማር የብርድ ስሜትን ለመከላከል እንደሚጠቅም ነው። በልጆች ላይ ሳል ለመቀነስ እንዲሁም የተሻለ እንቅልፍ እንዲያገኙ ይረዳል። 🔺 ቁስልን ያድናል:- ማርን ቁስል እና ቃጠሎ ላይ መቀባት የተለያዩ ቦታዎች እንደ ባህላዊ መድሃኒት ይቆጠራል። ጥንትዊ ግብጽ ውስጥ እንደ መድሃኒት ይውል ነበር። ማር ውስጡ ባክቴሪያ የሚዋጉ፣ ቁስል የሚያድኑ፣ ኢንፌክሽን የሚከላከሉ እና እብጠትን የሚቀንሱ ንጥረነገሮችን የያዘ ነው። ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል በመድሃኒት መልክ የተዘጋጀ ማርን ገዝቶ መጠቀም ይመከራል። ቁስሉ ከባድ ከሆነ ዶክተርን ማማከር ይመከራል። 🔺 የንብ መነደፍ ሲያጋጥም፡- ህመሙን ለመቀነስ እና እብጠቱን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ 🔺 የልብን ጤንነት ይጠብቃል፡- አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማር የደም ግፊትን እና የደም ቅባትን መጠንን ይቀንሳል፤ የልብ ምትን ይቆጣጠራል፤ የጤነኛ ሴሎችን ሞት ይከላከላል፡፡ 🔺 በህፃናት ላይ የሚከሰት ሳልን ይቀንሳል፡- ከ 1 አመት በላይ ለሆኑ ህጻናት ማር እንደ ተፈጥሯዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሳል ህክምና ሊያገለግል ይችላል፡፡ 🔺 በቀላሉ በአመጋገብ ስርአታችን ውስጥ መጨመር ይቻላል፡- ማርን በመጠቀም እርጎን ወይም መጠጦችን ለማጣፈጫነት በመጠቀም፣ በብዙ የምግብ አዘገጃጀት ውስጥ እንደ አንድ ንጥረ ነገር በመጨመር፣ ከሻይ ጋር በመጠጣት እና እንዲሁም ብቻውን በመዋጥ መጠቀም ይቻላል፡፡ ⏩ አንድ አመት ያልሞላቸው ልጆች ማር መመገብ የለባቸውም። ማር በውስጡ ህጻናትን የሚያሳምም ቦቱሊዝም የተባለ ንጥረነገር ሊይዝ ይችላል፡፡ ⏩ ማር ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች ቢኖሩትም የስኳር አይነት መሆኑን ግን አስታውሱ፤ ስለዚህ እሱን መጠቀም የደምዎን የስኳር መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ⏩ በተጨማሪም ከፍተኛ መጠን ያለው ማር ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ መመገብ ለክብደት መጨመር አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ እንደ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ወይም የልብ ሕመም ያሉ በሽታዎችን ይጨምራል። ስለዚህ, ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ አወሳሰድ ይጠቀሙ፡፡ እናመሰግናለን            መልካም ጤንነት https://t.me/+9-8fYhrqMelmZTRk
Hammasini ko'rsatish...
Health

Happiness is the highest form of health.

👍 15🥰 1
Repost from N/a
ማስቲካን በማኘክ የሚገኙ የጤና             ጥቅሞች      የምናገኛቸው ጥቅሞች እነሆ፦ 1. ጭንቀትን ያስወግዳል! በተለያዩ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማስቲካ የሚያኝኩ ሰዎች ከማያኝኩት/ከማይጠቀሙት በተሻለ ሁኔታ ከገቡበት ጭንቀት በፍጥነት ይወጣሉ፡፡ 2. ክብደትን ይቀንሳል! የተለያዩ ጣዕም ያላቸው ማስቲካዎችን ለማኝክ ከፍተኛ ካሎሪ/ጉልበት እንድናወጣ ስለሚያደርገን ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡ 3. የምግብ ስልቀጣን ያፋጥናል! ማስቲካ ማኝክ በአፋችን ውስጥ የምራቅ መጠን እንዲጨምር/እንዲበዛ ያደርጋል ይህ ሁኔታ የምግብ ስልቀጣን/መፈጨትን የማፋጠን ከፍተኛ ሀይል አለው፡፡ 4. ሀሳብን ለመሰብሰብ ይረዳል! ማስቲካ ማኝክ ከማንኛውም ጊዜ በላይ እንድንነቃቃ እና ሃሳባችንን እንድንሰበስብ ያደርጋል፡፡ በተለይ በስብሰባ እና በመማሪያ ክፍል ውስጥ (ምንም እንኳን መምህሮች ፈቃደኛ ባይሆኑም) ማስቲካ ማኝክ ነቃ ብለንና ሃሳባችንን ሰብሰብ አድርገን እንድንከታተል ይረዳናል፡፡ 5. የትውስታ አቅምን ይጨምራል! ማስቲካ በምናኝክበት ጊዜ አማካይ የልብ ምታችን ይጨምራል ይህ ሁኔታ ወደ አእምሮአችን የሚገናውን የኦክስጂን መጠን ይጨምረዋል፡፡ ስለዚህ አእምሮአችን በብቃትና በትኩረት ስራውን እንዲወጣ/እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡ 6. መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል! ማስቲካ ማኝክ መጥፎ የአፍ ጠረንን ከመከላከሉም በላይ ጥርሳችን እንዳይበሰብስ ይረዳል፡፡ በምናኝክበት ወቅት ከፍተኛ ምራቅ ስለምናመነጭ በአፋችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ ለአፍ ጠረንና ለጥርስ መቦርቦር ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡ 7. የሲጋራ ሱስን ለማቆም ይረዳል! የተለያዩ የሲጋራን ሱስ ለማቆም የሚረዱ ማስቲካዎች በውስጣቸው ኒኮቲን የያዙ በገበያ ላይ ይገኛሉ እነዚህን ማስቲካዎችን በማኝክ የሲጋራ ሱስን ማቆም ይቻላል፡፡ 8. ካሎሪን ለማቃጠል ይረዳል! ማስቲካ በምናኝክበት ወቅት በመንጋጋ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ስራ ይሰራሉ፡፡ እንደሚታወቀው ስራ ለመስራት ሀይል ያስፈልጋል ስለዚህ የመንጋጋ ጡንቻዎች በሠዓት 10 ካሎሪ ያህል ይቀንሳሉ ይህ ደግሞ ክብደትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያበረክታል፡፡ 9. የገርድ በሽታን ይከላከላል! ይህ የበሽታ አይነት በጨጓራችን ውስጥ ያለው አሲድ(HCL) በጉሮሮ/የምግብ ቧንቧዎች ወደ ላይ ሲመለስ ልባችን አካባቢ የማቃጠል ስሜት የሚፈጥርብን በሽታ ነው፡፡ ይህን በሽታ በቀላሉ ለመከላከል ማስቲካ በማኝክ በምራቅ አማካኝነት ወደ ላይ የሚመጣውን አሲድ ጨጓራ ውስጥ ማስቀረት ይቻላል፡፡ 10. የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ለማግኝት! ማስቲካ በውስጡ የተለያዩ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ቫይታሚን ሲ በውስጡ ይዟል፡፡ በተጨማሪም የአፍ ውስጥ ባክቴሪያን የሚያጠፉ እንደ ዛይሊቶል አይነት ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ https://t.me/+9-8fYhrqMelmZTRk
Hammasini ko'rsatish...
Health

Happiness is the highest form of health.

👍 12🙏 1
Repost from N/a
ለወዛም ፊት ምን ማድረግ አለብኝ ፊታችን ወዛም ሆኖ እየተቸገርን ግን ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም ዛሬ ይህን ችግራችንን በቀላሉ ለመፍታት የሚያስችለንን ውህዶች እንዴት በቤት ውስጥ መጠቀም እንደምንችል እንመለከታለን ፡፡ እንቁላል ፡- እንቁላል በቫይታሚን ኤ የበለፀገ በመሆኑ ለቅባታማ የፊት ቆዳ ጠቃሚ ነው ዘዴ ፡- እንቁላል ነጩን ክፍል ሰሀን ላይ አድርጎ በማንኪያ መምታት ከዚያ ፊት ላይ ተቀብቶ እስኪደርቅ ድረስ ጠብቆ ለብ ባለ ውሀ መታጠብ ሎሚ ፡- ሎሚ የፊታችን ቆዳ በጣም ወዛም እና ቅባታማ ከሆነ ወዛችን እንዲቀንስ ይረዳናል ዘዴ ፡- አንድ የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ውሀ ጋር በመደባለቅ በንፁህ ጥጥ እየነከርን የፊታችን ቆዳ መቀባት ከዚያ ከ10 ደቂቃ በኋላ ለብ ባለ መታጠብ ማር ፡- ወዛም የፊት ቆዳን ለማድረቅ ይጠቅማል ዘዴ ፡- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ማር ፣ አንድ የሻይ ማንኪያ የወተት ዱቄት ፣ አንድ የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ሁሉንም አንድ ላይ በመደባለቅ ፊታችን ላይ መቀባት ከ 10- 15 ደቂቃ አቆይቶ በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ ቲማቲም፡- በውስጡ ያለው ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ እና በተፈጥሮ ዘይትን የሚቀንሱ አሲዶች በውስጡ ስላለው ለወዛም ፊት ጠቃሚ ነው እንዲሁም ቡጉርን ለመከላከል ይረዳል። ዘዴ ፡- ግማሽ ቲማቲም ቆርጠን ፊታችንን ማሸት ከዚያ እስኪደርቅ ለ10 – 15 ደቂቃ አቆይቶ በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ ነው። ተጨማሪ የተለያዩ የጤና ነክ መረጃዎች ለማግኘት ሊንኩን ተጭነው ቤተሰብ ይሁኑ። Join https://www.facebook.com/profile.php?id=100083276795470
Hammasini ko'rsatish...
Health | Addis Ababa

Health, Addis Ababa, Ethiopia. 4,273 likes · 10 talking about this. Medical & health

👍 6 1👏 1
👍 6