uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 16 123 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 232-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 221-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 16 123 obunachiga ega bo‘ldi.

01 Noyabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 598 ga, so‘nggi 24 soatda esa 74 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 23.12% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.46% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 729 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 686 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 29 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 02 Noyabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

16 123
Obunachilar
+7424 soatlar
+847 kun
+59830 kun
Postlar arxiv
ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን አገልግሎታችንን በቴሌግራም ጭምር እንድናስፋፋ በሰጣችሁን አስተያየት መሠረት እነሆ ጀምረናል፡፡ አድራሻችን የሚከተለው ነው፤ ለሌሎችም ያስተዋውቁ፤ <<የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት>> ወይም https://t.me/joinchat/AAAAAE2hgYCjGkwz9N1jIw በቴሌግራም አስተያየት (comment) ለመስጠት <<medihanaelem>> በሚል

እንኳን ለቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል (በዓለ ዕረፈት) አደረሰን፥ አደረሳችሁ፡፡ በዚህች በመስከረም 29 ቀን አርሴማ ቅድስት ወሰማዕት እና የእርሷ ማኅበርተኞች ድል አድራጊዎች 27 ሰማዕታት በሰማዕትነት ያረፉባት ዕለት ነች፡፡ እግዚአብሔር ከእነዚህ ቅዱሳን ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸውን ይክፈለን፡፡ እነዚህም ቅዱሳን፤ 1ኛ. አርሴማ፤ ቅድስት ወሰማዕት ኃያል ተጋዳሊት 2ኛ. ኢያሚኖስ፤ ጸሎትን የሚያሳርግ ካህን 3ኛ. አፍጢኖስ፤ ከብዙዎች የተመረጠ 4ኛ. በርቲኖስ፤ ጻድቅና ቸር 5ኛ. ጢሞና፤ በመላላክ ሥራ አገልጋይ የኾነ 6ኛ. ጢሞዓና፤ ተአጋሽና ጸዋሚ 7ኛ. ዘኬዎስ፤ ከከበሩ የከበረ 8ኛ. እስጢፋኑ፤ ተጋዳይና የበደሉትን ይቅር ባይ 9ኛ. አርሞና፤ ከጎልማሶች ይልቅ ደም ግባቱና መልኩ ያማረ 10ኛ. ኪርያኮስ፤ ሥጋውን ያላረከሰ ንጹሕ 11ኛ. አንጥያኮስ፤ ቡሩክ የኾነ የአቡሪ ልጅ 12ኛ. ያዕቆብ፤ የእግዚአብሔር ታማኝ የኾነ 13ኛ. ቡራኬሌስ፤ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የኾነ 14ኛ. አስቂርያቆስ፤ ክርስቶስን የሚወደው 15ኛ. አስኪርያኖስ፤ ባለሟል የኾነና ግርማው የሚያስፈራ 16ኛ. ሚርያኖስ፤ ፊቱና መልኩ ደስተኛ የኾነ 17ኛ. ትትግርጦስ፤ ወደ ንስሐ የተመለሰ 18ኛ. ያስቲኖስ፤ የሚፈርድና የሚበይን 19ኛ. ጥልያኖስ፤ ያላመኑ ሰዎችን የሚገስጽ 20ኛ. ዑልያኖስ፤ የዚህ ዓለም ጥበብ መምህር የኾነ 21ኛ. ጴርቅላስ፤ በስም አጠራርና በሽምግልና መልካም የኾነ 22ኛ. ኬብያኖስ፤ ተጋዳይ የኾነ 23ኛ. ጴጥሮስ፤ የጠራ የባሕርይ ዕንቊ 24ኛ. ጰኵንዮስ፤ የሮምያ ሹም 25ኛ. ሐናንያ፤ የዋህና ሽንገላ የሌለው 26ኛ. ሐሊባኖስ፤ ጾምና ጸሎትን የሚወድ 27ኛ. ኤስያኖስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጎልማሳ የኾነ 28ኛ. ኤልያብ፤ በረኛና የሰማዕት መጀመሪያ፡፡ ሰላም ለፀዐተ ነፍስኪ በጊዜ ኃለፈ ሰይፍ፤ መንገለ ክሣድኪ ድኑን ለአምሳለ መሥዋዕት ውኩፍ፡፡ እስእለኪ አርሴማ በከናፍር ወአፍ፤ ረድኤትኪ ትሩፍ በላዕሌየ ያንጸፈጽፍ፤ እስመ አርአየኒ ዘንተ ሞትኪ ትሩፍ፡፡ ሰላም ለዘአዕረፉ ምስሌኪ ፳ወ፯ቱ ሰማዕታት፤ ረድኤቶሙ ትረድ ላዕሌየ ዘምስለ ብዙኅ ምሕረት፡፡ ወኀበ ሀለወ ስሞሙ ምስለ ስምኪ ቅድስት፤ ዓዲ ኢይቅረብ አርሴማ ሕማመ ብድብድ ወሞት፤ በኵሉ አዝማን ወበኵሉ ዓመታት፡፡

✤✤ እንኳን ለማኅሌተ ጽጌ አደረሳችሁ፤ ምን እንኳን በመጽሐፈ ገጽ (Facebook) ጽሑፎችን ማቅረብ ከጀመርን በርካታ ዓመታት ብናስቈጥርም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በነመጽሐፈ ገጽ ፋና ወጊ ኾነን ሥርዐተ ማኅሌትን ይዘን መቅረብ ከጀመርን ግን 5ኛ ዓመታችን ኾነ፤ እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድም ዘንድሮም 5ኛ ዓመታችን (የ7ኛ ዙር ዓመት ሙሉ የማኅሌተ ጽጌ ሥርዐተ ማኅሌትና በዓመት ውስጥ የሚገኙ የክብረ በዓላት ሥርዐተ ማኅሌትን ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡ (የታተመውንወረቀት /hard copy/ ከፈለጋችሁ በሰ/ትቤታችን ትምህርት ክፍልና ቤተ መጻሕፍት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ✤ የማኅሌት ቁመት የላይ ቤትና የታች ቤት ኾኖ እንደየአድባራቱ ይትበሃል የሚቆም እንደመኾኑና ማኅሌተ ጽጌ በኹሉም አድባራት በደመቀ ኹኔታ ስለሚቆም የላይ ቤቱንም ኾነ የታች ቤቱን በአንድነት አቅርበንላችኋል፤ የላይ ቤት የምትቆሙ አድባራት ‹‹ዘግምጃ ቤት›› የሚለውን፤ የታች ቤት የምትቆሙ ‹‹ዘጎንደር በዓታ›› በሚል አስቀምጠንላችኋል፡፡ ደብራችን ቀጨኔ ደብረ ሰላም የላይ ቤት የሚቆምበት ደብር እንደመኾኑ ላይ ቤቱን እያስቀደምን ታች ቤቱን አስከትለን አስቀምጠናል፡፡ የላይ ቤት የሚቆምባቸው አድባራት የታች ቤቱን አየዘለሉ፤ የታች ቤት የሚቆሙ አድባራት የላይ ቤቱን እየዘለሉ እንዲጠቀመቡት ኹሉንም አዘጋጅተነዋል፡፡ የላይ ቤትና የታች ቤት በአንድነት የሚቆሙት ቀለም ሲኾን ግን ‹‹ዘግምጃ ቤት ወዘበዓታ›› ብለን አስቀምጠነዋል፡፡ /በማኅሌት በምትቆሙ ጊዜ በጸሎታችሁ ደብራችንን ደብረ ሰላምንና ሰ/ት/ቤታችንን ፍኖተ ሕይወትን አስቡን፡፡ ✤ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤  ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው፡፡ የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው፡፡ ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡ ✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤  ከማኅሌተ ጽጌ፤ ጽጌ አስተርአየ(የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብር ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡  ከሰቈቃወ ድንግል፤ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡  ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡  ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡  የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤  የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡ ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት) (፯ኛ ዙር ዓመት፤ ፩ኛ ሳምንት፥መስከረም ፳፯) በዓለ መድኀኔዓለም ወአባ ጽጌ ድንግል፡፡ የመዝሙሩ ፍሬ ሓሳብ፤ ከሚጠፋ ዘር የተገኙትን የሚንከባከብ ጌታ ከማይጠፋ ዘር የተገኛችሁትን አብልጦ ይንከባከባል፡፡ (1ኛ. ጴጥ. ፩፥፳፮፣ ማቴ. ፮፥፳፭)

ꔰ ማኅሌተ ጽጌ ምን ማለት ነው? ማኅሌተ ጽጌ ከሁለት የግዕዝ ቃላት ጥምረት የተገኘ ነው፡፡ ማኅሌት ማለት ምስጋና፣ ማወደስ ማለት ሲኾን፤ ጽጌ ማለት ደግሞ አበባ፣ የፍሬ ምልክት፤ ውበት፣ ደም ግባት ያለው ማለት ነው፡፡ ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ በአንድነት ሲነገር እና ሲተረጎም ደግሞ የአበባ ምስጋና ማለት ነው፡፡ ይህም ድንግል ማርያም እና የማሕፀኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ በጎ መዓዛ በአላቸው አበባዎች እና ፍሬዎች እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት ምስጋና ማለት ነው፡፡ የዘመን (የወራት) ስምም ይኾናል፤ ዘመነ (ወርኃ) ጽጌ 40 ቀን ነው፤ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ነው፡፡ በዚህ 40 ወራት የሚጾመው ጾም ጾመ ጽጌ ሲባል ጾሙም የፈቃድ ጾም ነው፤ በሀገራችን ዘመነ ክረምት አልፎ መስከረም 26 ቀን ዘመነ ጽጌ ይጀመራል፡፡ ዘመኑ አበቦች የሚያብቡበት እና ሜዳዎችን እና ተራሮችን የሚስጌጡበት ዘመን ነው፡፡ ፍሬ የተባለ ጌታን ያስገኘች እመቤታችን በአበባ ትመስላለችና ዘመኑ የጌታችንን እና የእመቤታችንን ነገር በአበባ እና በፍሬ ለመመስል የተመቸ ነው፡፡ የማህሌተ ጽጌ ደረሲ አባ ጽጌ ድንግል ይህንን የአበቦችን ነገር ከእመቤታችን ስደት ጋር እያደረገ፣ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪኮችን እያጣቀሰ ማኅሌተ ጽጌ (የአበባ ማኅሌት) የተባለውን ጸሎት ደርሷል፡፡ በዘመነ ጽጌ ወቅት ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ማኅሌት ይቆማል፤ የሚቆመው ቁመትም አባ ጽጌ ድንግል የደረሱት ማኅሌተ ጽጌና ሰቈቃወ ድንግል ነው፡፡ አባ ጽጌ ድንግል ጓደኛቸው አባ ገብረማርያም የጀመሩትን ማኅሌተ ጽጌ አብነት በማድረግ በተለይም በጎንደር ዘመነ መንግሥት በእቴጌ ምንትዋብ ዘመን በጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቊም ማርያም የማኅሌተ ጽጌ ቁመት መቆም ተጀምሯል፤ ቆይቶ ግን ይህ ማኅሌት ወደ ዘንሥር ዮሐንስ ማእከላ ለጎንደር ተዛውሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ ሲቆም ቆይቶ በመምህር ተክሌ ጊዜ ወደ መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ተዛውሮ በጎንደር አብያተ ክርስቲያናት በብቸኝነት በዚህችው ደብር የጎንደር አድባራት ሊቃውንት በመሰባሰብ ሲቆም ቆይቷል፤ ከ1999(2000)ዓ.ም. ጀምሮ በደብረ ፀሐይ ቊስቋምና የተወሰኑ ተወሰኑ የጎንደር አብያተ ክርስቲያናት የማኅሌተ ጽጌ ቁመትን ቢጀምሩም ቅሉ አሁንም ግን የጎንደር አድባራት በዋነኛነት በመካነ ነገሥት ግምጃቤት እየተሰባሰቡ የሚቆሙት የማኅሌተ ጽጌ ቁመት እጅግ በጣም ልብን የሚማርክና ኅሊናን የሚመስጥ ነው፡፡ በሌሎች የሃገራችን ክፍሎችና በመዲናችን በአዲስ አበባ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ የአገልጋይ ካህናት እጥረት በሌለባቸው ኹሉ ይቆማል፡፡ በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ከደብራችን ምሥረታ ጀምሮ የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ልዩ በኾነና ደማቅ በኾኑ ሥርዐቶች ጭምር ይቆማል፤ ምንም እንኳን ደብራችን በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. ቢመሠረትም በተለያዩ ቦታዎች ታቦተ ሕጉ ሲዘዋወር ከቆየ በኋላ አሁን ያለው ሕንፃ ቤ.ክን በ2ዓመት ከ6 ወር ሥራ ተጠናቅቆ ቅዳሴ ቤት ሁኖ የተመረቀው በወርኃ ጽጌ በጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም. ነው፤ በቅዳሴ ቤት ማኅሌቱም ላይ ከተቆሙት መካከል ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› የሚለው ቀለም ሲገኝበት እስካሁንም ድረስ በማኅሌተ ጽጌ የሚወረብ ቀለምም ነው፡፡ ከዛን ዕለት ጀምሮም ማኅሌተ ጽጌ በልዩ ኹኔታ በደብራችን እየተቆመ ይገኛል፤ ይኸውም፤ ✤ ማኅሌተ ጽጌን በላይ ቤት አቋቋም፤ የማኅሌተ ጽጌን ወረቦች ደግሞ በጎንደር ወረብ ✤ የማኅሌተ ጽጌን ዚቅ በላይ ቤት አቋቋም፤ የዚቁን ወረቦች ደግሞ በራሱ በደብራችን ይትበሃል ✤ በወርኃ ጽጌ የሚዘመሙ የክብረ በዓላት ዝማሜን ደግሞ በተክሌ ዝማሜ እየተዘመሙ ይገኛል፡፡ ✤ ሌላው በቅድስትሰ ሃገር ኢየሩሳሌም በጸሓፌ ትዕዛዝ ኀይሌ ወልደ ሩፋኤል የተሳለችውና በደብራችንና በመናገሻ ገነተ ጽጌ ብቻ የምትገኘው ስዕለ እግዝዕትነ ማርያም (ኢትዮጵያን ይዛ እንባዋን ስታብስ ‹‹ኃዘና ስምዒ ወብካያ ለሃገሪትና ኢትዮጵያ›› የሚል ጽሑፍ ያለባት ስዕል) ወጥታ በዑደት ጊዜ የምትባርከው በዚሁ በዘመነ ጽጌ በመኾኑ፤ ✤ በሃገራችን ደረጃ ከ50 ዓመታት በፊት በወቅቱ በነበሩት በንቡረ ዕድ ዓሊ በማኅሌተ ጽጌ ላይ የተጀመረውና (ልዩ ኅብርና ውበት ባላቸው ጉንጉን አበቦች) ወርኃ ጽጌን ለማሰብ በማኅሌቱ ጊዜ ጉንጉን አበባ መታደሉ፤ (ይህ አበባ ዛሬ ለሌሎች አድባራት ምሳሌ ሁኖ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት መሰጠት ተጀምሯል) ✤ ከተለያዩ ገዳማትና አድባራት ይህንን ማኅሌት ለመቆም የሚመጡ በርካታ ሊቃውንትና ምዕመናን መኖራቸው፤ ✤ ‹‹እንዘ ተሐቅፊዮና ክበበ ጌራ ወርቅ›› እየተባለ ወረብ እየተወረበ ዑደት በሚደረግበት ጊዜ ከጥንት ጀምሮ ጧፍ ቤተ ክርቲያኑ እያደለ በብርሃንጎርፍ ቤተ ክርስቲያኑ አብርቶ መታየቱና፤ ……… በሌሎችም ኹኔታዎች ልዩ ያደርገዋል፡፡ በኹሉም አብያተ ክርስቲያናት ያሉ ካህናትና ምዕመናንም ድካም ሳይሰማቸው ወርኃ ጽጌ ደርሶልን ባገለገልን እያሉ በናፍቆት የሚጠበቁት ወራት ነው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ ቤት ሰሌዳ መጽሔት/ (ጽሑፉን ለዘገበልን ወንድማችንን አምላከ አባ ጽጌ ድንግል ወጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይስጥልን፤ በረድኤት በበረከት ቅዱሳን ሊቃውንቱ ይጎብኙልን፡፡)

✤✣✤ገዳመ ጽጌ ድግል፤ የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተው በታላቁ አባት በአቡነ ጽጌ ድንግል ሲኾን፤ እኝህ ታላቅ አባት እጅግ ሰፊ ኾኖ የሚያምረውንና ዕጹብ ድንቅ የሚያሰኘውን ባለሦስት ክፍል (ቅኔ ማሕሌት፣ ቅድስትና መቅደስ) ያለውን የገዳመ ጽጌን ውቅር ዋሻ ቤተክርስቲያን ያነጹ፣ ከሰባቱ ቅዱሳን ዘጋሥጫ (አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል፥ አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፥ አቡነ ያዕቆብ ዘቀዳሚት ግሸን ደብረ ከርቤ፥ አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት፥ አቡነ ዘካርያስ ዘወለቃ፥ አቡነ ዮሴፍ ዘወለቃ፥ የዝቋላው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘምስካበ ቅዱሳን ገዘዛ) አንዱ የኾኑና የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ የኾኑ በዚህም በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ የምንጸልይበትንና የምናመሰግንበትን ማሕሌተ ጽጌን ባለ ፭ት አርኬና እንደ መዝሙረ ዳዊት በ፻፶ መዝሙር ልክ አድርገው የደረሱና ጸሐፊያቸው በኾኑ ጓደኛቸው አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ አጽፈው ለትውልድ ያስተላለፉ፤ እንዲሁም ሰቈቃወ ድንግልን ከጓደኛቸው አቡነ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና ጋር አብረው የደረሱ ቅዱስ አባት ናቸው፤ እንዲሁም በዘመናቸው ከነበሩት ከጓደኛቸው ከታላቁ አባት አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ጋር ብዙ ገቢረ ተዓምራትን የሠሩ (የወለቃ ወንዝ ድልድይን ጨምሮ ያነጹ)፥ አሁንም ብዙ ገቢረ ተዓምራትን የሚሠሩ አባት ናቸው፡፡ ገዳሙ የሚገኘው በደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ በወግዲ ወረዳ ልዩ ስሙ ደብረ (ገዳመ) ጽጌ ጫቀታ በሚባል ቦታ፤ ለዐባይ ወንዝ ገባሮች ከኾኑትና በበረሀ ውስጥ ከሚጓዙት አንዱ በኾነው በወለቃ ወንዝ አቅራቢያ ነው፡፡ ገዳሙ ለታላቁ አባት በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረትም አኹንም ድረስ ፈውሰ ሥጋ፥ ፈውሰ ነፍስ እየሰጠ ይገኛል፤ የገዳሙ ፍየሎችና ከብቶችም በአካባቢው ከሚገኙት ነብሮች ጋር አብረው ያለምንም አደጋ ይኖራሉ፡፡ ገዳሙ በግራኝ መሐመድ ወረራ ወቅት 500 መነኰሳት በሰማዕትነት የተሰየፉበት ሲኾን ከዚህ ጀምሮ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ተዘግቶ ቆይቶ በልዑል ራስ ካሣ ኀይሉ አማካይነት ተከፍቶ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፤ በድጋሚ በጣሊያን ወረራ ወቅት አደጋ ደርሶበታል፤ በደርግ ዘመንም የገዳሙ 84 ጋሻ መሬት ስለተወሰደበት እንደገና እስከ ከ1995ዓ.ም. ገዳሙ ዘግቷል፤ ነገር ግን በ1995ዓ.ም. በበጎ አድራጊ ምዕመናን ድጋሚ ሊከፈት ችሏል፡፡ ማሕሌተ ጽጌ የተደረሰበት ይህ ገዳም እስከ 2008ዓ.ም. ማሕሌቱ. ሳይቆምበት ቆይቶ ከ2009ዓ.ም. ጀምሮ ማሕሌቱ እየተቆመ ይገኛል፡፡ ለበርካታ ዓመታት የሊቁ የአባ ጽጌ ድንግል በዓለ ዕረፍት መስከረም 27 መከበር አቁሞም ነበር፤ እንደ አምላከ አበው ፈቃድ ዘንድሮ በ2011ዓ.ም. ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ ወደ ገዳሙ ለመሄድ ለሚፈለጉ ምዕመናን፤ (በተለይ ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ የተጓዛችሁ በዛው ለመሄድ ቅርብ ነው፡፡) 1ኛ) ከደሴ ከተማ ለምትነሱ ወግዲ በሚል መኪና ከተሳፈሩ በኋላ ከተወሰኑ የእግር ጕዞ በኋላ ይገኛል፤ 2ኛ) ከጎጃም በመካነ ሰላም ለምትነሱ ወግዲ በሚል መኪና ከተሳፈሩ በኋላ ከተወሰኑ የእግር ጕዞ በኋላ ይገኛል፤ 3ኛ) በመርሐ ቤቴ በሚዳ ለምትነሱ ወግዲ በሚል መኪና ከተሳፈሩ በኋላ ከተወሰኑ የእግር ጕዞ በኋላ ይገኛል፡፡ † በዚሁ አጋጣሚ የታለቁ ሊቅ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በዓለ ጽንሰታቸውም ጥቅምት 3 ስለሚከበር አብሮ ማክበር ይቻላል፡፡ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/ (የገዳሙን ኹኔታ የዘገበልንን ወንድማችንን አምላከ አባ ጽጌ ድንግል ወጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይስጥልን፤ በረድኤት በበረከት ቅዱሳን ሊቃውንቱ ይጎብኙልን፡፡)

ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ የማያደርግ የሕግ ፍጻሜ ነውና፤ ሮሜ 13፥10-11፣ አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያምም የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር (በአንድነት) አገልግለዋል፣ ማለትም አንድ ዓመት አባ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25፣ ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ ገዳመ ጽጌ (ደብረ ብሥራት) ገብቶ ከመስከረም 26 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎትን ከአባ ጽጌ ብርሃን ጋር ፈጽሞ ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብረ ሐንታ ይመለሳል፤ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አባ ጽጌ ብርሃን ከገዳመ ጽጌ (ከደብረ ብሥራት) ወደ ደብረ ሐንታ ሄዶ እንደዚሁ እንደ አባ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አገልግሎ ይመለሳል፣ እኒህ ሁለቱ ቅዱሳን ሊቃውንትም ታሪኩ ከላይ እንደተገለጸው እንዲህ እያደረጉ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍቅርና በትሕትና ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ ምንጭ ፡- የማሕሌት ጽጌ ትርጕምና ታሪክ፣ የቤተክርቲያን መረጃዎች፣ መዝገበ ታሪክ፣ ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ ቤት ሰሌዳ መጽሔት/

ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን)፤ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለጸሎት፣ ለማስጋና፣ ለልመና እና ምዕመናኖቿን ለማስተማር ከምትጠቀምባቸው የመዝሙር እና የጸሎት መጻሕፍት መካከል አንዱ በ14ኛው መክ.ዘመን በተነሱት ሊቅ በአባ ጽጌ ድንግል የተደረሰው ማኅሌተ ጽጌ ነው፡ ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሄድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው፡፡ ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ በቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ ብሎም ወደ ኢትዮጵያ መሰደድ እና መንከራተት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ በዚህ ወቅት በየሳምንቱ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ሌሊት የሚደርስ ምስጋናና ጸሎት ነው፡፡ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን) በ14ኛው መ.ክ.ዘ የነበረ ሊቅ ሲኾን፤ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን) ሀገሩ ይፋት ሃይማኖቱ ኦሪት ነበረ፡፡ በንጉሥ ሰሎሞን ፈቃድና በካህኑ አዛርያስ መሪነት የብሉያት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ ተርጕመው ሊያስተምሩ፣ ታቦተ ጽዮንን ከኢየሩሳሌም ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡትና የብሉያት መጻሕፍት ሊቃውንት ከነበሩት ከ318 ሌዋውያን (ከቤተ እስራኤላውያን) ነገድ ነው፡፡ የተወለደውም በሰሜን ሸዋ በይፋት አውራጃ ውስጥ ሲሆን፤ መጀመርያ ኢእማኒ (ያላመነና ያልተጠመቀ) ነበር፣ ከዕለታት አንድ ቀን ይህ ሰው፤ በወጣትነት ዕድሜው አውሬ ለማድን ወደ ጫካ ሄደ፣ ጫካዋም በዚያው በይፋት አውራጃ የምትገኝና ልዩ ስሟ ደንስ (ገዳመ ደንስ) ትባላለች፣ በጫካዋ ውስጥም ፈቷ በጽጌረዳ አበባ የተከበበና ያጌጠ፣ እጅግም ደስ የምታሰኝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል አይቶ በሥዕሏ ውበት እየተደነቀ ሥዕሏን ሲመለከት እንደ እርሱ ያልተጠመቀ ጓደኛው መጥቶ፣ ‹‹ምን እየፈለግህ ነው? የክርስቲኖችን ሥዕል ነውን?›› ብሎ ለድንግል ማርያም ምስጋና ይግባትና በያዘው በትር ሥዕሏን ሲመታት ወዲያው ተቀሥፎ ሞተ፣ ከዚህ በኋላ ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ የመሰለ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በነጭ ወፍ ተመስሎ፡ ወደ እርሱ መጥቶ አንድ ቀይ መነኩሴ እሰኪመጣ ድረስ፣ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ነግሮት ተሠወረ፣ የአቡነ ዜና ማርቆስ የገድል መጽሐፍ፣ እንደሚናገረው ካህን ከነበረው ከአባቱ ከዘርዐ ዮሐንስ አና ከእናቱ ማርያም ዘመዳ በ1262 ዓ.ም. ኅዳር 24 ቀን በሰሜን ሸዋ ግዛት በሚገኘውና ልዩ ስሙ እቲሳ ቅዱስ ሚካኤል በሚባለው አጥቢያ የተወለደው አቡነ ዜና ማርቆስ ደብረ ብስራት ከሚባለው ገዳሙ ወደ ይፋት መጥቶ ከነብዩ ኢሳይያስ ትንቢት ከምዕ. 11፥1 ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ እያለ በግእዝ ቋንቋ ሲያነብ አባ ጽጌ ድንግል በሰማ ጊዜ አባቶቼ አይሁድ የነቢያትን ትንቢት ንባቡን አስተምረውኛል አውቀዋለሁ፤ ትርጕሙን ግን አላውቀውምና ተርጕምልኝ አለው፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም ሲተረጕምለት እንዲህ አለ፤ ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ የሚለው ንባብ ከእሴይ ነገድ የሕይወት በትር የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትወለዳለች ማለት ነው፡፡ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ የሚለው ንባብ ደግሞ፤ እመቤታችን ተወልዳ፣ ከእርሷም ጌታ በድንግልና ይወለዳል፣ ከጌታም ክብር ይገኛል ማለት ነው፣ ይህም ጌታ ተወልዶ ትንቢቱ በእውነት ተፈጽሟል ብሎ ተረጐመለት፡፡ ኢሳ 7፥14፣ ማቴ18፥24፡፡ ይህ ሰውም (አባ ጽጌ ድንግልም) በዚህ ትርጕም ደስ ተሰኝቶ አባት ሆይ የኢሳይያስን ትንቢት በመልካም ሁኔታ ተረጐምከው፣ መልካም ነገርንም ተናገርክ አለውና፣ ሥዕሏ ወዳለችበት ቦታ ወስዶ ታሪኩ ከላይ እንደተገለጸው፣ በጫካ ውስጥ ያያትን ሥዕል ጓደኛው በያዘው ብትር ሲመታት ወዲያውኑ እንደተቀሠፈና ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ፣ ‹‹አንድ ነጭ ወፍ /ቅዱስ ሩፋኤል/›› ወደ እርሱ መጥቶ ቀይ መነኵሴ እስኪመጣ ድረስ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ያነጋገረውን ሁሉ ነገረው፣ አቡነ ዜና ማርቆስም ከሥዕሏ የተደረገውን ተአምር ሰምቶ፣ እጅግ ደስ አለውና በል መጀመሪያ እመቤታችን በድንግልና በወለደችው በፈጣሪ ልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን ይህችን ሥዕል ያስገኘ፣ ሰማይና ምድርን፣ በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፣ እርሱ እንደኾነ እውቅ አለውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቆ ጽጌ ብርሃን ብሎ ሰየመው፡፡ ከዚህ በኋላ ሥዕሏን በገዳመ ደንስ ደብረ ብሥራት ወደሚባለው ገዳም ወስዶ በዘመነ ጽጌ ጥቅምት አንድ ቀን በክብር አስቀመጣት የምትከብርትንም ቀን ጥቅምት 3 እና ሰኔ 8 ቀን አደረገ፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም ጽጌ ብርሃንን ለመዓርገ ምንኵስና አበቃው፤ የአባ ጽጌ ብርሃንም ጽጌ ድንግል የሚል ቅጽል ስም አለው፣ በማኅሌት አገልግሎት ጊዜም ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ቤተ ክርስቲያኒቱንና ሥዕሏን እየዞረ ሲያጥን፣ እመቤታችን የካህናቱን አገልግሎት እንደምትባርክ፣ ካህናቱ በግልጽ ይረዱ ነበር፣ አባ ጽጌ ብርሃንም ከመጠመቁ በፊት በአባቶቹ በአይሁድ ሥርዓት እያለ የብሉያት መጻሕፍትን የተማረ ነበር፣ የሐዲሳት መጻሕፍት ትርጓሜን ግን ከአቡነ ዜና ማርቆስ ተማረ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ላሉ አሕዛብ ሁሉ የድኅነት ምክንያት ትሆኑ ዘንድ ብርሃናቸው፣ መምህራቸው አደረግኋችሁ ብሉ ጌታ ነቢዩ ኢሳይያስንና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን እንደመረጣቸው፣ ኢሳ 49፥6.፣ የሐ.ሥራ13፥47 ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ስብከተ ወንጌልን እንደ ዕለት ጉርስና እንደ ዓመት ልብስ አድርጎ፣ መላ ኢትዮጵያን ዞሮ፣ አስተምሮና ባርኮ የዕድሜ ባለጸጋም ሆኖ በተወለደ በ140 ዓመት በ1402 ዓ.ም ታኅሣሥ 3 ቀን ፣ ዐርብ ጠዋት ዐረፈ፡፡ አባ ጽጌ ብርሃንም በወሎ ክፍለ ሀገር በወራይሉ አውራጃ፣ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ ለሚባለው ገዳም የሕግ መምህር ሆኖ ከተሸመውና ከጓደኛው ከአባ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን፣ እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ፡ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት፣ በአባቷ በዳዊት መዝሙር መጠን 150 አድርጎ ደረሰ፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ኹሉ በማኅሌተ ጽጌ እመቤታችንን በአበባ፥ ጌታችን በፍሬ፤ ወይም እመቤታችንን በፍሬ፥ ጌታችን በአበባ እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት እንደ ሰቈቃወ ድንግል፤ ማለት እመቤታችን ከልጇ ከመድኀኔዓለም፥ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደቷ ወቅት ያየችውን መከራ፥ ልቅሶ ዋይታ የሚዘከርበት የማኅሌተ ጽጌ አርኬ ነው፡፡ የሰቈቃወ ድንግልን ደራሲ በተመለከተ አባ ጽጌ ድንግል ደረሱት የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አባ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ/ ወይም /አባ አርኬላዎስ/ ነው የደረሱት የሚሉም አሉ፡፡