uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 16 126 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 230-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 226-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 16 126 obunachiga ega bo‘ldi.

31 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 520 ga, so‘nggi 24 soatda esa 7 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 22.41% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.30% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 597 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 653 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 28 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 01 Noyabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

16 126
Obunachilar
+724 soatlar
+197 kun
+52030 kun
Postlar arxiv
#ታኅሣሥ_12_የአቡነ_ሳሙኤል_በዓለ_ዕረፍት_ከሚከበርባቸው_ቦታዎች_ዋናዎቹ፤ ✤✤1. በሁሉም የዋልድባ ገዳም ክፍልች (በውስጡ ባሉት 3ት ገዳማት፣ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት፣ ጸሎት/ስዕል/ ቤቶችን፣ የአትክልት ቦታዎችንና ሞፈር ቤቶች)፤ እነዚህም፡- 1.1. ዋልድባ አብረንታንት ገዳም (የአብረንታንት መድኀኔዓለም ገዳም) 1.2. ዋልድባ ዳልሽህ ገዳም (ዋልድባ ዳልሽህ አባ ሳሙኤል ቤ.ክ.) 1.3. ዋልድባ ሰቋር ገዳም (የኪዳነምሕረት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስና የመድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ያካተተ) 1.4. አቴና (መቃብረ ሳሙኤል)፤ ሌሊቱንና ቀኑን ሙሉ ገድላቸው እየተነበበ 1.5. አባ ናፃ የአቡነ ተሥፋ ሐዋርያት ገዳም 1.6. ደንደሮቃ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ 1.7. ማይገባ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም 1.8. ማይ ሃርገጽ ቅ/ጊርጊስ ቤ.ክ 19. ዕጣኖ ማርያም ቤ.ክ 1.10. ማይ ለበጣና ሌሎችም የስዕል ቤቶች፣ የአትክልት ቦታዎች ✤2. በተወለዱበት በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ጽዮን ማርያም፤ ✤3. ምንኵስናን በተቀበሉበት በደብረ በንኰል አቡነ መድኀኒነ አግዚእ ገዳም ✤4. በቆብ ወንድማቸው በአባ ያሳይ መንዳባ መድኀኔ ዓለም ገዳም ✤ 5. በቆብ አያታቸው በአቡነ ተክለሃይማኖት ደብረ ሊባኖስ ገዳም በውዳሴና በቅዳሴ (ከጥንት ጀምሮ በደብረ ሊባኖስ ቅዳሴ በየቀኑ በማይቀደስበት ጊዜ በዓመት ውስጥ ጥቂት ቀናት በሚቀደሱበት ጊዜ የቅዳሴ ቀናቸው ከማይታጎሉ አንደኛውና ዋነኛው የአቡነ ሳሙኤል በዓለ ዕረፍት ነው) ✤✤5. 3. አቡነ ሳሙኤል በመሠረቷቸው ገዳማት፤ ✤5.3.1 በደብረ ዐባይ አቡነ ሳሙኤል ገዳም /ሽሬ አጠገብ/ ፣ እጅግ ደማቅ በኾነ ኹኔታ ✤5.3.2 በአብጠራ (አብጠራህ) አቡነ ሳሙኤል ገዳም /ደባርቅ/፣ ✤5.3.3 ደብረ ገነት አቡነ ሳሙኤል ገዳም /አዲስ አበባ አቃቂ አጠገብ/) በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ✤5.3.4 ጎንደር አዘዞ አባ ሳሙኤል ✤✤5.4 በተጨማሪም በስማቸው በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ይከበራል፤ ለአብነትም፤ 5.4.1 በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አቡነ ሳሙኤል 5.4.2 በአዲስ አበባ ወረገኑ ቅዱስ ሚካኤል እና ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል 5.4.3 በአዲስ አበባ ሲምሲ ሚካኤል (በድርብነት) 5.4.4 በታጠቅ በዓለ ወልድ ቤ.ክ (በድርብነት ይከብራል) ፤/ ወደ መናገሻ መንገድ ሲሄዱ) 5.4.5 ** በነቀምቴ አቡነ ሳሙኤል #ባርከኒ አባ እንሣእ በረከተከ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባ ሳሙኤል/፫/ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ፡፡ ፨ታሪኩንና ፎቶዎቹን ለሰበሰበልን ወንድማችን አምላከ አበው መድኀኔ ዓለም በረድኤት በበረከት ይጎብኝልን፨ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

#ጸልዩ_በእንተ_ሃገሪትነ_ቅድስት_ኢትዮጵያ፡፡ (ስለ ቅድስቲቱ ሃገራችን ኢትዮጵያ ጸልዩ፥ ጸልዩ፥ ጸልዩ!!!) #ጸልዩ_በእንተ_ሰላመ_ቤተ_ክርስቲያን_አሐቲ_ቅድስት_ጕባኤ_እንተ_ሐዋርያት_ርትዕት_በኀበ_እግዚአብሔር፡፡ (ሐዋርያት በሰበሰቧት በእግዚአብሔር ዘንድ ሰለቀናች፤ ክብርት ስለምትኾን አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጸልዩ፡፡) #ጸልዩ_በእንተ_ሰላም_ፍጽምት_ወፍቅር_ተአምኁ_በበይናቲክሙ_በአምኃ_ቅድሳት፡፡ (ፍጽምት ስለምትኾን ሰላምና ፍቅር ጸልዩ፤ እርስ በእርሳችሁ በተለየች ሰላምታ እጅ ተነሳሱ፡፡) #አድኅነኒ_ወባልሐኒ_እምእዴሆሙ_ለደቂቀ_ነኪር_እለ_ከንቶ_ነበበ_አፉሆሙ_ወየማኖሙኒ_የማነ_ዐመፃ፡፡ (አድነኝ አፋቸውም ምናምን ከሚናገር ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከኾነ፤ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ፡፡) /#መዝ.፻፵፫፥፯/ #ኃዘና_ስምዒ_ወብካየ_ለሃገሪትነ_ኢትዮጵያ፡፡ (በፎቶ የምትመለከቷት የእመቤታችን ስዕል በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ. ብቻ የምትገኝ አስደናቂና ተዓምር አድራጊ ስዕል ስትኾን፤ የተሳለችውም ጠላት ሃገራችንን በወረረበት ወቅት በ፲፱፻፴ዓ.ም. በኢየሩሳሌም በሰዓሊና በወቅቱ ትልቅ ባለሥልጣን በነበሩት በኀይሌ ወልደ ሩፋኤል (ኃ.ወ.ሩ.) ነው፡፡)

ኦ እግዚኦ መሐራ ለነፍሰ መራሔ መንግሥትነ #ግርማ_ወልደ_ጊዮርጊስ፡፡ ኢትዮጵያን በርዕሰ ብሔርነት ለ12 ዓመታት (ከ1994 እስከ 2006 ዓ.ም.) ያገለገሉት ፕሬዚደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ በሃገራችን ታኅሣሥ 10 ብሔራዊ የሐዘን ቀን ኾኖ ታስቦ ይውላል፡፡ **በሕፃንንታቸው የአብነት ትምህርትን የተማሩት ርዕሰ ብሔራችን 6ት ቋንቋዎችንም የሚያውቁ ናቸው፡፡ #በሁለቱ_ቅዱስ_ሲኖዶስ_መካከል_እርቅ_እንዲወርድ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ትልቅ ጥረት ያደረጉትንና ደብዳቤ የጻፉትን የሃገራችንም ኾነ የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ መቼውንም ቢኾን ሲያስታውሰው ይኖራል፡፡

#ታኅሣሥ_6_የአርሴማ_ቅድስት_ወሰማዕትና_የእርሷ_ማኅበርተኞች_ድል_አድራጊዎች_27_ሰማዕታት_ሥጋቸው_በክብር_የፈለሰበትና_ቤተ_ክርስቲያኗ_ቅዳሴ_ቤት_የተከበረበት_ዕለት ነው፡፡ 1ኛ. አርሴማ፤ ቅድስት ወሰማዕት ኃያል ተጋዳሊት 2ኛ. ኢያሚኖስ፤ ጸሎትን የሚያሳርግ ካህን 3ኛ. አፍጢኖስ፤ ከብዙዎች የተመረጠ 4ኛ. በርቲኖስ፤ ጻድቅና ቸር 5ኛ. ጢሞና፤ በመላላክ ሥራ አገልጋይ የኾነ 6ኛ. ጢሞዓና፤ ተአጋሽና ጸዋሚ 7ኛ. ዘኬዎስ፤ ከከበሩ የከበረ 8ኛ. እስጢፋኑ፤ ተጋዳይና የበደሉትን ይቅር ባይ 9ኛ. አርሞና፤ ከጎልማሶች ይልቅ ደም ግባቱና መልኩ ያማረ 10ኛ. ኪርያኮስ፤ ሥጋውን ያላረከሰ ንጹሕ 11ኛ. አንጥያኮስ፤ ቡሩክ የኾነ የአቡሪ ልጅ 12ኛ. ያዕቆብ፤ የእግዚአብሔር ታማኝ የኾነ 13ኛ. ቡራኬሌስ፤ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የኾነ 14ኛ. አስቂርያቆስ፤ ክርስቶስን የሚወደው 15ኛ. አስኪርያኖስ፤ ባለሟል የኾነና ግርማው የሚያስፈራ 16ኛ. ሚርያኖስ፤ ፊቱና መልኩ ደስተኛ የኾነ 17ኛ. ትትግርጦስ፤ ወደ ንስሐ የተመለሰ 18ኛ. ያስቲኖስ፤ የሚፈርድና የሚበይን 19ኛ. ጥልያኖስ፤ ያላመኑ ሰዎችን የሚገስጽ 20ኛ. ዑልያኖስ፤ የዚህ ዓለም ጥበብ መምህር የኾነ 21ኛ. ጴርቅላስ፤ በስም አጠራርና በሽምግልና መልካም የኾነ 22ኛ. ኬብያኖስ፤ ተጋዳይ የኾነ 23ኛ. ጴጥሮስ፤ የጠራ የባሕርይ ዕንቊ 24ኛ. ጰኵንዮስ፤ የሮምያ ሹም 25ኛ. ሐናንያ፤ የዋህና ሽንገላ የሌለው 26ኛ. ሐሊባኖስ፤ ጾምና ጸሎትን የሚወድ 27ኛ. ኤስያኖስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጎልማሳ የኾነ 28ኛ. ኤልያብ፤ በረኛና የሰማዕት መጀመሪያ፡፡ ሰላም ለዘአዕረፉ ምስሌኪ ፳ወ፯ቱ ሰማዕታት፤ ረድኤቶሙ ትረድ ላዕሌየ ዘምስለ ብዙኅ ምሕረት፡፡ ወኀበ ሀለወ ስሞሙ ምስለ ስምኪ ቅድስት፤ ዓዲ ኢይቅረብ አርሴማ ሕማመ ብድብድ ወሞት፤ በኵሉ አዝማን ወበኵሉ ዓመታት፡፡

#ላልሰሙት_አሰሙ_Shareeeee_ለመጀመሪያ_ጊዜ_በኹሉም_የአዲስ_አበባ_አብያተ_ክርስቲያናት_የሚደረግ_ልዩ_ጕባኤ #ልዩ_ማሳሰቢያ_ከዛሬ_ዐርብ_ታኅሣሥ_5_እስከ_እሑድ_ታኅሣሥ_7_ለ3ት_ተከታታይ_ቀናት_በአዲስ_አበባ_በሚገኙ_አብያተ_ክርስቲያናት_ልዩ_የዐውደ_ምሕረት_የሠርክ_ጕባኤ_ስላለ_በሚቀርባችሁ_በማንኛውም_ቤተ_ክርስቲያን_እንድትሳተፉ_ቤተ_ክርስቲያናችን_ጥሪዋን_ታስታላልፋለች__መርሐ_ግብሩ_ኹሉን_ባቀፈ_መልኩ_ለመጀመሪያ_ጊዜ_በመኾኑ_እንዳያመልጣችሁ_፡፡ *ቃሌንም በአፉ አድርጋለሁ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ ዘዳ. ፲፰፥፲፰ **"ድምፃቸው ወደ ምድር ኹሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ" መዝ ፲፰፥፬ ***‹‹የእግዚአብሔር ድምፅ ነው፤ …… የእግዚአብሔር ቃል ያድግና ይበዛ ነበር፡፡›› ሐዋ.፲፪፥፳፪

#✤#በኣታ_ለማርያም፤ እመቤታችን አባትና እናቷ ኢያቄምና ሐና በስዕለት(ለቤተ መቅደስ ሊሰጡ ብፅዓት ገብተው) ያገኟት ናት፡፡ በአባት በእናቷ ቤትም ፫ ዓመት ተቀመጠች፤ ከእንግዲህ ወዲያማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባኤ አድርጎ ቆያቸው። **ከዚያውም ደርሰው እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ ፯ እጅ አብርታ፥ ከመብረቅ ፯ እጅ አስፈርታ፥ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታየቻቸው፤ እነርሱም እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምን እንጋርድላታለን? ብለው ሲጨነቁ በዚህም መካከል እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኀብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች። ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው፡፡ ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር ላንተ ነው የሚኾነውና ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፤ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ ሲጠጋ ወደ ሰማይ ራቀው፥ መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደ ሰማይ ራቃቸው፥ መጠቃቸው፡፡ **ከዚህም በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡ ***ሁለተኛም ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ነገር የሚያውቅ የለም፤ ሕፃኒቱን ከዚያው ትተሽ አንቺ ወዲህ ነዪ አላት፤ እሽ ብላ ሕፃኒቱን እዚያው ትታ ወደነሱ ሄደች፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወርዶ ፩ ክንፉን ጋርዶ ፩ ክንፉን አጎናፅፎ ኅብስቱን አብልቷት፥ ወይኑን አጠጥቷት፤ እመቤቴ ሆይ መንገድ ባስመታሁሽ ማሪኝ ብሎ የብርሃን መሶብ፥ የብርሃን ጽዋ ይዞ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ **ሕዝቡም የምግቧማ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋራ ምን ያጋፋታል፤ ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን እንጂ ብለው ዙፋኑን ዘርግተው፥ ምንጣፏን አንጥፈው፥ መጋረጃውን ግራና ቀኝ ጋርደው ከቤተ መቅደስ አኖሯት፡፡ ***ይኸውም የተደረገው ታኅሣሥ ፫ ዕለት ነው፤ በአታ የሚለው ስያሜም የተሰጠው በዚሁ ነው፡፡ ‹‹አመ ፫ ለታኅሣሥ በኣታ›› እንዳለ መቅድመ ተአምር፡፡ በዚህም፤ ✤#መቅደሲቱ_ወደ መቅደስ ገባች፤ #ቅድስቲቱ_ወደ ቅድስት ገባች፤ #ክብርቲቱ_ወደ ክብርት ቤቷ ገባች፤ #ልዩ_የሆነችው_ወደ ልዩ ሥፍራ ገባች፤ #ቅድስተ_ቅዱሳኗ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገባች፤ #ንጽሕተ_ንጹሐኗ ወደ ንጽሕ አዳራሽ ገባች፤ #ቤተ_መቅደሷ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች፡፡ ሊቃውንትም ‹‹መቅደስ ዘኢትትነሠት /የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ››/ እያሉ አመሠገኗት፡፡ **እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች፤ ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላእክት ጋራ እየተጫወተች 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ፤ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ፲ተ ወ፪ተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ወስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ። ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ››። እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ***ምግቧ ከየት የተገኘ ነው ቢሉ በገበሬ እጅ ያልተዘራ በቤተ ሰብእ እጅ ያልተሠራ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ ያማረ የተመረጠ ነው እንጂ ፡፡ ‹‹ኦ ድንግል አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይኪ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እም ሰማየ ሰማያት ዘበሰለ፡፡ ኦ ድንግል አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይኪ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድ›› (ድንንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን እንጂ፡፡ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጥን ነው እንጂ፡፡) /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/። ***ስታድግም በንጽሕናና በቅድስና ነው፡፡ ‹‹ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና ኖርሽ እንጂ።›› /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/ ***እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ብዙ የክፋት ምክር ይመክሩ ነበር። ከዚህም ውስጥ አንዱ መጥቁል ወደሚባል ጠንቋይ ሄደው ‹‹ፍታሕ ማዕከሌነ ኢያቄም ወሐና›› ብለው እመቤታችንን እንዲያጠፋ እጅ መንሻን ሰጡት፤ መጥቁልም በመካከል አይሁድ በኋላ ሁነው ነጋሪት እየጎሰሙ፥ እምቢልታ እየነፉ እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ለመግደል ለቤተ መቅደስ ፪ ምንዳፈ ሐፅ ሲቀራቸው፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ እዚያ ድረስ ያልተደረገና ያልተነገረ መብረቅ ነጎድጓድ ወርዶ አጋንንትንም፥ መጥቁልንም፥ አይሁድንም ቀጥቅጦ አጠፋቸው። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በማግሥቱ ወጥታ አይታ መጥቁል ሆይ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንህ ካንተ መከራ መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ከዚህ በኋላ በድኑ ለዝክረ ነገር የ፫ ቀን መንገድ እየሄደ ይሸት ጀመር። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊሮስ፣ ሰራሰቅሰሬል›› ብላ የአምላክ ኅቡዕ ስምን ብትደግም መሬት ተከፍቶ ዋጣቸው ከነሥጋቸውም ሲኦል ወረዱ፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እጅግ ታፈረች የሚናገራት ጠፋ ‹‹ኦ ግርምት ድንግል›› /እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም/። ✤#በዓለ_ሢመቱ_ለቅዱስ_ፋኑኤል_ሊቀ_መላእክት፤ #ሰዳዴ አጋንንት ነው፤ /ሄኖክ 10፥8፣ ድርሳን ዘፋኑኤል/ #መጋቤ ድንግል ነው፡፡/ተአምረ ማርያም/ #ማኅሌታዊ ነው፤ #በመንበረ መንግሥቱ ዙሪያ ከሚቆሙት ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው፡፡ /ሄኖክ 20፥39/ #በአራቱ የዓለም ማዕዘናት ሹም አንዱ ነው፡፡ #ለመልካም ነገሮች ከሚራዱ መላእክት አንዱ ነው /መዝ. 33፥7/ #ካህነ ንስሐ ነው /ሄኖክ 10፥5/ #ዐቃቤ ጻድቃን ነው፡፡ /2ኛ ነገ. 6፥14/ #ምስለ_አብያጺሁ_ከመ_አብ_እንዘ_ይሴስየኪ_መና፤ #ፋኑኤል_ጽጌ_ነድ_ዘይከይድ_ደመና፡፡ ✤#ኢትዮጵያዊው_አቡነ_ዜና_ማርቆስ_በዓለ_ዕረፍታቸው ነው፡፡ እኒህ ታላቅ አባት በምድረ ጉራጌ በሚገኘው በምሁር ኢየሱስ ገዳም 40 ዓመታትን ሱባኤ የገቡ፤ ምድረ ጉራጌን (ሙሉ ሸዋን ጨምሮ እስከ ደቡብ) እንዲሁም በሌሎችም የሃገራችን ክፍሎች ያስተማሩ፤ በርካታ ሊቃውንትን /አባ ጽጌ ድንልንና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታን ጨምሮ ሌሎችን ሊቃውንትም/ ያፈሩ ፈርጥ ሲኾኑ፤ በስተመጨረሻ በተአምራት የተሞላውን ታላቁን ገዳም ደብረ ብሥራትን (ጅሩ) መሥረተው በክብር አርፈዋል፡፡ #ከዋይዜማው_ጀምሮ_የሚቆመውን_የበኣታ_ለማርያም_ሥርዐተ_ማኅሌትንም_አቅርበንላችኋል_ላልደረሰው_አዳርሱ፡፡

✤#የበኣታ_ማርያም_አብያተ_ክርስቲያናት፤ #ደብረ ኤረር በዓታ ወልደታ፤ በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአብራሃ ወአጽብሃ የተመሠረተ፡፡ #ደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ ዑርኤል ወበኣታ፤ ጎንደር ከተማ፤ ከ300ዓመታት በፊት በጎንደር ዘመነ መንግሥት የተሠረተችና የታች ቤት አቋቋም ዋና ምስክር ጕባኤ ቤት፡፡ #ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ወስዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት፤ /አ.አ. መካነ አጽሙ ወተዝካረ ስሙ ለዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ 1910ዓ.ም. በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ለአባታቸው ምኒልክ መታሰቢያ የተሠራ/ #መቀሌ በኣታ ለማርያም #ባሕር ዳር በኣታ ለማርያም፤ #ጮቢ በኣታ ለማርያም ገዳም፤ ሸዋ #ሆሳዕና በኣታ ለማርያም፤ /በዛፍ ላይ ድንቅ ተአምር የሚታይበት/ #ጂንካ በኣታ ለማርያም፤ #ደብረ በአታ ለማርያም /ሂውስተን አሜሪካ/ ✤#የቅዱስ_ፋኑኤል_አብያተ_ክርስቲያናት፤ #ጋዥ ሜዳ ድሬ አክርሚት ፋኑኤል፤ /ሰሜን ሸዋ፥ ሃገረ ማርያም/ #አዲስ አበባ ካራ ቆሬ ቅዱስ ፋኑኤል ቤ.ክ. #አዲስ አበባ አያት ቅዱስ ፋኑኤል ✤#የአቡነ_ዜና_ማርቆስ_አብያተ_ክርስቲያናት፤ #ምሁር ኢየሱስ ገዳም /ጉራጌ ሃገር/ #ደብረ ብሥራት /ሰሜን ሸዋ፥ እነዋሪ፥ ጅሩ/ …………. ሌሎችን በየአጥቢያችሁ ያሉትንና የምታውቋቸውን አብያተ ክርስቲያናት እናንተ ጨምሩበት

ዋርያ ነግሮናል ያዕ 5፡17-20፡፡ ከኤልያስ ብዙ ነገር ወይም ተግባር ስለሚማሩ ከቅዱስ መጽሐፍ ከ 1ኛ ነገሥ 17፡1 ጀምረው እስከ 2ኛ ነገሥ 2፡11 ረጋ ብለው ይመርምሩ ክርስትናዎትንም ይፈትሹ፡፡ #ታኅሣሥ_1 #ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው፤ *በጥንታዊው ደብረ ኃይል እንጦጦ ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ፤ *በደብረ ኤልያስ ጎጃም፤ *በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን (በድርብነት አለ) *በብሥራተ ገብርኤል ቅዱስ ኤልያስ (ኋላ ብሥራተ ገብርኤል በመባል በሚጠራው) *በሻሸመኔ ልደታና በሌሎችም የቅዱስ ኤልያስ አድባራትና ገዳማት ይከበራል፡፡ ሥርዐተ ማኅሌቱን በዜማ መጻሕፍት ያልተጻፈ በመኾኑ ላልደረሰው በ Facebook, Email, Viber, Xender, Bluetooth በማድረስ ይተባበሩ፡፡ #በጸሎታችሁ_ሰ/ት/ቤታችንን#አትርሱን፨ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/joinchat/AAAAAE2hgYCjGkwz9N1jIw /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

#ኤልያስ የሚመስጠውንና ብዙ ቁም ነገር የሚሸመትበትን የነቢዩ አልያስ ታሪክ እነሆ፤ #ደመና ደመና ….. በሠረገላ፤ ኤልያስ ኤልያስ ….. በሠረገላ፤ በእሳት ሠረገላ ….. በሠረገላ፤… ሰወረው ደመና ….. በሠረገላ፤ ኤልያስ ያረገው… በሠረገላ፤ በእሳት ሠረገላ…. በሠረገላ፤ በጾም በጸሎት ነው …. በሠረገላ፤ አይደለም በሌላ …. በሠረገላ፡፡ እንኳን ለቅዱስ ኤልያስ ዓመታዊ ክብረ በዓል (የልደት ቀን) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ፡፡ ✤ የሰማርያው ነቢይ ኤልያስ ከቅዱሳን አበው ነቢያት አንዱ ሲኾን አባቱ ኢያሴዩ ይባላል፡፡ በነቢይነትም ሆነ በብቃት ኤልያስን የሚያክል፤ በሥራው የሚወክል ከእሱ በፊትም ኾነ በኋላ በተአምራት የተሞላ እሳት ለበስ ነቢይ እሱ ከመረጠው ከደቀ መዝሙሩ ከኤልሳዕ በቀር አልተነሳም፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ከኢዮርብዓም እስከ እርሱ ድረስ ለአያሌ ዓመታት በሰይጣን ግፊት በሰው ሠራሽ ጣዖት የተመረዘ በኃጢአትም ረዘረዘ፣ የግፈኛው አክአብና የዘማዊቷ ኤልዛቤልን መንግሥት በሦስት ዓመት ከመንፈቅ በከባድ ድርቅ በመናጥ፣ እንዲሁም አፈር እንደበላው ብረት የዛገ አስተሳሰባቸውን በሰው ደምና በቅሚያ ገንዘብ የተሞላ ሰውነታቸውን በማን አለብኝነት ያበጠ ልባቸውን እንደሰም በማቅለጥ የሚይዙትንና የሚጨብጡትን ያሳጣ በፈጣሪው ለዚህ ሥራ የተመረጠ ሰመ ጥር ነቢይ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ነውና፡፡ ኤልያስ የከተማ ነቢይ ብቻ አይደለም ባሕታውያን ተብለው ከሚጠሩት ነቢያተ ጽድቅም አንዱ እንደነበር ሕልውናው ምስክር ነው፡፡ (( ኤልያስ ብዙ ነገር ስለሚያስተምር የቀና እምነቱን ውጤት ጥቂት መመልከት እኔ ማነኝ ለሚሉት እጅ ይዞ ይመራል፡፡ ✤ 1. ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት እንዲከለከል ምድርም የተከሉባትን እንዳታጸድቅ የዘሩባትን እንዳታበቅል ለባለንብረቱ አመለከተ ይህም ጥያቄው ከእግዚአብሔር መልስ አግኝቷል፡፡ ነገሥ 17፥1-2፡፡ ከዚህ ላይ የሊቀ ነቢያት ሙሴንና የኢሳይያስን ቃል ያስጠቅሳል ዘዳ 32፥1-4፣ ኢሳ 1፥2-5፡፡ በእነዚህ እስከፊ ዓመታት ውስጥ በመሪዎች አመፅ በኤልያስ ተግሣጽ የሚመለከተውም የማይመለከተውም የሚልሰውና ሚቀምሰው አጥቶ በዋለበት እንደ ቅጠል ረገፈ እንደሻሸተ ነጠፈ፡፡ የኀጥአን ፍዳ ጻድቅ ይደፋ ይሏል ይህ ነው፡፡ ዛሬም በአምስቱ ክፍለ ዓለም የብዙኃኑ እልቂት ሲፈጸም የሚታየው በጥቂት እግዚአብሔር የለሽ ሰይጣን ጁንታዎች ሽፍቶች መሆኑን ከአክአብና ኤልዛቤል ይማሯል፡፡ ይህን የኤልያስን ጠበቅ ያለ እገዳ ከስምንት መቶ አምሳው ነቢያተ ሐሰት ካህናተ ጣዖት አንዱም ወደ ሚመለከተው በጸሎቱም ሆነ በመሥዋዕቱ አመልክቶ ሊያስነሳ ወይም ለማስነሳት የቻለ የለም፡ ጠንቋዮችና አታላዮች በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ ከቤተ መንግሥት ተለይተው አይርቁም፡፡ 1ኛ ነገሥ 18፥22፣ዳን 2፥1-14፡፡ ✤ 2. አመጸኞች አክአብንና ኤልዛቤልን ምንነታቸውን ካሳወቀ በኋላ የዘጋውን ለመክፈት ወደ ፈጣሪው በመጸለይ ዝናም አዝንሟል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 18፥41-46፣ ያዕ 5 17-18 እግዚአብሔር ለወዳጆቹ የገባውን ቃል ኪዳን አያጥፍም አቁም ሲሉት ያቆማል ስጥ ሲሉት ይሰጣል እንጂ ምን አገባቸው ብሎ እንደፈለገው አያደርግም፡፡ የእግዚአብሔር ሐዋርያ ስለ ኤልያስ ማንነት ሲያደንቅ ኤልያስ እንደኛ ሰው ነበር ዝናም እንዳይዘንም ከለከለ እንደገናም እንዲዘንም አደረገ በማለት በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖች ከቀና ክርስትናቸው ምን እንደሚጠበቅባቸው ከእምነታቸው ምን ማግኘት እንዳለባቸው ይጠይቃል ያዕ.5፥13-20፡፡ ዛሬስ ምን ይመስሎታል፡፡ ኤልያስ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ ነው፡፡ ነገር ግን በረዶ ያዘነመላቸው አንደኛ ሙሴ ዘፀ 9፥13-21 ሁለተኛ ኢያሱ 10፥9-12 ሦስተኛም ሳሙኤል 1ኛ ሳሙ 12፥1-19 ይመለከታል፡፡ ✤ 3. በተፈጥሮ የማይመስላቸው በቋንቋም የማይግባባቸው እንኳን ለሰው ሥጋ ሊያመጡ ከሰው ሥጋ የሚነጥቁ አሞራዎች ከየት እንደሚያመጡት የማይታወቅ እንጀራና ሥጋ ለምግብ እንዲያመላልሱለት አደረገ 1ኛ ነገሥ 17፥6-7፡፡ እነዚህ አሞራዎች ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ በጋ ከክረምት የለምንም እረፍት ኤልያስን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ እምነት ካለ ተአምር መሥራት አይገድም ይህንም ከኤልያስ ይማራል፡፡ ✤ 4.ለአንዲት መበለት ዱቄትና ዘይት አበረከተ፡፤ ኤልያስ ቁራሽ እየለመነ ያደረገውን ተአምር ልብ ይሏል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 17፥16-24፡፡ ✤ 5. ዱቄትና ዘይት ያበረከተላት ሴት ልጇ ቢሞት ከሞት አስነሳው 1ኛ ነገሥ. 17፥20-23 ይህች ሴት በእምነቷ አርአያነት ያላት ደገኛ ሴት ናት፡፡ ኤልያስን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ፣ ኀጢአቴንስ ታስብ ዘንድ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን ብላዋለች፡፡ ኤልያስም በእግዚአብሔር ኀይል ማንኛውንም ችግር ለመፍታት ሙሉ መብት ነበረውና ወዲያውኑ የሞተውን ብላቴና ጠጋ ብሎ ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት አስነስቶ የብላቴናውን እናት አስደስቷል 1ኛ ነገሥ 17 17-24 ሐዋርያ እምነት ጀግኖችን በመዘገበበት አንቀጽ ይችን ሴት ልብ ይሏል፤ ዕብ 11፥35፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ እናቶች ያስፈልቷል፡፡ ይህችን ሴት የሚመስሉ እናቶች 2ኛ ነገሥ. 4፥18-38 ፣ሉቃ 7፥11-17 ተመዝግበዋል፡፡ በሐዋርያት ሥራም ያሉት እናቶች ከእነዚህ ጋር ያነጻጽሯል የሐዋሥ 9 36-43፡፡ ✤ 6. ለብዙ ጊዜ በቤተ መንግሥት ተሰግስገው አክአብና ኤልዛቤልን በሐሰት ሲደልሉ ግብዝ ሕብረተሰቡን ሲያታልሉ ለፍቶ ያገኘው ገንዘቡን ሲሸልጉ በኀጢአት ሊያስወጉ የነበሩ ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖትን በሕብረተሰቡ ፊት እስከ መምህራቸው ሰይጣን በቅሌት አከናንቦ ሲያስቅባቸው ውሏል፤ 1ኛ ነገሥ 18 20 -29፡፡ ሰይጣን በሰማርያ በምድር እንደዚያ ቀን ሰው መዘባበቻ በመሆን የውርደት ቀን ገጥሞት አያውቅም፡፡ በገዛ አገሩና መንደሩ፡፡ 7. ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት ያቀረበው ንጹሕ መሥዋዕቱን ከሰማይ እሳት ወርዶ በሰው ፊት በላለት 1ኛ ነገሥ 18 30-40፡፡ በዚህም ማንነቱን በሰይጣንና በሰይጣን አቀንቃኞች ፊት አስመስክሯል፡፡ ✤ 8. ምግብና መጠጥ መልአክ ከሰማይ አመጣለት ያንን ተመግቦ ለአርባ ቀን ያለምንም ምግብ መጠጥ ተጉዟል 1ኛ ነገሥ 19፥5-7 ✤ 9. እሳት ከሰማይ በማዝነም ሊጣሉት የመጡትን መምለኪያነ ጣኦት ምሉአነ ኀጢአት የሰይጣን ሠራዊት በሰው ደም የሰከሩ በዲያብሎስ የሚመሩ ጠላቶቹን አጋይቷል 2ኛ ነገሥ 1 9-13 ✤ 10. በመጎናጸፊያው የዮርዳኖስን ባሕር ከፍሎ ከነ ደቀመዝሙሩ በደረቅ ተሸግሯል 2ኛ ነገሥ. 2፥11 ✤ 11. ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ918 ዓመተ ዓለም ሳይሞት በሕይወቱ መራራው ሞት ዕያየው በብርሃን ሠረገላ ወደሰማይ አርጓል 2ኛ ነገሥ. 2 6-9 ✤ 12. እንደ እያስፈላጊነቱ ከፈጣሪው ጋር ለብዙ ጊዜ ተነጋግሯል ከአንድ እስከ አስራ አንድ ያደረጋቸውን ተአምራት የፈጸመለት ታማኝ ፈጣሪው ሰው በሆነበት ወራት በተራራ ከጓደኞቹ ጋር ብርሃነ መለኮቱን ገለጠለት ማቴ 17 ፥3 ፡፡ ከዚህ ዓለም ከተሰናበቱ በኋላ ወደዚህ ዓለም መጥተው የፈጣሪጣቸውን ሰው መሆን ያዩ ከነቢያተ ጽድቅ ሙሴና ኤልያስ ብቸኞች ናቸው ብፁዓን ከተባሉት ሐዋርያትም ተቆጥረዋል፤ በዚህም ቅዱሳን ከሞት በኋላ እንደሚያማልዱም መስክሯል፡፡ ማቴ 13፥16-17፡፡ ኤልያስ ሰው መባል ወይም ተብሎ በመጠራት እንደማንኛውም ሰው መሆኑ መልአክ አለመሆኑን ሐ