uz
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 368 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 620-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 191-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 368 obunachiga ega bo‘ldi.

22 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -33 ga, so‘nggi 24 soatda esa -2 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 22.71% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 7.98% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 489 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 226 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 22 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 23 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 368
Obunachilar
-224 soatlar
+317 kunlar
-3330 kunlar
Postlar arxiv
#ኢ. #ና. #ን. #አ.  ‹‹#የጻፍሁትን_ጽፌያለሁ::›› #ኢ ፩ኛ) #፠#ኢየሱስ_፤ ፠ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከሥጋ ማርያም ጋር ተዋሕዶ፤ ከሁለት አካል አንድ አካል፥ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆኖ፤ በዘመነ ሥጋዌ ከተጠራባቸው ስሞች መካከል፤ ኢየሱስ፥ ክርስቶስ፥ አማኑኤል፥ መድኀኔ ዓለም፥ መድኅን፥ የሰው ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ ቃል፥ እግዚአብሔር ወልድ፥ አንድዬ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ጌታ፥ … የሚሉ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ፠ ኢየሱስና ክርስቶስ የሚሉት ስሞች ከጥንት ጀምሮ (የሰው አእምሮ ገና ያልበሰለ፤ ክፉዎች አይሁድም ነገሩን ለፌዝ፥ ለቧልት ያውሉት ነበርና፤ ምንም እንኳን በግልጽ ባየገለጹም)፤ በነቢያት የተነገሩና በመላእክት የተበሠሩ፤ የጌታን አምላክነት የሚያሳዩ፤ የጌታን አዳኝነት የሚያመለክቱ ስሞች ናቸው፤ /መ.አውሳብዮስ/፡፡   ለምሳሌ፤ ልበ አምላክ ዳዊት ‹‹እምቅድመ ፀሐይ ሀሎ ስሙ፤ ስሙ ከፀሐይ በፊት ነበረ፡፡›› /መዝ 71÷17/ ብሏል፤ እንዲሁም ነቢዩ ሙሴ በምሳሌ ጠርቶታል፤ የሊቀ ካህንነቱ አገልግሎት ሊቀ ካህኑ የክብርና የከፍታ ምልክት፣ የነዌ ልጅ ኢያሱም የአዳኛችንን ምሳሌ ተሸክሞ ነበር፡፡›› /ዘጸ. 25፥40፣ ዘሌ. 4፥5፡16፤ 6፥22/ ብሏል ይህንንም የመልክአ ኢየሱስ ደራሲም ‹‹አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ፤ አኅጉረ ፀር ወረሰ ኢያሱ፡፡›› (የስምህን አክሊል በራሱ ላይ አድርጎ የጠላትን ሀገሮች ኢያሱ ወርሷል) ብሎ አመስጥሮታል፡፡ • ይህንን ከዓለም በፊት የነበረውን ስሙን ከሰማይ ተቀብሎ ለእመቤታችን እንዲናገር የተላከው መልአክ፤ መጋቤ ሐዲስ ቅዱስ ገብርኤል ሲሆን ‹‹ስሙን የመሰየም›› ሥልጣን የተሰጣት ደግሞ እመቤታችን ናት፡፡ ˝ኢየሱስ ትይዋለሽ˝ /ሉቃ 1÷31/ ፠ #ኢየሱስ_ማለትም(ትርጓሜውም)፤ ሀ) መድኃኒተ ሥጋ ፥ መድኃኒተ ነፍስ ማለት ነው፡፡ * በዕብራይስጥ የሹኣ፥ ኢያሱ ወይም «ያሕዌ መድኃኒት ነው» የሚል ትርጉም አለው። ፠ እርግጥ ነው፥ በትንቢት፥ በምሳሌና በጥላ ቀድሞ ለተነሡት « አዳኞች» ኢያሱዎች ተሰጥቷል። (ለምሳሌ ዘካርያስ 3፥1 ላይ ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን ያስታውሷል።) ሆኖም ግን እነዚህ « አዳኞች» ያዳኑት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ነው፡፡ ያዳኑትም የእግዚአብሔርን ኃይልና ረድኤት አጋዥ በማድረግ ነው፤ ያዳኑት(የታደጉትም) ከምድራዊ ጠላቶቻቸው ስለሆነ ማዳናቸው ውሱን ነው፡፡ *አማናዊው ኢያሱ አዳኛችን ግን ያዳነው « ሕዝቡን» (የራሱን ሕዝብ) ነው። ያዳነውም እግዚአብሔር ተጠቅሞበት ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ስለሆነ መድኃኒት ሆኖ ነው። ሕዝቡን ያዳነውም «ከኃጢአታቸው» ነው። ይህ አነጋገር የሚገባው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። በመሆኑም እንደቀድሞዎቹ እግዚአብሔር በምሳሌና በጥላ ሳይሆን ራሱ በመካከላችን በማደሩ ‹‹አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር፡፡›› እንደ ሆነና በዚህም የነቢዩ የኢሳይያስ ትንቢት ፍጻሜ እንዳገኘ ነበር የእግዚአብሔር መልአክ የገለጠው። ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ማዳኑም የአምላክነቱ መገለጫ ነው። ለ) ሕዝቡን በኃጢአታቸው ከመጣባቸው ፍዳ የሚያድናቸው መድኀኒት ማለት ነው፡፡ /ማቴ 1፥21፣ ተረፈ ኤርምያስ) (ዳግመኛም ወገኖቹን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ኢየሱስ ይባላል፡፡ /ቅ.ኤፍሬም/፡፡) (‹‹ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን›› /ሰቈቃወ ድንግል/) ሐ) ኃጢአታችንን የሚያስተሠርይልን ማለት ነው፤ ‹‹አመ ይእኅዝዎ ለኢየሱስ ፀሐይ ጸልመ›› /ቅዱስ ያሬድ፥ ድጓ/ መ)  ዳግማይ አዳም ማለት ነው (የኢየሱስ የስሙ ቊጥር ከአዳም የስም ቊጥር ጋር የተባበረ ነውና) *ኢየሱስ፡- አ=40, የ=90, ሰ=7, ሰ=7 ድምር =144፤ *አዳም፡-አ=40, ደ=100, መ=4 ድምር =144 *ዳግማይ አዳም የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ወደ ኤዶም ገነት አገባው ማለቱ ኤዶም፡-አ=40, ደ=100, መ=4 ድምር =144 #ና. ፪ኛ) #፠#ናዝራዊ_፤ ከናዝሬት የመጣ /ማቴ 2፥ 23/፤ በሌላም ትርጕምም ቸር፥ እረኛ፣ በዕብራይስጥ ደግሞ የተለየ ፣ አክሊል የተቀዳጀ ፣ የተቀደሰ ማለት ነው፡፡ ፠ ‹‹ኢየሱስ ናዝራዊ አምላኮሙ ለናዝራውያን›› እንዲል /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፤ መጽሐፈ ምሥጢር/ ፠ ማቴ. 2÷23 «በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጻም ዘንድ ናዝሬት ወደ ምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ፡፡›› ፠ ትንቢቱ (በማቴዎስ ወንጌል የተገለጠው) ልጄ እንደ ሶምሶን ናዝራዊ ይባላል የሚል ነው፤ ነገር ግን በ66ቱም ሆነ በ81ዱ መጻሕፍት አይገኝም፤ መጽሐፉ በምርኮ ጊዜ ጠፍቷል፤ ይህም ከ66ቱ መጻሕፍት ሌላ መጽሐፍ የለም ለሚሉ ወገኖች ማስረጃ እንደሆነ አስተውል፡፡ *፠* በመጽሐፍ ቅዱስ ስማቸው የተጠቀሰው ናዝራውያን 2ት ናቸው እነርሱም ሶምሶንና ጌታችን፤ በምን ይመሳሰላሉ ቢሉ:: **ሶምሶን በተናቀች በአህያ መንጋጋ ጠላቶቹን እንዳጠፋ፤ ጌታም አይሁድ፣ አጋንንት፣ መናፍቃን በናቁት ሞቱ ሞትን አጥፍቷል፡፡ /መሳ. 15÷9-19/ **ሶምሶን በሕይወተ ሥጋ ካጠፋቸው አሕዛብ ይልቅ በሞቱ ያጠፋቸው ይበዛሉ፡፡ ጌታም በሕይወተ ሥጋ ሳለ ካጠፋቸው አጋንንት ይልቅ በሞቱ ያጠፋቸው ይበዛሉ፡፡ /ምሳ. 16÷23-31/ #ና. ፫ኛ) #፠#ንጉሥ_፤ አፄ፣ ባለዘውድ፣ ሹም፣ አለቃ፣ ማለት ነው፡፡ /ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም እንዲል፡፡/ #አ ፬ኛ) #፠#አይሁድ_፤ ማለት የታመኑ፣ ምስጉኖች፣ ምዕመናን ማለት ነው፡፡ ፠ አይሁድ የሚከው ቃል እስከ ባባሎን ምርኮ ድረስ ከ12ቱ ነገደ ያዕቆብ (እስራኤል) የይሁዳ ብቻ ነበረ፡፡ ከምርኮ በኋላ እስከ ክርስቶስ ድረስ ግን ለእስራኤል ሁሉ (ለ12ቱም ነገድ) መጠሪያ ሆኗል፡፡ /ዘፍ. 29፥ 35/ #የአይሁድ_ንጉሥ (#ማዕከላዊ_ስም) ፠ ሰብአ ሰገል ስም ማዕከላዊ (የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ) እያሉ ነው ለጌታ መብዓ ይዘው የመጡት፤ ስለምንድነው ቢሉ? * አምላክ (ስም ላዕላዊ) እያሉ ያልመጡበት፤ ሰማይና ምድር የማይችለው ምን ወስኖት ምን ችሎት ነው ብለው እንዳይዘባበቱባቸው፡፡ አንድም ትንቢት የተነገረልን ሱባዔ የተቈጠረልን እኛ እያለን እንዴት ለእነርሱ ተገለጠላቸው ብለው እንዳይዘባበቱባቸው፤ አንድም አሕዛብ ናቸው በየት አውቀውት ብለው እንዳዘብቱባቸው ነው፡፡ * የተወለደው ሕፃን (ስም ታህታዊ) እያሉ ያልመጡት፤ በእስራኤል ሃገር በአንድ ቀን ውስጥ ብዙ ሕፃናት ተወልደው ብዙ ሕፃናት ይሞታሉ፤ ስንቱን እናውቅላችኋለው ባሏቸው ነበርና፡፡

#ጸሎተ ሐሙስ ፣ #ሕጽበተ እግር ፣ #የምሥጢር ቀን † በዚህች ዕለት ጌታችን በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ ይህ ዕለት #የምሥጢር_ቀንም ይባላል፡ ፡ †በመብል ያጣነውን ክብር በመብል የተመለሰልን ዕለት በመሆኑ ጌታችን በሰጠን ሥልጣን ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር በማብቃቱ #የነጻነት_ሐሙስም ጭምር ይባላል ፡፡ † በዚህ ዕለትም ሌላ የተፈጸመው ተግባር #ሕጽበተ_እግር ነው፡፡ ወንጌሉ «፡ተነሣ፡ልብሱንም፡አኖረ፥ማበሻም፡ጨርቅ፡ወስዶ፡ታጠቀ፤ ፤በዃላም፡በመታጠቢያው፡ውሃ፡ጨመረ፥የደቀ፡መዛሙርቱንም፡እግር፡ሊያጥብና፡በታጠቀበትም፡ማበሻ፡ጨርቅ፡ሊያ ብስ፡ዠመረ። ፤ወደ፡ስምዖን፡ጴጥሮስም፡መጣ፤ርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡የእኔን፡እግር፡ታጥባለኽን፧አለው። ፤ኢየሱስም፡መልሶ፦እኔ፡የማደርገውን፡አንተ፡አኹን፡አታውቅም፥በዃላ፡ግን፡ታስተውለዋለኽ፡አለው። ፤ጴጥሮስም፦የእኔን፡እግር፡ለዘለዓለም፡አታጥብም፡አለው።ኢየሱስም፦ካላጠብኹኽ፥ከእኔ፡ጋራ፡ዕድል፡የለኽም ፡ብሎ፡መለሰለት። ፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፦ጌታ፡ሆይ፥እጄንና፡ራሴን፡ደግሞ፡እንጂ፡እግሬን፡ብቻ፡አይደለም፡አለው። ፤ኢየሱስም፦የታጠበ፡እግሩን፡ከመታጠብ፡በቀር፡ሌላ፡አያስፈልገውም፥ዅለንተናው፡ግን፡ንጹሕ፡ነው፤እናንተ ም፡ንጹሓን፡ናችኹ፥ነገር፡ግን፥ዅላችኹ፡አይደላችኹም፡አለው። ፤አሳልፎ፡የሚሰጠውን፡ያውቅ፡ነበርና፤ስለዚህ፦ዅላችኹ፡ንጹሓን፡አይደላችኹም፡አለው። ፤እግራቸውንም፡ዐጥቦ፡ልብሱንም፡አንሥቶ፡ዳግመኛ፡ተቀመጠ፥እንዲህም፡አላቸው፦ያደረግኹላችኹን፡ታስተውላ ላችኹን፧ >>ዮሐ 13 ፥ 1-10 በቃል ያስተማረውን ትኅትና በተግባር ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሮል፡፡ “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሁት ነኝና” እንዲል /ማቴ. 11፥29/፡፡ ይህንም ሲፈጽም አሳልፎ ሊሰጠው ያለውን የአስቆሮቱን ይሁዳ አለየውም፡፡ † በዚህ ዕለት ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጠው ተናገረ በዚህም ማንነቱን ጭምር ለይቶ ነገራቸው “እጁን በወጭቱ ያጠለቀው እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ነው” † የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ማደሩ #ጸሎተ_ሐሙስ ለመባሉ ምክንያት ነው ፤ /ማቴ.26፥36-46፣ ዮሐ.17/በዚች ዕለት ጌታችን በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ ይህ ዕለት የምሥጢር ቀንም ይባላል፡፡ በመብል ያጣውን ክብር በመብል የመለሰበት ዕለት በመሆኑ ጌታችን በሰጠን ሥልጣን ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር በማብቃቱ #የነጻነት_ሐሙስም ጭምር ይባላል ይባላል፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/finotehiwotee http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com