uz
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 396 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 567-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 182-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 396 obunachiga ega bo‘ldi.

28 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 15 ga, so‘nggi 24 soatda esa 5 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 21.32% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.24% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 282 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 576 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 17 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 29 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 396
Obunachilar
+524 soatlar
+287 kunlar
+1530 kunlar
Postlar arxiv
#ዕርገተ_እግዚእነ እንኳን ለጌታችን በዓለ ዕርገት፤ ኀሙስ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም. አደረሳችሁ፥ አደረሰን፤ ‹‹አልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለመሕያው፤ ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡›› እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ዮሐ.3፥13 * የሰውን ልጅ በመውደዱ ልዑል ባሕርዩን ዝቅ አድርጎ ከሰማይ ወረደ፥ ሥጋ ለበሰ፥ በምድር ላይ ተመላለሰ፥ ምድርን በኪደተ እግሩ ቀደሰ፥ ድውያንን ፈወሰ፡፡ * ፍጹም ሰው እንደ መሆኑ ተራበ፥ ተጠማ፤ ፍጹም አምላክ መሆኑንም ያስረዳ ዘንድ አምስት ገበያ ሕዝብ በአምስት እንጀራ በሁለት ዓሣ አጠገበ ማቴ.14፥19፡፡ * መምህረ ትሕትና ነውና ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በዚህ ዓለም ኖረ ለሐዋርያት ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን አስተማረ፤ ትምህርት በሚገባ ከተረዳለት በኋላ ለድኅነተ ዓለም በማዕከለ ምድር በቀራንዮ ተሰቀለ፡፡#ወገብረ_መድኀኒተ_በማዕከለ_ምድር_በምድር_መካከል_መድኀኒትን_አደረገ_እንዲል _መዝ.73፥12 * ነቢያት እንደተናገሩ በሞቱ ዓለምን አድኖ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጾ ተነሣ፡፡ የተተነበየውን ትንቢት ፈጽሞ ተነሣ፡፡ * በሞቱ ሞታችንን ሻረልን፤ ‹‹በሞቱ ሞትን አጠፋው›› እንዲል መጽሐፈ ኪዳን፡፡ ሕንፃ መነኰሳት ‹እርሱ በሁሉ ምሉዕ ሲሆን በመቃብር ለመቀበር ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘውት ታየ፡፡ ከመሬት ውስጥ በመቀበሩም ሙስና መቃብርን አጠፋ፤ ከሥሩም ነቀለው ከተነሣ በኋላ ትንሣኤውን መጀመሪያ ለማርያም መግደላዊት ገለጸ ማር.16፥9፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ትንሣኤው ሲመሰክር ‹‹ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረም፤ መጽሐፍ እንደሚል፤ በሦስተኛው ቀን ተነሣ፡፡ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፡፡ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ›› 1ቆሮ.15፥3-8 ብሎ ክርስቶስ ትንሣኤውን ለተከታዮቹ በሙሉ የገለጠ መሆኑን መስክሯል፡፡ *የሚያምኑ ፈሪሳውያንም ‹‹ትንሣኤው ምትሐት ነው›› እንዳይሉ እየታየ እያስተማረ እስከ 40 ቀን ድረስ መቆየቱን ይገልጽልና፡፡ በዚህም የአርባ ቀን ከትንሣኤ በኋላ ቆይታው ሦስት ቀን ጉባኤ አድርጎ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛ ጊዜ ነበረ እንዲል ዮሐ.21፥14 ይህንም ሊቃውንት አባቶቻችን፡- 1ኛ) *የትንሣኤ 2ኛ) *የአግብኦተ ግብር /ዳግም ትንሣኤ/ 3ኛ) *የጥብርያዶስ፡፡ በዚህ 40 ቀን ቆይታ መጽሐፈ ኪዳንን ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡ * ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም ዕርገቱን ለመናገር ከሰማየ ሰማያት መውረዱን አስቀድሞ ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ማንም ወደ ሰማይ የወጣ የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው ብሎ ከዕርገቱ በኋላ በየማነ አብ፥ በዘባነ ኪሩብ ፥ ወደ ሰማይ የወጣ ከእርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ አስረግጦ ነገረን፡፡ ሲጀምር ከሰማይ መውረዱን ማስቀደሙ ወረደ ብሎ ዐረገ ለማለት ይመቻል፡፡ ተጸነሰ ተወለደ ለማለት ጥንቱ ከሰማያት ወረደ ማለት እንደሆነ ሁሉ፤ ‹‹ተሰቀለ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ ተነሣ›› ለማለት ‹‹ጥንቱ፤ ተጸነሰ፥ ተወለደ፥ አደገ፥ ተመላለሰ፥ ሠላሳ ዓመት ኖረ›› የሚለው ነው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ዮሐንስ ጠርዝና ጠርዙን ይዞ ተናገረ፡፡ * ‹‹ወረደ ዐረገ›› የሚሉት ሁለት ቃላት የዓለም ድኅነት መነሻና መድረሻ ናቸው፤ እነዚህን ሁለት ቃላት ስናይ በሁለቱ መካከል የተፈጸሙትን የአምላክ ሥራዎች ልብ ማለት ይገባል፡፡ ቤት በመሠረት ይጀመራል በጣሪያ ይፈጸማል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ይህን የቤዛነት ሥራ ሲያስረዳ በዮሐ.1፥14 ‹‹ቃል ሥጋ ኮነ፤�ቃል ሥጋ ሆነ›› ብሎ ጀምሯል፤ ይህንንም ቃል ‹‹ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም›› በማለት ሰው መሆኑን ብቻ ሳይሆን በአርያም የሚኖር መሆኑን አስተማረን፡፡ እንግዲህ ጌታችን ዕርገት እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ ፥ እንደ ውኃ ፈሳሽ አለመሆኑን ቀድሞ በነቢያት የተነገረ፤ ኋላም በሐዋርያት የተመሰከረ መሆኑን ማወቅ ያስፈለጋል፡፡ #የክርስቶስ_ዕርገት_በትንቢተ_ነቢያት ፠ ‹‹ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም ጨለማ /ዲያብሎስ/ ከእግሩ በታች ነበር በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ በነፍሳትም ክንፍ በረረ፡፡›› መዝ.17፥9 ፠ ‹‹አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ መዝ.46፥5 ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ ፥ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ›› መዝ.67፥18፡፡ ፠ ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ፤ በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ›› መዝ.67፥33፡፡ #የክርስቶስ_ዕርገት_በትምህርተ_ሐዋርያት ፠ ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ማር.16፥19 ፠ ‹‹እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡››�ሉቃ.24፥50 ፠ ‹‹ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው፤ እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ ለብሰው ሁለት ሰዎች /መላእክት/ በአጠገባቸው ቆሙ ደግሞም ‹‹የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት ዳግመኛ ይመጣል፡፡›› አሏቸው››� ሐዋ.1፥9-12 በማለት ሐዋርያት የክርስቶስን ዕርገት ከመላእክት ጋር ሆነው እንደተመለከቱ ደስታውን እንደተካፈሉ ቅዱስ ሉቃስ ጽፎልናል፡፡ በትንሣኤው ነጭ ልብስ ለብሰው የታዩ መላእክት የደስታ ዘመን ነው ሲሉ በዕርገቱም ነጭ ልብስ ለብሰው የዕርገቱን የምሥራች ለሐዋርያት አብስረዋል፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot .YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

#ግንቦት_21_ደብረ_ምጥማቅ_ማርያም ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘግንቦት_21፡፡ ደብረ_ምጥማቅ_ማርያም የምናከብርበት ምክንያት #ግብጻውያን ክርስቲያኖች ከግንቦት 21 እስከ 25 የእመቤታችንን በዓል (ምሰሶ አቁመው፥ አጎበር ጥለው፥ ድንኳን ተክለው፥ ድባብ ዘርግተው ያከብራሉ፤ እመቤታችንም ከቅዱሳን ጋር በመገኘት ትባርካቸዋለች፡፡) እነዚህ 5ት ቀናትም #ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት 5ቱን ከተ.ቊ 25ኛ እስከ 29ኛ ያለውን ይይዛሉ፡፡ እነርሱም፤ ፠25ኛና 26ኛ፤ ግንቦት #21 ና 22 ቀን በግብጽ ሃገር ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምዕመናን በግልጽ የታየችበት ነው፡፡ ፠27ኛ፤ ግንቦት 23 ቀን ደብረ ምጥማቅ በተባለች ቦታ የታየችበት ነው፡፡ ፠28ኛ፤ ግንቦት 24 ተሰዳ ግብጽ የገባችበት ነው፤ /ኢሣ.1 9፥11፣ ማቴ.2፥13-15/ ፠29ኛ፤ ግንቦት 25 ልጇ መድኀኔዓለም ክርስቶስ የደረቁ በትሮችን ተክሎ ያለመለመበት በዓል ነው፡፡ እነዚህ ከላይ ያየናቸውን የደብረ ምጥማቅ በዓላት (ከግንቦት 21-25) በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በግብፅ ተነሥቶ የነበረው ንጉሥ የግብጽ ክርስቲያኖች በዓሉን እንዳያከብሩ በመከልከሉ፤ ኢትዮጵያውያንም ይህንን በዓል ለማክበር ወደ ግብፅ ይሄዱ ነበርና ፤ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ለመጽናኛ እንዲሆን በሃገራችን የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያምን መሠረተ፤ እመቤታችንም ብዙ ቃል ኪዳንን ሰጠችው፤ ይኸው ቃል ኪዳኗ ሳይታጠፍ በጻድቃኔ ማርያም ዛሬ ድረስ ስፍር ቊጥር የሌለው ብዙ ተዓምራትና የምሕረት ሥራ የሚፈጸምባት ቅዱስ ቦታ ኾና ትገኛለች፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ በሃገራችን ግንቦት 21 የደብረ ምጥማቅ ክብረ በዓል በስሟ ተሰይሞ ! በዋነኛነት የሚከበርባቸው ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፤ *1ኛ) #ደብረ_ምጥማቅ_ጻድቃኔ_ማርያም_ገዳም /ሰሜን ሸዋ/ *2ኛ) ሐመረ ብርሃን ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን /ጎንደር ከተማ/ *3ኛ) ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም /አዲስ አበባ/ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #ግንቦት_24_በዓተ_ግብጽ_፤ እመቤታችን እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከልጇና ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋር ለ3 ዓመት ከ6 ወር ከተሰደዱ በኋላ ወደ ግብጽ ሃገር ገብታ በሰላም ያረፈችበት ቀን ነው፡፡ #ግንቦት_24_በዓተ_ግብጽ *በአዲስ አበባ ታቦተ ሕጉ የሚነግሥባቸው ቦታዎች፤ ፠እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቅድስት ቊስቋም ማርያም፡፡ (365ት ቀናት ሙሉ ዝክር በማኅበረ መድኀኔ ዓለም አዳራሽ የሚዘከርባት ቤ/ክ) ፠ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን፡፡ (የቤ/ክርስቲያኑ ዐጸድ እጅጉን ልብን የሚገዛና የሚማርክ) ፠ ቃሊቲ ደብረ ቊስቋም ማርያም፡፡ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ቀ.ደ.ሰ.መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት፡፡ ꔰ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ꔰ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

አቡነ ዓቢየ እግዚእ እስከዛሬ_ድረስ #በላስታ_ተራራ_ጭላዳ_እህል_እንዳይበላ_ለገዘቱት #በጎንደር_ከተማ_ጅብ_እንስሳቶችን_እንዳይበላ_ለገዘቱት፡፡ ለታላላቆቹ አባቶች ለአቡነ ዓቢየ እግዚእና ለአቡነ ዮሴፍ ዓመታዊ በዓል (ግንቦት 19) በሰላምና በጤና አደሳችሁ፡፡ /#በጻድቃን_ተዓምራት_ማድረግ_ለምትጠራጠሩ፤/ #ጻድቃን_ከበዓለ_ዕረፍታቸው_በኋላ_ዛሬም_ከማማለድም_አልፈው_በቃልኪዳናቸው_ተዓምራት_እንደሚያደርጉ_ኑና_እዩ_ተመልከቱ፡፡ ተዓምራትን ማየት ለምትፈልጉ ኹሉ ሂዳችሁ እዩ!!!!!)፡፡ ፠ ክብረ በዓላቸው ✍️ የአቡነ ዓቢየ እግዚእ በተንቤን መረታ ደብረ መድኃኒት፣ በጎንደር ከተማ ጥንታዊ በኾነው በዓቢየ እግዚእ ኪዳነምሕረት፣ በመቀሌ እንዳ ገብርኤል /እንዳ አቡነ ዓቢየ እግዚእ/፣ በአዲስ አበባ ሞጆ አካባቢ ባለው ቤ.ክ በድምት ይከበራል፡፡) እንዲሁም ✍️ (የአቡነ ዮሴፍ በላስታ ላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኘውና ወደ ላለበላ የሚጓዝ ኹሉ ሊያየው በሚችል በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘውና በኢትዮጵያ በከፍታ ከራስ ደጀን ተራራ ቀጥሎ በሚገኘው የዋሻ ገዳማቸው ይከበራል)፡፡ ሁለቱም ቅዱሳን አስካሁን ጊዜ ድረስ የሚታይ ባለ አስደናቂ የቃልኪዳን ተዓምራት አላቸው፤ አቡነ ዮሴፍ ከላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ገዳማቸው #ጭላዳ_እህል_ጠባቂ_ሳያሻው_እህል_እንዳይበላ_ገዝተውታል፤ አቡነ ዐቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ቦታ (ለምሳሌ በጎንደር ከተማ) አሁንም ድረስ #ጅብ_እንስሳቶችን_እንዳይበላ_ገዝተዋል፡፡ #አቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋቱ * በወሎ ላስታ ሰውንና ዝንጀሮን በቃል ኪዳን ያስተሳሰሩ #እስከዛሬ_ድረስ_ዝንጀሮ_እህል_እንዳይበላ_የገዘቱ፤ * እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው፤ * ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑ (እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባና አቡነ ዘርዓ ቡሩክ) ናቸው፤ * ወደ ደብረ ሐዊ በመሄድ ሱባዔ ገብተው ቅዱስ ያሬድን በተሰወረበት የተመለከቱ፤ * ገዳማቸው በላሊበላ በቅርበት አቡነ ዮሴፍ ተራራ ተብሎ በሚጠራ ተራራ ቦታ ላይ የሚገኝ የዋሻ ቤ.ክ አላቸው፡፡ #አባ_ዓቢየ_እግዚእ_፤ * አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእ እና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ፡፡ * አጥምቀው 'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጕመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው:: * በሕፃንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ፡፡ * ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኰስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኵሰዋል፡፡ * በደብረ በንኰል ገዳም በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያንን አግኝተዋል፤ በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር፡፡ ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል፡፡ * ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ፡፡ ከትግራይ እስከ ደንቢያ ሃገረ ስብከታቸው ነው:: * አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ፤ ቀኑ ነሐሴ 10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ፤ ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ፤ ይህን ድንቅ ያዩ ከ1,000 በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል፤ ይህም ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል:: * ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ፤ ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች፤ ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ፥ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር፤ በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ፥ እባብና መሰል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት፤ ይህንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ፤ በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ፡፡ የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ ‹‹በስምህ የተማጸኑ፥ በቃል ኪዳንህ ያመኑ፥ በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም፤ በሰማይም እሳትን አያዩም፤ ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም፡፡›› ብሏቸው አርጓል፡፡ ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል፡፡ ዛሬም ድረስ ከብቶችን ጅብና መሰል አውሬ እየበላ የሚያስቸግራቸው ምዕመናን ገድላቸውን ሲያስነብቡ ይርቃሉ፡፡ * አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው፥ 3 ሙታንን አስነስተው፥ ብዙ ድውያንን ፈውሰው፥ ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው፥ የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው፥ በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል፡፡ #ግንቦትት ፲፱፤ #በዓለ_ዐቢየ_እግዚዕ፡፡ #በመላው_ዓለም_የአቡነ_ዐቢየ_እግዚእ_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ #በአዲስ_አበባ_የሚከበርባቸው_ #፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል)፤ አድራሻው፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ብሥራተ ገብርኤል፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(መርካቶ) → ሜክሲኮ → ብሥራተ ገብርኤል፤ ፪. ኤረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፤ (የአቡነ ዐቢየ እግዚእ ክብረ በዓልና የኤረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ቅዳሴ ቤቱ) አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ጎሮ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ጎሮ፡፡ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፡፡ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር ከተማ → አራዳ (ቀበሌ 16)፡፡ ፪. ተንቤን መረታ ዐቢየ እግዚእ ገዳም፤ አድራሻ፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ተንቤን፥ መረታ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → ተንቤን፡፡ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → በአዲዓርቃይ (በዳንሻ ሁመራ) → ሽረ → አኵስም → ተንቤን፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot .YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .