uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 622 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 302-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 181-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 622 obunachiga ega bo‘ldi.

08 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 67 ga, so‘nggi 24 soatda esa 14 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 8.25% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 4.62% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 1 288 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 721 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 12 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 09 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 622
Obunachilar
+1424 soatlar
+867 kun
+6730 kun
Postlar arxiv
#አስቸኳይ! ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል። +++++++++++++++++++++++++++++++++++ (ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ) የጸጥታ ኃይሉ ፎቅ ላይ በመሆን በቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ወዳሉት ምእመናን በስናይፐር እየተኮሰ ሲሆን በዚህም አንዲት ሴት ተገድላለች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምእመናንና ምእመናት ቆስለዋል። ከውጪ በኩልም ሕገ ወጡ ቡድን ብር በመክፈል ያደራጃቸው ቡድኖች ድንጋይ በመወርወር ላይ ናቸው በዚህም የቤተ ክርስቲያኑን በር ሰብረውታል። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ጌዲዮና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በተለያየ አቅጣጫ እየተተኮሰ እንደሆነና የጸጥታ አካላት የመከላከል ሥራ እንዳልሠሩ ገልጸዋል። የከተማዋ ነዋሪ ያልሆኑ ግለሰቦችን በመኪና ጭነው እያስገቡ ነው ሲሉም ጠቁመዋል፣ ምእመናን አሁንም በጽናት እንዲጠብቁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አስቸኳይ! ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ በስናይፐር የታገዘ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል። የጸጥታ ኃይሉ ፎቅ ላይ በመሆን በቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ወዳሉት ምእመናን በስናይፐር እየተኮሰ ሲሆን በዚህም አንዲት ሴት ተገድላለች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምእመናንና ምእመናት ቆስለዋል። ከውጪ በኩልም ሕገ ወጡ ቡድን ብር በመክፈል ያደራጃቸው ቡድኖች ድንጋይ በመወርወር ላይ ናቸው በዚህም የቤተ ክርስቲያኑን በር ሰብረውታል።

"መንግስት ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰበሰበ ወራሪ ቡድን ጋር በማበር በጠራራ ፀሐይ ሕግ ሲጥስና የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው" - ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ) ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በመንግሥት አካላት የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን አስመልክቶ ጥሪ አቅርበዋል። ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባሠፈሩት መልእክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤተ ክርስቲያን እና በክርስቲያኖችን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የማሳደድ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቀዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ እናስከብራለን በሚል በትግራይ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰበሰበ ወራሪ ቡድን ጋር በማበር በጠራራ ፀሐይ ሕግ ሲጥስና የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነውም ሲሉ ድርጊቱን ኮንነዋል። የተፈጸመው ድርጊት ከዘር ጭፍጨፋ የሚተናነስ አይደለም ያሉት ብፁዕነታቸው የሕዝቡን ሰብዓዊ መብት ካላስከበረ መንግሥትነቱ ምን ላይ ነው ሲሉም ጠይቀዋል። ብፁዕነታቸው ለሻሸመኔ እና ምዕራብ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን ከዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ያልተናነውን ይህንን ዘመን በጾም በጸሎትና በክርስቲያናዊ ጥንካሬ እንዲያልፉ ያሳሰቡ ሲሆን የፌደራልና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚፈስሰውን በግፍ የኦርቶዶክሳውያን ደም እንዲያስቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። #TMC_Addia_Ababa

በሻሸመኔ ከተማ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሰማዕትነትን ተቀበለ! ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ) በዛሬው ዕለት ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ሻሸመኔ ይመጣል መባሉን ተከትሎ ጠዋት ሁለት ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተፈጸመ ሕዝቡን ለመጥራት በከተማዋ ያሉ አድባራት ደወል ደውለዋል። ይህንን ጥሪ ሰምቶ ሁሉም ምእመን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ ይጀምራል። በዚህ ጊዜ ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሔዱ ምእመናን የቤተ ክርስቲያኑ በር በመዘጋቱ ከውጪ ቆመው ነበር። በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የከተማው ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን ተኩስ መክፈቱም ነው የተነገረው። እስካሁን ድረስ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሰማዕትነትን መቀበሉንና በውል ያልታወቀ ሰውም በጥይት መመታቱን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ከጥቂት ዓመታት በፊት አስከፊ እልቂትና ውድመት የደረሰባት የሰማዕታት ከተማ ሻሸመኔ ዛሬም በሕገ ወጡ ቡድን ምክንያት ሞት ተደግሶላታል። ያለውን ሁኔታ ለማጣራት ወደ መልአከ ፀሐይ ቀሲስ ዮሐንስ ዘለዓለም የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ክፍል ኃላፊ የስልክ ቃለ ምልልስ አድርገን ነበር። ኃላፊውም ሁላችንም ለመሞት ተዘጋጅተናል ብለዋል። በመንግሥት በኩል ያለው ተጽዕኖም ከባድና መራር ነው ሲሉ አንስተዋል። ከጠዋት አንስቶ የአብያተ ክርስቲያናቱ በር በጸጥታ ኃይሎች ቢዘጋም ሕዝቡ አጥሩን እየገነጠለ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ቅጽር ጊቢ እየገባ እንደሆነም ነው የተሰማው። በሌላ በኩል በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት ዛሬ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚመጡ መረጃ ስለደረሳቸው የጭሮ ከተማ ሕዝበ ክርስቲያን በከተማው የሚገኙትን 4 አብያተ ክርስቲያናት በንቃት እየጠበቀ ይገኛል። ትናንት ሌሊት ሊቀ ጳጳሷ የታሠሩባትና መቆየት አይችሉምጨ ተብለው ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ የተደረጉባት በአርሲ ሀገረ ስብከቷ መናገሻ አሰላ ኦርቶዶክሳውያን እየታሠሩ መሆኑንና በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ያሉትም እንዲወጡ እየተነገራቸውና ያ የማይሆን ከሆነ የኃይል እርምጃ እንደሚወሰድባቸውም ተዝቶባቸዋል።

"ምዕመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር መንግስት ኃላፊነቱን ይወስዳል" ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾመው ቡድን መንበረ ጵጵስና እና ቤተ ክርስቲያን ሰብረን እንገባለን በማለት በምእመናን ላይ ስጋት መፍጠሩን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮ፣ ቡርጂና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማምሻውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን አሳወቁ። ከሰሞኑን የሀገረ ስብከቱ አገልጋዮች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ይህንንም ለሚመለከተው የዞን ፀጥታ አካል ለማሳወቅና ጥበቃ እንዲያደርጉ ብንደውልም፣ መልእክት ብንጽፍም ሊመልሱልን አልቻሉም ብለዋል። በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለኦሮምያ ክልል የሚመለከታቸው አካላት በተለይም ጥበቃና ከለላን በተመለከተ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስቀድሞ ደብዳቤ ቢጻፍም ምንም አይነት የቃልም ሆነ የተግባር መልስ እንዳልተሰጣቸውም ተናግረዋል። ብፁዕነታቸው አክለውም መንግሥት በሕገ ወጡ ቡድን የሚደረገውን ድርጊት ማስቆም ካልቻለ ምእመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል ብለዋል። በመጨረሻም ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ያሬድ በአሰላ መቆየት አይችሉም ተብለው በዚህ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል።