uz
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 337 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 645-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 190-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 337 obunachiga ega bo‘ldi.

12 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -81 ga, so‘nggi 24 soatda esa -5 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 22.54% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.85% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 456 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 664 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 26 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 13 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 337
Obunachilar
-524 soatlar
-127 kunlar
-8130 kunlar
Postlar arxiv
#ግንቦት_24_በዓተ_ግብጽ_፤ እመቤታችን እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከልጇና ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋር ለ3 ዓመት ከ6 ወር ከተሰደዱ በኋላ ወደ ግብጽ ሃገር ገብታ በሰላም ያረፈችበት ቀን ነው፡፡ ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ፤ ወፍም ቤቷን ሰራች፡፡ መዝ. ፹፫፥፫ *በአዲስ አበባ ታቦተ ሕጉ የሚነግሥባቸው ቦታዎች፤ ፠እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቅድስት ቊስቋም ማርያም፡፡ (365ት ቀናት ሙሉ ዝክር በማኅበረ መድኀኔ ዓለም አዳራሽ የሚዘከርባት ቤ/ክ) ፠ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን፡፡ (የቤ/ክርስቲያኑ ዐጸድ እጅጉን ልብን የሚገዛና የሚማርክ)

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፩ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩ኛ). #ደብረ_ሕይወት_ማይዳዕሮ_ጰራቅሊጦስ_ገዳም፤ (እመቤታችን በስደቷ ወቅት ያረፈችበት፤ ጃንደረባው ባኮስ አድራሻው፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ዓዲ አቡን (ኤርትራ ጠረፍ)፤ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#በዓለ_ጰራቅሊጦስ ሥርዐተ ማኅሌቱ በዓለ ጳራቅሊጦስ ከ፱ኙ ዐበይት በዓላተ እግዚእ አንዱ እንደመኾኑ በኹሉም ገዳማትና አድባራት ይከበራል፤ ነገር ግን ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በሐዋርያትና በመንፈስ ቅዱስ ስም በተሰየሙ አብያ ክርስቲያናት ይከበራል፤ ይልቁንም በአዲስ አበባ ብቸኛ በኾነው #በጽርሐ_ጽዮን_ሐዋርያት_መንፈስ_ቅዱስና_/ኋላ/#ጎላ_ሚካኤል_ (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አገብ) ቤተ ክርስቲያን ይከበራል፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፥ መጽንዒ (የሚያጸና)፥ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኀጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጕምን ይሰጣል (መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት፣ ገጽ ፪፻፹፫)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በኀጢአት ጭቃ የወደቁትንና የሚወድቁትን እንደሚያነጻቸው፤ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ላሉት ኹሉ በፈተናቸውና በመከራቸው ኹሉ እንደሚያበረታቸው (እንደሚያጸናቸው)፤ የሚነዋወፁትን እንደሚያረጋጋቸው፤ ያዘኑትን እንደሚያጽናናቸው፤ የሚደክሙትን እንደሚያበረታቸው፤ የተከዙትንም ሐሴትን እንደሚሰጣቸው የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ጻድቃንን ወደ ተጋድሎ፤ ሰማዕታትን ወደ ደም፣ መነኰሳትን ወደ ገዳም፣ ማኅበረ ክርስቶስንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ልቡናቸውን የሚያነሣሣና የሚመራ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ /ዮሐ.፲፮፥፲፪/፡፡  #በዓለ_ሃምሳ_በብሉይ እስራኤል ዘሥጋ በዓለ ኃምሳን የሚያከብሩት ስለ ብዙ ምክንያት ነው፡፡   ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያኽልም፤ ፩ኛ) ከምድረ ግብጽ ከወጡ በኋላ ምድረ ከነዓን ገብተው ለመዠመርያ ጊዜ እሸት የበሉበትን የሚዘክሩበት ነው፡፡ ዳግመኛም በበረኻ ሳሉ እግዚአብሔር ከሰማያት ኅብስተ መናን አውርዶ፥ ከጭንጫ ውኃን አመንጭቶ እንደመገባቸው ይዘክሩበታል፡፡ በመኾኑም በዚኽ በዓል ቀዳምያት፥ ዐሥራትና በኵራት እያወጡ፣ በየዓመቱ ከሚዘሩት እኽል እሸት (በብዛት ስንዴ) እየበሉ እግዚአብሔርን ስለ ምድር ፍሬ የሚያመሰግኑበት በዓል ነው፡፡ ፪ኛ) እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ በሃምሳኛው ቀን በደብረ ሲና ሕገ ኦሪትን ስለተቀበሉበት ይኽን ያስቡበታል፡፡ ፫ኛ) እግዚአብሔር ከምድረ ግብጽ በታላላቅ ገቢረ ተአምራት ስላወጣቸው ይኽን ያስቡበታል፡፡   ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው ይኽ በዓል እኽል በሚታጨድበት በመከር ወቅት የሚከበር በዓል ነው፡፡ መከር ሲገባ መጀመርያ ከሚሰበስቡት እኽል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ታዝዘው ነበር /ዘጸ. ፳፫፡፲፮/፡፡ በመኾኑም ከበዓለ ፋሲካ ጀምረው ሰባት ሳምንታት (፵፱ ቀናት) በየዕለቱ አንድ መስፈርያ እኽል ይሰጡ ነበር፡፡ በ፶ኛው ቀን ደግሞ ሊቀ ካህኑ ከተሰበሰበው እኽል በትልቅ መስፈርያ አድርጎ ካቀረበ በኋላ መሥዋዕተ በግ ይሠዋ ስለነበር ታላቅ በዓል ኾኖ ይከበር ነበር /ዘሌ. ፳፫፥፲-፲፯፣ ዘዳ. ፲፪፥፭-፯/፡፡ ***አማናዊ ትርጓሜ - በሐዲስ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ድኅነተ ዓለምን በፈጸመበት ዓመት ግን፥ እስራኤል ዘሥጋ ከላይ በገለጥነው መንገድ ከያሉበት ተሰባስበው በዓሉን በኢየሩሳሌም ሲያከበሩ፤ ለእሥራኤል ዘሥጋና ለእሥራኤል ዘነፍስ ብርሃን እንዲኾኑ የመረጣቸው ሐዋርያትም ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸውን ተስፋ እየተጠባበቁ በደብረ ጽዮን በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰባስበው ነበር /ሉቃ. ፳፬፡፵፱/፡፡       በዓለ ሃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜም ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፤ መንፈስ ቅዱስ ነበር፡፡ በዚኽም ብሉይና ሐዲስ ተገናኙ፤ ተተካኩ፡፡ የነቢያት ትንቢታቸው፥ የሐዋርያትም ስብከታቸው የኾነው ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በደብረ ታቦር ተራራ እንዳገናኛቸው፥ በዚያም ክብረ መንግሥቱን፥ ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጸላቸው የሚታወስ ነው /ማቴ. ፲፮፡፩-፯/፡፡ በምሴተ ኀሙስም በቤተ አልዓኣዛር የብሉይ ፋሲካን እንዳዘጋጁና እርሱም መሥዋዕተ ብሉይን በመሥዋዕተ ሐዲስ እንደተካው የተጻፈ ነው /ማቴ. ፳፮፡፲፯-፳፱/፡፡ በበዓለ ኃምሳ የኾነውም ልክ እንደዚኹ ነው /ሐዋ. ፪/፡፡ ይኽ ኹሉ በኢየሩሳሌም፣ በመዠመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን በተሰየመች በቤተ ማርያም (የማርቆስ እናት) ተፈጸመ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለፊተኞችም ለኋለኞችም እናታቸው እንደኾነችም ታወቀ፤ ተረዳ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት በዲድስቅልያ ፴፩ ላይ፡- “ከዕርገቱ ቀን በኋላ ታላቅ በዓል ይደረግ፤ በዚኽች ቀን በሦስተኛው ሰዓት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና እኛም በርሱ ስጦታዎች ተሞላን፤ አዳዲስ ቋንቋም ተናገርን” በማለት በዓሉን በቤተ ክርስቲያን ልናከብረው እንዲገባ ሥርዐት ሐዋርያት የሠሩልንም ስለዚኹ ነው፡፡ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት የታነጸችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይኽንኑ በዓል ከጌታችን ዘጠኝ ዐበይት በዓላት አንዱ በማድረግ በድምቀት ታከብረዋለች፡፡ #ርደተ_መንፈስ_ቅዱስ     ጌታችን እንደነገራቸው መቶ ሃያው ቤተ ሰብእ በቤተ ማርያም ኀይልን ከአርያም እስኪለብሱ ድረስ ተሰብስበው ነበር፡፡ በትዕግሥት ከመጠበቅ ውጪ መንፈስ ቅዱስ መቼ እንደሚወርድም አያውቁም ነበር /ሐዋ. ፪፥፪/፡፡ ጌታችን ባረገ በዐሥረኛው ቀን ግን እኔና እናንተ እንደምንሰማው ዓይነት ያይደለ፥ ነገር ግን ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፡፡ ያሉበትን ቤት ሞላው፡፡ ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት ኾኖ ታያቸው፡፡ በበደልን ጊዜ ከእኛ ርቆ ነበርና አኹን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ስለታረቅን በኹሉም አደረባቸው:  /ማቴ. ፫፡፲፩/፡፡ ኀይል የሚኾናቸው ሀብትን፣ ሀብት የሚኾናቸው ዕውቀትን ገንዘብ አደረጉ፡፡ #መንፈስ_ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ አካላተ ሥላሴ አንዱ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር የሚሠለስ የሚቀደስ የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ እንደ አብና ወልድ ፍጹም ገጽ፥ ፍጹም መልክዕ፥ ፍጹም አካል አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንጂ ሕጹጽ (ብትን፣ ዝርው) አይደለም፡፡ በተለየ ግብሩም መሥረፅ (መውጣት) ነው፤ መሥረጹም ከአብ ብቻ እንጂ አንዳንዶች (ካቶሊኮችና መካነ ኢየሱሶች) እንደሚሉት ከወልድም ጭምር አይደለም /ዮሐ.፲፭፡፳፮/፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አያሠርጽም፤ አይወልድም፤ አይወለድም፡፡ በባሕርይ፥ በመለኮት፥ በሥልጣን፥ በሕልውና፥ በአገዛዝ፥ ዓለማትን በመፍጠርና በማሳለፍ ከአብና ከወልድ ጋራ የተካከለ ነው  /ጸሎተ ሃይማኖት/፡፡ ቀዳሚነትም ኾነ ተቀዳሚነት የሌለው ይልቁንም ከአብና ከወልድ ጋር የተካከለ (ዕሩይ) ነው፡፡ ከአብና ከወልድ ጋር ዓለም ሳይፈጠር ፥ ዘመን ሳይቈጠር ይህ ነው በማይበል ዘመን የነበረ ቀዳማዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አሁንም ያለ ማዕከላዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አብሮ ተካክሎ ይህ ነው ለማይባል ዘመን ወደፊት የሚኖር ደኃራዊ ነው፡፡ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #በአዲስ_አበባ_የሚከብርበት_ #፫_ብቸኛው_ደብር፡፡ ፩ኛ). #ጽርሐ_ጽዮን_ሐዋርያትና_ጎላ_ቅዱስ_ሚካኤል_ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ኢምግሬሽን አጠገብ፥ ጎላ፤ ፪ኛ). #ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ_ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት ት/ቤት፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → ዊንጌት (አስኮ በሚለው ታክሲ)፤ ፫ኛ). #መንበረ_ልዑል_ቅዱስ_ማርቆስ_ቤ/ክ አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ 6 ኪሎ፤

በዓለ ጰራቅሊጦስ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን መሪ ቃል:- "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህ
በዓለ ጰራቅሊጦስ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን መሪ ቃል:- "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማጀራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የዘንድሮ የሰንበት ት/ቤቶች ቀን የሁሉም ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት በየአሉበት ቦታ "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ4:3 በሚል መሪቃል እንዲከበር መልእክት አስተላለፈ። እንደሚታወቀው ላለፋት አስርት ዓመታት በቅዱስ ሲኖዶስ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ደንብ ከጸደቀበት እና በረከታቸው ይደርብን እና በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፖትርያርክ የበዓለ ጰራቅሊጦስ ቀን የሰንበት ት/ቤቶች ቀን እንዲሆን በሰጡት አባታዊ መመሪያ ያ መሠረት በየዓመቱ በዓለ ጰራቅሊጦስን ቀን መሠረት አድርጎ የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሁሉም አህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት የሁለት ቀን ጠቅላላ ጉባኤውን እና የጉባኤው ማጠቃለያ ቀን በበዓለ ጰራቅሊጦስ ዕለት ከአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አመራሮች እና ልብሰ ስብሐት የለበሱ የሰንበት ት/ቤት አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ የሰንበት ት/ቤቶች ቀንን በጋራ ሲያከብር መቆየቱ ይታወሳል። ይሁን እና በዚህ ዓመት በዓሉ የዋለበት ቀን ከ7ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ዋዜማ ላይ በመሆኑ የየአህጉረ ስብከት ተወካዮች ለመገኘት ባለመቻላቸው ጠቅላላ ጉባኤው የተዘዋወረ በመሆኑ ሁለም ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ቀንን "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ4:3 በሚል መሪ ቃል እንዲከበር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መልእክት አስተላልፏል። የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በዕለቱ ሁላችንም በየአጥቢያችን በሚኖር የሰንበት ት/ቤት ጉባኤ የሰንበት ት/ቤቶች ቀንን መሪ ቃሉን መሠረት በማድረግ ከአባላቶቻችን ጋር እንድናከብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በመርሐ ግብሮቹም መሪ ቃሉን መሠረት ያደረገ ቃለ እግዚአብሔር እና በዝማሬ እንድናከብር እያልን በድጋሚ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለሁሉም የሰንበት ትቤት አባላት እና አመራሮች እንኳን ለሰንበት ት/ቤቶች ቀን እና ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ እያለ ሰንበት ት/ቤቶች በዕለቱ በዓሉን አክብረው እንዲውሉ እና የሰንበት ት/ቤት አመራሮችም እንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታችሁን ለመላው አባላቶቻችሁ እንድታስተላልፋ ከወዲሁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

እንኳን አደረሳችሁ፡፡ #ግንቦት_21_ደብረ_ምጥማቅ_ማርያም_የምናከብርበት_ምክንያቱና_ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘግንቦት_21፡፡ ግብጻውያን ክርስቲያኖች ከግንቦት 21 እስከ 25 የእመቤታችንን በዓል (አጎበር ጥለው፥ ድንኳን ተክለው፥ ድባብ ዘርግተው ያከብራሉ፤ እመቤታችንም ከቅዱሳን ጋር በመገኘት ትባርካቸዋለች፡፡) እነዚህ 5ት ቀናትም ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት 5ቱን ከተ.ቊ 25ኛ እስከ 29ኛ ያለውን ይይዛሉ፡፡ እነርሱም፤ ፠25ኛ. ግንቦት 21 ቀን በግብጽ ሃገር ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምዕመናን በግልጽ የታየችበት ነው፡፡  ፠26ኛ. ግንቦት 22 ቀን በግብጽ ሃገር ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምዕመናን በግልጽ የታየችበት ነው፡፡ ፠27ኛ. ግንቦት 23 ቀን ደብረ ምጥማቅ በተባለች ቦታ የታየችበት ነው፡፡ ፠28ኛ. ግንቦት 24 ተሰዳ ግብጽ የገባችበት ነው፤ /ኢሣ.1 9፥11፣ ማቴ.2፥13-15/ ፠29ኛ. ግንቦት 25 ልጇ መድኀኔዓለም ክርስቶስ የደረቁ በትሮችን ተክሎ ያለመለመበት በዓል ነው፡፡ እነዚህ ከላይ ያየናቸውን የደብረ ምጥማቅ በዓላት (ከግንቦት 21-25) በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተነሥቶ የነበረው የግብፁ ንጉሥ እንዳያከብሩ በመከልከሉ፤ ኢትዮጵያውያንም ይህንን በዓል ለማክበር ይሄዱ ነበርና አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ለመጽናኛ እንዲሆን በሃገራችን የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያምን መሠረተ፤ እመቤታችንም ብዙ ቃል ኪዳንን ሰጠችው፤ ይኸው ቃል ኪዳኗ ሳይታጠፍ በጻድቃኔ ማርያም ዛሬ ድረስ ስፍር ቊጥር የሌለው ብዙ ተዓምራትና የምሕረት ሥራ የሚፈጸምባት ቅዱስ ቦታ ኾና ትገኛለች፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ በሃገራችንም ግንቦት 21 የደብረ ምጥማቅ ክብረ በዓል በዋነኛነት!!! (በዋነኛነት!!!) የሚከበርባቸው ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፤ *1ኛ) #ደብረ_ምጥማቅ_ጻድቃኔ_ማርያም_ገዳም፡፡ /ሰሜን ሸዋ/ *2ኛ)  ሐመረ ብርሃን ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን /ጎንደር ከተማ/ *3ኛ) ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም /አዲስ አበባ/ (ሥርዐተ ማኅሌቱን ላልደረሰው በማድረስ ይተባበሩ፡፡) ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ቀ.ደ.ሰ.መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

እንኳን ለታላላቆቹ አባቶች ለአቡነ ዓቢየ እግዚእና ለአቡነ ዮሴፍ ዓመታዊ በዓል (ግንቦት 19) በሰላምና በጤና አደሳችሁ፡፡ /#በጻድቃን_ተዓምራት_ማድረግ_ለምትጠራጠሩ፤ #ጻድቃን_ከበዓለ_ዕረፍታቸው_በኋላ_ዛሬም_ከማማለድም_አልፈው_በቃልኪዳናቸው_ተዓምራት_እንደሚያደርጉ_ኑና_እዩ_ተመልከቱ፡፡ ተዓምራትን ማየት ለምትፈልጉ ኹሉ ሂዳችሁ እዩ!!!!!)፡፡ ክብረ በዓላቸው (የአቡነ ዓቢየ እግዚእ በተንቤን መረታ ደብረ መድኃኒት፣ በጎንደር ከተማ ጥንታዊ በኾነው በዓቢየ እግዚእ ኪዳነምሕረት፣ በመቀሌ እንዳ ገብርኤል /እንዳ አቡነ ዓቢየ እግዚእ/፣ በአዲስ አበባ ሞጆ አካባቢ ባለው ቤ.ክ በድምት ይከበራል፡፡) እንዲሁም (የአቡነ ዮሴፍ በላስታ ላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኘውና ወደ ላለበላ የሚጓዝ ኹሉ ሊያየው በሚችል በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘውና በኢትዮጵያ በከፍታ ከራስ ደጀን ተራራ ቀጥሎ በሚገኘው የዋሻ ገዳማቸው ይከበራል)፡፡ ሁለቱም ቅዱሳን አስካሁን ጊዜ ድረስ የሚታይ ባለ አስደናቂ የቃልኪዳን ተዓምራት አላቸው፤ አቡነ ዮሴፍ ከላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ገዳማቸው ጭላዳ እህል ጠባቂ ሳያሻው እህል እንዳይበላ ገዝተውታል፤ አቡነ ዐቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ቦታ (ለምሳሌ በጎንደር ከተማ) አሁንም ድረስ ጅብ እንስሳቶችን እንዳይበላ ገዝተዋል፡፡ #አቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋቱ (በወሎ ላስታ ሰውንና ዝንጀሮን በቃልኪዳን ያስተሳሰሩ #እስከዛሬ_ድረስ_ዝንጀሮ_እህል_እንዳይበላ_የገዘቱ፤ እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው፤ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑ (እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባና አቡነ ዘርዓ ቡሩክ) ናቸው፤ ገዳማቸው በላሊበላ በቅርበት አቡነ ዮሴፍ ተራራ ተብሎ በሚጠራ ተራራ ቦታ ላይ የዋሻ ቤ.ክ አላቸው፡፡ #አባ_ዓቢየ_እግዚእ_፤ አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእ እና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው 'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጕመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው:: ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኵሰዋል:: በገዳሙ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል:: በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር:: ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል:: ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ሃገረ ስብከታቸው ነው:: አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ:: ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ1,000 በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይህም ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል:: ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሰል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይህንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም:: በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጉዋል:: ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል:: አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው፥ 3 ሙታንን አስነስተው፥ ብዙ ድውያንን ፈውሰው፥ ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው፥ የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው፥ በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል:: የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው:: ** አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን:: ሥርዐተ ማኅሌቱን ላልደረሰው በማድረስ ይተባበሩ፡፡ #ግንቦትት ፲፱፤ #በዓለ_ዐቢየ_እግዚዕ፡፡ #በመላው_ዓለም_የአቡነ_ዐቢየ_እግዚእ_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ #በአዲስ_አበባ_የሚከበርባቸው_ #፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል)፤ አድራሻው፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ብሥራተ ገብርኤል፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(መርካቶ) → ሜክሲኮ → ብሥራተ ገብርኤል፤ ፪. ኤረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፤ (የአቡነ ዐቢየ እግዚእ ክብረ በዓልና የኤረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ቅዳሴ ቤቱ) አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ጎሮ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ጎሮ፡፡ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፡፡ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር ከተማ → አራዳ (ቀበሌ 16)፡፡ ፪. ተንቤን መረታ ዐቢየ እግዚእ ገዳም፤ አድራሻ፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ተንቤን፥ መረታ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → ተንቤን፡፡ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → በአዲዓርቃይ (በዳንሻ ሁመራ) → ሽረ → አኵስም → ተንቤን፡፡ ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ፍኖተ ሕይወት፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#ዜና_እረፍት በደብራችን በጣም ለረጅም ዓመታት በተለያዩ አግልግሎቶች በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩት አባታችን አባ ገብር ሚካኤል ከዚህ አለም ድካም አረፉ :: ስርዓተ ቀብራቸዉም ግንቦት 16/2018
#ዜና_እረፍት በደብራችን በጣም ለረጅም ዓመታት በተለያዩ አግልግሎቶች በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩት አባታችን አባ ገብር ሚካኤል ከዚህ አለም ድካም አረፉ :: ስርዓተ ቀብራቸዉም ግንቦት 16/2018 ከቅዳሴ በኋላ በደብራችን ይፈፀማል።     "እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ መምህርነ ገብረ ሚካኤል"

ግንቦት 16 ተዝካሩ ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በዚህችም ቀን የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው። በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸ
+3
ግንቦት 16 ተዝካሩ ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በዚህችም ቀን የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው። በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር እስከ መለሳቸውና የክብር ባለቤት ጌታችን በእጆቹ ላይ በሚያደርገው ተአምራት በትምህርቶቹም ከሰይጣን ወጥመድ እስከ አዳናቸው ድረስ ጣዖታትን ከሚያመልኩ ከክፉዎች ሰዎች ስለደረሰበት መከራ ነው። በሸመገለም ጊዜ ወንጌልን ጻፈላቸው ሦስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን እስከሚጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶታልና የወልድንም አኗኗሩንና ሰው መሆኑን ዓለም የማይወስነውንም ተአምራቱን። ከዚህም በኋላም ወደ ሰማይ እንደ ወጣና በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሠራዊት ሥርዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ። ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ሊሆን ግብጻውያን ይህን ሠሩ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ውስጥ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ቀን ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ምንጭ - ስንክሳር /ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958