cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኢትዮጵያ

ስለ ሀገራችን ታሪክ ፣ ባህል ፣ ጥንታዊ ቅርሶች ፣ ገዳማት ፣ መጎብኘት ስላለባቸው ስፍራዎች መረጃ ለማግኘት ካስፈለገ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ። ኢሉሚናቲን እናወግዛለን። የዚህ ቻናል አላማ ትውልዱ ሐይማኖቱንና ታሪኩን ያውቅ ዘንድ እና ሙሉ ትውልድ ይሆን ዘንድ ማገዝ ነው ። አንድነታችን ለህልዉናችን @HISCULHEROFETHIOPIA

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
389
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
-630 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #ግንቦት ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን #ለሀገረ_ቶና ለከበረ ልታስተው የመጣችውን ሴት በማስተማር ለቅድስና ላበቃ #ለአባ_አሞንዮስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር ከምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰብት፦#አባ_አሞንዮስ ለቅድስና ካበቃት #ከቅድስት_ሳድዥ ከመታሰቢያዋ፣ #ከቅዱስ_አሞኒ ረድእ #አባ_ዳርማ ከዕረፍት፣ #ከአባ_ኄሮዳና #ከአባ_ዘካርያስ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉበት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_አሞንዮስ፦ ይህም ቅዱስ ጐልማሳ ሁኖ ሳለ አባ እንጦንዮስ ወደ ምንኵስና ሲጠራው ራእይን አየ። በነቃም ጊዜ ተነሥቶ ወዲያውኑ ወደ አባ ኤስድሮስ ሔደ ከእርሱም አስኬማን ለብሶ እያገለገለውም በእርሱ ዘንድ ኖረ። ❤ ከዚህ በኋላ ወደ ደብረ ቶና ተመልሶ ለራሱ በዓትን ሠራ በታላቅ ገድልም ተጠምዶ በቀንና በሌሊትም ተጋደለ። ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ በሴት መነኵሲት አምሳል ወደርሱ መጣ የበዓቱን ደጃፍ በአንኳኳ ጊዜ ከፈተለትና ገባ "ቅዱሱም ተነሥተን እንጸልይ" አለው ያን ጊዜ ተንኰሉን ገለጠ መልኩም እንደ እሳት ላቦት ሆነ ቅዱሱንም "እኔ ታላቅ ጦርነት አመጣብሃለሁ" አለው። ❤ ከዚህም በኋላ መልኳ ውብ ወደ ሆነ ወደ አንዲት ወጣት ሴት ሰይጣን ሒዶ አነሣሣት። ቅዱስ አሞንዮስን እርሷ ጋራ በኃጢአት ልትጥለው ቀጭን ልብሶችን ለብሳ ወደ ርሱ በምሽት ጊዜ ደረሰች። እንዲህም እያለች ደጃፉን አንኳኳች "እኔ መጻተኛ ሴት ነኝ መንገድንም ስቼ በምሽት ጊዜ ከዚህ ደረስኩ አራዊትም እንዳይበሉኝ በውጭ አትተወኝ እግዚአብሔርም ስለ እኔ ደም እንዳይመራመርህ" አለችው። በከፈተላትም ጊዜ የሰይጣን ማጥመጃው እንደ ሆነች የላካትም እርሱ እንደሆነ አወቀ በአምላካውያት መጻሕፍት ቃልም ገሠጻት ለኃጥአን ስለ ተዘጋጀ የሲዖል እሳትም አስገነዘባት ሁለተኛም ለጻድቃን ስለ ተዘጋጀ ፍጹም ተድላ ደስታ ነገራት። ያን ጊዜም የሚላትን ታስተውለው ዘንድ እግዚአብሔር ልቧን ከፈተላት። መልካሙንም ልብስ ከላይዋ አውጥታ ጣለች ከእግሮቹ በታችም ሰግደች ነፍሷንም ያድን ዘንድ በማልቀስ ለመነችው። የጠጉር ልብስም አለበሳት ራስዋንም ተላጭታ በገድል ሁሉ በብዙ ትሩፋትም ተጠመደች በቀንም በሌሊትም ዐሥራ ሁለት ጊዜ የምትጸልይ ሁናለችና በየሁለትና በየሦስት ቀንም ትጾማለች። ❤ ሰይጣንም በአፈረ ጊዜ በመነኵሴ ተመስሎ በየአንዳንዱ ገዳም ሁሉ በመግባት እያለቀሰና እያዘነ እንዲህ አላቸው "በአባ አሞንዮስ ቤት ሴት አለችና እርሱ ታላቅ ገድል በኋላ የአንዲትን ሴት ፍቅር ወዶአልና እርሷም በእርሱ ዘንድ በበዓቱ ውስጥ ትኖራለች እነህ መነኰሳትን አሳፈራቸው እስኬማውንም አጐሳቈለ"። ❤ የመላእክት አምሳል የሆነ ጻድቅ አባ ዕብሎ ያን ጊዜ ተነሣ አባ ዮሴፍንና አባ ቦሂንም ከእሱ ጋራ ወሰዳቸው። ወደ ቅዱስ አሞንዮስ ገዳም ደብረ ቶና ደረሱ ደጃፋንም በአንኳኩ ጊዜ ያቺ ሴት ወደ እርሳቸው ወጣች እርስ በርሳቸውም "ያ መነኵሴ የነገረን እውነት ነው ተባባሉ። የከበረ አሞንዮስም ሳድዥ ብሎ ስም አውጥቶላታል ይህም የዋሂት ማለት ነው። ገብተውም ጸሎት አድርገው የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ እስከ ምሽት ተቀመጡ። አባ አሞንዮስም "አምበሻ እየጋገረችልን ነውና ተነሡ ሳድዥን እንያት" አላቸው። በገቡም ጊዜ በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ቁማ እጆቿም ወደ ሰማይ ተዘርግተው ስትጸልይ አገኙዋት። አይተውም ስለዚህ ድንቅ ሥራ እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርም አመሰገኑ። ❤ ከዚህ በኋላም አቅርባላቸው በሉ። በዚያችም ሌሊት መልአክ ስለ አባ አሞንዮስና ስለ ሳድዥ ገድላቸውን ለአባ ዕብሎ ነገረው "ወደዚህም ዛሬ ያደረሳችሁ እግዚአብሔር ነው የሳድዥን ዕረፍት እንድታዩ" አላቸው። ሦስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ የሚያስጨንቅ የሆድ ዝማ ታመመች በእግዚአብሔር ፊት አንዲት ስግደትን ሰገደችና በዚያም ነፍሷን ሰጠች መልካም አገናነዝም ገንዘው ቀበሩዋት። ❤ አባ አሞንዮስም ትሩፋቷን ሊነግራቸው ጀመረ እርሷ በእርሱ ዘንድ ዐሥራ ስምንት ዓመት ስትኖር ከቶ ፊቷን እንዳላያት ምግባቸውም አምባሻና ጨው እንደሆነ። ከጥቂ ቀን በኋላም አባ አሞንዮስ ግንቦት 20 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በአባ አሞንዮስና በቅድስት ሳድዥ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 20 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #"ሰላም_ሰላም_ለረዳኢተ_አሞንዮስ ሳድዥ። ዝ ብሂል የዋሂተ ግዕዝ። በሑረታቲሃ አዳም ወበምግባራ ሐዋዝ። ኢውዕየት ቀዊማ ከመ ዘመጥልል ውኂዝ። ማዕከለ ውዑይ ወርሱን ማሕበዝ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_20።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዝርዎሙ ለአሕዛብ እለ ይፈቅዱ ቀትለ። ይምጽኡ ተናብልት እምግብፅ። ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር"። መዝ 67፥30-31 ወይም መዝ 74፥2-3፡፡ የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 13፥1-11፣ 1ኛ ጼጥ 2፥11-20 እና የሐዋ ሥራ 13፥44-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ16፥24-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ቅዱስ ካሌብ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
50Loading...
02
Media files
80Loading...
03
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለካሌብ ወለሣህል ኄራን መዋዕያን ነገሥት፤ #እለ_ሃይማኖቶሙ_ምሉዕ ከመ ደመና ክረምት፤ #ለመንገለ_እግዚአብሔር እለ አርአዩ ቅንአተ፤ እለ ዓቀቡ በንጽሕ መንግሥተ፤ ዘተወፈዩ ጽድቀ #ወቅድሳተ_ወሃይማኖተ_በመንፈስ_ቅዱስ እለ አፍረዩ፤ #ለእግዚአብሔር ርእሶሙ እለ አቅነዩ"። ትርጉም፦ #ለእግዚአብሔር_ራሳቸውን_ያስገዙ፤ #በመንፈስ_ቅዱስ_ፍሬን_ያፈሩ፤ እውነትን፣ ክብርንና #ሃይማኖትን_የተቀበሉ፤ መንግሥትን በንጽሕና የጠበቁ፤ #የእግዚአብሔር ወደሚኾን አምልኮት ቅንአትን ያሳዩ፤ #ሃይማኖታቸው_እንደ_ክረምት_ደመና_ምሉእ የኾኑ ቸሮችና ድል ነሾች ለኾኑ ነገሥታት ለሣህልና #ለቅዱስ_ካሌብ_ሰላምታ_ይገባል። #ሊቁ አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ። ምንጭ ፦ ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ)
60Loading...
04
ድጓ ዘጻድቃን ነገሥት አቡን በ፮ አርኅዉ ሊተ አናቅጸ ጽድቅ እባዕ ውስቴቶን ወእግነይ ለእግዚአብሔር ዛ አንቀጽ እንተ እግዚአብሔር ጻድቃን በክብር የዋሃን በክብር ራትዓን በክብር በትፍሥሕት ይበውዑ ውስቴታ በኃሤት። ገጽ ፻፲ (110) ትርጓሜ ፦   የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤  ወደ እነርሱ    ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግን ዘንድ ፤ ይህችም በር የእግዚአብሔር ደጅ ናት ፤ ጻድቃን በክብር ፣ የዋሃን በክብር ፣  ቅኖችም በክብር     በደስታ  ወደርሷ ይገባሉ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ
90Loading...
05
https://youtu.be/jOkH2Qou3Lw?si=qCXLiGobY2HW-cx8
80Loading...
06
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"          📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ                    ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም           📌   ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፳        አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ በዚች ቀን የከበረ ጻድቅ የኢትዮጵያ ንጉሥ ካሌብ አረፈ። ❖ ይህ ቅዱስ እግዚአብሔርን የሚፈራውና በፍጹም ልቡ የሚወደው ሃይማኖቱም የቀና ነው፤ በናግራን አገር ያሉ ክርስቲያኖችን አይሁድ እንደሚገድሏቸው በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ መንፈሳዊ ቅናትንም ቀና። ❖ ከዚህም በኋላ ተነሣ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብቶ በመሠዊያው ፊት ቆመ ዐይኖቹንም ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ ብሎ ጸለየ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ሆይ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠርህ መላእክት ሁሉ አእላፈ አእላፋት አንተን የሚያመሰግኑህ ለአንተም የሚገዙ ዐይኖቻቸው ብዙ የሆነ ኪሩቤል ክንፎቻቸው ስድስት የሆነ ሱራፌልም ጽኑዕ ክቡር ልዩ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር በቅዱሳን የሚመሰገን እያሉ ያለማቋረጥ የሚያመሰግኑህ፣ ብርሃንን እንደ ልብስ የሚጐናጸፍ የክብር ባለቤት ለሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱ እግዚአብሔር ሆይ የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ የጠፉ በጎችን ይመልሳቸው ዘንድ ልጅህን ይኸውም ቃልህ ነው በፈቃድህ የላክኸው አንተ ነህ። ❖ ተናጋሪ በግ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳትለይ ከሰማይ የወረድክና ስለ እኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆንክ ከጨለማም ከድንቁርናም አውጥተህ ወደ ብርሃን ወደ ሕይወት ወደ ዕውቀት የመራኸን፤ አሁንም ከሀዲ ወንጀለኛ ፊንሐስ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች እንደ በጎች በማረድ እንደ ገደላቸው በእሳትም አቃጥሎ የወገኖችህንና የርስትህን ልጆች እንዳጠፋቸው እይ። ❖ እነሆ አብ ሆይ እኔ አመንሁብህ በአንድ ልጅህም በሕያው ቅዱስ መንፈስህም በመሠዊያህ ክብርም ተማፅኛለሁ በሃይማኖትህም ጸንቼአለሁ እነሆ ስለ አምልኮትህና ስለ ምእመናን ወንድሞቼ ስለ ቀናሁ በአንድ ልጅህ መስቀል ጠላቶችህን ልዋጋቸው እወጣለሁና ከአለኝታዬ እንዳታሳፍረኝ የማያውቁህም አምላካቸው ወዴት ነው እንዳይሉ። ❖ ስለ በደሌና ስለ ኃጢአቴም ጸሎቴን የማትሰማ ልመናዬንም ንቀህ የምትተው ከሆነ በዚሁ ቦታ ብትገድለኝ ይሻለኛል፤ አቤቱ መሐሪ ይቅር ባይ ርኅሩህ ርስትህ የሆኑ ምእመናንን በከሀድያን ጠላቶችህ እጅ አሳልፈህ አትስጥ። እኛ ወገኖችህና የርስትህ መንጋዎች ስለሆን ለአንተም ምስጋና እናቀርባለን ምስጋና ገንዘብህ ነውና ለዘላለሙ። ❖ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ካሌብ ከሀገረ መንግሥቱ ወጥቶ ሔደ የናግራንን ሀገር ያጠፉአት አይሁድን ገደላቸው ብዙ ተአምራትም አድርጎ ስለ አደረገለት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ሀገረ መንግሥቱ በታላቅ ክብር በታላቅም ደስታ ተመለሰ፤ ለእግዚአብሔር ምን ዋጋ እከፍለዋለሁ ለጌትነቱና ፍጹም ለሆነ ገናናነቱ መባ አድርጌ ነፍሴንና ሥጋዬን ከማቀርብለት በቀር አለ። ❖ ከዚህም በኋላ ይህን ዓለም ንቆ መንግሥቱንም ትቶ ወጣ ደጋጎች መነኰሳት ወደሚኖሩበት ወደ አባ ጰንጠሌዎን በተራራ ላይ ወደ አለ ገዳም እስከ ደረሰ በእግሩ ሔደ፤ ወደ ዋሻ ውስጥም ገብቶ ሰውም እንዳያየው የዋሻውን በር ዘግቶ በዚያ ውስጥ ኖረ ከዚያችም ወጥቶ ዳግመኛ ዓለምን እንዳያይ ማለ። ❖ ከእርሱ ጋራም ያገባው ዕቃ የለም ከምንጣፍ ከሸክላ ጽዋ ከለበሳት የምንኲስና ልብስ በቀር ምግቡም አምባሻና ጨው የሚጠጣውም ውኃ ነው፤ የክብር ባለቤት ከሆነ ከእግዚአብሔር ቃል መቃብር መስኮት ላይ ይሰቅልለት ዘንድ የኢየሩሳሌሙን ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስን እየለመነው ዋጋው ብዙ የሆነ የነገሠበትን ዘውድ ላከ፤ ወደ ዋሻውም ከገባ በኋላ ከማንም ጋራ አልተነጋገረም እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ በፍቅር አንድነት አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                        ✍️  በዚች ዕለት የሀገረ ቶና የከበረ አባ አሞንዮስ አረፈ፤ ይህም ቅዱስ ጎልማሳ ሁኖ ሳለ አባ እንጦንዮስ ወደ ምንኩስና ሲጠራው ራእይን አየ፤ በነቃም ጊዜ ተነሥቶ ወዲያውኑ ወደ አባ ኤስድሮስ ሔደ ከእርሱም አስኬማን ለብሶ እያገለገለውም በእርሱ ዘንድ ኖረ። ✍️  በዚችም ቀን ከአባቶች መምህራን ዐሥራ ስድስተኛ የሆነ በደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት ሆኖ የተሾመ የከበረ አባት አባ ዘትረ ወንጌል አረፈ። ❖ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ እንደ መላእክት ንጽሕናን የለበሰ ትሕትናን ቅንነትን የሚወድ ነበረ። ❖ የምንኵስናንም ልብስ ከለበሰ በኋላ መልካም ገድልን ተጋደለ በክርስቶስ መንጋ ላይም ጠባቂ ሆኖ ተሾመ ከዚያም በኋላ በበጎ እርጅና አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። 📌 ግንቦት 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አፄ ካሌብ (መናኙ ንጉሠ ኢትዮዽያ) 2.ቅዱስ አሞንዮስ ገዳማዊ (ታላቁ አሞኒ ዘቶና) 3.ቅድስት ሳድዥ የዋሂት 4.አባ ሖር ጻድቅ 5.አባ ዳርማ ገዳማዊ 6.ቅዱስ ዘካርያስ አንጾኪያዊ 7.አባ ዘትረ ወንጌል ዘደብረ ሊባኖስ 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት) 2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር 3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
60Loading...
07
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"          📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ክርስቶስ ተንሥአ እም እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም    🛎   ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፱              አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን ከአባ መቃርስ ገዳም ቅዱስ አባት ቀሲስ ይስሐቅ አረፈ።     ❖ ይህም አባት ከምሥር ከታናናሽ ቦታዎች ከአንዲት ቦታ ነው ወላጆቹም ድኆች ሲሆኑ ግን በበጎ ስራ ባለጸጎች ናቸው፤ አረጋውያን መነኰሳትም የእጅ ስራቸውን ሊሸጡ ወደ ምሥር በሄዱ ጊዜ ተከትሏቸው ወደ አስቄጥስ ገዳም መጥቶ ሲአገለግላቸው ኖረ፤ በቀንበራቸውም ተጠምዶ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ በዘመኑም ሁሉ ከቶ ምንም ጥሪት አላደረገም፤ እንደ አባቶቻችን ሁለት ልብሶችን ለምን አልገዛህም ሲሉት እርሱም እኔ እስከ ዛሬ ሕዝባዊ ነኝ በዓለም ሳለሁም ሁለት ልብስ የለኝም ነበር ብሎ ይመልስላቸዋል። ❖ ሁለተኛም አባቶቻችንም እኮ ሰሌንና ማቅ ይለብሳሉ ለእኛም አንድ ልብስ ይገባናል ይህ አይበቃንምን አላቸው፤ ሁልጊዜ የሚያለቅስ ሆነ ለምን ታለቅሳለህ ብለው በጠየቁት ጊዜ ወላጆቼ ሙተውብኝ ድኃ አደግ አድርገውኛልና ይላቸዋል፤ ከምግቡም የማዕጠንት አመድ ጨምሮ እየበላ ብዙ ዘመናት ኖረ። ❖ ከዚህ በኋላ ጭንቅ በሆነ ደዌ ተይዞ በታመመ ጊዜ ከወንድሞች አንዱ ምግብ ሰርቶ አመጣለት፤ እርሱም ከቶ አልቀመሰም ያም ወንድም ይህ ጥሩ ምግብ ነው ለበሽታህም መድኃኒትነት አለውና ብላ ብሎ ብዙ ለመነው፤ እርሱም ወንድሜ ሆይ እመነኝ እኔ በዚህ ደዌ ውስጥ ሠላሳ ዓመት እኖር ዘንድ እወዳለሁ ብሎ መለሰለት፤ በዕድሜውም በሸመገለ ጊዜ ትሩፋቱና ጽድቁም በበዛ ጊዜ ቅስና ይሾሙት ዘንድ አረጋውያን ተሰብስበው ተማከሩ። ❖ እርሱም ከእርሳቸው ሸሽቶ ከተዘራ ማሳ ውስጥ ገብቶ ተሠወረ፤ እርሱንም እየፈለጉ ዞሩት አላገኙትም ያቺንም ማሳ አልፈው ከዳርዋ ተቀመጡ ጥቂት ሊያርፉ፤ ከእርሳቸውም ጋር አህያ ነበረ ወደ ማሳውም ሩጦ ገብቶ ይህ አባት በተሸሸገበት ቦታ ቆመ፤ አህያውን ሊያስወጡትም በገቡ ጊዜ ያንን አባት አገኙት፤ ደግሞ እንዳይሸሽ ሊአሥሩት ፈለጉ አሁንስ ዐውቄዋለሁ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አላቸው ከዚያም አብሮአቸው ሒዶ ቅስና ሾሙት። ❖ ከዚህ በኋላም ተጋድሎውንና ለአረጋውያን መታዘዙን ጨመረ ወጣቶችንም በጎ ሥራ ያስተምራቸዋል ሰምታችሁ የምትታዘዙ ሁኑ ከትሩፋት ሁሉ ይህ ይበልጣልና አላቸው፤ የሚያርፍበትም ጊዜ ሲደርስ ከእርሱ በኋላ የሚሠሩትን እንዲአስተምራቸው በዚያ ገዳም ያሉ ጎልማሶች በጠየቁት ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ በገዳሙ ውስጥ ጸንታችሁ እንድትኖሩ እኔ ስሠራ ስታዩኝ እንደነበረ እናንተም እንዲሁ በፈቃዳችሁ ሥሩ፤ እኛ አባቶቻችን በአረፉ ጊዜ አዝነን አልቅሰን ነበር እንደሚሠሩትም በሠራን ጊዜ ከእነርሱ በኋላ ተጽናንተን በገዳም የምንኖር ሆን። ይህንንም እያለ በፍቅር በሰላም አረፈ የሕይወት አክሊልንም አገኘ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከቱም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። 📌 ❖ በዚችም ቀን ኃይለኛ ተጋዳይ ቅዱስ ኤስድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፤ ይህም ቅዱስ ከእስክንድርያ አገር ከከበሩ ከቤተ መንግሥት ወገኖች ውስጥ ነው አባቱም በብዙ ሠራዊት ላይ የተሾመ መኰንን ነው፤ ስሙም በደላዖን ነው የእናቱም ስም ሶፍያ ነው ሁለቱም ከክርስቲያን ወገን ናቸው ይህንንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ ኤስድሮስ ብለው ሰየሙት። ❖ ከብዙ ወራት በኋላም ከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ የሚያደርገውን የኃጢአትና የበደልን ብዛት በአየ ጊዜ እርሱ ከመንግሥት ታላላቆች ውስጥ ስለሆነ ምስፍናውን ትቶ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋራ ገለል አለ፤ ስለ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጻተኞች በመሆን ከዚህ ዐላዊ ንጉሥ ፊት ሸሽተው ሳሙኤል ከሚባል ሰው ዘንድ ተሰባስበው በገዳም ተቀመጡ። 📌 በዚችም ቀን ከቅዱስ ኢስድሮስ ጋራ ስምንት መቶ አምስት ሺህ ሰባት ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ በረከታቸውም ትደረሰን ለዘላለሙ አሜን።                         📌   በዚችም ዕለት የዓለም ብርሃን የሆነ አባ ዮሴፍ አረፈ፤ ይህም ቅዱስ ያዩትና የሰሙት እስቲአድንቁት ድረስ በአባቱ ቤት ሳለ የዚህን ዓለም ጥበብ ሁሉ ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ተረጐመ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾሙት፤ የነፍሱንም ድኅነት እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ብርሃናዊ መልአኩን ሚካኤልን ላከለትና ዮሴፍ ሆይ ይህን ኃላፊውን ዓለም ትወደዋለህን? አስጸያፊ አይደለምን በውስጡም ያለው ሁሉ አለው። ❖ ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ እርሱ የመረጠውን መንገድ ይመራው ዘንድ እግዚአብሔርን እየለመነ ጾምና ጸሎትን ጀመረ ከወለቃ አውራጃም ስሙ አባ ዘካርያስ የሚባል ነበረ እርሱም ለዮሴፍ ዘመዱ የሆነ በጭልታም ዮሴፍን ወስዶ የምንኲስና ልብስ አለበሰው ወደ ትግራይ ምድርም ወሰደውና በዚያ ተግባረ እድ ለምንኲስና ሥራ የሚገባ ጽሕፈትን ስፌትን ተማረ። ❖ ከዚህም በኋላ ወደ በረሀ ዱር ገብተው የእንጨት ፍሬ እየበሉ ከዝኆኖች ከአንበሶችና ከዘንዶዎች እየተፈተኑ በየአይነቱ በሆነ ተጋድሎ በመድከም ኖሩ፤ በጽድቃቸውም ኃይል ብዙ ተአምራትን አደረጉ። 📌 ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 2.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም (የ12ቱ ሐዋርያት መቃብር ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ) 3.አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ (ኢትዮዽያዊ) 5."805,007" ሰማዕታት (በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ) 6,አባ ይህሳቅ ገዳማዊ 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2.አቡነ ስነ ኢየሱስ
120Loading...
08
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"                             ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም    📌 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፰       አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ስምንት በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ ከትንሣኤው በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ከአብ የሚሠረጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ ብሎ ተስፋ እንደ ሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። ❖ እናንተም ከአርያም ኃይልን እስከምትለብሱ በኢየሩሳሌም ኑሩ አላቸው፤ ሁለተኛም ያ እውነተኛ መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ ዕውነት ሁሉ ይመራችኋል አላቸው፤ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው እርሱም አለቃቸው የሆነ ጌታችን አጽናኚውን ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ነው ሊልክልን ተስፋ አስደርጎናል የምናሰማውንና የምናደርገውን ልብ ያስደርገን ዘንድ። ❖ ይህንንም ሲነግራቸው እነሆ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ ሰሙ በዓለም ውስጥ እንደርሱ ያለ የማያውቁት ጣፋጭ መዓዛ አሸተቱ፤ የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎችም በየአንዳንዳቸው ላይ ሲወርዱ ታዩ፤ በአዲስ ቋንቋም ተናገሩ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ሊሆን አርባ ቀን ጾሙ፤ ሁለተኛም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በዓለ ኃምሣ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሁነው አብረው ሳሉ፤ ድንገት ከሰማይ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትም ቤት ሁሉ መላው። ❖ የተከፋፈሉ የእሳት ልሳኖችም ታዩአቸው በየአንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተመሉ። በየራሳቸውም በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀምር መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው።ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። ❖ ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ደንግጠው ሁሉም ተሰበሰቡ በየሀገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና፤ ተደንቀውም በድንጋጤ እንዲህ አሉ፤ እነሆ እሊህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን የጳርቴና የሜድ የኤላሜጤም ሰዎች ስንሆን፤ በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም በፍርግያም በጵንፍልያም በግብጽም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊብያ ወረዳዎች የምንኖር በሮሜም የምንቀመጥ አይሁድም ወደ ይሁዲነት የገባን የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች ስንሆን የእግዚአብሔርን ገናናነት በቋንቋችን ሲናገሩ እነሆ እንሰማቸዋለን። ❖ ሁሉም ደንግጠው የሚናገሩትን አጡ፤ እርስ በርሳቸውም እንጃ ይህ ምን ይሆን አሉ ሌሎች ግን እያፌዙባቸው ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል አሉ፤ ጴጥሮስም ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤ የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ። ❖ ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤ ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለው ነው እግዚአብሔር አለ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አሳድራለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ ጐበዛዝቶቻችሁም ራእይን ያያሉ ሽማግሎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፤ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ መንፈስ ቅዱስን አሳድራለሁ ትንቢትን ይናገራሉ፤ ድንቆችን በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል ታላቅ የሆነ የጌታ ቀንም ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል።የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል። ❖ ዳዊትም እንዲህ አለ ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ደስ የሚያሰኝ ደኅነትህንም ስጠኝ፤ በጽኑዕ መንፈስህም አጽናኝ ለዝንጉዎች ሕግህን እንዳስተምራቸው፤ ሁለተኛም መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉ አለ፤ ደግሞ ቅዱስ መንፈስህ በጽድቅ ምድር ይምራኝ አለ፤ ደግሞም በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤ ኢሳይያስም እንዲህ አለ በእኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ለድኆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ለተማረኩትም ነፃነትን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠ እለው ዘንድ ላከኝ። ❖ ጌታችንም እንዲህ አለ ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ይህን ነገርኳችሁ፤ ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል፤ እኔ ሰላምን እተውላችኋለሁ የአባቴንም ሰላም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ስጦታ አይደለም ልባችሁ አይታወክ አትፍሩም ። ❖ እኔ እሔዳለሁ ወደእናንተም ተመልሼ እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ፤ ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አለ እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚገኝ የዕውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለእኔ ይመሰክራል፤ እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋራ ኖራችኋልና ምስክሮቼ ናችሁ። ❖ እንዳትሰነካከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል ከዚህም በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንደሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፤ እኔም ዕውነት እነግራችኋለሁ እኔ ብሔድ ይሻላችኋል እኔ ካልሔድኩ ግን አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ወደ እናንተ አይመጣምና ከሔድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ ። ❖ እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይውቅሰዋል፤ ስለ ኃጢአት በእኔ አላመኑምና ስለ ጽድቅም ወደ አብ እሔዳለሁና እንግዲህም አታዩኝምና ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ይፈረድበታልና አላቸው፤ የምነግራችሁም ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን ዛሬ ልትሸከሙት አትችሉም እርሱ የዕውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል። ❖ እርሱ እኔን ይገልጣል ከእኔም ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋልና ለአባቴ ያለው ሁሉ የኔ ገንዘብ ነውና ስለዚህ ከእኔ ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋል አልኳችሁ፤ ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና፤ ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ ምንድነው ይህ ነገር ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና የሚለን። ❖ ጌታ ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደሚሹ ዐወቀባቸው እንዲህም አላቸው ስለዚህ ነገር እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ስለአልኳችሁ፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ እናንተ እንደምታዝኑ እንደምታለቅሱ ዓለም ደስ ይለዋል እናንተ ግን ታዝናላችሁ ነገር ግን ኀዘናችሁ ደስታ ይሆናችኋል፤ ሰው የሆነበትንም ሥራ በፈጸመ ጊዜ ሒዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፤ ስታጠምቋቸውም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሉ፤ ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ አላቸው። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከቸር አባቱ አዳኝና ሕይወት ከሆነ ቅዱስ መንፈሱ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። 📌 ግንቦት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት 2.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ 3.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት
110Loading...
09
Media files
140Loading...
10
Media files
120Loading...
11
🌿እንኳን ለታላቁ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✝በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ♱ቅዱስ ኤዺፋንዮስ 📝ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ጽድቅ ከቅድስና : ድርሰት ከጥብቅና የተሳካለት አባት ነው:: "ኤዺፋንያ" ማለት የመለኮት መገለጥ ሲሆን "ኤዺፋንዮስ" ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው። 💡ቅዱስ ኤዺፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ቤተ ገብርኤል ውስጥ ነው። ቤተሰቦቹ ከአንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድሆች ነበሩ። በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረሃብ ሊያልቁ ሆነ። ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና ሊሸጠው ገበያ አወጣው። 📝ፊላታዎስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤዺፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው:: በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ክርስቲያኑ በትእምርተ መስቀል አማትቦ አዳነው:: በፈንታው ግን አህያው ሞተ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ እያደነቀ ሔደ። 📝ከቆይታ በኋላ ሀብታም አጎቱ ገንዘቡን አውርሶት በመሞቱ ገና በ16 ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ:: ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር። 💡አንድ ቀን ደግሞ ሉክያኖስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ሲሔዱ ነዳይ አገኙ:: ባለጠጋው ኤዺፋንዮስ አለፈው:: ያ ድሃ ክርስቲያን ግን የለበሳትን አውልቆ መጸወተው:: በዚሕ ጊዜ መልዐኩ መጥቶ የብርሃን ልብስ ሲያለብሰው ኤዺፋንዮስ ተመለከተ። 📝ኤዺፋንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ከእህቱ ጋር በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ:: ሃብት ንበረቱን ግማሹን መጸወተ:: በተረፈው ደግሞ መጻሕፍትን ገዝቶ ወደ አባ ኢላርዮን ገዳም ገባ:: በዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና ተጋደለ። በጸሎቱ ዝናም አዘነመ : ድውያንን ፈወሰ : ብዙ ተአምራትንም አደረገ። 📝 እግዚአብሔርም ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ሽቶታልና በቆዽሮስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: ብሉይ ከሐዲስ የወሰነ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ:: በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ:: በአፍም በመጽሐፍም ብሎ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ቤተ ክርስቲያን "ጠበቃየ" ትለዋለች። 📝ከደረሳቸው መጻሕፍት መካከል "ሃይማኖተ አበው ዘኤዺፋንዮስ : መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ስነ ፍጥረት)" ዛሬም በቅርብ ይገኛሉ:: ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ተመላልሶ በ406 ዓ.ም. ዐርፏል:: እድሜውም 96 ዓመት ያህል ነበር። 🤲አምላካችን ከቅዱሱ ሊቅ በረከት ያድለን! 🗓 ግንቦት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ) 2. ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ 3. አባ ሉክያኖስ ጻድቅ 4. ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ 🗓 ወርኀዊ በዓላት 1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት) 2. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ) 3. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ 4. አባ ገሪማ ዘመደራ 5. አባ ዸላሞን ፈላሢ 6. አባ ለትጹን የዋህ 📖"የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል። እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው። እኛ ግን የማይጠፋውን። ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም። ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም። ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ።'' (1ቆሮ. 9:25) ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨ ምንጭ ፦ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት
150Loading...
12
Media files
150Loading...
13
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #ግንቦት ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ከኢየሩሳሌም ከዮርዳዮስ ያመጡት ውሃ እስከ ዛሬ በገዳማቸው መነኰሳት የሚጠቀሙት ለሆነ፤ ገርዓልታ እና ሐውዜን ላይ እጅግ አስገራሚ ሁለት ታላላቅ ገዳማትን ለገደሙት #ለአቡነ_ገብረ_ሚካኤል ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር በሰላምና በጤና አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ገብረ_ሚካኤል፡- እኚህ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ በታላቅ ተጋድሎአቸው ይታወቃሉ፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ትግራይ ገርዓልታ ነው፡፡ ጻድቁ አቡነ ገብረ ሚካኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማርና አስደናቂ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደሶችን በማነጽ ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ እጅግ አስናቂው ገዳማቸው ገርዓልታ ጠራሮ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል፡፡ ❤ ከገርዓልታ በደቡባዊ አቅጣጫ የሚገኘው ይህ የአቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂ ገዳም እንደ ደብረ ዳሞ በገመድ ብቻ ከሚወጣው ከአቡነ ገብረ ናዝራዊ ገዳም ጋር የሚዋሰን ሲሆን ገዳሙ ለመድረስ የመኪናውን መንገድ ከጨረሱ በኋላ በእግር አንድ ሰዓት ይፈጃል፡፡ በገዳሙ ውስጥ ጻድቁ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ብዙ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ የጌታችን የሾህ አክሊል ምሳሌ የሆነውና ጻድቁ ያደርጉት የነበረው የድንጋይ ቆብ፣ መቋሚያቸው፣ የእጅ መስቀላቸውና መጻሕፍቶቻቸው ይገኛሉ፡፡ ሌላው አስደናቂ ነገር ሀገሩ በረሃ ቢሆንም ጻድቁ ከኢየሩሳሌም ዮርዳኖስ ያመጡትና ዋሻው ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው ያጠራቀሙትን ውኃ መነኰሳቱ ሁልጊዜ የሚጠቀሙበት ቢሆንም ውኃው ግን ከዓመት እስከ ዓመት መጠኑ አይቀንስም፡፡ ❤ ሊቀ ብርሃናት መርቆርዎስ አረጋ የቅዱሳን ታሪክና ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በሚሉት ሁለት መጽሐፎቻቸው ላይ እንደጠቀሱት በገዳሙ ውስጥ ከዓመት እስከ ዓመት የምትበራው አንዲት ጧፍ ብቻ ናት፡፡ ጧፏ ነዳ የማታልቅ ስትሆን አለቀች ትቀየር ሳትባል አስገራሚ በሆነ ተአምር ከዓመት እስከ ዓመት ትበራለች፡፡ ሌላኛው የአቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ከሀውዜን ከተማ በስተደቡብ አቅጣጫ ከአስደናቂው የአቡነ ይምዓታ ጎሕ ገዳም 16 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ነው፡፡ ጠራሮ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው ይሄኛውም ገዳማቸው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ አስደናቂ ነው፡፡ አቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂውን ዋሻ ፈልፍለው ከጨረሱ በኋላ ግድግዳውና ዓምዶቹ ላይ የሳሏቸው የሐዋርያትና የቅዱሳን ሥዕላት ከጥንታዊነታቸው በተጨማሪ እጅግ ውብና አስደናቂ ናቸው፡፡ ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ ጻድቁ ቅዱሳት ሥዕላቱን የሳሏቸው በሸራ ላይ ሳይሆን በአሸዋማው የዋሻው ፍልፍል ግድግዳ ላይ መሆኑ ነው፡፡ ከአባታችን አቡነ ገብረ ሚካኤል ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን! ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ። ምንጭ ፦ ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ)
90Loading...
14
Media files
190Loading...
15
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም 🛎      ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፮          አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ስደስት በዚች ቀን ዕውቀትን ከልቡ ያፈለቀ የኢየሩሳሌሙ ሰው የአልዓዛር ልጅ ኢያሱ ሢራክ አረፈ። ❖ እርሱም በጥንተ ትንቢቱ የባሕር አሸዋን የዝናም ጠብታን የዘመንን ቁጥር ማን ቈጠረ አለ፤ ከአብ ጋራ ስለ አለው አንድነት የጥበብ አኗኗር ከዓለም መፈጠር በፊት ነው ለጥበብ መገኛዋ ለማን ተገለጠ የጥበብ ምክሯንስ ማን አወቀ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ የምትቀመጥ እጅግ የምታስፈራ ናት አለ። ❖ ሁለተኛም እኔ ከልዑል አፍ ወጥቼ ምድርን አንደ ጉም ሸፍንኋት በሰማያትም እኖራለሁ ዙፋኔንም በደመና ምሰሶ ላይ ዘረጋሁ ብቻዬን በሰማይ ዳርቻ ዞርኩ በውቅያኖስም ጥልቅ ውስጥ ማረፊያ እየፈለግሁ በባሕሩ ውኃ ላይ ሁሉ ተመላለስኩ አለች አለ፤ ስለ ወልደ እግዚአብሔርም ሰው መሆን እንዲህ አለ እግዚአብሔር በያዕቆብ ዘንድ እደሪ በእስራኤልም ዘንድ ተዋረሺ አለኝ አለች። ❖ ደግሞ ስለ መድኃኒታችን ሞትና ስለ አይሁድ መጥፋት በወጥመዱ ይጠመዳሉ የመሞቻቸው ጊዜም ሳይደርስ ይሠጥማሉ አለ፤ ስለ ንስሓና ከንስሓ በኋላ ወደ ኃጢአት ስለ መመለስ እንዲህ አለ ከታጠቡ በኋላ ቆሻሻን መዳሰስ ምን ይጠቅማል። ❖ ደግሞ ስለ ቤተክርስቲያን መታነፅና ስለ ሕዝብ እንዲህ አለ፤ አቤቱ በስምህ የተጠሩና በበረከት ያባዛኃቸውን ወገኖችህን ይቅር በል መመስገኛህና ማደሪያህ የሆነች ሀገርህ ኢየሩሳሌምንም ይቅር በል፤ የቃልህንም በረከት በጽዮንና በልጆቿ ላይ ምላ፤ ስለሹማምንትና ስለ ሰባቱ መዐርጋት ሲናገር እንዲህ አለ ሰባቱን ኃይሎች የተቀበለች የሰው ሰውነቱ ጉበኛ ናት። ❖ ከዚህም ሁሉ ጋር መንገድህን ያቀናልህ ዘንድ ወደ ልዑል እግዚአብሔር ጸልይ፤ ስለ ጻድቃንም እንዲህ አለ የጻድቃን ልጆች በዱር ጠል የዱር አበባ እንዲ አብብ እንዲሁ ብቀሉ አብቡም እንደ ሊባኖስም መዓዛ መዓዛችሁ እንዲሁ የጣፈጠ ይሁን። ❖ ዳግመኛም የእግዚአብሔርን ሥራ ሲያስብ እንዲህ አለ የሰማይን ንጽሕናውንና ጽናቱን ብርሃኑንም ያሳይ ዘንድ በሰማይ ገጽ ላይ ፀሐይን ማውጣቱን በቀትርም ጊዜ አገሩን ማቃጠሉን አስቦ፤ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ላቦቱን ማን ይቃወመዋል የፀሐይ ዋዕይ ሦስተኛውም ተራሮችን ያቃጥላቸዋል ከእርሱም የእሳት ወላፈን ይወጣል አለ፤ ጨረቃም ለዓለም ምልክቱ ነው በእርሱም የዘመናት የበዓላት ምልክት ይታወቃል፤ ስለ ከዋክብትም የሰማይ ጌጦቿ የከዋክብት ብርሃናቸው ነው በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ እንዲሁ ያበራሉና በሥርዓታቸውም ጸንተው ከልካቸውም ሳይፋለሱ ሳይሳሳቱ ጸንተው ይኖራሉና አለ። ❖ ስለ ቀስተ ደመናም ተናገረ ቀስቱን አየሁ ፈጣሪውንም አከበረ ብርሃኑ መልካም ነውና የልዑል ሥልጣንም ያዘጋጀዋል፤ ስለ በረድና መብረቅም ተናገረ ስለ እርሱ ትእዛዝም በረድ ይዘንማል በቃሉም መብረቅ ይፈጥናል ደመናትም እንደ አዕዋፍ ይበራሉ ነፋስም በእርሱ ፈቃድ ይነፍሳል የነጐድጓድ ድምፅና ብልጭልጭታው ምድርን ያስፈራታል ዐውሎውና ውርጩ ነፍስን ያስጨንቃታል። ❖ ሰማይን እንደ ብረት ልብስ የሚሸፍነው እንደ ስለታም የብርጭቆ ስባሪ ይብለጨለጫል አለ፤ ስለ ዝናምም ተናገረ ዝናም የወረደ እንደሆነ ምድርን ድስ ያሰኛታል በትእዛዙም ባሕር ይደርቃል አለ፤ አባቶችንም በተሰጣቸው ሀብት ሲያመሰግናቸው ኄኖክ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘው፤ ኖኅም ጻድቅ ሁኖ እንደተገኘ። ❖ አብርሃም ታማኝ እንደሆነ ይስሐቅም ለሰው ሁሉ የሚጠቅም በረከት እንደተሰጠው ለያዕቆብም በቸርነቱ እንደ ተገለጠለት ዐሥራ ሁለቱንም ነገድ እንደወለዳቸው በሰውና በእግዚአብሔርም ዘንድ እንደ ተወደዱ። ❖ ሙሴንም ስም አጠራሩ የከበረ የምላእክትም ብርሃን መልኩና ስም አጠራሩ የሆነ አለ፤ ወንድሙ አሮንንም የዘላለም ሕግን እንደ ሠራለት በልብሰ ተክህኖና በወርቅ አክሊል እንዳስደነቀው አለ፤ ሹመቱ ሦስተኛ የሚሆን የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስንም ወደሰ። ❖*የነዌ ልጅ ኢያሱን ለእስራኤል ልጆች የርስታቸውን ምድር እንዳወረሳቸው እጁንም በአነሣ ጊዜ እንደተመሰገነ፤ ሳሙኤልንም በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ እንደሆነ ናታንንም በዳዊት ዘመን ትንቢት እንደተናገረ፤ ዳዊትንም ታናሽ ሁኖ ሳለ አርበኛውን ጎልያድን እንደገደለው አምስግኖታል ሰሎሞንንም በሰላም ወራት እንደነገሠ። ❖ ኤልያስንም ሙት እንዳስነሣ እሳትንም ከሰማይ እንዳወረደ ራሱም በእሳት ሠረገላና በእሳት ፈረሶች እንደዐረገ ኤልሳዕንም በዘመኑ ጠላቶች እንዳስደነገጡት ሁለት ሙታኖችንም እንዳስነሣ አንዱን በሕይወት ሳለ አንዱን ከሞተ በኋላ። ❖ ሕዝቅያስንም አገሩን አጽንቶ እንደ ጠበቀ የፋርስንም ሠራዊት በጸሎቱ አጥፍቶ ስለ ሀገራቸው ጽዮን የሚያለቅሱትን ደስ እንዳሰኛቸው ርኵሰትንና ኃጢአትንም እንደ አስወገደ ኢዮስያስንም የኢዮስያስ ስም አጠራሩ መልካም ነው እንዳለው። ❖ ኤርምያስንም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እንዳከበረው፤ ሕዝቅኤልም የእግዚአብሔርን ጌትነቱን እንዳየ፤ ዘሩባቤልንም በቀኝ እጅ እንዳለ ኀቲም ቀለበት ነው እንዳለው። ❖ ስምዖንን በዘመኑ ቤተ መቅደስ እንደታነፀ በሕዝቡ ከምርኮ መመለስም እንደ ተመሰገነ በመጽሐፉ መጨረሻም፤ በሁሉ ቦታ ታላላቅ ሥራ የሚሠራና ዕድሜያችንን የሚያስረዝም እግዚአብሔር አምላክን አመስግኑት አለ፤ ይህንንም ተናግሮ በፍቅር አንድነት አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 በዚችም ቀን የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው፤ በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር እስከ መለሳቸውና የክብር ባለቤት ጌታችን በእጆቹ ላይ የሚያደርገው ተአምራት በትምህርቶቹም ከሰይጣን ወጥመድ እስከ አዳናቸው ድረስ ጣዖታትን ከሚያመልኩ ከክፉዎች ሰዎች ስለደረሰበት መከራ ነው። ❖ በሸመገለም ጊዜ ወንጌልን ጻፈላቸው ሦስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን እስከሚጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሣሥቶታልና የወልድንም አኗኗሩንና ሰው መሆኑን ዓለም የማይወስነውንም ተአምራቱን። ❖ ከዚህ በኋላም ወደ ሰማይ እንደ ወጣና በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሠራዊት ሥርዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ፤ ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ሊሆን ግብጻውያን ይህን ሠሩ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ውስጥ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ቀን ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።      📌 ግንቦት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ) 2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ) 3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት) 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም) 2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት) 3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/ላሊበላ ወንድም) 4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ 5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 7.አባ ዳንኤል ጻድቅ
230Loading...
16
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"                             ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም       🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፭         አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ አምስት በዚች ቀን ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ሐዋርያ ስምዖን ምስክር ሆኖ አረፈ። ❖ እርሱም ናትናኤል ተብሎ ይጠራል በገሊላ አውራጃ የቃና ሰው ነው የኦሪትና የነቢያትንም መጻሕፍት ተምሮ ያወቀ ነው። መንፈሳዊ ቅንዓትም በውስጡ አለበት ስለዚህም ቀናዒ ተባለ እርሱም ንጹሕ ፊት አይቶ የማያደላ በሃይማኖቱ ዕውነተኛ ነው። ❖ ስለዚህም ፊልጶስ ስለርሱ ሙሴ የጻፈለትን የዮሴፍ ልጅ የሚሉትን የናዝሬቱን ክርስቶስን አገኘነው ባለው ጊዜ ከናዝሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይቻላልን አለው እንጂ አላደላለትም ፊልጶስም ታይ ዘንድ ና አለው፤ በመጣም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ይህ በልቡ ሽንገላ የሌለበት ዕውነተኛ እስራኤላዊ ነው አለው፤ አሁንም ምስጋና ወደመቀበል አልተመለሰም በየት ታውቀኛለህ አለው እንጂ ልብንና ኵላሊትን የሚመረምር ጌታችንም ፊልጶስ ሳይጠራህ በፊት በበለስ ዕንጨት ሥር አየሁህ አለው። ❖ ያን ጊዜም የተሠወረውን የሚያውቅ አምላክ መሆኑን ተረድቶ ጌታዬና ፈጣሪዬ በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ አለው እንደ አይሁድ መምህራንም አልተቃወመም እነርሱ ከዚህ የሚበልጥ ድንቅ ተአምራትንና ኃይሎችን አይተው ለዕውነት አልተገዙምና። ❖ ስለርሱ እንዲህ ተብሏል ጐልማሳ ሁኖ ሳለ ከአሕዛብ ወገን ከሆነ ጐልማሳ ጋራ ተጣልቶ አንዲት አመታትን መትቶ ገደለው በቤቱ ዐፀድም በአለ ዕፀ በለስ በሥሩ ቀበረው ይህንንም ማንም አላወቀበትም፤ ሁለተኛም በሕፃናት ዕልቂት ጊዜ እናቱ በአገልግል ውስጥ አድርጋ በበለስ ዕንጨት ላይ ሰቅላ ትሸሽገው እንደ ነበር በጭልታም አውርዳ አጥብታ መልሳ ትሰቅለዋለች የከመራውም ጊዜ ጸጥ እስከ አለ ድረስ እንዲህ ታደርግ ነበር፤ መድኃኒታችንምም በምልክት ከእርሱ የሆነውን በገለጠለት ጊዜ የተሠወረውን የሚያወቅ ሁሉንም የሚመረምር በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ተረዳ፤ ያንጊዜም ራሱን ዝቅ አድርጎ ለመድኃኒታችን ተገዛለት። ❖ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ ተከተለው ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያትም ጋራ ተቈጠረ፤ አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በተቀበለ ጊዜ የሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ተገለጠለት መለኮታዊ ምሥጢርንም አወቀ ወደ ኵርጅ አገርና ወደ እልብጅህ ከተማ ከሀድያን በድንቁርና ወደሚኖሩበት ሁሉ ገብቶ የሃይማኖትን ብርሃን አበራላቸው፤ ከተራቃቂዎችና ከሰነፎችም ብዙዎችን መልሶ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ሃይማኖት ልባቸውን አበራላቸው፤ የክርስትና ጥምቀትንም አጥምቆ ነጣቂዎች ተኵላ የነበሩትን የዋሃን በጎች አደረጋቸው። ❖ ሁለተኛም ወደሌሎች የከሀድያን አገሮች ወደ በራንጥያ ደሴትም ሒዶ በውስጣቸው ሰበከ፤ ይዘውም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃዩት እርሱ ግን ኃይልና ብርታትን ተጨመረ በእግዚአብሔርም ኃይል ሙታንን አስነሣ እንዲአጠምቃቸውም ለመኑት የክርሰትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ብዙ ዘመንም ኖረ፤ ከዚህም በኋላ ከሀድያን ይዘው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት በዚህም ምስክርነቱን ፈጽሞ ከወንድሞቹ ሐዋርያት ጋራ የማይጠፋ መንግሥትን ወረሰ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን ለሁላችን የክርስቲያን ወገኖችም በረከቱ ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። 🛎 በዚችም ቀን በላይኛው ግብጽ ውስጥ በደንደራ ከተማ አራት መቶ ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ፤ ብዙ ሥቃይንም ሲያሠቃዩአቸው ከኖሩ በኋላ የምስክርነታቸው ፍጻሜ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት መጨረሻ ራስን በመቆረጥ ሆነ። በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። 🛎 በዚችም ዕለት የባሕታዊ ሚናስ ዲያቆንና የአባ ሐርበጥላክያ ሰማዕታት የሆኑ የኤስድሮስም ማኅበር የሆኑ ቀርጢኖስና ሚስቱ መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 ግንቦት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን) 2.ቅዱስ ሚናስ ባሕታዊ 3.ቅዱስ ቀርጢኖስ ሰማዕት 4."400" ቅዱሳን ሰማዕታት 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ 2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ 4.ቅድስት እንባ መሪና 5.ቅድስት ክርስጢና
250Loading...
17
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✍️"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" 📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም 📌 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፬ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ አራት በዚች ቀን ከመንፈሳውያን ሐዋርያት ጋራ አንድነት ያለው የከበረ አባት ጳኩሚስ አረፈ። ❖ ይህም ቅዱስ ከአባ ጰላሞን ዘንድ መንኲሶ ሲያገለግለው የምንኵስናንም በጎ ሥራ እየሠራ ብዙ ዘመናት ኖ፤ ከዚህም በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገልጾለት እንደ አባቶቻችን ሐዋርያት የአንድነትን ማኅበር ለመሥራት መነኰሳትን እንዲሰበስብ አዘዘው። ❖ ከዚህም በኋላ ብዙዎች ሰዎችን ሰብስቦ በየቦታው ብዙ ገዳማትን ሠራላቸው፤ ለሁሉም በእጃቸው ሠርተው በሚአገኙትና በምግባቸው አንድነት እንዲሆኑ በጸሎት ጊዜ በመብልም የሚሠሩትን ሥርዓት ሠራላቸው እርሱ ከሁሉም በላይ አበ ምኔት ሁኖ ከበታቹ ከገዳማት ለየአንዳንዱ አበ ምኔት ሾመላቸው። ❖ ከሀገረ እስዋን ወሰን ከአትፉ ከአክሚም ከተናዱስ እስከ ላዕላይ ግብጽ መጨረሻ ከደቡብም ከባሕራውያን የተመሳቀለ መንገድ ድረስ ሁሉንም ገዳማት በመዞር ይጐበኛቸዋል፤ ይህም አባት ስለዚህ ዓለም ከንቱ ውዳሴና በመካከላቸውም ጥል እንዳይኖር ከልጆቹ ክህነትን እንዲሾሙ አያሰናብትም ግን ለየአንዳንዱ ገዳም የሚቀድሱላቸውን ቀሳውስት ከዓለም አደረገ። ❖ ሊቀ ጳጳሳት ሐዋርያዊ አትናቴዎስ ወደ ላዕላይ ግብጽ በወጣ ጊዜ ይህን አባት ጳኩሚስን ቅስና ሊሾመው ወደደ ከእርሱም ሸሸ፤ የከበረ አትናቴዎስም ልጆቹን የማይናወጽ ቤትን የሠራህ ሆይ ከከንቱ ውዳሴ የራቅህ አንተ ብፁዕ ነህ ልጆችህም ብፁዓን ናቸው ብሎሃል በሉት አባታችሁን አላቸው። ❖ አንድ ጊዜም ሲኦልን ያይ ዘንድ ወደደ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክም ነጥቆ አውጥቶ በገነት የጻድቃንን ማደሪያ እንዲሁም በሲኦል የሥቃይን ቦታ አሳየው፤ ይህም አባት በአንድነት ማኅበር ላይ እያጽናናቸውና ሥርዓትንም እየሠራላቸው አበምኔት ሆኖ አርባ ዓመት ኖረ፤ ከዚህም በኋላ በእርሱ ፈንታ ደቀ መዝሙሩን ቴዎድሮስን ሹሞላቸው በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። 📌 በዚችም ቀን የምስር ገዢ በሆነ በቡላሚስ ዘመን ከሀገረ ፈርማ ሰማዕት የሆነ አባ ሲማኮስ አረፈ፤ ይህም ቅዱስ ቀጭን ልብሶችንና የከበሩ የሐር ልብሶችን የሚሠራ ነው፤ ወዳጆችም አሉት እነርሱም ቴዎድሮስና ሲሲኮስ ናቸው ክርስቲያኖችን ሊአሠቃይ መኰንን ቡላሚስ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ይህ ቅዱስ የዚህን ዓለም ክብር ንቀው እስከተዉ ድረስ ባልንጀሮቹን ይመክርና ያስተምራቸው ጀመር። ❖ ከዚህም በኋላ ወዳጆቹን ተሰናብቷቸው ለሀገረ ድሜራ ቅርብ ወደሆነ ወደ ሀገረ በክሩዝ ወጣ መኰንኑንም አንዲቷን ሴት ሲአሠቃያት አገኘው፤ ወደ እሳት ምድጃም ጨምሮዋት በሰማዕትነት ሞተች፤ በኋላ ግን እሳቱ ቀዝቃዛ ሆነ ይህ ቅዱስም ይኽንን ይመለከት ነበር። ❖ ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ፊት ቀርቦ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበረ፤ ሰቀሉት ከመንኰራኲርም ውስጥ ጨምረው አበራዩት ከእርሱም ብዙ ደም ፈሰሰ ወደ አንዲት ዕውርት ሴትም ደሙ ደርሶ ነካት ያን ጊዜም ድና አየች። ❖ ከዚያም ደግመው በእንጨት ላይ ሰቀሉት እርሱም ይረዳው ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ፈጽሞ ይማልድ ነበር፤ መኰንኑም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ሰያፊውም ይቆርጠው ዘንድ ሰይፉን መዘዘ ኃይል ተነሥቶት ማንቀሳቀስ አልተቻለውም፤ እንዲሁም ሁለተኛው ሦስተኛው እስከ ዐሥራ አራት ሰይፈኞች ኃይላቸው ደክሞ በምድር ላይ ወደቁ። ❖ ከዚህ በኋላ በአንገቱ ገመድ አስገብተው እስከ ረዢም ተራራ አናት ድረስ ጐተቱት፤ ነፍሱንም በክብር ባለቤት ጌታችን እጅ ሰጥቶ የምስክርነት አክሊልን ተቀበለ፤ ከወታደሮች ውስጥ ዲዳና ደንቆሮ ነበረ የቅዱሱን ሥጋ በአየ ጊዜ ጆሮቹ ሰሙ አንደበቱም ተናገረ እድኩ ከተባለ ሀገርም ምእመናን መጥተው የቅዱስ ሲማኮስን ሥጋ ወሰዱ፤ የድሜራና የታይን የሁለቱ አገሮች ሰዎች ተሰበሰቡ መኰንኑ ቢላሞስም ፈርቶ ሸሸ ከሥጋውም ድንቆች ታላላቅ ተአምራት ለበሽተኞችም ፈውስ ሆነ፤ አረማውያንም አይተው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ተጠመቁ፤ በሰማዕትነትም ሞቱ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ሰባት መቶ ኃምሳ ሆነ ወንዶችና ሴቶች ወጣቶችም። ❖ ከዚህ በኋላ የቅዱስ ሲማኮስን ሥጋ ተሸክመው በርሙን ወደሚባል አገር በታላቅ ክብር ወሰዱ፤ የሀገሩ መኰንንም ከራሱ መልካም ልብሶችን አምጥቶ ገነዘው ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ሥጋውን በውስጧ አኖረ ከእርሱም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሲማኮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 📌 ግንቦት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ዻኩሚስ (አበ መነኮሳት ሣልሳዊ) 2.አባ ሲማኮስ ሰማዕት 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) 2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ 3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው) 5.አባ ስምዖን ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ 7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
220Loading...
18
Media files
190Loading...
19
Media files
200Loading...
20
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ አርሳኒ +"+ =>ቅድስት ሃይማኖት እዚህ ዛሬ እኛ ጋር የደረሰችው በበርካታ ሰማዕታትና ጻድቃን ደም ነው:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዎቿ እንጨትና ድንጋይ እንዳይመስሏችሁ:: አጽመ ቅዱሳን ነው እንጂ:: +ቅዱሳን ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስን እንደ እኔ እና እንደ ዘመኑ ትውልድ በከንፈራቸው የሚሸነግሉ አልነበሩም:: እነርሱ በፍጹም ልባቸው ስለ ፍቅሩ ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ እንጂ:: በቅድስናቸው ከተመሰከረላቸው ቀደምት ቅዱሳን አንዱ ደግም ቅዱስ አርሳንዮስ ነው:: +ቅዱሱ የተወለደው በ345 ዓ/ም ሮም ውስጥ ነው:: በወጣትነቱ ይሕ ቀረህ የማይሉት የጥበብና የፍልስፍና ሰው ነበር:: በተለይ በትልቁ የሮም ቄሳር ቴዎዶስዮስ ዘመን በቤተ መንግስት አካባቢ የተከበረና የንጉሡ ልጆች መምሕር ነበር:: አኖሬዎስና አርቃዴዎስን ቀጥቶ ያሳደጋቸውም እርሱ ነበር:: +በድንግልና እስከ 40 ዓመቱ ድረስ ሮም ውስጥ ቆየ:: ከዚህ በኋላ ግን ስለ ሰማያዊ ነገሮች ሲያስብ መልዐኩ በሕልም ወደ ግብፅ ሒድ አለው:: በመጀመሪያ ወደ እስክንድርያ ቀጥሎ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ መነኮሰ:: በቆይታ ግን ብሕትውና ምርጫው ሆነ:: +ቅዱስ አርሳኒ በእነዚሕ ነገሮቹ ይታወቃል:- 1.በምንም ምክንያት ከማንም ጋር አያወራም:: (ለ60 ዓመታት በአርምሞ ኑሯል) 2.በቤተ መቅደሱ ግድግዳ ተጠግቶ እንባውን ሲያፈስ የርሱን አካል አርሶ በመሬት ላይ ሲፈስ ይታይ ነበር:: ከእንባው ብዛት ቅንድቦቹ ተላልጠው አልቀው ነበር:: 3.በርካታ ድርሳናትን ደርሷል:: ብዙዎቹ ዛሬም ግብጽ ውስጥ አሉ:: 4.ሸንጎበቱን ወደ ደረቱ አዘንብሎ ስለሚቆም ማንንም ቀና ብሎ አያይም ነበር:: 5.ለጸሎት አመሻሽ 11:00 አካባቢ ላይ ይቆምና ጸሎቱን የሚጨርስ ፀሐይ ግንባሩን ስትመታው ነው:: 6.ሁል ጊዜ ራሱን "አንተ ሰነፍ (ሐካይ) እያለ ይገስጽ ነበር:: 7.በገዳማውያን ታሪክ የርሱን ያሕል በቁመቱ ረዥም አልተገኘም ይባላል:: የራሱ ጸጉር በጀርባው የወረደ ሲሆን ጽሕሙን በስዕሉ ላይ እንደምታዩት ነጭና እስከ መታጠቂያው የወረደ ነበር:: +እነዚህ ግን በጣም ጥቂቶቹ ናቸው:: +ቅዱስ አርሳንዮስ አካሉ በተጋድሎ ደቆ: ለ60 ዓመታት በግሩም መንፈሳዊነት ኑሮ በ100 ዓመቱ በዚሕች ዕለት ዐርፏል:: ❖አምላካችን እግዚአብሔር ከታላቁ የቅድስና ሰው አርሳኒ በረከት አይለየን:: =>ግንቦት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አርሳንዮስ - አርሳኒ (ጠቢብ ገዳማዊ) =>ወርኀዊ በዓላት 1.እግዚአብሔር አብ 2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት 3."99ኙ" ነገደ መላዕክት 4.ቅዱስ አስከናፍር 5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች 6.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ =>+"+ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል:: ደግሞ ተገርቷል:: ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም:: የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው:: በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን:: በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን:: ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ:: ወንድሞቼ ሆይ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም:: +"+ (ያዕ. 3:7-11) ወስብሐት ለእግዚአብሔር
200Loading...
21
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሀ ወሰላም       🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፫       አንድ  አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን የከበረ አባት በገድል ተጠምዶ የኖረ ብልህ አርሳንዮስ አረፈ። ❖ ይህም ቅዱስ ከሮሜ አገር ሰዎች ከባለጸጎችና ከታላላቆቿ ነው፤ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምረው ዲቁናን አሾሙት፤ ከዚህም በኋላ አቴና ወደሚባል አገር ሒዶ ፍልስፍናን የፀሐይንና የጨረቃን የከዋክብትንም አካሔዳቸውን የዘመናትንም መለኪያና መቊጠሪያ ተምሮ በመልካም አጠና፤ ከብዙዎችም ከፍ ከፍ አለ በመንፈሳዊ ትምህርቱም ፍጹም ሁኖ አምላካዊ ትሩፋትን የሚሠራ ሆነ። ❖ በሮሜ አገርም ታላቁ ቴዎዶስዮስ በነገሠ ጊዜ ልጆቹን አኖሬዎስንና አርቃዴዎስን የሚያስተምርለት ጥበበኛ ደግ ሰው ፈለገ፤ ይህንንም ቅዱስ ወደ ንጉሥ ወሰዱት፤ ንጉሡም ልጆቹን አኖሬዎስንና አርቃዴዎስን እንዲያስተምርለት አዘዘው እርሱም ታዝዞ የንጉሡን ልጆች እንደሚገባ ሊያስተምር ጀመረ፤ በብዙ ትግልና ድካም ስለሚአስተምራቸው ያለርኅራኄ ብዙ ድብደባን ይደበድባቸው ነበር። ❖ ንጉሥ ቴዎዶስዮስም በአረፈ ጊዜ ልጆቹ አኖሬዎስ በሮሜ አገር አርቃዴዎስም በቊስጥንጥንያ ነገሡ፤ እግዚአብሔርም በአርሳንዮስ ልብ ፍርሀትን አሳደረ በታናሽነታቸው ጊዜ ሲአስተምራቸው የሚመታቸው ስለሆነ በዚህ ምክንያት ከዓለም ይወጣ ዘንድ የነፍሳቸውንም ድኅነት ለሚሹ የሚበራ መብራት ሆኖ ሌሎች ይበሩበት ዘንድ አነሣሣው፤ ምን እንደሚአደርግ በልቡ እያሰበ ሳለ እነሆ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ የሚል ቃል መጣ አርሳኒ አርሳኒ ከዚህ ዓለም ውጣ አንተም ትድናለህ፤ ይህንንም ቃል በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ተነሣ እንጂ አልዘገየም ወዲያውኑ ልብሱን ለውጦ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ። ❖ ከዚያም የከበረ የአባ መቃርስ ገዳም ወደ አለበት ወደ አስቄጥስ በረሀ ደርሶ በጾም በጸሎት በመስገድ በመትጋት በአርምሞና በትሩፋት ሁሉ ፍጹም ተጋድሎን ተጋደለ፤ ስለ ዝምታውም በጠየቁት ጊዜ እኔ ስለራሴ ብዙ አዝናለሁ አላቸው እርሱ ግን በውስጥና በአፍኣ ትሑትና ቅን የዋህ ነው የእግዚአብሔርንም ሥራ ይሠራል፤ ሁል ጊዜም እጅ ሥራውን አያቋርጥም ከዕለት ምግቡ የሚተርፈውንም ይመጸውታል። ❖ የነፍሳቸውንም ድኅነት ለሚሹ ጥቅም ያላቸውን ብዙ ድርሰቶችንና ተግሣጾችን ደረሰ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያንም በሚገባ ጊዜ ሰው እንዳያየው በምሰሶ ኋላ ይሠወራል፤ ይህም አባት ድንቆች ተአምራትን ያደርጋል የብዙዎች ሰዎችን ገድል እግዚአብሔር ገልጦለታልና፤ መልኩም ያማረ ሕዋሳቱም የጸኑ ፊቱም ብሩህና እጅግ ደስ የሚል ጽሕሙም ከወገቡ መታጠቂያ የሚደርስ ረጅም ነው፤ ከልቅሶ ብዛትም የተነሣ የቅንድቡ ጠጉር ተነቀለ ቁመቱም ረጅም ነው ግን ያጐነብሳል ወደ መልካም ሽምግልናም ደረሰ ዕድሜውም ሁሉ መቶ ዓመት ሆነ፤ በሮሜም አርባ ዓመት ኖረ በአስቄጥስ ገዳም ሠላሳ አምስት በምስር ገዳም ሃያ ዓመት በእስክንድርያ ሦስት ዓመት ከዚህም በኋላ ወደ ምስር ገዳም ተመልሶ በዚያ ሁለት ዓመት ተቀምጦ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                              ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥                   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ የጣሊያን ፋሽስት ወታደሮች እነ አቡነ ጴጥሮስንና ኢትዮጲያዊያን ጀግኖችን ነገሥታትን ሊቃውንት በምታፈራውን ደብረ ሊባኖስ ለይ ከፍተኛ ጥቃት የተፈጸመበት ዕለት ነው:: ❖ በዕለቱ ግንቦት አሥራ ሁለት በደብረ ሊባኖስ ገዳም የአባታችንን ፍልሰተ አጽም ለማክበር ተስብስበው ባሉ መኖኮሳት ዲያቆናትንና ምእመናን ላይ ኢሰባዊ የሆነ አረመኒያዊ ድርጊት በመፈጽመው ከ2000-3000 የሚደርሱ ምእመናን የጨፈጨፉበት ዕለት ነው፤ ምክንያታቸውም የኢትዮጲያዊነት መሰረት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የልብ ትርታ የሆነች ቦታ ደብረ ሊባኖስ ነችና ገዳሙ ላይ ዘመተ። ❖ ደብረ ሊባኖስንና በውስጧ ያሉትን ማጥፋት ኢትዮጲያን ማጥፋት ነው ብለው በ1929 ዓ.ም ከግንቦት 10 እስከ 13 ድረሰ በገዳሙ ያገኙት መነኰሳት ካህናትና ምእመናን በሙሉ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀ ወታደር መስቀል፣ ወንጌልና ዳዊት በታጠቁ ምእመናን ላይ ጭፍጨፋ ያካሄድበት ቀን ነው:: ❖ በዚህም ቡዙዎችም ታፍነውና ታፍሰው ተረሽነዋል ቡዙዎችም በሰማዕትነት አልፈዋል፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በሰማዕትነት ያለፉት ደማቻው አገራችንንና ሰው ያጣች ቤተክርስቲያናችን ይጠብቅልን። 📌 ግንቦት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  1.ቅዱስ አርሳንዮስ - አርሳኒ (ጠቢብ ገዳማዊ)   📌 ወርኀዊ በዓላት 1.እግዚአብሔር አብ 2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት 3."99ኙ" ነገደ መላዕክት 4.ቅዱስ አስከናፍር 5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች 6.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
140Loading...
22
Media files
240Loading...
23
††† እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ††† ††† ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን : ክብራችን : ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን? *አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም):: *ልቡናው የቅድስና ማሕደር:: *ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው:: *እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ! ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- "ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ : ሙሉ አካሏ ነው::" ††† የሊቁ ዜና ሕይወት በጥቂቱ ††† ††† ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ:: ሊቁ በሕጻንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር:: ትምሕርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም:: በጥበበ እግዚአብሔር እንጂ:: ምን ትምሕርት ባይገባው ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር:: አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው:: ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ:: ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምሕሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው:: ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና:: ከዚህ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ : ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ:: ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ:: እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው:: ካህኑ ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ወሰነ:: በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር:: ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት:: ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት:: ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት : ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት:: ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር : ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ:: ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት:: ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ:: ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ:: ቅዱስ ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ : ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላት ከሃገሩ ወጣ:: ††† ቅዱስ ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት:- 1. አምስት ያሕል መጻሕፍትን ጽፏል:: 2. በጣና ቂርቆስ : በዙር አባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል:: 3.በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋሃ መላእክትና በተባሕትዎ ኑሯል:: ††† በ576 (571) ዓ/ም በተወለደ በ71 ዓመቱ በዚህች ቀን ተሰውሯል:: ††† አባቶቻችን:- *ጥዑመ ልሳን *ንሕብ *ሊቀ ሊቃውንት *የሱራፌል አምሳያ *የቤተ ክርስቲያን እንዚራ *ካህነ ስብሐት *መዘምር ዘበድርሳን *ማኅሌታይ *ልዑለ ስብከት እያሉ ይጠሩታል:: ††† የቅዱሱ ጸሎትና በረከት ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: ††† ግንቦት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ 2.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ 3.ቅዱሳን ክርስቲናና ይስሐቅ (የቅዱስ ያሬድ ወላጆች) 4.ቅድስት ታውክልያ እናታችን (ንግሥናን ንቃ ሰማዕት የሆነች) 5.ቅድስት ኤፎምያ ሰማዕት 6.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 7.ቅድስት አናሲማ ገዳማዊት 8.አባ በፍኑትዮስ ገዳማዊ 9.አባ አሴር ሰማዕት (ኢትዮዽያዊ) 10.አባ በኪሞስ ጻድቅ ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት 2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት 3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና ††† "እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ:: እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ:: በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደሆነ አላውቅም:: እግዚአብሔር ያውቃል:: ወደ ገነት ተነጠቀ:: ሰውም ሊናገር የማይገባውን: የማይነገረውን ቃል ሰማ::" ††† (2ቆሮ. 12:2-5) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +°✝ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ✝°+ =>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: ግን እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር:: << ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? >> +ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል:: +ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው:: +ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት:: +ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር:: +ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር::
110Loading...
24
+ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል " አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል:: +ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: +በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: +አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ (ግብዣ አዘጋጀ):: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ:: +ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ:: +በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው:: +"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር:: +"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር:: +'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም:: +አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች:: +ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል:: +ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል:: ✔ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:- *ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ *አፈ በረከት *አፈ መዐር (ማር) *አፈ ሶከር (ስኳር) *አፈ አፈው (ሽቱ) *ልሳነ ወርቅ *የዓለም ሁሉ መምሕር *ርዕሰ ሊቃውንት *ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) *ሐዲስ ዳንኤል *ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው) *መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ *ጥዑመ ቃል - - - +እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ ይክፈለን:: +ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ56 ዓመታት በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመዋል:: +እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች:: ❖ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር ያድለን:: ❖ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (የዓለም ሁሉ መምሕር) 2አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ (ፍልሠታቸው) 3.ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ (ቃል ኪዳን የተቀበለችበት) 4.አባ አብርሃም ዘደብረ ሊባኖስ 5.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ 6.እስክንድር ንጉሠ ኢትዮዽያ 7.ቅዱስ መስቀል (የተአምር በዓሉ) 8.አባታችን ያሬድ (የማቱሳላ አባት) 9.ቅዱስ ሚናስ ዲያቆን❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት2፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ 3፡ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ 4፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ 5፡ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ 6፡ ቅዱስ ላሊበላ 7፡ ቅድስት መስቀል ክብራ ++"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:13-16) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
150Loading...
25
Media files
160Loading...
26
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"                             ቀናችንን በጸሎት እንጀምር በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም 🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፩ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚች ቀን የቅዱስ ዮስጦስ ሚስት ቅድስት ታውክልያ በሰማዕትነት አረፈች።     ❖ በየካቲት ዐሥር እንደ ተጻፈ የእስክንድር ገዢ እርስበርሳቸው ከአለያያቸው በኋላ ቅድስት ታውክልያን ወደ ሀገረ ፃ ወሰዱዋት፤ በሀገረ ፃ መኰንንም ፊት የመኰንኑ እስክንድርያን መልእክት በአነበቡ ጊዜ መንግሥታቸውን ትተው እንዴት ከመንግሥታቸው ሞትን መረጡ ብሎ አደነቀ። ❖ ከዚህ በኋላ መኰንኑ ሸነገላት ብዙ ታላላቅ ቃል ኪዳኖችንም ገባላት፤ የከበረች ታውክልያም እኔ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር መንግሥቴን ተውኩ ከልጅነት ባሌም ተለየሁ በልጆቼም አልተጽናናሁም ለመሆኑ አንተ የምትሰጠኝ ስጦታ ምን ያህል ነው ብላ መለሰችለት፤ ይህንንም ሰምቶ ታላቅ ግርፋት እንዲገርፉዋት አዘዘ የሥጋዋም ቊርበት እስከሚቆራረጥ ገረፉዋት። ❖ ከዚህ በኋላም ከእሥር ቤት አስገቡዋት የእግዚአብሔርም መልአክ ተገለጠላትና ቊስሎቿን አዳናት፤ እሥረኞችም አይተው አደነቁ ብዙዎቹም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት አገፉ፤ የምስክርነቷ ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለከበረች ታውክልያ ተገልጾላት አጽናናት ከክብር ባለቤት ጌታችንም የተሰጡዋትን ቃል ኪዳኖች ነገራት። ❖ በዚያን ጊዜም ራስዋን ይቆርጡ ዘንድ መኰንኑ አዘዘ የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች፤ ምእመናን ሰዎች መጥተው ለወታደሮች ብር ሰጥተው የቅድስትን ሥጋ ወሰዱ በመልካም መግነዝም ገንዘው የስደቱ ወራት እስኪፈጸም በሣጥን ውስጥ አኖሩዋት፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።                  ✍️ በዚችም ዕለት የከበረ ኤጲስቆጶስ አባ በፍኑትዮስ አረፈ፤ ይህም ከታናሽነቱ በአባ መቃርስ ደብር በአስቄጥስ ገዳም መነኰሰ ታላቅ ተጋድሎንም በመጋደል ብዙ ትሩፋትን ሠራ፤ አዘውትሮ ይጾም ነበረ ቅጠላቅጠልን ይበላል እንጂ በእሳት የበሰለ አይበላም በገዳሙ ውስጥም መጻሕፍትንና የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ተምሮ ቅስና ተሾመ በዚያም ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ እነሆ ትሩፋቱና ጽድቁም በሁሉ ዘንድ ታወቀ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊላታዎስም ልኮ ወደ እርሱ አስመጥቶ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾመው። ❖ ኤጲስቆጶስነትም ከተሾመ በኋላ ቅዳሴ በሚቀድስ ጊዜ ካልሆነ በቀር ከቶ ልብሱን አልለወጠም ቅዳሴውንም ሲፈጽም ከጠጉር የተሠራውን ማቅ ይለብሳል፤ እንዲህም የሚጋደልና የሚጸመድ ሆኖ ኖረ በዚህ ሁሉ ዘመንም ከመነኰሳት ጋራ ያገለግል ነበረ በታመመ ጊዜም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀው። ❖ የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኢጲስቆጶስነት ስለተሾምኩ ጸጋህን በውኑ ከኔ ታርቃለህን ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ወደርሱ መጥቶ አስተውል ዕወቅ አንተ በገዳም ሳለህ በታመምክ ጊዜ የሚጎበኝህ የለም ወይም የሚአገለግልህና ለደዌህ መድኃኒትን የሚሰጥህ አታገኝም ነበር፤ ሰለዚህ እግዚአብሔር የሚረዳህና ደዌውንም ከአንተ የሚያርቅልህ ሆነ፤ ዛሬ ግን እነሆ አንተ በዓለም ውስጥ ነህ በአንተ ዘንድ የሚጐበኝህና የሚአገለግልህ አለ ለደዌህም መድኃኒትን የምትሻውንም ምግብ ታገኛለህ አለው። ❖ ይህም አባት በኤጲስቆጶስነት ሹመት ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ የሚያርፍበትም በቀረበ ጊዜ ካህናቱንና ዲያቆናቱን መምህራኑን ጠራቸው፤ የአብያተ ክርስቲያናትንም ንዋየ ቅዱሳታቸውንና ገንዘባቸውን ሁሉ ሰጣቸው እንዲህም አላቸው ዕወቁ እኔ ወደ እግዚአብሔር እሔዳለሁና እንደሚገባም በመካከላችሁ እንደ ኖርኩ እናንተ ታውቃላችሁ፤ ለኤጲስቆጶስነት ሹመቴም እጅ መንሻ ከሚአመጡልኝ እንኳ አንድ የብር አላድ እንዳልሠወርኩ በፊቱ ልቆም ያለኝ የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኔ ላይ ምስክርን ይሁን አላቸው። ❖ ይህንም ሰምተው አለቀሱ ተሳለሙትም እንዲባርካቸውና በክብር ባለቤት ጌታችንም ዘንድ መራዳቱን እንዳይረሳ ለመኑት እርሱም ባረካቸው፤ እግዚአብሔርም ያክብራችሁ እስከ መጨረሻዪቱም ሕቅታ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጽናችሁ ይህንንም ብሎ በሰላም አረፈ፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። 🛎 በዚችም ቀን የባሌ መምህር አባ አሴር በሰማዕትነት አረፈ ይኸውም በንጉሥ ወናግ ሰገድ ዘመን ወደ ኢየሩሳሌም ወርዶ ሳለ መጀመሪያ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡ። በኋላም የጌታችን እግር በቆመበት በኢየሩሳሌም መግቢያ በእሳት አቃጠሉት።በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 🛎 በዚች ቀንም ቅድስት አናሲማ አረፈች ይቺም ቅድስት በደናግል ገዳም መንኵሳ ራስዋን እብድ አስመስላ ኖረች፤ በሌሊትም በጾምና በጸሎት ሥጋዋን በመቅጣት ራሷን ታሠቃያለች ሰዎችም በሚያዩዋት ጊዜ ራስዋን አእምሮዋን እንደሳተች ታስመስላለች መበለቶችም ይሰድቧታል። ❖ እግዚአብሔርም ገድሏን ለአባ ዳንኤል ገለጠ፤ እርሱም ከደናግል ገዳም ሔዶ ትሩፋቷንና ገድሏን ሁሉ ለእመ ምኔቷ ነገራት እርሷም ለእኀቶች መነኰሳይያት ነገረቻቸው ከዚያችም ዕለት ወዲህ አከበሩዋት፤ እርሷም ስለ አዋረዱዋትና ስለ አጐሳቈሉዋት እኀቶችን እያመሰገነች ደብዳቤ ጽፋ ትታ ከንቱ ውዳሴን በመጥላቷ ተሠውራ በሌሊት ወጥታ ወደ ዱር ሸሸች በዚያም በሰላም አረፈች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።   🛎 በዚችም ቀን በዲዮቅልጥያኖስ መንግሥት ዘመን ቅዱስት ኤፎምያ በሰማዕትነት አረፈች፤ የዚችም የእናቷ ስም ቴዎድርስያኒ ነው እርሷም የክብር ባለቤት ክርስቶስን የምታምንና የምትፈራው ናት፤ ሰይጣንም ክርስቲያኖችን በማስገደድ ለጣዖት እንዲያሰግድ አንቲሂጳጦስን በአነሣሣው ጊዜ ይቺን ቅድስት ኤፎምያን ከብዙ ክርስቲያኖች ጋራ አሥረው አመጡዋት፤ አንቲሂጳጦስም ለአማልክት ሠዊ አላት፤ እኔ ከክብር ባለቤት ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አልሠዋም የአባቶቼን ተስፋ ለማግኘት ልቤ የጸና ነውና አለችው። ❖ ያን ጊዜ አንቲሂጳጦስ ተቆጥቶ ዐጥንቷ እንዲሰበር ሕዋሳቷ ሁሉ እንዲለያይ ከሠረገላ መንኰራኩር ውስጥ ይጨምሩዋት ዘንድ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ አዳናት ሁለተኛም ነበልባሉ አርባ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ እስከሚል እሳትን አንድደው ከውስጡ ይወረውሩዋት ዘንድ አዘዘ፤ በእሳቱ መካከልም ቁማ ጸለየች እየጸለየችም በደኅና ወጣች ብዙዎችም በጌታ አምነው በሰማዕትነት አረፉ። ❖ ከዚህም በኋላ እስከ ማግሥት ከወህኒ ቤት ጨመራትና በማግሥቱ ወደ ሸንጎ አወጧት እርሱም ለአማልክት ሠዊ አላት፤ ቅድስት ኤፎምያም ሣቅ ብላ እኔስ ለማይናገሩ ደንጊያዎች አልሠዋም አለችው፤ አንቲሂጳጦስም ሰምቶ ሥጋዋን ይገፉ ዘንድ መቃጥን ያላቸው አራት ደንጊያዎችን እንዲያመጡ አዘዘ፤ ሁለተኛም አራዊት ከአሉበት ኲሬ ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዝዞ ከዚያ ወረወሩዋት፤ አራዊት ግን ተሸክመው አውጥተው ከውኃው ዳር አቆሙዋት፤ ደግሞ ስለታሞች ደንጊያዎችንና ሰይፎችን በመሬት ውስጥ እንዲተክሉ ተቆራርጣ ትሞት ዘንድ በላያቸው እንዲያስሮጡዋት አዘዘ ሩጣም ተሻገረች ምንም የነካት
170Loading...
27
የለም፤ ደግሞም በግለቱ ታር ዘንድ ደብድበው ከብረት ምጣድ ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዘዘ ግን ምንም ምን አልነካትም። ❖ ከዚህ በኋላም አራዊትን ሁሉ ድባትንም ሰበሰበ፤ በላይዋም ወሰዱዋቸው አንበሶችም እግርዋን ሳሙ አንዲትም አውሬ ተሸብራ እግርዋን ነከሰቻት ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ የተመሰገንሽ ኤፎምያ ወጥተሽ ወደ ከበረ ቦታ ነዪ፤እንዲህም ገድሏን ምስክርነቷን ፈጸመች እናትና አባቷም መጥተው ገንዘው በአዲስ መቃብር ውስጥ ቀበሩዋት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚች ቅድስት ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።       📌 ግንቦት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ 2.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ 3.ክርስቲናና ይስሐቅ (የቅዱስ ያሬድ ወላጆች) 4.ቅድስት ታውክልያ እናታችን (ንግሥናን ንቃ ሰማዕት የሆነች) 5.ቅድስት ኤፎምያ ሰማዕት 6.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 7.ቅድስት አናሲማ ገዳማዊት 8.አባ በፍኑትዮስ ገዳማዊ 9.አባ አሴር ሰማዕት (ኢትዮዽያዊ) 10.አባ በኪሞስ ጻድቅ 📌 ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት 2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት 3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
160Loading...
28
✨✨✨✨✨✨✨✨ ✨✨✨✨✨✨✨✨                   ✥ ቅዱስ ያሬድ ✥ ✥መላእክት ምስጋናቸው እረፍታቸው ፣ እረፍታቸው ምስጋናቸው ሆኖ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ እግዚኣብሔርን ያለማቋረጥ ያመሰግናሉ፡፡ ቤተክስቲያንም አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ናትና ይህን አብነት በማድረግ ልዑል እግዚኣብሔር ሃያ አራት ሰዓት የሚመሰገንበትን የምስጋና ሥርዓት ዘርግታለች፡፡ሕያው እግዚኣብሔር የአዳም ልጆች በመላእክት ምስጋና እንዲያመሰግኑት በመውደዱ ሰማያዊውን ምስጋና ይማር ዘንድ ቅዱስ ያሬድን መረጠ፡፡ 👉ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን 505 ዓ.ም ኣክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ ያሬድ ማለት መውረድ ማለት ነው ፡፡ ሰማያዊውን ጣእመ ዜማ ወደ እኛ የሚያወርድ ነውና፡፡‹‹ዋይ ዜማ!!! ዘሰማዕኩ እመላእክት ቅዱሳን ›› ‹‹ ከሰማይ ከቅዱሳን መላእክት የሚያስደንቅ ዜማ ሰማሁ›› በማለት እንደተናገረ በኣክሱም መጽሓፍትን እያስተማረ ሳለ ከሰማያውያን መላእክት ጣእመ ዜማን ተማረ፡፡ በተመስጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ተነጠቀ፡፡ በዚያም መላእክት ልዩ ጣእም ባለው የዜማ ድምፅ ሲያመሰግኑ ሲዘምሩና ሲያሸበሽቡ አየ፡፡ ከጣዕመ ዜማውም የተነሣ ተደነቀ፡፡ የእግዚኣብሔርን ስም እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን በጠራ ጊዜ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዜማ ተገለጸለት፡፡ ተመልሶም ወደ ምሥራቅ ዞሮ እጁንም ዘርግቶ ‹‹ ሃሌ ሉያ ለአብ ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፣ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን . . . ›› ብሎ በኣክሱም ከተማ ሙራደ ቃል /የቃል መውረጃ/ በተባለችው ሥፍራ ለመጀመሪያ ጊዜ ዜማን በዐውደ ምሕረት ያሰማ የዜማ ደራሲ ነው፡፡ 👉የቅዱስ ያሬድ አስተዋጽኦ 📌ዓለም ከሚያውቃቸው የዜማ ደራስያን ከሞዛርትና ከሌሎችም አስቀድሞ ቅዱስ ያሬድ ግእዝ፣ እዝል ፣ አራራይ በተሰኙ የዜማ ስልቶች የማይሰለችና ዘመን ተሸጋሪ ዜማን፣ የዜማ ምልክቶችንና የተለያዩ ድርሰቶችን በመድረስ ሃገራችን የዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሃብት ባለቤት እድትሆን ኣድርጓል፡፡ 📌📌 ቅዱስ ያሬድ በሰዓታት ፣በወራትና በዘመናት የተከፋፈሉ ድንቅ ምስጋናዎችን ከብሉያትና ከሐዲሳት ንባብና ምሥጢር ለቤተክርስቲያን እንደ ሰምና ወርቅ ኣስማምቶ የአገልግሎት ሥርዓትን የሠራ የቤተ ክርስቲያን ዓምድ ነው፡፡ 📌📌 የቅዱስ ያሬድ ዜማ ድንቅና ጥልቅ የነገረ ሃይማኖት አስተምህሮት ፣ የቅዱሳት መጽሓፍትን ንባብ ትርጓሜ እንዲሁም የታሪክ ምስክርነትን የያዘ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ድርሰት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዛሬ በጉባኤ ቤት ለዜማ ትምህርት ቤተክርስቲያን የምትገለገልበትን ሥርዓተ ትምህርትና የመማሪያ መጽሓፍትን የደረሰ ሊቅ ነው፡፡ ድረሰቶቹም ምዕራፍ ፣ ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ዝማሬና መዋሥዕት ይባላሉ፡፡ 📌📌ቅዱስ ያሬድ በአክሱም በመምህሩ በጌዴዎን ወንበር ተተክቶ መጽሓፍተ ብሉያትና ሓዲሳትን ኣስተምሯል፡፡ ከኦቡነ አረጋዊና ከኣፄ ገብረ መስቀል ጋርም በመሆን በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎት በጣና ቂርቆስ ፣ በዙር ኣባ ኣቡነ ኣረጋዊ ገዳም እንዲሁም ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ እስከ ብርብር ማርያም በመሄድ ያስተማረ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡   አጠቃላይ በሥነ ጽሑፍና በቋንቋ እድገት በነገረ መለኮትና በታሪክ ትምህርት እንዲሁም በሥርዓተ ጸሎት የቤተ ክርስቲያን ኣንድነት በማስጠበቅ ረገድ ጽኑ መሠረትን የጣለ ታላቅ ሊቅ ነው፡፡ 👉 የቅዱስ ያሬድ ምናኔ 📌📌 ቅዱስ ያሬድ የሕይወት ዘመኑን በጸሎትና በብሕትውና ለማሳለፍ ወደ ሰሜን ተራራ ምድረ ጸለምት በመሄድ /በሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት በበየዳ ወረዳ በሚገኝ ሥፍራ/ ብርድ በጸናበት በረዶ በሚፈላበት በሐዊ ተራራ በጽሙና ተቀምጧል፡፡ በዚያም ጉባኤ ዘርግቶ ትምህርት አስፋፍቶ ለሃያ ሁለት ዓመታት ኣስተምሯል፡፡ 📌📌ቅዱስ ያሬድ ዘመኑን ሁሉ በማኅሌት እግዚኣብሔርን በማገልገል በጣእመ ዜማው ዲያብስን ድል መትቶ በዚያው በሓዊ ተራራ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ ገብቶ ግንቦት 11 ቀን በሰባ ኣምስት ዓመቱ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ ተለይቷል(ተሰውሯል)፡፡ ቤተክርስቲያንም ቅድስናውንና ኣማላጅነቱን ኣምና በስሙ ጽሌ ቀርጻ፣ ቤተክርስቲያን አንጻ ፣ ድርስቶቹንም የቤተክርስቲያን መገልገያና የስርዓተ ኣምልኮ መፈጸሚያ አድርጋ እየተጠቀመችባቸው ተገኛለች፡፡ በምናኔ በኖረበት ሥፍራም በስሙ ገዳም ተገድሞ መናንያን አሰረ ፍኖቱን ተከትለው ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ በረዶውንና ውርጩን ታግሠው በስሙ እየተማጸኑ ይኖራሉ::                   እንኳን አደረሳችሁ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
200Loading...
29
††† "ናቡከደነፆርም መልሶ:- መልአኩን የላከ : ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን : የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን : በእርሱ የታመኑትን ባርያዎቹን ያዳነ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ::" ††† (ዳን. 3:28) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
150Loading...
30
❖ በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶት ጽና አትፍራ አንተ ጠላቶችህን ድል አድርገህ የሰማዕትነትን አክሊል ትቀበላለህና አለው፤ ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን ወደ ተጠመቀባት ወደ ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ በሥዕሉ ፊት ቁሞ ጸለየ፤ በርሱም ዘንድ ሰውነቱን አደራ አስጠበቀ ወደ መኰንኑም ወጥቶ ክርስቲያን እንደ ሆነ ታመነ፤ ያንጊዜም ከከባዶች እንጨቶች ጋራ የኋሊት አሥረው ከረኃብና ከጽምዕ ጋራ ከፀሐይ ውስጥ ጣሉት፤ መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ጌታችን ተገለጠለት፤ ሰላምታም ሰጠው ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግም ቃል ኪዳን ሰጠው። ❖ ከዚህ በኋላም መኰንኑ ራሱን እንዲቆርጡት አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ራሱ እኔ ክርስቲያን ነኝ እያለች ሦስት ጊዜ በተራራው ላይ በረረች ሃምሳ ምዕራፍ ያህልም ሒዳ ከባሕር ወደቀች፤ ከዚህም በኋላ ሆዱን ሰንጥቀው ባሩድና ሙጫ ዘይትን መልተው ከእሳት ውስጥ ጣሉት፤ እሳቱ ግን ምንም አልነካውም ከዚህም በኋላ በየጥቂቱ ከትፈው በእንቅብ አድርገው ከባሕር ውስጥ ጣሉት፤ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ከራሱ ጋራ አንድ ሆኖ እንደ ቀድሞው እስና በሚባል አገር በባሕሩ ወደብ ታየ ምእመናንም ወስደው በታላቅ ክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሰማዕት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።   📌 ግንቦት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ሠለስቱ ደቂቅ ቅዱሳን (አናንያ: አዛርያና ሚሳኤል) 2. ቅዱስ አብርሃም ጸራቢ (ሰማዕት) 3. አባ ሚካኤል ገዳማዊ 4. አባ ይስሐቅ ግብጻዊ 📌 ወርሐዊ በዓላት 1. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3. ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ 4. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 5. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 6. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 7. ቅዱስ ዕፀ መስቀል
140Loading...
31
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"          📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ                    ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም      🛎  ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲            አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥር በዚች ቀን የከበሩ ጻድቃን ሠለስቱ ደቂቅ አናንያ አዛርያ ሚሳኤል የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው። ❖ እሊህም ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም ልጆቹ ናቸው ዳንኤልም የእኅታቸው ልጅ ነው በምርኮ ጊዜም ከእስራኤል ልጆች ጋራ ተማርከው ወደ ባቢሎን ወረዱ፤ ከእስራኤል ልጆች ምርኮ ውስጥ በመብልና በመጠጥ እያስተማረ አሳድጎ በሠራዊቱ መካከል ጭፍሮቹ ያደርጋቸው ዘንድ ነውር ነቀፋ የሌለባቸውን ወጣቶች ንጉሥ መረጠ፤ እሊህም ከተመረጡት ውስጥ የተቆጠሩ ሆኑ የእኅታቸው ልጅ ዳንኤልም፤ ምግባቸውን በሚሰጡአቸው ጊዜ አረማውያን ከአረዱአቸው ውስጥ መብላትን አልወደዱም ከንጉሥ ማዕድም ከሚመጣ ከሥጋው እንዳያበላቸውና እንዳያጠጣቸው አለቃውን ለመኑት። ❖ እግዚአብሔርም በባለሟሎች አለቃ ፊት ቸርነቱን አደረገላቸው፤ የባለሟሎች አለቃም ንጉሡ ጌታዬን እፈራዋለሁ የምትበሉትንና የምትጠጡትን ምግባችሁን ስለ አዘዘ ከባልንጀሮቻችሁ እናንተን ከስታችሁ ቢያያችሁ ንጉሥ ራሴን ይቀጣኛል አላቸው፤ በእነርሱ ላይ የተሾመ አሚሳድን እንዲህ አሉት እኛን ባሮችህን ዐሥር ቀን ፈትነን ከምድር ዘር ሽምብራን ይስጡን እንበላ ዘንድ ውኃንም እንጠጣ ዘንድ፤ ቃላቸውንም ሰምቶ ዐሥር ቀን ፈተናቸው ዐሥር ቀንም ከአለፈ በኋላ የንጉሡን ማዕድ ከሚመገቡ ከእነዚያ ልጆች ይልቅ ሰውነታቸው ወፍሮ መልካቸውም አምሮ ታየ። ❖ ከዚህ በኋላ አሚሳድ የሚበሉትን ምግብ የሚጠጡትን ወይን እየወሰደ ለአራቱ ሁሉ ልጆች ሽምብራ ይሰጣቸው ነበር፤ እግዚአብሔርም ዕውቀትንና ጥበብን መጻሕፍትን በማንበብ ሁሉ ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ያዘዘው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ወደርሱ አመጡአቸው የባለሟሎችም አለቃ ወደ ንጉሡ ወደ ናቡከደነፆር አገባቸው። ❖ ንጉሡም ጠየቃቸው በሰው ሁሉ ዘንድ እንደ አናንያና እንደ ዳንኤል እንደ ሚሳኤልና እንደ አዛርያ ያለ አልተገኘም በንጉሡም ፊት ቆሙ፤ ንጉሡም የፈለገውን የምክርና የጥበብን ነገር ሁሉ በግዛቱ ካሉ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሰዎች ሁሉ ይልቅ በነሳቸው ዘንድ ዐሥር እጥፍ አገኘ፤ ንጉሡም እጅግ ወደዳቸው በባቢሎን አገር ሁሉ ላይ ገዢዎች አድርጎ ሾማቸው። ❖ ንጉሥም ጣዖትን ከወርቅ ባሠራ ጊዜ ሰዎችን ሁሉ እንዲሰግዱለት አዘዛቸው፤ ሦስቱ ልጆችም ለዚያ ጣዖት ባልሰገዱ ጊዜ የሚቀኑባቸው ወደ ንጉሥ ነገር ሠርተው በንጉሥ ፊት አቀረቧቸው ስለ አልሰገዱለትም ጠየቃቸው እነርሱም እኛስ ለሠራኸው ለወርቅ ምስል አንሰግድም አሉት፤ ንጉሥም ተቆጥቶ ከምትነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ። ❖ እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ የእሳቱን ነበልባል አጠፋው በጥዋት ጊዜ እንደሚቀዘቅዝ በእሊህ በሦስቱ ልጆች ዘንድ እንደ ጥዋት ውኃ ቀዝቃዛ አደረገው፤ ከዚያም የእሳቱ ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ከፍ ከፍ ብሎ በውጪ ያሉትን አቃጠላቸው እሊህን ሠለስቱ ደቂቅን ግን ምንም አልነካቸውም፤ ይህን ድንቅ ሥራ አይቶ በፊታቸው ሰገደ የሰማይና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔርንም አመነ ለእሊህም ልጆች ሹመታቸውን ከፍ ከፍ አድርጎ ክብርን ጨመረላቸው። ❖ ከዚህም ዓለም የሚወጡበት ጊዜ ሲደርስ በበዐታቸው እየጸለዩ ሳሉ ሰግደው ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ፤ ወዲያውኑ ታላቅ ንውጽውጽታ በባቢሎን አገር ሆነ፤ ንጉሡም ፈርቶ ስለ ምን ይህ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ብሎ ዳንኤልን ጠየቀው ነቢይ ዳንኤልም ይህ ሦስቱ ልጆች ስለ አረፉ ከዓለም ለመውጣታቸው ምልክት ነው ብሎ ነገረው። ❖ ንጉሡም ወደርሳቸው ደርሶ ታላቅ ኀዘንን አዘነ ከዝሆን ጥርስም ሦስት ሣጥኖችን እንዲሠሩላቸው በሐር በግምጃ ልብሶች ገንዘው ቅዱሳኑን በሣጥኑ ውስጥ እንዲያኖሩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዛቸውም አደረጉ፤ ሁለተኛም የወርቅ ሣጥን ሠርተው እርሱ በሚሞት ጊዜ ሥጋውን በውስጡ አድርገው በከበሩ ሠለስቱ ደቂቅ መካከል እንዲያኖሩት አዘዘ እንዲሁም አደረጉለት። ❖ ከዚህ በኋላ የከበረ አባት አባ ቴዎፍሎስ በእስክንድርያ ሊቀ ጵጵስና በተሾመበት ወራት በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ሠራ ሥጋቸውን ወደዚያች ቤተ ክርስቲያን ሊያመጣ ወዶ ሥጋቸውን እንዲያመጣለት አባ ዮሐንስ ሐፂርን ወደ እርሳቸው ሀገረ ባቢሎን ላከው፤ ወደ ባቢሎን ሀገርም በደረሰ ጊዜ ወንዞቿን አየ በውስጧ ከቶ ሰው አልነበረም የወርቁ ምስልም በዚያ አለ፤ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም የቅዱሳን ሥጋ ወደአለበት አደረሰው የንጉሡም ሥጋ በመካከላቸው ነበረ፤ ሥጋቸው በአለበትም ቦታ ሰገደ፤ እንዲህም ብሎ በማልቀስ ጸለየ የከበራችሁ አባቶቼ ሆይ የከበረ አባት ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ በስማችሁ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ሥጋችሁን በውስጧ ሊያኖር እኔን ልኮኛልና ከእኔ ጋራ ትሔዱ ዘንድ ፈቃዳችሁ ይሁን። ❖ በዚያን ጊዜ እንዲህ የሚል ቃል ከሥጋቸው ወጣ ለሃይማኖት አባት ለአባ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው የድካምህን ዋጋ እግዚአብሔር ይስጥህ ነገር ግን እኛን እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ሥጋዎቻችን ከንጉሡ ሥጋ እንዳይለዩ እግዚአብሔር ስለአዘዘን ከዚህ አንወጣም ድካሙንም ከንቱ አናደርግም፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትከብርበት ዕለት በሌሊት መብራቶችን ይሰቅሉ ዘንድ እንዲአዝ በውስጣቸውም ዘይትና ፈትል እንዲያደርጉ በእሳት ግን አይለኩሱአቸው፤ እኛም ከዚያ ደርሰን በእኛ የእግዚአብሔር ኃይል በዚያ ይገለጣል ብለህ ንገረው አሉት። ❖ አባ ዮሐንስ ሐፂርም ተመልሶ እንደነገሩት እንዴትም እንዳዘዙት ሁሉንም ለአባ ቴዎፍሎስ ነገረው እርሱም ሠለስቱ ደቂቅ እንዳዘዙ አደረገ፤ በዚችም በግንቦት ወር በዐሥር ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትከብርበት ሌሊት የከበሩ ሠለስቱ ደቂቅ ተገለጡ ያለ እሳትም መብራቶችን አበሩ ሊቀ ጳጳሳቱና ለዚህ ጸጋ የታደሉ ሁሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ እርከን ላይ ሲዞሩ ሠለስቱ ደቂቅን አዩአቸው በየአይነቱ በሆነ ደዌ የታመሙ ብዙ በሽተኞችም ከቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ መገለጥ የተነሣ ያን ጊዜ ተፈወሱ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። 🛎 በዚችም ቀን አብርሃም ፀራቢ በሰማዕትነት አረፈ ይህም ቅዱስ የሰማዕት ቴዎድሮስ ገዳም ተብላ ከምትጠራ ከመርቅያስ አገር ሰዎች ነው፤ ወላጅ እናቱም የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ሃይማኖት እንዲማር ለመምህር ሰጠችው፤ ጌታችንም ዐይነ ልቡናውን ገልጦለት ትምህርቱን ሁሉ የቤተ ክርስቲያንንም ሕግ ተማረ። ❖ ከዚህም በኋላ መጾም መጸለይና መስገድ ጀመረ ዘጠኝ ዓመትም በሆነው ጊዜ ከደንጊያ የሚሠራ የውኃ መሔጃ መጥረብን ተማረ በዚህም ብዙ ገንዘብ አከማቸ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች የሚመጸውት ሆነ፤ በአንዲት ዕለትም በሌሊት ሲጸልይ የዚችን ዓለምና በውስጧ ያለው ሁሉ ኃላፊ መሆኑን አሰበ፤ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ ስም ምስክር ሆኖ መሞትን ወደደ።
180Loading...
32
ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል። በራሱ ኃይል ስልጣን። የእግዚአብሔር ሰለም ከእናተ ጋር ይሁን። የጌታችን የመደኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞቱ በራሱ መሥዋዕትነት እንጂ በኃይል ወይም በግዳጅ አለመሆኑ ትንሣኤው አረጋግጧል።የክርስቶስን ትንሣኤ ማመን ማለት በእርሱ ፍቅር በእርሱ ምሥዋዕት ሆኖ መቅረብና በእርሱ የሰው ልጆችን ከሞት ባርነት ነጻ ማውጣት ማመን ነው። ከዚህ ተጨማሪ በእርሱ ኃይል አስቀድሞ ስለራሱ በተናገራቸው ቃላትና ከእግዚአብሔር ጋር አንድ በመሆኑ ማመን ነው። ይህ ኃይል በሥጋው ሞቶ በመለኮቱ ሕያው የሆነው የአንድዬ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ነው። ይህ ኃይል ለዮሐንስ በራዕዩ እንደሚከተለው የተነገረው የአንድዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ነው።".....አትፍራ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እንሆም ከዘላለም አስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ የሞተና የሲዖል መክፈቻ አለኝ።"ራእ 1:8። ስለዚህ ኃይል አንድዬ ሐዋርያውን ቅዱስ ጴጥሮስን በሐምሣኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደባቸው ጊዜ ሰክረዋል የሚል ቃል ከአይሁድ በተነገረባቸው ጊዜ እንዲህ ብሎ አናግሮታል"እግዚአብሔር ግን የሞትና ጣር አጥፍቶ አስነሰው ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።" ሐዋ 2:24። ዳዊትንም ትንቢት አናግሮታል"...ነፍሴን በሲዖል አትተዋትምና ቅዱስ መበስበስን ያይ ዘንድ አተሰጠውም። " መዝ 15: 8-11።ቅዱስ ጳውሎስም ፦ "....ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና። " ሮሜ 6 :9። ስለዚህ የጌታችን ትንሣኤ የሚያስተምረን ወደፊት የማይምት ሞት የማይገዛው አምላካችን ነው። አለም ያላት አምላክ ግን "የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ" 2ኛ ቆሮ 4:4 ተብሎ እንደተነገረ አለም ያላት አምላክ ወደውጭ የሚጣል እና የሚፈረድበት ነው። ዮሐ 12:31-32 ራእ 20:10። መልካም ጊዜ።
250Loading...
33
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን           በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም      🛎 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፱       አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዘጠኝ በዚች ቀን የጻድቅ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ቅድስት ዕሌኒ አረፈች። ❖ ይቺም ቅድስት በፊት የአንድ ነጋዴ ሰው ሚስት ነበረች እርሱም በነገረ ሠሪ ንጽሕት ሁና ሳለች ወደ ባሕር ጣላት፤ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ፈቃድም ሮሐ ከሚባል አገር ደርሳ የበራንጥያ ንጉሥ ቊንስጣ አገኛት፤ ውበቷንና ደም ግባቷንም አይቶ አገባት ለክርስቲያን ነገሥታት መጀመሪያቸው የሆነውን ቈስጠንጢኖስን ወለደችው ምግባርንና ሃይማኖትን በማስተማር በመልካም አሳደገችው። ❖ ልጇም በነገሠ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ሒደሽ የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን መስቀል ግለጪ የከበሩ ቦታዎችንም ሥሪ የሚላትን በሕልሟ አይታ እንዴት እንዳየች ይህን ለልጇ ነገረችው እርሱም ከብዙ ሠራዊት ጋራ ሰደዳት። ❖ በደረሰችም ጊዜ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ጌታችን መስቀል መረመረች አዳኝ የሆነ መስቀሉንም ሁለቱ ወንበዴዎች ከተሰቀሉባቸው መስቀሎች ጋራ አገኘችው፤ የክብር ባለቤት የክርስቶስ መስቀል የትኛው እንደሆነ ታውቅ ዘንድ በወደደች ጊዜ ከራሱ በላይ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል በእንጨት የተቀረጸበት ጽሑፍ ያለው እንደሆነ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ቅዱስ መቃርስ ነገራት። ❖ ከዚህ በኋላ ከእርሱ ምልክት ታይ ዘንድ ፈለገች የሞተ ሰውም አግኝታ መስቀሎችን በበድኑ ላይ አኖረች አልተነሣም፤ ከዚህ በኋላ ሦስተኛውን መስቀል በላዩ አኖረች፤ ያን ጊዜ ምውት ተነሣ ሃይማኖቷም ጸና ደስታዋም በዛ። ❖ ከዚህ በኋላም ዜናቸው በመስከረም ወር በዐሥራ ሰባት የተጻፈ በከበሩ ቦታዎች ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን ትሠራ ዘንድ ጀመረች፤ ለአባ መቃርስም በከበሩ ቦታዎች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲሠራ ብዙ ገንዘብ ሰጠችው። ❖ ከዚህ በኋላ ወደ ልጇ ተመልሳ የሆነውን ሁሉ ነገረችው የከበረ መስቀል በመገኘቱ እጅግ ደስ አለው፤ ይቺም ቅድስት በጎ ገድሏን ከፈጸመችና እግዚአብሔርንም ከአገለገለች በኋላ ስለ ካህናትም ልብስና ቀለብ ለአብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት ብዙ ጉልቶችና ርስቶችን ለድኆችና ለምስኪኖችም እንዲሁ ከሠራችና ከተከለች በኋላ በሰላም አረፈች መላ ዕድሜዋም ሰማንያ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                    አርኬ ✍️ ሰላም ለዕሌኒ ውስተ ምድረ ሕይወት ኤልዳ። ምክረ መንፈስ ቅዱስ አመ ወስዳ። ለሐይወ በድን በለኪፈ መስቀል ቅድመ ዐውዳ። እምአይቴ አንተ ትቤሎ ወእምአይ እንግዳ። ዘተረከብከ ግዱፈ በበዳ። በዚችም ዕለት የበይደርና የስልዋኖስ መታሰቢያቸው ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። 📌 ግንቦት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅድስት እሌኒ ንግሥት 2. ቅዱስ ስልዋኖስ 📌 ግንቦት 9 ቀን የሚከበሩ ወርሐዊ በዓላት 1. አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት) 2. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ) 3. "318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ) 6. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)
190Loading...
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #ግንቦት ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን #ለሀገረ_ቶና ለከበረ ልታስተው የመጣችውን ሴት በማስተማር ለቅድስና ላበቃ #ለአባ_አሞንዮስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር ከምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰብት፦#አባ_አሞንዮስ ለቅድስና ካበቃት #ከቅድስት_ሳድዥ ከመታሰቢያዋ፣ #ከቅዱስ_አሞኒ ረድእ #አባ_ዳርማ ከዕረፍት፣ #ከአባ_ኄሮዳና #ከአባ_ዘካርያስ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉበት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_አሞንዮስ፦ ይህም ቅዱስ ጐልማሳ ሁኖ ሳለ አባ እንጦንዮስ ወደ ምንኵስና ሲጠራው ራእይን አየ። በነቃም ጊዜ ተነሥቶ ወዲያውኑ ወደ አባ ኤስድሮስ ሔደ ከእርሱም አስኬማን ለብሶ እያገለገለውም በእርሱ ዘንድ ኖረ። ❤ ከዚህ በኋላ ወደ ደብረ ቶና ተመልሶ ለራሱ በዓትን ሠራ በታላቅ ገድልም ተጠምዶ በቀንና በሌሊትም ተጋደለ። ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ በሴት መነኵሲት አምሳል ወደርሱ መጣ የበዓቱን ደጃፍ በአንኳኳ ጊዜ ከፈተለትና ገባ "ቅዱሱም ተነሥተን እንጸልይ" አለው ያን ጊዜ ተንኰሉን ገለጠ መልኩም እንደ እሳት ላቦት ሆነ ቅዱሱንም "እኔ ታላቅ ጦርነት አመጣብሃለሁ" አለው። ❤ ከዚህም በኋላ መልኳ ውብ ወደ ሆነ ወደ አንዲት ወጣት ሴት ሰይጣን ሒዶ አነሣሣት። ቅዱስ አሞንዮስን እርሷ ጋራ በኃጢአት ልትጥለው ቀጭን ልብሶችን ለብሳ ወደ ርሱ በምሽት ጊዜ ደረሰች። እንዲህም እያለች ደጃፉን አንኳኳች "እኔ መጻተኛ ሴት ነኝ መንገድንም ስቼ በምሽት ጊዜ ከዚህ ደረስኩ አራዊትም እንዳይበሉኝ በውጭ አትተወኝ እግዚአብሔርም ስለ እኔ ደም እንዳይመራመርህ" አለችው። በከፈተላትም ጊዜ የሰይጣን ማጥመጃው እንደ ሆነች የላካትም እርሱ እንደሆነ አወቀ በአምላካውያት መጻሕፍት ቃልም ገሠጻት ለኃጥአን ስለ ተዘጋጀ የሲዖል እሳትም አስገነዘባት ሁለተኛም ለጻድቃን ስለ ተዘጋጀ ፍጹም ተድላ ደስታ ነገራት። ያን ጊዜም የሚላትን ታስተውለው ዘንድ እግዚአብሔር ልቧን ከፈተላት። መልካሙንም ልብስ ከላይዋ አውጥታ ጣለች ከእግሮቹ በታችም ሰግደች ነፍሷንም ያድን ዘንድ በማልቀስ ለመነችው። የጠጉር ልብስም አለበሳት ራስዋንም ተላጭታ በገድል ሁሉ በብዙ ትሩፋትም ተጠመደች በቀንም በሌሊትም ዐሥራ ሁለት ጊዜ የምትጸልይ ሁናለችና በየሁለትና በየሦስት ቀንም ትጾማለች። ❤ ሰይጣንም በአፈረ ጊዜ በመነኵሴ ተመስሎ በየአንዳንዱ ገዳም ሁሉ በመግባት እያለቀሰና እያዘነ እንዲህ አላቸው "በአባ አሞንዮስ ቤት ሴት አለችና እርሱ ታላቅ ገድል በኋላ የአንዲትን ሴት ፍቅር ወዶአልና እርሷም በእርሱ ዘንድ በበዓቱ ውስጥ ትኖራለች እነህ መነኰሳትን አሳፈራቸው እስኬማውንም አጐሳቈለ"። ❤ የመላእክት አምሳል የሆነ ጻድቅ አባ ዕብሎ ያን ጊዜ ተነሣ አባ ዮሴፍንና አባ ቦሂንም ከእሱ ጋራ ወሰዳቸው። ወደ ቅዱስ አሞንዮስ ገዳም ደብረ ቶና ደረሱ ደጃፋንም በአንኳኩ ጊዜ ያቺ ሴት ወደ እርሳቸው ወጣች እርስ በርሳቸውም "ያ መነኵሴ የነገረን እውነት ነው ተባባሉ። የከበረ አሞንዮስም ሳድዥ ብሎ ስም አውጥቶላታል ይህም የዋሂት ማለት ነው። ገብተውም ጸሎት አድርገው የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ እስከ ምሽት ተቀመጡ። አባ አሞንዮስም "አምበሻ እየጋገረችልን ነውና ተነሡ ሳድዥን እንያት" አላቸው። በገቡም ጊዜ በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ቁማ እጆቿም ወደ ሰማይ ተዘርግተው ስትጸልይ አገኙዋት። አይተውም ስለዚህ ድንቅ ሥራ እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርም አመሰገኑ። ❤ ከዚህ በኋላም አቅርባላቸው በሉ። በዚያችም ሌሊት መልአክ ስለ አባ አሞንዮስና ስለ ሳድዥ ገድላቸውን ለአባ ዕብሎ ነገረው "ወደዚህም ዛሬ ያደረሳችሁ እግዚአብሔር ነው የሳድዥን ዕረፍት እንድታዩ" አላቸው። ሦስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ የሚያስጨንቅ የሆድ ዝማ ታመመች በእግዚአብሔር ፊት አንዲት ስግደትን ሰገደችና በዚያም ነፍሷን ሰጠች መልካም አገናነዝም ገንዘው ቀበሩዋት። ❤ አባ አሞንዮስም ትሩፋቷን ሊነግራቸው ጀመረ እርሷ በእርሱ ዘንድ ዐሥራ ስምንት ዓመት ስትኖር ከቶ ፊቷን እንዳላያት ምግባቸውም አምባሻና ጨው እንደሆነ። ከጥቂ ቀን በኋላም አባ አሞንዮስ ግንቦት 20 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በአባ አሞንዮስና በቅድስት ሳድዥ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 20 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #"ሰላም_ሰላም_ለረዳኢተ_አሞንዮስ ሳድዥ። ዝ ብሂል የዋሂተ ግዕዝ። በሑረታቲሃ አዳም ወበምግባራ ሐዋዝ። ኢውዕየት ቀዊማ ከመ ዘመጥልል ውኂዝ። ማዕከለ ውዑይ ወርሱን ማሕበዝ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_20።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዝርዎሙ ለአሕዛብ እለ ይፈቅዱ ቀትለ። ይምጽኡ ተናብልት እምግብፅ። ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር"። መዝ 67፥30-31 ወይም መዝ 74፥2-3፡፡ የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 13፥1-11፣ 1ኛ ጼጥ 2፥11-20 እና የሐዋ ሥራ 13፥44-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ16፥24-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ቅዱስ ካሌብ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
Hammasini ko'rsatish...
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለካሌብ ወለሣህል ኄራን መዋዕያን ነገሥት፤ #እለ_ሃይማኖቶሙ_ምሉዕ ከመ ደመና ክረምት፤ #ለመንገለ_እግዚአብሔር እለ አርአዩ ቅንአተ፤ እለ ዓቀቡ በንጽሕ መንግሥተ፤ ዘተወፈዩ ጽድቀ #ወቅድሳተ_ወሃይማኖተ_በመንፈስ_ቅዱስ እለ አፍረዩ፤ #ለእግዚአብሔር ርእሶሙ እለ አቅነዩ"። ትርጉም፦ #ለእግዚአብሔር_ራሳቸውን_ያስገዙ፤ #በመንፈስ_ቅዱስ_ፍሬን_ያፈሩ፤ እውነትን፣ ክብርንና #ሃይማኖትን_የተቀበሉ፤ መንግሥትን በንጽሕና የጠበቁ፤ #የእግዚአብሔር ወደሚኾን አምልኮት ቅንአትን ያሳዩ፤ #ሃይማኖታቸው_እንደ_ክረምት_ደመና_ምሉእ የኾኑ ቸሮችና ድል ነሾች ለኾኑ ነገሥታት ለሣህልና #ለቅዱስ_ካሌብ_ሰላምታ_ይገባል። #ሊቁ አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ። ምንጭ ፦ ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ)
Hammasini ko'rsatish...
ድጓ ዘጻድቃን ነገሥት አቡን በ፮ አርኅዉ ሊተ አናቅጸ ጽድቅ እባዕ ውስቴቶን ወእግነይ ለእግዚአብሔር ዛ አንቀጽ እንተ እግዚአብሔር ጻድቃን በክብር የዋሃን በክብር ራትዓን በክብር በትፍሥሕት ይበውዑ ውስቴታ በኃሤት። ገጽ ፻፲ (110) ትርጓሜ ፦   የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤  ወደ እነርሱ    ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግን ዘንድ ፤ ይህችም በር የእግዚአብሔር ደጅ ናት ፤ ጻድቃን በክብር ፣ የዋሃን በክብር ፣  ቅኖችም በክብር     በደስታ  ወደርሷ ይገባሉ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ
Hammasini ko'rsatish...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"          📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ                    ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም           📌   ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፳        አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ በዚች ቀን የከበረ ጻድቅ የኢትዮጵያ ንጉሥ ካሌብ አረፈ። ❖ ይህ ቅዱስ እግዚአብሔርን የሚፈራውና በፍጹም ልቡ የሚወደው ሃይማኖቱም የቀና ነው፤ በናግራን አገር ያሉ ክርስቲያኖችን አይሁድ እንደሚገድሏቸው በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ መንፈሳዊ ቅናትንም ቀና። ❖ ከዚህም በኋላ ተነሣ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብቶ በመሠዊያው ፊት ቆመ ዐይኖቹንም ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ ብሎ ጸለየ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ሆይ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠርህ መላእክት ሁሉ አእላፈ አእላፋት አንተን የሚያመሰግኑህ ለአንተም የሚገዙ ዐይኖቻቸው ብዙ የሆነ ኪሩቤል ክንፎቻቸው ስድስት የሆነ ሱራፌልም ጽኑዕ ክቡር ልዩ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር በቅዱሳን የሚመሰገን እያሉ ያለማቋረጥ የሚያመሰግኑህ፣ ብርሃንን እንደ ልብስ የሚጐናጸፍ የክብር ባለቤት ለሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱ እግዚአብሔር ሆይ የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ የጠፉ በጎችን ይመልሳቸው ዘንድ ልጅህን ይኸውም ቃልህ ነው በፈቃድህ የላክኸው አንተ ነህ። ❖ ተናጋሪ በግ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳትለይ ከሰማይ የወረድክና ስለ እኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆንክ ከጨለማም ከድንቁርናም አውጥተህ ወደ ብርሃን ወደ ሕይወት ወደ ዕውቀት የመራኸን፤ አሁንም ከሀዲ ወንጀለኛ ፊንሐስ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች እንደ በጎች በማረድ እንደ ገደላቸው በእሳትም አቃጥሎ የወገኖችህንና የርስትህን ልጆች እንዳጠፋቸው እይ። ❖ እነሆ አብ ሆይ እኔ አመንሁብህ በአንድ ልጅህም በሕያው ቅዱስ መንፈስህም በመሠዊያህ ክብርም ተማፅኛለሁ በሃይማኖትህም ጸንቼአለሁ እነሆ ስለ አምልኮትህና ስለ ምእመናን ወንድሞቼ ስለ ቀናሁ በአንድ ልጅህ መስቀል ጠላቶችህን ልዋጋቸው እወጣለሁና ከአለኝታዬ እንዳታሳፍረኝ የማያውቁህም አምላካቸው ወዴት ነው እንዳይሉ። ❖ ስለ በደሌና ስለ ኃጢአቴም ጸሎቴን የማትሰማ ልመናዬንም ንቀህ የምትተው ከሆነ በዚሁ ቦታ ብትገድለኝ ይሻለኛል፤ አቤቱ መሐሪ ይቅር ባይ ርኅሩህ ርስትህ የሆኑ ምእመናንን በከሀድያን ጠላቶችህ እጅ አሳልፈህ አትስጥ። እኛ ወገኖችህና የርስትህ መንጋዎች ስለሆን ለአንተም ምስጋና እናቀርባለን ምስጋና ገንዘብህ ነውና ለዘላለሙ። ❖ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ካሌብ ከሀገረ መንግሥቱ ወጥቶ ሔደ የናግራንን ሀገር ያጠፉአት አይሁድን ገደላቸው ብዙ ተአምራትም አድርጎ ስለ አደረገለት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ሀገረ መንግሥቱ በታላቅ ክብር በታላቅም ደስታ ተመለሰ፤ ለእግዚአብሔር ምን ዋጋ እከፍለዋለሁ ለጌትነቱና ፍጹም ለሆነ ገናናነቱ መባ አድርጌ ነፍሴንና ሥጋዬን ከማቀርብለት በቀር አለ። ❖ ከዚህም በኋላ ይህን ዓለም ንቆ መንግሥቱንም ትቶ ወጣ ደጋጎች መነኰሳት ወደሚኖሩበት ወደ አባ ጰንጠሌዎን በተራራ ላይ ወደ አለ ገዳም እስከ ደረሰ በእግሩ ሔደ፤ ወደ ዋሻ ውስጥም ገብቶ ሰውም እንዳያየው የዋሻውን በር ዘግቶ በዚያ ውስጥ ኖረ ከዚያችም ወጥቶ ዳግመኛ ዓለምን እንዳያይ ማለ። ❖ ከእርሱ ጋራም ያገባው ዕቃ የለም ከምንጣፍ ከሸክላ ጽዋ ከለበሳት የምንኲስና ልብስ በቀር ምግቡም አምባሻና ጨው የሚጠጣውም ውኃ ነው፤ የክብር ባለቤት ከሆነ ከእግዚአብሔር ቃል መቃብር መስኮት ላይ ይሰቅልለት ዘንድ የኢየሩሳሌሙን ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስን እየለመነው ዋጋው ብዙ የሆነ የነገሠበትን ዘውድ ላከ፤ ወደ ዋሻውም ከገባ በኋላ ከማንም ጋራ አልተነጋገረም እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ በፍቅር አንድነት አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                        ✍️  በዚች ዕለት የሀገረ ቶና የከበረ አባ አሞንዮስ አረፈ፤ ይህም ቅዱስ ጎልማሳ ሁኖ ሳለ አባ እንጦንዮስ ወደ ምንኩስና ሲጠራው ራእይን አየ፤ በነቃም ጊዜ ተነሥቶ ወዲያውኑ ወደ አባ ኤስድሮስ ሔደ ከእርሱም አስኬማን ለብሶ እያገለገለውም በእርሱ ዘንድ ኖረ። ✍️  በዚችም ቀን ከአባቶች መምህራን ዐሥራ ስድስተኛ የሆነ በደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት ሆኖ የተሾመ የከበረ አባት አባ ዘትረ ወንጌል አረፈ። ❖ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ እንደ መላእክት ንጽሕናን የለበሰ ትሕትናን ቅንነትን የሚወድ ነበረ። ❖ የምንኵስናንም ልብስ ከለበሰ በኋላ መልካም ገድልን ተጋደለ በክርስቶስ መንጋ ላይም ጠባቂ ሆኖ ተሾመ ከዚያም በኋላ በበጎ እርጅና አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
📌 ግንቦት 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አፄ ካሌብ (መናኙ ንጉሠ ኢትዮዽያ) 2.ቅዱስ አሞንዮስ ገዳማዊ (ታላቁ አሞኒ ዘቶና) 3.ቅድስት ሳድዥ የዋሂት 4.አባ ሖር ጻድቅ 5.አባ ዳርማ ገዳማዊ 6.ቅዱስ ዘካርያስ አንጾኪያዊ 7.አባ ዘትረ ወንጌል ዘደብረ ሊባኖስ 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት) 2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር 3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
Hammasini ko'rsatish...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"          📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ክርስቶስ ተንሥአ እም እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም    🛎   ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፱              አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን ከአባ መቃርስ ገዳም ቅዱስ አባት ቀሲስ ይስሐቅ አረፈ።     ❖ ይህም አባት ከምሥር ከታናናሽ ቦታዎች ከአንዲት ቦታ ነው ወላጆቹም ድኆች ሲሆኑ ግን በበጎ ስራ ባለጸጎች ናቸው፤ አረጋውያን መነኰሳትም የእጅ ስራቸውን ሊሸጡ ወደ ምሥር በሄዱ ጊዜ ተከትሏቸው ወደ አስቄጥስ ገዳም መጥቶ ሲአገለግላቸው ኖረ፤ በቀንበራቸውም ተጠምዶ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ በዘመኑም ሁሉ ከቶ ምንም ጥሪት አላደረገም፤ እንደ አባቶቻችን ሁለት ልብሶችን ለምን አልገዛህም ሲሉት እርሱም እኔ እስከ ዛሬ ሕዝባዊ ነኝ በዓለም ሳለሁም ሁለት ልብስ የለኝም ነበር ብሎ ይመልስላቸዋል። ❖ ሁለተኛም አባቶቻችንም እኮ ሰሌንና ማቅ ይለብሳሉ ለእኛም አንድ ልብስ ይገባናል ይህ አይበቃንምን አላቸው፤ ሁልጊዜ የሚያለቅስ ሆነ ለምን ታለቅሳለህ ብለው በጠየቁት ጊዜ ወላጆቼ ሙተውብኝ ድኃ አደግ አድርገውኛልና ይላቸዋል፤ ከምግቡም የማዕጠንት አመድ ጨምሮ እየበላ ብዙ ዘመናት ኖረ። ❖ ከዚህ በኋላ ጭንቅ በሆነ ደዌ ተይዞ በታመመ ጊዜ ከወንድሞች አንዱ ምግብ ሰርቶ አመጣለት፤ እርሱም ከቶ አልቀመሰም ያም ወንድም ይህ ጥሩ ምግብ ነው ለበሽታህም መድኃኒትነት አለውና ብላ ብሎ ብዙ ለመነው፤ እርሱም ወንድሜ ሆይ እመነኝ እኔ በዚህ ደዌ ውስጥ ሠላሳ ዓመት እኖር ዘንድ እወዳለሁ ብሎ መለሰለት፤ በዕድሜውም በሸመገለ ጊዜ ትሩፋቱና ጽድቁም በበዛ ጊዜ ቅስና ይሾሙት ዘንድ አረጋውያን ተሰብስበው ተማከሩ። ❖ እርሱም ከእርሳቸው ሸሽቶ ከተዘራ ማሳ ውስጥ ገብቶ ተሠወረ፤ እርሱንም እየፈለጉ ዞሩት አላገኙትም ያቺንም ማሳ አልፈው ከዳርዋ ተቀመጡ ጥቂት ሊያርፉ፤ ከእርሳቸውም ጋር አህያ ነበረ ወደ ማሳውም ሩጦ ገብቶ ይህ አባት በተሸሸገበት ቦታ ቆመ፤ አህያውን ሊያስወጡትም በገቡ ጊዜ ያንን አባት አገኙት፤ ደግሞ እንዳይሸሽ ሊአሥሩት ፈለጉ አሁንስ ዐውቄዋለሁ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አላቸው ከዚያም አብሮአቸው ሒዶ ቅስና ሾሙት። ❖ ከዚህ በኋላም ተጋድሎውንና ለአረጋውያን መታዘዙን ጨመረ ወጣቶችንም በጎ ሥራ ያስተምራቸዋል ሰምታችሁ የምትታዘዙ ሁኑ ከትሩፋት ሁሉ ይህ ይበልጣልና አላቸው፤ የሚያርፍበትም ጊዜ ሲደርስ ከእርሱ በኋላ የሚሠሩትን እንዲአስተምራቸው በዚያ ገዳም ያሉ ጎልማሶች በጠየቁት ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ በገዳሙ ውስጥ ጸንታችሁ እንድትኖሩ እኔ ስሠራ ስታዩኝ እንደነበረ እናንተም እንዲሁ በፈቃዳችሁ ሥሩ፤ እኛ አባቶቻችን በአረፉ ጊዜ አዝነን አልቅሰን ነበር እንደሚሠሩትም በሠራን ጊዜ ከእነርሱ በኋላ ተጽናንተን በገዳም የምንኖር ሆን። ይህንንም እያለ በፍቅር በሰላም አረፈ የሕይወት አክሊልንም አገኘ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከቱም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። 📌 ❖ በዚችም ቀን ኃይለኛ ተጋዳይ ቅዱስ ኤስድሮስ በሰማዕትነት አረፈ፤ ይህም ቅዱስ ከእስክንድርያ አገር ከከበሩ ከቤተ መንግሥት ወገኖች ውስጥ ነው አባቱም በብዙ ሠራዊት ላይ የተሾመ መኰንን ነው፤ ስሙም በደላዖን ነው የእናቱም ስም ሶፍያ ነው ሁለቱም ከክርስቲያን ወገን ናቸው ይህንንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ ኤስድሮስ ብለው ሰየሙት። ❖ ከብዙ ወራት በኋላም ከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ የሚያደርገውን የኃጢአትና የበደልን ብዛት በአየ ጊዜ እርሱ ከመንግሥት ታላላቆች ውስጥ ስለሆነ ምስፍናውን ትቶ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋራ ገለል አለ፤ ስለ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጻተኞች በመሆን ከዚህ ዐላዊ ንጉሥ ፊት ሸሽተው ሳሙኤል ከሚባል ሰው ዘንድ ተሰባስበው በገዳም ተቀመጡ። 📌 በዚችም ቀን ከቅዱስ ኢስድሮስ ጋራ ስምንት መቶ አምስት ሺህ ሰባት ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ በረከታቸውም ትደረሰን ለዘላለሙ አሜን።                         📌   በዚችም ዕለት የዓለም ብርሃን የሆነ አባ ዮሴፍ አረፈ፤ ይህም ቅዱስ ያዩትና የሰሙት እስቲአድንቁት ድረስ በአባቱ ቤት ሳለ የዚህን ዓለም ጥበብ ሁሉ ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ተረጐመ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾሙት፤ የነፍሱንም ድኅነት እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ብርሃናዊ መልአኩን ሚካኤልን ላከለትና ዮሴፍ ሆይ ይህን ኃላፊውን ዓለም ትወደዋለህን? አስጸያፊ አይደለምን በውስጡም ያለው ሁሉ አለው። ❖ ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ እርሱ የመረጠውን መንገድ ይመራው ዘንድ እግዚአብሔርን እየለመነ ጾምና ጸሎትን ጀመረ ከወለቃ አውራጃም ስሙ አባ ዘካርያስ የሚባል ነበረ እርሱም ለዮሴፍ ዘመዱ የሆነ በጭልታም ዮሴፍን ወስዶ የምንኲስና ልብስ አለበሰው ወደ ትግራይ ምድርም ወሰደውና በዚያ ተግባረ እድ ለምንኲስና ሥራ የሚገባ ጽሕፈትን ስፌትን ተማረ። ❖ ከዚህም በኋላ ወደ በረሀ ዱር ገብተው የእንጨት ፍሬ እየበሉ ከዝኆኖች ከአንበሶችና ከዘንዶዎች እየተፈተኑ በየአይነቱ በሆነ ተጋድሎ በመድከም ኖሩ፤ በጽድቃቸውም ኃይል ብዙ ተአምራትን አደረጉ።
📌 ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 2.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም (የ12ቱ ሐዋርያት መቃብር ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ) 3.አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ (ኢትዮዽያዊ) 5."805,007" ሰማዕታት (በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ) 6,አባ ይህሳቅ ገዳማዊ 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2.አቡነ ስነ ኢየሱስ
Hammasini ko'rsatish...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"                             ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም    📌 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፰       አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ስምንት በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ ከትንሣኤው በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ከአብ የሚሠረጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ ብሎ ተስፋ እንደ ሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። ❖ እናንተም ከአርያም ኃይልን እስከምትለብሱ በኢየሩሳሌም ኑሩ አላቸው፤ ሁለተኛም ያ እውነተኛ መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ ዕውነት ሁሉ ይመራችኋል አላቸው፤ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው እርሱም አለቃቸው የሆነ ጌታችን አጽናኚውን ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ነው ሊልክልን ተስፋ አስደርጎናል የምናሰማውንና የምናደርገውን ልብ ያስደርገን ዘንድ። ❖ ይህንንም ሲነግራቸው እነሆ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ ሰሙ በዓለም ውስጥ እንደርሱ ያለ የማያውቁት ጣፋጭ መዓዛ አሸተቱ፤ የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎችም በየአንዳንዳቸው ላይ ሲወርዱ ታዩ፤ በአዲስ ቋንቋም ተናገሩ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ሊሆን አርባ ቀን ጾሙ፤ ሁለተኛም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በዓለ ኃምሣ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሁነው አብረው ሳሉ፤ ድንገት ከሰማይ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትም ቤት ሁሉ መላው። ❖ የተከፋፈሉ የእሳት ልሳኖችም ታዩአቸው በየአንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተመሉ። በየራሳቸውም በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀምር መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው።ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። ❖ ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ደንግጠው ሁሉም ተሰበሰቡ በየሀገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና፤ ተደንቀውም በድንጋጤ እንዲህ አሉ፤ እነሆ እሊህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን የጳርቴና የሜድ የኤላሜጤም ሰዎች ስንሆን፤ በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም በፍርግያም በጵንፍልያም በግብጽም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊብያ ወረዳዎች የምንኖር በሮሜም የምንቀመጥ አይሁድም ወደ ይሁዲነት የገባን የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች ስንሆን የእግዚአብሔርን ገናናነት በቋንቋችን ሲናገሩ እነሆ እንሰማቸዋለን። ❖ ሁሉም ደንግጠው የሚናገሩትን አጡ፤ እርስ በርሳቸውም እንጃ ይህ ምን ይሆን አሉ ሌሎች ግን እያፌዙባቸው ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል አሉ፤ ጴጥሮስም ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤ የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ። ❖ ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤ ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለው ነው እግዚአብሔር አለ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አሳድራለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ ጐበዛዝቶቻችሁም ራእይን ያያሉ ሽማግሎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፤ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ መንፈስ ቅዱስን አሳድራለሁ ትንቢትን ይናገራሉ፤ ድንቆችን በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል ታላቅ የሆነ የጌታ ቀንም ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል።የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል። ❖ ዳዊትም እንዲህ አለ ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ደስ የሚያሰኝ ደኅነትህንም ስጠኝ፤ በጽኑዕ መንፈስህም አጽናኝ ለዝንጉዎች ሕግህን እንዳስተምራቸው፤ ሁለተኛም መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉ አለ፤ ደግሞ ቅዱስ መንፈስህ በጽድቅ ምድር ይምራኝ አለ፤ ደግሞም በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤ ኢሳይያስም እንዲህ አለ በእኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ለድኆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ለተማረኩትም ነፃነትን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠ እለው ዘንድ ላከኝ። ❖ ጌታችንም እንዲህ አለ ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ይህን ነገርኳችሁ፤ ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል፤ እኔ ሰላምን እተውላችኋለሁ የአባቴንም ሰላም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ስጦታ አይደለም ልባችሁ አይታወክ አትፍሩም ። ❖ እኔ እሔዳለሁ ወደእናንተም ተመልሼ እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ፤ ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አለ እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚገኝ የዕውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለእኔ ይመሰክራል፤ እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋራ ኖራችኋልና ምስክሮቼ ናችሁ። ❖ እንዳትሰነካከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል ከዚህም በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንደሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፤ እኔም ዕውነት እነግራችኋለሁ እኔ ብሔድ ይሻላችኋል እኔ ካልሔድኩ ግን አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ወደ እናንተ አይመጣምና ከሔድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ ። ❖ እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይውቅሰዋል፤ ስለ ኃጢአት በእኔ አላመኑምና ስለ ጽድቅም ወደ አብ እሔዳለሁና እንግዲህም አታዩኝምና ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ይፈረድበታልና አላቸው፤ የምነግራችሁም ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን ዛሬ ልትሸከሙት አትችሉም እርሱ የዕውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል። ❖ እርሱ እኔን ይገልጣል ከእኔም ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋልና ለአባቴ ያለው ሁሉ የኔ ገንዘብ ነውና ስለዚህ ከእኔ ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋል አልኳችሁ፤ ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና፤ ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ ምንድነው ይህ ነገር ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና የሚለን። ❖ ጌታ ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደሚሹ ዐወቀባቸው እንዲህም አላቸው ስለዚህ ነገር እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ስለአልኳችሁ፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ እናንተ እንደምታዝኑ እንደምታለቅሱ ዓለም ደስ ይለዋል እናንተ ግን ታዝናላችሁ ነገር ግን ኀዘናችሁ ደስታ ይሆናችኋል፤ ሰው የሆነበትንም ሥራ በፈጸመ ጊዜ ሒዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ፤ ስታጠምቋቸውም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሉ፤ ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ አላቸው። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከቸር አባቱ አዳኝና ሕይወት ከሆነ ቅዱስ መንፈሱ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
📌 ግንቦት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት 2.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ 3.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት
Hammasini ko'rsatish...