cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ነገረ_ማሪያም

እግዚአብሔር በቸርነቱ አለምን ሊያድን ቸርነቱን ለመግለፅ ምክንያት የሆነችውን ክብሯን ፡ድንግልናዋን፡ንፅሕናዋን እና ልዕልናዋን የምናወሳበት የምንማርበት ነው። @#የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
147
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

✅ስንክሳር 🚩ግንቦት 11 ✅ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ✏ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን : ክብራችን : ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን? *አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም):: *ልቡናው የቅድስና ማሕደር:: *ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው:: *እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ! ✏ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- "ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ : ሙሉ አካሏ ነው::" ✅ የሊቁ ዜና ሕይወት በጥቂቱ ✏ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ:: ሊቁ በሕጻንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር:: ትምሕርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም:: በጥበበ እግዚአብሔር እንጂ:: ✏ምን ትምሕርት ባይገባው ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር:: አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው:: ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ:: ✏ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምሕሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው:: ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና:: ✏ከዚህ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ : ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ:: ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ:: እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው:: ✏ካህኑ ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ወሰነ:: በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር:: ✏ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት:: ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት:: ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት : ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት:: ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር : ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ:: ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት:: ✏ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ:: ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ:: ቅዱስ ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ : ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላት ከሃገሩ ወጣ:: ✅ ቅዱስ ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት:- 1. አምስት ያሕል መጻሕፍትን ጽፏል:: 2. በጣና ቂርቆስ : በዙር አባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል:: 3.በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋሃ መላእክትና በተባሕትዎ ኑሯል:: ✥ በ576 (571) ዓ/ም በተወለደ በ71 ዓመቱ በዚህች ቀን ተሰውሯል:: ✥ አባቶቻችን:- *ጥዑመ ልሳን *ንሕብ *ሊቀ ሊቃውንት *የሱራፌል አምሳያ *የቤተ ክርስቲያን እንዚራ *ካህነ ስብሐት *መዘምር ዘበድርሳን *ማኅሌታይ *ልዑለ ስብከት እያሉ ይጠሩታል:: ✥ የቅዱሱ ጸሎትና በረከት ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: 🚩 ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦ 1.ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ 2.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ 3.ቅዱሳን ክርስቲናና ይስሐቅ (የቅዱስ ያሬድ ወላጆች) 4.ቅድስት ታውክልያ እናታችን (ንግሥናን ንቃ ሰማዕት የሆነች) 5.ቅድስት ኤፎምያ ሰማዕት 6.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 7.ቅድስት አናሲማ ገዳማዊት 8.አባ በፍኑትዮስ ገዳማዊ 9.አባ አሴር ሰማዕት (ኢትዮዽያዊ) 10.አባ በኪሞስ ጻድቅ 🚩ወርሐዊ በዓላት፦ 1.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት 2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት 3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና ✅ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀሀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
Hammasini ko'rsatish...
ትንሣኤ ክርስቶስ ስለ ክርስቶስ መነሣት አስቀድሞ ትንቢት ተነግሯል፡፡ ይህም ዳዊት "ይትነሣዕ እግዚአብሔር ወይዘረው ጸሩ ወይጉየዩ ጸላዕቱ እምቅድመ ገፁ" እግዚአበሔር ያነሣ፣ ጠላቶቹም ይበተኑ፣ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ፡፡ መዝ. 67፡1 "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመዘንቃህ እምንዋም ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ" እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደኃያል ሰው ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ መዝ. 77፡65 በደቂቀ ነቢያት፡- በሠኑይ ዕለት ይቀስፈነ ወበሠሉስ መዋዕል ይሠርየነ ወየሐይወነ አመሣልስት ዕለት ይትነሣእ ወንቀውም ምስሌሁ፡፡ በኦሪት አንበሳ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ዕርግ እምንዝኅትከ እየተባለ በብሉይ በሐዲስ በብዙ ዓይነት ተነግሯል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በሞቱ ድል አድርጎ ተነሣ ማለት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ዝም ብሎ ድንጋዩ እንደ ተገጠመ ተነሥቶ ሄደ፡፡ ከዚያ በማርቆስ ወንጌል እንደተጻፈው ሴቶች ወደ መቃብሩ ሂደው "መኑ ይከሥትለነ" "ድንጋዩን የሚገለብጥልን ማነው?" ሲሉ መላእክት አነሱላቸው፡፡ /ማር. 16፡1-8፤ ማቴ. 28፡1-8 ሉቃ. 24፡1-10 ዮሐ. 20፡1/ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ክታቡ "ክርስቶስ ላንቃላፉት በኵር ሆኖ ተነሥቷል፡፡" ይላል ይህም ማለት መጀመሪያ ትንሣኤ ዘጉባኤ የተነሣ እሱ ነው፡፡ ሌላ ገና አፈር ሆኖ ለመነሣት ዕለተ ምጽአትን ይጠብቃል "ተነሥአ እግዚእነ ከመይምሐረነ በተንሥኦቱ እንከሰ ዳግመ ኢይመውት" ከእንግዲህ ወዲያ ሁለተኛ አይሞትም" እነ አልአዛር ቢነሱ ተመልሰው ሞተዋል፣ ትንሣኤ ዘጉባኤን ይጠብቃሉ፡፡ ጌታችንና እመቤታችን ግን ተመልሰው አይሞቱም እንዲህ ያለው ትንሣኤ ዘጉባኤ ይባላል፡፡"ቀደመ ተነሥኦ እምኲሉሙ ሙታን" ከሙታን አስቀድሞ ተነሣ የተባለው ስለዚህ ነው፡፡ እስከ አሁን ሁለቱ ብቻ ናቸው ትንሣኤ ዘጉባኤ የተነሡት፡፡ ከዚህ ጋር አብሮ ሊታይ የሚገባው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን እንደተነሣ ማርያም መግደላዊነት ቀርባ ልትነካው ባሰበች ጊዜ ገና ወደ አባቴ አላረኩምና አትንኪኝ ብሎ እንደነገራት በዮሐንስ ወንጌል ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ የዚህ ዋና ትርጉሙ ጌታችን ሴት እንዳትነካው /ንቆ/ ሳይሆን ማርያም መግደላዊት የሚያርግ መስሏት ስለነበር ገና 40 ቀን እቆያለሁ ለማለት ነው፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ በሌላ ምዕራፍ "አኅዛ እገሪሁ ወሰገዳ ሎቱ" እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት ይላል፡፡ አሁንም በዚሁ ምዕራፍ 20 ቁጥር 24 "ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከእነርሱ ጋር አልነበረም ምልክት ከእጆቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት በጎኑ ካላገባሁ አላምንም" ማለቱን ያስረዳል፡፡ በእርግጥ ቶማስ ጌታ ከሙታን ተነሥቶ በዝግ ቤት ገብቶ ለቀደ መዛሙርቱ ሰላም ለእናንተ ይሁን ሲላቸው አልነበረም በዚህም ምክንያት ተጠራጥሮአል፡፡ ጌታ ደግሞ ለምን ተጠራጠርክ ካልዳሰስኩህ አላምንም ብለሃል፡፡ በልና የተወጋው ጎኔን እይ፤ የተቸነከረው እጄን ተመልከት፡፡ ብሎ እንዲዳስሰው ፈቀደለት፡፡ ቶማስም ሲዳስስ እሳተ መለኮት ቀኝ እጁን አቃጠለው፡፡ "እግዚእየ ወአምላኪየ" ፈጣርዬ አምላኬ አምላኪየ "መዳሰሱ ሲያይ" እግዚእየ ማቃጠሉን ሲያይ አምላኪየ አለ፡፡ ይኸንን "እግዚእየ ወአምላኪየ" ያለውን ወስዶ በሃይማኖተ አበው "አንተ ቀዳማዊ ወአንተ ዳኅራዊ" አንተ መጀመሪያ አንተም መጨረሻ ነህ ብሎ ተርጉሞታል፡፡ ይህች ገቦ መለኮት የዳሰሰች እጅ ሳትሞት ሕያዊት ሆኖ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር ትኖራለች፡፡ ጥር 21 ቀን የአስተርእዮ ዕለት በዓሉ ይከበራል፡፡ ይህ ታሪክ የሚገኘው መጽሐፈ እንድልስ በሚባለው ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም "ይትፌሣሕ ሰማይ ወትተሐሰይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ኅምዝ" ያለው ትሑታኑ ደቂቀ አዳም ልዑላኑ መላእክት ጌታ አስታረቃቸው ሁሉም ደስ አላቸው ማለቱ ነው ሰማያውያንና ምድራውያን በክርስቶስ አንድ ሆኖአልና፡፡ "ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ" "ምድርም በክርስቶስ ደም ተቀድሳ የክርስቶስን ትንሣኤ ታከብራለች"፡፡ አንድም ያመኑ ምዕመናን ሁሉ በክርስቶስ ደም ነጻ ወጥተው በዓለ ትንሣኤን ያከብራሉ መጽሐፍ ለግዕዛን ሰጥቶ መናገሩ የተለመደ ነው፡፡ "ትባርኮ ምድር ለእግዚአብሔር" ምድር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች ይህ ማለት ማኅበረ ምዕመናን እግዚአብሔር ያመሰግኑታል ማለት ነው፡፡ ክብር ምስጋና ይግባውና መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር በመቆየት ሙስና መቃብርን አጥፍቶ፣ ሞትን ድል ነስቶ ተነሥቶልናል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
በዓለ ፋሲካ በብሉይ የነበረ በግ ምሳሌ በብሉይ ኪዳን በጉ ዓመት የሆነው፤ ቀንዱ ያልከረከረ፤ ጥፍሩ ያልዘረዘረ፤ ዓመት የሞላው ጠቦት አይታችሁ ከ10 እስከ 14 ቀን በመዓልቱ በሁለት እጅ ብርሃን፤ ከሌሊቱ በአንድ እጅ ጨለማ ሰውት፡፡ ስትሰውትም ሰባት፤ አሥር፣ አሥር ሁለት ሆናችሁ ሰውት ብሎአቸዋል፡፡ በጉ ቀንዱ ያልከረከረ፤ ጥፍሩ ያልዘረዘረ መሆኑ፤ ጌታም ምክንያተ ኃጢአት የለበትምና ነው፡፡ ደሙን ስትቀቡት "ወሶበ ርእየ መልአከ ሞት ደመ በግዕ ለበወ ሞተ እግዚእ ፈርሐ ወኢቀርበ" እንዲል "ይህ የክርስቶስ ምሳሌ ነው ሲለው ነው፣ አባር ቸነፈሩ ከእስራኤል ቤት እንዳይገባ ይሆናል"፡፡ ደመ በግዑን ያየ መልአከ ሞትም እስራኤልን እያለፋቸው መሄድ ጀመረ፡፡ የግብጻውያን በኩር፣ ይገድላል፡፡ ያ የክርስቶስ ምሳሌ በመሆኑ የደመ በግዑ የደም ምልክት ያለው ቤት ሞት አይገባውም፡፡ በደመ ክርስቶስ የተዋጀ፣ በደመ ክርስቶስ መዳኑን ያመነ ሰውም ሞተ ነፍስ አያገኘውም፡፡ ላቱ እስከ ምጽአት የሚነሱ መምህራን፣ ጸጉሩ የመንፈስ ቅዱስ፣ ስለሀብቱ ብዛት፣ ቀንዱ የሥልጣነ እግዚአብሔር፣ ዓይኖቹ የነቢያት ምሳሌ ናቸው"፡፡ በዚህ ዕለት በተለይ በምዕመናን የሚፈጸም ሌላ ድርጊት አለ፡፡ ይኸውም ዳቦ ይጋገራል፣ ንፍሮ ይነፈራል፣ ይኸ ልማደ ሀገር ቢሆንም የተቻለው ዓርብንና ቅዳሜን ያክፍል፣ ያልተቻለው ቅዳሜን ብቻ ያክፍል ብሏልና፡፡ ለአክፍሎት የሚስማማን ምግብ የሚጾም ሰው እንዳይደክም "ጉልባንን" አብዝቶ ይበላል፡፡ ጾሙን የጀመረው "ያዕቆብ እኁኁ ለእግዚእነ" የጌታ ወንድም ያዕቆብ ነው፡፡ ይኸውም የጌታ ትንሣኤን ሳላይ አልበላም በማለት ጀምሮታል፡፡ ጌታ ከተቀበረ በኋላ ሐዋርያት እህል እንብላ አሉ፡፡ "ያዕቆብ በሦስት ቀን እነሳለሁ" ብሏል አይሆንም ቢላቸው እንግዲያስ እኛም እንጹም ብለው ጹመዋል፡፡ እኛም ያንን ይዘን እንጾማለን፡፡
Hammasini ko'rsatish...
ቀዳም ሥዑር ሚያዝያ 23፣2013 ዓ.ም. ቅዳሜ፡ – ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ ምእመናን ሆይ፣ በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓተ መላእክት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የዕለታቱን ክብርና ስያሜ ከማወቅና ከመረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃየማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡ ምንጭ፡-@Abershyerufallij fb page ፣ ሚያዝያ 2013፣ አዲስ አበባ፡፡ https://telegram.me/gedamochachn13
Hammasini ko'rsatish...
ገዳሞቻችን

"ለሚጠይቋችሁ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ።" 1ኛ ጴጥ 3:15 ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ⓐⓑⓡⓢⓗ z RUFAL እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው !! 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:13 @AbateRUFAEL13 💒💒💒💒💒💒💒💒 ተመሰረተ August 28 /2018 ነሀሴ 22/2010

4_5922795489283016332.aac6.94 MB
+++ የይሁዳ እግሮች +++ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመሥጠት ከአይሁድ ጋር የተስማማው ረቡዕ ዕለት ነበር፡፡ ይህን ስምምነት አድርጎ እንደጨረሰ ወደ ጌታና ወደ ደቀ መዛሙርቱ ማኅበር ተመለሰ፡፡ ከረቡዕ ጀምሮ እስከ ሐሙስ ማታ ድረስም ከጌታ ፊት ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ አሳለፈ፡፡ ይህ በትክክል ይሁዳ ምን ዓይነት አስመሳይና ክፉ ሰው እንደነበረ ያሳያል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሁኔታዎች አስፈርተውት ጌታውን ለሦስተኛ ጊዜ አላውቀውም ብሎ ከካደ በኋላ ጌታችን ለአንድ አፍታ ቀና ብሎ ስለተመለከተው ብቻ የጌታውን ፊት በድፍረት ለመመልከት አቅም አጥቶ መራራ ልቅሶን እያለቀሰ ከአጥር ውጪ ወጥቶ ነበር፡፡ ይሁዳ ግን አሳልፎ ሊሠጠው ከተስማማባት ሰዓት ጀምሮ ድምፁን አጥፍቶ ከጌታችን ጋር እንደ ወትሮው አብሮ ሲቀመጥ አንድ ጊዜ እንኳን አልተሸማቀቀም ልብ አድርጉ! በራሱ ሃሳብ አመንጪነት ፣ ራሱ ወደ አይሁድ ሸንጎ ሔዶ ፣ ብር ለመቀበል ተስፋ ተቀብሎ ከመጣ በኋላም የጌታችንን ዓይኑን እያየ ‹አሳልፌ የምሠጥህ እኔ እሆንን?› ብሎ ለመጠየቅም ድፍረት ነበረው! በዚያች ሰዓት እንደ ዳታንና አቤሮን መሬት ተሰንጥቃ ስላልዋጠችው ፣ ምላሱ ከጉሮሮው ጋር ስላልተጣበቀ ፣ በድፍረትና በመናቅ በእውነተኛው ጌታ ላይ የተናገሩት የሽንገላ ከንፈሮቹ ዲዳ ባለመሆናቸው የፈጣሪን ትዕግሥቱን እናደንቃለን፡፡ ሁሉን የሚያውቀው ጌታ ግን ይሁዳ ሊሸነግለው መሞከሩን ቢያውቅም ‹አንተ አስመሳይ!› ብሎ አላዋረደውም የእግዚአብሔር ነቢይ ኤልሳዕ ሎሌው ግያዝ የማይገባውን ገንዘብ ከለምጹ ከነጻው ከሶርያዊው ንዕማን ተቀብሎ ቤቱ ወስዶ ከሸሸገ በኋላ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ ከፊቱ መጥቶ ሲቆም ‹ግያዝ ሆይ ከወዴት መጣህ?› ብሎ ጠይቆት ነበረ፡፡ ግያዝም ‹‹እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሔድሁም›› አለ፡፡ ኤልሳዕም ፡- ‹‹ልቤ ከአንተ ጋር አልሔደምን?›› ብሎ ያደረገውን እንዳወቀበት ከነገረው በኋላ የንዕማን ለምጽ በአንተ ላይ ይጣበቃል ብሎ ረግሞት እንደ በረዶ ለምጻም ሆኖ ወጣ፡፡ (፪ነገሥ. ፭፥፳‐፳፯) ሐዋርያው ጴጥሮስም ሐናንያና ሰጲራ የተባሉ ባልና ሚስት ገንዘባቸውን ከቤታቸው ሸሽገው መንፈስ ቅዱስን ሊያታልሉና በማስመሰል በፊቱ ሊቆሙ ሲሞክሩ ‹እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሻችሁም› ብሎ በካህን ቃሉ ተናግሮ ተቀሥፈው እንዲሞቱ አድርጓቸዋል፡፡ (ሐዋ. ፭፥፩-፲) የነቢያትና የሐዋርያት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኤልሳዕና ከጴጥሮስ በላይ የልብን የሚያውቅና መቅጣት የሚቻለው ነው፡፡ ሆኖም ከአይሁድ ጋር ሊሸጠው ተዋውሎ የመጣው ይሁዳ ዓይኑን በጨው አጥቦ ‹አሳልፌ የምሠጥህ እኔ እሆንን?› እያለ ሲዘብትበት በታላቅ ትዕግሥት ዝም አለው፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን ሊያታልሉ የሞከሩ ሰዎች እንዲህ ከተቀጡ የነቢያትን አምላክ ሊያታልል የሞከረ ‹‹…እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?›› (ዕብ. ፲፥፳፱) ከሁሉም ልብ የሚሰብረው ሐሙስ ምሽት የሆነው ነገር ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ›› የእግር ሹራብ በማይደረግበትና ክፍት ጫማ በሚደረግበት በዚያ ዘመን ቀኑን ሙሉ ሲጓዙ የዋሉበትን የሐዋርያቱን በአቧራ ያደፉ እግሮች ሊያጥብ ተነሣ፡፡ (ዮሐ.፲፫፥፬) በእስራኤል ባህል እግር ማጠብ የሎሌዎች ሥራ ቢሆንም የሰማይና የምድር ንጉሥ ግን በትሕትና እንደ ሎሌ ሆነ፡፡ (፩ሳሙ. ፳፭፥፵፩) ጌታችን አጎንብሶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ይሁዳም ሊታጠብ ተራውን ይጠብቅ ነበር፡፡ ጌታውን ሊሸጥ በተስማማበት ማግሥት ጌታችን አጎንብሶ እግሩን አጠበው፡፡ ‹‹ወኀፀበ እግረ ይሁዳ አስቆሮታዊ ዘያገብኦ›› ‹‹የሚያስይዘውን የአስቆሮቱ የይሁዳንም እግር አጠበ›› እንዲል (ግብረ ሕማማት ዘሐሙስ) ከአንድ ቀን በፊት ክፋትን ለማሴር ወደ አይሁድ ካህናት ግቢ የሮጡትን የይሁዳን እግሮች ጌታችን አጎንብሶ አጠባቸው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሊያስይዘው ወደ አይሁድ የሚሮጥባቸውን እግሮች ፣ የሚይዙትን ወታደሮች እየመራ ወደ እርሱ የሚመለስባቸውን እግሮች አጠበለት፡፡ ምንም እንኳን በነገው ዕለት እግሮቹን እንዲቸነከር አሳልፎ የሠጠው መሆኑን ቢያውቅም ሰውን ወዳጁ ክርስቶስ ግን የአስቆሮቱ ይሁዳን ለመጨረሻ ጊዜ እግሩን አጥቦ ተሰናበተው እንደ ነቢዩ ዳዊት ‹‹አቤቱ፥ ምሕረትህን እንዴት አበዛህ!›› ከማለት በቀር በምን አንደበት ልንናገር እንችላለን? (መዝ. ፴፮፥፯) ‹‹ጠላቶቻችሁን ውደዱ›› ያለን ጌታ አሳልፎ የሚሠጠውን የይሁዳን እግር ሲያጥብ ከማየትስ በላይ በቂም በቀል ለሚቆስለው ልባችን ምን መድኃኒት ይኖር ይሆን? ይሁዳ ሆይ እስቲ አንድ ጊዜ ንገረን ፤ ጌታ አጎንብሶ እግርህን ሲያጥብህ እንዴት አስቻለህ? ‹እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ› የሚሰገድለት አምላክ እግርህን ሲያጥብህ እንዴት ትንሽ እንኳን አልተሰማህም? አንተ እግሩን ልታጥበው እንኳን የማይገባህ ፈጣሪ እግርህን ሲያጥብህ እያየህ እንዴት ልብህ ደነደነ? መጥምቁ ዮሐንስ ‹የጫማውን ጠፍር ልፈታ አይገባኝም› ያለው ጌታ አጎንብሶ ሲያጥብህ እንዴት ልብህ በጸጸት አልተሰበረም? ረቡዕ አሳልፈህ ልትሠጠው ተስማምተህ መጥተህ ሐሙስ አጎንብሶ ሲያጥብህ እንዴት አልጨነቀህም? ከአይሁድ ጋር የተስማማኸው ነገር ‹ይቅርብኝ› ለማለት ጌታችን ከእግርህ በታች ዝቅ ብሎ ካጠበህ ሰዓት የተሻለ ማሰቢያ ጊዜ ከየት ይገኛል? በፍቅሩ ውስጥ ክፋትህ ፣ በትሕትናው ውስጥ ትዕቢትህ እንዴት አልታየህም? እንዴትስ እግሮችህን ሠጥተህ ያለ አሳብ ታጠብህ? ቅዱስ ጴጥሮስ እንኳን ‹‹ጌታ ሆይ አንተ እንዴት የእኔን እግር ታጥባለህ?› ብሎ ተጨንቆ ጠይቆ ነበር፡፡ ‹የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም› ብሎ ተከላክሎም ነበር፡፡ ልበ ደንዳናው ይሁዳ ግን ዝም ብሎ እግሮቹን ሠጠ፡፡ የከዳውን ጌታ የቁልቁል እየተመለከተ ለአፍታ እንኳን ልቡ አልተመለሰም፡፡ ሐዋርያት ጌታ ባጠበው እግራቸው ለጊዜው ፈርተው ቢሮጡም በኋላ ግን በጸጸት ተመለሱበት፡፡ በአምላክ እጅ በታጠበ እግራቸው ያለመሰልቸት ዓለምን ዞረው ወንጌሉን አስተምረው እስከሞት ድረስ ታመኑ፡፡ በእግራቸውም እንደ ስማቸው ሐዋርያት (ተጓዦች) ሆኑበት፡፡ ይሁዳ ግን በአምላክ እጅ በታጠበው እግሩ ወደ አይሁድ ገስግሶ ጌታ ለሚያንገላታው ጦር መንገድ እየመራበት ተመለሰ፡፡ ‹‹ኦ እግዚኦ ዘኢትደፈር ይሁዳ ደፈረከ›› ‹‹አቤቱ የማትደፈር አንተን ደፋር ይሁዳ ደፈረህ!›› (ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ ፩፥፳፩) ("ሕማማት" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ) 💚 @kokuha_haymanot 💚 💛 @kokuha_haymanot 💛 ❤️ @kokuha_haymanot ❤️
Hammasini ko'rsatish...
✅ስንክሳር 🚩ሚያዚያ 12 ✅ቅዱስ ኤርምያስ፦ ✏ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ600 አካባቢ የነበረ ነቢይ ነው:: አባቱ ኬልቅዩ ይባላል:: ከካኅናተ እስራኤል አንዱ ነበር:: ✏እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕጻንነቱ ነበር:: "ከእናትህ ማሕጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ: ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል:: (ኤር. 1:5) ✏ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም:: ከ70 ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና:: ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" (ባለ እንባው ነቢይ) ይሉታል:: ✏ዘመኑ ዘመነ ኃጢአት (ዘመነ ዐጸባ) ነበር:: እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም:: ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት:: እግዚአብሔር ግን በኢትዮዽያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው:: ✏የተሰበከላቸውን የንስሃ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር የሚባል የአሕዛብ ንጉሥ መጥቶ አሥሩን ነገድ ማርኮ አሦር (ነነዌ) አወረዳቸው:: በሁዋላ ደግሞ በኃይለኝነቱ የታወቀው የባቢሎን ንጉሥ ይማርካቸው ዘንድ ወደ ሁለቱ ነገድ ኢየሩሳሌም ደረሰ:: ኤርምያስ ወደ ከተማዋ ዳር ወጥቶ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቀሰ:: ✏ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው:: ነቢዩ የተናገረው አይቀርምና ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ: እኩሉንም ማርኮ: ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ: የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጐ ባቢሎን አወረዳቸው:: ✏ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን (ከመከራው የተረፉት) ይዘውት ወደ ግብፅ ወረዱ እንጂ አልተማረከም:: ✏በዚያም ተአምራትን አድርጐ አራዊትን አጥፍቷቸዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት: ነቢይ: መምሕርም ነውና ወደ ሕዝቡ (ወደ ባቢሎን) ወረደ:: በዚያም ትንቢትን እየተናገረ: ሕዝቡን ከ70 ዓመታት በሁዋላ ወደ ሐገራቸው እንደሚመለሱ እያስተማራቸው በባቢሎን ቆይቷል:: ያለ በደሉም በመከራቸው ተካፋይ ሆኗል:: ✏ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው:: ✏በዚህ ተበሳጭተው ሊወግሩት ሲሉ ጸጋ በዝቶለት: ምስጢርም ሰፍቶለት ስለ ነገረ ሥጋዌ (ስለ ክርስቶስ የማዳን ሥራ) አምልቶና አጉልቶ ትንቢት ተናገረ:: አንዴ ልቡናቸው ታውሮ ኤርምያስ ነው ብለው ድንጋዩን በድንጋይ ሲወግሩት ውለዋል:: ዘግይቶ ግን ኤርምያስ ራሱን ገለጠላቸው:: ስለ እነርሱ ሲል 70 ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት:: ✏ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ 52 ምዕራፎች ያሉት ሐረገ ትንቢት ተናግሯል / ጽፏል:: ዜና ሕይወቱ ከራሱ የትንቢት መጽሐፍ በተጨማሪ በተረፈ ኤርምያስ: በመጽሐፈ ባሮክ: በገድለ ኤርምያስ: በዜና ብጹዐን: በመጽሐፈ ስንክሳርም ተጽፏል:: ✏በዚህች ዕለት ንጉሡ ሴዴቅያስ ቅዱስ ኤርምያስን አስሮት እያለ ኢትዮዽያዊው ቅዱስ አቤሜሌክ ያስፈታበት (ከረግረግ ያወጣበት) ይታሰባል:: ✥ቸር እግዚአብሔር በኤርምያስ ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿን ከስደትና ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: 🚩ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦ 1.አቡነ ሳሙኤል ዘቆየጻ (ኢትዮዽያዊ) 2.ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ 3.ቅዱስ አቤሜሌክ ኢትዮዽያዊ 4.ቅዱስ ባሮክ 5.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ዘኢየሩሳሌም 🚩ወርሐዊ በዓላት፦ 1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት 2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ 4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት) 5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ 7.ቅዱስ ድሜጥሮስ ✅ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
Hammasini ko'rsatish...
††† እንኳን ለነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርምያስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ኤርምያስ ††† ††† ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ600 አካባቢ የነበረ ነቢይ ነው:: አባቱ ኬልቅዩ ይባላል:: ከካኅናተ እስራኤል አንዱ ነበር:: እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕጻንነቱ ነበር:: "ከእናትህ ማሕጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ: ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል:: (ኤር. 1:5) ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም:: ከ70 ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና:: ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" (ባለ እንባው ነቢይ) ይሉታል:: ዘመኑ ዘመነ ኃጢአት (ዘመነ ዐጸባ) ነበር:: እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም:: ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት:: እግዚአብሔር ግን በኢትዮዽያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው:: የተሰበከላቸውን የንስሃ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር የሚባል የአሕዛብ ንጉሥ መጥቶ አሥሩን ነገድ ማርኮ አሦር (ነነዌ) አወረዳቸው:: በሁዋላ ደግሞ በኃይለኝነቱ የታወቀው የባቢሎን ንጉሥ ይማርካቸው ዘንድ ወደ ሁለቱ ነገድ ኢየሩሳሌም ደረሰ:: ኤርምያስ ወደ ከተማዋ ዳር ወጥቶ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቀሰ:: ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው:: ነቢዩ የተናገረው አይቀርምና ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ: እኩሉንም ማርኮ: ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ: የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጐ ባቢሎን አወረዳቸው:: ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን (ከመከራው የተረፉት) ይዘውት ወደ ግብፅ ወረዱ እንጂ አልተማረከም:: በዚያም ተአምራትን አድርጐ አራዊትን አጥፍቷቸዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት: ነቢይ: መምሕርም ነውና ወደ ሕዝቡ (ወደ ባቢሎን) ወረደ:: በዚያም ትንቢትን እየተናገረ: ሕዝቡን ከ70 ዓመታት በሁዋላ ወደ ሐገራቸው እንደሚመለሱ እያስተማራቸው በባቢሎን ቆይቷል:: ያለ በደሉም በመከራቸው ተካፋይ ሆኗል:: ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው:: በዚህ ተበሳጭተው ሊወግሩት ሲሉ ጸጋ በዝቶለት: ምስጢርም ሰፍቶለት ስለ ነገረ ሥጋዌ (ስለ ክርስቶስ የማዳን ሥራ) አምልቶና አጉልቶ ትንቢት ተናገረ:: አንዴ ልቡናቸው ታውሮ ኤርምያስ ነው ብለው ድንጋዩን በድንጋይ ሲወግሩት ውለዋል:: ዘግይቶ ግን ኤርምያስ ራሱን ገለጠላቸው:: ስለ እነርሱ ሲል 70 ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት:: ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ 52 ምዕራፎች ያሉት ሐረገ ትንቢት ተናግሯል / ጽፏል:: ዜና ሕይወቱ ከራሱ የትንቢት መጽሐፍ በተጨማሪ በተረፈ ኤርምያስ: በመጽሐፈ ባሮክ: በገድለ ኤርምያስ: በዜና ብጹዐን: በመጽሐፈ ስንክሳርም ተጽፏል:: በዚህች ዕለት ንጉሡ ሴዴቅያስ ቅዱስ ኤርምያስን አስሮት እያለ ኢትዮዽያዊው ቅዱስ አቤሜሌክ ያስፈታበት (ከረግረግ ያወጣበት) ይታሰባል:: ††† ቸር እግዚአብሔር በኤርምያስ ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿን ከስደትና ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ††† ሚያዝያ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ሳሙኤል ዘቆየጻ (ኢትዮዽያዊ) 2.ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ 3.ቅዱስ አቤሜሌክ ኢትዮዽያዊ 4.ቅዱስ ባሮክ 5.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ዘኢየሩሳሌም ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት 2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ 4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት) 5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ 6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ 7.ቅዱስ ድሜጥሮስ ††† "ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል: ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር: ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም:: እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላቹሃል:: እላችሁአለሁና: በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ እንግዲህ ወዲህ አታዩኝም::" ††† (ማቴ. 23:37-39) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Hammasini ko'rsatish...
መጋቢት 9 ሐዋርያው ቅዱስ ኩትን ቅዱስ ኩትን በዘመነ ሐዋርያት የነበረ: ከአሕዛብ ወደ ክርስትና በቅዱስ ጳውሎስ አማካኝነት የተመለሰ: ከቅዱሳን ሐዋርያት እግር ሥር ቁጭ ብሎ ይማር ዘንድ የታደለ: በፍፁም ድንግልናው የተመሰገነ ሐዋርያዊ አባት ነው:: ይህ ቅዱስ ሚስት ነበረችው:: ግን በትዳር ውስጥ ሆኖ ድንግልናን መጠበቅ እንደሚቻል ያሳየ የሐዲስ ኪዳን ሰው ነው:: ቅዱስ ኩትን በንጽሕናው: በአገልግሎቱና በጣዕመ ስብከቱ በሐዋርያትና ምዕመናንም ተወዳጅ ነበር:: ለብዙ ዘመናት በወንጌል አገልግሎት ኑሮ በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና አርፏል:: ፈጣሪ ከበረከቱ ያድለን:: መጋቢት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኩትን ሐዋርያ 2.ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት 3.ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት 4."2,000" ሰ... ይህን ፅሁፍ ሙሉውን አንብቦ ለመጨረስ እንዲሁም የሌሎች ቅዱሳንኖችን ስንክሳር (መንፈሳዊ ታሪኮችን) ለማግኘት በታች ባልው አድራሻ (ሊንክ) ተጠቅመው ይጫኑ። https://telegram.me/gedamochachn13
Hammasini ko'rsatish...
ገዳሞቻችን

"ለሚጠይቋችሁ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ።" 1ኛ ጴጥ 3:15 ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ⓐⓑⓡⓢⓗ z RUFAL እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው !! 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:13 @AbateRUFAEL13 💒💒💒💒💒💒💒💒 ተመሰረተ August 28 /2018 ነሀሴ 22/2010

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.