cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Metti Ćity Muslim Jeme'a/የሜጢ ከተማ ሙስሊም ጀመዓ

☞ የጉዞው ተግዳሮት ብርቱ ሲሆን ብርቱዎች በርትተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ...

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
181
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ህይወታችን ለዲናችን "" ከዙፋኑ ላይ ከተደላደለ ንጉስ ይልቅ በሱጁድ ላይ ያለ ሙስሊም በላጭ ነው "" ﻭَﭐﺳْﺘَﻌِﻴﻨُﻮﺍ۟ ﺑِﭑﻟﺼَّﺒْﺮِ ﻭَﭐﻟﺼَّﻠَﻮٰﺓِ ﻭَﺇِﻧَّﻬَﺎ ﻟَﻜَﺒِﻴﺮَﺓٌ ﺇِﻟَّﺎ ﻋَﻠَﻰ ﭐﻟْﺨَٰﺸِﻌِﻴﻦَ በመታገስና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷም (ሶላት) በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡(አልበቀራ 45) ﻗُﻞْ ﺇِﻥَّ ﺻَﻠَﺎﺗِﻰ ﻭَﻧُﺴُﻜِﻰ ﻭَﻣَﺤْﻴَﺎﻯَ ﻭَﻣَﻤَﺎﺗِﻰ ﻟِﻠَّﻪِ ﺭَﺏِّ ﭐﻟْﻌَٰﻠَﻤِﻴﻦَ «ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡(አንአም 162) ﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﯽٰ ﻋﻨﻪ ، ﺃﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﷺ ﻗﺎﻝ ‏« ﺃﻗﺮﺏ ﻣﺎﻳﻜﻮﻥ ﺍﻟﻌﺒﺪ ﻣﻦ ﺭﺑﻪ ﻭﻫﻮ ﺳﺄﺟﺪ، ﻓﺄﻛﺜﺮﻭﺍﺍﻟﺪﻋﺎﺀ ‏» ‏( ﺭﻭﺍﺀ ﻣﺴﻠﻢ ) አቢ ሁረይረህ በዘገቡት ሀዲስ ላይ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም " አንድ ባርያ ለጌታው ቅርብ የሚሆነው ስጁድ ላይ ሲሆን ነው " ስጁድ ላይ ስትሆኑ ዱአ አብዙ ( ረዋሁል ሙስሊም) https://t.me/YemettiKetemaMuslimoch
Hammasini ko'rsatish...
Metti Ćity Muslim Jeme'a/የሜጢ ከተማ ሙስሊም ጀመዓ

☞ የጉዞው ተግዳሮት ብርቱ ሲሆን ብርቱዎች በርትተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ...

#የጦር_ሜዳ_ጀግና #ኻሊድ_ኢብን_አል_ወሊድ_(ረ.ዐ) . #ክፍል_2 ......... ለማድረግ ወሰነ ሁኔታውን በራሱ አንደበት ሲተርከው ብንከታተል የተሻለ ነው። እንዲህ ይላል “መጀመሪያ ያመራሁት ወደ ዑሥማን ኢብን ጦልሓ ነው። ሃሳቤን ሳዋየው አብሮኝ እንደሚጓዝ ገለጠልኝ። ሁለታችን በሌሊት ተነስተን ስንጓዝ ሊነጋ አቅራቢያ በአንድ ገላጣ ስፍራ ስንደርስ ዐምር ኢብን አል-ዓስን ኣገኘነው። ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ወዴት እየተጓዝን እንደሆነ ጠየቀን። ወደ መዲና እያቀናን እንደሆነ ስንገልጽለት እርሱም እንዲሁ ኢስላምን ለመቀበል ወደዚያው እንደሚጓዝ ነገረን፡፡ ሦስታችንም በሶፈር ወር የመጀመሪያው ቀን 8ኛው ዓሂ መዲና ደረስን። ነቢዩን (ሰዐ.ወ) ዘንድ እንደቀረብኩ “የአላህ ሰላም ስነቢዩ ላይ ይሁን” አልኳቸው። እርሳቸውም በብሩህ ፈገግታ ለሰላምታዬ ምላሽ ሰጡኝ። ወዲያው የምስክርነት ቃሌን ሰጥቼ ሰለምኩ። ነቢዩም (ሰዐ.ወ)፡- “ብሩህ አእምሮ እንዳለህ ስለማውቅ አንድ ቀን ወደ እውነታው እንደሚመራህ አስብ ነበር” አሉኝ። ቃል ኪዳን ከተጋባችኋቸው በኋላ “ከመንገዱ ሰዎችን ለማገድ የፈጸምኳቸውን ኃጢአቶች ይምረኝ ዘንድ አላህን ይለምኑልኝ” አልኳቸው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ጊዜ “ኢስላም ሁሉንም ቀደምት ኃጢያቶች ያስምራል” አሉኝ። “ቢሆንም አላህን ይለምኑልኝ” በማለት ተማጸንኩ። በመጨረሻም “አላህ ሆይ! ኻሊድ ከኢስላም በፊት የፈጸማቸውን ኃጢአቶቹን ሁሉ ማረው” በማለት ዱዓ አደረጉልኝ። ይህ ከሆነ በኋላ ዐምር ኢብን አል-ዓስና ጦልሓ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ቀርበው ቃል-ኪዳን ተጋቧቸው። ይህ በዘመነ ጃሂሊያም ሆነ ከሰለመ በኋላ በወታደራዊ አመራር ስኬት ጫፍ ላይ የደረሰ ሰው ለመሆኑ ምን ምን አንኳር ገድሎችን አስመዝግቧል? ይህን ለማወቅ የኋልዮሽ ተጉዘን የሙእታህን ዘመቻ ማስታወስ ሊኖርብን ነው። ሙስሊሞች ሮማውያን ጋር ከተፋጠጡባቸው ታሪካዊ ክስተቶች አንዱ ሆኖ ይህ ጦርነት (ሙእተህ በምትባል ዮርዳኖስ ውስጥ የምትገኝ አካባቢ ' ነው። ሙስሊሙን ሠራዊት በተለመደው አኳኋን አሸኛኘት ያደረጉለት ያለፈው ይህ ጦርነት የተፈጸመ ነው። ሙስሊ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ለሰራዊቱ፡ *** ክፍል 3 ይቀጥላል ይህንን ታሪክ ሸር አድርጉ https://t.me/YemettiKetemaMuslimoch
Hammasini ko'rsatish...
Metti Ćity Muslim Jeme'a/የሜጢ ከተማ ሙስሊም ጀመዓ

☞ የጉዞው ተግዳሮት ብርቱ ሲሆን ብርቱዎች በርትተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ...

🌹#የጦር_ሜዳ_ጀግና🌹 #ኻሊድ_ኢብን_አል_ወሊድ_(ረ.ዐ) . #ክፍል_❶ { እንቅልፍ የሌለውና ሌሎችንም እንቅልፍ የከለከለ ታላቅ ሰው } በኡሑድ ጦርነት ዋነኛው የሙስሊሞች ጠላትን ገዳያቸው ነበር ፤ በቀሩት ጦርነቶች ደግሞ ጠላትን አብዝቶ በሰይፉ የፈጀ የከሀዲያን ጠላት ሆነ። የዚህን ታላቅ ሰው ታሪክ የትላይ መጀመር እንደሚሻል በራሱ ፈተና ነው ። እርሱ ለራሱ እውነተኛ ታሪኩ እንደተጀመረ እሚያምነው ራሱን ለኢስላም ሰጥቶ ከነብዩ ሰለላሁ አይሂ ወሰለም ቃል ኪዳን በመግባት እጅ ለእጅ ከተጨባበጠበት ቅጽበት በኋላ ነው ።ከዚያ በፊት የነበረውን ሕይወት ሁሉ ከንቱ የከንቱ እንደሆነ ነው የሚቆጥረው ። በእርግጥም እንዲህ በመሰቡ አልተሳሳተም ። ስለሆነም በክህደትና በጣኦታዊነት ከጠለሸው የሕይወቱ ክፍል ሳይሆን ታላቅ ድል ወዳስ መዘገበበትና ሁሌም ሲወሳ የሚኖር አንጸባራቂ ስም ወደ ተከለበት የታሪኩ ከፍል ብናመራ ይሻላል። አዎን! የሰይፉላህ ኻሊድ ኢብን አል-ወሊድን (ረ ዓ ) ገድል ልናስነብባችሁ ነው በአላህ ፈቃድ። አንድ ዕለት ኻሊድ (ረዐ) በጥልቅ ተመስጦ ውስጥ ሆኖ ያለፈውን ጊዜና መጪውንም በሃሳብ ያብተለትላል። ይህ አዲስ የመጣ ሃይማኖት እርሱና ብዙሃኑ የቁረይሽ ጣኦታዊያን ከሚገምቱት እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ይዞታውንና አድማሱን እያሰፋ ነው። ታዲያ ይህን እውነታ በመካድ ከእንግዲህ በኋላ ሊባከኑ የሚገባቸው ቀናት መኖር አለባቸውን? አዎን! ኢስላም መለኮታዊ ቡራኬ ያልተለየውና ሁሉን ሰሚና ተመልካች የሆነው አንድ ፈጣሪ የመረጠው መንገድ ነው። እናም ኻሊድ ለራሱ እንዲህ አለ፡- “በአላህ ይሁንብኝ ሐቁ በግልጽ እየታየ ነው ። ይህ ሰው የእውነት ነብይና መልዕክተኛ ነው። እስከመቼ ሳስተባብለው እኖራለሁ ?በአላህ ይሁንብኝ በፍጥነት ወደርሱ ሄጀ ሃይማኖቱን መከተል አለብኝ ። ኻሊድ { ረ ዓ } ይህን ቁርጠኛ አቋም ከወሰደ በኋላ እንደርሱ ዓይነት ዝንባሌና ስሜት እንዳደረባቸው ወደ ጠረጠራቸው ሰዎች በመሄድ በጉዞው እንዲቀላቀሉት ........... ክፍል 2 ይቀጥላል ሸር ይደረግ https://t.me/YemettiKetemaMuslimoch
Hammasini ko'rsatish...
Metti Ćity Muslim Jeme'a/የሜጢ ከተማ ሙስሊም ጀመዓ

☞ የጉዞው ተግዳሮት ብርቱ ሲሆን ብርቱዎች በርትተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ...

#ቆንጆ_ነች_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነው ። #የመጨረሻው_ክፍል ዓቲካ ሶስተኛ ባላን አጣች፤ ሰዪዲና ዙቤይር ኢብኑ ዓዋም ብዙ ትዝታና የማይረሱ ቀናትን አሳይተዋት ነበር፤ ሐዘናንም በዚያ በላቀ ግጥማ ገልጻው ነበር፤ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ሐዘን ጋር የቀረባት ላይ ፈገግ ብላ፤ ሊያጽናናት የሞከረውን ይልቅ እርሳ የአላህ ራህመት ሰፊነቱን በመንገር ትሸኛቸው ነበር፤ ነገር ግን ሰዎች ተሰናብተዋት ሲሄዱ ቤት ውስጥ፤ የሰይድና ዙቤይር ድምጽ፤ አካል የሌለበት ቤት ውስጥ ጭር ብሎ በትዝታ ውቅያኖስ ውስጥ ትዋኝ ነበር። ሰይዲና ዙቤይር አንድ ነገር ትተውላት የሄዱት ልብሳቸው ላይ የነበረው የሚወዱት ኢጥር ሽታቸው ነበር፤ ዓቲካ ምነኛ ቻይ ሴት ነች፤ሰዪዲና ዙቤይርንም ከመውደዳ የተነሳ ሞተውም እንካን የሚፈልጉትን ነገር አማልታለች፤ ያ የተወችውንም የመስጂድ ሰላት፤ እንደዚያው ለማቆም ወስና ነበር፤ የባል ሃቅ ከሞት ቡሃላም......... ያሰላምያ አላህ ወንዶቻችንና ሴቶቻችንን በህይወት እያሉ ያለባቸውን ሁቁቆች የሚያማሉ አድርጋቸው። እዚህ ላይ አሳሳቢው ነገር ለሰይዲና ዙቤይር መገደል መንሲኤ የነበረው በመዲና ውስጥ የተፈጠረው ፊትና ከባድ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው፤ከሰዪዲና ዑመር ኢብኑ ኸጣብ ቡሃላ ኸሊፋ የነበሩት አሚረል ሙእሚኒንና ሰዪዲና ዑስማን ኢብኑ አፋን ከአስሩ በጀነት ቡሽራ ያገኙት ናቸው፤ ረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ሰዪዲና ዑስማንን እንደወደዳቸው እንዳወደሳቸው ነው የሞቱት፤ እንዲያውም በእሁድ ጦርነት ላይ፤ ነቢያችን አሌይሂ ሰላቱ ወሰላም ከሰዪዲና ዑመር ኢብኑ ኸጣብና ሰዪዲና ዑስማን ጋር ይህ ተራራ ላይ ሲወጡ፤ የእሁድ ተራራ ተንቀጥቅጦ ነበር፤ ረሱልም ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም "ያ እሁድ ተረጋጋ እላይህ ላይ ያለው ነቢይና ሁለት ሸሂዶች ናቸው" ብለው ነበር፤ይህ ፊትና የተጠነሰሰው የመን ውስጥ ይኖር የነበረው የሁዲ ቅጽል ስሙ ኢብን ሰውዳእ ወይም የጥቁራ ልጅ ተብሎ የሚጠራ የአላህ ጠላት ነው፤ እናቱ በጣም ጥቁር ነበረች ይባላል፤ ይህ ሰው የሰዪዲና ዑመርን መሞት እድል ተጠቅሞ እስልምና ተቀብያለሁ በማለት ብዙ ተካታዮችን አፍርቶ መዲና በመሄድ የእስልምናን አቂዳ በመቀየር ማስተማር ጀመረ ፤ ከዚያ ሰሃባዎችን ለማከፋፈል ሞከረ፤ በመጨረሻም አሚር አልሙእሚኒን ዑስማን መገደል አለባቸው አለ፤ሰዪዲና ዑስማን ቤታቸው ቁጭ ብለው ቁርዓን እየቀሩ ሳለ የፊትና ሰዎች መጥተው የቤታቸውን በር በእሳት ካቀጣጠሉ ቡሃላ፤ ቤት ገብተው በሰይፍ ዘጠኝ ጊዜ ወግተዋቸው፤ ሶስቱ ለአላህ ነው ስድስቱ ለራሳችን በማለት ከፍተኛ ወንጀል ሰርተው ነበር፤ ሰይዲና ዑስማን ደማቸው ቁርዓን ላይ ፈሰሰ፤ከዚህ ቡሃላ የፊትና በርን የሚዚጋ ወንድ ጠፋ፤ የአላህ ራህመት ሆኖ ታላላቆቹ ሰሃባዎች ይህ ክስተት ከመፈጠሩ በፊት በጥቂት ጊዜ አከታትለው ታመው ሞቱ፤ በዚህም ሰበብ መዲና ውስጥ እርስ በእርስ ደም መፋሰስ ሆነ፤ይህንን ማየት ያልፈለገውና ወደ አላህ ቶሎ በፍጥነት መሄድ የፈለገው ታላቁ ሰሃቢ ሰዪዲና አሊይ አቢ እብኒ ጣሊብን አንድ መፍትሄ መጣላቸው፤ ዓቲካ!ዓቲካን ለትዳር ጠየቃት፤ ዓቲካም የነበረባት ሐዘን ሳይቀልላት ሰዪዲና አሊይ አቢ እብኒ ጣሊብን አግብታቻቸው ምን እንደሚፈጠር ታውቃለች፤ ስለዚህ ወዲያው ፍቃደኛ ሳትሆን "ያ አሊይ እኔ ቃል ኪዳን እገባላሃለሁ፤ በቅርቡ ሸሃዳን እንደምታገኝ" አለቻቸው፤ ያ አሊይ ሸሃዳን ለማግኘት እኔን ማግባት አያስፈልግህም አለቻቸው፤ ሰዪዲና አሊይ ዓቲካን በተመኛት በጥቂት ቀናት ሸሃዳን አገኙ፤ ረዲየላሁ አንሁም አጅመዒን፤ከዚህ ቡሃላ ለትዳር የጠየቃትና ለአራተኛ ጊዜ ያገባት ሰዪዲና ሑሴይን አሊይ አቢ ኢብን ጣሊብ የረሱሉላህ ሰለላሁ አሌይህ ወሰለም የልጅ ልጅ ናቸው፤ ዓቲካ ከሰዪዲና ሑሴይን ጋር በመገባታ ከረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም አማችነትን አገኘች፤ ምነኛ የታደለች ሴት ነች፤እዚህ ላይ ግን ዓቲካ እስካሁን ቤት ሆና ነበር የባሎቻን ሸሃዳ ስትሰማ የነበረው፤ አሁን ግን ሰዪዲና ሑሴይን የሄዱበት ቦታ አብራቸው በመሄድ ጂሃዱ ላይም በመሳተፍ ላይ ነበርች፤ ሸሃዳም ከመጣ ከባላ ጋር አብራ ሸሃዳን አንድ ላይ መቅመስን የምትጠላ ማን ሴት አለች፤ ነገር ግን ኩፋ በሚባለው የኢራቅ ከተማ ውስጥ ሰዪዲና ሑሴይን ዓቲካ ፊት ለፊት ይገደሉና እራሳቸውን ከዚያ አፈር ላይ ብድግ አድርጋ ያለቀሰችው ለቅሶ ገዳዮቹም ሊያዩት ያልቻሉት የሚያሳዝን ክስተት ነበር፤ዓቲካ ሀዘና የከፋ ነበር፤ ዓቲካ ከዚያን ቀን ቡሃላ ተገልላ ስትኖር አይና ይሰወራል፤ አዎ ዓቲካ እነዚያን ወጣቶች በመልካ ማርካ ሊያገባት ቤታን ጠዋፍ ያደረጉላት፤ ታላልቅ ሰሃባዎችን የማረከች፤ ብዙ ሰው በውበታ ያደነቃት ዓቲካ አይነ ስውር ሆነች፤ ኢባዳዋን አልተወችም፤ እንደገና ለትዳር የሚጠይቃትን ሁሉ ረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም አማቼ ናቸው፤ በሳቸው ላይ ማንንም አልጨምርም ብላ ተከለከለች፤እመቤታችን ዓቲካ በሂጅራ አቆጣጠር በአርባኛው አመት ምህረት ታማ ትሞታለች፤ያ ሁሉ ኸይራት ስራዎቻ፤ አኽላቃ፤ የባል ሐቅ፤ ውዴታና ፍቀራ፤ ሰብርና ዒባዳዋ........... ስንቱ ይወሳል፤ በዚህ ሁሉ ታጅባ ወደ አላህ ሄደች፤ይህቺ ሴት ለአለም ሴቶች ትምሳሊት ነች፤ ዓቲካስ ወደ አላህ ይዛ የሄደችውን ይዛ ሄዳለች፤እህቴ ሆይ አንቺስ ምን ይዘሽ ወደ አላህ የምትሄጂው??? ነው። ተ…ፈ…ፀ…መ ➥ሼር እንዳይረሱ JOIN ⇒ https://t.me/YemettiKetemaMuslimoch •┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈
Hammasini ko'rsatish...
Metti Ćity Muslim Jeme'a/የሜጢ ከተማ ሙስሊም ጀመዓ

☞ የጉዞው ተግዳሮት ብርቱ ሲሆን ብርቱዎች በርትተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ...

#ቆንጆ_ነች_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነው !! #ክፍል_ስድስት_7 ዓቲካ በረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም የአክስት ልጅ ላይ እያሳደረች የነበረው ተጽኖ ወደር አልነበረውም፤ ሰዪዲና ዙቤይርም ግን መቋቋም አልቻሉም፤ ለሁለተኛ ጊዜ ዓቲካን መስጂድ መሄዳን መጥላታቸውን ሲገልጹላት፤ ዓቲካም ይህ ጥያቄያቸው በቅናት ላይ የተመሰረተና ሊቀይሩት ይችሉ ዘንድ በለዘብታ፤ فقالت له: يا ابن العوام أتريد أن ادع لغيرتك مصلى صليت فيه مع رسول الله –صلى الله عليه وسلم- وأبي بكر وعمر؟ የዓዋም ልጅ ሆይ (በዚያን ጊዜ የሜወዱትን ሰው ሲጠሩ በአባቱ ስም ነበር) ረሱል ሰለላሁ ወሰለም ጋር አቢበክርና ዑመር ጋር የሰገድኩበትን ሙሰላዬን ለቅናትህ ብዬ እንድተው ፈለግክ ወይ ብላ ጠየቀቻቸው፤ሰይዲና ዙቤይርም ላ ወላሂ አልከለክልሺም አሉ፤ነገር ግን ያደረባቸው ቅናት ቀላል አልነበረም፤ በጣም ያሳዝናሉ፤ ለሰላት ከወጣች የምትመለስ አይመስላቸውም፤ ልባቸው አልረጋ አለ፤ማስገደድ ባህሪያቸው አልነበረም፤ አትሂጂ ማለትም አይበቃላቸውም፤ ነገር ግን ይህ ቅናት ወደሚያስገርም ድርጊት ይመራቸዋል፤ ኢኽዋኒ ወአኸዋቲ ከዚህ በታች በምነግራቹህ የሰዪዲና ዙቤይር ድርጊት ተገርማችሁ ምንም አይነት ኒጌቲቭ ኮመንተ እንዳታደርጉ፤ ሲጀመር በሃሳባችሁም ውስጥ እንዳታመጡት፤ ምክንያቱም ከረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ሰሃባዎች ጋር አደብ ሊኖረን ይገባል፤ ነቢያችንም አሌይሂ ሰላቱ ወሰላም አስጠንቅቀዋል፤ልብ ብለን እናንበው፤ عن عبد الله بن مغفل المزني _رضي الله عنه_ قال : قال رسول الله -صلى الله عليه وسلم-" الله الله في أصحابي አላህ አላህ በሰሃቦቼ (አላህን ፍሩ ሰሃባዎቼን በሚመለከት ) لا تتخذوهم غرضًا بعدي ، እኔ ከሞትኩ ቡሃላ እስልማናን ለመውጋት እነርሱን አላማ አታድርጋቸው فمن أحبهم فبحبي أحبهم እነርሱን የወደደ እኔ እንደምወደው ሆኖ ነው የሚወዳቸው و من أبغضهم فببغضي أبغضهم ، እነርሱን ያስከፋ ያስቆጣ እኔ እንደምከፋበት እንደምቆጣበት ሆኖ ነው የሚያስቆጣቸውእነርሱን አዛ ያደርገ እኔን አዛ እንዳደረገ ነው و من آذاهم فقد آذاني እኔን አዛ ያደረገ አላህን አዛ እንዳደረገ ነው و من آذاني فقد آذى الله ، . و من آذى الله فقد أوشك أن يأخذه አላህን አዛ ያደረገ አላህ ክፉኛ ሊወስደው ተቃርቦዋል አሉበሌላ ሐዲስ ላይ عن أبي هريرة _رضي الله عنه_ قال : قال رسول الله -صلى الله عليه وسلم-لا تسبوا أصحابي لا تسبوا أصحابي አስሃባዎቼን እንዳትሰድባቸው አስሃባዎቼን እንዳትሰድባቸው ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ فوالذي نفسي بيدهلو أن أحدكم أنفق مثل أحد ذهبا ما أدرك مد أحدهم ولا نصيفه ) አንዳቹህ የእሁድን ተራራ የሚያክል ወርቅ ብታወጡ የአንዳቸውንም ደረጃ አትደርሱም ነበር ወላ ግማሹን አሉከዚህ አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ቡሃላ እንግዲህ ሰሃቦችን በክፉ ማንሳት ወይም ሊያስብ የሚዳፈር ያለ አይመስለኛም፤ወደ ዓቲካ ታሪክ ስንመለስ፤ ሰዪዲና ዙቤይር ረዲየላሁ አንሁ ዓቲካ ላይ ከመቅናታቸው የተነሳ አንድ የሚያስገርም ነገር ይሰራሉ፤ አንድ ቀን የሱብህ ሰላትን ለመስገድ ወደ መስጂድ ስትሄድ፤ ሰዪዲና ዙቤይር ውዱእ አድርገው ቀድመዋት ወጡና በኒ ሰዐድ የሚባለው ቦታ ላይ አድፍጠው ጠብቀዋት፤ በዚያ ጨለማ ሰውነታን መታ አድርገዋት በፍጥነት ተሰወሩ፤ዓቲካም ደንግጣ ዞር ብላ ስታይ ማንም ዬለም፤ مالك؟ قطع الله يدك ምን ሆነሃል አላህ እጅህን ይቁረጠው አለችና በጣም ተደናግጣ የነቢዩ አሌይሂ ወሰላም መስጂድ መሄዳን ትታ ወደ ቤታ ተመልሳ ትሄዳለች፤ ሰላታንም እቤት ሰግዳ ሰዎች እንዲህ አደብ አጡ በማለት በጣም አዝና ስለደረሰባት ነገር እያሰላሰለች ሳለ ሰይዲና ዙቤይር እቤት ተመልሰው ምነው መስጂድ አላየሁሽም ይላታል፤አላህ ይርሃመክ የአብደላ አባት ካንተ ቡሃላ ሰዎች ተበላሹ፤ ዛሬ ለሴት ልጅ መስጂድ ሄዳ ከመስገድ ጋዳ ውስጥ መስገዳ ይሻላታል በማለት ከዚያን ቀን ጀምሮ መስጂድ ሄዳ መስገድ አቆመች፤ ሰዪዲና ዙቤይር ድርጊታቸው ቢጸጽታቸውም ሊቋቋሙት ያልቻሉት ስሜት እዚህ አደረሳቸው፤ ዓቲካ ሰይዲና ዙቤይርን ወዳ፤ ቤቷን አሙቃ ትዳራን አሳምራ በደስታ እየኖሩ ሳለ፤ ዓቲካን ሃዘናን ማስረሳት ሳይሆን የሚሸፍኑላት ሰይዲና ዙቤይር ከልክ ያለፈ ውዴታን እናክብካቤ በማሳየት ነበር፤ያ ነቢያችን አሌይሂ ሰላቱ ወሰላም ተንቢየው ያለፉት ፊትና መዲና ውስጥ እንደ እሳት ሲቀጣጠል ወንድሜን አሊይ ኢብን አቢ ጣሊብን አልዋጋም በማለታቸው ብቻ ሰዪዲና ዙቤይር ተቃዉሞ ከፋሲቆች ገጥማቸው መንገድ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ በዓምሩ ኢብኑ ጀርሙዝ ይገደላሉ፤ ሰዪዲና ዙቤይር መንገድ ላይ ደማቸው ፈሶ ሙጅሪሞች ያ ንጹህ ደማቸው ላይ ተራመዱ፤ ሰይዲና ዙቤይር ባላሰቡበት ወቅት ነው የተገደሉት፤ዓቲካ ፊታ ጠቆረ፤ ዙቤይር ያስጀመርከኝን ፍቅር ሳታስጨርሰኝ እንደወጣህ ቀረህ...................... በማለት ታነባ ጀመር፤ ለገዳዩ ደግሞ በግጥም ስትጠይቀው......................ሳይስበው አድፍጠህ ከሃለው መጥተህ ገድልከው፤ውጤቱን ታውቀው ነበር፤ ልገልህ ነው ብለህ ቀድመህ ብትነግረውያ ዓምሩ ስይፍህን አውጥተህ ብትሞሻልቅ ባገኘህው እጅህ ሽባ ይሁን ሙስሊም ገድለህ የሸሂድ ደም ቅጣቱ የከፋ ነውዓቲካ የሐዘን ማዕበል መታት፤ ሌት ተቀን አለቀሰች፤ ሶስት ባል ፤ ሶስት ፍቅር፤ ሶስት ትዝታ፤ ሶስት ሸሂድ..............................ሰዪዲና ዙቤይር ብዙ ንብረት ስለነበራቸው ከሌላ ሚስት የወለዳቸው ልጃቸው አብደላ ወደ ዓቲካ መጥቶ ዓቲካ ሆይ አንቺም እናታችን ነሽ የአባታችን ሐቅ ይገባሻል ነይ ውርስ ተካፊዪ ብሎ ሲጠራትየዙቤይር ትዝታ ይበቃኛል ብላ እንቢ ብላ መለሰቻቸው፤ ተመለከቱ እዚህ ላይ ጠያቂዎቹንም መላሻንም፤ ያ አላህ............አብደላም እቤት ሂዶ ተመልሶ ወደ አቲካ መጥቶ ድርሻዋን ስድስት መቶ ሺህ ዲርሃም አስረከባት፤ የአብደላን እናትንም እዚህ ላይ አደንቃለሁ፤ አይመስላቹሁም?"ሸሃዳን የፈለገ እርሳን ያግባት" ሰዪዲና አብደላህ ኢብኑ ዑመር ይቀጥላል....... ክፍል 8 ይቀጥላል ➥ሼር እንዳይረሱ https://t.me/YemettiKetemaMuslimoch •┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈
Hammasini ko'rsatish...
Metti Ćity Muslim Jeme'a/የሜጢ ከተማ ሙስሊም ጀመዓ

☞ የጉዞው ተግዳሮት ብርቱ ሲሆን ብርቱዎች በርትተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ...

#ቆንጆ_ነች_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነው። #ክፍል_አምስት( 6 ) ዓቲካ ረዲየላሁ አንሃ የመጣላትን የትዳር ጠለብ ማመን አልቻለችም፤ አሁን ግልጽ የሆነላት ነገር ቢኖር ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው የሚሆነው፤ ገና ሳታገባው ትሳሳለት ጀመር፤ አሁን አግብቶኝ ትንሽ ሳይቆይ ሸሃዳ ሊያገኝ እንዳይሆን ብቻ በማለት አሰበች፤ ነገር ግን ዙቤይር ኢብኑ ዓዋምን ደረጃውን ታውቃለች፤ የረሱሉላህ ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም የአክስት ልጅ፤ የነቢይ ሃዋሪይ፤ ታሪኩ ተወርቶ የማያልቅ ታላቅ ሰሃቢ መሆኑን ታውቃለች፤ በበድር ጦርነት ላይ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ መላኢካዎች ሙስሊሞችን እንዲያግዙ በላከበት ጦርነት ላይ ዙቤይር ኢማማው ቢጫ ነበር፤ ታዲያ ሰዪዲና ጅብሪል የመላኢካዎች መሪ ከሰማይ አወራረዱ በዙቤይር ምስል ነበር ተብሎ ይነገርለታል፤ ዓቲካ ሁሉንም ሰለ ዙቤይር ጠንቅቃ ስለምታውቅ ...... የረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ቤተሰብ ስትገባ ከዙቤይር ቢን ዓዋም ጋር ለመጋባት በመወሰን ነው፤ከኒካሃ በፊት ዓቲካ አንድ ሸርጥ ታስቀምጣለች፤ ምንድን ነው ሸርጢሽ ዓቲካ? ቤቱ በስማ እንዲጻፍ? ላ ወላሂ፤ መኪና እንዲገዛላት ወይም የፈለገችውን ለብሳ ስትወጣ እንዳይናገራት? ላ ወላሂ፤ እና ሸርጡ ምንድን ነው? እርሳ ላይ ሌላ እንዳያገባ ወይም የበፊቱን ሚስቱን እንዲፈታ? ላ ወላሂ፤ ዓቲካ ሸርጣ አንድ የአላህ ቤት መስጅድ ሄዳ የምትሰግደውን ሰዪዲና ዙቤይር እንዳይከለክላት ነበር፤ ይህ ማንም ሊነጥቃት የማይችለው የሰይዲና ዑመር ኢብኑ ኸጣብ ሃዲያ ነበር፤ ሰዪዲና ዙቤይርም በዚህ ሸርጥ ተስማምተው ዓቲካ ላይ ኒካቸውን አሰሩ፤አሁንም የመጀመሪያው ሌሊት ለዓቲካ አስቸጋሪ፤ አሳዛኝና ሆድ የሚያባባ ነበር፤ ነገር ግን ነግሮች ከቀን ወደ ቀን እየተለወጡ ይመጣሉ፤ሰዪዲና ዙቤይር በየቀኑ ለዓቲካ ያላቸው ውዴታና ፍቅር እየጨመረ ይሄዳል፤ እንዴት አይጨምርም? አኽላቃ የሚረታ፤ ውበታ የሚማርክ ያገባችውን ባል በሙሉ አላህ የደነገገባትን ሀቆች አሳምራ ሰጥታ ማታ እጃን ወደ ሰማይ ዘርግታ ያረብ የባሌን ሐቅ አማልቼ እንድሰጥ እርዳኝ ላጎደልኩትም ማረኝ የምትል ሴት ላይ እንዴት ውዴታ አይጨምርም፤ከጊዜ ቡሃላም ሰዪዲና ዙቤይር ቢን ዓዋም ረዲየላሁ አንሁ ላይ አዲስ ባህሪ ይታይባቸው ጀመር፤ ይህውም ዓቲካ ላይ መቅናት መጀመራቸው ነው፤ ያ ሰላም........ ዓቲካ የነቢዩን አሌይሂ ሰላቱ ወሰላም የአክስት ልጅና የነቢዩ ሃዋሪይ፤ በጦር ሜዳ ላይ በሰይፋቸው ጠላትን እንደ ዛፍ ቅጠል የሚያረግፉትን ጀግና፤ ሰዪዲና ጂብሪል ጦርነት ሊካፈል ሲወርድ የዙቤይርን ምስል ተመስሎ የወርደበት ታላቁ ጀግና ሰሃቢ ዛሬ ባንቺ ይቀናሉ፤ ምነኛ ሴት ነሽ?ከውዴታቸው የተነሳ እንደ ሚስት ብቻ ሳይሆን እንደ ሁሉም ነገር እየተንከባከባት የሞቀ ትዳራቸውን ይመሩ ነበር፤ ነገር ግን ምናለ ቢዘልቅ........? ሰዪዲና ዙቤይር በየቀኑ ቅናታቸው እየጎላና ከአንደበታቸው ማውጣት ጀመሩ፤ አንድ ቀን ዓቲካ መስጂድ ልትሄድ ስትወጣ፤ ያ ዓቲካ አላት፤ والله إنك لتخرجين وإني اكره ذلك «ወላሂ ከቤት የምትወጪው እኔ መውጣትሺን እየጠላሁ ነው።» አላት፤ እርሳም ከበር ተመልሳ፤ በተረጋጋ መልኩ ከፈለግክ አልሄድም አቆማለሁ በማለት ጠጋ ብላ ታባብላቸዋለች፤ ያ ሰላም........................ ያ አላህ አኽላቃችንን አሳምርልን.ተመልከቱ እሳቸው ባላቤታ ዙቤይር የሚመልሱትን፤ እንዴት እከለክልሻለሁ ስታገቢኝ ሸርጥሽ ሆኖ ብለው ከቤት አውጥተው ወደ መስጂድ ይሸኛታል #ክፍል_ሰባት_ይቀጥላል ➥ሼር እንዳይረሱ JOIN ⇒ https://t.me/YemettiKetemaMuslimoch •┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈
Hammasini ko'rsatish...
Metti Ćity Muslim Jeme'a/የሜጢ ከተማ ሙስሊም ጀመዓ

☞ የጉዞው ተግዳሮት ብርቱ ሲሆን ብርቱዎች በርትተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ...

مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَمَن يُؤْمِن بِاللَّهِ يَهْدِ قَلْبَهُ ۚ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ https://t.me/YemettiKetemaMuslimoch
Hammasini ko'rsatish...
Metti Ćity Muslim Jeme'a/የሜጢ ከተማ ሙስሊም ጀመዓ

☞ የጉዞው ተግዳሮት ብርቱ ሲሆን ብርቱዎች በርትተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ...

የዱንያ ሰው ነን ወይንስ የአኼራ❓❓ 🌴 አንድ ሰውዬ ወደ አንድ ሷሊሕ የኾነ ጓደኛው ዘንድ ገባና ✍ "እኔ ለዱንያ ከሚኖሩ ሰዎች ልሁን ወይንስ ለአኼራ ከሚኖሩ ሰዎች ልሁን ማወቅ እፈልጋለሁ" አለው ሷሊሑ፧ "አንተ ዘንድ የኾመ ብር የሚሰጥህ ሰው እና ሰደቃ የሚጠይቅህ ሰው ቢገባ የትኛውን የበለጠ ትወዳለህ?" አለው ሰውየው፧ ዝም አለ ሷሊሑ፧ "ብር የሚሰጥህን የበለጠ የምትወድ ከኾንክ አንተ ከዱንያ ሰዎች ነህ፤ ሰደቃ የሚጠይቅህን የበለጠ የምትወድ ከኾንክ አንተ ከአኼራ ሰዎች ነህ" አለው ሰውየው፧ እየደጋገመ "سبحان الله (ለአላህ ጥራት ይገባው) ማለትን ጀመረ ሷሊሑ፧ ቀጠለና "ለዚህም ነበር ከፊል ሷሊህ የኾኑ ሰዎች ሰደቃ የሚጠይቃቸው ሰው ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ እያሉ ተነስተው ይቀበሉትና «ይህ እኮ ምንም ደሞዝ ሳልከፍለው ምንዳዬን ተሸክሞ ወደ አኼራ የሚያደርስልኝ ሰው ነው» ብለው ይስሙት ነበር" አለው ሰውየው፧ "إنا لله وإنا إليه راجعون (እኛ የአላህ ነን ወደ እሱም ተመላሾች ነን)" አለ ሷሊሑ፧ እንዲህ አለው ✍ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጥ, ደጋጎች በተጓዙበት ተጓዝ ትደርስባቸዋለህ‼ ✍«እነርሱን መምሰል ባትችሉ እንኳ ተመሳሰሉ በመልካም ሰዎች መመሳሰል መዳን ነው።»‼ ✍ተጨንቆ የመጣብህ ሰው ካለ አድምጠው‼ ✍ምክንያት ይዞ የመጣብህ ሰው ካለ ተቀበለው‼ ✍ፈልጎ የመጣብህ ሰው ካለም ስጠው‼ 🌱የቀልብ መንጣት ማለት ከአቧራ አይደለም፤ ባይኾን አላህ ለወደደው ብቻ መርጦ የሚሰጠው የኾነ ስጦታ ነው‼ ብሎ መከረው። 📖ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል📖 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/YemettiKetemaMuslimoch
Hammasini ko'rsatish...
Metti Ćity Muslim Jeme'a/የሜጢ ከተማ ሙስሊም ጀመዓ

☞ የጉዞው ተግዳሮት ብርቱ ሲሆን ብርቱዎች በርትተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ...