cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አስገራሚ እዉነታዎች እና ቀልዶች😂

✔ለማመን የሚከብዱ የአለማችን 🌍እዉነታዎች ✔ስለሴቶች እንድሁም ስለ ወንዶች አንዳንድ ሚስጥርም እናወራለን ✔ ፈገግ ሚያረጉ ቀልዳ ቀልዶች ✔አስደናቂ የ እንሰሳት አኗኗሮች ✔ መሠረታዊ የጤና ምክሮች ✔ለእናንተ ጠቃሚ ያልናቸዉን ነገር ሁሉ እዚህ ያገኛሉ 💯👇👇👇👇👇👇👇👇👇 💡 #Share እና #join አድርጉ👈 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ @Afuu_Man

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
179
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

00:29
Video unavailable
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም ተነስቷል በዚህ የለም😍
Hammasini ko'rsatish...
16.26 MB
የጓደኛዬ ፍቅረኛ የመጨረሻው ክፍል 🌹🌹🌹❤️❤️❤️❤️🌈🌈 አትኩሬ ስመለከት ማራናታ ነበረች ምነው መሬቱ ተሰንጥቆ በዋጠኝ ብዬ ተመኘሁ ከይቤ ጀርባ ስለነበረች አላያትም ግን ዛሬ እንዴት ላግኝ አልሽኝ በቃ በጥንቃቄ ያጣድፈኝ ጀመር በጣም ደንግጬ ስለነበር በተቀመጠበት ጥዬው ሄድኩኝ ሁኔታዬ ግራ ስለገባው ምንም አላለኝም ወደ ኋላዬ ሳልመለከት ወጣው ቤት ስደርስ አላመንኩም ነበር ወይ ውርደት ቀለልኩ ከዛ ብዙም ሳትቆይ ማራናታ አራስ ነብር ሆና መጣች ቀናብዬ አይኗን ማየት አቃተኝ ትንሽ ጮክ ብላ ካየችኝ በኋላ ሳቋን ሐቀቀች ግራ ገባኝ ሰራሁልሽ አለችኝ ማከለት አልኳት ከዛ ሁሉንም አስረዳችኝ ይቤ እና እሳ ፍቅረኛማቾች እንዳልሆኑ እኔን ለመቅረብ ሲሉ የሠሯት ድራማ መሆኑን ነገረችኝ ከ 10ጊዜ በላይ እውነቷን እንደሆነ ጠየኳት እንባዬን መቆጣጠር አቅቶኝ እያለቀስኩ አዎን አለችኝ ከዚያ ስልኬ ሜሴጅ ገባ ይቤ ነበር ከማራናታ ጋር የተለመደው ቦታ አንድ ሰዓት ላይ እንገናኝ አለ አሌድም ብዬ ነበር መራናታ ተቆጣችኝና ተነስተን መለባበስ ጀመርን እንደዛሬ አምሮብኝ አያውቅም አይደርስ የለ ሰዓቱም ደርሥ መንገድ ጀመርን ልቤ በጣም ይመታ ነበር ስንደርስ አስተናጋጇመታ መራችን ከአንድ ያማረ ወንበር ይቤ መምጣታችንን ሲያይ ተነስቶ ጠበቀን በጣም አምሮበት ነበር ፈገግ ብሎ የሚያምር ቀይ አበባ ሰጠኝ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ አቅፎ እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝ ማራናታም መታ ሁለታችንንም አቀፈችን አሁን ላለሁበት ያማረ ህይወት ጓደኛዬን እያመሠገንኩ ኖራለሁ ::::::::::::::::::🎀🎀🎀🎀:::::::::::::: https://t.me/eketbeb
Hammasini ko'rsatish...
£$k p!c+ure

@EKE

​​ 👩‍❤️‍💋‍👩 የጓደኛዬ ፍቅረኛ 💏 💞Part 8 ❥..........🍃💐💐🍃............❥ ይቤን ወድጄዋለሁ ስልኬን ስከፍት ይሄ ነው ከምለው በላይ ሚሴጅ ልኳል ደውሎ ወረደብኝ መልስ አልሰጠሁትም የተሸነፈ ሰው ምን አቅም አለው በዚህ መሀል ማራናታ ይቤን ከዚህ ባለይ መፈተን አልፈልግም እስከ አሁን የፈተንኩት ራሱ ውስጤ በፍረሀት ነበር አለችኝ እናስ ምንድ ነው ምትይኝ አልኳትኝ በቃ እሱ ጋር ያለሽን ግኑኝነት አቁሚ አልሻለሁ ውዷ ጓደኛዬ እኔም ሀሌታ መላሽ ያድረገኝ በምትፈልጊው ሁሉ ከጎንሽ አለሁ አለችኝ በቃ ልቤ ስንጥቅ አለ ይቤ ጋር ያለኝን ግኑኝነት ማቆም ማለት ለእኔ አይታሰብም ግን እንደ ምንም ብዬ ለማራናታ ስል ማቆም እንዳለብኝ ወሰንኩ ይቤ ጋር ያለኝን ግኑኝነት አቀዘቀዝኩ ይቤ ደግሞ ጭራሽ ባሰበት ምን እንደ ሆንኩ ደጋግሞ ሲጠይቀኝ ፍቅረኛዬ ከሌላ ወንድ ጋር ሳወራ እየደበረው ነው አልኩት በሰአቱ በጣም አዘን እኔም አልቅሼ ወይም ጩሄ በወጣለኝ አልኩ ግዜው እየሄደ ነው አንድ ቀን ወደ ማምሻ አከባቢ የማላውቀው ስልክ በተደጋጋሚ ተወደለ ማነው ይሄን ታክል የፈለገኝ ብዬ ስልኩን ሳነሳው እየሩስ ናት ደነገጥኩ እየሩስ ማለት ማራናታ መጀመርያ ቀን ወደ ሆቴል ስትሄድ ተከትያት ስሄድ ሆቴሉ ላይ ሪስፔሽን ክፍል ላይ ያገኘኋት ልጅ ናት ሄሎ ስላት ድምጿ እየተቆራረጠ እየሩስ ነኝ አንዴ ካገኘሽኝ ሆቴል ቶሎ ነይ ብላ ዘጋችብኝ እኔም ደንግጬ ተዋክቤ ወጣሁ ልክ እንደ ደረስኩ ስታየኝ ደስ አላት ሰላም ብያት ምነው እንደዚህ አጣድፈሽ የጠራሽኝ በሰላም ነው አልኳት ምን ሰላም አለ ብላ ፈገግ አለች ይሄውልሽ ያደላላው ሙሉቀን ማራናታ ምትባል ልጅ እንደ መጣች ሩም 304 ትሂድ ንገርያት ብሎኝ ነው ስትል ደነገጥኩ ደላላው ከሆቴሉ አልወጣም ወደ መጠጥ ባሩ ሂዶ ነው ሩሙን የያዘው ደግሞ ያ ቅሌታም አጎቷ ነው ብላ ሳትጨርስ ማራናት ወደ እኛ ስትመጣ አየኋት ሮጥ ብዬ ጥግ ይዤ ቆምኩ እሷ እየሩሱ ጋር እያወራች ደላላው ከየት መጣ ሳልል ከኋላዋ መጥቶ አቅፎ ሰላም አላት በጆሮ ጠጋ ብሎ የሆነ ነገር ሹክ ብሏት ሄደ እሷም ወዲያው ወደ ደረጃው ወጣች ስደውልላት እያየችው ዝም ብላ መንገዷን ቀጠለች ተከትያት ወደ ላይ ወጣሁ ምንም ቃሏን ብታጥፍም ስትጎዳ ግን ቁሜ ማየት አልፈለኩም እንደምንም ሩጬ ሂጄ እጇን ይዤ ከሆቴሉ ወጣሁ ከድንጋጤ የተነሳ ምንም አልተናገረችኝም ቤታቸው ደጃፍ ላይ አድርሼ ምንም ሳልናገራት ወደ ቤት ሄድኩ በቃ ልቤ የተሰበረ ያህል ተሰማኝ ሁሉም ነገር አስጠላኝ እሷ እንደዚህ አይነት ህይወት ውስጥ መግባቷ በጣም ነው ያሳዘነኝ እሷን አጥቼ ይቤን አጥቼ እንዴት እንደ ምሆን አላውቅም ምንም የማያውቀው ይቤ ራሱ አሳዘነኝ ኢንተርኔት ሚባል መጠቀም አቆምኩ ስልኬን ዘግቼው ነው የምውል ይቤ ሲናፍቀኝ ስልኬን እከፍተዋለሁ እሱም መክፈቴን ሲያውቅ ወዲያው ይደውላል በጣም እንደ ደበረው በዛ ላይ ማራናታም ኢንተርኔት መግባት እንደ አቆመች ነገረች ይበልጥ አሳዘነኝ ከወር በኋላ ማራናታ እቤት መጣች ቀና ብላ አይኔን ማየት አቃታት ጥፋቱ እንደ ገባት ሳውቅ ተነስቼ አቀፍኳት በዚህ መሃል ግን እያወራን እያለ ይቤ እንደዘጋት እንደ በፊቱ እንደማያወራት ነገረችኝ እናስ አልኳት አይ ነገሩን ነው የነገርኩሽ እንጂ ምንም እንድታደርጊ አይደለም ግን በቃ በጣም ስለ ተሰማኝ ነው ይሄን ታክል እንደ ጎዳሁት አልታወቀኝም ነበር ስትል የሆነ ነገር ተሰማኝ ውስጤ ለይቤ ይሄ ነው ከሚባለው በላይ ልቤ ቦታ ሰጦታል ብቻ አላውቅም ነገሮች ሁሉ እያደሩ በሄዱ ቁጥር እየጠነከሩ ሄዱ አንድ ቀን ግን እንደ ምንም ብዬ ይቤን ላግኝህ አልኩት በጣም ደነገጠ እንገናኝ ብሎ ብዙ ግዜ ለምኖኛል ምን አልሽኝ እስቲ ድገሚው አለኝ ማይመቸህ ከሆነ ተው በቃ አልኩት እረ ብሎ ተርበተበተብኝ አንድ ሆቴል ተቀጣጠርን እና ተገናኘን ግን በቃ ገና ሳየው ልቤ ይደነግጣል እንደምንም ራሴን አረጋግቼ ቀስ ብዬ ቁጭ አልኩ ይቤ ጫዋታውን ጀመር እኔም የፈለኩበትን ጉዳይ ልነግረው ብዬ አይኔን ሳማትር ከሆቴሉ ኮረደር ላይ ተሸፋፍኖ የተቀመጠ ሰው ላይ አይኔ አረፈ… ╔═══❖•🍄🍄•❖═══╗ ይቀጥላል ╚═══❖•🍄🍄•❖═══╝ ❥............🍃💐💐🍃.............. https://t.me/eketbeb https://t.me/eketbeb
Hammasini ko'rsatish...
£$k p!c+ure

@EKE

​​❣❣የጓደኛዬ ፍቅረኛ📚📚 🌼🌼ክፍል ሰባት🌼🌼 📚📚📚📚 ❥............🍃🌹🍃..............❥ ከይቤ ውጭ ብዙ የማናግራቸው በተለያየ ሶሻል ሚድያ እና ግሩፖች የተዋወቅነ ወንድ ጓደኞች አሉኝ የሚገርመው እነሱም ይቤ ጋር በጣም በቀረብኩ መጠን ቀረቡኝ ብዙ ሚስጥሬን ማማክራቸው ልጆች አሉ አንደ መምህሬ የማያቸው አሉ ስጠፋ እንኳ ቀጥታ እየደወሉ ሚጠይቁኝ አሉ ይሄ ን ታክል እነሱ ጋር ትስስርን ፈጥርያለሁ ይቤ ደግሞ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ነገሮች ሁሉ ግራ እያጋቡኝ ነው በቃ ሌሎች ጓደኞቼ ለረጅም ደቂቃ ስልክ እያወራሁ ደውሎ መስመር ከተያዘበት ይናደዳል በዚህ ማራናታ ታስጨንቀኛለች በዚህ ይቤ ካላገኘውሽ ይለኛል ማራናታ ድንገት ወደ እኔ ደውላ መስመር ተይዟል ካላት ቀጥታ ወደ ይቤ ትደውላለች እሱ ጋር አለ መሆኔን ከተረዳች ምንም አትልም ድንገት እኔ ጋር ባይሆንም የሁለታችን ስልክ በተመሳሳይ ሰአት መስመሩ ከተያዘ አለቀለኝ ልትበላኝ ነው ምት ደርሰው ብቻ ሁሉም ነገር አከቅሜ በላይ ነበር አንድ ቀን ግን የፈራሁት አልቀረም ካላገኘውሽ ሞቼ እገኛለሁ አለ እኔም እንደምንም ብዬ ለማራናት ሁኔታውን ነገርኳት በጣም ደነገጠች አብረን እንሄዳለን አለችኝ ምን ብለሽ እስከ አሁን እኔነኝ ሳስፈትንህ የነበርኩ ልትይው ነው አልኳት ሁኔታዋ በጣም አናደደኝ እሺ በቃ ግን እጅሽ ላይ ቀለበት አድርገሽ ነው ምትሄጂ አለችኝ ሳቄን አልቻልኩም ማሽላ እያረረ ይስቃል አለ የሀገሬ ሰው እሺ ደስ እንዳለሽ አልኳት ልክ በተቀጣጠርንበት ቀን ልንገናኝ ብለን አንድ ካፌ ላይ ተቀጣጠርን ልክ ለባብሼ እንደወጣሁ ማራናታ ከየት መጣች ሳልል ፊቴ ላይ ተገትራለች እንዴ ወዴት ነው እኔኮ ምሄደው ብዬ ሳልጨርስ ለሸኝሽ ብዬ ነው እግረ መንገዴን እኔም የምሄድበት ቦታ አለኝ ስትል ውስጤ እየሳቀ አብረን ሄድነ ካፌው አከባቢ ስንደርስ ተላያየን ልክ ወደ ካፌው እንደ ገባሁ በምልክት ጠራኝ የእውነት ለመናገር ፎቶውን ካየሁት በላይ ውበቱ ገረመኝ ማራናታ ወዳም አደል አንደዚህ የሆነችብኝ አልኩ በልቤ ሰላምታ ተለዋውጠን ትንሽ እንደ ተጫወትን ስልኩ ጠራ እሱ ወሬውን አላቆመም ስልኩን አንሳው እንጂ አልኩ ባላየውም ማን እንደ ሆነ ሰለ ማውቀው ነው ብሎ ሄሎ ማርቲ አለ ማራናታ እንደ ሆነች ገባኝ ቤቲ ያልኩሽ ልጅ ጋር የተለመደ ካፌ ውስጥ ነኝ ብሎ ዘጋባት እያወራን ሁለት ዲቂቃ ሳይሞላን ማራናታ ፊቴ ላይ ቁማለች በድንጋጤ ውሀ ሆንኩ ቀና ብዬ አይኗን እንኳ ማየት አቃተኝ ተነስቶ ሰላም አላትና ተዋወቅያት ማራናታ ያልኩሽ ልጅ እሷ ናት አለኝ አይኔን አፍጣ እያየች ለሰላምታ እጇን ዘረጋችልኝ ወይኔ አምለኬ ድረስ አልኩ በልቤ ነገሩን ተመካክረን ብናደርግም ግን ይሄን ታክል ገፅታዋንማ አትቀይርብኝም አልኩ በልቤ አንቺ ተዋወቅያት እንጂ ሲለኝ ከሀሳቤ አነቃኝ ፈገግ ብዬ ሰላም አልኳት እኛ ጋር ቁጭ አለች በዛ ቅፅበት ስልኬ ሲጠራ ማን እንደ ሆነ እንኳ ሳላይ ስልክ ላናግር ብያቸው ወጥቼ በዛው ቀረሁ ስልኬን ወዲያው አጠፋሁት ከምንም በላይ ስላየሁት ደስ ብሎኛል ግን በዛው ልክ ልቤ በጣም ተረበሸ ስልኬን ድጋሚ ለሳምንት ዘጋሁት ማራናታ እንድከፍተው ብትጨቀጭቀኝም ጆሮ አልሰጠኋትም ልቤን እንደ አጣሁት ገባኝ ምንም ይሄን ነገር ወድጄ ባላመጣውም ስህተቱ የእኔ እንደ ሆነ ቢገባኝም ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም አይንን ከሚያየው ነገር መጋረድ ይቻላል ልብን ግን ከሚሰማው ነገር ማስቆም አይቻልም ይቤን ወድጄዋለሁ ስልኬን ስከፍት ይሄ ነው ከምለው በላይ ሚሴጅ ልኳል 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ ይቀጥላል ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ❥............🍃🌹🍃..............❥ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 https://t.me/eketbeb https://t.me/eketbeb
Hammasini ko'rsatish...
£$k p!c+ure

@EKE

​​📚የጓደኛዬ ፍቅረኛ🌺 ❤️❤️ክፍል ስድስት❤️❤️ 🌼🌼❥............🍃🌹🍃..............❥ አንድ ቀን ጥዋት ላይ ማራናታ ጋር ስለ እሱ እያወራን አሁን የመጨረሻ አንድ ነገር ተባበሪኝ አለች ደነገጥኩ ምን አልኳት በፍረሀት ውስጥ ሁኜ ለአንድ ሳምንት ስልክሽን አጥፊልኝ አለች ምን አልኳት በጣም ደነገጥኩ አዋ ምነው ችግር አለው ምን አስደገጠሽ አለችኝ አየተርበተበትኩ የግዴን እረ የለም ባንቺ ምክንያት ከኢንተርኔት ልለይ ነው እንዴ አልኳት ፈገግ እያልኩ እስካሁን ካስቸገርኩሽ አይበልጥም አለች እሺ በቃ በኋላ እዘጋዋለሁ አልኳት በቃልቤ ከምናገረው በላይ ተርብሿል ነገሩ አልገባኝ ቢል ለተወሰነ ሰአት ብቻዬን ቁጭ አልኩ ይቤን ወድጄው ነው እንዴ አልኩ የእውነት ይሄ ውስጤ ላይ ተፈጥሮ ከሆነ እኔ ባለጌ ሰው ነኝ እንዴት ጓደኛዬ ላይ ተደርቤ እላለሁ በልቤ ብዙ ነገር አመላለስኩ መጨረሻ ላይ አንደ ምንም ብዬ ይቤን ለአንድ ሳምንት ፀበል ልሄድ ስለ ሆነ አልገባም ብዬ ሪከርድ አድርጌለት ወጣሁ የእውነት ለመናገር አይደለም ከተላመዱት ሰው ይቅርና ትናት ካወቁት ሰው ጋር ለአንድ ቀን መለያየት ራሱ ይከብዳል ይቤ ለደቂቃ ከሀሳቤ አልጠፋም ሶስተኛው ቀን ላይ አልቻልኩም በቃ ማንም ወንድ እንደዛ ናፍቆኝ አያውቅም በመሀል ማራናት ደውላ ጠራችኝና አንድ ካፌ ላይ ተገናኘን እና ይቤ እንደ ተቀየረባት ትነግረኝ ጀመር ይቤን ስተዋወቀው ስሜን ቤቲ ነበር ያልኩት ቆይ ምኑ ነው የተቀየረብሽ አልኳት አሰር ግዜ ቤቲ ናፈቀችኝ ይለኛል በቃ ወሬው ሁሉ ስላንቺ ነው በቃ ውስጤ ፍርቷል የገዛ ፍቅረኛዬን ፈተንኩ ብዬ እንዳላጣው እየፈራሁ ነኝ አለችኝ እኔ መጀመርያም ነግሬሻለሁ እኔ ከዚህ ውስጥ የለሁበትም ስላት ዋናው ተዋናይ ማን ሆነና አለችኝ ደነገጥኩ በተቀመጥኩበት ጥላኝ ሄደች እንደ ምንም ብዬ ተከትዬ አብሬ ወጣሁ ረዳኋት ብዬ ጭራሽ ፍቅርዋን ላፍርስባት ብዬ በጣም ተሰማኝ ቀኑም ደረሰና ልክ በሳምንቱ ስልኬን ስከፍተው.. ይሄ ሚሴጅ አንደ ጉድ ይገባ ጀመረ በጣም ብዙዋቹ መልዕክት ልኮልኝ ነበር ከሁሉ ግን ቀድሜ የሮጥኩ ወደ ይቤ ሚሴጅ ነው ገና ማንበብ ሳልጀምር ቀጥታ ደወለ ሄሎ ከማለቴ ምን በደልኩሽ ምን አደረኩሽ እያለ ይወርድብኝ ጀመር እርግጠኛ ነኝ ይሄድሸበት ፀበል አላዳነሽም አለኝ አልገበኝም አልኩት በናፍቆት እንዲ እየተቀጣሁ እንዲህ እያሳመምሽኝ ምዕረት መፈለግሽ ነዋ አለኝ እእ እንደ እሱ ከሆነ መቀጣት ሲያንስህ ነው አልኩት አቤት ሲል አዋ የራሱን ፍቅረኛ ትቶ የሰውን ፍቅረኛ በመናፈቅ ነዋ አልኩት በዚህ ተሳስቀን አለፍ ነው ስላገኘሁት ብቻ ቀኑ ደስ ብሎኝ ዋለ ቀናት እየገፉ ሄደ ይቤ ጋር ያለኝን ግኑኘነት እያጠበቀው ሄደ ከይቤ ውጭ ብዙ የማናግራቸው በተለያየ ሶሻል ሚድያ እና ግሩፖች የተዋወቅነ ወንድ ጓደኞች አሉኝ የሚገርመው እነሱም ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ ይቀጥላል ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ❥............🍃🌹🍃..............❥ @liyuko1 @liyuko1
Hammasini ko'rsatish...
​​🌹🌹የጓደኛዬ ፍቅረኛ📖📖 🥀🥀 ❄️❄️ክፍል አምስት❄️❄️ ❥............🍃🌹🍃..............❥ ማራናት ስለ እሱ ባህሪ የነገረችኝ ነገር እና እኔ ከቀረብኩት በኋላ ያየሁበት ባህሪ በጣም ይለያያል ልጁ ሲበዛ ግልፅ ነው ማራናታ ምትባል ፍቅረኛ እንዳለችው ነገረኝ በጣም እንደ ሚወዳት እሷ ግን ተጠራጣሪ ነገር እንደ ሆነች ነገረኝ ይሄን ማወቅህም አንድ ነገር ነው አልኩ በልቤ በዚህ ሁሉ ነገር እኔ እና ማራናት አንደ ማንተዋወቅ ነው የሚያውቀው አንድ ቀን ግን ማራናታ ልክ እንደ መሸ ጠብቃ ቤት መጣችና እንደ ለመደችው ከላይ ለብሳ የነበረውን አውልቃ እርቃን እስክት መስል በጣም አጭር ሚኒዋን ለብሳ ወጣች እኔም ደነግጬ ስለ ነበር ምንም አልተናገርኳትም ድጋሚ እንደዚህ አይነት ጥፋት ላትሰራ ቃል ገብታልኝ አደል እንዴ አልኩ ተመልሳ መጣችና ይቤ ቀጥሮኝ እኮ ነው አልነገርኩሽም አደል አለች ስለ ቸኮልኩ እኮ ነው ብላ ፈገግ አለች ትዝ ሲለኝ ይቤ ዛሬ ልታገኘኝ እንደ ምትፈልግ ነግራኝ ነበር ብሎኝ ነበር እሱ ጋር ከሆነስ ደስ ይለኛል ብዬ እኔም አንድ የሰፈሬን ልጅ ይዣት ወክ ወጣን ሰአቱ ከምሽቱ አንድ ሰአት አከባቢ ነው ብዙም ሳንቆይ ይቤ ደወለልኝ በጣም ደነገጥኩ እሷ ጋር ከሆን ለምን ደወለልኝ ብዬ ብዙ ሀሳብ መጣብኝ ልክ ሊዘጋ ሲል አነሳሁት መጥቼ ላንሳልሽ አለ ካላስቸገርኩህ አልኩት መናናቅ ይሉሻል ይሄን ነው አለ ክብር ከአንደበት በሚወጣ ነው ብለህኝ ነበር እኮ ስለው ሳቀብኝ የነገሩሽን አትረሺም ሲለኝ ያደረጉኝንም እንደዛው አልኩት እዚጋ ሳቁን አልቻለም ደህና ቀልደኛ ወጦሻል የትነሽ አለኝ ፍቅረኛዬ ጋር ወክ እያደረግን ስል ምን አለ አዋ ምነው ዛሬ ቀጠሮ አለኝ በለህ ነበር እኮ ስለው አዋ ባክሽ ነበረ ግን አልተመቻትም ሲለኝ ወዲያው ዘግቼበት ደወልኩላት የትነሽ ስላት አሁን ወደ ቤት እየሄድኩ ነኝ እቤት መጥቼ የለሽም አለችኝ እና አደውይልኝም ስላት ወክ ወጠሽ ይሆናል ብዬ ነው ብላ ዘጋችብኝ እዚህ ጋ ልቤ ደነገጠ ማራናታ የደበራት ነገር እንዳለ ገብቶኛል በሰአቱ ምንም አልተናገረችኝም ይቤ ጋር ይሄ ነው ከሚባለው በላይ ተግባባን በቃ ምርጥ ልጅ አይገልፀውም በቃ በዚህ መሀል ግን አንድም ቀን ስለ ራሴ ስሜት አስቤም ሆነ ተጨንቄ አላውቅም ለራሴ እስኪ ገርመኝ ድረስ ብዙ ነገሬን ቀየረው አንድ ቀን ሌሊት በዋትስ አፕ ይቤ ጋር እያወራን እያለ ማራናታ ቀጥታ ደወለችልኝ ከደቂቃዋች በፊት በመሀል ዋትስ አፕ ላይ እያወራሁ ስልክ እየገባብኝ እንደ ነበረ አይቻለሁ ግን ቁጡሩን ስለ ማላውቀው መልሰ አልሰጠሁም ልክ አንስቼው ሄሎ እንዳልኳት ምነው ፍቅረኛሽ አደረግሽውሳ ሌላው ቢቀር ያንታክል ስደውልልሽ አንዴ አታነሽልኝም እንዴ ብላ አጉረመረመችብኝ በጣም ስለ ተናደድኩ ምንም አላልኳትም ይቅርታ ብዬ ስልኩን ጭራሽ ዘጋሁ የዛን ሌሊት ሁኔታዋ በጣም አናዶኛል በርግጥ ይቤ ጋር ከጓደኝነት የዘለለ በመሀከላችን ምንም ነገር አልተፈጠረም ነበረ ግን ቀን ላይ ሳላገኘው ከዋልኩ ቅር ይለኛል በዛ ላይ ማራናታ በየቀኑ እሱን እንድጠይቅላት የምትፈልገውን ነገር ገና ልጠይቀው ስጀምር አሁን ሰለ እሷ ተይና ስለ እኔ እና አንቺ እናውራ ይለኛል ነገሩ ትንሽ ግራ ሲያጋባኝ ጠፍቼ እውልና ቀጥታ ሲደውልልኝ ፍቅረኛዬ ጋር ነኝ ብዬ እዘጋበታለሁ ማታ ላይ ሁሌም ኦንላይን ካጣኝ ቀጥታ ይደውላል እንደዚህ እያልን ወራትን አስቆጠርን አንድ ቀን ጥዋት ላይ ማራናታ ጋር ስለ እሱ እያወራን አሁን የመጨረሻ አንድ ነገር ተባበሪኝ አለች ደነገጥኩ ምን አልኳት ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ ይቀጥላል ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ❥............🍃🌹🍃.............. https://t.me/+UWdCbaB_07g1OTk0
Hammasini ko'rsatish...
አስገራሚ እዉነታዎች እና ቀልዶች😂

✔ለማመን የሚከብዱ የአለማችን 🌍እዉነታዎች ✔ስለሴቶች እንድሁም ስለ ወንዶች አንዳንድ ሚስጥርም እናወራለን ✔ ፈገግ ሚያረጉ ቀልዳ ቀልዶች ✔አስደናቂ የ እንሰሳት አኗኗሮች ✔ መሠረታዊ የጤና ምክሮች ✔ለእናንተ ጠቃሚ ያልናቸዉን ነገር ሁሉ እዚህ ያገኛሉ 💯👇👇👇👇👇👇👇👇👇 💡 #Share እና #join አድርጉ👈 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ @Afuu_Man

መናገር ፈርቶ እንጂ ግራ ስለገባው፣ የብዙዎች ብሎክ ፎንቃ አለ ከጀርባው!
Hammasini ko'rsatish...
ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብዬ በሀሳብ እየተብሰለሰልኩ ሳለ ከቢሮው ውጪ "ተካልኝ ተካልኝ ሴት ልጅህ አደጋ ደርሶባት ሆስፒታል እንደገባች ሞታለች "የሚለውን ድምፅ ሰማሁ ይሄንን ስሰማ የቢሮውን መስኮት ከፍቼ ዘልዬ ወጣሁ... #ልክ_ዘልዬ_እንደወጣው ቢሮዬ 10ኛ ፎቅ መሆኑ ትዝ አለኝ ... ከዚያም ጭራሽ ሴት ልጅ እንደሌለኝ አስታወስኩ ከዚያም ስሜ ተካልኝ እንዳልሆነም አስታወስኩ... ከዛም ስልኬ አንስቼ ይሄን ፖሰትኩ😝😁
Hammasini ko'rsatish...
​​ 🌹የጓደኛዬ ፍቅረኛ📖 🔥ክፍል ➍ 💘 ❥............🍃🌹🍃..............❥ ለምን መጀመርያ አልደውልላትም ብዬ ደወልኩላት ስልኳ ይጠራል ከዛው ክላስ ውስጥ ነው አላነሳልኝ አለች ትግስቴ አለቀ ከውስጥ ሳቅ ነገር ይሰማኛል በሩን እንኳኳሁት በዚህ መሀል ደላላው ሙሉቀን ከየት መጣ ሳልል አንቺ ፈጣጣ ምን ትሰርያለሽ እዚህ ብሎ ለማውራት እንኳ ግዜ ሳይሰጠኝ ይዞኝ ወጣ ቆይ ምን ነካህ አልኩት ባክሽ ዝም በይ በዚህ ሰአት መቼም ለዝናና መጣሁ አትይኝም ብሎ አጉረመረመ ታናሿ እህቴ ጋር ስላለሁ ልናገረው አልፈለኩም በዝምታ አለፍኩት ያን ቀን በጣም ነበር የተሰማኝ ነገውን አክስቴን ጥየቃ ወደ ጎንደር ሄድኩ በተደጋጋሚ ብትደውልልኝም ላናግራት ግን አልቻልኩም ገና ሳለወራት እንባዬ ይቀድመኛል ማራናት ማለት ሁሉ ነገሬ ናት ከጓደኛም በላይ እህቴ ናት መቼም ከራሳቹ በላይ የምትወዱት ሰው የምታውቁትን ነገር ሲደብቃቹ ሚሰማቹን ስሜት ታውቃላቹ ልክ በሳምንቱ ጎንደር መጣች በፊት አክስቴን ለመጠየቅ አብረን ነበር ምንመጣ ስለ ሁሉም ነገር ከእግሬ ስር ወድቃ ይቅርታ ጠየቀችኝ ባጠይቀኝም በእሷ የሚጨክን ልብ የለኝም ከምንም በላይ ሴትነቴን እንድወደው ያደረገችኝ ልጅ ናት ታድያ እንዴት በራሷ ላይ ይሄ ነገር መጣ ብዬ ጥያቄ ፈጠረብኝ በዚህ መሀል ወደ አ/አ በተመለስን በወራችን አንድ ነገር ላስቸግርሽ ነው እባክሽን እንቢ እንዳትይኝ አለችኝ ደነገጥኩ ምንም ነገር አድርጊልኝ ለማለት ቀጥታ እንጂ ምትነግረኝ ለምናኝ አታውቅም እኔ ነገሩ ትንሽ ከበድ ያለ እንደሆነ ቢገባኝም የምችለውን ሁሉ ልረዳት እንደ ምችል ነገርኳት እሺ በቃ ነገሩን ባለፈው ጀምሬልሻለሁ የምወደው ልጅ እንዳለ ነግሬሽ ነበር አሁን ላይ አብረን እንድን ሆን በጣም ይፈልጋል እኔ ደግሞ ምንም ያህል ብወደውም ግን በቃ በራሴ መንገድ ደግሞ ልፈትነው ፈልጌ ነው አሁን አንቺ የምትረጂኝ ልክ እንደ ምትወጂው መስለሽ እንድትቀርቢው ነው ምፈልግ አለችኝ በጣም ደነገጥኩ አንቺ አብደሻል እንዴት አፈቅረዋለሁ በምትይው ሰው እንደዚህ አይነት ነገር ታስቢያለሽ አይከብድም አልኳት ታድያ የእህቴ ታሪክ እኔ ላይ እንዲደገም ትፈልጊያለሽ እንዴ አለችኝ በጣም ግራ ገባኝ እህቷ ከዚህ በፊት ፍቅረኛዋ የገዛ ጓደኛዋን አግብቷታል ይሄን ነገር ሁሌም ትዝ ስለ ሚላት ወንዶችን ትጠራጠራለች ይሄን ነገር ላደርገው እንደ ማልችል ላስረዳት ሞከርኩ ግን ምንም ልሰማኝ አልቻለችም ጭራሽ ለአንድ ሳምንት ዘጋችኝ በዚህ ቀን በምፈልገው ካልረዳሽኝ መቼ ልትረጂኝ ነው አለችኝ ሁሉም ነገር ቢከብድም እሷን ላለማስከፋት ስል እሺ አልኳት ግን የሆነ ነገር ቢፈጠር ሀላፊነቱን አንቺ ነሽ ምትወስጂው አልኳት እንዴ FBI የስለላ ድርጅት ይውሰድ እንጂ እኔ ምን ቤት ነኝ አለች እየሳቀች እኔ ነግሬሻለሁ ብያት ሰልኩን እና ሚጠቀማቸውን ሶሻል ሚድያ ተቀብዬ ተለያየን ልክ በሁለተኛ ሳምንታችን የተወሰነ ተግባባን ልጁ ፎቶውን አይለቅም ግን ጫዋታው ጥርስ አያስከድንም እኔም ብዙ ወንዶች ጋር እቀራረባለሁ ለዛም ይመስለኛል የወንድን ልጅ ባህሪ አይከብደኝም በዚህ ሁሉ መሀል የምናወራቸውን ነገሮች ለማራናታ እልክላታለሁ በዚህ መሀል እንደ ተለመደው ወደ ዋትስ አፕ ስገባ ባማላውቀው መንገድ ልቤ ድንግጥ አለ ለመጀመርያ ግዜ ፎቶውን ፕሮፋይ አድርጎታል ለምን እንደ ደነገጥኩ ምንም አልገባኝም በርግጥ ማራናታም ብትሆን ስለ ልጁ መልክ እና ቁመና ነገረችኝ እንጂ ፎቶውን አላሳየችኝም ነበር ልጁ ቆንጆ የሚባል ወንድ ነው በዚህ ሁኔታ ይቤ ጋር በጣም ተግባባን ከሚነገርለት በላይ ቀልደኛ ነው ግን ማራናት ስለ እሱ ባህሪ የነገረችኝ ነገር እና እኔ ከቀረብኩት በኋላ ያየሁበት ባህሪ በጣም ይለያያል ልጁ ሲበዛ ግልፅ ነው ማራናታ ምትባል ፍቅረኛ እንዳለችው ነገረኝ በጣም እንደ ሚወዳት እሷ ግን ተጠራጣሪ ነገር እንደ ሆነች ነገረኝ ይሄን ማወቅህም አንድ ነገር ነው አልኩ በልቤ በዚህ ሁሉ ነገር እኔ እና ማራናት እንደ ማንተዋወቅ ነው የሚያውቀው አንድ ቀን ግን....... ╔═══❖•🌺🌸•❖══ይቀጥላል ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ ❥............🍃🌹🍃..............❥ https://t.me/+UWdCbaB_07g1OTk0
Hammasini ko'rsatish...
አስገራሚ እዉነታዎች እና ቀልዶች😂

✔ለማመን የሚከብዱ የአለማችን 🌍እዉነታዎች ✔ስለሴቶች እንድሁም ስለ ወንዶች አንዳንድ ሚስጥርም እናወራለን ✔ ፈገግ ሚያረጉ ቀልዳ ቀልዶች ✔አስደናቂ የ እንሰሳት አኗኗሮች ✔ መሠረታዊ የጤና ምክሮች ✔ለእናንተ ጠቃሚ ያልናቸዉን ነገር ሁሉ እዚህ ያገኛሉ 💯👇👇👇👇👇👇👇👇👇 💡 #Share እና #join አድርጉ👈 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ @Afuu_Man

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.