cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

🇵🇸 ‏ፍልስጢን ‏🇵🇸

🇵🇸 I DREAM OF A DAY TO SEE A FREE PALESTINE ˚˚˚ ፍልስጢናውያኖች ስለ ሙስሊሙ ሁሉ ኡማ ክብር ታሪክ ንብረት እና ማንነት ሲሉ ነፍሳቸውን እየገበሩ ያሉ ጀግናና ፅኑ ህዝቦች ናቸው።ጉዳያቸው ጉዳያችን ህመማቸው ህመማችን ሊሆን እያንዳንዳችን ስለ ፍልስጢን ያገባናል ይመለከታል!እነሱ ከኛ እኛም ከነሱ ነን🤎! ˚˚˚ ስለ ፍልስጢን ብቻ😉!

Ko'proq ko'rsatish
Efiopiya2 814Amxar2 705Toif belgilanmagan
Reklama postlari
3 236
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-337 kunlar
-14030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ከሪም ዩኑስ ለ 40 አመት በፅዮናዊያን እስር ቤት ታስሮ ከቆየ ቡሀላ በዛሬው ቀን ተፈቷል.....ምናምን ብለህ
Hammasini ko'rsatish...
╔═══════════════╗ ኢዘዲን አልቀሳም ╚═══════════════╝ እሱ ከሶሪያ ወደ ፍልስጤም በመምጣት የራሱን የትግል እንቅስቃሴ የጀመረ ድንቅ ሙጃሂድ ነው፡፡ የመንግሥት ሠራተኛ በመምሰል በብዙ የፍልስጤም ክልሎች እየተዘዋወረ በአምስት አምስት አባላት የተደራጁ ህዋሳትን በሰፊው ያዋቀረው ኢዘዲን አልቀሳም ነው፡፡ ኢስላማዊ ህግጋት የትግሉ መመሪያ መሆን እንዳለባቸው አስተምሯል፡፡ ብቸኛው የነፃነት መንገድም ጂሃድ ፊ ሠቢሊላህ መሆኑን አስምሮበታል፡፡ አፅንዖትም አድርጎበታል፡፡ ይህ በኢዘዲን አልቀሳም የተደራጀ የህቡዕ ንቅናቄ በዓይነቱ ለየት ያለና በዓረብ ፍልስጤሞች የትግል ታሪክ ትልቁ የመስዋዕትነት ንቅናቄ ሆኖ ዘመናትን ተሻገረ፡፡ ማዘዣ ቢሮዎቹ ደሃው ህዝብ በሚበዛበት የኢያሪኮ ከተማ ነበር፡፡ በአካባቢው ላይ ተቀባይነት እያገኘ ሲመጣ አደረጃጀቱን አሰፋ፡፡ የዳዕዋ፣ የወታደራዊ ሥልጠና፣ የአቅርቦት፣ የኤሌክትሮኒክስና የውጭ ግንኙነት አካላትን በመፍጠር አቋሙን ይበልጥ አጠናከረ፡፡ እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1935 ኢዘዲን አልቀሳም የአብዮቱን መጀመር ይፋ አደረገ፡፡ ይህም የሆነው ሠላማዊ መፍትሄ የማፈላለጉ ጥረት በተደጋጋሚ ተሞክሮ ያለውጤት መቅረቱ እውን ከሆነ በኋላ ነበር፡፡ የአብዮቱን መጀመር ተከትሎ በቀሳም ታጣቂዎችና በእንግሊዝ ጦር መካከል ተከታታይ ግጭቶች ተካሄዱ፡፡ ብዙ ፍልሚያዎች ተደረጉ፡፡ አልቀሳም ማፈግፈግ ግድ ሆነበት፡፡ ከተወሰኑ የጦር ጓዶቹ ጋር አንድ ቦታ ላይ ከበባ ተደረገበት፡፡ እጁን በሰላም እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ አልፈቀደም፡፡ በተከተለው የተኩስ ልውውጥ አቅጣጫዋ በውል ያልተለየ ጥይት አገኘችው፡፡ ተገደለ፡፡ በተቀሩት ጓዶቹና በእንግሊዝ ጦር መካከል የከረረ ውጊያ ተካሄደ የሞቱት ሞተው የተቀሩት ጠላት እጅ ላይ ወደቁ፡፡ አልቀሳም የመሰዋቱ ዜና ሲሰማ መላው ፍልስጤም ተላወሰ፡፡ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ለፍልስጤማዊያን ሌላ የትግል ቃል ኪዳን ማሰሪያ ቀን ሁኖ ዋለ፡፡ የቀሳም ንቅናቄ በዓላማውና በተነሳሽነቱ ረገድ በዓይነቱ የመጀመሪያ፣ በአይሁዶችና በእንግሊዞች ላይ በቀጥታ ያነጣጠረ ወታደራዊ ንቅናቄ ነበር፡፡ኢዘዲን አልቀሳም ለፍልስጤም ነፃነት መዋጋትን ሊላህ ብሎ ኒያው አድርጎ ከሶሪያ ወደ ፍልስጤም በመምጣት ኑሮውን እዚያው ያደረገ አላህን ፈሪ ሰው ነበር፡፡ እሱ ባቀጣጠለው ስውራና በከፈለው መስዋዕትነት በፍልስጤሞች ዘንድ የላቀ ተነሳሽነት ተፈጠረ፡፡ ህዝቡ ተቀሰቀሰ፡፡ በእርግጥም እሱ ያመላከተው የትግል መንገድ፣ የውጊያ ስልትና የተጋፋጭነት አቋም ትምህርት ሰጪ ነበር፡፡ የአይሁድ/ እንግሊዝን ጣምራ ኃይል ጂሃድን መርሁ ባደረገ ስሌት መዋጋት እንደሚያስፈልግ በሁሉም ፍልስጤማዊ ዘንድ እየታመነበት መጣ፡፡ እስከዛሬም ድረስ ቀሳም በሚል ፅሑፍ አናታቸው ላይ በማሰር መፋለሙን ተያያዙት። በቀሳም መሞት የፍልስጤም አብዮት አብሮ አልሞተም፡፡ ነገሮች ቤንዚን እንደተርከፈከፈበት እሣት ይበልጥ ተቀጣጠለ፡፡ የ1936ቱ የረዘመ አብዮት ፈነዳ፡፡ የሥራ ማቆም አድማ፣ ተገዳዳሪ ሠልፍ፣ ለቅኝ አገዛዝ ህጎች አልታዘዝ ባይነት፣ የዚህ አብዮት ዓይነተኛ መለያዎች ነበሩ፡፡ ህዝባዊ አመጹ ብረታዊ ድጋፍም እየታከለበት ቀጠለ፡፡ ሁኔታው በፍልስጤሞች ወገን ባጭሩ ከላይ የተወሳውን ዓይነት ገጽታ ሲኖረው በአይሁዶች በኩል ደሞ የተጀመረው አፍራሽ ድርጊት በእንግሊዝ ጦር ሽፋን ሰጪነት እንደቀጠለ ነበር፡፡ በ1940ዎቹ ይበልጥ እየተጠናከረና ዓይን እያወጣ የመጣው የጽዮናዊያን እንቅስቃሴ ጭፍን ደረጃ በመድረስ የ1948ቱን የአይሁድ መንግሥት (Jewish state) ምሥረታ እውን አደረገ፡፡ ፍልስጤሞች ይህን ፈጣጣ ድርጊት በይሁንታ አላለፉትም፡፡ በቁጥርና በትጥቅ ከፍ ብሎ ተጠናክሮ ከተጋረደባቸው የእንግሊዝ ጦርና የአይሁድ ሠፋሪ ታጣቂ ኃይል ጋር እጃቸው ላይ ባለ ነገር ሁሉ ተፋለሙ፡፡ የተቀሰቀሰው የህዝበ ፍልስጤም ቁጣ በዋዛ እንደማይበገር የተረዱት እንግሊዞችና የአይሁዶች ሠፋሪ የተነሱበትን ግዛት የማስፋት እቅድ ዳር ለማድረስ ሲሉ እስከዛሬ ድረስ ጠባሳው ያልሻረውንና በሙስሊሙ ዓለም በተለይም ዓረብ ፍልስጤም ዘንድ መሪር ትውስታ ያስከተለውን አንነክባ ተብሎ የተሰየመውን የሜይ 15/1948ቱን አስከፊ ድርጊት በፍልስጤም ሠላማዊ ህዝብ ላይ ፈፀሙ፡፡ ╔═══════════╗ @palestine_history @palestine_history @palestine_history ╚═══════════╝
Hammasini ko'rsatish...
ሺ ጊዜ የንግግር ጠቢብ ቢኮንም የፍልስጤሞችን ጀግንነት በሰው ልጅ ቋንቋ መግለጽ አይቻልም ┈┈❈••✦ ✾ ✦••❈┈┈ የ19 ዓመቱ መሽቀርቀር የሚወድ እና ብዙ ጊዜ ሰልፊ ፎቶ መነሳት የሚያስደስተው አዳዲስ ልብሶችና እስማርት የሞባይል ስልኮችን የሚቀያየር ዑመር አቡ ለይሊ የተባለ ወጣት ከወደ ፍልስጤም ለመስጂደል አቅሳ ክብር ህይወቱን አሳልፎ ሰጠ። የቱንም ያክል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የማረከው ወጣት ቢሆንም በኢስላም ላይ ያየውን ውርደት አይቶ ለማለፍ ዘመናዊ ቁሶቹ አባብለው እንዲታገስ ሊያደርጉት አልቻሉም። የመስጂደል አቅሳ መደፈር አንገበገበው። ወደ አቅሷ ጉዞ ጀመረ። የመስጂዱ በር በእስራኤል ወታደሮች መዘጋቱን ተመለከተ። በሩን ክፈቱልኝ ሲልም ጠየቀ። ወታደሮቹም አንከፍትልህም ነበር መልሳቸው። መስጂዱ የእኛ ነው እናንተ ስለዚህ በርም ሆነ ስለ መስጊዱ ምን አግብቷችሁ ነው አዛዥ የሆናችሁት? በመለት ጮኸ። እንደማይከፍቱለት ነገሩትና እንቢ ካለ እርምጃ እንደሚወስዱበት አስፈራሩት። ከመስጂዱ ትንሽ ራቅ ብሎ ከተጓዘ በኋላ አንዱን የአይሁድ ወታደር መሳሪያውን ቀምቶ አካባቢው ላይ ባሉ የእስራኤል ነፍሳት ላይ ሁሉ በራሳቸው ጥይት ገደላቸው። እሱን ለማግኘት ከ300 በላይ የእስራኤል ጦር ተሰማራ። በመጨረሻ በአንድ ከሀዲ ፍልስጤማዊ ጠቋሚነት ተደብቆ የነበረበትን ቦታ የእስራኤል ወታደሮች በከባድ መሳሪያ ሳይቀር መደብደብ ጀመሩ። እጅ ሳይሰጥ አንድ ጥይት እስክትቀረው ድረስ ብቻውን ከመቶ በላይ የእስራኤል ወታደር ጋር ተታኩሶ ሸሂድ ሆነ። በቤቷ ደብቃው የነበረችውም የአንዲት አሮጊት ቤት በዶዞር እንዲፈርስ ተደረገ። ዑመር አቡ ለይሊን የአይሁድ መገናኛ ብዙሃኖች ሳይቀሩ የፍልስጤም ራንቦ ብለው ሰየሙት። ለአቅሷ የተሰውትን ጀግኖች ሁሉ አላህ ጀነተል ፊርደውስን ይሸልማቸው። ┈┈❈••✦ ✾ ✦••❈┈┈ ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያስተላልፉ ቻናላችንን ለመቀላቀል ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇👇 @palestine_history @palestine_history
Hammasini ko'rsatish...
የሼኽ ኻሊድ አር-ራሺድ ዳዕዋዎች

★ የቦልዩድ የፊልም ኢንደስትሪ እርኩስ አድርጎ የሰራቸው የኢስላም ሙጃሂዶች እውነተኛ ታሪክ ★ ጭንቅላታቸው ተቆርጦ በፈረንሳይ ሙዚየም ውስጥ የሚገኙ ጀግኖች ★ የሼኽ ኻሊድ አርራሺድን አማርኛ ትርጉሞችን የዩቱዩብ ፔጃችንን ሰብስክራይብ አድርገው ይከታተሉ 👇👇

https://youtube.com/channel/UCPgxFIQ_qZ2XHM1di_y_xoA

ለአስተያየትዎ ↪️ @Mahimahisho

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ እጅግ ውብና አስገራሚ የፍልስጢን ታሪኮችን የጀግኖቻችንን ወግ በአዲስ ወኔ በአዲስ መንፈስ ወደናንተ ልናደርስ ተዘጋጅተን ጨርሰናል ከነገ ጀምሮ ዘወትር 3 ሰዓት የምናደርሳችሁ ይሆናል ኢንሻ አላህ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ሳሚያ ትባላለች የመጀመሪያዋ እና ብቸኛዋ በቁድስ ከተማ የምትገኝ ሴት የባስ ሹፌር ናት @palestine_history
Hammasini ko'rsatish...
📸ለናብሌስ ከተማ ሸሂዶች ሽኝት እየተደረገ
Hammasini ko'rsatish...