ESSA YUSUF
4 414
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar
- Kanalning o'sishi
- Post qamrovi
- ER - jalb qilish nisbati
Ma'lumot yuklanmoqda...
Obunachilar o'sish tezligi
Ma'lumot yuklanmoqda...
የቁንድዶ ፈረሶች
ስንቶቻችሁ ስለነዚህ አስገራሚ ፈረሶች ታሪክ ታውቃላችሁ?
ቁንድዶ እጅግ በጣም በተፈጥሮ የተዋበ ተራራ ነው:: የሚገኘው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ በጃርሶ እና ጉርሱም ወረዳ ነው:: ይህ ተራራ ጫፉ ላይ ውሃ አለ:: አረንጓዴ እና በተፈጥሮ ፀጋ የታደለ ነው:: ብዙ የውጭ እና የሃገር ውስጥ ተመራማሪዎች ስለዚህ ተራራ እና ፈረሶቹ ብዙ ምርምር አካሂደዋል::
በአለም ላይ ብቸኛ ባለቤት የሌላቸው የዱር ፈረሶች እዚሁ ላይ ይገኛሉ:: ፈረሶቹ አመጸኛ ናቸው፤ ሰዎችን ሲያዩ ማንፏረር፣ ጆሮ መቀሰር፣ ለጸብ መጋበዝ ይቀናቸዋል:: የኤጀርሳ ጎሮ ገበሬዎች ወደ ተራራው ይልኳቸው የነበሩ ማቲ እረኞች ሳይቀሩ በፈረሶቹ ይነከሱ፣ ይገደሉም እንደነበር ተዘግቧል:: በአሁን ሰአት የፈረሶቹ ቁጥር እየተመናመነ መጥቷል::
ታሪካቸው እስካሁን ድረስ ህዝቡን ለሁለት ከፍሏል:: ግማሹ የአህመድ ግራኝ ወታደሮች ፈረሶች ናቸው ሲሉ ገሚሶቹ ደግሞ የዐጼ ገላውዲዮስ ፈረሶች ናቸው በማለት ይከራከራሉ:: ብዙም ያልተነገረላቸው እና በሚገባው ልክ እንክብካቤ ስላልተደረገላቸው ባክኖ የቀረ የቱሪዝም ሃብት ሆኗል::
የኦሮሚያ ቱሪዝም ቢሮ አይኑን ገልጦ ልክ እንደ ወንጪ አይነት ፕሮጀክቶችን እዚህ አከባቢ ማድረግ አለበት:: አስገራሚ የቱሪዝም መዳረሻ ይወጣዋል:: ፈረሶቹና ተራራው ለአከባቢው ልዩ ግርማ ሞገስን ሰተውታል:: ባለሃብቶችም በአከባቢው የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችን ቢገነቡ ለቱሪስቶች ማረፊያነት ጠቃሚ ነው::
ትኩረት ለቁንዳዶ ተራራ ፈረሶች
👍 9🥰 1😢 1
Repost from KMN
Hammasini ko'rsatish...ልዩ ቆይታ ከዶ/ር ፀጋዬ አራርሳ ጋር
ወደብ ወይስ አደብ... የኦሮሚያዉ ርኃብ እና የማይነገረዉ ጦርነት
👍 3
በብዙ የፈጠራ ስራዎቹ የሚታወቀው ወጣት ሸሃብ ሱሌይማን Shehab Suleyman ሙሉ በሙሉ የራሱ ፈጠራ የሆነውን ሞተር ማምረቱን ገልፁጿል:: የሞተሩም ስም ኡርጂን " urjiin" በሚል ሰይሞታል:: ሙሉ በሙሉ በሃገር ውስጥ የተመረተው ኡርጂን ሞተር ምርቶቹን ለገበያ አቅርቧል:: በራሳችን ምርት እንኩራ::
የባሌ ምድር ያፈራችው ወጣት ሹሄብ ከዚህ ቀደም የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን በመፍጠር ለህዝብ ማቅረቡ ይታወቃል:: እኛም እንደነዚህ አይነት ወጣት የስራ ፈጠራ ባለሙያዎችን ማበረታታት አስፈላጊ ነው::
ይህ የቁቤ ትውልድ ይለያል ስልህ በምክንያት ነው
👍 19👏 1