cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 456
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-77 kunlar
-1630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሸክሜ ቀላል ነው ይላል፣ በሌላ ቦታ ወደ መንግስተ ሰማያት የምትወስደው መንገድ ጠባብ ናት ይላል ከባድ መሆኗን ሲያጠይቅ። ይሄ ሁለቱ እንዴት ይታረቃል የሚለውን መጋቤ ሀዲስ ልዩ መልስ ሰጥተዋል። https://t.me/raiye_mariyam
Hammasini ko'rsatish...
ሸክሜ ቀላል ነው.m4a5.53 MB
00:51
Video unavailableShow in Telegram
3.64 MB
2🕊 1
ዕርገተ ክርስቶስ፤ እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁ (ሰኔ 06 2016)      ዕርገት ከታች ወደ ላይ፥ከምድር ወደ ሰማይ መውጣት ማለት ነው።ቅዱስ ዳዊት፡-የጌታ ርደቱን (ከሰማይ ወደ ምድር መውረዱን) በመዝሙረ ትንቢት እንደ ተናገረ ሁሉ ነገረ ዕርገቱንም ተናግሯል።ይኸንንም:-“እግዚአብሔር በእልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ፤” በማለት የራቀውን አቅርቦ፥ የረቀቀውን አጉልቶ በመንፈስ ዘምሯል።መዝ፡፵፮፥፭      ይህ ትንቢት የሚፈጸምበት ሰዓት በደረሰ ጊዜም ጌታ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ደቀ መዛሙርቱን አስከትሎ ወደ ቢታንያ ሄዷል። በአንብሮተ እድም ባርኳቸዋል (ሹሟቸዋል)። እየባረካቸውም ራቃቸው፥ወደ ሰማይም ዐረገ። (ዕርገቱ በርህቀት እንጂ በርቀት አልነበረም)።ሉቃ፡፳፬፥፶።      ከዚያ በፊት ትንሣኤውን እርግጠኞች እንዲሆኑ በተለያየ ቦታ እየተገለጠ ተዳስሶላቸዋል፥አብሯቸው በልቷል፥ጠጥቷል፥ምሥጢረ መጻሕፍትን ገልጦላቸዋል።መጽሐፈ ኪዳንንም አስተምሯቸዋል ።“ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ፥ ዐርባ ቀን እየታያቸው፥ስለ እግዚአብሔርም መንግስት ነገር እየነገራቸው፥በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።”ይላል።የሐዋ ፩፥፫።       የጌታ ዕርገቱ በትንቢት የተነገረ፥በቅዱሳን መላእክትና በቅዱሳን ሐዋርያት የተመሰከረ ነው።እነርሱ በእውነት የዓይን ምስክሮች ናቸውና።የሐዋ፡፩፥፱-፲፩።ስለሆነም ዕርገቱ የታመነ ነው ።ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዕርገቱ ፍጹም የታመነ መሆኑን ሲያስረዳ “ሕማም የሚስማማውን ግዙፍ ሥጋን ተዋሕዶ ሳለ ከስቅለቱ አስቀድሞ በባሕር ላይ ከሄደ፥ዛሬ ነፋስን ከፍሎ ሲያርግ ቢታይ ማንም ማን አይጠራጠር፤ሥጋው አልተለወጠምና።”ያለው ለዚህ ነው።ሃይ፡አበው፡ክፍል ፲፫፥፲፭።     የጌታ ጥንተ ዕርገቱ ሐሙስ ግንቦት ፰ ቀን ፴፬ ዓ.ም. በዘመነ ማርቆስ ነበር። https://t.me/raiye_mariyam
Hammasini ko'rsatish...
ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

ግንቦት ፳፩ ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር፤እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየአገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ ፤ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተ...ከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር፤ህዝቡ የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል፤እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር፤አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው። ወይ ግሩም ታዲያ ይህ በዚያ ደጉ ዘመን ነበር፤አሁን ግን ኃጢያታችን ሲበዛ በረድኤት ካልሆነ በገሃድስ ተገልጻ አትታይም ለበቁ ካልሆነ። ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን አባ መርትያኖስ አረፈ፤ ይህም በህጻንነቱ መንኩሶ ለ 67 ዓመት በፍጹም ተጋድሎ የኖረ ነው። ይህ ገድል ትሩፋቱ በሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ እነሆ አንዲት በዝሙት ስራዋ እጅግ የምትታወቅ ሴት ዘንድ ወሬው ደረሰ፤ እርሱ እኮ የሴት ፊት ስላላየ ነው እንጂ በፍትዎት ይወድቃል ከክብሩም ይዋረዳል አለቻቸው ባልንጀሮቿም የለም በፍጹም አያደርገውም አሏት፤ እኔ በዝሙት ከጣልኩት ምን ትሰጡኛላችሁ አለቻቸው ብር እንሰጥሻለን አሏት፤በዚህ ተወራርደው ሄደች፤ ሽቶ ተቀባብታ አምራ ተውባ ሄደች፤ስንክሳሩ እጅግ ውብ መልከመልካም ነበረች ይላታል፤ እስኪመሽ ከገዳሙ አቅራቢያ ቆይታ በሩን አንኳኳች የመሸቢኝ እንግዳ ነኝ አሳድረኝ ትለዋለች፤ ነፍሱ ተጨነቀች ባስገባት የዝሙት ጦር ይነሳብኛል ብተዋት እንግዳ ሆኜ መጥቼ መቼ ተቀበላችሁኝ ብሎ ይፈርድቢኛል ደግሞም አውሬ ይበላታል ብሎ አሰበ፤ባስገባት ይሻለኛል ብሎ አስገባት የተቀበችው ሽቶ ዝሙት የሚቀሰቅስ ነው፤ ቀረበችው፤አባቴ በዚህ ማንም አያየንም አብረን እንተኛ አለችው፤እሳት እያነደደ ነበርና እሺ ምን ችግር አለው እዚህ አሳት ላይ ምንጣፍሽን አንጥፊና እንተኛለን አላት፤ አንድም እግሩን ወደ እሳቱ ማገደው ይላል አይንህ ብታሰናክልህ ካንተ አውጥተህ ጣላት አይደል የሚለው መጽሐፉ፤ ደነገጠች ምንድን ነው አባቴ አለችው፤ ይህ ያስደንቅሻልን የገሃነም እሳትን ታዲያ እንዴት ልትችይው ነው አላት እግሩ ስር ወድቃ ይቅር በለኝ አለችው እርሱም ሌሊቱን ሙሉ ሲያስተምራት አደረ፤ ሲነጋ አልተመለሰችም አመንኩሰኝ ከዚህ በኃላ ወደ ዓለም አልመለስም አለችው አመነኮሳት ከደናግል ገዳም ወስዶ ለእመምኔቷ አደራ ሰጣት፤የሚገርመው ይህች እናት ከብቃቷ የተነሳ የመፈወስ ሀብት ተሰጣት ብዙ በሽተኞች ወደርሷ እየመጡ ይፈወሱ ነበር፤ አባ መርትያኖስ ግን ድጋሚ ሌላ ሴት መጥታ እንዳትፈትነው ሰው የማይደርስበት ከባህር መካከል ባለች ደሴት ብቻውን መኖር ጀመረ፤ ከብዙ ዘመን በኃላ መርከብ ተሰብሮ ብዙዎች ሲሞቱ አንዲት ሴት በመርከቡ ስባሪ ተጣብቃ እርሱ ካለበት ደሴት ደረሰች ባያት ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ከእርሷ ጋር በአንድነት ስለመኖሩም አዘነ፤ ይምትበላውን ሰጥቷት የምትለብሰውን አዘጋጅቶላት ሲያበቃ ተወርውሮ ወደ ባህሩ ገባ ዓሳ አንበሪም ተሸክሞ ወደ የብስ አደረሰው ከዚህ በኃላ በአንድ ቦታ ላለመቀመጥ ወስኖ በ108 አገሮች የሚገኙ ታላላቅ ገዳሞችን ዞረ በመጨረሻም በዛሬዋ ቀን በክብር አረፈ፤ እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚያብሔር ይመስገን፤ እኛንም ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን። https://t.me/raiye_mariyam
Hammasini ko'rsatish...
ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2 1
ጾሙስ አበቃ.....? ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል! አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ? የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ! አባ ገብረ ኪዳን https://t.me/raiye_mariyam
Hammasini ko'rsatish...
ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

👍 2
♡YAHWEH PROMOTION♡ ↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ። ↪  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ               ➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN ☎ Tel      :- +251943686155   :- +251977157265 📞 ያገኙናል https://t.me/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
Hammasini ko'rsatish...
ሰአሊ ለነ ቅድስት

ፍቅር ግን ከሁሉ ይበልጣል

⛪የህይወት ምክር⛪
❤ ምክረ አበው ❤
✅ ተአምረ ማርያም ✅
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፩
⛪ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እንማማር ⛪
✅መንፈሳዊ ትምህርት✅
🔸የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች 🔸
💟የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ💟
👏ኑ እንዘምር 👏
🎚ነይ ነይ እምዬ ማርያም🎚
📍Ortoodooksi 📍
ዘሰዋስም
💧የመ/ር ዘበነ ለማ መግለጫዎች 💧
💠ሐመረ ኖህ💠
💧የንግስ መዝሙሮች 💧
መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
♦የቤተክርስቲናችን መዝሙርና ግጥሞች♦
♻ ምስባክ ወማኅሌት ♻
⚜አምኃ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ ⚜
🔸የክርስቶስ ጃንደረባ 🔸
🔸ነ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንወቅ 🔸
🔸ማስያስ 🔸
🀄የመንፈስ ፍሬዎች 🀄
1⃣አንዲት ሃይማኖት1⃣
☦መዓዛ ሠናይ☦
⚜ንቁ ክርስትያኖች ⚜
💠ደቂቀ እስጢፋኖስ 💠
📯ከብሮን የዜማ መሳርያ 📯
⚜የማርያም ፍሬዎች⚜
⚜ቅድስት ፌብሮኒያ⚜
💠መኅርኒ ድንግል💠
🔸ትንሿ ቤተክርስቲያን🔸
📯ራእየ ማርያም 📯
ዘመርቆሬዎስ
✍ከባለ20ሺ -30ሺ ለማስመዝገብ
✍ከባለ10ሺ-20ሺ ለማስመዝገብ
📝ነጻ ፕሮሞሽን ለሁሉም 📝
Free FaceSwap🤖
Best DeepNude🙈
♡YAHWEH PROMOTION♡ ↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ። ↪  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ               ➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN ☎ Tel      :- +251943686155   :- +251977157265 📞 ያገኙናል https://t.me/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
Hammasini ko'rsatish...
ሰአሊ ለነ ቅድስት

ፍቅር ግን ከሁሉ ይበልጣል

⛪የህይወት ምክር⛪
❤ ምክረ አበው ❤
✅ ተአምረ ማርያም ✅
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፩
⛪ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እንማማር ⛪
✅መንፈሳዊ ትምህርት✅
🔸የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች 🔸
💟የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ💟
👏ኑ እንዘምር 👏
🎚ነይ ነይ እምዬ ማርያም🎚
📍Ortoodooksi 📍
ዘሰዋስም
💧የመ/ር ዘበነ ለማ መግለጫዎች 💧
💠ሐመረ ኖህ💠
💧የንግስ መዝሙሮች 💧
መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
♦የቤተክርስቲናችን መዝሙርና ግጥሞች♦
♻ ምስባክ ወማኅሌት ♻
⚜አምኃ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ ⚜
🔸የክርስቶስ ጃንደረባ 🔸
🔸ነ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንወቅ 🔸
🔸ማስያስ 🔸
🀄የመንፈስ ፍሬዎች 🀄
1⃣አንዲት ሃይማኖት1⃣
☦መዓዛ ሠናይ☦
⚜ንቁ ክርስትያኖች ⚜
💠ደቂቀ እስጢፋኖስ 💠
📯ከብሮን የዜማ መሳርያ 📯
⚜የማርያም ፍሬዎች⚜
⚜ቅድስት ፌብሮኒያ⚜
💠መኅርኒ ድንግል💠
🔸ትንሿ ቤተክርስቲያን🔸
📯ራእየ ማርያም 📯
ዘመርቆሬዎስ
✍ከባለ20ሺ -30ሺ ለማስመዝገብ
✍ከባለ10ሺ-20ሺ ለማስመዝገብ
📝ነጻ ፕሮሞሽን ለሁሉም 📝
Free FaceSwap🤖
Best DeepNude🙈
ድንግል ማርያም ቅድስ ዩሐንስ አፈወርቅ መናፍቃን የድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና እውነታውን አስረግጦ አስተምሯል።   መናፍቃን ዮሴፍ የበኩር ልጇን እስከ ምትወልድ አላወቃትም የሚለውን (ማቴ 1-25) ተብሎ ስለተጻፈ ድንግል ማርያም ጌታን ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር በትዳር ኖራለች ብለው ስለተነሱበት የተሳሳተ ሃሳብ ሲመልስ እስከ የሚለው ሃረግ ወይም ቃል ዮሴፍ የበኩር ልጇን እስከምትወልድ አላወቃትም ማለት አንድም ወንድ እንደማታውቅ አንድም እስከ የሚለው ፍፃሜ የሌለው እስከ ነው። በመሆኑም ጌታን እስከምትወልደው የምትወልደው መድኃኒአለም እንደሆነ አላወቀም ፤የድህነት ምክንያት ሆና እንደተመረጠች አያውቅም ነበረ። በሉቃስ ወንጌል ላይም ማርያም ነገሩን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ነበር ። ከቅዱሳን የከበረች ከመልአክት የበለጠች እንደነበረች አያውቅም ነበር። በሌላው ጌታን በጸነሰች ግዜ ገጽዋ ይለዋወጥ ነበር ይህንንም ሲያይ ዮሴፍ ጻድቅ ስለነበረ ሳይገልጣት ተዋት። ኢትዮጵያዊ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን መፃፋቸው "አላወቃትም " የሚለውን ሲያመሰጥሩ ማወቅ በ፪ ይከፈላል: ከአለማወቅ ወደ ማወቅ፤ ካለመገናኝት ወደ መገናኝት ። በማቴ(1፥25) ላይ ያለው አለማወቅ አዳም ሄዋንን አወቃት፤ ዳዊት አቢሳን አላወቃትም በሚለው ፍቺ ማለትም ካለመገናኝት ወደ መገናኝት በሚለው ሳይሆን ፤ ከአለማወቅ ወደ ማወቅ ማለትም ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኖን ካለማወቅ ወደማወቅ እንዲሁም  ቅድስት ድንግል ማርያም በሆዷ ጌታችንን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተሸከመች የጌታችን መልክ በተለወጠ ጊዜ የእሷም መልክ ይለወጥ ስለነበር መልኳን አላወቀም ነበር። ይህን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲያስረዱ ብርጭቆ ውሃ ሲይዝ የውሃ መልክ፤ ጠጅ ሲይዝ የጠጅ መልክ እንደሚይዝ ፣ የድንግል ማርያምም መልክ ይለዋወጥ ነበር። እንደ ሮማን የምትቀላቀልበት ጊዜ አለ፤ እንደ ናርዶስም የምትነጣበት ጊዜ ነበር።ብለው አስተምረዋል ። 2ኛ ሌላው መናፍቃኑ ያነሱ የነበሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የጌታ ወንድሞች ተብሎ (በማቴ ፥12-46:50፤ማር-3-31:35፤ሉቃ-8-19:21)ላይ የተመዘገበው ጽንሰ ሃሳብ በመያዝ ማርያም ሌላ ልጆች አሉዋት ከዮሴፍ የተወለዱ  ለሚሉት ዮሐንስ አፍወርቅ መልስ ሲሰጥ በመስቀሉ እግር ስር ያከናወነውን ምስጢር አራቆ በመተርጎም እንዲህ አስተምሯል። ማርያም ጌታን ከወለደች በኋላ መናፍቃን እንደሚሉት ከዮሴፍ ጋር በሚስትነት ኖረች ካሉ። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን በመሥቀል ላይ ሆኖ በዕለተ አርብ ከመሥቀል ስር ስለነበረችው እናቱ እነሆ ልጅሽ አላት። ልጆች አሏት ካሉ ለምን በመሥቀል ሥር አልተገኙም፣ ለሚወደው ደቀመዝሙር ለምን በአደራነት ሰጠው ወደ ቤቱስ እንዲወስዳት አዘዘው ብቸኛ ስለነበረች አይደለምን እንዴ ይህንን ልብ ብለን እናስተውል። በማለት አስተምሯል በሌላው ለምን ወንድሞች ተባሉ የሚል ጥያቄ ከተነሳ በመንፈሳዊ ህይወት ወንድማማቾች ስለሆኑ ከምንም በላይ ግን ዮሴፍን በምስጢር የድንግል ማርያም እጮኛ ጠባቂ እንዲደረግ የምስጢረ ስጋዌንም ነገር ያለግዜው ላለመግለጽ ምስጢር ለማድረግ ነው። አበው አስተማሩን እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ። በተዋሕዶ ሰው ሆኖ አለምን ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል። ድንግል ማርያም ጌታን ከመፀነሳም በፊት ድንግል ከፀነሰችም በዋላ ድንግል ናት። እንዲሁም ከመውለዷ በፊት ድንግል ከወለደችም በዋላ ድንግል ናት። ይህንንም በትንቢት እግዚአብሔር ስለተገለጸለት ከአብይ ነብያት መክአከል አንዱ ሕዝቃኤል (በምዕራፍ 44-1:4) ወደ ምስራቅም ወደሚመለከተው በር አመጣኝ ይህ በርም ዝግ ነበር የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ለዘላለምም ዝግ ሆኖ ይኖራል ። ምሥራቅ ያላት ድንግል ማርያምን ነው ፀሐይ ከምስራቅ እንዲወጣ ጨለማው ዓለም ብርሃን እንዲያደርግ ፀሐይ ፅድቅ ክርስቶስም ከአማናዊት ምሥራቅ ከድንግል ማርያም ተወልዶ በኀጥያት ለጨለመው ዓለም የጽድቅ ብርሃን ሆኖ ተገልጧል።(ዮሐ 1-15)ጠቢቡ ሰለሞንም በመኃልዬ መኃልይ መዝሙሩ እህቴ ሙሽራዬ ሆይ የተዘጋ ገነት የታተመ ፈሳሽ ነሽ በማለት ስለዘላለማዊ ድንግልነዋ ጽፏል።(መኃ፤4-12) https://t.me/raiye_mariyam
Hammasini ko'rsatish...
ራዕየ ማርያም ✝

በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የተሰጣቸውን ትምህርት ችላ በማለት ሲጨፍሩና ሲደንሱ የጥፋት ውሃ ድንገት ጠራርጎ እንደወሰዳቸው የዓለም ኅልፈት የክርስቶስ መምጣት እንዲሁ ባልታሰበበት ሰዓት ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ። ሠማይ እና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈፅሞ አያልፍም። ማቴ 24:35

👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.