የትም ብትሆን አላህን ፍራ
የዚህ channel አላማ "ከኔ የሰማቿትን አንዲት አንቀፅ እንኳን ብትሆን ለሌሎች አድርሱ " የሚለውን ነብያዊ መልእክት (አስተምእሮ) በተግባር ለማዋል ነው insha allah ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት..... @Neharrr
Ko'proq ko'rsatish226
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar
- Kanalning o'sishi
- Post qamrovi
- ER - jalb qilish nisbati
Ma'lumot yuklanmoqda...
Obunachilar o'sish tezligi
Ma'lumot yuklanmoqda...
"ከእናንተ አንዳችሁ ምድረ -በዳ መሬት ላይ ያጣትን ግመሉን በድንገት ሲያገኝ ከሚሰማው ደስታ የበለጠ አላህ በባርያው ተውበት ንስሃ ይደሰታል "፡፡
ረሱል( ሰ.ዕ.ወ)
ውብ ጁመዓ
@iteqillahk
❤ 2
ማንንም #ብትጠጋው ጎደሎ ነው ✅
✍️ ሀያል ያልከው ከርእሱ በላይ ሀያል አለ ሀብታም ያልከው ከእርሱ በላይ ሀብታም አለ አዛኝ ያልከው በውስጡ ጭካኔ አለ
☝️ #አሏህ አዘወጀል የተሟላ ጌታ እሱ ነው በእርሱ ተመካ ከእርሱም ከጅል✅
@iteqillahk
♡ መረጋጋትን እንፈልጋለን
አላህን በማውሳት ውስጥ እንጂ አናገኛትም
⇨እረፍት እንፈልጋለን
በሰላት ውስጥ እንጂ አናገኛትም
⇨ደስታን እንፈልጋለን
አላህን በማፍቀር ውስጥ እንጂ አናገኛትም
⇨እንፈልጋለን እንፈልጋለን እንመኛለን ...
ህይወትን በአላህና ከአላህ ጋር እንጂ
አናገኛትም ።
⇄ ለአላህ ሁን ህይወት ላንተ ትሆናለች
@iteqillahk
"አንዳንድ ሰዎች በህይወት አልፈዋል፤ ስነምግባራቸው ግን ህያው አድርጎ አቆይቷቸዋል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በህይወት አሉ ስነምግባራቸው ግን ገድሏቸዋል።" ይላሉ
ኢማሙ ሻፊዒ ራህመቱላህ አለይህ 🩶
በአኽላቅ ህያው ከሚሆኑት አሏህ ያርገና
🤲🤲🤲🤲
@iteqillahk
"ከዱንያ ትንሽ ነገር ብቻ ስትፈልግ የበለጠ ነፃነትህን እያገኘህ ትመጣለህ "
ኡመር ኢብኑል ኽጣብ (ረ.ዓ )
@iteqillahk
❤ 1
"ኡመር ቢን አል ኸጣብ እንደ ሰለሙ ቤተሰቦቻቸውን ሰብስበው ከእንግዲህ እኔ በአላህና በመልክተኛው ማመኔን እወቁ እናንተም በአላህ እንድታምኑ አዝዣችኋለሁ" አሉ ፡፡ በሰማዉ የተደሰተዉ ልጃቸው አብዱላህ...."አባቴ እኔ ሙስሊም ከሆንኩ አመት ሆኖኛል" ይላቸዋል ፡፡ ኡመርም" እኔ አባትህ ወደ ጀሀነም ስሄድ ዝም ብለህ ትመለከተኛለህ ወላሂ እመታሃለሁ" አሉት፡፡ ሁሌም ስለዚህ እርስ ሲወራ ልጃቸዉን ቸብ ያደርጉት ነበር ...
የወደድነው ኽይር ሁሉ
ለምንወዳቸው የሚሆንበት ውብ ቀን 😍
اللهم صلِّ على سيدنا محمد رسول الله صلى الله عليه وسلم
@iteqillahk
🥰 3
አንድ ወንድም አጋጣሚውን እንዲህ ይተርክልናል ።
የሆነ ጊዜ ወንድሜ አዲስ ቤት ሰራና ለመዘየር ሄኩኝ በአዲሱ ቤቱ ወንድሜም በጥሩ መስተንግዶ ተቀበለኝና ጥሩ ጊዜ አሳለፍኩ ወደ ሰዓቱ ስመለከት ለኢሻ ሶላት ግማሽ ሰዓት ይቀር ነበር ...!
ለወንድሜ ወደ መስጂድ መሄድ እንደምፈልግ ስነግረው ገና ነው አዛን አልተባለም አለ...?
ሶላት እስኪደርስ ድረስ ቁርዓን እየቀራሁ እጠብቃለሁ ልሂድ ብየ ሄኩኝ ...
ወደ መስጂድ ስደርስ መስጂዱ ባዶ ሁኖ አገኘሁት ቁርዓን አንስቼ መቅራት ጀመርኩ..!
ከትንሽ ደቂቃ ብኋላ አንድ ልጅ ወደ መስጅድ በመግባት ሰላምታ አቀረበልኝና ሶላት ቆመ ሁለት ረከዓ ሰገደ አሰላመተ በድጋሜ ሶላት ቆመ ሱጁድ ላይ በጣም ይቆይ ነበር ....
በሶላቱ በጣም ተገረምኩ በዚህ እድሜው በዚህ ልክ ኹሹእ ሲያደርግ አላህ ጋር ያለው ግንኙነት አስቀናኝ ። ሱጅድ ላይ ሲቆይ ምን እያለ ነው ብየ ጠጋ ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ ...
ወደ ልጁ ተጠግቼ ሳዳምጠው ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ማልቀስ ጀመርኩ ጌታውን እንዲህ እያለ ሲጣራ ነበር...
ያረቢ አባቴ የሆነ ነገር ሲቸግረን ወደዚህ እንድመጣ አደራ ብሎኛል..
እኔም ኢሄው እጅህ ላይ የተናነሰ ደካማ ራሀብተኛ የተቸገረ ሁኜ ቀርቤለሁ....
ያረቢ ትናንት ጀምሮ ምንም እንዳልበላን አንተም ታቃለህ .. ያረቢ ትናንሽ ወንድሞቼና እህቶቼ ረሀብን መቋቋም አይችሉም .. እኔና እናቴ ግን መቋቋም እንችላለን ...
ነገር ግን ታናናሾቼ በረሀብ ምክንያት ሲያለቅሱ ሳይ ወደ አላህ ሂጄ የሚበላ እንዲሰጠን እጠይቀዋለሁ አልኮቸው!
አባቴ እንዳስተማረኝ ያረቢ እባክህን እናቴና ታናናሾቼ ዘንድ አታሳዝነኝ እባክህን
አንተ እኮ አሸናፊ ሀብታም አዛኝ በጣም ሩህሩህ መልካም ነገሮች በሙሉ በእጅህ ነው አንተም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ ያረቢ
የዱዓ አደራረጉ በጅጉ ልብ ይነካል እድሜው ገና አስር ቤት ቢሆንም ሁኔታው ልብ ይነካል አላህን ደጋግሞ ይለምናል ሱጁድ ላይ እያለ ታናናሾቹን አላህ ምግብ እንዲሰጣቸው እያለቀሰ ይማፀናል ።
ሰወች መተው ኢሻን እስክንሰግድ ድረስ ተከታተልኩት ። ኢሻን ሰግደን ስንጨርስ ወንድሜን አገኘሁትና ይህ ልጅ ማነው ታቀዋለህ ወይ ስል ጠየኩት...?
ወንድሜም አዎ አቀዋለሁ የመስጅዳችን ኢማም ልጅ ነው አባቱ ሙቷል አላህ ይዘንለት አለኝ ።
የት እንደሚኖር ልጠቁመኝ ትችላለህ አልኩት ወንድሜም ታሪኩ ምንድን ነው አለኝ..?
ምንም የለም ዝም ብለህ ቤቱን አሳየኝ ....!
ከመስጅድ ወተን የልጁን ቤት አሳየኝ ወደ ሱቅ ሂጄ በርካታ የሚበላ ምግብና በርከት ያለ ገንዘብ በውስጡ አስቀምጫ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ቆሮቁሬ ቶሎ ተደበኩኝ!
ልጁም ወደ ውጭ ወጣና ቀይና ግራውን ሲመለከት ማንም የለም ወደ ታች ሲመለከት ምግቡን አየው የተቆጠሩትን ምግቦች እየነካካ እንዲህ ሲል ጮሀ እናቴ ሆይ በርካታ ምግብ አገኘሁ አላህ አመጣልን ....
በጣም ደስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ለአላህ ሱጁድ አደረገ .....
#ፌስቡክ ላይ ሲዘዋወር ያገኘሁት መልክት ነው።
@iteqillahk
❤ 2👍 1🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
🦋🦋ምላስህ ሊናገር የማይፈልገውን ፊትህ እንዳይናገር ተጠንቀቅ🦋🦋
@iteqillahk
Photo unavailableShow in Telegram
🌴🌴ልክ እንደ ሰላት ሁኚ ።
ጦሀራዎች እንጂ የማይቀርቡሽ።🌴🌴
@iteqillahk
👍 2
ጠላትህ ወዳጅህ ይሆን ዘንድ 1000 እድል ስጠው ወዳጅ ጠላት ይሆን ዘንድ ግን አንድም እድል አትስጠው፡፡😍😉
@iteqillahk
Boshqa reja tanlang
Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.