cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የደ/ፀ/ሳ/ቅ/ጊዮርጊስ አጥቢያ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችና ጎልማሶች መንፈሳዊ ማኅበር

ዓላማችን ቤተከርስቲያን ማገልገልና በጎ አድራጎት ስራ መስራት እንዲሁም መንፈሳዊ ጉዞና መንፈሳዊ ሕይወታችንን የምናሳድግበት ነው ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
200
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
+630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
"ጲስጲር" (Pispir) በሚገኘው የቅዱስ እንጦንስ ገዳም ውስጥ እንዲህ ሆነ÷ አንድ ወንድም በኃጢአት መውደቁን እያነሡ ሌሎች ወንድሞች ከሰሱት:: እርሱም ወደ አባ እንጦንስ ሔደ÷ ነገር ግን ከጥቂት ቆይታ በኋላ ጥቂት ወንድሞች ተከትለውት ይወቅሱትና ይከሱት ጀመር:: እርሱም ክሱን መቃወሙንና ራሱን መከላከሉን ቀጠለ:: በዚህ የአጥፍተሃልና የአላጠፋሁም ክርክር ውስጥ ሳሉ ግን ቅዱስ ቢፍኖቴዎስ ድንገት ጣልቃ ገብተው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ÷ "ውኃ ውስጥ ወድቆ እስከ ጉልበቱ ድረስ በጭቃ የሰጠመ ሰው ዐየሁ÷ ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ሊረዱትና ከጭቃ ውስጥ ሊያወጡት መጡ÷ ነገር ግን በማውጣት ፈንታ እስከ አንገቱ ድረስ አሰጠሙት" ታላቁ ቅዱስ እንጦንስ ይህንን ሲሰማ ወደ ቅዱስ ቢፍኖቴዎስ እየጠቆመ "ይህን ሰው ተመልከቱት÷ በእውነት ነፍሳትን መማረክና ማዳን ይችላል" አለ:: የወደቁትን በማንሳት ፈንታ በክስና በወቀሳ ጫማ ረግጦ ከማስጠም እንርቅ ዘንድ የቅዱስ ቢፍኖቴዎስን ማስተዋል ያድለን:: ዲ/ን ሕሊና በለጠ
Hammasini ko'rsatish...
የከበረ ሰላምታችንን በልዑል እግዚአብሔር ስም እያቀረብን የደብረ ፀሐይ ሣሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በደብሩ ላይ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን የወጣቱ ተሳትፎ ግን እጅግ ደካማና አነስተኛ ነው በመሆኑም ሁላችንም መንፈሳዊ ግዴታ ያለብን መሆኑን አውቀን ዘወትር ደጁ እየሄድን ከመሳለም ባሻገር የልማት ሥራዎች ላይ ተሳታፊ በመሆን የበረከቱ ተካፋዮች እንድንሆን በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን አናስተላልፋለን። አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሁላችን ጋር ይሁን
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ከኅዳር 15 አስከ21 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሔደው የምህላና የጸሎት መርሐ ግብር ከላይ በተጠቀሱት ሰባት ቀናት ከማለዳው 12:00 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 1:00 ሰዓት በምሽት መርሐ ግብር ደግሞ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ የሚከናወን ሲሆን ሕዝበ ክርስቲያኑ በየ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ በመገኘት በመርሐ ግብሩ ላይ እንዲሳተፍ እየገለጸ አጠቃላይ መርሐ ግብሩ ቀደም ሲል በተሰጠው መግለጫ መሰረት የሚፈጸም መሆኑን ያስታውቃል። የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የምሕላና የጸሎት መርሐ ግብርን በተመለከተ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ ማሳሰቢያ። * ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ከኅዳር 15 አስከ21 ቀን 2016 ዓ.ም  የሚካሔደው የምህላና የጸሎት መርሐ ግብር ከላይ በተጠቀሱት ሰባት ቀናት ከማለዳው 12:00 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 1:00 ሰዓት በምሽት መርሐ ግብር ደግሞ  ከምሽቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ የሚከናወን ሲሆን  ሕዝበ ክርስቲያኑ በየ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ በመገኘት በመርሐ ግብሩ ላይ እንዲሳተፍ እየገለጸ አጠቃላይ መርሐ ግብሩ ቀደም ሲል በተሰጠው መግለጫ መሰረት የሚፈጸም መሆኑን ያስታውቃል።                  የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ምንጭ: EOTCPR
Hammasini ko'rsatish...
መኑ ከመ እግዚአብሔር "ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም" "በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል" ~~~~ ፩.ትላንት እስራኤልን ከባርነት ቀንበር ሲፈቱ ሙሴን በመተባበር ባህረ ኤርትራን ከፍሎ በደረቅ መሬት አሻግሮ ውሃን ከጭንጫ እያፈለቀ መናን ከሰማይ እያወረደ ፤ቀን በደመና ሌሊት በብርሃን አምድ የመራቸው ሚካኤል ነው፤ ከዚህም የተነሳ መጋቤ ብሉይ ተብሏል። ፪. በኋላም በሙሴ እግር ኢያሱ ሲተካ የኢያሪኮን ቅጥር እንዲያፈርስ ሰባቱን የአህዛብ ነገስታት ድል አድርገው ምድረ ርስት ከነዓንን እንዲወርሱ የተራዳ ሚካኤል ነው። ፫.ትውልድ ሁሉ ወደ አባቶቻቸው ተከማችተው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ያደረገውን ድንቅ ተአምር ረስተው በመበደላቸው በከለዳውያን ተማርከው ለ70 ዘመን በባቢሎን ምድር በምርኮ ሳሉ ለህዝብ ልጆች ከእግዚአብሔር ምህረትን ይለምን ዘንድ የቆመ ሚካኤል ነው። ዘካ 1፥12 ፬.በመላእክት ዘንድ ፈተና በተነሳበት ጊዜ የቀደመውን እባብ ዘንዶውን ተዋግቶ ያሸነፈ ሚካኤል ነው።ራዕ12÷3 ፭. በመጨረሻው ዘመን ሃይማኖት ከምድር ስትመነምን ለእዉነተኞች ክርስቲያኖች የሚቆም ሚካኤል ነው። ዳን 12፥1 ሚካኤል ማለት አሸናፊ ድል አድራጊ ማለት ነው። ሚካኤል ማለት ተራዳኢ መጋቢ ማለት ነው። ሚካኤል ማለት የይርቅታና የርህራሄ መዝገብ ማለት ነው ሚካኤል ማለት መልአከ ምክሩ ወአበጋዙ ለእግዚአብሔር ማለት ነው። ሚካኤል ማለት መኑ ከመ እግዚአብሔር ማለት ነው። ሚካኤል ማለት ዕፁብ ድንቅ ማለት ነው። ለህዝብ ልጆች ለእግዚአብሔር ሰዎች ለወዳጆችህ መቆም ልማድህ የሆነው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ሆይ ለወዳጆችህ ለእግዚአብሔር ልጆችለኢትዮጵያውያን በመከራው ዘመን ሁሉ ልክ እንደ ጥንቱ ትቆምልን ዘንድ እንለምንሃለን።
Hammasini ko'rsatish...
🌹 ፈጥኖ ደራሻችን አማላጃችን #ሚካኤል ሆይ 🌹 የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ አንተ ነህ እኮንየሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ እኮን ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና ፤ በጠራንህ ጊዜ ሁሉ    🙏 በይቅርታና በቸርነት   🙏 ድረስልን አትራቀን      🙏   / መልክአ ሚካኤል /              +    +    +    🍂 ከመላዕክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ በአምላክ የተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ አሳዳጊዬ ነው ሆኖ እናት አባቴ #ሚካኤል ባለበት ይሸሻል ጠላቴ          +   +   + ብዙ ልጆች አሉት ለስሙ ምስክር በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር ስለፍፁም ምልጃው ለኔግን ይለያል መላኩ #ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል          +   +    + ከመላዕክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ በአምላክ የተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ አሳዳጊዬ ነው ሆኖ እናት አባቴ #ሚካኤል ባለበት ይሸሻል ጠላቴ       +   +   + ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ ወቶ #ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ               +    +    + በባህራን ታሪክ በነተላፊኖስ በአፎምያ መትረፍ በነ ዱራታኦስ በነብዩ ዳንኤል መች ይፈጸምና #የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና                 +     +     + በጉዞ የረዳቹ በባህር በየብሱ ፈጥኖ ደርሶላቹ እንባን ስታፈሱ ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ #በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ             +    +    + ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን ንጉሥ ለወደደው አንሰግድለታለን እንኳን #ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት / ሊቀ መዘምራን ቴዎድርስ ዮሴፍ /     +🍂 +🍂+🍂+🍂+🍂+🍂+🍂+ የሊቀ መላእክት የ #ቅዱስ_ሚካኤል ጥበቃ አይለየን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ በአማላጅነቱ ይሰውረን                           🙏 #ሠዓሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት  እንደሳሉት  #ሠዓሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ       +   🌺 +  🌸  +  🌺  +
Hammasini ko'rsatish...
🌺 በዓለ ሢመቱ #ለሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል ሕዳር 12 🍂 " #ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት፤ በኃይላት ላይ የተሾምክ ሚካኤል› ሲል ቅዱስ ኤጲፋንዮስ እንዳመሰገነው፤ 🍂 #ቅዱስ_ሚካኤል በኃይላት መላእክት ላይ የተሾመ ሊቀ መላእክት እንደመሆኑ በዓለ ሢመቱ ኅዳር ፲፪ ቀን በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል፡፡ (መጽሐፈ አክሲማሮስ) ኃይላት የተባሉት መላእክትም ሰዎች በዓለም ፈተና ውስጥ ሆነው ሰይጣን ሊያደክማቸው ሲፈልግ ኃይልን ብርታትን የሚሰጡ፣ ይህን ዓለም ንቀው በበርሃ ወድቀው ከሥጋ ምኞት ጋር የሚጋደሉትን፣ በከተማም እየኖሩ መንፈሳዊ ትሩፋት የሚያደርጉትን ደግሞ የሚያበረቱ ናቸው፡፡ 🍂ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ‹እርሱም ወደ ሰማይ ያረገ እግዚአብሔርም ተቀምጦ ያለ መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም የተገዙለት ነው…› ሲል  ‹ኃይላት› በማለት ያነሣቸው በኢዮር አራተኛይቷ  ከተማ  የሚኖሩትን  ነው፡፡ በእነዚህ ላይ እግዚአብሔር  ቅዱስ ሚካኤልን አለቃቸው አድርጎ ሾሞታል፡፡ (፩ኛጴጥ.፫፥፳፪) #የቅዱስ_ሚካኤል  ሢመት  በነገደ  መላእክት  ላይ ብቻም ግን  አይደለም፤  የእግዚአብሔር  ሕዝብ  በሆኑት  ላይም ጭምር ነው፡፡ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ ‹‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!›› ማለት እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፤ 🍂 አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት ደግሞ የስሙን ፊደላት በመተንተን እንዲህ ተርጉመውታል፤ ሚ-መኑ፣ ካ-ከመ፣ ኤል-አምላክ፤ ‹‹መኑ ከመ አምላክ፤ እንደ አምላክ  ማን ነው!›› (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ) የሰማይ ሠራዊት ሁሉ አለቃቸው  ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ  ይህ ኃያል መልአክ  ቅዱስ  ሚካኤል በብሉይ  ኪዳን  የእግዚአብሔር  ሕዝብ  የተባሉትን  እስራኤል  ዘሥጋን  ሲረዳና  ሲጠብቅ  እንደነበረ ተጽፎልን  እናገኛለን፡፡ 🍂 ለምሳሌ  መልአኩ  ቅዱስ  ሚካኤል  ለኢያሱ  በኢያሪኮ  ምድረ  በዳ  እንደተገለጠለት  ‹‹… ዐይኑን  አንሥቶ  ተመለከተ፤  እነሆም፥  የተመዘዘ  ሰይፍ  በእጁ የያዘ  ሰው  በፊቱ  ቆሞ አየ፤  ኢያሱም  ወደ  እርሱ  ቀርቦ፥  “ከእኛ  ወገን  ወይስ  ከጠላቶቻችን  ወገን  ነህ?”  አለው፡፡  እርሱም “እኔ  የእግዚአብሔር  ሠራዊት  አለቃ  ነኝ፤  አሁንም  ወደ  አንተ መጥቼአለሁ፡፡” ሲል ተናግሯል፡፡ (ኢያ.፭፥፲፫) እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ‹‹ በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ፥ ወዳዘጋጀሁልህም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ ፥እኔ መልአኬን በፊትህ እልካለሁ››  እንዲል፤  ሹመቱ  በእግዚአብሔር  ሕዝብ  ላይም  በመሆኑ  ስለ  እነርሱ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ይለምንላቸው  ነበር፡፡ (ዘፀአት.፳፫፥፳) 🍂ነገር ግን ኃጢአት ሲሠሩ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ይቀጣልና ሕዝቡን  ‹‹ራስህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እንቢም አትበለው፤ ስሜ በእርሱ ስለሆነ ይቅር አይልምና›› ብሎ  አስጠንቅቋቸው  ነበር፤   ይህም   ቅዱስ  ሚካኤል  በእግዚአብሔር  ሕዝብ  ላይ  መሾሙን  ያስረዳናል፡፡  (ዘፀ.፳፫፥፳፩) ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር  ሕዝብ  ላይ  ቅዱስ ሚካኤል  ስለመሾሙ ሲመሰክር ‹‹በእውነት   በመጽሐፍ   የተጻፈውን   እነግርሃለሁ፤   በዚህም  ነገር  ከአለቃችሁ  ከሚካኤል  በቀር   የሚረዳኝ  ማንም  የለም›› ብሎአል፡፡  ስለዚህም  ለኢያሱ   የተገለጠውና  እስራኤላውያንንም  የመራው  መልአክ  ቅዱስ  ሚካኤል  መሆኑን እንረዳለን፡፡ (ዳን.፲፥፳፩) 🍂የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት በሐዲስ ኪዳንም እንደነበር ይህ ነቢይ በትንቢቱ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ  ልጆች  የሚቆመው  ታላቁ  ሚካኤል  ይነሣል›› በማለት  ተናግሮለታል፡፡   ስለዚህም   ቅዱስ  ሚካኤል   እኛን  ከሰይጣን  አሽክላና  ወጥመድ  ይጠብቀንና  በጸሎቱ  በእግዚአብሔር  ፊት  ይቆምልን  ዘንድ  በእኛም  ላይ  ሹም  ነው፡፡ ምክንያቱም  እኛ  የእግዚአብሔር  ሕዝቦችና  የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡  (ዳን.፲፪፥፩) በመጽሐፈ ስንክሳርም ተመዝግቦ እንደምናኘው ቅዱስ ሚካኤል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠርቶለታል፤ እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲያደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲያደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልዳልና፡፡ (ስንክሳር ኅዳር ፲፪) 🍂ስለሆነም በኃጢአት ባርነት ተይዘን በችግር እና በመከራ ውስጥ ተዘፍቀን ለምንኖር ሰዎች ስለ  ሕዝበ  እስራኤል  በእግዚአብሔር  ፊት  የቆመው  ሊቀ  መላእክት  ቅዱስ  ሚካኤል  ለእኛም  ያማልደንና ተራዳኢ ይሆነን ዘንድ በጸሎት እንማጸነው።  🍂 አምላካችን  እግዚአብሔርም  የምሕረት  ፊቱን  ወደ  እኛ  በመመለስ በጸብና  በጦርነት  ምትክ  ፍቅርን፣  ሰላምንና  መግባባትን፤  በመለያየት  ምትክ አንድነትን እንዲሰጠን በቅዱስ ሚካኤል ስም እንለምን። 🙏 #የሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል 🙏 አማላጅነትና ተራዳኢነት  አይለየን፤  አሜን፡፡ / መጽሐፈ ዘኅዳር 12 : መጽሐፈ አክሲማሮስ / ዲያቆን ጌታባለው አማረ የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.