cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኪነት በዮዳኒ

በዚህ የጥበብ ቤት▼▼▼ 🎨ስዕል 📔ወግ 📖የመጽሐፍ ጥቆማ 📚መጽሐፍት 🗒ግጥም 🗣ትረካ 🎭ኪነጥበባዊ መረጃና ትምህርት 📑ወቅታዊ ፅሁፍ ያገኛሉ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 914
Obunachilar
-124 soatlar
+287 kunlar
+3430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ተወዳዳሪ ፍቅረማርያም ኮድ⓽ የሞት ገጽ አየር ላይ የሚንሳፈፍ የወፍ ላባ የሆነ ያህል እየተሰማው ነው፡፡ ንፋሱ እንዳሻው የሚጫወትበት እግሮቹ አየር ላይ ተንጠልጥለዋል በአንገቱ ላይ ገመድ ገብቶ እየተንዠዋዠወ ነው፡ ልክ እንደልጅነቱ፡ ራዕይ ይሁን ህልም ፡ ምትሀት ይሁን ቅዠት ብቻ ከወትሮ የተለየ ነገር ፡የሚያይ ይመስላል፡፡ የሚንቀሳቀስ ጨለማ፡፡ ክንፍ ያለው ጽልመት ወደሱ ይመጣል ፡ የሞት መልዐክ ሳይሆን አይቀርም፡፡ሰውነቱ ለሱ መታዘዙን ትቷል፡፡አይኖቹም እያየኋቸው እራሳቸውን ከድነዋል፣ የሰውነቱም መብራት ጠፍቷል፡፡ የሞት መልአኩም አላስፈቀደውም ለነገሩ እሱም አልጠየቀውም ፡ ብቻ ነጋዴ ወድ እንቁ ከእጁ አምልጦ ሲወድቅበት ለማንሳት እንዲቸኩል ተስገብግቦ አነሳውና ፡ በአክናፉ ጠቅልሎ ወደ አየረ አየራት ተነጠቀ፡፡ ******✿****** ሕይወቴ ልክ እንደ ጨቡዴ ነው ፡ ጨቡዴ የቱ አትሉኝም ፡ ጨቡዴ እንዳንዴ ብዬ እመልስላችሁ ነበር፡፡ ሰኞ ጠዋት ወጥታ እሁድ ማታ የምትጠልቅ ህይወት ፡ ታዲያ እሱም ለታደሉት ነው ፡ ልክ እንደኔ ላሉት ሰኞ ዕለት ፡ ለሰው እንግዳ ለሀገሩ ባዳነኝና እያለቀስኩ ተወለድኩ ማክሰኞ ዕለት ፡ በእንባዬ ተጠመኩ ፡ እርሱንም ገድቤ እየጠጣሁ ለአቅመ አዳም ደረስኩ! እሮብ ዕለት ፡ የደስታ ቀን ፡ ጨቡዴ ያገባበት ቀን ደረስኩ ፡፡ጨቡዴ አግብቶማ እኔ አላጣም በማለት ይህው እኔም የትዳር አጋሬን እየጠበኳት ነው ፡ የመምጫዋ ምልክት ምን ይሆን? አስባለሁ፡ እግዚአብሔር አምላክም እንደ አዳም ከባድ እንቅልፍን አልጣለብኝም፥ አላንቀላፋሁምም፤ ከጎኔም አንዲት አጥንትን አሎሰደም ስፍራውንም በሥጋ አልዘጋውም።የጎኔ አጥንት አሁንም እንዳለ አለ ፡ ጎኔ አልተከፈተም ፡ የጎደለ አጥንትም የለም ፡ የኔ ሄዋን ገና አሎጣችም አሁንም፡ ከጎኔ ተደብቃለች ፡ እስካሁን ጠንካራ አጥንት ናት ስጋም አለበሰችም ፡ እኔም ብቻዬን እሆን ዘንድ መልካም ነው? ፡ አይደለም ! ስለዚህ እኔ ሚስት ሳላገኝ እሮብ አትጨልም!:: ፀሐይ አትጥለቅ ጨረቃም ትዘግይ ፡ በማለት ፡ እንደ ኢያሱ ቀኑን ገዘትኩት ፡ ፍጥረትን ለፍላጎቴ አስገዝቼ ፡ እሷን ፍለጋ ጎዳና ወጣሁ ፡ መሬት መሬቱን አያለሁ ከሰማይ ወድቃስ ቢሆን ብዬ ፡ በአየርም አያታለሁ ፡ ክንፍ ቢኖራትስ እየበረረችስ እንደሆነ እያልኩ ፡ ብቻ ያደክማል ያልፈለኳት ቦታ የለም ፡ እግሬን መጓዝ ቢያቅተው ከአንድ ጥላ ስር ለማረፍ ተገደድኩ ፡ ትንሽ አቅሜን አሰባስቤ አካባቢውን ሳማትር ፡ አንዲት ሴት ፡ ቡና ታፈላለች፡ በተመሳሳይ ሰዓት ፡ አንድ ልጅ አዝማሪ የተሰኘውን የመዘክር ግርማ ስነግጥም መፅሀፍ ታነባለች ፡ እዚ የህይወት መንደር ውስጥ እኔ ህይወቴን አየኀት ፡ ልቤ እኔን ትታ ልትሮጥ ይሁን እርግጠኛ አደለሁም ብቻ ከደረቴ ጋር እየተጋጨች ትቆማለች፣ ለራሴ ነገርኩት የጎንህ አጥንት ያቹዋትና በል ስጋ አልብሳት ብዬ ፡ ስፈራ ስቸር አጠገቧ ደረስኩ ስለምን ላውራት ፡ ግራ ገባኝ ፡ አንዴ ሰማዩን አንዴ ምድሩን አያለሁ ፡ እሷ ሁኔታዬ አስጨንቋት ትኩር ብላ ታየኛለች ፡ ወዲያው የምን መፅሀፍ ነው?" ስል ቀረብ ብዬ ጠየቀኳት የግጥም መፅሀፍ መሆኑን ነገረችኝ ።"አሪፍ ነው?" አልኳት 'አዎ' አለቺኝ "አንዳንዴ ስራ የማይኖርበት ትርፍ ጊዜ ስላለኝ ለማንበብ አስባለሁ " አልኳት "ጥሩ ነው " አለቺኝ "ተማሪ ነሽ?" ጠየኳት 'አዎ ' የት? 'ዩኒቨርሲቲ ገቢ ነኝ' ቀን እየሰራው ማታ እማራለሁ "እረ  ..እኔ ስለተማሪ በሰማሁ ቁጥር ወንድሜ ትዝ ይለኝና ወስጤ ይረበሻል " 'ወንድምክ የት ሄደ ? ስትል መለሰችልኝ የሀዘን ፈገግታ ፈግጌ ሰማይ ቤት ከመለአኩ ጋር አልኳት፡ ******✿******* ምድርን ቁልቁል ሲመለከታት እየራቀች እየረቀቀች ከመኖር ወዳለመኖር ተሸጋገረች ፡ የዓለም ነገር በዚህ የለም ፡ ዙሪያውን በመደነቅ ሲቃኝ በሰፊው ህዋ ውስጥ ብዛት ያላቸው የሚንሳፈፉ ነፍሳትን ተመለከተ ፡ ከእነርሱ መካከል እርሱ ሲታይ እንደ አንድ የዘር ቅንጣት ያለ ነው ፡ ከርቀት ብርሃናቸው ከጽሐይ ሦስት እጥፍ የሚያበሩ ቁጥራቸው ከዝናብ ጠብታ የሚበልጡ መላዕክት አምላካቸውን ያመሰግናሉ፡፡ ከጎኑ የቆመው ግዙፍ የሞት መላዕክ ፡ ጀርባውን መታ አድርጎት አንቺ ነፍስ ፡ ምንድነው በአትኩሮት የምትመለከችው ? ሲል ጠየቀው እሱም ፡ ይህ ከርቀት የሚታየኝ ቦታ የት ነው ? ሲል ጥያቄውን በጥያቄ መለሰ መልአኩም" ገነት ትባላለች የተመረጡ የሚገቡበት ሲል አያይዞ መለሰለት እባክህን እዚያ ውሰደኝ ሲል ተማጸነው ? ትንሽ በማስካካት ከሳቀ በኋላ አንቺ ደግሞ ምን መልካም ነገር አለሽ? እሱም ፡ በመንፈሳዊ ጉባኤያት ላይ እሳተፋለሁ ወደዚህ ከመምጣቴ አስቀድሞም በቴሌብዥን መስኮት ስመለከት የነበረው መንፈሳዊነት ወስጤን ቢያነደው እዚህ ለመድረስ ሞትን በቅሎ አድርጌ ተሳፍሬያለሁ እራሴን ያጠፋሁትም ገነትን የመሰለች ቦታ እግዜርን የሚያህል ጌታ ለማግኘት ነው ሲል መለሰ፡፡ መልአኩም ፡ ተሳስተሀል እዚህ የምትገባው ፡ ሲፈቀድልህ ነበር እኮ ፡ ጠቢቡ ለሁሉም ጊዜ አለው ሲል እንዴት አላስተዋልከውም ፡ ለመወለድ ጊዜ አለው ፡ ለመሞትም እንደዛው ፡ ያለጊዜው የተወለደ ልጅ ጭንጋፍ ነው በእውነቱ ሃይማኖት ነበረህ ፡ ምግባር ግን ካንተ እርቃለች ፡ በይ አንቺ ነፍስ ማደሪያሸ በዚያ አይደለም ወደዚህ ነው እያለ ፡ ወደ እሳት ባህር አመላከተው ፡ በድንጋጤ ፡ ይሄ ምንድን ነው ሲል ጠየቀ እሱም ሲኦል በማለት ነገረው በኋላ ሳቁን ለቀቀው ፡ካ.ካ.ካ በመቀጠል እየገፈተረ ወደ እሳት ባህሩ አደረሰው በል ግባ ያንተ ገነት ይሄ ነው ሲል ገፈተረው ******✿*******
Hammasini ko'rsatish...
ስለወንድሜ የነገርኳትን ለማመን ከብዷታል እንደማፈርም እንመደንገጥም ብላ 'እንዴት ?' አለችኝ "የሜዲስን ተማሪ ነበረ በጣም ጎበዝ ሊመረቅ አንድ አመት ሲቀረው ራሱን አንቆ ገደለ" 'በስመ አብ ምን ሁኖ?' "እኔ ምን አውቄለት ያን ቀን ገብርኤል ቤ/ክ ጉባዔ ቆይቶ አብረን ቡና ጠጥተን ቲቪ ሲያይ ካረፈደ በኋላ ሽንት ቤት ገብቶ እራሱን በገመድ አንጠልጥሎ ገደለ አሁን ይሄን ምን ትይዋለሽ ፡ ለ10 አመታት እስርቤት ውስጥ ነው ያሳለፍኩት ሁሉነገር ሲጨልምብኝ ሰዎች በኔ ሲጫወቱ ፡ ጠጪዎች በኔ ሲዘፍኑ እንኳ ህይወት በቃኝ ብዬ ራሴን አላጠፋሁም ፡፡ እሱን ብሎ መካሪ¡ እ.እ..! አይዞህ ነገ ሌላ ቀን ነው እያለ ሲመክረኝ የነበረው ታንቆ ለመሞት ነው ? "አይዞህ በቃ ተረጋጋ የሚሆነውን ከመሆን አናስቀረውም አሜን ብሎ ከመቀበል ውጪ ብላኝ እርሷም በራሷ የሃሳብ ባህር ሰመጠች እ.እ. ለመናገር አፋን ከፈተች " ዓለም ልክ እንደ ታይታኒክ መርከብ ናት የሆነ ቀን ተሰርታ ያሎነ ቀን ምትፈርስ ፡ ለሃዘን ቀርቶ ለደስታ ጊዜ የሌላት ፡ ሁሉን አጋጣሚ ትሰጣለች ፡ ሳትቀበላት ሁሉን ትነጥቅሃለች ፡ ሕይወት ውብ መልኳን ታሳይሃለች መልክሽ ማማሩ ገና ስትላት እርቃኔን ሳለኝ .. ትጠይቃለች ፡ ቀለም በጥብጠህ ሸራ ወጥረህ መሣል ሳትጀምር ትገልሃለች...ቢሆንም ፡ እልፍ ዓመት የህይወትን ትርጉም እየፈለጉ ከመኖር ፡ የአንድ ጊዜ የመርከብ ጉዞ ያህል ደስተኛ ሆነው መሞት ያማረ ነው፡ የህይወትም ትርጉሙ እርሱ ነው ለልብህ ፣ ለዓይምሮህ ፣ ጥሩ ትዝታ መተው"፡፡ በማለት በየዋህነት መከረችኝ ፡ ሳላቅማማ ተቀበልኳት እኔም ቀበል አድርጌ...እና ተማሪ ሳይ እሱ ትዝ ይለኛል እንዲች ብለሽ እንዳይጨንቅሽ ለማናባቱንስ ሲቀር ይቀራል ራስሽን ጠብቂ እናትዬ " 'እሽ ' "ቡና ልጋብዝሽ ?" እሺታዋን በፈገግታ መለሰችልኝ ፡ አየኋት አየችኝ ወደድኳት ወደደችኝ ፡ ሐሙስ በፍቅሯ ታመምኩ ፣ አርብ ፡ ባሰብኝ ፣ ቅዳሜ ሞተ፣ እሁድ ተቀበረ የሚለውን ቀናት ለጨቡዴ ተውኩለት ዕለቱን እንደቆመ ዘነጋሁት ******✿******* የሞት መንገድ ልዩ ነው ፡ አንዱን ልቡን አንዱን ነብሱን ይቀማል ..........ማብቂያ የለውም ሕይወት በመሞት ውስጥ ይቀጥላል ✍️ፍቅረማርያም @gbw_dan
Hammasini ko'rsatish...
3
ተወዳዳሪ:ፍቅረማርያም መወዳደሪያ:✍️ጽሁፍ CODE⓽ ROUND ❷Anonymous voting
  • 10
  • 9
  • 8
  • 7
  • 6
  • 5
  • 4
  • 3
  • 2
  • 1
0 votes
ተወዳዳሪ:Ikram Kedir መወዳደሪያ:✍️ጽሁፍ CODE⓼ ROUND ❷Anonymous voting
  • 10
  • 9
  • 8
  • 7
  • 6
  • 5
  • 4
  • 3
  • 2
  • 1
0 votes
CODE⓼ ROUND ❷ የህይወት ወለላን ጨምቄ በሰባት የሞት ዋንጫዎች ሞላሁት ። ህመም እንዳይሰማኝ በወይን ዘለላ ሰፈርኩት ። እያንዳንዱን ዋንጫ ጨልጬ ወደ ኋላ ወረወርኩት ። የቱ ጋር ይሆን ያረፈው የቱስ ጋ ይሆን የተሰበረው ። ወድቆ ሲያቃጭል ንፋሱ ጎጆዬን ሞት ደሞ እኔን ሊጥለኝ ይታገላል ። ታዲያ ስብራቱ እንዴት ይሰማኛል ። ትላንት ከትላንት ወዲያ ነፍሴ ስትሰባበር ሀሴትን ወደ ውስጡ እያንቆረቆረ በደስታ ሲዘምር ነበረ ዛሬ ደሞ ከውስጡ ሀዘን እየደፋ ለምንድ ነው ነገ ደርሶ በኔ የሚከፋ ። ይልቁንም በወይኑ ጣዕም ህመሜን እንደረሳሁት እሱም ስብራቱን ይርሳ ። ህመሙን እያባበለ ቁስልን ከመፍጠር ውጪ ምን ሊያተርፍ ነው ተጋድሞ የሚያነባው ። እምባው ፈሶ ወርዶ አያሽርለት ፤ ዋንጫነቱን አይመልስለት ። በማንባት የሚሽር ቢሆን ባህርን ፈጥረን ህመማችንን ባሰመጥነው ፤ ጎጆዋችንን አቅንተን ሞትን በመለስነው ። ግና በሰመጠ አፍታ ገፃችን ከደስታ ሳይፋታ ከላዩ አንሳፎ መኖሩን ያስታውሰናል ፤ የወይኑ ጣዕም ጠፍቶ የህይወት ምሬት ይገባናል። ወይኑስ እንዴት ያለ ግብዝ ነው ጣዕሙን ለመግለጥ ፡ ካፈር ገብቶ ለመረገጥ ዋንጫውን አሳልፎ የሚሰጥ። ✍️ኢክራም ከድር @gbw_dan
Hammasini ko'rsatish...
👍 1👏 1
ተወዳዳሪ:ኤልያስ ገላሼ መወዳደሪያ:✍️ጽሁፍ CODE⓻ ROUND ❷Anonymous voting
  • 10
  • 9
  • 8
  • 7
  • 6
  • 5
  • 4
  • 3
  • 2
  • 1
0 votes
CODE⓻ ROUND ❷ አይኖቻችን ሳይከፈቱ ፤ ፀሐይ ተራራን ሳትሰነጥቅ ፤ ተፈጥሮ በለገሰቻቸው ጥበብ ፡ ወደ ግራ ፣ ወደ ቀኝ ፡ እያረገዱ እፅዋት ምድርን ሲያጅቡ ፡ አእዋፍ በዜማ ፤ ቤተ እምነቶች በፀሎት ፡ ቀናችንን ሊባርኩ ሲሰናዱ ፥ ለእርሱ ግን የሒሊናውን ሞት የሚለፍፉ ፡ ነብያተ ሰይጣን ነበሩ ፤ የሕሊናው ሬሳ ቅርናት : እሰከ ሒወተ ልኩ ድረስ : እንደሚጠነባው የሚተነብዩ ። ኑሮ ያልቀናትን ፥ ያዘመመች ጎጆ ፡ ባለችበት ደግፎ ፡ ለማቆየት ለሚፍገመገመው ፡ ብረቱ ግን ፡ አእዋፍ ዛሬ ሙሾ ተቀኙ። መርጦ አልቃሽ አይደለም ። ወታደር ነው ፤ ወታደር መርጦ አያለቅስም። ቤቱ በራፍ ላይ ቆሞ ፡ ማደሪያ ጎጆውን ፡ የመገላመጥ አይነት ፡ ከታች ጀምሮ ፡ እስከጣሪያዋ ድረስ ፡ ይመለከታታል ፤ አይኖቹ የማይፈስ እንባ ይቋጥራሉ ። እዚች የባለቤቷ ፡ መለዋወጥ ያልቀናት ፡ ጎጆ ውሰጥ ፡ እልፍ እመአእላፍ ታሪኮች ፡ በየስርቻው ወደቀዋል ። ባለቤቷ በተለወጠ ቁጥር ፡ እየረገጣቸው ፡ የነበራቸው መልክና ክብር ፡ ፈፅሞ ተቀይሯል። ብዙ ንፁሀን ፡ ሰዎች በእጁ ላለቁበት ፥ ነገር ግን ፡ ለሰው ነብስ ቀርቶ ፡ የሰውን ስጋ ፡ ለሚቀራመቱት ፡ ለእነዚያ አሞሮች ፡ ነብስ ለሚጨነቅ ፡ ለሱ ፡ በዚህ ዘመን መገኘት ፡ ውድቀት ነው ። ተፈጥሮን ሊሞገት ፡ ወደ ሰማይ ፡ ያንጋጥጣል ። ለፈጣሪው ዘወትር ፡ እንዲህ እያለ ያንሾካሹካል ..... " የምኖረውን የፃፍክልኝ አንተ ፤ የወደፊቱን የምታውቅ አንተ ፡ ስለምን? የክፋት መሸጋገሪያ ፡ ድልድይ ታደርገኛለህ?" " ሰው የተፃፈለትን ፡ የሚኖር ከሆነ ፡ በሚያጠፋው ጥፋት ስለምን? እሱ ብቻ ይጠየቅበታል ? የፃፈለትስ ?" ጊዜ የጫነበትን ነቀርሳ ፡ ከትከሻው ማውረድ አይችልም ። ብዙ ነብሶች ፡ የሚጮኹበት ህሊናውን ፡ ማሳረፍ አይችልም ። የጋራ መኖሪያ ፡ ጎጆዋችንን ለመጠበቅ ፡ ብዙ ንዑሳን ፡ ጎጆዎችን አፍርሷል ። ትልቅ ንፁህ ፡ ሀገር ለመፍጠር ፡ መጥፎዎች መጥፋት ፡ አለባቸው ። ስለነሱ ክፋት ፡ ንፁህ ነብሶች ፡ በእጁ ዋጋ ከፍለዋሉ ። ምክንያቱም እሱ ወታደር ነው። ስለ ብዙሀኑ ሲል የንፁሀን ነብስ ህሊናውን ያሰረበት ፤ ወታደር ነው ፤ መረጦ አልቃሽ አይደለም ፤ ወታደር መርጦ አያለቅስም ፤ ስለ ሁሉም ንፁህ ነብስ ፡ እኩል ያነባል እንጂ...... "ህሊናቸው ለሚያስጨንቃቸው ንፁህ ወታደሮች ይሁንልኝ።" ✍️ኤልያስ ገላሼ @gbw_dan
Hammasini ko'rsatish...
🫡 2
CODE⓺ ROUND ❷ አየሁኝ አንዲት ሴት ÷ በአንዲቱ ገጿ ብዙ ሀሳቦችን በአንዴ የምትገልፅ ተዘነጋኝ እንጂ የሆሄው ድርደራ በፊደል ልቀልፅ በአርምሞ ሳያት ስዕል የምትመስል ከሀሳቤ መንገድ ከምናቤ መሀል የኑሮዋን ክታብ መዝገብ ስቆነፅል ለማኖር መሞትን ከግብሯ ስቀፅል ይህንን አየሁኝ ይሄን አስተዋልኩኝ የደረተው ልብሷ ገጿን ቢሸፍንም አተኩሮ ላያት ከውበቷ አንጻር ከመልኳ አኳያ የጨርቁ መቆሸሽ ምንም ነው ምንም ከእግልቱ ብዛት   ጠቁሮ     የገረጣው ፊቷ ከመከራው ብዛት ቅርጽ አልባ የሆነው አቋም አካላቷ ከበፊት ለሚያውቋት ደረትን ያስደቃል ያስወርዳል ሙሾ ታክማለች ቢሉም በየት በኩል ትዳን መልሶ እየመጣ የህመሟ ግርሾ በገረጣው ቅንድቧ ስር የማያቸው አይኖች እንቁ ይመስላሉ አይቶ ላስተዋለ በአዕምሮ ውስጥ ያለን የሀሳብ ሞገድን ገተው ያቆማሉ ለሚጠሯት ሁሉ ፈገግ ትላለች ከንፈሯ ሲከፈት በጥርሶቿ ንጣት ፀሀይዋ ታፍራለች ለዛችው ቅጽበታት በዚያችው ሰዓታት በእውነት ታፈዛለች ምን ቢያማትም እንኳን ለሠው ትስቃለች እውነትም እውነትም እናት ነች በደመነ ፊቷ የተገራረደው ቁጥብ ፈገግታዋን በደንብ ላስተዋለው ግሩም ቁንጅናዋ አዋራ የሸፈነው ተመን ማይወጣለት ዕንቁ ነው ሚመስለው ጠጅ በመሸጥ ውስጥ ራሷን አታለች በዚህም ምክንያት ክብሯን ተገፋለች ተስፋዋን አታለች ሀብቷን ተነጥቃለች እንደምትታየው በጣም ጎስቁላለች ለሞት የቀረበ ድካምን ደክማለች እንዲ ለመሆኗ ዋና መንስኤዎቿ በየዘመናቱ አግብተው የፈቱት ስግብግብ ባሎቿ ከአባቶቻቸው ራስወዳድነት ጭካኔ የወረሱት አመለ ዥንጉርጉር የከፉት ልጆቿ እንደያመላቸው ጀግና ወይም ፈሪ አባቱ ሲረግጣት ልጁ ደሞ አባሪ ጎበዝ እና ሰነፍ ከጠላት የሚያብርለናቱ መገረፍ ለጋስ ወይ ቂመኛ ከቤቱ የሚዘርፍ ከራሱ ለራሱ የሆነ ቀማኛ ከሀዲ መለስ ብሎ አማኝ በእናቱ ቤት ውስጥ ፍርፋሪ ለማኝ ሆነው   ከማህጸኗ ወተው ቢወለዱም እንኳን ለርሷ ቀርቶ ለራሳቸው አረቡም በእኩልነት ሚዛን ምዘና ቢለኩ ከፍቅራቸው ይልቅ ክፋቱ መዘነ በሚሰሩት ስራ ረሀብ ጦርነት እድላቸው ሆነ ግን ይህ ሁሉ ሆኖ ህመሟን ሚያስታግስ አንድ እንኳ ቢጠፋ ይህች ምስኪንእናት ይህች ምስኪን ሴት አላት ትልቅ ተስፋ ከገጠማት ችግር ከአካሏ መራቆት ይበልጣል እጅጉን የመንፈቅ ልዕልና የነፍሷ መናፃት ከቶ በምን ይሆን ልቤ የተመካ በምን ሚዛን ይሆን ተስፋሽ የሚለካ        እንደ ቅዱስ ያሬድ ጥኡም አንደበቱ        ዜማ እንዳወረሱት ስሉስ አዋፋቱ        እስኪገለጽልኝ የቃል አቡሻህር የፊደል እትብቱ        ጥቂቷን ቆንጥሬ በየውጣ እስካውቀው ቅኔን ከነስልቱ        ይቅርብኝ መናገር ስላንቺ ማውራቱ        ግፍ ከሚሆንብኝ የዕድሜሽን ሁዳዴ በቃላት መግደፉ         ይቅርብኝ ልከልከል አንቺን ከመጻፉ         አንደበቴ እስኪያድብ ከመጎላደፉ @gbw_dan
Hammasini ko'rsatish...
👏 2
ተወዳዳሪ:ህሉ መወዳደሪያ:✍️ጽሁፍ CODE⓺ ROUND ❷Anonymous voting
  • 10
  • 9
  • 8
  • 7
  • 6
  • 5
  • 4
  • 3
  • 2
  • 1
0 votes