Andu personal Edu. Consultant and Trainer
Kanalga Telegram’da o‘tish
Channel Objectives: 1. Use simple, accessible, and modern methods to enhance teaching. 2. Reduce teacher workload to improve efficiency and focus. 3. Strengthen school systems and administrative processes. 4. Ensure ongoing access to current knowledge and
Ko'proq ko'rsatish2 505
Obunachilar
-424 soatlar
+67 kun
+3730 kun
Postlar arxiv
ማንኛውም ተቋም የትምህርት ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት የቀጣይ ዓመት የአዲስም ሆነ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ማካሄድን የሚከለክል ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለአስተያየት ክፍት ተደርጓል።
• በመመሪያው መሰረት ከበጋው ትምህርት ውጪ በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ሰበብ መደበኛውን ስርዓተ ትምህርት ማስተማር የተከለከለ ሲሆን ፤ ማጠናከሪያ ወይም የክረምት ትምህርትን ምክንያት በማድረግ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ማራቅ፣ ለፈተና እንዳይቀመጡ ማድረግ ወይም ምዝገባ መከልከልም አይቻልም።
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን፣ ፍትሃዊነትንና ተገቢነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ወጥ የሆነ አሰራርና ተጠያቂነትን ለመዘርጋት ያስችላል ያለውን "የአጠቃላይ ትምህርት የእውቅና ፍቃድና እድሳት አሰጣጥ መመሪያ (ረቂቅ)" አዘጋጅቶ በትምህርት ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጥባቸው ክፍት አድርጓል።
ረቂቅ መመሪያው በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ በሚገኙ የመንግሥት፣ የግል እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ በመደበኛ ትምህርት ቤቶች ብቻ ሳይወሰን በርቀት ትምህርት፣ በማጠናከሪያ ትምህርት (ቲቶሪያል)፣ በመሰረታዊ ቋንቋ ማሰልጠኛዎች እና በማማከር አገልግሎት ላይም የሚተገበር ነው።
እንደ ረቂቅ መመሪያው ድንጋጌ፣ የትምህርት ተቋማት እውቅና ፈቃድ ለ2 ዓመታት የሚያገለግል ሲሆን እድሳቱም በየሁለት ዓመቱ የሚከናወን ይሆናል።
አዲስ ለሚቋቋሙ ተቋማት የሚሰጠው የቅድመ እውቅና ፈቃድ ደግሞ የአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ይኖረዋል።
የቅድመ አንደኛ፣ የአንደኛ ደረጃ (1ኛ-6ኛ ክፍል)፣ የመካከለኛ ደረጃ (7ኛ-8ኛ ክፍል) እና የማጠናከሪያ ትምህርት ፈቃድና እድሳት በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች በኩል ይሰጣል።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (9ኛ-12ኛ ክፍል)፣ የቋንቋ ማሰልጠኛዎች፣ የርቀት ትምህርት እና የማማከር አገልግሎቶች እውቅና ፈቃድና እድሳት ደግሞ በማዕከል በትምህርት ቢሮው ደረጃ ይሰጣል።
የትምህርት ተቋማት እንደ አገልግሎት ዘርፋቸው በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ብቻ ማመልከት እንዳለባቸው ረቂቁ ደንግጓል።
በዚህም መሠረት ለአዲስ አጠቃላይ ትምህርት ተቋም የቅድመ እውቅና ማመልከቻ ከመጋቢት 1 እስከ ሚያዝያ 30፣ ለእውቅና እድሳትና እርከን ማሳደግ ከየካቲት 1 እስከ መጋቢት 30 ድረስ ብቻ በአካል ወይም በበይነ-መረብ ማመልከት ይቻላል።
የርቀት ትምህርት ለአንደኛ ወሰነ ትምህርት ከግንቦት 1 እስከ ሰኔ 30፣ እንዲሁም ለሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ከኅዳር 1 እስከ ታኅሣሥ 30 ድረስ ማመልከቻዎችን ይቀበላል።
የቋንቋ እና የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጡ ደግሞ አገልግሎቱን ከመጀመራቸው 1 ወር አስቀድመው ማመልከት አለባቸው።
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ያላመለከተ ተቋም አገልግሎቱን ማግኘት እንደማይችል ተመላክቷል።
አዲስ የሚቋቋሙ ተቋማት የቅድመ እውቅና ፈቃድ ለማግኘት ከተቀመጠው ስታንዳርድ ቢያንስ 85 በመቶ ማሟላት አለባቸው፤ በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ ቀሪውን 15 በመቶ አሟልተው 100 በመቶ ሲደርሱ ሙሉ እውቅና ያገኛሉ።
በመጀመሪያው ዙር ምዘና 100 በመቶ ያሟላ ተቋም ግን በቀጥታ ሙሉ እውቅና ይሰጠዋል።
በረቂቁ ድንጋጌ መሰረት የተሟላ እውቅና ፈቃድ እና እድሳት የሚሰጠው መመዘኛዎቹን 100 በመቶ ለሚያሟሉ ተቋማት ብቻ ነው።
ለልዩ ፍላጎት ትምህርት ብቻ የተቋቋሙ ማዕከላት ግን የእውቅና እና የእድሳት ፈቃድ ለማግኘት ከተቀመጠው ስታንዳርድ ቢያንስ 65 በመቶ ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው በረቂቁ ተመላክቷል።
ምዘና ተካሂዶ ውጤቱ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚገለጽ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዙር ያላሟሉ ተቋማት በ30 ቀናት ውስጥ ክፍተታቸውን አርመው ለአንድ ጊዜ ብቻ ዳግም እንዲመዘኑ ይደረጋል።
እንዲሁም ተቋማት ባስመዘገቡት ግብዓት መሠረት እየሰሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከኅዳር 1 ጀምሮ ድህረ-እውቅና ምዘና ይካሄዳል።
የትምህርት ተቋማት ስለሚሰሩበት ግቢ እና ሰነዶች በተመለከተም ተቋማቱ በራሳቸው ግቢ የሚሰሩ ከሆነ የተረጋገጠ የይዞታ ካርታ ማቅረብ አለባቸው።
የራሳቸው ሕንፃ የሌላቸው ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ለሁለት ዓመት የትምህርት ዘመን የሚቆይ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የኪራይ ውል እና የይዞታ ካርታ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ይዞታቸው ካርታ የሌለው ከሆነ ለአንድ ጊዜ እድሳት ብቻ የሚያገለግል የባለቤትነት የመሬት ይዞታ ደብተር ወይም ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
በተጨማሪም የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጡ ባለሙያዎች በመምህርነት ሙያ ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እና ቢያንስ የአምስት ዓመት የማስተማር ልምድ ሊኖራቸው ይገባል።
የርቀት ትምህርት ተቋማትም የተማሪዎች የፊት ለፊት ገለጻና የቤተ-ሙከራ አገልግሎት የሚሰጡበትን ቦታ ከትምህርት ቤቶች ጋር ውል ገብተው ማቅረብ እንዳለባቸው ተደንግጓል።
ተቋማት ተማሪዎችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የመቀበል ግዴታ ያለባቸው ሲሆን አማካይ ውጤትን፣ የባህሪ ሪፖርትን፣ ደረጃን ወይም የቅድመ ቅበላ ፈተናን መሠረት በማድረግ በተማሪዎች ላይ ቅድመ ሁኔታ መጣል አይቻልም።
ፆታን፣ ሃይማኖትን፣ ብሔርን፣ ማህበራዊ መሠረትን፣ ፖለቲካዊ አመለካከትን ወይም የልዩ ፍላጎት ሁኔታዎችን (አካላዊ፣ አእምሯዊና ስነ-ልቦናዊ) መነሻ በማድረግ መከልከልም ሆነ አድሎ መፈጸም በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ማንኛውም ተቋም የትምህርት ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት የቀጣይ ዓመት የአዲስም ሆነ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ማካሄድ አይችልም ይህን ጥሶ የተገኘ ተቋም ምክርና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ካላስተካከለ ለ1 ዓመት እውቅና ፈቃዱ ይታገዳል።
ማጠናከሪያ ትምህርት በወላጆችና ተማሪዎች ፈቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆን አለበት ተብሏል።
ከበጋው ትምህርት ውጪ በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ሰበብ መደበኛውን ስርዓተ ትምህርት ማስተማር የተከለከለ ሲሆን፤ ማጠናከሪያ ወይም የክረምት ትምህርትን ምክንያት በማድረግ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ማራቅ፣ ለፈተና እንዳይቀመጡ ማድረግ ወይም ምዝገባ መከልከል እንደማይቻል መመሪያው አስቀምጧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
