cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Tibeb Media Ethiopia

ህጋዊ ፍቃድ ያለው የተእማኒ የመረጃ ምንጭ ሙያዊ ስነምግባር መርሃችንነው ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
45 966
Obunachilar
-5124 soatlar
-2897 kunlar
-1 20130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ዋርካ አካዳሚ ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2016 ተመረቀ ፡፡ Journalist Abdlwehab Bilall የዋርካ አካዳሚ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምርቃት ስነስርዓት ቅዳሜ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ተጋባዥ እንግዶችና የሚድያ ባለሙያዎች በተገኙበት ተካሄዷል ፡፡ የምርቃት በዓሉ አከባበርም በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ቀጥሎ ግንቦት 10 እና 11 ለሁለት ቀን በሚዘልቅ የካርኒኒቫል ፌስቲቫል ይከናወናል፡፡ ለሁሉም ክፍት በሆነው በዚህ ዝግጅት ላይም ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በተለያዩ ጨዋታዎች፣ ምግብና መጠጦች መዝናናትና ትምህርት ቤቱን መጎብኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡ ዋርካ አካዳሚ ከትምህት አመራርና ፔዳጎጂ፣ ከሳይኮሎጂ፣ በዓለም አቀፍ ኪነጥበብ፣ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ከባንኪንግና አለምአቀፍ ፋይናንስ አመራር ሙያዎች በተውጣጡ ባለሙያዎች የተቋቋመ ተቋም ነው። በመጪው 2017 የትምህርት ዓመት ትምህርት ቤቱ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍሎቸን በመክፈት ትምህርት ይጀምራል፡፡ ዋርካ አካዳሚ የተማሪዎችን የፈጠራ መንፈስ የሚያነቃቃና በትምህርትና ብቃትናበቴክኖሎጂ እውቀት የሚጎለብቱበት ከባቢ ለመፍጠር አልሞ የተነሳ የትምህርት ተቋም ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ በአንድ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን ብዛት እስከ 25 ብቻ በመጠን ለእያንዳንዱ ተማሪ ተገቢውን ትኩረት በመስጠትና የአገር ዓቀፉን ካሪኩለም ህግ ተከትሎ የዋርካን ግቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት በሚያዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ተማሪዎቹን በአገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ አቅዷል፡፡ ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማሩን ሂደት በሚያግዙ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች የተሟላ ሲሆን ተጨማሪ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ከውጪ በማስገባት ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ ዋርካ ከትምህርት ልህቀት በተጨማሪ የተማሪዎችን ሁለገብ እድገት ላይ የሚያተኩሩ ዘዴዎችንና ስርዓቶችን በመቅረጽ ልጆች በሰብአዊ ክህሎታቸው፣ በስነምግባር፣ በባህሪና በአካል የሚገለጽጉበትን ሁኔታ ለመፍጠር ይሰራል፡፡ ትምህርት ቤቱ ለመምህራንና ሰራተኞች ተከታታይ ስልጠናዎችን በመስጠት ጥራትን ለመጠበቅና ለማሻሻል የሚሰራ ሲሆን በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ መምህራኑ መካከል አብሮ የመስራት ሂደቶችን በመቀየስ ወጥ የሆነ የትምህርት ጥራትና የምዘና መስፈርቶች ለመፍጠር አቅዷል፡፡ በአገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ የትምህርተት ተቋማት ጋር ትብብር በመፍጠር ተጨማሪ እሴቶችን መሰብሰብም የእቅዱ አንድ አካል ነው፡፡ እስካሁንም ዋርካ ደቬንቸር ከተሰኘው በስዊዘርላንድ የሚገኝ ተቋም ጋር ስምመነት ያደረገ ሲሆን፣ ደቬንቸር ለዋርካ መምህራን የኦንላይን ስልጠናዎችን በመስጠት በተፈለገው መስክ ኤክስፐርት የሆኑ አማካሪ ባለሙያዎችን በማቅረብና ወደፊትም ፈቃደኛ መምህራንን በዋርካ አካዳሚ በማምጣት የልምድ ልውውጥ ለማድረገ ተስማምተዋል፡፡ የዋርካ አካዳሚ ከወሰን ካራ መንገድ አቤም ሆቴል መስቀለኛ መንገድን ወደ ግራ ታጥፈው 50 ሜትር ላይ ይገኛል:: Tel: 0904-770088 0933 501212 0116609186
Hammasini ko'rsatish...
👍 5 1
ኤስ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት የብዙዎችን ህይወ በመለወጥ ስራ ላይ መቆየቱን ገለፀ ። Journalist Abdlwehab Bilall @top fans ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት የቤተሰባቸውን እንክብካቤ ያጡ እና የቤተሰባቸውን እንክብካቤ ለማጣት በአደጋ ላይ ያሉ ህጻናት የቤተሰብ እንክብካቤና ጥበቃ አግኝተው እንዲያድጉ ለሁለንተናዊ እድገታቸው የሚያስፈልገውን ሁሉ በማሟላት እንክብካቤ ሲሰጥ መቆቱን የገለፀው ተቋሙ። ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ለሚገኙ ህጻናት ያጡትን ቤት እና ቤተሰብ በመተካት ያላቸውን እምቅ ችሎታ ለማውጣት እንዲረዳቸው አቅማቸውን ለማጎልበት የሚረዷቸው የተለያዩ እድሎችን በመፍጠርና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እንዲያገኙ በማድረግ ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት ለህጻናቱ የተስፋ ብርሃን አብሪ ፈንጣቂ ሆኖ ህጻናቱን ሲያገለግል መቆየቱ ተዘግቧል። ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ በሀገራችን ስራውን ከጀመረበት ከ966 ዓ.ም ጀምሮ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የበርካታ ህጻናት፣ ቤተሰቦችንና ማህበረሰቦችን ህይወትየመለወጥ ስራን ከሰሩትና በመስራት ላይ ካሉት ድርጅቶች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ መሆኑ ተቋሙ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አሳውቋል ። የድርጅቱ ልዩ መገለጫው በሆነው የቤተሰብ እንክብካቤ በማጣታቸው ቤትና ቤተሰብ ለሚያስፈልጋቸው ህጻናት ቤተሰብን በመመስረት፣ ህይወትን የምትጋራቸው እናትና ስሜታዊ ቁርኝትን በማዳበር አለኝታ የሚሆኗቸው እህትና ወንድም አግኝተው በቤታቸው ብሎም በመንደራቸው ውስጥ ህይወትን የማ ጋሩበትን ከባቢ በመፍጠር በውስጣቸው ያለውን እምቅ ችሎታ አውጥተው ተጠቅመው በሁለት እግራቸው የሚቆሙ የህብረተሰቡ አንድ አካል መሆን እንዲችሉ ለእነዚህ ህጻናትና ወጣቶች አስፈላጊውን ሁሉ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል ። ድርጅቱ በቤተሰብ እና ማህበረሰብ አቅም ግንባታ ፕሮግራሞቹ የአያሌ ቤተሰቦችንና ማህበረሰቦችን አቅም በማጎልበት ህጻናት ዘላቂነት ያለው የተሻለ እንክብካቤና ድጋፍ አግኝተው ማደግ የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ተግባሩን በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ላይ ሲሰራ መቆየቱንም አስታውቋል ። ድርጅቱ በአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ ድጋፍ ፕሮግራሞቹም በተፈጥሮም ይሁን በሰው ሰራሽ ችግሮች ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የማህበረሰብ አባላትም የተለያዩ የእለት እና የመልሶ ልማት ስራዎችን ከውኗል። የድርጅቱን የልማት ስራዎች ዘላቂነት ለማስቀጠል ይረዳም ዘንድ ከተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ መዋቅሮችን የሁለንተናዊ አቅም ማጎልበት ስራዎችን ሰርቷል። በአጠቃላይ፣ በአማራጭ የቤተሰብ ክብካቤ፣ በቤተሰብ እና ማህበረሰብ አቅም ግንባታ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ በትምህርት፣ ጤና እና በወጣቶች ማብቂያ ፕሮግራሞቻችን ከ 8,100,000 በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ለመድረስ ችሏል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 6
DMC ሪልእስቴት በሜቆዶኒያ ለሚገኙ ከ500 በላይ አረጋዊያን የምሳ ግብዣ አደረገ ። በግምባታው ዘርፍ የካበተ ልምድ በማዳበር ወደ ሪልእስቴት ዘርፍ የተቀላቀለው DMC ሪልእስቴት ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት በመቄዶንያ ለሚገኙ አረጋዊያን የምሳ ግብዣ ያደረገ ሲሆን በቀጣይነት ማእከሉን ለመደገፍ ቃልገብተዋል ። የDMC ከፍተኛ አመራሮች አያት የሚገኘውን ማእከሉን የጎበኙ ሲሆን ። በቦሌ በቅርቡ የተገነባውን የሪል እስቴቱን ቢሮ የሜቆዲንያ አረጋዊያን መርቀውታል። ድርጁቱ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም እንደየ ደረጃው እጅግ ዘመናዊ ግርግዳ ያማይጋሩ አፓርትመንት ቤቶች በለቡ መብራት ሀይል ሳይት በመገንባት ለገበያ አቅርቧል ። ከስቲዲዮ እስከ አራት መኝታ ያላቸው እጅግ ልዩና ዘመናዊ ቤቶችን ለሽያጭ ያቀረበ ሲሆን ። በሁሉም ቤቶች ቅናሽ መደረጉም ተገልጿል ። የለቡ መብራት ሀይል ሳይት አለም አቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ለነዋሪዎች አስፈላጊውን ሁሉ አቅፎ ያየዘ መሆኑም ተዘግቧል ። DMC እንዳስታወቀው ቤቶቹ እጅግ ዘመናዊና ቅንጡ ቢሆኑም የቤቶቹ ዋጋ የማህበረሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበ ሲሆን የባንክ ብድርም የተመቻቸ መሆኑ ተዘግቧል
Hammasini ko'rsatish...
5👍 2
የድምፃዊት ቻቺ ታደሰ ደርሷል ሰአቱ ነጠላ ዜማ እንደሚለቀቅ ተገለፀ። ይህን ነጠላ ዜማ በዋናነት በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶች እንዲቆሙ የሰላም ጥሪ የሚያስተላልፍ የሙዚቃ ስራ እንደሆነ ተዘግቧል ። የሙዚቃው ግጥምና ዜማ በቻቺ ተዳሰነ በወንድሟ ጳውሎስ ታደሰ የተሰራ ሲሆን ማስተሪንጉን ኪያለም ሰርቶታል ። በዚህ ሙዚቃ ቅንብር ምንም አይነት የኮምፒውተር ስራ ያልተቀላቀለበት ሲሆን ሙሉ ስራው በሙዚቃ መሳሪያዎች ላይቭ ቅጂ የተሰራ ነው ። በአጠቃላይ የሙዚቃ ስራው በሙያው ብዙ ልምድ ያካበቱ ና ጥልቅ የሙዚቃ እውቀት ያላቸው ባለሞያዎች የተሳተፉበት እንደሆነ ድምፃዊቷ ለጋዜጠኞች በሰጠችው መግለጫ አስታውቃለች ። ይህ ሙዚቃ ዛሬ ከ10 ሰአት ጀምሮ በቻቺ ታደሰ ዩትዩብ ቻናል ይለቀቃል ። ድምፃዊቷ ከሙዚቃው ስራ በተጨማሪ በውጭ ሀገር የሚወለዱ ኢትዮጵያዊያን ሀገራቸውን እንዲያውቁ የሚያስችል ፕሮጀክት ቀርፃ እየሰራች እንደሆነ አስታውቃለች ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 11
👍 9🥰 1
የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም ለመገንባት ሁሉም የእምነቱ እንዲረባረብ ተጠየቀ ። Journalist Abdlwehab Bilall የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም አካባቢ ለማልማት እና በገዳሙ ዙሪያ ተጠግተው ቤት ሰርተው እየኖሩ የሚገኙ ዜጎች ካሳ በመክፈል ገዳሙን ለማስፋት የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር በካፒታል ሆቴል የፊታችን ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት እስከ ለሊት 6:00 ሰዓት በካፒታል ሆቴል እንደተዘጋጀ ገዳሙ አሳወቀ። «የአባቶቼን ርስት አልሰጥም» በሚል መሪ ሐሳብ በሚዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ላይ ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ የሶማሌ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሁሉም ምዕመናን እንዲሳተፉ በዛሬው እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጥሪ አቅርበዋል። የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም በዓላውያን መንግስታት ዘመን በደረሰበት መከራና ፈተና የተነሣ ተዳክሞ በመቆየቱ የገዳሙ የይዞታ ቦታ በመሉ በአካባቢው አርሶ አደር እና በሌሎች ጥቃቅን ነጋዴዎች እጅ ከገባ አያሌ ዘመናትን ያስቆጠረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድነት ገዳሙ ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን ተከትሎ በርካታ አባቶች መነኮሳትና እናቶች መነኮሳይያት ወደ ገዳሙ በመግባት በመልሶ ማቋቋም ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ቢሆንም የገዳመ ይዞታ ለረጅም ዘመናት በሌሎች ግለሰቦች እጅ ተይዞ በመቆየቱ ምክንያት እንኳንስ ለገዳሙ ልማት ይቅርና ለመነኮሳቱ መጠለያ ቤት መሥሪያ ቦታ በመጥፋቱ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙ የቦታውን ጥበት አስመልክቶ መፍትሔ እንዲሰጠው ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርቦ በገዳሙ ዙሪያ ሰፍረው የሚገኙት አርሶ አደሮች በሙሉ የቦታቸው እና የቤታቸውን ግምት ካሣ እየተከፈላቸው ቦታውን ለቀው ለገዳሙ እንዲያስረክበ በመወሰኑ አንድነት ገዳሙ በእጅጉ የተደስተ ቢሆንም ከቦታው ለሚነሱት አርሶ አደሮች የካሣ ግምት እንዲከፍል የተወሰነው ገዳሙ በመሆኑ እና ገዳሙ ደግሞ እንኳንስ ለካሣ የሚከፍለው ይቅርና ለገዳሙ መነኮሳትም የእለት ምግብ እየሸመተ /እየገዛ/ የሚኖርና በቂ ገቢ የሌለው በመሆኑ የካሣውን ግምት መክፈል ባለመቻሉ ችግሩን የበለጠ ውስብስብ አድርጎታል፡፡ ከ251 በላይ መናኒያን ፣ ከ300 በላይ የአብነት ተማሪዎች እና ከ30 ሺህ እስከ 50 ሺህ ጸበልተኞች ተቀብሎ እያስተናገደ የሚገኘው የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም የቦታ መጥበብ ዘለቄታዊ ችግር ለመፍታት እና በገዳሙ ዙሪያ ለመስራት ለታሰበው የልማት ስራ ለመስራት በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ላይ በመላው ዓለም የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ ልጆችና የጻድቁ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግል ወዳጆች፣ እንዲሁም በጎ አድራጊ ግለሰቦችና ድርጅቶች እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል። የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብሩ ኢቲ አርት ፣ ቋንቋየነሽ ፣ መንክር ፣ ነጋሽ ሚዲያ እና ሌሎችም መንፈሳዊ ሚዲያዎች በእለቱ በየማህበራዊ ድረገጾቻቸው በመላው አለም ለሚገኙ ተመልካቾች በቀጥታ መርሐግብሩን እንደሚያስተላልፉ ተገልጿል። ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም ከባህር ዳር ከተማ ሰሜን ምሰራቅ አቅጣጫ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ላጉና ቀበሌ አስተደደር ውስጥ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ውበት የተነባበሩበትና በርካታ መነኮሳት የከተሙበት ታላቅ የአንድነት ገዳም እናገኛለን፡፡ ይህ ገዳም የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ገዳም ሲሆን ገዳሙ ተፈጥሯዊ ውበትን ከታሪክ ጋር አጣምሮ የያዘ በሀገራችን ከሚገኙት የአንድነት ገዳማት አንዱ ነው፡፡ ገዳሙ የተመሰረተው በ1574 ዓ.ም በፃድቁ በአቡነ ሐራ ድንግል እንደሆነ ይነገራል፡፡ በቦታውም ፃድቁ አቡነ ሐራ ለ49 አመታት ያህል ሲፀልዩበት ኑረዋል፡፡ በ1626 ዓ.ም በአፄ ሱስኒዮስ ዘመነ መንግስት የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በአፄ ፋሲል እና በፃድቅ በአቡነ ሐራ በቦታው ላይ ተተክላለች፡፡ በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደግሞ በአጼ ዮሐንስ አራተኛው አቡነ ሐራ ድንግል መቃብር ላይ ለፃድቁ ለአቡነ ሐራ ድንግል መታሰቢያ ሲባል የራሳቸው የፃድቁ ቤተ ክርስቲያን ተመስርቷል፡፡ ንጉሱ አጼ ዮሐንስ 4ኛው በራሳቸው ላይ ነቀርሳ ወጦባቸው ሲታመሙ በአካባቢው የሚፈወስ ቦታ አለ ተብለው ሰለተነገሩ ቦታውን በማፈላለግ መጥተው በፀበሉ ተጠምቀው በእምነቱ ቢቀቡ ሰለዳኑ የፃድቁን ቤተክርስቲያን እንደ አሰሩ ይነገራል፡፡ ገዳሙን መርዳት ለምትፈልጉ በሙሉ 👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000610362463 👉 አባይ ባንክ 9221111060954312
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
https://shorturl.at/drCFW እባካችሁ ይህን መረጃ ሼር በማድረግ ተባበሯት
Hammasini ko'rsatish...
ፋና ቲቪ በድህነቴ ነገደብኝ |እባካችሁ በደሃ አትነግዱ |

ልጇን ባጃጅ ውስጥ አስቸኝታ የምትነዳዋ ታታሪ እናት ፋና ቲቪን አወገዘች

ወዳጆች ላልቸወሰነ ጊዜ የምገኝበት ፔጅ ይህ ስለሆነ ፎሎው በማድረግ ይከተሉኝ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=61558010381419&mibextid=ZbWKwL
Hammasini ko'rsatish...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

4