cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Adiss News™

#ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ማንኛውም መረጃ በሰዓቱ እናደርሶታለን ። የእርሶም አስተያየት እና ጥቆማ ለኛ ገንቢ ነውና በGroup https://t.me/Zenalers ያድርሱን። እናመሰግናለን 🙏

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
733
Obunachilar
+224 soatlar
+27 kunlar
+530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
በነፃ 😎 ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 93.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ትርፍ ስላገኘው ከነገ ሐምሌ 5 ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ * 1GB Data * 25 ደቂቃ የድምጽ እና * 50 አጭር መልዕክት የምስጋና ስጦታ አበርክተንልዎታል ብለዋል:: እንኳን ደስ ያላችሁ ቀስ እያላችሁ ተጠቀሙ ብለዋል!
Hammasini ko'rsatish...
👍 1🔥 1
በፔርሙዝ ዉስጥ ተሸሽጎ ሊዘዋወር የነበረ የዲሽቃ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ በቦረና ዞን ነገሌ ከተማ በፔርሙዝ ዉስጥ በመደበቅ ለማዘዋወር የተሞከረ የዲሽቃ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉን የነገሌ ቦረና  ከተማ አስተዳደር  ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አስቻለዉ ቡልቻ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ዋና ኢንስፔክተሩ ከነገሌ ከተማ ወደ አዶላ ዋዩ ሲጎዝ ነበረበ ኮድ 3 72685 ኦሮ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ዶልፊን ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ በፔርሙዝ እና በጫማ ዉስጥ ተደብቆ ሊዘዋወር የተሞከረ የዲሽቃ ጥይት መያዙን ገልጸዋል። ፖሊስ የጦር መሳሪያዉን ለማዘዋወር የሞከረዉን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም  የነገሌ ቦረና  ከተማ አስተዳደር  ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አስቻለዉ ቡልቻ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። የኮንትሮባንድ እና የህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች በየጊዜዉ ስልታቸዉን እየቀያየሩ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸዉም ተመላክቷል። @Zenalerase @Zenalerase
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#Update ታግተው ከነበሩት 167 ተማሪዎች ውስጥ 160ዎች መለቀቃቸውን የኦሮሚያ ክልል አረጋገጠ‼️ ባለፈው ሳምንት ከዳባርቅ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ወደመኖሪያ ቤቶች ሲመለሱ ከነበሩት ‹‹ 167 ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ መለቀቃቸውን ›› የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ ለአሻም አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹ ተማሪዎቹ ከታገቱበት የተለቀቁት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ መሆኑንም ›› ኃላፊው አክለዋል፡፡ ተማሪዎቹ የታገቱት በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት/በመንግስት ሽብርተኛ በሚል በተፈረጀው ኦነግ ሸኔ መሆኑን የተናገሩት ኃይሉ አዱኛ ‹‹ ቀሪዎቹን ተማሪዎቹን ለማስፈታት የፀጥታ ኃይሎች ጥረት ›› እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህን እገታ በተመለከተ ዩናይትስ ስቴትስ አሜሬካ በኢትዮጵያ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በኩል ባወጣችው መግለጫ ‹‹ ገንዘብ ለማግኘት በሚል የሚደረገውን እገታ ›› ኮንና ነበር፡፡ @Zenalerase @Zenalerase
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
በመዲናዋ በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን በተሽከርካሪ የገጩ አካላት 150-300 ሺ ብር ተቀጡ። በአዲስ አበባ በተገነቡ መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የሚጥሉ፣ ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሚሄዱ እንዲሁም ከተማዋ አረንጓዴ ለማድረግ በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን በግዴለሽነት በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት ተቀጡ። በዚህም 3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ፣ 50 ሺሕ እና 20 ሺሕ ብር የተቀጡ ሲሆን 5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ የተተከሉ ዘንባባ ዛፎችን ገጭተው በመጣላቸው እንደየጥፋት ደረጃቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር እንዲሁም 11 ሰዎች ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር ተቀጥተዋል:: @Zenalerase @Zenalerase
Hammasini ko'rsatish...
በአዲስ አበባ በግንባታ ላይ የነበረ ቤት በመኖሪያ ቤት ላይ ተደርምሶ በመኝታ ላይ የነበረ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ ዛሬ ሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም  ከንጋቱ 11:45 ሰዓት ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 አርሴማ ቤተክርስቲያን አካባቢ እየተገነባ ያለ ቤት ከስሩ ባለ መኖሪያ ቤት ላይ ተደርምሶ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። ህይወታቸዉ ያለፈዉ ግለሰብ በቤት ዉስጥ ተኝተዉ የነበሩ በጾታ ወንድ የሆኑ የ50 ዓመት ዕድሜ የተገመቱ መሆናቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በስፍራዉ ፈጥነዉ የደረሱት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረጉት ርብርብ ሶስት ሰዎችን ከአደጋዉ መታደግ ችለዋል። በአዲስ አበባ የግንባታ ስራ ላይ በተለይም በግለሰቦች የሚገነቡ ግንባታዎች የደህንነት መስፈርቶችን ጠብቆ ባለመስራታቸዉ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ በተደጋጋሚ አደጋዎች እያጋጠሙ ይገኛል። የግንባታ ስራዎች በሚከናወኑበት ጉዳዩ የሚመለከታቸዊ አካላት ግንባታዎቹ የአደጋ ደህንነት መስፈርት ተጠብቀዉ ስለመሰራታቸዉ የተጠናከረ ቁጥጥር በማድረግ የማስተካከያ እርምጃዎችን መዉሰድና የህግ ተጠያቂነትን ማስፈን ያስፈልጋል ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል። @Zenalerase @Zenalerase
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
በርካታ ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው። ✔የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም የሚወስዱ ሲሆን ✔ የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል። ✔ዘንድሮ ከ 700,000 በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚወስዱ መገለፁ ይታወሳል። ዛሬ ተማሪዎች ሲቀበሉ ከነበሩት ዩኒቨርስቲዎች መካከለ ወራቤ፣ ወሎ፣ ደምቢ ዶሎ እና መቅደላ አምባ ይገኙበታል። ለተማሪዎች መልካም እድል እንመኛለን ‼ @Zenalerase @Zenalerase
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
በዝምታ የቀጠለው ጦርነት! በሶማሊ እና አፋር ክልሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ውጊያ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል። ውጊያው በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ ሲሆን ሁለቱም ኃይሎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ውጊያ መግባታቸውን ከአካባቢው የሚወጡ የመረጃ ምንጮች ይገልፃሉ! @Zenalerase @Zenalerase
Hammasini ko'rsatish...
👏 3🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
#Update “ ለትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ሪፓርት አድርጌአለሁ ” - ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የዩቨርሲቲ ተወካይ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስማማው ዘገዬ፣ “ ጉዳዩን ሰምተናል። ከዚህ ድርጊት ያመለጡ ተማሪዎች ነግረውናኛል ” ብለዋል። “ እንደነገሩኝ እኔ ማድረግ ያለብኝን ለሚመለከተው የፌደራል መስራያ ቤት፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ሪፓርት አድርጌአለሁ ” ነው ያሉት። “ እነርሱም ‘ ለሚመለከተው የጸጥታ አካል ሪፓርት እናደርጋለን ’ ብለውኛል ” ያሉት ዶክተር አስማማው፣ “ እኔ ከእገታ ያመለጡትን ልጆች Informally communicate አድርጌአቸው ነበር ” ብለዋል። አክለው፣ “ መከላከያ አብዛኛዎቹን ልጆች አስመልሶ መከላከያ ካምፕ ውስጥ ያደሩ ልጆች እንዳሉ ሰምቻለሁ። የተወሰኑ ደግሞ በሌላ መኪና ተሳፍረው አዲስ አበባ የገቡ እንዳሉ ሰምቻለሁ ” ነው ያሉት። “ ግን ቀሪ ልጆች በጣም ዝናባማ ስለነበር መከላከያና ፓሊስ ሳይደርስባቸው አጋቾቹ ይዘዋቸው የሄዱ የተወሰኑ ልጆች እንዳሉ ሰምቻለሁ ” ሲሉ ተናግረዋል። ከዩኒቨርሲቲው የወጡት ተማሪዎች ቁጥራቸው ስንት ነው ? ለሚለው ጥያቄ በምላሻቸው፣ “ ቁጥራቸውን አናውቀውም የኛ ሲነር ተማሪዎች የመጨረሻ ግቢ የቆዬ 2ኛ፣ 3ኛና 4ኛ ዓመት ተማሪዎች ከደባርቅ ጎንደር ነው የተሳፈሩት በአውቶብስ ” ብለዋል። “ ቁጥራቸውን በእርግጠኝነት አላውቀውም ” ያሉት ዶክተር አስማማው ፥ “ ግን በሶስት አውቶብስ የኛ ተማሪዎች እንደተሳፈሩ መረጃው አለኝ። ከ3ቱ ሁለቱ አውቶብሶችን ነው ያስቆሟቸው ” ነው ያሉት። የታጋች ተማሪዎች ሁኔታ የሚመለከታቸው አካላትን በመጠየቅ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።  @Zenalerase @Zenalerase
Hammasini ko'rsatish...
👏 4👍 1
#ATTENTION🚨 “ የ2 አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” - ከእገታ ያመለጠ ተማሪ “ ‘ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም ፤ ታግተናል ’ አለችኝና ከዛ ስልኳ አይሰራም ” - የአንዷ ታጋች ተማሪ እህት “ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው ” - የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ሰኞ እለት ተሳፍረው ወደ ቤተሰብ እየተጓዙ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን የዓይን እማኝ፣ የታጋች ቤተሰብና ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። አንድ ከእገታው አመለጥኩ ያለ ተማሪ ፥ ሶስት (3) አውቶብሶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተጓዙባቸው የነበሩ ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ ገብረ ጉራቻ የሚባል ቦታ ሲደርሱ መታገታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል። ከ3 አውቶብሶች 2ቱን ታጣቂዎች እንዳስቆሟቸው፣ ተሳፋሪዎቹን ካስወረዷቸው በኋላ አግተው ወደ ጫካ እንዳስገቧቸው፣ እርሱ ገለባ ውስጥ ተደብቆ እንዳመለጠ ገልጾ፣ “ የሁለቱ አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” ብሏል። ከታጋቾቹ መካከል የሚያውቃቸው የIT ፣ የአኒሚል ሳይንስ ዲፓርትመንት ተማሪዎች እንዳሉ ገልጾ፣ ያገቷቸው “የሸኔ ታጣቂዎች” መሆናቸውን አስረድቷል። አንዷ የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል፣ “ ረቡዕ 3 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ደወለችልኝ (እየሮጡ ነበር፣ የተኩስ ድምጽም ነበር) ‘በቃ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም። ላታገኝኝ ትችያለሽ በታጣቂዎች ታግተናል’ አለችኝ። መለሽ ስደውል ስልኳ አይሰራም ” ብላለች። ቤተሰቡ ሁሉ በጣም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ታጋቾቹን በህይወት እንዲያተርፏቸው ተማጽናለች። በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፤ የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በበኩሉ፣ እገታው እውነት መሆኑን እንዳረጋገጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል። ኀብረቱ በሰጠው ቃል “ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው። ‘ ገንዘቡን ካላመጣችሁ እንገድላችኋለን ’ እያሏቸው ይገኛል ” ሲል የሰማውን አስረድቷል። የሞቱ ፣ የተጎዱ ስለመኖራቸው የደረሰው መረጃ እንደሌለ የገለጸው ማህበሩ ፣ የሚመለከታቸውን  አካላት ሁሉ ለማነጋገር ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል። በጉዳዩ ላይ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሰጠንን ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል። ግልባጭ👇 #TikvahEthiopiaFamilyAA @Zenalerase @Zenalerase
Hammasini ko'rsatish...
🤬 2😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
"የኑሮ ዉድነቱ ቀንሷል" ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ☺️ የዋጋ ግሽበቱ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ጠ/ሚኒስትሩ በተያዘው በጀት ዓመት የኑሮ ዉድነቱ እንደቀነሰ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። መንግስት የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ በርካታ እቅዶችን ይዞ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በሰብል ምርትም አምና እንደሀገር 395 ሚሊዮን ኩንታል ተመርቷል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ዘንድሮ 507 ሚሊዮን ኩንታል መመረቱን ገልጸዋል።ይህንን ዉጤት በርካታ የአለማቀፍ ተቋማት እያደነቁት መሆኑንም ገልጸዋል። የኑሮ ዉድነቱ በኢትዮጵያ ላይ ብቻ የተከሰተ አለመሆኑንም ለማስረዳት ሞክረዋል። የተከበሩ አቶ አቤኔዘር በቀለ የኑሮ ዉድነቱ ከፍቷል ፥ የመንግስት ሰራተኛዉ መኖር አቅቶታል ፤ መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባ ነዉ ፥ የኑሮ ዉድነቱን ማረጋጋት አልተቻለም። ስለሆነም እንደመንግስት በቀጣይ አመታት የህዝብን ጥያቄ ለመፍታት ምን ታቅዷል? ሲሉ ላቀረቡት ጥያቄ ነዉ ምላሽ የሰጡት። @Zenalerase @Zenalerase
Hammasini ko'rsatish...
😁 5👍 2🤯 1🙏 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.