cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አሪፍ ግጥሞች❤❤

የተመረጡና የታላላቅ ገጣሚያን ግጥሞችን ወደ እናንተ ዉድ ተከታዮቹ ያደርሳል !!

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
226
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Hammasini ko'rsatish...
ደስተኛ የሚያደርጉን 10 መርሆች | ፈታ መዝናኛ

#motivation #motivational #motivationalvideo

አንቺን ሳስብ፤ ሀሳብ ስስብ፤ ይገርመኛል ስናፍቅሽ፤ ቆይ ግን እስኪ ልጠይቅሽ። : : በደህና ነው ግን በመልካም? መልክ ግብርሽ ያለኝ ለኔ ኧረ ወግድ አልተካም? በጤና ነው ግን በበጎ? አንቺነትሽ ያልተገኘው ካንቺ ውጪ ተፈልጎ? እንጃ! : : እወድሻለሁ ! #ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita) ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ 🍏🍏 ➺@arifgitmoch 🍊🍊🍊 ➺@arifgtmoch 🍎🍎🍎🍎➺@arifgitmoch
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
12ቱ አስፈላጊ የሕይወት መርሆች !!

#motivation

(@bekalushumye) ➻➻➻➻➻➻➻➻➻ ዛሬም እንደ በፊቱ... ዛሬም እንደ ትላንቱ እናፍቅሽ ጀምሪያለሁ - በጠዋቱ፣ "ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ!" አይደል ተረቱ?! አንዳንድ ልቦችም ልክ እንደ ብርሌ፣ አንዴ ከወደቁ ያፈስሳሉ ሁሌ። ዳግም ልብ አይሆኑም አንዴ ከወደቁ፣ አንድ'ዜ ከነቁ ከተሰነጠቁ! አንዳንድ እምባዎችም... አሉ ለዝንታለም ደርቀዉ የማያዉቁ። አሉ ትዝታዎች ማብቂያ የሌላቸዉ መቼም ማያበቁ፣ አሉ ተስፈኞችም ... እስካለም ፍፃሜ ፍቅር ሚጠብቁ። እና በኔም በኩል... አንቺን ከልቤ ስር ፈልቅቆ የሚጥል መድኃኒት የለኝም፣ እንዳንቺም ልጠላሽ ብርታት አላገኝም፣ ላንቺ ያለኝ ፍቅር... እኔ ብሞት እንኳን ሚሞት አይመስለኝም። ➻➻➻➻➻➻➻➻➻ 🍏🍏 ➺@arifgitmoch 🍊🍊🍊 ➺@arifgtmoch 🍎🍎🍎🍎➺@arifgitmoch
Hammasini ko'rsatish...
👍 1🥰 1
➥ከመንገድ ነው የጎተተኝ ፈልጎኝ ነው ቤቱ ያስገባኝ ከተናቁት ተርታ ወስዶ የንግስናን ክብር የቀባኝ ህፃን ነበርኩ ትንሽ ግልገል ጉርድፍ መዳፍ ሚጨብጠኝ በሀይል ቃል የምሰበር ለሰው መስገድ ያጎበጠኝ ከትቢያ ነው ወርዶ ያነሳኝ አመድ ልብሴን ያራገፈው ዛሬ እኔ እንደ ባዳ አላውቀውም ብዬ ላልፈው ሲቀበለኝ ትዝ ይለኛል ቀራጭ ነበርኩ ሀጢያተኛ ቀርቦ ክንዱን አንተራሰኘኝ በእርሱ ሰላም እንድተኛ አልጠየቀኝ ስለ ሀጢያቴ ለምን ከዚህ እንደገባው እንደ ወዳጅ ስቦ ሲያቅፈኝ ትከሻው ላይ እኔ አነባው አስገረመኝ የርሱ ምርጫ ውሃ እምባዬን አፈሰሰው እንዲሰብከው እንዴት ጠራ ክብሩን መሬት የጣለ ሰው ንፁህ ሆኖ ሳይጠየፍ ቆሻሻዬን በጥላቻ በእርቃኗ ለቆመች ነፍስ የርሱ ምላሽ ማቀፍ ብቻ ለምን በደልክ አላለኝም የእርሱን ፍቅር ሳልታደል እኔን መውደድ አያስጥለው ያሰመጠኝ ጥልቅ በደል ና ይለኛል ዳግም ሊያቅፈኝ ከሰው ግብር ስለቃቅም በነገ ላይ መሾም እንጂ ስለትላንት አይጠይቅም! . . By @mikiyas_feyisa ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ 🍏🍏 ➺@arifgitmoch 🍊🍊🍊 ➺@arifgtmoch 🍎🍎🍎🍎➺@arifgitmoch
Hammasini ko'rsatish...
🥰 2
➥አሁን ለት አልነበር? ➬ ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ (በቃሉ ሹምዬ) "እሰይ ነጋ" ብለን---- ስንዘምር የነበር!? አሁን ለት አልነበር? ፀሀይ ወጣች ብለን ስንሞቅ የነበር?! (አሁን `ለት አልነበር?!!) ይገርማል...... በቅፅበት በድንገት በትንሽ ደቂቃ.... በተንጠለጠለ (ቅድም በተባለ) ትላንት ባልሞላ የጊዜ ሽራፊ (የሰዓት እራፊ) ሰማዩ ሲጠቁር ምስራቅ ቦዶ ሲሆን.... ጨለማ ሲውጠው የቀትርን ሰዓት.... ድቅድቅ ሲለውጠው መብራትም መጥፋትም (መንጋትም መምሸትም) አሁን ባሁን ሲሆን አየሁ ደጋግሜ.....፤ ለካ እንደ ሰው አጥሯል..... የጀምበርም ዕድሜ። @Bekalushumye ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ 🍏🍏 ➺@arifgitmoch 🍊🍊🍊 ➺@arifgtmoch 🍎🍎🍎🍎➺@arifgitmoch
Hammasini ko'rsatish...
1
Photo unavailableShow in Telegram
➥አንቺ ስትመጪ➬ ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ አንቺ ስትመጪ ቅጠሎች ረገፉ ለዉበትሽ ሰግደዉ መሬት ተነጠፉ አንቺ ስትመጪ ፀሀይ ቀናች መሰል በብርሃን ድምቀት ትበልጪያት ይመስል አንቺ ስትመጪ ጨረቃም አፈረች ለተፈጥሮ ዉበትሽ ቆማ መሰከረች አንቺ ስትመጪ ህመሜም ቀለለ ጤነኛ መሰልኩኝ ዉስጤም ተታለለ ግን መሄድሽ ላይቀር መሰናበትሽ ለምን ትመጫለሽ እዣው በቀረሽ ብዬ አሰብኩኝ እና ራሴን ሞገትኩት መሄድሽን እያወቅኩ መምጣትሽን ናፈኩት by @blaco20 ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ 🍏🍏 ➺@arifgitmoch 🍊🍊🍊 ➺@arifgtmoch 🍎🍎🍎🍎 ➺@arifgitmoch
Hammasini ko'rsatish...
( በቃሉ ሹምዬ) ➻➻➻➻➻➻➻ ይሄውልሽ.... አንችን ማፍቀር ማለት፣ ብርድ እንደመጠበቅ| በ'ኩለ ቀን ግለት። . ውሀን እንደ መዉቀጥ| ግድግዳ እንደ መግፋት፣ ምንም ለዉጥ የሌለዉ| ትርጉም አልባ ልፋት። ትርፉ ድካም ብቻ፣ የመዛል ጉራንጉር|የመልፋት ስርቻ። . መስታወት ፊት ቆመሽ.. ጉንጭሽን ለመሳም... `ምታደርጊዉ ጥረት! ትርፍ አልባ የሆነ የነጋዴ ወረት። በስተመጨረሻ... መክሰር| መክሰር| ብቻ! (ልክ እንደ ጉልቻ...) ዘላለም መጎለት፣ አንቺን ማፍቀር ማለት!! ➻➻➻➻➻➻➻➻➻ . @Bekalushumye ©አሪፍ ግጥሞች @arifgitmoch
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
➥ሀገር ስጠኝ...🚶 ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ ( ከ @begitimEnawga) ሀገር ስጠኝ እስቲ ወዳጄ ማለት ሚያስችለኝ ''እዛ ሄጄ ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ" ሀገር ስጠኝ የምኮራበት መልስ የሌላቸው እንቆቅልሾች የማይበዙበት ግራ ሲገባኝ ምን አውቄልህ ማልባልበት እስቲ ሀገር ስጠኝ አንድ ትልቅ ከሰፈር ጎሳ ከብሄር ሚልቅ ሀገርን ስጠኝ ሰላም ያለበት ሰው ለፍቶ ሰርቶ የሚያተርፍበት ካለሰቀቀን የሚኖርበት:: ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ © አሪፍ ግጥሞች @arifgitmoch 👇👇👇 inbox @arifgtmoch
Hammasini ko'rsatish...