cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Amhara Bureau of Agriculture

BOA

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 537
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+77 kunlar
+2430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

147A9068 copy.JPG10.64 MB
147A9141 copy.jpg11.31 MB
147A9152 copy.jpg11.09 MB
147A9175 copy.jpg12.46 MB
147A9184 copy.jpg14.51 MB
147A9190 copy.jpg13.16 MB
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በሩዝ ሠብል ልማት ላይ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ ሠኔ 19/2016 ዓ/ም የግብርና ቢሮ የ2016/17 ምርት ዘመን በሩዝ ሠብል ልማት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የዞንና የወረዳ ግብርና ኃላፊዎች፣የምርምር ተቋማትና የቢሮው ማናጅመንት በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩም ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ሲሆኑ በንግግራቸውም የዛሬው ፕሮግራም የሩዝ ሠብል ልማት በክልል ደረጃ የትላይ እንዳለ ለማወቅ፣መልማት የሚችል መሬት እያለ ለምን ማልማት እንዳልቻለ የምናይበትና በ2016/17 ምርት ዘመን 270 ሽህ ሄክታር መሬትበማልማት ሩዝ ሰብልን በማልማት ከ14 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማምረት አለብን ብለዋል፡፡ ሩዝ በአገር ደረጃ የአማራ ክልል ለመጀመርያ ጊዜ የመጣ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የዘንድሮው የሩዝ የንቅናቄ መድረክ መፈጠሩ አጠቃላይ የ2016/17 በሁሉም የሠብል ዓይነት 169 ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት አቅደን እየሰራን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ዕቅዳችን ማሳካት የምንችለው ሩዝን በክላስተር በታታሪነት፣በቁጭትና በጊዜ የለኝም መንፈስ ሁነን ከሠራን ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ድረስ አክለውም ጥቁር አፈርን በማንጣፈፍ በሩዝ ምርትና ሌሎች ተሞክሮ የሚሆን ክልል ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ኋላ መሄድ የለብንም በተለይ የኤክስቴንሽን ስራና ተቆርቋሪነትን በመጨመር ግብርናውን ትራንስፎርም ካላደረግን ተሠሚነታችን እና የመወሰን አቅማችን ዝቅ ይላል፡፡ ስለዚህ የባለድርሻና አጋር አካላት እነዚህን ተግባራት ቆጥሮ በመያዝ የ2016/17 ምረት ዘመን ዕቅዳችን ማሳካት እንችላለን ሲሉ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ውይይትም ሁለት የመወያያ ሠነድ የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው የፎገራ ሩዝ ምርምር ተቋም የሩዝ ተመራማሪ አቶ ዘላለም ታደሰ የሩዝን ታሪካዊ አመጣጥ፣ተስማሚ ስነ ምህዳር፣ የሩዝ አመራረት ዘዴ፣የሩዝ ዝርያዎችና በምርምር የተገኙ ዝርያዎችን በማቅረብ የሩዝን ምርትና ምርታማነት ለማስጨመር የሩዝ ሠብል ፓኬጅን በመጠቀም ምርትና ምርታማነታችን መጨመር እንደሚቻል በሠነዱ አቶ ዘላለም ታደሰ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ሁለተኛ የሩዝ ሠብል ልማት በ2015/16 ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የተሻሉ የተሻሉ ዞኖችን በዝርዝር አቅርበዋል ደቡብ ጎንደር፣ማዕከላዊ ጎንደርና ሰሜን ሸዋ የተሸሉ መሆናቸውን በመግለጽ የኢትዮርይስ ፕሮጀክት የሚያከናውናቸውን ተግባራትን በተመለከተ ዘር ማቅረብ፣የሩዝ ማሽን መፈልፈያና መሰል ስራዎችን እንደሚሰራ የኢትዮ ርይስ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አለባቸው አሊጋዝ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም በመድረኩም የተለያዩ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የዘር አቅርቦት፣የግብዓት አቅርቦት፤ የመነሻ ዘርና የሩዝ መፈልፈያ ማሽኖች መቅርብ አንዳለበት ተነሰቶል በዚህም መልስና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ የሰጡትየግብርና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው ሲሆኑ በክልላችን 1.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሩዝ ሠብል ልማት የማልማት ፖቴንሻል አለን እንዴት 270 ሽህ ሄክታር ማልማት ይከብደናል፤ የዘር ችግር የተነሠው በተለይ ትኩረት የምናደርገው ወደ ሩዝ ልማት የገቡ አዲስ አካባቢዎችን ብቻ ነው ትኩረት የምናደርግ ፤ሌሎች ዘርን በመቀያየር መዝራት ይቻላል፡፡ በክላስተር መዝራት ፤ በክልል ደረጃ የሩዝ መፈልፈያ ማሽን እቅዱን ላሳኩ ዞን አንሰጣለን ሲሉ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የግብርና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው ከዕቅድ በላይ ማሳካት ይቻላል ከተባበርንና ከተጋገዝን ከ30 በላይ የሠብል አይነቶች አሉ ከነዚህ ውስጥ የተመረጡ ኮሜዲቲዎችን ትኩረት በማድረግ በክላስተርእና የሠብል ፓኬጆችን በመከተል መስራት፣ሁላችንም በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ የማሳ ልየታ ማድረግ፤ ያለውን የሠላም ሁኔታ እናውቀዋለን ነገር ግን የግብርና ስራ ለነገ የማይባል መሆኑን በመረዳት እቅዳችን ማሳካት አለብን ሲሉ አቶ አጀበ ስንሻው ገልፀዋል፡፡  ዘጋቢ አሻግረው ፈረደ  ካሜራ ማን ጌታቸው ታፈረ
Hammasini ko'rsatish...
DSC_0188.JPG0.69 KB
photo_2024-06-21_03-55-29 (2).jpg0.90 KB
photo_2024-06-21_03-55-29.jpg0.56 KB
photo_2024-06-21_03-55-30 (2).jpg1.69 KB
photo_2024-06-21_03-55-30.jpg1.55 KB
በአማራ ክልል ከስድስት ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለቡና ልማት ተስማሚ ስነ ምህዳር ያለው መሆኑ ተገለፀ ቡና ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ዋነኛ የገቢ ምንጭ፣ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ፣ የውጭ ምንዛሪ ቀዳሚ ምንጭ እና የማህበራዊ ህይወት ትስስር መሰረት ነው። ኢትዮጵያ ለዓለም ካበረከተችው እንቁ ስጦታዎች መካከል ቡና ዋነኛውና የመጀመሪያው ስለመሆኑ ብዙ ተብሏል። ቡና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በስፋት ይመረታል። በአማራ ክልልም የቡና ምርት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፋ ይገኛል። በክልሉ የቡና ልማትን ለማስፋፋት ዓላማ ያደረገ የምክክር መድረክ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ/ም በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ በቡና ልማትና ግብይት የሚሰሩ የክልል ተቋማት፣ የዞንና የወረዳ የአትክልትና ፍራፍሬ ባለሙያዎች እና የቡና አምራች አርሶ አደሮች ህብረት ስራ ማህበራት ተገኝተዋል። በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) አስተባባሪ አቶ ተስፋሁን መንግስቴ እንዳሉት በአማራ ክልል ቡናን በስፋት ለማካሄድ ተስማሚ የአየር ንብረት፣ ታታሪና ቡናን የማምረት ልምድ ያለው አርሶ አደር፣ አዳዲስ ዝርያዎችን ለማባዛት ችግኝ ጣቢያዎች መኖራቸው እና የመስኖ መሰረተ ልማት እየተስፋፋ መምጣቱ ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ገልፀዋል። ሆኖም ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀም በየደረጃው ያለ የግብርና ተቋም፣ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። በአማራ ክልል ከስድስት ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለቡና ልማት ተስማሚ ስነ ምህዳር ያለው ሲሆን ይህም ከኦሮሚያ ክልል ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ እንዲገኝ የሚያስችለው ይሆናል። በክልሉ በ10 ዞኖች፣ በ70 ወረዳዎችና በ435 ቀበሌዎች ቡናን ማልማት እንደሚቻል ተገልጿል። በክልሉ የቡና ልማትን ለማስፋፋት በየአመቱ በአማካኝ ከሰባት እስከ ስምንት ሚሊዮን የቡና ችግኝ ይተከላል። በአማራ ክልል የቡና ልማት ምቹ ሁኔታዎች፣ ማነቆዎችና የመፍትሔ ሀሳቦች በሚል እንዲሁም በክልሉ የቡና ልማትና ግብይት ለማሻሻል ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በክልሉ የቡና ምርት ግብይት የሚያካሂዱ 32 ህብረት ስራ ማህበራትና አንድ ዩኒየን ይገኛል። አዘጋጅ:- አንተነህ ሰውአገኝ ካሜራ:- ድረስ ተስፋ ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የግብርና ቤተሰብ ይሁኑ👇 ድረገጽ http://www.amhboard.gov.et/ ቴሌግራም  https://t.me/AmharaBureauofAgriculter ፊስቡክ  https://www.facebook.com/profile.php?id=100064357704820 ዩቱዩብ  https://www.youtube.com/@amharaagriculturebureau6055
Hammasini ko'rsatish...
Amhara Bureau of Agriculture

BOA

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለውን የክላስተር እርሻ ገቢራዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን እናሳድግ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ የአማራ ክልልን ግብርና በሜካናይዜሽን፣ በምርጥ ዘርና ማዳበሪያ አቅርቦት፣ በምርምር የወጡ አዳዲስ ዝርያዎችን በማስተዋወቅ፣ ለባለሙያዎችና ለአርሶ አደሮች ስልጠናዎችን በመስጠት የግብርና ዘርፉን ለማሻገር ስር ነቀል እርምጃዎች ተወስደዋል። ሌላው የትኩረት ማዕከል ደግሞ የክላስተር እርሻን በማስፋፋት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረትም ተጠቃሽ ነው። የግብርና ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ከሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ ጋር በክላስተር እርሻ ምንነትና አስፈላጊነት ዙሪያ ቆይታ አድርገናል። ክላስተር በአንድ የተወሰነ አካባቢ ያሉ አርሶአደሮች አጎራባች መሬቶችን አንድ ላይ በማሰባሰብ፣ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ አብረው የሚሰሩበት፣ ሀብትና እውቀት የሚጋሩበት፣ ልምድ የሚለዋወጡበት አሰራር የሚፈጥር ነው። ለዘርፉ ሁለንተናዊ እድገት የግብርና ባለሙያዎች የሚሰጧቸው አገልግሎቶች፣ ድጋፎች እና ክትትሎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ፣ በምርምር ተቋማት የሚገኙ የምርምር ውጤቶችም ፈጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ የተሻለ እድል ሊፈጥር የሚችል እንደሆነም ይታመናል ሲሉ ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ አብራርተዋል። በአማራ ክልል በ2016/17 የመኸር ምርት ዘመን 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በክላስተር እርሻ የኮሞዲቲ ሰብሎችን ለማልማት የታቀደ ሲሆን ወደ 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ኩንታል ምርት በክላስተር ከሚለማው ማሳ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል ። ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ እንደገለፁት በምርት ዘመኑ በመደበኛ ከሚሸፈነው ከአምስት ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ውስጥ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በክላስተር እርሻ ይሸፈናል ብለዋል። በክልሉ በተመረጡ አስር ሰብሎች ላይ የክላስተር እርሻ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ስንዴ ፣ጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣አኩሪ አተር፣ ሰሊጥ፣ ሩዝ እና ሌሎችም በክላስተር ከሚመረቱ መካከል ዋነኞቹ መሆናቸውን ተናግረዋል። የክላስተር እርሻ ዘዴ ዋና ጥቅም መሬት በማሰባሰብ ወጪን በመቀነስ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻል ነው። በዚህ ዘዴ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ማሳደግ ብቻ ሳይሆን አመጋገብ ላይም ለውጥ እንዲያመጣ ማስቻል ነው። የክላስተር እርሻ በዋናነት አርሶ አደሮች ከተበጣጠሰ የማሳ አጠቃቀም በመውጣት በአንድ ላይ እንዲያመርቱ ለመደራጀት እና አስፈላጊው የግብርና ቴክኖሎጂን ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ያግዛል። የግብርና ባለሙያዎችም በተናጠል ከሚከናወን የግብርና ስራ ይልቅ በክላስተር የሚለማ እርሻ ላይ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የተሻለ አቅም ይፈጠርላቸዋል በማለት አስረድተዋል። በየደረጃው የሚገኙ የግብርና ባለሙያዎችም አርሶ አደሩ የክላስተር እርሻ ዘዴን እንዲያዘወትር ግንዛቤ በመፍጠር፣ የክህሎት ስልጠና በመስጠትና ለአርሶአደሩ የገበያ ትስስር በመፍጠር የማይተካ ሚና እየተወጡ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል። አርሶ አደሩ በክላስተር እርሻ ተጠቃሚ እንዲሆን ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ያሉ የግብርና ባለሙያዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ አርሶ አደሩን በሙያ የመደገፍ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የክላስተር አሰራር ዘዴ በአንድ የተወሰነ አካባቢ ያሉ አርሶአደሮች አብረው የሚሰሩበት፣ አጎራባች መሬቶችን አንድ ላይ በማሰባሰብ፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ሀብትና እውቀት የሚጋሩበት እንዲሁም ልምድ የሚለዋወጡበት ጭምር በመሆኑ በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ያሉት ዳይሬክተሩ የክላስተር እርሻ ዋና አላማም የክልሉን አርሶአደሮች ምርታማነትና ትርፋማነት ማሻሻል ስለመሆኑ አንስተዋል። በአማራ ክልል የክላስተር እርሻ ከሚታረሰው መሬት 48 በመቶ እንዲሁም ከታቀደው ምርት 60 በመቶ ይሸፍናል ያሉት ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ 39 ሽህ 834 የክላስተር አደረጃጀት ለመፍጠር ታቅዶ እስካሁን ባለው መረጃ 31 ሽህ 228 ወይም የእቅዱን 78% የክላስተር አደረጃጀት መፍጠሩን ገልፀዋል። አዘጋጅ:- አንተነህ ሰውአገኝ ካሜራ:- ጌታቸው ታፈረ ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የግብርና ቤተሰብ ይሁኑ👇 ድረገጽ http://www.amhboard.gov.et/ ቴሌግራም  https://t.me/AmharaBureauofAgriculter ፊስቡክ  https://www.facebook.com/profile.php?id=100064357704820 ዩቱዩብ  https://www.youtube.com/@amharaagriculturebureau6055
Hammasini ko'rsatish...
Amhara Bureau of Agriculture

BOA

Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የስንዴ ሰብል የአመራረት ፓኬጅ ክፍል ሁለት ሰብል ጥበቃና እንክብካቤ 👉 በሰብል ጥበቃና እንክብካቤ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ወቅታዊ የተባይ አሰሳ ማካሄድና የተቀናጀ የተባይ መከላከል ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ 👉ተገቢ የመርጫ መሳሪያና የመርጫ ጫፍ መጠቀም 👉 ዲፍሌክተር ኖዝል (የመርጫ ጫፍ) እና የመርጫ መሳሪያ ግፊት መቆጣጠሪያ ዝቅተኛ ግፊት ሀይል ላይ በማድረግ ለፀረ- አረም ኬሚካል መጠቀም፡፡ 👉 ኮን ኖዝል (የመርጫ ጫፍ) እና የመርጫ መሳሪያ ግፊት መቆጣጠሪያ ከፍተኛ ግፊት ሀይል ላይ በማድረግ ለፀረ ነፍሳት እና በሽታ ኬሚካል መጠቀም፡፡ አረም መከላከል በባህላዊ መከላከል 👉 የሰብል ፈረቃ መጠቀም፣ከአረም የጸዳ ማሳ ማዘጋጀት፣ንጹህ ዘር መጠቀም፣ 👉በእጅ ማረም፡ - • 1ኛ አረም ሰብሉ ከበቀለ ከ18-20 ቀን፣ • 2ኛ አረም ሰብሉ ከበቀለ ከ35-40 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ማካሄድ • 3ኛ አረም እንደአስፈላጊነቱ ታይቶ የሚታረም ይሆናል፡፡ በኬሚካል መከላከል 👉የስንዴ ሰብልን በተቻለ መጠን በእጅ ማረም ጥሩ ቢሆንም የጉልበት ዕጥረት በሚኖርበትና የአረሙ ክስተት ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ የተመረጡና የተመዘገቡ ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መሠረት መጠቀም፣ ነፍሳት ተባይ ቁጥጥር ክሽክሽ 👉 ይህ ተባይ ከሰብሉ ቡቃያ እስከ ዕድገት ደረጃ በሰብሉ ላይ በመከሰትና የተክሉን ፈሳሽ በመምጠጥ ጉዳት የሚያደርስ ተባይ ነው። በባህላዊ መከላከል 👉 የእርሻ ቦታ ንጽህናን መጠበቅ፣ሰብልን እያፈራረቁ መዝራት፤ለተባዩ እንደ አማራጭ ምግብነት የሚያገለግሉ ተክሎችን ቀድሞ ማስወገድ፣ 👉 በነጭ ሽንኩርት መከላከል:- 100 ግራም የተወቀጠ ነጭ ሽንኩርት፣ ግማሽ ሊትር ውሃ፣ 10ግራም ዱቄት ሳሙናና፣ 2 ማንኪያ የሚኒራል ዘይት ማዘጋጀት፡፡ በደቃቁ የተወቀጠውን ነጭ ሸንኩርት ከዘይቱ ጋር ለ24 ሰዓት መዘፍዘፍ፤ ሳሙናውን ከውሃ ጋር መበጥበጥና ከዘይቱና ሽንኩርቱ ድብልቅ ጋር መቀላቀል፡፡ በዚህ መሠረት የተዘጋጀውን ቅልቅል በጨርቅ አጥልሎ አንድ እጅ ከ20 እጅ ውሃ ጋር በጥብጦ በመርጫ መሳሪያ መርጨት፤ 👉በትንባሆ መከላከል፡- 1 ኪ/ግ የተወቀጠ የትንባሆ ቅጠልና ግንዱ ከ15 ሊትር ውሃ ጋር ለ1 ቀን መዘፍዘፍና አንድ እፍኝ ቁርጥራጭ ሳሙና መጨመር፣ ከዚያም ከአንድ ቀን በኋላ በጨርቅ ማጥለልና ወዲያውኑ መርጨት ወይም 250 ግራም የተወቀጠ ትምባሆ ቅጠል፣ 30 ግራም የዱቄት ሳሙና እና 4 ሊትር ውሃ ቀላቅሎ ለ30 ደቂቃ መቀቀል፡፡ ይህን ቅልቅል አንድ እጅ ከ4 እጅ ውሃ ጋር በጥብጦ በጨርቅ ማጥለልና በመርጫ መሳሪያ መርጨት፤ 👉በእንስሳት ሽንት መከላከል:- የእንስሳቱን ሽንት በተለያዩ እቃዎች በማጠራቀም ከ7-15 ቀን ድረስ እንዲብላላ ማድረግና የተብላላውን የከብት ሽንት ከውሃ ጋር እኩል በእኩል በሆነ መጠን በጥብጦ በመርጫ መሳሪያ መርጨት።በተለይ ለፀሐይ ቢጋለጥ የመብላላት ሂደቱን ያፋጥነዋል፡፡ በኬሚካል መከላከል 👉 ነፍሳት ተባዩ በየዓመቱ አይቀሬ በሆነባቸው አካባቢዎች 👉ማርሻል 25% ኢሲ፣ ሮገር ወይም ኢትዮላታዮን 40% ኢ.ሲ 1-2 ሊትር፣ዲያዚኖን 60% ኢሲ 0.5 ሊትር፣ ማላታዮን 50% ኢሲ 2 ሊትር፣ ካርቦሳልፋን 50% ኢሲ 1 ሊትር በሄ/ር ሂሳብ በ200 ሊትር ውሃ በርዞ መርጨት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የተመዘገቡ ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መጠቀም ይቻላል፡፡ የገብስ ዝንብ (Shoot fly)፣ ደገዛና ፌንጣ በጤፍ ስብል ላይ የተጠቀሰውን መከላከያ ዘዴ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ መሰክን መከላከል (Chuffer grub) በባህላዊ መከላከል (Cultural practice) 👉 ማሳን በበጋ ወራት ጠለቅ አድረጎ ማረስ፣ እርሻው በመንደር (ጓሮ) አካባቢ ከሆነ በእርሻ ጊዜ ዶሮዎችን በማሰማራት ከአፈሩ በላይ የሚወጡትን ቅንቡርሶች እየለቀሙ እንዲበሏቸው ማድረግ ያስችላል፡፡ በኬሚካል መከላከል 👉ክሩዘር 350% ኤፍ.ኤስ (Flowable solution) ከ100-200 ግራም በ1ሊትር ውሃ በጥብጦ 1ኩ/ል ዘር አሽቶ መዝራት፣ 👉 የመሰክ ተባይ በየዓመቱ በሚከሰትባቸው አካባቢዎች የተባዩ ክሰተት አይቀሬ መሆኑ ከተረጋገጠ ከዘር በፊት አፈሩን (እርሻዉን) በፀረ-ተባይ ኬሚካል መርጨትና በተገቢዉ ሁኔታ በእርሻ ከአፈሩ ጋር እንዲቀላቀል (እንዲገናኝ) ማድረግ፡፡ ለዚህም ዱርስባን 48% ኢሲ 2.5 ሊትር/ሄር፣ ማላታይን 50% 50% ኢሲ 2 ሊትር/ሄር፣ ካርባሪል 85% ደብልዉ ፒ 1.5 ኪ.ግ/ሄር በ1000 ሊትር ዉሃ በጥብጦ መርጭት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የተመዘገቡ ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መጠቀም ይቻላል፡፡ ምስጥን (Termite) መከላከል በባህላዊ መከላከል (Cultural practice) 👉የሰብል ቅሪቶችን ከማሳው ላይ ቶሎ ማንሳት፣ ሰብሉ እንደታጨደ ማሳውን ወዲያውኑ ማረስ፣ ኩይሳውን ቆፍሮ ንግስቷን አውጥቶ መግደል፣ የተብላላ የከብት ሽንት በኩይሳው ዉስጥ መጨመር፣ 👉 መርዛማ ፀረ-ተባይ እጽዋትን መጠቀም • የአሳ ባቄላ (Fish bean) ቴፍሮዚያ (Tephrosia vogelli) የተባለውን እጽዋት ቅጠሉን ጨቅጭቆ በውሃ በመበጥበጥ በኩይሳው ውስጥ መልቀቅ፤ • ቅጠሉን አድርቆና ፈጭቶ /ወቅጦ/ በዛፎችና በሌሎች ምስጥ አዘውትሮ በሚታይባቸው አካባቢዎችና በሰብል ክምር ስር መነስነስ፤ • ከሰብሉ ስር ቅጠሉን መጎዝጎዝ (Mulching)፣ በኬሚካል መከላከል 👉 ኩይሳው ባለበት ቦታ በመቆፈር ለአንድ ኩይሳ ዱርስባን 48% ኢ.ሲ ወይም ዲያዚኖን 60% ኢ.ሲ ከ20-30ሚ.ሊትር ከ15-20 ሊትር ውሃ እየበረዙ መጨመር፣ 👉 ሌሎች በአገራችን የተመዘገቡ ፀረ-ነፍሳት ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መሰረት መጠቀም ይቻላል፡፡ ነቀዝን መከላከል 👉 በየአካባቢው ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉትን ባህላዊ መከላከያ ዘዴዎች ጥራቱን የማያበላሹትን መርጦ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለምሳሌ አዞ ሀረግ ቅጠሉና ግንዱን ቆራርጦ በእህል ማካማቻው አፍና በተከማቸው እህል መሀል ማስቀመጥ፣ የመረዝ ቅጠል አድርቆ በመፍጨት ዱቄቱን እህሉ ጋር አደባልቆ ማስቀመጥ፡፡ 👉 ፀረ-ተባይ ኬሚካል መጠቀም ካስፈለገ ግን አክትሊክ 2% ዱቄት በተባዩ ለተወረረ 50 ግራም ላልተወረረ ደግሞ 25 ግራም ለ1 ኩ/ል ሂሳብ በማስላት በጥንቃቄ ከእህሉ ጋር በአካፋ አደባልቆ ማከማቸት ያስፈልጋል፡፡ የስንዴ በሽታ ቁጥጥር 👉ቢጫ ዋግን (yellow rust)፣ የግንድ ዋግን (Stem rust) እና የቡናማ ዋግን (brown rust) መከላከል በባህላዊ መከላከል 👉ከላይ የተጠቀሱትን በሽታዎች በአንጻራዊነት የሚቋቋሙ ዝርያዎችን (ቀቀባ፣ ደንፌ/ደንደአ፣ ሚሊኒየም፣ ታይ፣ አባይ፣ እመጓ፣ አዴት-1) መጠቀም፣ በኬሚካል መከላከል 👉ቲልት 250 ኢ.ሲ (ኘሮፒኮናዞል) 0.5 -1 ሊትር፣ ጀባ 25 ኢ.ሲ፣ ናቹራ 250 ኢ.ደብሊው፣ ናቲቮ ኤስ.ሲ 300፣ ፕሮግረስ 250 ኢ.ሲ፣ Rex® Duo፣ በተጨማሪም ሌሎች የተመዘገቡ ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መጠቀም ይቻላል፡፡ ] ሴኘቶሪያ በሽታ በባህላዊ መከላከል 👉 የሰብል ፈረቃን መጠቀም፣ 👉 ሰብል ከተሰበሰበ በኋላ የሰብሉን ቅሬት ሰብስቦ ማቃጠል፤ 👉ቅሬቱ ተሰብስቦ ከተቃጠለ በኋላ 2 ጊዜ ደጋግሞ በማረስ የቀረውን ቅሬት ሰብል ወደ አፈር ውስጥ አንዲቀበር ማድረግ፤ 👉 በማሳው ላይ እና በማሳው ዙሪያ የሚበቅሉ ወፍዘራሽ (Volunteer) የስንዴ ተክሎችና የበሽታው መቆያ አስተናጋጅ ተክሎችን ማሰወገድ። በኬሚካል መከላከል 👉ቲልት 250 ኢ.ሲ(ኘ
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.