cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝

📢 ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን እና ገዳማት ስርዓት ፣አሁናዊ ዜና እና ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ፡ ቅዱሳን መካናት እና ገዳማት ታሪክ 📢 የቅዱሳን ገድላት 📢 ቅዱሳን አበው ሊቃውንት 📢 ህዝበ ክርስቲያንን ማንቃት 📢 ቅድመ ኢትዮጵያ ትንሳዔ እና የኢሉሚናቲ ኅቡእ ማኅበር ኢትዮጵያ ላይ የተሸረቡትን ሴራዎችን ማጋለጥ ለውይይት @Tinsae_ze_ethiopiaofficialgrp

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
3 963
Obunachilar
-824 soatlar
-657 kunlar
-28530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
በመንግስት አፋኞት ከተወሰደ በኃላ እስከ አሁን ያለበት ሁኔታ በቤተሰብም ሆነ በህግ ባለሙያ አልተጎበኘም ሁላችንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ድምፅ ልንሆነው ያስፈልጋል
Hammasini ko'rsatish...
በቅድስት ቤትክርስቲያን ሥርዓተ አስተምህሮ ውስጥ በጊዜ ቅዳሴ ከወንጌል በኋላ ዲያቆኑ “ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን “ በማለት ያዛል። ይኸውም ፍሬ ቅዳሴ ህብስት እና ወይኑ ወደ ከበረ ስጋ ወደሙ ሚለወጥበት ጊዜ ስልሆን ይህም ለንዑሰ ክርስቲያን ማለትም በማህተመ መንፈስ ቅዱስ ላልታተሙ ላልተጠመቁ ክርስትና ላልተነሱ የተፈገደ የተገባ ስልይድለ ነው። በዚህ ላይ አስተያየት ስጡበት …
Hammasini ko'rsatish...
ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባታችን አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት። "ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባታችን አባ መቃርዮስም: "ስትሰድባቸው ፤ስታመሰግናቸው እና  ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት። @Tinsae_ze_ethiopia
Hammasini ko'rsatish...
እንኳን ለዳግም ትንሣኤ አደረሳችሁ በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ስትመሰክሩ፤ ስታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Hammasini ko'rsatish...
✏የድንግል ማርያም ልደት (መወለድ) "The Nativity of the blessed Virgin Mary” 👉የፈጣሪያችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደችበትን ግንቦት አንድን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልደታ_ለማርያም በማለት ከጥንት ጀምሮ በታላቅ መንፈሳዊ ሐሤት በቅዳሴ፣ በማሕሌት የምታከብርላት ሲኾን፤ በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት ያሉ ክርስቲያኖችም ይኽነን በዓል “The Nativity of the blessed Virgin Mary” (የተባረከችው የድንግል ማርያም ልደት (መወለድ) በማለት ያስባሉ። 👉ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ ቀን ሊቁ ዮሐንስ ዘደማስቆ እንዲህ ብሏል፦ "'The day of the Nativity of the Mother of God is a day of Universal joy, because through the Mother of God, the entire Human race was renewed. " 🙏ትርጉም (የአምላክ እናት የልደቷ ቀን ለዓለም ሁሉ የደስታ ቀን ነው፥ ምክኒያቱም በአምላክ እናት የሰው ሁሉ ዘር ባሕርይ ታድሷልና) ይህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሲገናዘብ ሊቀ መልአክ ቅ/ገብርኤል ካህኑ ዘካርያስን ልጅ እንደሚወልድ ባበሠረው ጊዜ “•••ደስታ ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።”ሉቃስ 1፥14 በማለት ነግሮታል። የጌታ መልእክተኛ የሆነ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ በመወለድ ብዙዎች ደስ ይለቸዋል ከተባለ የአምላክ እናት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም በመወለዷ ምን ያህል ሰውን ሊያስደስት እንደሚችል ማወቅ ይቻላል። 👉አባ ሕርያቆስም የእመቤታችን መጸነስና መወለድ ሲገልጽ:- “ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለሽም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!” ቅዳሴ ማርያም 🙏(ቅዱስ ኤፍሬም ) 👉ፍህም የተሸከመች የወርቅ ማዕጠንት ድንግል ሆይ ቡሩክ ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍህም የተሸከምሽ የወርቅ ማዕጠንት አንቺ ነሽ ። ፍህም የተባለውም ኃጢአትን የሚያስተሠርይና በደልን የሚደመስስ ነው፤ ይኸውም ካንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው 🙏የእመቤታችን በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን ‼ ©️Ethio beteseb media @Tinsae_ze_ethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
ልደታ ለማርያም በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡ በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡ ከዚህም በኋላ ይህችን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች። ስሟንም ‹ማርያም› ብላ ሰየመቻት። ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና። የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን፡፡ ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት @Tinsae_ze_ethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
"ከውሸት ፣ ከክፋት ፣ ከመወነጃጀል ነጽተን ትንሣኤውን በእውነትና በፍቅር እናክብር " ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በዓለ ትንሣኤን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ትንሣኤ ማለት ሕዝበ ክርስቲያኑ በጠቅላላ አምኖ የሕይወትን ትንሣኤ ስናከብር ነው በማለት የገለጹ ሲሆን አያይዘውም በዓለማችን ላይ የ ትንሣኤ ሕይወትን የሚለማመድ እና በሞት ጥላ ስር የሚኖሩ አሉ በመሆኑም በሞት ጥላ ለሚኖሩት ትንሣኤ የሚባል ነገር የለም ነገር ግን በሕይወት ትንሣኤ ስንኖር ዛሬ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ትንሣኤ ነው በማለት ምክራቸውን ለግሰውናል። ምድራችን ሁል ጊዜ በበሽታ ላይ ነው ያለችዉ በሕመም ላይ ነው ያለችው ስለዚህ ትንሣኤ ዛሬ ነው ካልን ከውሸት ፣ ከክፋት ፣ ከመወነጃጀል ነጽተን ትንሣኤውን በእውነትና በፍቅር እናክብር በዓሉም የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት ይሁንልን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ©️ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል @Tinsae_ze_ethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
"ከውሸት ፣ ከክፋት ፣ ከመወነጃጀል ነጽተን ትንሣኤውን በእውነትና በፍቅር እናክብር " ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በዓለ ትንሣኤን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ትንሣኤ ማለት ሕዝበ ክርስቲያኑ በጠቅላላ አምኖ የሕይወትን ትንሣኤ ስናከብር ነው በማለት የገለጹ ሲሆን አያይዘውም በዓለማችን ላይ የ ትንሣኤ ሕይወትን የሚለማመድ እና በሞት ጥላ ስር የሚኖሩ አሉ በመሆኑም በሞት ጥላ ለሚኖሩት ትንሣኤ የሚባል ነገር የለም ነገር ግን በሕይወት ትንሣኤ ስንኖር ዛሬ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ትንሣኤ ነው በማለት ምክራቸውን ለግሰውናል። ምድራችን ሁል ጊዜ በበሽታ ላይ ነው ያለችዉ በሕመም ላይ ነው ያለችው ስለዚህ ትንሣኤ ዛሬ ነው ካልን ከውሸት ፣ ከክፋት ፣ ከመወነጃጀል ነጽተን ትንሣኤውን በእውነትና በፍቅር እናክብር በዓሉም የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት ይሁንልን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ©️ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል @Tinsae_ze_ethiopia
Hammasini ko'rsatish...
በትንሣኤ እና በጠቅላላው በሐምሳው ቀናት ክርስቲያናዊ ሰላምታችን በረዥሙ እንዲሁም በአጭሩ (ሐሳብ መስጠት ይቻላል!!!) +++ Orthodox Greetings at Easter & the 50 days: ++++ ሀ/ በረዥሙ ካህን: ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን Priest:- Christ is risen from the dead ሕዝብ፦ በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን People:- With great strength and authority ካህን: ዓሠሮ ለሰይጣን Priest:- He chained Satan ሕዝብ፦ አግዓዞ ለአዳም People:- He freed Adam ካህን:- ሰላም Priest:- Peace ሕዝብ፦ እምይእዜሰ People:- Henceforth ካህን:- ኮነ Priest:- Became … ሕዝብ፦ ፍሥሐ ወሰላም People:- Joy and peace ++++++ ለ/ በአጭሩ፤ + Short greeting form (as in the Other Orthodox Churches) in our day to day encounters could be:- ** ሰላምታ አቅራቢ:- "ክርስቶስ ተንሥአ [እሙታን]" = (ክርስቶስ ተነሥቷል) ++ Greeter:- Christ is risen [from the dead.] ** ሰላምታ ተቀባይ:- "በአማን ተንሥአ እሙታን!!" = (በእውነት ተነሥቷል) ++ Person receiving the greeting:- "Truly He is risen [from the dead.]" + በሌሎች ክርስቲያኖች ዘንድ ያለው ሰላምታ!!!! ** “Christ is Risen!”, ** “Truly, He is Risen”. (This is used in almost all Christian nations, each translating it to its own language.) A/ Greek: ** “Χριστός ἀνέστη! Ἀληθῶς ανέστη! ** (Khristós Anésti! Alithós Anésti!)”, B/ Latin: ** “Christus resurrexit! Resurrexit vere!”, C/ Aramaic Syriac: “ܡܫܝܚܐ ܩܡ! ܫܪܝܪܐܝܬ ܩܡ!‎ (Mshiḥa qām! sharīrāīth qām! ; Mshiḥo Qom! Shariroith Qom!)”, D/ Hebrew: “המשיח קם! באמת קם!‎ (Hameshiach qam! Be’emet qam!)”, E/ Arabic: “المسيح قام! حقا قام!‎ (al-Masīḥ qām! Ḥaqqan qām!); المسيح قام! بالحقيقة قام!‎ (al-Masīḥ qām! Belḥāqiqāti qām!)”. F/ Coptic, the Paschal greeting is: ** Neo-Bohairic as “Pikhristos Aftonf! Khen oumethmi aftonf!” and in Old Bohairic as “pikhristos afdonf! khen oumetmei afdonf!”. ++++ ©️ TMC @Tinsae_ze_ethiopia
Hammasini ko'rsatish...
ኢሀሎ ዝየ ተንሥአ በከመ ይቤ፤ ነዓ ርእያ ኀበ ተቀብረ። ወንጌል ዘማቴዎስ 28፥6 #ትንሣኤ የዕለቱን ወንጌል እናንብብ! ሚያዝያ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በበዓለ ትንሣኤ የሚነበብ የማቴዎስ ወንጌል ም 28 ፥ 1 - 19 የማርቆስ ወንጌል ም 16 ፥ 1 - 20 የሉቃስ ወንጌል ም 24 ፥ 1 - 12 የዮሐንስ ወንጌል ም 20 ፥ 1 - 18 መልካም በዓለ ትንሣኤ ! ©️TMC
Hammasini ko'rsatish...
1