cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Ethio Construction

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም tiktok https://www.tiktok.com/@ethiocons ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
26 624
Obunachilar
+2724 soatlar
+2867 kunlar
+38430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ፅድት_ያለች_ካድ_app ካድ_ፋይል_በስልካችሁ_ለመክፈት ለተቸገራችሁ አንድ ፅድት ያለች #app ይዠላችሁ መጥቻለሁ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን በማውረድ ሳይት ላይ ለምትሰሩም እሱን መጠቀም ትችላላችሁ❗️ Check out "DWG FastView-CAD Viewer&Editor" https://play.google.com/store/apps/details?id=com.gstarmc.android
Hammasini ko'rsatish...
DWG FastView-CAD Viewer&Editor - Apps on Google Play

* Convert any drawing to PDF/JPG file offline, Fully compatible with AutoCAD!

👍 17 2
Photo unavailableShow in Telegram
በሲሚንቶ ኮንክሪት የሚገነቡ መንገዶች በመላው አለም ተመራጭነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ ከፍተኛ የመንገድ መሠረተ ልማት ለሚያካሂዱ ሀገሮች ደግሞ በሲሚንቶ ኮንክሪት የሚገነቡ መንገዶች አዋጪ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። በተለይ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ለአስፋልት ኮንክሪት የሚሆን ቢቱሜን (ሬንጅ) ከውጪ ከማስመጣት፣ ሲሚንቶን በስፋት አምርታ ተጠቃሚ መሆን ትችላለች። በመጪዎቹ ወራትም በኢትዮጵያ በቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ የሚያመርት ግዙፍ ሲሚንቶ ማምረቻ ፋብሪካ ወደ ሥራ ይገባል። አሁን በቅርቡ ህንድ እንኳን፣ ከሙምባይ እስከ ናግፑር ከተማ 700 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ስድስት ሌን ያለው የፈጣን መንገድ ግንባታን በሲሚንቶ ኮንክሪት ገንብታ ለምርቃት ዝግጁ ማድረጓ እየተሰማ ነው። በህንድ በ2018 የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረው የዚህ መንገድ ጅምሮ በመጪው ሰኔ ይመረቃል። ይህ በሲሚንቶ ኮንክሪት የተገነባው መንገድ ላይ 33 ትላልቅ ድልድዮች፣ 274 አነስተኛ ድልድዮች እና 6 የዋሻ ውስጥ መተላለፊያዎች እና ሌሎች 65 ተሻጋሪ መንገዶችን ያቀፈ ነው። በሲሚንቶ ኮንክሪት የሚገነቡ መንገዶች፣ በአስፋልት ኮንክሪት ከሚገነቡ መንገዶች ይልቅ ተመራጭ እየሆኑ የመጡት፣ በሲሚንቶ የሚገነቡ መንገዶች ረጅም አመት ስለሚቆዩ ነው። በዚያም ላይ በሲሚንቶ ኮንክሪት የሚገነባ መንገድ የጥገና ወጪም የለበትም።
Hammasini ko'rsatish...
👍 26😍 2 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ተስፋዬ ወፍጮ ቤት እየተባለ በሚጠራ አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ የአፈር ናዳ መከሰቱ ተነገረ፡፡ 🚧ህንጻ ለመገንባት የአፍር ቁፋሮ እያደረጉ የነበሩ በርካታ ሰራተኞች የአፍር ናዳው እንደተናደባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለጣበያችን ተናግረዋል፡፡ ✳️ከአፈር ናዳው እስካሁን ድረስ አንድ ሰው ብቻ ማውጣት እንደተቻለ የገለጹት ነዋሪዎቹ በቦታው ያለው ነገር የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡ 🔰የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ሰራተኞች ባሁኑ ሰአት በቦታው መገኝታቸቀው የተነገረ ሲሆን ሰራተኞቹን ለማዳን ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ⏺የአፈር ናዳው የደረሰው ህንጻው ከህንጻው አጠገብ ባሉ መኖርያ ቤቶች መሆኑ ነው የተነገረው፡፡ #FirstSafety https://t.me/ethioengineers1
Hammasini ko'rsatish...
😭 10👍 8 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአፍሪካ ረጅሙ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ነው።  ✨ Iconic Tower ይባላል፤ ቁመት 400 ሜትር ሲሆን፣ 77 ወለሎች አሉት።  ጠቅላላ የወለሎቹ ስፋት ደግሞ 250 ሺህ ስኩዌር ሜትር ነው። ይህ ሕንፃ በግብጽ ከዋና ከተማዋ ካይሮ ወጣ ብሎ ከተገነባው አዲሱ የአስተዳደር ዋና ከተማ ውስጥ ከተገነቡ 20 ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ በአመዛኙ የቢሮ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል። https://t.me/ethioengineers1
Hammasini ko'rsatish...
👍 19 2👏 1
ፕሪ እስትረስድ ኮንክሪት ኮንክሪቱ ላይ ሎድ ከመጫኑ በፊት Axial Compressive Stress አፕላይ ይደረግባቸል። ✨ለምሳሌ አንድን ቢም ከጎንና ከጎን Compressive ፎርስ ስናደርግበት የ ‹‹ በ ›› ፊደል አይነት ቅርፅ ይኖረዋል (ሲጋነን) ኢሄ የታጠፈው ቢም እላዩ ላይ ሎድ ሲጫንበት ቢሙ ወደ ነበረበት ቦታው ይመለሳል:: እንደዛ ነው pre-stressed ኮንክሪቶች act የሚያደርጉት PSC Vs RC RC beam ላይ ለዲዛይን assume ስናደርግ ኮንክሪቱ ምንም አይነት tensile stress አይሸከምም - tensile እስትረሱን የሚሸከመው ፌሮው ነው ብለን ነው ሌላው assumption ፌሮው ቴንሽኑን ይሸከማል ብንልም የፌሮውን አቅም fully utilize አናደርገውም ወይም ደሞ ሙሉ ለሙሉ አንጠቀምበትም የዚህም ምክንያቱ ኮንክሪቱ ቴንሽን ዞን ውስጥ የሚከሰተውን Crack width ለመገደብ ወይም limit ለማድረግ ነው። ከላይ በተገለፁት ሁለት ምክንያቶች ማለትም የኮንክሪቱንም የፌሮውንም አቅም ሙሉ ለሙሉ ባለመጠቀማችን የተነሳ ለትልልቅ ሎዶች RC ከ PSC አንፃር ኢኮኖሚካል አይደለም። የዚህም ምክንያቱ የ RCን አቅም ሙሉ ለሙሉ ስለማንጠቀምበት ነው በተጨማሪም RC ላይ ትልልቅ Grade ያላቸው ኮንክሪትና ፌሮ መጠቀማችን ብዙም ዋጋ የለውም ከ RC ድክመት ለመዳን Pre-Stressed ኮንክሪቶች ተፈጠሩ ከRC በተሻለ መልኩ የኮንክሪቱንና የብረቱን እስትሬንግዝ ይጠቀማሉና። ✨Methods of Prestressing 1) Pre tensioning👇 A, ቢሙን ካስት ማድረጊያ mold እናዘጋጃለን። B, ሞልድ ውስጥም PSC ኬብሎች ወይም tendon እናስቀምጣለን C, እነዚህ ኬብሎችም ላይ Tensile ፎርስ apply እናደርጋለን D,አፕላይ እንደተደረገ ኮንክሪቱን ሞልድ ውስጥ አስገብተን ኮንክሪቱን ካስት እናደርጋለን E, ኮንክሪቱ ሲደርቅ ፎርሶቹን remove እናደርጋለን ቢሙም ዝግጁ ሆነ ማለት ነው:: 2) Post tensioning እዚህ ላይ ኮንክሪቱ ከደረቀ በኋላ ነው Compressive force አፕላይ የምናደርገው Apply የሚደረጉት ፎርሶች ኮንክሪቱ ላይ compressive stress ሲፈጥሩ ብረቱ ላይ ደሞ tensile stress ይፈጥራሉ ማለት ነው:: 😱Join our TikTok channel 👇 https://www.tiktok.com/@ethiocons
Hammasini ko'rsatish...
👍 25👏 1
https://t.me/tapswap_mirror_1_bot?start=r_371415119 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
Hammasini ko'rsatish...
5👍 3
✅ ፒያሳ ❤ 📱የምህንድስና ውጤቶች https://t.me/ethioengineers1
Hammasini ko'rsatish...
👍 26😭 4 2🤔 2
የምህንድስና ውጤቶች ናቸው https://t.me/ethioengineers1
Hammasini ko'rsatish...
👍 40👏 2 1
አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ የድልድዩ_ግንባታ_ስራ፡- 📌ከድልድዩ ግንባታ ጎን ለጎን  ተያያዥ የኮንክሪት ስትራክቸር ስራዎችና፣ የተሽከርካሪ መወጣጫ /ramp/ ፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የድልድይ ላይ መብራቶች ስራም ያካተተ ነው ፡፡ ይህ ድልድይ ኤክስትራ ዶዝድ የሚባል ስያሜ የተሰጠው ተንጠልጣይ ድልድዮች (ሰስፔንሽን) ከሚባሉት ድልድዮች የተለየና ይልቁን የመኪና ተሸካሚው ዴክ ከፊትና ከሁዋላ ከግራና ከቀኝ በ18 ኬብሎች በአጠቃላይ በ72 ኬብሎች (በገመዶች የተወጠረ) ሆኖ ጠቅላላ ክብደቱ በገመዶቹ አማካይነት ወደ ቋሚው ምሰሶ የሚተላለፍና ከምሰሶውም ወደ መሰረቱ የሚዘልቅ ነው፡፡ ☄ይህ አይነቱ ድልድይ የረጃጅም ኬብል ስቴይድ (በገመድ የተወጠረ) ድልድዮችና  የረጃጅም ቦክስ ገርደር አይነት ድልድዮች ውሁድ ሆኖ ስፋታቸው ከ 250 ሜትር እከ 500 ሜትር በሚደርሱ ወንዞች ላይ አመቺና ወጪ ቆጣቢ ሆነው እንዲሰሩ በመጀመሪያ በፈረንሳይ ሀገር የተፈለሰፈ በቀጣይ ግን በብዛት ጃፓን ሀገር ስራ ላይ የዋለ የድልድይ አይነት ነው፡፡ ☄የተጠናቀቀው የድልድዩ የምህንድስና ሰነዶች እንደሚያመለክቱት የቋሚው ምሰሶ ከመሰረት በላይ (piers) 7 ሜትር  ከፍታ እና ታወሩ 27 ሜትር ከፍታ ሲኖረው ከውሀና ከመሬት በታች እስከ 24 ሜትር ጥልቀት ባላቸው በርካታ ፓይሎች የተዋቀረ ነው፡፡ ✅ለድልድይ ግንባታው ጥቅም ላይ የዋሉ #ዋና_ዋና_ግብዓቶች ✳️የተለያዩ የጥንካሬ ደረጃ (Grade C-30, C-40, C-50, and C-55) ያላቸው አርማታ 54,138.68 ሜ.ኩ ✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የአርማታ ብረት 9,241.45 ቶን ✳️የተለያዩ ስፋት እና የጥራት ደረጃ ያላቸው የማንጠልጠያ  እና መወጠሪያ 474.37 ቶን   👍የድልድይ ግንባታ ሥራውን ከዚህ ቀደም በሀገራችን ከተሠሩት #የተለየ_የሚያደርገው 🔰የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየስ ሳይከናወን በሀገራችን ብዙም ያልተለመደ እና አዲስ ቴክኖሎጅ (ማለትም ተንሸራታች የሆነ ብረት የድልድይ አቃፊ) ግብዓት በመጠቀም መሠራቱ 🔰ድልድዩ በከተማ ውስጥ እንደመሠራቱ የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥ ባሻገር የቱሪሰት መስህብ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ የአካባቢውን ማህበራዊ፣ ተፈጥሮአዊ እሴቶችን በማገናዘብ ቅንጡ ተደርጎ መሠራቱ 🔰በድልድዩ መወጠሪያ ገመዶች ላይ የተለየ መስተጋብር መስጠት የሚችሉ መብራት የተገጠመ መሆኑ ይገኙበታል፡፡ ❇️#የኘሮጀክቱ_ሁለንተናዊ_ፋይዳ ⏺በአሁኑ ወቅት ከአቅሙ በላይ አገልግሎት  በመስጠት ላይ የሚገኘውን  ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ ላይ ይደርስ የነበረውን  የትራፊክ መጨናነቅ እና ጫና ያስቀራል፡፡ ⏺ለሀገሪቱ የገቢ ወጪ የንግድ እንቅስቃሴም የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረክታል። ⏺ድልድዩን ለሚያቋርጡ እግረኞች የትራፊክ አደጋ ሳያሰጋቸው በተዘጋጀላቸው 5 ሜትር ስፋት ባለው መሄጃ ላይ በመጠቀም  ከስጋት ነጻ  ያደርጋቸዋል፡፡ ⏺ብስክሌት ለሚጠቀሙ የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆኑ ቱሪስቶች  ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ⏺በተጨማሪም በባህርዳር ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡ ☄ብዙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ላላት ባህርዳር እና አካባቢዋ  አዲሱ ድልድይ እራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ በመሆን አዎንታዊ ሚናውን ይወጣል፡፡ 📌አንዱን አካባቢ ከሌላው ጋር በማስተሳሰር የምርትና የሸቀጥ ልውውጥን ያለእንግልት በቀላሉ እንዲያከናወኑም ይረዳል ፡፡ https://t.me/ethioengineers1
Hammasini ko'rsatish...
Ethio Construction

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም tiktok

https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ

👍 28 4
ባህር ዳርበባህር ዳር ከተማ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ መጠናቀቁ ተሰምቷል። ✔ድልድዩ 380 ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡ የጎን ስፋቱም 43 ሜትር ሲሆን በግራና በቀኝ በአንድ ጊዜ 6 ተሽርካሪዎች ማስተናገድ ይችላል። ✔5ሜትር የእግረኛ መሄጃ የተሰራለት ሲሆን በሁለቱም አቅጣጫ ለብስክሌት ተጠቃሚዎች የሚሆን መስመርን ያካተተም ነው። ✔ድልድዩ 65,683 ኪሜ የሚሸፍነው፤ ከግብፅ ተነስቶ፤ በሱዳን በማቋረጥ ኬንያ እና ታንዛንያን አልፎ እስከ ደቡብ አፍሪካ የሚያገናኘው የኔትዎርክ መንገድ አካልም ነው። ✔ቀድሞ የነበረው ድልድይ ከ60 ዓመታት በላይ ለማህረሰቡ የትራንስፖርት ማመላለሻ መንገድ በመሆን ሲያገለግል ቆይቶ ለአዲሱ ቦታውን የሚያስረክብም ይሆናል። ✔ግንባታው በአንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰላሣ ሰባት ሚሊዮን  ብር  የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ወጪው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው። https://t.me/ethioengineers1
Hammasini ko'rsatish...
👍 39 9👏 7😭 1