cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዴርቶጋዳ

ማንም ሰው ላይመጣ እኛን ለመለወጥ አናፈገፍግም አናቅማማም ለለውጥ ዴርቶጋዳ ዴርቶጋዳ ያቀረቀርንበት አንገት ያስደፋህ ቀን ነግቷል ብለህ ተነስ ፍዳና ሰቀቀን 👌👌👌👌👌👌👌👌👌 @yegnafiker @yegnafiker @yegnafiker Join yargu

Ko'proq ko'rsatish
Efiopiya10 994Amxar9 348Toif belgilanmagan
Reklama postlari
263
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

"we are Shaped and fashioned by what we love" (ብዙ ነገራችን የሚቀረፅው በምንወደው ነገር ነው።) የምንወደው ነገር ማንነታችንን በቅጡ ያሳያል። ግፋ፣በቀል፣ምቀኝነት፣ሐሜት በጉያችን ይዘናል። የሚቀርፀን እሱ ነው። ውሳኔያችን፣ፍርዳችን፣ እይታችን የሚቆነጠረው ከዚህ ይመስላል። እንዲህ እየተመለከትን የተሻለ ነገር መጠበቃችን ያስገርማል። የችግሩ ሁሉ ምንጭ የተሰራንበት አፈር ነው። አፈሩ ከግፍ፣ከበቀል፣ከምቀኝነት ከአስመሳይነት ጋር አብሮ ተለውሷል። የተሻለ ነገር እንዲመጣ የምንወደውን ነገር መቀየር አለብን። ለእልህ፣ለአላዋቂነት፣ለክፋት የገበረው ስብዕናችን ለእውነት፣ለፍትህና ለመልካምነት ለመልካምነት መገበር ካልጀመረ ስቃያችን ዘለዓለማዊ ነው። @ZHabbesha @ZHabbesha @ZHabbesha @ZHabbesha
Hammasini ko'rsatish...
#ሀበሻ ደግ ነዉ። ገና ያኔ ድሮ ጣሊያን ሲነሳ ሞኝ አድርጎት ነበር ይሄን ጀግና አንበሳ እቅዱን ሊያሳካ ባህር አልፎ መቶ ሴራውን ዘረጋ ያንን እንቶ ፈንቶ ሀበሻም ደግ ነዉ እንግዳን አክባሪ ተቀብሎት ነበር ያንን ሞት አብሳሪ መች ገብቶት ሀሳቡ የዚህ የመሰሪ ደግነት መሆኑን እያየ ሀበሻነት ሴራውን ከማሴር አንዴም አላሰበም ከቶ ሊራራለት እንዲህ ሲል ጀመረ የሴራውን ጥንስስ ስምምነት አለ የሀበሻን ሀሞት አስቦ ሊበጥስ ሀበሻም ደግ ነው እሺ አለ ተስማማ ፈረመዉ ያንን ዉል አንድም ሳያቅማማ ታድያ ከውሉ ቀን ወዲህ ትፎክር ጀመረ ጣሊያን ለነገረ እያለች ከኔ በላይ ሚበጅ የለም ለሀበሻ ምድር አፄው ከነ ሚስቱ ነገሩን ሲሰሙት የኢጣሊን ሴራ ትርጉሙን ሲረዱት በጣም በመናደድ እጅግ በመቆጣት ለአንበሳዉ ነገሩት ወር-ኢሉ እንዲከት ያኩሩዉ አንበሳ ንጉሡን አክባሪ ጊዜም አልፈጀበት ሲቀበል የአፄውን ጥሪ ሀገሩን ለማዳን ከባእድ ወራሪ ......... ታድያ ጦሯን ሰብቃ ኢጣሊ አደዋ ከተመች ህልሟን ለማሳካት ብዙ እያስበች ታድያ የዉድቀቷን ጉዞ ሀ ብላ ጀመረች ኩሩዉም ሀበሻ በእግሩ ተጉዞ አድዋ ሲደርስ ቁጣዉ ተቀስቅሶ ሆኖ አራስ ነብር ጣሊያንን ገርፎ ከተታት ከባህር። #ⓃⓄⓂⓄⓇⒺ ⒶⒻⓇⒾⒸⒶ #ⓃⓄⓂⓄⓇⒺ ⒺⓉⒽⒾⓄⓅⒾⒶ ......ገጣሚ የ @nomoreethiopia1 መስራች #share it
Hammasini ko'rsatish...
ትናንትና_ማታ ላሟሟሽ ሲገባኝ እንደ አሞሌ አጥቤሽ፣ በመጨረስ ፈንታ ለነገ ቆጥቤሽ፣ አስተርፌሽ ለሰው፣ የፀፀት ሱናሚ አለሜን አመሰው፣ ምነው ቢቻል ኖሮ፣ ፈገግታሽን ቋጥሮ፣ ሙዳይ ውስጥ መደበቅ፣ ጃንደረባ ቀጥሮ ጭንሽን ማስጠበቅ፣ ክፍት ልቤን ይዤ ዝግ ደጅሽን ፀናሁ፣ በሰበብ ወድጄሽ ያለሰበብ ቀናሁ። ፍቅር በተባለ ግራ አጋቢ ነገር፣ ከጨመተው አገር፣ ከሰከነው ቀዬ፣ መናፍቅ ይመስል በአዋጅ ተነጥዬ፣ እንደ ካፖርቴ ቁልፍ ልቤን የትም ጥዬ፣ የትም ስከትለሽ፣ የትም ሆኖ እድልሽ፣ ሁሉ ያንቺ ወዳጅ ሁሉ ባላንጣዬ፣ መፈቅር ሆኖ እጣሽ መቅናት ሆኖ እጣዬ፣ ላንቺ ብስል ፍሬ ለኔ ገለባ ግርድ፣ ላንቺ እቅፍ አበባ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ፣ ማነው የበየነው ይሄን ግፈኛ ፍርድ፣🤔🥲 #በእውቀቱ_ስዩም @ZHabbesha @ZHabbesha
Hammasini ko'rsatish...
ዛሬ አንድ አባት ምናሉኝ👇 ስማ ልጄ የአንዲትን ሀገር መሪ ልትጠላ ትችላለህ መብትህ ነው የምትተዳደርበትንም ስርዓት ልትጠላ ወይም ልትቃወም ትችላለህ ይሄም መብትህ ነው ምክኒያቱም ስርዓትም ሆነ የሀገር መሪ የሚያልፉ የሚቀያየሩና የሚሻሻሉ ናቸውና 👇 ግን ልጄ ሀገርህን ልትጠላትም ሆነ ፊትህን ልታዞርባት አይገባም ሀገርህ ስምህ ክብርህ አንተነትህ ናት ለመኖር ኦክስጂን በሚያስፈልግህ ልክ ሀገርህም ታስፈልግሃለችና ውደዳት ጠብቃት አስፈላጊም ከሆነ ሙትላት እኔምለው በዚህ ሀሳብ ላይ ተቃውሞ ያለው ሰው ይኖር ይሆን እንዴ🤔🤔🤔 @ZHabbesha @ZHabbesha
Hammasini ko'rsatish...
"ብዙ አስመሳይ ሰዎች ባሉበት አለም ውስጥ አስመሳዮች ላይ ከመፍረድህ በፊት አንተ ከነሱ አንዱ አለመሆንህን አረጋግጥ። ምክኒያቱም የብዙዎቻችን ችግር እኛ የምንፀየፈውን ነገር መሆናችን፣ የምናወግዘውን ነገር መስራታችን የምንከለክለውን ነገር መስራታችን ነውና" #2Pack @ZHabbesha @ZHabbesha
Hammasini ko'rsatish...
"ህይወት ምርጫ አላት ግን ሁሌም አደለም። አንዳንዴ ምርጫ አይኖርም።ወይ ደሞ አንድ ምርጫ ብቻ ይኖራል። አለመምረጥ መቻል ደሞ ክፉ ነው። ምን ሆነህ ነው ስትባል እንዲህ ሆኜ ነው ማለት አለመቻል ህመሙ የከፋ ነው" @ZHabbesha @ZHabbesha
Hammasini ko'rsatish...
"በውድቀት የሚታወቁ ሰዎች ተስፋ ቆርጠው በቆሙበት ሰዓት ምን ያህል ለውጤት ቅርብ እንደነበሩ ያላስተዋሉ ሰዎች ናቸው" #Thomas_Edison..👆👆 በህፃንነትህ ቀና ለማለት ሞክረህ በስንተኛው የተሳካልህ ይመስልሃሌ? ለመዳህ(ዳዴ) ለማለት ያደረከው ሙከራ ምን ያህል አደከመህ? በእግርህ ለመቆም ምን ያህል ጊዜ ፈጀብህ? ስንት ጊዜ እጆችህ ያዙትን ከለቀቁ በኋላ ተመልሰው ይዘውታል? ስንቴ ወደ ምድር አጎንብሰህ እራስህን አድነሃል? ለመራመድ ባደረከው ሙከራ ስንቴ ወድቀሃል? እነዚህን ልምምዶች ቆጥረህ "ሁለተኛ ለመራመድ አልሞክርም?" አለማለትህን አስተውለህ ታውቃለህ? ዛሬ እንደ ልብህ የምትንቀሳቀሰው ከስህተትህ ባሻገር አልፈህ ስለመጣህ ነው። ትወድቃለህ ውዳቂ ግን አደለህም።ትሳሳታለህ ስህተተተኛ ግን አደለህም። ትሸነፋለህ ተሸናፊ ግን አደለህም። ያሳለፍከው የስህተት ልምምድ ሁሉ በአንተነትህ ላይ በሌላ በኩል ልትማራቸው የማትችላቸውን አስገራሚ ትምህርቶችን ትተውልህ ያልፋሉ። ይህ እይታ ልምምዶችህና ያሳለፍካቸውን ነገሮች አለወጣቸውም። ለነዚህ ሁኔታዎች ያለህን ምላሽ ግን በሚገባ ይለውጠዋል። ይህ አስገራሚ እይታ እያንዳንዱ ክስተት ወደትምህርትና ለእድገትህ ወደመጠቀም ይለውጥሃል። @ZHabbesha @ZHabbesha
Hammasini ko'rsatish...
አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ፣ ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ፣ እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ፣ ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ፣ ቀን እየሄደ ቀን መጣ፣ ልቤ ከሃሳብ ሳይወጣ፣ መታ ታብስው እንባዬን፣ ሀገሬን ጥሯት አርማዬን፣ መቼም ከዚህ ምድር ላይ ሄዶ ነው ሁሉም ቀሪ፣ ሀገር ናት ቋሚ ሰንደቅ ለዘለዓለም ኗሪ፣ ትናንትም እንደ ጀንበር እያዩት ከአይን ይርቃል፣ ኢትዮጵያ እንድትመጪ ስንት ቀን ይበቃል፣ እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ፣ ግን ባባሁ ናፈኩሽና እንባ ቀደመኝ፣ እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ፣ በወንዜ በሀገሬ እያለሁ ሀገር ናፍቄ፣ ወተሽ በምስራቅ አንቺ የአለም ጀንበር፣ አንድ አድርጊንና ጠላትሽ ይፈር፣ የቦረኩበት በልጅነቴ፣ የያኔው መልክሽ በቅ ሲል ፊቴ፣ እየመለሰኝ ወደ ትናንቱ፣ ናፍቆኝ በብርቱ ትዝ አለኝ የጥንቱ፣ አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ፣ ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ፣ እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ፣ ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ፣ ሀገር ልክብሩ ሲጣራ ከፋ ያደረግነው ባንዲራ፣ ዘመም ሳይል ቀን ጎድሎ፣ ባክሽ ኢትዮጵያ ነይ ቶሎ፣ ብዙ ነሽ አንቺ ሀገሬ የሞላሽ ታምራት፣ ምኩራብሽ የተፈራ የነፃነት ቤት፣ የአርበኞች የድል ችቦ ለድውልድ እንዳበራ፣ መኖር ለሀገር ሲሆን ሞትም አያስፈራ፣ እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ፣ ግን ባባሁ ናፍኩሽ እንባ ቀደመኝ፣ እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ በወንዜ በሀገሬ እያለሁ ሀገር ናፍቄ፣ አመት አውዳመት ድገመን ሲሉ፣ ልጆች በቀዬ ችቦ እያበሩ፣ መስቀል ፋሲካ ኢድ እንቁጣጣሽ፣ አውዳመት ይሁን አንቺ ካልመጣሽ፣ ዘመን አድሰሽ በፍቅር ቀለም ብቅ በይ ኢትዮጵያ ሁኚና መስከረም፣ ሆነሽ መስከረም ብቅ በይና፣ እንበል አስዮ ናና ቤሌማ፣ ብቅ በይና ሆነሽ ሙሽራ፣ ይብቃና ስደቱ ስቃይ መከራ ዘር ያበቀለው ታጭዷል መከራ፣ የኢትዮጵያዊነት አሁን ነው ተራ፣ . . 👆ቴዲ አፍሮ @ZHabbesha @ZHabbesha
Hammasini ko'rsatish...
"ከምናደንቃቸው ስኬታማ ሰዎች ጀርባ ያለውን የስህተት ብዛት ብናይ....ለካ እኔ ደጋግሜ መሳሳት ስለምፈራ ነው ብዙ ነገር ጀምሬ የማቆመው እንጂማ እንደዚህ መሳሳት መቼ ያቅተኛል እንል ነበር። ህልምህ ጋር ለመድረስ ስህተትንና ሽንፈትን እንደ መንሰላል ልትጠቀምባቸው ይገባል። እየተሳሳትክ ካልሆነ ከነበርክበት ቦታ እየተንቀሳቀስክ አደለም ማለት ነው" #SHER_JOINE Please🙏🙏🙏 @ZHabbesha @ZHabbesha
Hammasini ko'rsatish...
ዴርቶጋዳ፪ ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪❤️🇹🙏🇪🇹 ማንም ሰው ላይመጣ እኛን ለመለወጥ፣ አናፈገፍግም አናቅማማም ለለውጥ፣ ዴርቶጋዳ.... ዴርቶጋዳ... ያቀረቀርንበት አንገት ያስደፍን ቀን፣ ነግቷል ብለህ ተነስ ፍዳና ሰቀቀን፣ በባዕዳን ምድር የሰው ጎጆ ሳጋ፣ በእናት ሀገር ጓዳ ሰባተኛ ዜጋ፣ እስከመቼ ድረስ እንቅብ በእንቅብ ላይ፣ አሜን እንላለን ሲደፋብን ከላይ፣ @ZHabbesha https://t.me/ZHabbesha
Hammasini ko'rsatish...
ኢትዮ_ቅምሻ💚💛❤️

ማንም ሰው ላይመጣ እኛን ለመለወጥ፣ አናፈገፍግም አናቅማማም ለለውጥ፣ ያቀረቀርንበት አንገት ያስደፍን ቀን፣ ነግቷል ብለህ ተነስ ፍዳና ሰቀቀን፣ በባዕዳን ምድር የሰው ጎጆ ሳጋ፣ በእናት ሀገር ጓዳ ሰባተኛ ዜጋ፣ እስከመቼ ድረስ እንቅብ በእንቅብ ላይ፣ አሜን እንላለን ሲደፋብን ከላይ፣ @ZTewahddo @Amorthodox 4 any comments