cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Books @reading

ሰላም የ Books@reading ተከታዮች ........በዚህ channel:- 1):- ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀማቸው መፃህፍት በስፋት ይዳሰሳሉ.... ማለትም (የህግ መፃህፍት, የቀኖና መፃህፍት, የስርዓት መፃህፍት, የተግሳፅ መፃህፍት, የምክር መፃህፍት ) 2):- ስርዓታቸውን የጠበቁ ልብ-ወለዶች እና ትረካዎች በስፋት ይዳሰሳሉ። 3):-አስተማሪ ፁሁፎችና አስገራሚ ታሪኮች ይቀርቡበታል።....

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
167
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

በጅማ ማእከል የትብብር እና ህዝብ ግንኙነት ገፅ (ወረዳ ማእከላትና ግቢ ጉባኤያትን ጨምሮ), [26.09.20 12:55] ቅድስት እሌኒ ከመስከረም 17 ቀን አስጀምራ እስከ መጋቢት 10 ቀን ሌሊትና ቀን ለሰባት ወራት ያህል የጉድፍን ኮረብታ ቆፍረው ቆሻሻውንም ካስወገዱ በኋላ ሦስት መስቀሎች ተገኙ ፡፡ የጌታም መስቀል ሙት በማስነሣቱ ተለይቶ ታውቋል፡፡ መስቀሉ የተገኘው መጋቢት 10 ቀን 326 ዓ. ም. ነበር፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መስቀሉ ከተቀበረበት ተራራ ተቈፍሮ የወጣበት መጋቢት 10 ቀንም በቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሥርዓት ይከበራል፡፡ በተጨማሪም መስከረም 17 ቀን ንግሥት ዕሌኒ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረችበትን የመታሰቢያ በዓል ታቦት አውጥተው ዑደት በማድረግ በቤተ ክርስቲያን ያከብሩታል፡፡ በ327 ዓ.ም የጌታን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ መስቀል በቅድስት እሌኒ ከተቀበረበት ከወጣና በክብር ለረጅም ዓመታት በኢየሩሳሌም ከተቀመጠ በኋላ ዐረቦች ኢየሩሳሌምን በመውረራቸው ምክንያት በአረማውያን እጅ እየተማረከ ከአንዱ ሀገር ወደ አንዱ ሀገር ሲንከራተት ቆይቷል፡፡ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖችም በመስቀሉ መማረክ ያዝኑና ይበሳጩ ስለነበር ጦራቸውን አሰልፈው መስቀሉ ወደሔደበት ሀገር በመዝመት ጦርነት ያካሔዱ ነበር፡፡ ቅዱስ መስቀሉን እንደተከፋፈሉት፡ በ778 ዓ.ም አራቱ አኅጉራት ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ በአራቱ የመስቀሉ ክንፍ የተያያዙት ምልክቶችን በማንሳት የተከፋፈሉ ሲሆን በወቅቱ በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ዐረቦች በእስክንድርያ ለሚኖሩ አባቶች የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግሮቹ እና እጆቹ ተቸንክረው የተሰቀለበትን ሙሉ መስቀል ላኩላቸው፡፡ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስም በክብርና በጥንቃቄ እንዲቀመጥ አድርጓል፡፡ ይህም የመስቀሉ ክፋይ (ግማደ መስቀል) በእስክንድያ እስከ 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ የግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ መግባት፡ የጌታችን ቅዱስ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ የቻለበት 1394 ዓ.ም. ዐፄ ዳዊት ሁለተኛ በነገሡ በ29ኛ ዓመታቸው የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን 47ኛው ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል በወቅቱ የነበረው የግብጽ ፈርዖን አሠራቸው ክርስቲያን የሆኑ ዜጎቹን “የእኔን ሃይማኖት ካልተከተላችሁ መኖር በግብጽ መኖር አትችሉም” ብሎ ከአቅማቸው በላይ ግብር ጣለባቸው፡፡ መከራው የጸናባቸው የግብጽ ክርስቲያኖች “ከደረሰብን መከራና ሊቀጳጳሳችንን ታስፈታልን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተማጽነናል” ሲሉ ለአፄ ዳዊት መልእክት ላኩባቸው፡፡ አጼ ዳዊትም ወታደራቸውን ወደ ግብፅ አዘመቱ፡፡ በወታደሩም ኃይል የዓባይን ወንዝ ለመገደብ ተነሱ፡፡ ይህን የሰሙ የወቅቱ የግብጽ መሪ መርዋን እልጋዴን መኳንቱን ሰብስበው “ምን ይሻለናል ብለው ምክር ያዙ” የዐባይን ወንዝ ከምናጣ “ሊቀጳጳሱን አቡነ ሚካኤልን እንፈታለን በክርስቲያኖችም ላይ መከራ አናደርስም” ብለው ቃል በመግባት ብፁዕ አቡነ ሚካኤልን ሁለት እልፍ ወቂት ወርቅ እጅ መንሻ አስይዘው ለዐፄ ዳዊት አማላጅ ላኩ፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም “ብርና ወርቅ አልፈልግም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ነው የምፈልገው” አሏቸው፡፡ የሀገራችን ሕዝብ በውኃ ጥም ከሚያልቅ ብንስማማ ይሻለናል ብለው መስከረም 10 ቀን 1395 ዓ.ም. ከመስቀሉ ጋር ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የእመቤታችን ሥዕል ጨምረው ሰጧቸው፡፡ መስከረም 10 ቀን በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ግማደ መስቀሉ ከእስክንድርያ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበትን የመታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ይከበራል፡፡ ዐፄ ዳዊት መስከረም 10 ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ከግብፃውያን የተቀበሉበት ቀን በመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን ተቀጸል ጽጌ በመባል የሚታወቅ ሲሆን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ የመስቀሉ በመስቀለኛ ቦታ መቀመጥ፡ ከዐፄ ዳዊት በኋላ በቦታቸው የተተኩት ዐፄ ዘርዐያዕቆብ “አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል” የሚል ራዕይ በማየታቸው መስቀሉን በ1443 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት በተለያዩ ቦታዎች ለማሳረፍ ጥረት አድርገዋል፡፡ በደብረ ብርሃን፤ በሸዋ ደርሄ ማርያም፤ በጨጨሆ፤ በአንኮበር፤ በመናገሻ አምባ፤ በእንጦጦ፤ ወዘተ አሳርፈውት አልተሳካላቸውም፡፡ በመጨረሻም መስከረም 21 ቀን 1446 ዓ.ም. በራዕይ በተነገራቸው ቅዱስ ስፍራ በግሸን ደብረ ከርቤ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አኑረውታል፡፡ መስከረም 21 ቀን ግማደ መስቀሉ በሚገኝበት በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም በታላቅ በዓለ ንግሥ ያከብሩታል፡፡ በአጼ ዳዊት እግር የተተኩት ልጃቸው ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ “አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል /መስቀሌን በመስቀልያ ስፍራ አስቀምጥ/” የሚል ራእይ በተደጋጋሚ እግዚአብሔር አሳያቸው፡፡ በኢትዮጵያ ካሉት መልከዐ ምድር ውስጥ የመስቀል ቅርጽ ያለው የቀራንዮ አምሳል የሆነ ቦታ ከፈለጉትና ካጠኑ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በቀራንዮ የተሰቀለበት ቀኝ እጁ ያረፈበት ግማደ መስቀል አሁን ግሼ አምባ በሚባለው ሥፍራ ላይ መስከረም 21 ቀን 1446 ዓ.ም ደብረ ከርቤ አሁን እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን የታነጸበት ቦታ ላይ እንዲያርፍ አደረጉ፡፡ አንዳንድ ወገኖች “መስቀሉን ለምን በዚያ አሳረፉት? ለምን ዛሬ ለሰዎች እንዲታይ ሆኖ አልተቀመጠም?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ የመስቀሉ ጠላቶች የሆኑት አይሁድ መስቀሉ ድውይን ስለፈወሰ ሙታንን ስላስነሳ ሰዎች እንዳይድኑበት በተንኮል ነበር የቀበሩት፡፡ የክርስቶስ የክብር ዙፋኑ በሆነው መስቀል ላይም ቆሻሻ እንዲደፋበት አድርገዋል፡፡ የመስቀሉ ወዳጆች የሆኑት ኢትዮጵያውያን አባቶች ግን መስቀሉን በመስቀለኛ ቦታ በክብር ነው ያሳረፉት፡፡ በመስቀለኛው ስፍራም ያሳረፉት በየአድባራቱ አዙረው ምድሪቱን ካስባረኩ በኋላ ከፈጣሪ በተሰጣቸው ትዕዛዝ ለመስቀሉ በተፈቀደው ቦታ በግሸን በደብረ ከርቤ ነው፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ ብዙ ጊዜ ሲማረክ የነበረው መስቀልን በክብር ተጠብቆ እንዲቆይ በመስቀለኛው ቦታ አሳረፉት፡፡ የቅዱስ መስቀል ክብር በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን ክርስቲያኖች መስቀልን የምናከብረው በመስቀሉ ላይ በተፈጸመው ቤዛነት ብዙ ነገሮችን ስላገኘን ነው። በክርስቶስ ቤዛነት ሞት ስለተሻረ አጥተነው የነበረውን ሕይወት አግኝተናል። ስለዚህ ነው “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና፤” የተባለው። 1ኛ ቆሮ.15፥22። የሰው ልጅ ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ክርስቶስ ሥጋውን የሕይወት እንጀራ አድርጎ በመስቀል ላይ ሰጠን። ይህንንም “እውነት እውነት እላችኋለሁ የሰውን ልጅ /የወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስን/ ሥጋውን ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤” ሲል አረጋግጦልናል። ዮሐ.6፥53-54።
Hammasini ko'rsatish...
በጅማ ማእከል የትብብር እና ህዝብ ግንኙነት ገፅ (ወረዳ ማእከላትና ግቢ ጉባኤያትን ጨምሮ), [26.09.20 12:55] ቅዱስ መስቀል፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩ የተሰጠ ምልክት! “አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል” እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ታላቅ ክብር ይሰጠዋል፡፡ የመስቀል በዓልም ከዘጠኙ የጌታችን ንዑሳን በዓላት አንዱ ሲሆን በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን ይከበራል፡፡ በዓሉም ከዋዜማው መስከረም 16 ጀምሮ ደመራ በመደመር ይከበራል፡፡ የመስቀል ደመራ በዓል ቅድስት ቤተክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ በአደባባይ ከምታከብራቸው በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህንን ታላቅ በዓል በማስመልከት በዚህች የአስተምህሮ ጦማር የመስቀልን ምንነት፣ የመስቀልን አገልግሎት፣ የመስቀልን ታሪክ፣ የመስቀልን ክብርና አንዳንድ ተያያዥ ጉዳዮች እንዳስሳለን፡፡ የቅዱስ መስቀል ምንነት: መከራ ክርስቶስ፣ መከራ ክርስትና፣ ዕፀ መስቀል በቤተክርስቲያን አስተምህሮ “መስቀል” የሚለው ቃል ሦስት መሠረታዊ ቁም ነገሮችን ያመለክታል፡፡ የመጀመሪያው ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከሞተ ነፍስ ለማዳን ሲል የተቀበለው መከራና የከፈለው መሥዋዕትነት (የክርስቶስ መከራ መስቀል) ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚያጋጥም ልዩ ልዩ ዓይነት መከራም (መከራ መስቀለ ክርስቲያን) ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው፡፡ በሦስቱም ቁም ነገሮች ነገረ መስቀል (የመስቀሉ ነገር) ከክርስትና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ መስቀል የሰላማችንና የድኅነታችን የመቀደሳችን ዓርማ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጆች ለማዳን፥ የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት መስዋዕትነት የከፈለበት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት መንበር፥ ሲሆን አምላካችንን የምንመለከትበት መስታወት ነው። የቅዱስ መስቀል አገልግሎት: የድኅነት ኃይል፣ የእምነት ዓርማ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዋጋ የከፈለበት ቤዛ ዓለም የተከናወነበት እንደመሆኑ መስቀል በቤተ ክርስቲያናችን በሁሉ አገልግሎት ሰፊ ድርሻ ያለውና እንዲሁም በንዋያተ ቅድሳት ላይ የሚውል አቢይ ምልክት ነው:: በነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት “ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው (መዝ 59:4) እንደተባለ ለክርስቲያኖች መስቀል የጠላት ሰይጣን ተንኮል የከሸፈበት ስለሆነ ከአንገታችን፣ ከእጃችን ሳይለይ የክርስቶስን ቤዛነት የምንመሰክርበት የድኅነታችንም ኃይል የተገለጠበት ነው:: አጋንንት የመስቀሉን ምልክት ባዩ ጊዜ ይንቀጠቀጣሉ፤ ካደሩበት ሰው ላይም በፍጥነት ይወጣሉ፡፡ ምእመናን በመስቀሉ ስንዳሰስ ከልዩ ልዩ ደዌ እንፈወሳለን፡፡ እዚህ ላይ ማስተዋል የሚያስፈልግ ነገር አለ፡፡ ቤተክርስቲያንና ክርስቲያኖች ቅዱስ መስቀል ስንገለገልበት የሕሊናችን ትኩረት በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ ቤዛ የሆነን ኢየሱስ ክርስቶስን በማሰብ የመስቀሉ ምልክትነት (ዓርማነት) ላይ ነው እንላለን እንጂ የመስቀሉን ቁሳዊ አካል (Physical structure) ላይ አይደለም የሚሆነው፡፡ መስቀል ከእንጨትም ተሠራ ከእንቁ ትኩረታችን መሆን ያለበት ምልክትነቱ፣ ዓርማነቱ ላይ ነው፡፡ ይህም በቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ህይወት የተገለጠ ህያው ምስክር ነው፡፡ መስቀልም የድኅነታችን ኃይል፣ የእምነታችን ዓርማ፣ የቤተክርስቲያናችን ሰንደቅ ዓላማ ነው፡፡ ስለዚህም የመስቀል ምልክት የሃይማኖታችን መገለጫ እንጂ ለሥጋዊ ሰውነታችን ማጌጫ አይደለም፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ክርስቲያናዊ ባህል የመድኀኒታችን የክርስቶስ መስቀል በብዙ ተግባራት ላይ በምልክትነት ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ለምሳሌ በየሸማ ልብሶች፤ እንደዚሁም በጆሮ፣ በአንገት፣ በእጅና ሌሎችም ጌጣጌጦች ላይ የመስቀል ምልክት አለ፡፡ ክርስቲያን ልጃገረዶች (በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል) በግንባራቸው፣ በጉንጫቸው፣ በአንገታቸው፣ በደረታቸውና በእጃቸው ላይ በመስቀል ቅርፅ እየተነቀሱ እምነታቸውን ይመሰክሩበታል፡፡ ክርስቲያኖች ከዚህ ዓለም በሞት ስንለይም በመቃብር ሣጥናችን ወይም በሐውልቶቻችን ላይ የመስቀል ምልክት ይቀመጣል፡፡ በቤት ውስጥም ስንተኛና ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፊታችንንና መላ ሰውነታችንን በትእምርተ መስቀል እናማትባለን፤ አባቶችና እናቶችም ውሃ ሲቀዱ፣ ሊጥ ሲያቦኩ፣ እንጀራ ሲጋግሩ፣ ምግብ ሲቈርሱ፣ ወዘተ በመስቀል አማትበው ነው፡፡ በአጠቃላይ መስቀል ብዙ ነገር ነው፤ መስቀል በክርስትና ሕይወት ውስጥ በሚደረጉ ተግባራት ኹሉ ያለው ድርሻ ጕልህ ነው፡፡ የቅዱስ መስቀል ታሪክ: ከደብረ ቀራንዮ እስከ ደብረ ከርቤ የቅዱስ መስቀሉ መቀበር፡ በብሉይ ኪዳን መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ መሣርያ ነበር፡፡ በደላችንን ሊያጠፋ የመጣው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ33 ዓ.ም ለሰው ልጆች ሲል በመስቀል ተሰቀለ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ሕሙማንን በመፈወሱ ምክንያት በርካታ አሕዛብ ክርስቲያን እንዲሆኑ አስችሏል፡፡ በተአምራዊነቱና በክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የተሰጠው በመሆኑ ይህን የተመለከቱ አይሁድ ቅዱስ መስቀሉን በአንድ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ እንዲቀበር አደረጉ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በየቀኑ ቆሻሻ ስለሚጥሉበት ቦታው ወደ ተራራነት ተቀየረ፡፡ ምንም እንኳን መስቀሉን ለማውጣት ባይችሉም በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች ቦታውን ያውቁት ነበር፡፡ በሰባ ዓመተ ምሕረት በጥጦስ ወረራ ኢየሩሳሌም ስለጠፋች በዚያ የነበሩ ክርስቲያኖች ተሰደዱ፡፡ የተቀበረበትን ቦታ የሚያውቅ ባለመገኘቱ መስቀሉ ከ300 ዓመታት በላይ ተዳፍኖ /ተቀብሮ/ ኖረ፡፡ የቅዱስ መስቀሉ ከተቀበረበት መውጣት፡ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን (በ327 ዓ.ም) የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ቅድት እሌኒ መስቀሉን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች፡፡ ቅድት ዕሌኒ በዕጣን ጢስ አመልካችነት መስቀሉን ከተቀበረበት ቦታ ለማውጣት ቍፋሮ ያስጀመረችበትን የመታሰቢያ በዓል የደመራ በዓል ተብሎ ይከበራል፡፡ በሀገራችን መስቀል የሚከበርበትን ጊዜ በማስመልከት ሁለት አይነት ትውፊት አለ፡፡ ጎንደር ትግራይና ኤርትራ እንዲሁም በገጠራማው የጎጃምና የወሎ ክፍሎች ደመራ የሚለኮሰው መስከረም 17 ሲሆን በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ መስከረም 16 ቀን ለ17 ዋዜማ ምሽት ላይ ይከበራል፡፡ የዚህን ልዩነት መነሻ መተንተን የዚህ ጽሁፍ ዓላማ ባይሆንም ቅዱስ መስቀልን ለማግኘት ደመራ ተሰርቶ የተለኮሰው መስከረም 16 ለ 17 አጥቢያ እንደሆነ አባቶቻችን ያስተምራሉ፡፡ ከዚህም በመነሳት አንዳንዱ አካባቢ በዋዜማው ሌላ አካባቢ ደግሞ በዕለቱ ያከብራሉ፡፡ በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን ደመራ ደምረው በመለኮስ በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት በዐደባባይ ያከብሩታል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
በጅማ ማእከል የትብብር እና ህዝብ ግንኙነት ገፅ (ወረዳ ማእከላትና ግቢ ጉባኤያትን ጨምሮ), [26.09.20 12:55] ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም፤” ብሎ እንደተናገረ ፍጹም የሆነውን ሰላም የሰጠን በመስቀል ላይ ነው። ይህንንም፡- ሞትን በኃይሉ ድል አድርጎ በተነሣ ጊዜ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፤” በማለት ለደቀ መዛሙርቱ አረጋግጦላቸዋል። ዮሐ.14፥27፤ 20፥19፣26። በመርገመ ሥጋ በመርገመ ነፍስ አርጅቶ የነበረው ሰውነታችን አዲስ የሆነው በመስቀል ላይ በተፈጸመው ቤዛነት ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን /ሰውነታችን/ ከእርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን።” ያለው ሮሜ.6፥6። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርቶስ በመስቀሉ ላይ በከፈለው ቤዛነት ከራሱ ጋር አስታረቀን (ታረቀን)፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ “በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷል፤” ብሏል። ቆላ.1፥20። መስቀልን ስናከብር አንዳንዶች ባለማወቅ ወይም እውነተኛውን የወንጌል አስተምህሮ ባለመረዳት “አባትህ የተገደለበትን መሣርያ እንዴት ታከብራለህ?” የሚል አንድምታ ያለው ሀሳብ ያነሳሉ፡፡ ይህም ስለክርስቶስ ስቀለት ያላቸውን ትክክለኛ ያልሆነ ግንዛቤ ያነፀባርቃል፡፡ ምክንያቱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለው በራሱ ፈቃድ (በፍቅር) እንጂ እነዚህ ወገኖች እንደሚያስቡት አይሁድ አስገድደውት አይደለም፡፡ መስቀሉም ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስና በእርሱ ምክንያት የመጣብን ሞት የተሸነፉበት ነው፡፡ መስቀሉ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሰላምን ያደለበት ነው፡፡ መስቀሉ የክርስቶስ የክብር ዙፋኑ ለእኛም የድል ዓርማችን ነው የምንለው ለዚህ ነው፡፡ ለአርአያነትና ለቤዛነት የመጣው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ጠላትን ድል አድርጎ ቤዛ የሆነን እናንተም በዚህ መስቀል ጠላታችሁ ዲያብሎስን ድል አድርጉበት ብሎ አርአያ ሊሆነንም ጭምር ነው፡፡ እውነተኛዋ ክርስትናም የምታሸንፈው በመግደል ሳይሆን በመሞት፣ በማጥቃት ሳይሆን መከራ በመቀበል፣ በማሳደድ ሳይሆን በመሰደድ፣ በማስገደድ ሳይሆን በማስወደድ፣ በክርክር ሳይሆን በፍቅር ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በመዝሙሩ “ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሀቸው ወዳጆችህም እንዲድኑ” (መዝ. 59፡4) እንዳለ ቅዱስ መስቀል እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ምዕመናን የተሰጠ ልዩ የድኅነት ምልክት ነው፡፡ የኪስኪስ ኤጲስ ቆጶስ ሊቁ አባታችን ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው “እግዚአብሔር ያገለገለባት መቅደስ ወዮ እንደምን ያለች ናት?!” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤራቅሊስ 48፡17) ብሎ እንዳመሰገናት እንደ እመቤታችን ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ያገለገለበት ወገኖቹንም ወደ ጽድቅ የመለሰበት የክብር ዙፋኑ (ማቴ. 20፡21) ቅዱስ መስቀል ወዮ እንደምን የከበረ ነው?! ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “ወንሰግድ ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ/ የጌታችን እግሮቹ በሚቆሙበት (በቆሙበት) ቦታ እንሰግዳለን” (መዝ. 131፡7) እንዳለ ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን፡፡ የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆኗ ምድራዊት ጽዮን በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተመሰገነችና የጸጋ ስጦታ ምንጭ መሆኗ እንደተነገረ፣ ተራሮችም የእግዚአብሔር ክብር ሲገለጥባቸው “ቅዱስ” (2ኛ ጴጥ 1፡18) እንደተባሉ ከዚያ በበለጠ ክብር የድኅነታችን ምስጢር የተፈጸመበትን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት መገለጫና ዘላለማዊ መቅደስ ቅዱስ መስቀልን እናከብረዋለን፡፡ ምልክታችን፣ አርማችን አድርገነው እንኖራለን፡፡ ምልክትና አርማ ሲባል ግን እንደምድራውያን ሰንደቆች ኃይል የሌለው ተዓምራትን የማያደርግ ሳይሆን እንደ ሙሴ በትር ሰይጣንን የሚረታ (ዘፀ. 14፡16)፣ ቅዱሳን መላእክት ከመስቀሉ ደመ ማኅተም የተነሳ ጠላት ዲያብሎስን እንዳሸነፉት ምዕመናንን የሚያጸና፣ የሚረዳ (ራዕይ 12፡11) ሰማያዊ አርማ ነው፡፡ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለቅዱስ መስቀል ልዩ ክብር ትሰጣለች፡፡ በጸሎቷ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ የባህርይ፣ አምላክን በድንግልና ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የጸጋ ምሥጋና ካቀረበች በኋላ “…ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምሥጋና ይገባል፡፡” እያለች ታከብረዋለች፡፡ የመስቀሉ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
Hammasini ko'rsatish...
⬆️ I.Q Test እና የስነ-ልቦና ጦርነት! ኤርሚያስ ኪሮስ (አማካሪ ሳይኮሎጂስት) ሰሞኑን አንድ ድርጅት የሀገራትን የማሰብ አቅም ለክቼ ነው ብሎ መረጃውን አውጥቶ ነበር። ኢትዮጵያንም ከአለም ሀገራት በ163ኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጠ ሲሆን የሀገራችን አማካኝ የI.Q ነጥብ 69 ነው ብሏል (በነገራችን ላይ በI.Q የደረጃ አፈታት መሰረት በአማካይ 69 ማለት የተወሰነ የአእምሮ ችግር ያለበት ወይም mentally metarded) እንደማለት ነው። ይሄንን ዜና ብዙ የሀገራችን ሚዲያዎች ሳይቀሩ እንደወረደ ሲያስተጋቡት አይቼ ”ከሰደበኝ ስድቤን የነገረኝ” የሚለውን የሀገሬን ብሂል አስታወሰኝ። እንዲህ አይነት ፍረጃዎች በሀገር ላይ ያላቸው የስነ ልቦና ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ስለ I.Q በጣም ጥቂት ነገር ልላቹ ወደደኩ። የማሰብን አቅም የሚለካውን ሙከራ (Intelligence Quotient) ለመጀመሪያ ጊዜ አልፍሬድ ቢኔት እና የስራ ባልደረባው ቴዎዶር ሳይመን በ1905 አዘጋጁት። ሙከራው በዋናነት ቃላዊና የሆኑና ያልሆኑ ነገሮችን መረዳት (verbal and non-verbal comprhension)፣ የተለያዩ ቅርጾችን መረዳት (l erceptual peasoning)፣ መረጃዎችን የማገናዘብ ፍጥነት(processing speed)፣ የማስታወስ ብቃትን (Working Memory) የሚመዝን ነው። ይሄ ሙከራ የተዘጋጀበት ዋናው ምክንያት ከእድሜና የክፍል ጓደኞቻቸው ጋር ሲነጻጸሩ የመማር እክል(learning disabilities) ያለባቸውን ለመለየትና ለማገዝ ነው። ከአንድ እናት ተገኝተው አንድ ቤት እየኖሩ የተለያየ ብቃት ያላቸውን ሰዎች በምናይበት ዘመን ላይ እንዲህ አይነት ሙከራዎችን ሀገርን ለመፈረጅ ጥቅም ላይ መዋሉ ትልቅ ችግር ያለበት እንደሆነ አምናለሁ። ችግሩን ለማሳየት መጠየቅ ካለባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ውስጥ የተወሰኑትን ልጥቀስ 1. ማነው የወከለን? (Sampling Error) ኢትዮጵያ ከ100 ሚሊየን በላይ ዜጎች የሚኖሩባት ሐገር ነች። እንዲህ አይነት ጥናት ሲሰራ ኢትዮጵያውያንን የወከሉት ሰዎች እነማን ናቸው? የትና ምን ተማሩ? በምን አይነት የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ናቸው? ከከተማ ወይስ ከገጠር ተመረጡ? የተሻለ የትምህርት እድል ያገኙና ያለገኙ እኩል ሊነጻጸሩ ይገባል? ተነጻጽረው ልዩነት ቢመጣስ ልዩነቱን የፈጠረው ያገኙት የትምህርት እድል ነው እንጂ እንዴት የማሰብ አቅም ነው ይባላል? 2. ባህል ከግንዛቤ ውስጥ ገብቷል?(Cultural Factors) ሙከራው በየትኛውም ባህል ውስጥ የሚሰራ (Culture-Fair) እንደሆነ ይናገሩለት እንጂ እውነታው እንደዛ አይደለም። ለምሳሌ ብዙውን ጊዜ ከሚጠቀሙበት ሙከራ አይነት ውስጥ የተለያዩ ምስሎችን መረዳትና መገጣጠም ሲሆን አሜሪካ ውስጥ ያለ ልጅና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ልጅ ስለ ተለያዩ ቅርጾች አንድ አይነት ግንዛቤ ሊኖራቸው አይችልም። አንድ ምሳሌ ልጨምርላቹ: በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖር አንድ ሰው በአውሮፓ ከሚኖረው ሰው የተሻለ ስለ እጽዋትና የባህል መድሃኒት የተሻለ እውቀት አለው። ብዙውን ጊዜ መመዘኛዎቹ ግን ከምእራቡ አለም የሚነሱ (ethno-centric) ናቸው። ጥያቄዎቹ ወካይ አይደሉም። 3.ማን ከማን ተነጻጸረ?(Socio Economic Factors) በጥሩ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለና መብላት ጥያቄው የሆነበት ልጅ እኩል የማሰብ ብቃት የላቸውም። ልዩነቱን የፈጠረው ተፈጥሯዊ የማሰብ አቅማቸው ሳይሆን የኑሯቸው ሁኔታ ነው። 4.ቋንቋ(Language) ብዙውን ጊዜ እንዲህ አይነት ሙከራዎች በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚዘጋጁ ናቸው። ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሰዎች በእናት ቋንቋቸው ቢጠቀሙ የበለጠ የማሰብ አቅማቻው ይጨምራል። የተሰጠው ሙከራ በምን አይነት ቋንቋ የተሰጠና ሙከራውን የወሰዱት ሰዎችስ የመረዳት አቅምቸው ምን ያህል ነበር? በሐገር ደረጃ የሚሰጠውን ፍረጃ የተሳሳተ እንደሆነ ብዙ መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። እንዲህ አይነቱ ፍረጃ ህዝባችን ማሰብ አልችልም፣ ችግር አለብኝ ብሎ እንዲያምን ታዳጊዎችም አለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን እንዳይችሉና የዝቅተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል። እኛም ሆንን ሚዲያዎቻችን ከመዘገባቸው በፊት ማመዛዘንን ብንለምድ ጥሩ ነው። እንዲህ እንመን፣ እናሳምን: “ፈጣሪ ለሁሉም የሰው ልጅ አንድ አይነት ጭንቅላት ሰጥቷል። እኛ ኢትዮጵያውያን ከማንም ያነሰ ተፈጥሯዊ የሆነ የማሰብ ችግር የለብንም። በአለም አቀፍ ድርጅቶችና መድረኮች ላይ ድንቅ ነገር ሰርተው እድሉን ስናገኝ ከማንም የማናንስና እምቅ ችሎታ ያለን መሆናችንን ያስመሰከሩ ኢትዮጵያውያን ምስክር ናቸው"። የስነ ልቦናው ጦርነት እንዴት እየተካሄደ እንዳለ የበለጠ ለመረዳት ለምትፈልጉ ከታች ያስቀመጥኩት ጽሁፍ ጠቃሚ ነው። Jelte M. Wicherts, Conor V. Dolana, and Han L.J. van der Maas, A systematic literature review of the average IQ of sub-Saharan Africans, Intelligence, Volume 38, Issue 1, January–February 2010, pp. 1–20 @eliasmeseret
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
የሰኔ 14/2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽን በተመለከተ ይህንን መረጃ አንብቡት፡፡ ጠቃሚ እና ጥንቃቄ መኖር እንደሚገባው የሚያሳስብ ስለሆነ ለጥንቃቄ ይጠቅማል፡፡ 🌞የ2012 ዓ.ም ግርዶሽ የሚታየው፡ ✨ሰኔ እሁድ 14/2012 ዓ.ም ነው ✨በግርዶሹ 6፡00 ሰዓት የሚፈጅ ጨለማ ይታያል ✨በመላ ኢትዮጵያ ይታያል ✨በተለይ ወለጋ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አላማጣ፣ ኢንጂባራ 98% ጨለማ ሆኖ ይታያል ✨ፀሐይ ወደ ሰሜን የምታደርገው ጉዞ ይገታል ✨የዓለምን አሰራር የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካን፣ የከፍተኛ የተፈጥሮ ኃይል ሊገኝ ይችላል ብለው ሳንቲስቶች ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡ ✨ቀለበታማ የፀሐይ ግርዶሽ ✨በዚህ አጋጣሚ ሰኔ እና ሰኞ ገጥሟል ✨ከምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ ግርዶሹ ይታያል ✨ፀሐይ 98% ትሸፈናለች 🌞የሚታይበት እና የሚያበቃበት፡ ✨ከማዕከላዊ አፍሪካ ከኮንጎ ይነሳል፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ የመን፣ ፓኪስታን፣ ታይዋን፣ ንድና ቻይናን አቋርጦ ፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ያበቃል፡፡ 🌞የፀሐይ ግርዶሽ በሚከሰትበት ጊዜ ይከሰታሉ ተብለው የሚጠበቁ… ✨አበቦች የፈኩትን መልሰው ይዘጉታል፣ ✨የቤት እንስሳት ሊደናገጡ ወይም ሊረበሹ ይችላሉ፣ ✨የደመናና እና የንፋስ እንቅስቃሴ ሊዛባ ይችላል ወይም የአየር ሁኔታ ሊቀየር ይችላል፣ ✨የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሊጨምር ችላል፡፡ 2015 በተለይ ከዚህ ቀደም በእንግሊዝ 4% ጨምሮ እንደታየ ይነገራል፡፡ ✨የኮሚኒኬሽን ሳታላይቶች ላይ መዛባት ሊከሰት ይችላል፡፡ ✨ወፎች መዘመር ሊያቆሙ ይችላሉ፣ 🌞ግርዶሹን ለማየት የተመረጠች አገር፡ ✨ግርዶሹን ለማየት ኢትዮጵያ ተመርጣለች…. ✨ግርዶሹ ደረቃማ የአየር ሁኔታ ያለበት አካባቢ ተመራጭ ሆኗል፡፡ ✨በተለይም ላሊበላ፣ ሮሃ፣ ላስታ፣ ✨ግርዶሹ ላሊበላን ያቋርጣል 🌞ሙሉ ግርዶሹ የሚታይበት ወቅት፡ ✨ከሌሊቱ ሰኔ 14/2012 ዓ.ም. ✨11፡00 ሰዓት ይጀምራል፣ ✨ከጠዋቱ 12፡45 እስከ ቀኑ 6፡33 ✨በቀን ሜርኩሪን እና ቬነስን እናያለን 🌞ማስጠንቀቂያ፡ ✨በዓይን ለማየት አይቻልም ዐይን ያሳውራል፣ ✨በሱቅ ውስጥ የሚሸጥ መነጽር መጠቀም አይገባም፡፡ ✨ለፀሐይ ግርዶሽ ተብሎ የተዘጋጀ መነጽር አለ፡፡ ✨መነጽሩ በአገር ውሰጥ አይገኝም፡፡ ✨ሲጨልም ማየት እንችላለን ነገር ግን ያለመነጽር ለማየት አንሞክር፣ ✨ዐይናችን ሊፈስ ይችላል፣ ከመጋቤ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ ተገኘ መረጃ ነው፡፡ ይሄ ትንቢት አይደለም እግዚአብሔርንም መፈታተን አይደለም እንደ እግዚአብሔር አዋቂ ለመሆን መሞከርም አይደለም እንደዚህ አይነት ነገሮች ከስንት ጊዜ አንዴ የሚከሰቱ ክስተቶች ናቸው ይህ ይፈጠራል ብሎ መናገር እግዚአብሔርን መፈታተን አይደለም እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ብሩህ አይምሮ የሰጠው ሁሉን እንዲመረምር ነውና ይልቁንም ምድራችን ላይ ምንም አደጋ ሳይሳርፍ እንዲያልፍ መፀለዩ የተሻለ ነው። ሰናይ ጊዜ። Join https://t.me/booksatreading
Hammasini ko'rsatish...
Books @reading

ሰላም የ Books@reading ተከታዮች ........በዚህ channel:- 1):- ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀማቸው መፃህፍት በስፋት ይዳሰሳሉ.... ማለትም (የህግ መፃህፍት, የቀኖና መፃህፍት, የስርዓት መፃህፍት, የተግሳፅ መፃህፍት, የምክር መፃህፍት ) 2):- ስርዓታቸውን የጠበቁ ልብ-ወለዶች እና ትረካዎች በስፋት ይዳሰሳሉ። 3):-አስተማሪ ፁሁፎችና አስገራሚ ታሪኮች ይቀርቡበታል።....

እስኪ አሁን online ያላችሁ እና ይህ መልዕክት የደረሳችሁ ኦርቶዶክሳውያን ሁላችሁም: ከታች👇🏼ያለውን ሊንክ በመጫን ቻናላችንን ተቀላቀሉ(Join/Subscribe አድርጉ):- https://t.me/yetenantun_lenege @yetenantun_lenege
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
የጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር- ግንቦት 12/2012 ዓ/ም

✞✞✞ ይህ “ የትናንቱን ለነገ ” የተሰኘ የቴሌግራም ስብስባችን ነው:: • በእርጅናና በተለያየ ምክንያት ጤናቸው የተጓደሉና በየመቃብር ቤቱ የወደቁ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ለመንከባከብ :: • የአብነት ትምህርት መምህራንን: ተማሪዎችን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ለመርዳት እንዲሁም የትናንቱን ለነገ ለማስቀጠል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ልጆች የሚመክሩበት ገፅ ነው:: እንኳን በደህና መጡ !!! ✟✟✟ ----------------------- ቻናላችን ደግሞ ይህ ነው:- (https://t.me/yetenantun_lenege ይግቡና ቤተሰባችን ይሁኑ:: እናመሰግናለን! "የትናንቱን_ለነገ"
Hammasini ko'rsatish...
ከቅዱስ ሲኖዶስ አዋጅ በፊት የተዘጉ አቢያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ !!!! የቅዱስ ሲኖዶሶ ውሳኔ ሰሞኑን ብዙዎቻችንን ሲያነጋግር ውሏል ። አንዳንዶቻችን እንዴት ቤተ-ክርሰቲያን ይዘጋል ? ስለምንስ ቀኖና ቤተ-ክርስቲያን ተሻረ ? ስንል ውለናል ። መጨነቁ መልካም ሆና ሳለ ነገር ግን አስቀድሞ ይዘጋ የተባለ ቤተ መቅደስ መኖሩን ፣ ከተባለም የትኛው ቤተ- መቅደስ እንደሆነ መለየት ያስፈልጋል ። ቤተ- ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት አይነት ዘይቤያዊ ፍቺ እንዳለው ቅድስት ቤተ-ክርስቲያናችን አስተምራናለች ።በዚህም የመጀመሪያው ቤተ-ክርስቲያን እያንዳንዱ ምዕመን ነው ። ታዲያ ቅዱስ ሲኖዶስ ይሔኛው ቤተ-መቅደስ ይዘጋ ብሏል እንዴ ? በፍጹም ! ይልቁንም ከአዋጁ በፊት አስቀድመን ቤተ-መቅደሶቻችንን የዘጋን ብዙዎች ነን ! ቤተ መቅደስ ወንጌል ይነበብታል፤ ቅዳሴ ተቀድሶ የጌታችን ሥጋ እና ደሙ ይታደልበታል ፤ ሲከፈትም ዕጣን ዕጣን ይላል። ነዋያተ ቅድሳቱም ከቤተመቅደስ ውጪ ሌላ አገልግሎት የላቸውም። ታዲያ በዚህ መስፈርትነት ቢለካ ያንተ፣ ያንቺ አና የእኔ ቤተ-መቅደስ ክፍት ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ ነው ብለን ለመናገር እንደፍር ይሆን ? ካልሆነ ስንት የተዘጉ አቢያተ- ክርስቲያናት ይኖሩ ይሆን ? ወንጌል ተገልጦ የማይነብባቸው ፣ የጌታን ስጋ እና ደም የማይቀበሉባቸው እንዲሁም በሜሮን የከበሩት ነዋያተ ቅድሳቶቹ ከቤተ መቅደስ ውጪ ሰፊ አገልግሎት ያላቸው አካላት ያሉት ቤተ መቅደስ እንደምን ያለው ነው ? እነዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ሳይሆን እኛው በኃጢአት ቆልፈን የዘጋናቸው ቤተ- መቅደሶች ናቸውና አስቀድመን በንሥሓ ሳሙና እሽት አድርገን አጥበን በቅዱስ ቁርባን መድኃኒትነት ለዘለዓለም ፈውሰን ዳግም አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እና ለማስከፈት ሊቀ ጳጳሳቱ እኛው ነን ! ኹለተኛው ቤተ-ክርስቲያን የክርስቲያኖች ሕብረት ነው። ይህ ሲባል ስብስቡ ከኹለት ይጀምራል። "ኹለትም ሦስትም ሆናችኹ በስሜ ብትሰበሰቡ በመካከላችሁ እገኛለሁ" እንዲል ታዲያ ይህ ሁለት እና ሦስት ምዕመን ያለው ቤተ መቅደስ ሩቅ አይደለም ።ይህችኛዋ ቤተ-ክርሰቲያን መኖሪያ ቤታችን ውስጥ ያለችዋ ናት ! እህት ወንድም ፤ እናት አባት ፤ አክስት አጎት ፤ ሚስት ልጆች ያለን ብዙዎች ነን ነገር ግን የዚህችኛዋስ ቤተ መቅደስ ውሎዋ እንዴት ነው ? ከተዘጋች ስንት ዘመን አስቆጠረች ? በሕብረት በጸሎት ከእግዚአብሔር ፊት ይቆምባት ይሆን ? ካልሆነ ፈጥነህ ለመክፈት እና አገልግሎት አስጀምረህ እግዚአብሔርን ቤትህ ለመጋበዝ ሊቀ ጳጳሱ አሁንም አንተ ነህ !!! ቤት ቁጭ ብዬ ምን እሰራለሁኝ አትበል ቤተ-ክርስቲያንም ተዘጋ ብለህ አታልቅስ ይልቁንስ ከዘጋኸው ዘመናት ያለፈውን ቤተ- መቅደስ አሁኑኑ በቤተሰብ ጸሎት አገልግሎት እንዲጀምር አድርገው ! የመጨረሻው እና ሦስተኛው ደግሞ ኹላችንም የምናውቀው ህንጻው ቤተ- ክርስቲያን ነው ! ይህችኛዋ ደግሞ ልዪ ናት ! ምስጢራት የሚፈጸምባት ፤ ወደዚህች ምድር ስንመጣ ዘለዓለማዊ የልጅነት ጸጋን ያገኘንባት ፤ ብንሞትም በጸሎት ፍትኃሐት የምንሸኝባት ስለሆነች ትዘጋ ቢባል ማዘን እና ማልቀስ ተገቢ ነው ! ነገር ግን ቅዱስ ሲናዶስ በፍፁም ትዘጋ አላለም !!! የሚደንቀው ደግሞ የማይታየው ከሚታየው ስለሚበልጥ ፤ የቅዱሳን መላእክት ፣ ድል የነሱ የቅዱሳን ሰማዕታት እንዲሁም የጻድቃን እና የደናግላን ሕብረት አካል ስለሆነች በሰው እጅ የሚዘጋ እና የሚከፈት ምድራዊ በር የሌላት መሆኑ ነው ! እንግዲያውስ ትዘጋ ካልሆነ ምንድነው የታዘዝነው ? በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጀው ቆራቢ ብቻ ቅዳሴው ላይ በቀጥታ እንዲሳተፍ ነው ። ወንድሞቼ እና እህቶቼ ባለመታዘዝ የተገኘ በረከት የለም ! ከቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ውጪ መሆን ክህደት ነው ! ባለመታዘዝ ቅስፈት እንጂ ድኅነት አይገኝም ! ወትሮውንም ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያዘው ቆራቢ ብቻ እንዲያስቀድስ ነው !!! ስለዚህ ለቅሶውን ንሥሓ ገብቶ ለቅዱስ ሥጋውና ለክቡር ደሙ ለመብቃት ብናደርገው ያዋጣናል ። እኛ አላዋቂ የሆን ጀማሪ ደቀ መዛሙርት አረጋውያን የኾኑ የሕይወት መምህራኖቻችን ብሎም የ--ነ--ፍ--ስ-- አባቶቻችን የሚያዙንን የመተግበር ሃይማኖታዊ ግዴታ አለብን!!! በእኛ ፈሪሳዊነት እና አለመታዘዝ ተንቀሳቃሽ ቤተ- መጻሕፍት የኾኑ አባቶችን ማጣት ንሥሓ የማይሽረው በደል ነው !!!! ዛሬ ኑ ችግር የለውም ያልናቸውን ምዕመናን አያድርገውና አንድ ካህን በወረርሽኙ ምክንያት ቢታመምብን ከባድ የዕምነት ፈተና ውስጥ የሚከት ብሎም ተስፋ የሚያስቆርጥ ስለሆነ ግድ የለም እንታዘዝ !!! #ለቅዱስ ሲኖዶስ አለመታዘዝ ክህደት ነው #ንስሓ ገብቼ ለመቁረብ ቤተ- መቅደስ እሔዳለኹ #የዘጋኋቸውን የግሌን እና የቤተሰቤን ቤተ መቅደስ እከፍታለኹ #አረጋውያን የሆኑ አባቶቼን ካህናትን እና ጳጳሳትን ጭምር የወለዱ እናቶቼን ከወረርሽኙ እጠብቃለኹ ፈጣሪያችን ይህን የጭንቅ ቀን አሳልፎ ትንሳኤውን ትንሳኤያችን ያድርግልን !!! ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት ከበደ (Not dndrda) መጋቢት 24 2012
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.