cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Deacon Cherinet

ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤አሜን 2ኛ ጴጥ 3፡18 በተዋህዶ እምነታችን ፀንተን እንኑር ! ጥቆማ ወይም ጥያቄ ካላቹ በዚህ የተለግራም ቦት👉🏽https://t.me/Cher2112bot ይጠቀሙ This channel is operated by Deacon Cherinet

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
397
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+317 kunlar
+13730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ሁለተኛ ክፍል 3. ተስፋ:— የጌታችን ዕርገት ያለ ተስፋ የሆነ ዕርገት አይደለም የኤልያስ ዕርገት በመጎናጸፊያው በኩል ለኤልሳዕ ተስፋ ከሆነው በላይ የጌታ ዕርገት ለቤተ ክርስቲያን በተዘረጉት የይቅርታ እጆች በኩል የተላለፈው ቡራኬ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሰማይ ወደዙፋኑ የተጠራችበት ተስፋ ነው፣ ኤልሳዕ በመምህሩ በኤልያስ መጎናጸፊያ ከተሰጠው እጥፍ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በእጅጉ የበለጠ ስጦታ በጌታችን ዕርገት ጊዜ ተቀብለናል፤ ይህም ተስፋ በሁለት የሚከፈል ነው፦ የመጀመሪያው ተስፋ የመንፈስ ቅዱስ ወደዚህ ዓለም መምጣት ሲሆን (ዮሐ 15÷26፣ሉቃ24÷49) ሁለተኛው ተስፋ ደግሞ የእኛ ዕርገት ነው የእርሱ ዕርገት የእኛ ዕርገት ነውና፣ ሊቃውንቱም "ዐርገ እግዚአብሔር ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን " (የንጹሐን ጻድቃንን ዕርገት ያረጋግጥ ዘንድ እግዚአብሔር ወልድ ዐረገ) በማለት ነግረውናል፤ ትንሣኤው ለትንሣኤያችን ማረጋገጫ እንደሆነ ዕርገቱም እንዲሁ ነውና ፡፡ ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ ይላል :— "በቀኜም ተቀመጥ አለው ይህ ሥጋ ቀድሞ አንተ መሬት ነህ ወደ መሬትነትህም ትመለሳለህ የሚል አዋጅን ሰምቶ ነበር ዛሬ ግን ስለዚህ ሥጋ ከሰማያት በላይ መሆን ብቻ አልበቃውም በመላእክት ቦታ አልተወሰነም።ይህም ክብር አልበቃውም፤ከመላእክት በላይ ከሆነ ከሱራፌልም በላይ ከፍ አለ ወጥቶ ከሊቃነ መላእክት በላይ ሆነ እንጂ ወደላይ መውጣት ብቻ አልበቃውም ወደ መንግሥት ዙፋን ወጥቶ በላዩ እስከመቀመጥ ደረሰ እንጂ…………የእኛን ባህርይ ከዚህ ከፍተኛ ያህል የርኅቀት መጠን በላይ አውጥቶ አኖረው፣ ቀድሞ ሰውን ካወረደበት ቦታ በታች ምንም የለም ዛሬም ሰውን ካወጣበት ቦታ በላይ ምንም የለምና።" በማለት የመጨረሻውን ስፍራችንን ይነግረናል (ሃይ . አበ 88÷23—27)፡፡ ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስም "ወአንሥአነ እግዚአብሔር አብ ምስሌሁ ወአንበረነ በየማኑ በየማኑ በሰማያት በኢየሱስ ክርስቶስ" (እግዚአብሔር አብ ከእርሱ ጋር ለመኖር አስነሥቶ በኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ በክብር አኖረን) ብሏል (ሃይ . አበ) ፡፡ ይህም ደግሞ እርሱ ራሱ ባለቤቱ "እምከመ ተለዐልኩ እምድር እስኅብ ኲሎ ኀቤየ" (ከምድር ከፍ ያልኩ እንደሆነ ሁሉን ወደኔ እስባለሁ, ዮሐ 12÷31) ዳግመኛም ፡"እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ " (ዮሐ 14÷3) በማለት የሰጠን የመጨረሻ ተስፋ የተረጋገጠበት ነው። 4. ቀጠሮ:— ይህ ቀጠሮ ዕርገታችን የሚከናወንበት ፤ ተስፋችን የሚጨበጥበት ቀጠሮ ነው እርሱም ዳግም ምጽአቱ ነው። ይህንንም ቀጠሮ ለቤተ ክርስቲያን አስይዘው የሄዱት ብሥራተ ትስብእቱን/ሥጋዌውን ለእመቤታችን ፣ብሥራተ ትንሣኤውን ለቅዱሳት አንስት የተናገሩ መላእክት ናቸው ፤ነጫጭ አልባሳት ለብሰው "………ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል" (ሐዋ 1÷11) በማለት አስረግጠው ተናግረዋል፣ አቡቀለምሲስ ዮሐንስም "እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል ፤ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል……" (ራእ 1÷7) በማለት በዕርገቱ ያየነውን ደመና በዳግም ምጽአቱ እንደምናየው አስተምሮናል(ሊቃውንት የጥምቀት፣የደብረ ታቦር፣የዕርገት፣የምጽአት ደመና የባህርይ ክብሩ/ክበበ ትስብእት/ሥጋ ማርያም ነው ብለው ተርጉመዋል )። እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ልጅነታችን ጠብቀንና አስጠብቀን የመንግሥቱን መሰጠት እየተጠባበቅን እንኖራለን። ዕርገቱ ዕርገታችን ነው ብለን በፍጹም እምነት እናምናለን! ይህን የወልደ አግዚአብሔርን ዕርገት የማያምኑ፤ አምላክነቱን የማይቀበሉ፤ እንዲሁም የእናቱን የእመቤታችንን ዕርገት የሚክዱ እንደ ይሁዳ አንጀታቸው ተዘርግፎ ንዋየ ውስጣቸው ወጥቶ ይሞታሉ! የጌታን ዕርገት ያመነ የእኛን ዕርገት ያረጋግጣል፣ የእኛን ዕርገት ያመነ ደግሞ የእናቱን ዕርገት እንዴት ይክዳል??? እኛ ግን "ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም" (የሙታንን መነሣትና ዕርገት እናምናለን፤የሚመጣውንም የዘለዓለም ሕይወት አዝማነ መንግሥተ ሰማያትን ተስፋ እናደርጋለን) እያልን በቅድስቲቱ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን እየተባረክን እንኖራለን!!! ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ ፤ ሉቃ24፡53፡፡ በትንሣኤው ላነሣን በእጆቹ ለባረከን በዕርገቱ ላሳረገን የማታልፍ ዘለዓለማዊት ርስቱን ለሚያወርሰን ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይድረሰው።።። ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን!!! አሜን!!!
Hammasini ko'rsatish...
3
#ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ✿ ቡራኬ ፣ ሹመት ፣ ተስፋ ፣ ቀጠሮ ✿ ጥንቱ ግንቦት 8 ቀን ዕለቱ ዕለተ ሐሙስ ጌታችን ያረገበት ዕለት ነው። በቀመረ ድሜጥሮስ በሊቃውንት ውሳኔ መሠረት ዕለቱን (ሐሙስን) ሳይለቅ በግንቦት 5 (ኢይወርድ/ታሕታይ ቀመር) እና በሰኔ 9 (ኢየዐርግ/ላዕላይ ቀመር) መካከል እየተመላለሰ የሚከበር ከዘጠኙ የጌታ ዐበይት በዓላት ዋናውና የመጨረሻውም ነው፡፡ ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ለሐዋርያት መጽሐፈ ኪዳንን እያስተማረ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያሳየ፣ ለነፍሳት ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን እየገለጠ 40 ቀን በዚህ ዓለም መቆየቱን ቀደም ብለን አስነበብናል! የጌታችን የዕርገት ታሪክ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል 24 ÷50 ጀምሮ የተጻፈ ሲሆን ደቀመዛሙርቱ በዓይናቸው እያዩት እየባረካቸው ከዓይናቸው መሠወሩ ተገልጧል፣ሐዋርያትም ለረጅም ሰዓታት ዓይኖቻቻውን የሥጋ ዓይን የማየት ማብቂያ የሆነው ግዙፍ መጋረጃ ሰማይ ላይ ተክለው የቆዩ ሲሆን ነጫጭ ልብስ የለበሱ መላእክት መጥተው "ዳግመኛ ይመጣል" በማለት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ አሰናብተዋቸዋል። ሐዋርያትም የተደረገላቸውንና የሚደረጉላቸውን አራት ነገሮች እያሰቡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። 1. ቡራኬ:— "አንሥአ እዴሁ ወባረኮሙ" እንዲል እጆቹን በላያቸው ላይ ጭኖ ባረካቸው፣ "እየባረካቸውም ራቃቸው፣ ወደ ሰማይም ዐረገ" ይላል (ሉቃስ ፣ቅ.ያሬድ)። ይህ ቡራኬ ለሐዋርያት በመዋዕለ ሥጋዌው ከሆነው ሁሉ የመጨረሻው ቡራኬ ነው ፤ ይህንን ቡራኬ መቀበል እስከዚህ ተራራ ድረስ መጽናትንና መታገሥን የሚጠይቅ ነው፤ ይህ ዕለት ደግሞ በክርስቶስ የጸኑት የተባረኩበት፤ክርስቶስን ዕሩቅ ብእሲ ብለው እንደተራ ሰው እና እንደ እቃ በወርቅና በብር የሸጡና የለወጡ ሰዎች አንጀታቸው ተዘርግፎ የሞቱበት ዕለት ነው፣ ቡራኬው ዛሬም የማይቋረጥ መሆኑን ሲያረጋግጥልን ደግሞ "ወእንዘ ይባርኮሙ ተረኀቆሙ ወዐርገ ሰማየ" (እየባረካቸው ራቃቸው ፤ወደ ሰማይም ወጣ) በማለት ይነግረናል (ሉቃ 24÷51)። ዛሬም ቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴ ፍጻሜ ላይ ካህኑ እጆቹን አመሳቅሎ "እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን " በማለት ያን የ"ዕርገት" በረከት/ቡራኬ ለምእመናን ስታድለውና ስታከፋፍለው ትኖራለች፤ ይህም ደግሞ "እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ " (ማቴ 28÷20) በማለት የገባልን ኪዳን ማረጋገጫ ቡራኬ ነው። በዚህም ቡራኬና ኪዳን ቤተክርስቲያን ጸንታበት፣ አስከ ዓለም ፍጻሜ ሳትፈርስ ሳትናወጥ ተማምናበት ትኖራለች።። እሊያ አዳምን ውብና ድንቅ አድርገው አከናውነው የፈጠሩ ፣ኋላም ልዩ ልዩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሙታንን ለማስነሣት የተዘረጉ፣ ለቤተ ክርስቲያን መስቀል ላይ የተቸነከሩላት እጆች፣ በተዘጋ ቤት ውስጥ በፍርሃትና በድንጋጤ ለነበረች የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን (ጉባኤ ሐዋርያት) "ሰላም ለኩልክሙ" በማለት የተዘረጉላት እጆች ፣በዕርገት የማያልቅ በረከትን ለመስጠት የተመሳቀሉላት እጆች እንደጣራ እንደ ጒልላት ሆነው ከድነዋት ምሕረትና ይቅርታ እየዘነበላት ትኖራለች። 2. ሹመት:— ቡራኬው በውስጡ ከያዛቸው ታላላቅ ምሥጢራት አንዱ "ሢመት መንፈሳዊ" ነው፤ ሐዋርያት እስከዚህ ቀን ድረስ የተሰጣቸው ሹመት ሁሉ በቡራኬ የተረጋገጠበትና የመጨረሻውን የክህነት ሥልጣን/ፕትርክናን የተቀበሉበት ዕለት ዕለተ ዕርገት ነው፤ መተርጒማነ ወንጌል ሊቃውንትም "ወእንዘ ይባርኮሙ ተረኃቆሙ ወዐርገ ሰማየ" ያለውን ሲተረጒሙ "ሾሟቸው የርቀት(ቀ ፊደል ጠብቆ ይነበብ) ያይደለ የርኅቀት ተሠውሯቸው ወደ ሰማይ ዐረገ" ብለዋል (ትር . ወን)። ዛሬም እነዚህ ተመሳቅለው እየባረኩን ተዘርግተው ያረጉ እጆች በአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት፣በሊቃነ ጳጳሳትና፣በጳጳሳት አማካይነት ካህናትን እየሾሙ ይኖራሉ። ይቀጥላል…
Hammasini ko'rsatish...
2👍 1🥰 1
“ንስሐ ልገባ እችላለሁ ወይም እገባለሁ ብለህ ኃጢአት አትሥራ፤ ይቅር ይለኛል በሚል ድፍረትም በኃጢአት አትውደቅ፤ አስታውስ ሞት አይዘገይሞ፡፡ እግዚአብሔርም አይሾፍበትም፡፡” ማር ይስሐቅ ሶርያዊ @deaconcherinet @deaconcherinet @deaconcherinet
Hammasini ko'rsatish...
6👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኃጢአት ምኞትህን የሚዛን ልክ በልብህ ውስጥ ያመጣጥን ዘንድ ማንኛውንም ዓይነት መንፈሳዊ ሥራ በመሥራት የክፋታቸውንና የአደጋቸውን መጠን ቀንስ። የምኞት ኃጢአት እስክታስወግደው ድረስ መልካም ፈቃድ በልብህ ውስጥ ቀስ በቀስ እንደሚያብብ እርግጠኛ ሁን። መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ እንደሚሰራ ሲታወቅህ ችላ አትበለው፤ ከእርሱ ጋር ሥራ እንጂ በምኞትህ ልትቀጥል አትሞክር። #አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ @deaconcherinet @deaconcherinet @deaconcherinet
Hammasini ko'rsatish...
👍 2 2
ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት። "ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "ስትሰድባቸው፣ ስታመሰግናቸው እና ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት። @Deaconcherinet @Deaconcherinet @Deaconcherinet
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 2🤣 1
"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል? "ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡ እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው? አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው። እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ @Deaconcherinet @Deaconcherinet @Deaconcherinet
Hammasini ko'rsatish...
+++ ጸልየህ ልታደርገው ትችላለህ? +++ ማልዶ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ወደ ሥራ የሚሄድ አንድ መንፈሳዊ ሰው በጉዞው ከሌላ መንገደኛ ሰው ጋር ይገናኛል። ጥቂት እንደ ተጨዋወቱ ይህ በመንገድ ያገኘው ሰው ከደረት ኪሱ የሲጋራ ፓኮ በማውጣት አንዱን መዝዞ እንዲወስድ ይጋብዘዋል። ያም መንፈሳዊ ሰው "አይ ይቅርብኝ" ሲል እምቢታውን ገለጸ። ባለ ሲጋራውም "ኃጢአት ነው ብለህ ስላሰብህ ነው እምቢ ያልከኝ? ማጨስ እኮ ከአስጨናቂዋ ሕይወት ፋታ ለመውሰድና ራስን ዘና ለማድረግ ይረዳል። ግድ የለህም አንዱን ሞክር" እያለ ሊያግባባው ጣረ።  በመጨረሻም መንፈሳዊው ሰው "ግድ የለም ለእኔ ይቅርብኝ። ባይሆን አንተ ይጠቅመኛል ካልህ በቃ ሲጋራውን ከመለኮስህ በፊት አንድ "አባታችን ሆይ" ጸልይና ጀምር" አለው። በዚህ ጊዜ ያ መንገደኛ ደንግጦ እንዲህ ሲል መለሰ "ጸሎት ጸልዬማ እንዴት እንዲህ አደርጋለሁ?!" በጸሎት ልትጀምር የማትችላቸው ማናቸውም ነገሮች ለአንተ መልካም አይደሉም። በልብህ ኃጢአት እንድታደርግ የሚገፉፉህ ክፉ ሐሳብ ሲመጣ "ይህን ጸልዬ ማድረግ እችላለሁ?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። ከጸሎት ጋር የማይጣጣም ከመሰለህ እርሱ ኃጢአት ነውና ተወው። ጸልዮ የሚዘሙት፣ ጸልዮ የሚሰርቅ፣ ጸልዮ ባልንጀራውን የሚሳደብ፣ ጸልዮ በወንድሙ ላይ ክፉ የሚያደርግ ማን ነው? ዲያቆን አቤል ካሳሁን @Deaconcherinet @Deaconcherinet @Deaconcherinet
Hammasini ko'rsatish...
8🙏 3
#ንስሐ እንዴትና ለማን እንገባለን? ንስሐ ገብተን፣ የኃጢአትን ስርየት አግኝተን፣ ከሰውና ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን በጽድቅ ጎዳና ለመራመድና በደህንነት ጸጋ ለመኖር እንድንችል ቢያንስ ሦስት ነገሮችን መፈጸም አለብን:: #የመጀመሪያው የንስሐ ሐዘን ማለትም እውነተኛና ልባዊ ጸጸት በቅድሚያ እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ #ሁለተኛው ኑዛዜ ሲሆን #ሦስተኛው ደግሞ ስለኃጢአታችን የሚሰጠንን የንስሐ ቅጣት የሚያመለክት የቀኖናን ሥርዓት መፈጸምና እንደዚሁም በካህኑ በኩል የምናገኘው የፍትሐት ጸጋ ነው:: #የንስሐ ሐዘን /ጸጸት/ ንስሐ የሚገባ ሰው በመጀመሪያ ኃጢአቱን እያስታወሰ ሰውና ፈጣሪውን መበደሉን እያሰበ የሚያደርግው ሐዘን ወደ ንስሐ የሚወስድ እውነተኛ ሐዘን ስለሆነ ሃዘኑን እግዚአብሔር ይቆጥርለታል፡፡ ብፁዓን ናቸው፣መጽናናትን ያገኛሉና» /ማቴ. ፭፥፬/ የተባለው የራሳቸውንና የሌላውን ኃጢአት እያሰቡ የሚያዝኑትን ተነሳሒያን ያመለክታል፡፡ #ንስሐ ማለት ጸጸትን የሚያመለክት ቢሆንም ቁጭትና ቅንዓት የሞላበት የዓለማዊ ጸጸት ሳይሆን እውነተኛው ሐዘንና መመለስ መሆኑን በቅድሚያ መገንዘብ ይኖርብናል:: ስለ እውነተኛው ሐዘን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚከተለው ያስተምረናል፡፡ « አሁን ስለ ንስሐ ስላዘናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላዘናችሁ አይደለም ፤በምንም ከእኛ የተነሳ እንዳትጎዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዝናችኋልና፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን ጸጸት የሌለበትን፣ወደ መዳንን የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ሐዘን ግን ሞትን ያመጣል።» /፪ኛቆሮ. ፯፥፱-፲/:: እንግዲህ እውነተኛውን ሐዘን ከእንባ ጋር አድርጎ በንጹህ ልቦናና ጸሎት ለእግዚአብሔር በማቅረብ ተነሳሒው እንደገና ላለመበደል መወሰን ይኖርበታል። ውሳኔውንም ለመፈጸም የሚያስችለውን የመንፈስ ቅዱስን ረድኤት በማግኘት ሁልጊዜ ተግቶ መጸለይ አለበት። @deaconcherinet @deaconcherinet @deaconcherinet
Hammasini ko'rsatish...
👍 2🙏 2
+++ እግዚአብሔር ሲቀጣን ... +++ "[አንድ] ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡ "#እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡" © ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገ. 36 @deaconcherinet @deaconcherinet @deaconcherinet
Hammasini ko'rsatish...
🥰 4👍 2
+ #ዝም_ብለን_የምንጠላው_ሰው + ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም? "እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም" "አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም" "እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም" ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ:: እግዚአብሔር ግን "አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል" (ዮሐ 3:16) የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል:: እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም:: @deaconcherinet @deaconcherinet @deaconcherinet
Hammasini ko'rsatish...