cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

NIGAT

Positive thinking, or an optimistic attitude, is the practice of focusing on the good in any given situation.

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
756
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+17 kunlar
-1030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
📕መሸበርና መፍራት የነገን ችግር አያስወግድልንም ይልቁኑስ የዛሬን ደስታ ያሳጣናል። 📘ሕይወት፣ የመዘጋጃና የመኖሪያ ዕድሜ የሌላት፣ ከአፈር ለተሠራ ሰው የተሰጠች ስጦታ ነች ፡፡ የሰው ልጅም ከተፈጠረ ጀምሮ ሕይወትን በውስጡ ለማሰንበት በትግል የሚኖር፣ሲያጣትም እጅግ ጠሊቅ ሐዘን ውስጥ የሚገባ ፍጡር ነው፡፡ 📗ሰዉ የራሱንና የሚወዳቸውን እስትንፋስ ለማቈየት፣ ከሰከንድ እስከ ሰዓታት ከዛሬው እየተበደረ ለማያውቀው ነገ ሲገብር፣ ለማያውቀው ነገ ደስታ ዛሬ ሲያለቅስ፣ ለማያውቀው ነገ ጥጋብ ዛሬ ሲራብ ሲታረዝ፣ ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር ነው…፡፡ 📒በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ 📘 ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡ 📖ሜሎሪና መፅሀፍ የተወሰደ 📕📔📗📕📗📔📕📗📔📕📗
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
* ከውድቀት በኋላ የሚመጣ ስኬት ምንያህል ጣፋጭ ነው? * ስኬትን ለማግኘት ብዙ ጊዜ መውደቅ አለብን። አንዳንድ ጊዜ በመቶዎች ወይም በሺዎች የሚቆጠሩ ጊዜያት መውደቅ ሊኖርብን ይችላል። ብዙውን ጊዜ እነዚህ ውድቀቶች እያንዳንዳቸው በራሳቸው የመጡ አስከፊ ክስተቶች ሊመስሉን ይችላሉ። ፍጹም ከጨዋታ ውጭ ሊያደርጉን እና ተስፋ ሊያስቆርጡንም ይችላሉ። ከዚህ ሁሉ ውድቀት በኋላ የሚመጣ ድልም ያንያህል ደስተኛ ላያደርገን ይችላል ብላችሁ ልታስቡም ትችላላችሁ። ይሁንና ስኬት ውድቀታችንን ሁሉ ድል የሚነሳ ታላቅ ሃይል ያለው፤ ወደፊት ጠንክረህ እንድትጓዝና ያለፈውን ውድቀትህን እንዳትደግም የሚያበረታህ፤ በሃሴትና በደስታ ተሞልተህ ወደላይ እድትወጣ የሚገፋህ እና ነገሮችን በማስተዋል እንድታደርጋቸው የሚያደርግህ ትልቅ አቅም ያለው ነው። አንዴ እዚያ ከደረስክ ሁሉንም ውድቀቶችህን ትረሳና የስኬት ጎዳናህን ትጀምራለህ፤ ያንጊዜ ስኬት ምን ያህል ጣፋጭ እንደሆነች ትረዳለህ።
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
የጋብቻዬ ቀለበት#

ሰው ላይ ዝም ብለን ከመፍረድ እንቆጠብ!! ንጋት ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቀኖን ያሳምሩ❤ 🙏❤

https://www.youtube.com/channel/UCdQd__rYYutDdq1PBXesS-A

ፍቅርህ ስኬት ነው? የይቅርታ ሃይል የሚለካው፣ ቢያሳምም በደል የሚተወው፣ ለሰው መኖር የሚቻለው፣ የአምላክ ፍቃድ ቅድሚያ የሚሰጠው፣ ጥልቁን ስሜት ለመጋራት ወደኋላ የማይባለው በእርግጥም ፍቅርን ከቃል በላይ መኖር ሲቻል ነው። ሰዎች ይሳሳታሉ በፍቅራቸው ግን ይተራረማሉ፣ ጥፋትን ይፈፅማሉ ነገር ግን ተጨማሪ የመስተካከያ እድል ይሰጣጣሉ፣ ከጉዳታቸው በላይ የሚወዱት ሰው ስለመጎዳቱ አብዝተው ያስባሉ፣ በሚወዱትና በሚያፈቅሩት ሰው ደስታ ሃሴት ያደርጋሉ፤ ነፍሳቸውን ያሳርፋሉ፤ መረጋጋትን ይጎናፀፋሉ። ነገር ግን ይህም ሆኖ ሳለ በአስደሳቹ የፍቅር ህይወት ድንበር መኖሩ አይቀሬ ነው። ዋንኛው ምክንያቱም ፍቅርን ለማፅናት፣ ለመጠበቅና ከለላ ለመስጠት ነው። በፍቅር ውስጥ እራስህን ትገድባለህ፣ ከብዙ ነገር ትጠበቃለህ፣ የእሳቤ ደረጃህን ታሳድጋለህ፣ የአንድን ሰው ህይወት በሃላፊነት ትረከባለህ። አዎ! ጀግናዬ..! ፍቅርህ እስኬት ነው? የመውደድህ ዳርቻ፣ የማክበርህ ጥግ፣ የእንክብካቤህ መጠን፣ የሃዘኔታህ ጫፍ እስኬት ነው? ያለህበትን የፍቅር ህይወት እስከምን ታከብረዋለህ? እስኬት ጊዜ ትሰጠዋለህ? ምንያክል በሙሉ ትኩረት ትጠብቀዋለህ? ሃሳብህ ትልቅ ከሆነ፣ በአላማ የምትኖር ከሆነ፣ ህይወትህን በትክክለኛው መንገድ መምረት የምትፈልግ ከሆነ የፍቅር ህይወትህን መስመር የማስያዝና አስደሳች የማድረግ ሃላፊነት አለብህ። አንተ ያልጠበከው ግንኙነት በማንም አይጠበቅም፣ አንተ ያላከበርካትን፣ ያልተረዳሃትን፣ ያላወካትን ወዳጅህን ማንም ካንተ በላይ ሊያከብራት፣ ሊረዳትና ሊያውቃት አይችልም። ትኩረት የሰጠሀው የፍቅር ግንኙነትህ የተረጋጋ ህይወትህ ዋስትና ነው። በአንዳንድ የህይወት አጋጣሚ ብትፈተን በእርሱ ትበረታለህ፤ በስራ ጉዳይ ብትሰበር በእርሱ ትጠገናለህ። አዎ! ፍቅር ሰላም ነው፤ ፍቅር መረጋጋት ነው፤ ፍቅር ሃይል ነው፤ ፍቅር ብርታት ነው። የትኛውም አይነት ፍቅር ሊሆን ይችላል የእራስ፣ የእናት፣ የአባት፣ የወንድም፣ የእህት፣ የልጅ፣ የጓደኛ፣ የተቃራኒ ፆታ፣ የሃገር ፍቅር ይሁን አዎንታዊ ሃይልን እስካመነጨና ውስጣዊ ሰላምን እስካረጋገጠ ድረስ ሁሌም የፍቅር ሃያልነት ፀንቶ እንደኖረ ነው። ነገር ግን ለምንም ነገር እምነትህ ወሳኝ እንደሆነው ሁሉ የፍቅርን ፍፁም ሃይል ለመመልከትም በፍቅር ሃያልነት ማመን ይጠበቅብሃል። መኖር በፍቅር ሲሆን ችግር ቢኖርም መፍትሔ ይኖረዋል፤ መሰናክል ቢበዛም መሻገሪያው ድልድይም በዛው ልይ ይዘጋጅለታል። ከምንም በፊት እራስህን ጠብቅ፣ ለጤናህ ተጠንቀቅ በመቀጠልም የፍቅር ህይወትህን ጨምሮ ሌሎች ግንኙነቶችህን ጠብቅ። አንተ በመኖርህ የፍቅር ህይወት ኖረህ፣ የፍቅር ህይወት ስላለህ ደግሞ የተሻለ ህይወት እየኖርክ እንደሆነ እርግጠኛ ሁን። የህይወት አጋር የምትፈልገው ለተሻለ ብርታና ጥንካሬ እንጂ ለውድቀትና ለስብራት እንዳልሆነ አስታውስ። ═════════❁✿❁ ═════════
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ንጋት ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቀኖን ያሳምሩ❤️ 🙏❤️ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/nigatethiopian ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCdQd__rYYutDdq1PBXesS-A ቴሌግራም፦ https://t.me/nigatethiopian ኢንስታግራም ፦ https://www.instagram.com/ ቲክቶክ ፡- https://www.tiktok.com/@nigatethiopia? 👍👍👍NIGAT
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...

መልኳ አይደለም! ብትወድቅ የሚያነሳህ፣ ብትሰበር የሚያጠነክርህ፣ ተስፋ ብታጣ ተስፋ የሚሰጥህ፣ ልጆችህን የሚቀርፅልህ፣ ብርታት የሚሆንህ፣ ከህልምህ ጎን የሚቆመው፣ እለት እለት የሚደግፍህ መልኳ ሳይሆን አመለካከቷ ነው፤ አቋሟ ሳይሆን እይታዋ ነው፤ ገጿ ሳይሆን ጥንካሬዋ ነው፤ ስብዕናዋ ነው። ለጊዜው በመልኳ ልትማረክ ትችላለህ፣ በተክለ ቁመናዋ ልትገዛ ትችላለህ፣ በእይታ ልትመርጣት ትችላለህ እርሷ ጋር የሚያቆይህ ግን ማንነቷ፣ አመለካከቷና የእሳቤ ደረጃዋ ነው። ብዙ መስፈርት፣ ብዙ መመዘኛ ማስቀመጥ ግንኙነትን ከማስተካከል ይልቅ የማበላሸትና ሚዛኑን የማሳጣት እድሉ በጣም ሰፊ ነው። ወዳጅ አገኛለሁ ብለህ በጊዜያዊ መስፈርት እራስህን አትክበብ። አዎ! ጀግናዬ..! መልኳ አይደለም! በአብሮነት ዘመን ዋስትና ያስፈልግሃል ጊዜያዊው መልክና ቁመና ግን ዋስትና ሊሆንህ አይችልም፤ ለግንኙነትህ ዘላቂነት ውበቷ ምንም የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፤ ያኔ እያልክ የምታወራበት ጊዜ ይደርሳል። በእርግጥም ለግንኙነትህ ቀጣይነት ከተጨነክ፣ እርሱ ካሳሰበህ ማተኮር ያለብህ ላይ አተኩር፣ ዋጋ ለሚሰጠው ዋጋ ስጥ። ፊት ልብ አይሆንም፣ አቋም በጉዞህ ሁሉ አይደግፍህም። ትክክለኛ ምርጫህ በመልክ ሳይሆን በማንነት ይረጋገጣል፤ ከሩቅ ሳይሆን በቅርበት ከእውቀት ቦሃላ ይፋ ይወጣል። ከማንም ጋር ለመሆን ስታስብ አላማህ ዘላቂና የሰመረ ግንኙነት እስከሆነ ድረስ ትኩረትህንም ዘላቂና ወሳኝ ነገር ላይ አድርግ፤ ጠንካራ ምክንያት ከጀርባ እንደሚያስፈልግህ አስተውል። አዎ! ጀግኒት..! የምታይው ቁመና ማስተዋልን ካልታደለ፣ የማረከሽ ተክለሰውነት በእውቀት ካልተቃኘ፣ የገዛሽ ሳቅና ጫወታ ለቁብነገርም ጊዜ ካልሰጠ ለውድቀት የቀረበ ግንኙነት ውስጥ እንደሆንሽ አስተወይ። ሰውን በመልክ ሳይሆን በባህሪም ብናውቀው አውቀን አንጨርሰውም። ውጫዊ እውቀት ደግሞ የማንነቱ ማሳያ ሊሆነን አይችልም። ባየሽው አትታለይ፣ በሰማሽው አትሸወጂ፣ ውስጡን ለመመርመር፣ ማንነቱን ለማወቅ ጊዜ ውሰጂ። ጊዜ ስንዴውን ከእንድርዳዱ፣ ጥሬውን ከብስሉ የሚለይ ሁነኛ መሳሪያ ነው። ቸኩለሽ አትወሰኚ፣ ፈጥኘሽ እራስሽን አትስጪ፣ የሚቀድመውን አስቀድሚ፣ ከመልክና ቁመና በላይ ወሳኙን የማንነት ጉዳይ በጥሞና ተመልከቺ።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ንጋት ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቀኖን ያሳምሩ❤️ 🙏❤️ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/nigatethiopian ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCdQd__rYYutDdq1PBXesS-A ቴሌግራም፦ https://t.me/nigatethiopian ኢንስታግራም ፦ https://www.instagram.com/ ቲክቶክ ፡- https://www.tiktok.com/@nigatethiopia? 👍👍👍NIGAT
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...