cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የፍቅር ሳይኮሎጂ💝

የተመቻቹን አይንት ጥያቄ መጥየቅ በፍቅር ሳይኮሎጂ የፍቅር ምክር እሰጣለን ፍቅር ለርሶ ምን ማለት ነዉ እና ወራበታለን🌺 @YEFIKIR_SAYCOLOJI 40-22-0952@ ፍቅር ይበልጣል።። ማንኛውም ሀሳብና አስተያየት በዚህ @YSCCOMBOT ላኩልን። ጥያቄ ጠይቀዉ ስለሚቆይ ይታገሱ

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
701
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

እኔ እችላለሁ💪 ለራስህ እንዲህ ብለህ ንገረው አይምሮህ መሬት ነው የዘራህበትን ነው የሚያበቅለው። 1. እኔ ልዩ ነኝ! እኔ ድንቅ ነኝ! 2. እኔ እችላለሁ! 3. በጎ አሳቢ አይምሮ አለኝ! 4. የጀመርኩትን የህይወትና ጉዞ በድል እጨርሳለሁ! 5. ስኬታማም፤ ደስተኛም፤ መንፈሳዊም ነኝ! ይሄኝ ለራስህ መንገር ወይ ድምፅ አውጥተህ ማንበብ ብቻ ስሜትህን ይቀይረዋል፤ ቀንህን ስለ ድክመትህ፣ ስለ ጭንቀትህ፣ ስለ ችግርህ በማሰብ አትጀምር! ምክንያቱም ጭንቀትና ችገር ከዘራህ ጭንቀትና ችግር ነው ምታጭደው፤ አይምሮህ ውስጥ አሪፍ ነገር ዝራ ወዳጄ! ደማቅ ሰንበት ተመኘንላችሁ🙏 https://t.me/YEFIKIR_SAYCOLOJI https://t.me/YEFIKIR_SAYCOLOJI
Hammasini ko'rsatish...
የፍቅር ሳይኮሎጂ💝

የተመቻቹን አይንት ጥያቄ መጥየቅ በፍቅር ሳይኮሎጂ የፍቅር ምክር እሰጣለን ፍቅር ለርሶ ምን ማለት ነዉ እና ወራበታለን🌺 @YEFIKIR_SAYCOLOJI 40-22-0952@ ፍቅር ይበልጣል።። ማንኛውም ሀሳብና አስተያየት በዚህ @YSCCOMBOT ላኩልን። ጥያቄ ጠይቀዉ ስለሚቆይ ይታገሱ

ሲወድቅ ጊዜ ነው የጣለኝ ፤ በእርግጥ ባልመረኮዝበት ሲወድቅ አልወድቅም ነበር ፤ ነገር ግን የፍቅር አጋሬን አለመመርኮዝ ይቻለኝ ነበር ? ጠርጥሬው ጠርጥሬው እምነቴ ሲፀና እና ስመረኮዝበት ጊዜ ነው የወደቀው ። እሱ ሲወድቅ አብርዬው ባልወድቅ እንዲህ ያመኝ ነበር ? አካል ሳይወድቅ እንዴት አካል እንዲህ ይታመማል ? ! ምን አያይዞን ነው እሱ ለወደቀው እኔ መሰበሬ ፤ የትኛው እድሜ ላይ ነው እምነቴ ሲበላ የምስቀው ? በደል ሲበዛ ያጠነክራል እንጂ ያልፈሰፍሳል እንዴ ? አልገባውም በልቤ ውስጥ ለእሱ ያለኝን ቦታ ፤ ቢገባው ኖሮ ቢገፉት እንኳን እንደወዛ አይገነደስም ነበር። ለካ ባልተሳተፍንበት ነገር መስዋዕት የመሆንን ያህል ከንቱነት የለም ፤ አጋራችን በመጣበት የትናንት ጦስ ነጋችንን ማቁሰሉ አለም ግርምቢጥ ለመሆኗ ዋነኛ ምስክር ነው ። የልብ ስብራት ፊት ላይ አለመታየቱ ነው እንጂ ቢታይ አብርሃም ሰብሯታል እና ይሰበር የማይል የለም ነበር በእርግጥ በደሉ ካልጨረፈን የማያመን ፣ የማይሰማን ሆነናል ። አብርሃም እንደው መርከስ ማንነቱ ካልሆነ በቀር እንዲህ ወድቆ አይጥለኝም ነበር ! እንዲህ እላዬ ተረጋግቶ ላየኝ ውስጤ እንደሚተራመስ ማመን አይቻለውም ። ጠንካራ መሳዮች ጉዳት ደፍሮ የሚያግዛቸው ፣ የሚያበረታቸው ማጣታቸው እና እነሱም ለእገዛ ምቹ አለመሆነቸውም ጭምር ይመስለኛል ። ህመማቸውን የሚያሳዩ ብፁዓን ናቸው ቅን ሰዎች ያፅናኗችዋል እና !! አብርሽ ሳስታውሰው እንድታወክ አድርጎ እስክደገፈው ጠብቆ ወድቆ ጣለኝ ለካ መውደቅ እንዲህ ቅፅበት ናት። © Adhanom Mitiku JOIN US 🙏 @YEFIKIR_SAYCOLOJl @YEFIKIR_SAYCOLOJl @YEFIKIR_SAYCOLOJl
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የሚወድህን ሰዉ አትራቅ፡ ስለ አንተ የሚያስብህን ሰዉ እና በንፁህ ልቡ የወደደህን ሰዉ አትግፋ ምክንያቱም አንድ ቀን ሰዉ ሁሉ ፍቱን ሲያዞርብህ ያ ሰዉ ይናፍቅህ ይሆናል... Like , share and forward ለፕሮፍያል የሚሆን ጥቅስ 🤍
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ያለ ምክንያት ስለወደድኩሽ በምክንያት አልጠላሽም 💙
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ሌሎች ማድረግ የማይፈልጉትን አንተ ታደርጋለህ፤ ብዙዎች ማወቅ ያልፈለጉትን አንተ ታውቃለህ፤ ሌሎች መማር የማይፈልጉትን አንተ ትማራለህ፤ ብዙዎች ለመስራት የሚያፍሩበትን አንተ ትሰራለህ፤ እነርሱ የማይመርጡትን የተለየ ምርጫ አንተ ትመርጣለህ፤ ብዙዎች የሚጠየፉትን ስራም በኩራት ትሰራለህ። የክብርህ ማነስ ከሰዎች መለየትህ ሳይሆን ሌሎች ስለቆዩ ብቻ በማትፈልገውና በማይገልፅህ ስፍራ መቆየትህ ነው። በመንጋው መዋጥህ መኖርህን እንዳያሳጣህ ተነጥለህ መታየቱን፣ አዲስ ተግባር መተግበሩን አትፍራ። አዎ! ጀግናዬ..! እለት እለት በእራስህ ቀለም መድመቁን እወቅበት። እነርሱ ማድረግ የማይፈልጉትን ስላደረክ፣ በእርግጥም እነርሱ ያላገኙትን ነገር ታገኛለህ። አቅምህንና የሚያዋጣህን የምታውቀው አንተ እስከሆንክ ድረስ ማንም የህይወት ምርጫህን እንዲወስንልህ አትፍቀድ። ብዙዎች ባለመፈለግ ቢያፈገፍጉ አንተ ግን ከብዙዎች ተነጥለህ፣ ከጥቂጦቶች ትቀላቀላለህ፣ በእራሳቸው መንገድ ከሚጓዙት ጋር ጉዞህን ትቀጥላለህ፤ የብዙዎች ምኞት የሆነውን ህይወት አንተ ትኖረዋለህ፣ ለብዙዎች ሃሳብ የሆነውን ነገር አንተ በቀላሉ ትፈፅመዋለህ፣ ለብዙዎች ቅንጦት የሆነውንም ለእራስህ መደበኛ ታደርገዋለህ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
''ትዝ ይልሻል ያ ቀን'' ትዝ ይልሻል ያ'ቀን አውራ መንገድ ላይ በሀሳብ ተሳፍረን እንዲሁ ስናዘግም አቅላችንን ስተን በሀሳብ ሰመመን መንገድ ላይ ተጋጭተን ለመጀመሪያ ግዜ አይን ለ አይን ተያይተን ይቅርታ ይቅርታ እኩል ተባብለን ተለያይተን ስንሄድ እኩል ተሳስቀን አካላችን ሄዶ ልባችን ተጣብቆ ፍቅራችን ገና ከጅምሩ አሳብቆ አውራ መንገድ ላይ ፍቅራችን ተዘርቶ በሀሳብ ብዛት አካላችን ተጋጭቶ ፍቅር የሞላበት ቤተሰብ መስርቶ የፍቅራችን ውሀልክ ባንቺ ተገንብቶ እስካሁን ያኖረን አንድላይ አፅንቶ ትዝ ካለሽ ውዴ በዛ ቀን እኮ ነው ሳላቅሽ ሳታቂኝ ቃልኪዳን ያሰርነው!            ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄               ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️                
Hammasini ko'rsatish...
📌#ፍልስፍና_ምንድን_ነው? 👉ፍልስፍና ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ የፍልስፍና ጥያቄዎችን የሚመልስ የጥናት መስክ ነው›› በማለት በቀላልፉ ከምናልፈው፣ ሐሳቡን በደንብ ለመረዳት በመጀመሪያ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ‹‹ፍልስፍና›› የሚባለው ነገር እንዴት እንደመጣ ማየቱ የተሻለ ነው፡፡ የፍልስፍና ውልደትን እነመልከት ? #የፍልስፍና_ውልደት ? 👉ከጥንት ዘመን ጀምሮ የሰው ልጅ ስለ ራሱ ህልውናና በዙሪያው ስላሉት በአግራሞት የሚጠይቃቸው < መሰረታዊ ጥያቄዎች> ነበሩት 👉የሰው ልጅን እና በዙሪያው ያሉትን ነገሮች ማን ነው የፈጠረን? 👉ከየት ነው የመጣነውስ? እኛንና ይሄንን ዓለም የፈጠረ ኃይል ይኖር ይሆን? ካለስ እሱ የት ነው የሚኖረው? ለምን አናየውም? 👉 የዓለም ፈጣሪ ካለ ባህሪውና ሐሳቡ እንዴት ያለ ነው? ከእኛ ጋር ያለው ግንኙነትስ ምን ዓይነት ነው? 👉ለምን እንሞታለን? ሞት የመጨረሻው ነው? ወይስ ከሞት በኋላ ሌላ ህይወት አለ? 👉 የመኖር ትርጉሙ ምንድን ነው? የመጨረሻው የህይወት ግብ ምንድን ነው? 👉እንዴትስ ነው መኖር ያለብን? ከሌሎች ሰዎች ጋርስ እንዴት ነው መኖር ያለብን? 👉እነዚህ ጥያቄዎች ከአግራሞት የሚወለዱ ናቸው፡፡ ማንኛውም ሰው እነዚህን ጥያቄዎች ሊጠይቅ አይችልም፤ በነገሮች አፈጣጠርና አሰራር፣ በተፈጥሮ ሚስጥራትና ኩነቶች አድናቆት የሚያድርባቸው ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው እነዚህን ጥያቄዎች ሊጠይቁ የሚችሉት፡፡ ፍልስፍናና ሳይንስ የተወለደው ከዚህ አድናቆትና መገረም ውስጥ ነው፡፡ አሪስቶትል ‹‹ፍልስፍና የሚጀመረው በመደነቅ ነው (Philosophy begins with wonder at the mysteries of the world)>> ያለውም ለዚህ ነው፡፡ ይቀጥላል........ በቀጣይ የፍልስፍና ትርጉምን እናያለን ? ©ብሩህ አለምነህ JOIN US 🙏 @YEFIKIR_SAYCOLOJl @YEFIKIR_SAYCOLOJl @YEFIKIR_SAYCOLOJl
Hammasini ko'rsatish...
​​❤️ፍቅር 😍እና ቅናት 1💓#የፍቅር ትክክለኛ ጥልቀቱን የምትረዱት ያች የመጨረሻዋ #የመለያያ ሰዐት ስትደርስ ነው፡፡ 2❤️#የሰው ነፍሱ በሚኖርበት #ሳይሆን ባፈቀረበት ነው፡፡ 3❤️#በዓለም ላይ #ራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር ያን ካደረክ ራስህን እየሰደብክ ነው:: 4❤️#እንደማንኛውም ሰው ከሚያያችሁን ሰውጋ #በፍቅር አትውደቁ፡፡ 5❤️#ፍቅር አይደለም ዕውር፤ ዕውርስ #ቅናት ነው፡፡ 6❤️#ቀናተኛ አፍቃሪ ላለመሆን ሞክር፤ በግልፅነት ቅናትን ለማስወገድ ሞክር፤ አለበለዚያ በመጨረሻም #ደስታንም ፍቅርንም እራስህንም ታጣለህ፡፡ 7❤️#ቅናት ከፍቅር #ይበልጥ ለራስ ወዳድነት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ 8❤️ቅናት የፍቅር #መቃብር ነው፡፡ 9❤️ቅናት እና ፍቅር እህትማማች #ናቸው፡፡ 10💕እንባ ልብ ሊገልጻቸው የማይቻለው #ቃላቶች ናቸው፡፡            ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄               ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️               @YEFIKIR_SAYCOLOJl @YEFIKIR_SAYCOLOJl @YEFIKIR_SAYCOLOJl
Hammasini ko'rsatish...
... ስፍራህ የሚሰጥህ ነው! ፨፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨፨ ለእነርሱ በቂ የሆነው ምክንያት አንተ ስትሰማው ሊቀየር አይችልምና ካልነገሩህ ለምን ብለህ አትጠይቃቸው፤ ካላካተቱህ እንዴት ብለህ ግራ አትጋባ፤ ካልጋበዙህ በፍፁም አትሒድ፤ ካገለሉህ እንዴት ብለህ አትጠይቃቸው። በህይወታቸው ቦታ እንዳለህ የምታውቀው አንተ ጠይቀህ ሳይሆን እነርሱ የሚያደርጉትን አይተህ ነው። ጊዜ አላፊና አላቂ ነው፤ አቅም የሚባክንና የሚሸረሸር ነው፤ ስሜት የሚዋዠቅና የሚወድቅ ነው። ያለአግባብ፣ ያለምክንያት በማይሆን ሰው፣ በማይሆን ስፍራ የሚባክን ነገር ደግሞ ያማል፤ አንጀት ይበላል፤ ያሳዝናል፤ ይቆጫል። እናም ካላጠበከው ሰው ያልጠበከው ነገር ቢገጥምህ እንኳን ብዙ አትገረም፣ ብዙ አትደነቅ፤ ግር አትጋባ፤ ይልቅ እውነተኛውን ቦታህን ለማወቅ ተጠቀመው። አዎ! ጀግናዬ..! በሰዎች ህይወት ውስጥ ያለህ ስፍራህ የምትጠይቀው ሳይሆን የሚሰጥህ ነው። ምናልባት ካልጠየክ የማታገኘው ስፍራ ሊኖር ይችላል አንተን የፈለገ፣ እገዛህን የሚሻ ሰው ግን ጥያቄህን አይፈልግም፤ አይጠብቅም። ሰው ፈልጎ ሊረሳህ ይችላል፤ አውቆ ሊዘነጋህ ይችላል፤ አስቦበት ሊያስቀርህ፣ ከህብረቱም ሊያስወጣህ ይችላል። ሁን ተብሎ በተፈፀመብህ ተግባር በእራስህ ላይ ጥያቄ አታዝንብ፤ ማናቸውም ያድርጉት ማናቸው ሃሳባቸውን ተቀብለህ ማንነትህን አሳይ፤ አንተን ባለማካተታቸው እራሳቸውን እንዲወቅሱ አድርግ፤ መዳብ የመሰለ እንቁ እንዳንጡ አሳያቸው፤ ክብርህን ጠብቀህ እራስህን አስከብር። መግፋታቸው እሾህ ሆኖ እስኪወጋቸው በእራስህ ማማ መታየትህን አታቁም። ተሽለህ ተገኝ፤ ደምቀህ ታያቸው። መሪ ተዋናይ መሆን በነበረብህ ፊልም ውስጥ ለምን ረዳት እንኳን አልሆንኩም በማለት አተከራ ውስጥ አትግባ፤ ጊዜህን አታባክን። ቦታህን እወቅ፤ ክብርህን ጠብቅ። ታግለህ የምታገኘው የሰው ትኩረት፣ በግዴታ የምትገዛው የሰው ልቦና እንደሌለ እወቅ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ @YEFIKIR_SAYCOLOJl @YEFIKIR_SAYCOLOJl
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.