Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ያካሄዱት ውይይት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ያካሄዱት ውይይት #PMAbiy #AbiyAhmed #…
See more
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከፌደራል ተቋማት የሰው ሃብት የስራ ክፍል ሃላፊዎች ጋር በፋይዳ ስርዓት ዙርያ ውይይት ተደረገ ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት ከከተማ አስተዳደሩ እና በፌደራል የመንግስት የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት አስተዳደር የስራ ክፍል ሃላፊዎች ጋር በፋይዳ ምዝገባ ዙርያ ላይ ውይይት አድርገዋል።
በእለቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንዲሁም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር ተገኝተዋል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በፋይዳ ምዝገባ ላይ የመንግስት ሠራተኛው ሚናውን በተገቢው እንዲወጣ እንዲሁም ስርዓቱ የሃገራችንን የፐብሊክ ሰርቪስ ዘርፍ ለማዘመን ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅዖ በመገንዘብ የአስፈፃሚነት ድርሻቸውን የስራ ክፍል መሪዎቹ እንዲወጡ በንግግራቸው አፅንዖት ሰጥተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ ለውይይት መነሻ የሚሆን ገለፃ በፋይዳ ስርዓት እና የሃገሪቱን የፐብሊክ ሰርቪስ ለማዘመን እየተተገበረ ካለው የዲጂታል ስርዓት ጋር የሚኖረውን መስተጋብር የሚዳስስ ሰነድ የቀረበ ሲሆን ገለፃውን መነሻ በማድረግ በተነሱ ሃሳቦች ላይ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ስራ-አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል እና የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ምላሽና ማብራርያ ሰጥተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የንግዱን ማህበረሰብ እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ባወያየንበት ወቅት በቀረቡልን ጥያቄዎች መሰረት መልስ እየሰጠን እንገኛለን ።
አዲስ አባባ ቀን ብቻ ሳይሆን ሌሊትም የሚሰራባት ከተማ እየሆነች ነው ።
ዛሬ ለአዲስና ለማስፋፊያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለሚቀርቡ የመስሪያ ቦታ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በገባነው ቃል መሰረት ግልፅ መስፈርት አዉጥተን በመስፈርቱ ቅድሚያ ለሚገባቸዉ አምራቾች ኢንዱስትሪዎች ቁልፍ ርክክብ አድርገናል ::
የመስሪያ ቦታ ቁልፍ የተረከባችሁ አርዓያ የሚሆን ስራ ሰርታችሁ ምርታማነትን በመጨመር እና የስራ እድል በመፍጠር ገበያን ማረጋጋት ይጠበቅባችኋል ፡፡
ያለንን መሬትና የሰው ሃይል ተጠቅመን በእልህ ስኬታማ እንሁን ፤ አምራቾችም ትልቅ ህልም ኖሯችሁ ዉጤታማ ሥራ ከእናንተ ይጠበቃል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሰው ሕይወት እንደዋዛ የሚቀጥፈው የከሰል ጭስ
*******
ወቅቱ የክረምት ነው። በልማድ ደግሞ ብርዱን ለመከላከል በርካቶች ቤታቸው ውስጥ ከሰል አቀጣጥለው መሞቅና በከሰል ምግብ ማብሰልን ያዘወትራሉ።
ይህ ልማድ ግን ጥንቃቄ ካልታከለበት ብዙዎችን ለአደጋ ሲያጋልጥ ተስተውሏል። ከሰልን በቤት ውስጥ በአግባቡ ካልተጠቀምን ለከፍተኛ የመተንፈሻ አካል በሽታና ለሞት እንደሚዳርግ የሕክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
በአግባቡ ጭሱ ያልወጣለት ከሰል ካርቦን ሞኖኦክሳይድ የተባለ መርዛማ ጋዝ ያመነጫል። ይህ መርዛማ ጋዝ ደግሞ በዓይን የማይታይና ሽታ አልባ ነው።
ከሰል፣ ኩበትም ይሁን ሌሎች በነዳጅ የሚሰሩ ምድጃዎች ይህን ጋዝ ሊያመነጩ ይችላሉ። ታዲያ ምግብ የሚያበስሉበት ቦታ ጠባብ እና በቂ የአየር ዝውውር የሌለው ከሆነ ጋዙ በክፍሉ ውስጥ ይጠራቀምና ለከፍተኛ አደጋ ያጋልጣል።
በካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝን የሚያመለክቱ የተለመዱ የሕመም ምልክቶችም ራስ ምታት፣ መደካከም፣ ማዞር/ማጥወልወል፣ ማቅለሽለሽና ማስታወክ፣ የደረት ሕመም፣ የትንፋሽ ማጠር፣ መዝለፍለፍ፣ የእይታ ብዥ ማለት እንዲሁም ራስን መሳት እንደሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ያናገራሉ።
የከሰል ጭስን እንዴት መከላከል ይቻላል?
የሕክምና ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት፤ በከሰል ምግብ ማብሰል ሲያስፈልግ በቂ አየር ባለበት ከተቻለም ከቤት ውጭ ማብሰል፤ ከቤት ውጭ ማብሰል ካልተቻለ ደግሞ ሙሉ በመሉ መቀጣጠሉና ጭሱ ማለቁ ሲረጋገጥ ወደ ቤት ማስገባት ይመከራል።
በተጨማሪም ከሰልን ቤት ውስጥ አለማቀጣጠል፣ የከሰል ምድጃ ሲጠቀሙ በር እና መስኮትን ክፍት ማድረግ፣ በከሰል ምግብ አብስለው ሲጨርሱ ደግሞ በውኃ ማጥፋትና በርና መስኮት በመክፈት ቤቱን ማናፈስ እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ።
Ethiopian Broadcasting Corporation
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ያካሄዱትን ውይይት ዛሬ ምሽት ሰኔ 12 በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ከምሽቱ 2:30 ላይ ይከታተሉ።
#PMOEthiopia
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በቀጣይ 90 ቀናት በሚተገበሩ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች እቅድ ትግበራ ዙሪያ ከሚመለከታቸው የከተማ ሴክተር ተቋማት እና የክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር በልዩ ትኩረት በሚፈፀሙ አቅጣጫዎች ላይ በም/ ከንቲባ ማእረግ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ጋር የተካሄደው ውይይት በምስል ሲቃኝ:-
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በቦሌ ክፍለ ከተማ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ የኅብረተሰብ ተሳትፎ እና የበጎ ፍቃድ ሥራዎች የ90 ቀናት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡
ከሰኔ 5 እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ተግባራዊ በሚደረገው የ90 ቀናት ዕቅድ በኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት፣ በመሠረተ ልማት፣ በጽዳት፣ በአደጋ መከላከል፣ በከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት እንዲሁም ሌሎች መስኮች በርካታ ሥራዎችን ለማከናወን የታቀደ መሆኑ በመድረኩ ላይ የተገለጸ ሲሆን፣ እነዚህን ተግባራት ለማከናወን የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ አቶ ደመቀ ዋኘው አመልክተዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌትነት ዓይናለም የ90 ቀናት ዕቅዱ በሁሉም መስኮች በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ኅብረተሰቡንና አጋር አካላትን በማስተባበር ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን የታለመ መሆኑን አውስተው፣ ለዕቅዱ ተፈጻሚነት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡ መድረኩ ባለድርሻ አካላት በዕቅዱ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ለአፈጻጸሙ ውጤታማነት የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት እንደሆነ ያመለከቱት ኃላፊው፣ በየደረጃው የሚገኙ አካላትም ዕቅዱን በመተግበር የበኩላቸውን ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባቸው አክለው አሳስበዋል፡፡
Bole Communication- ቦሌ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymana
የፒያሳ መልሶ ማልማት ሲጠናቀቅ ፤ አራዳ መጥተዉ የሚያጡት ምንም ነገር አይኖርም ሰፊ የስራ እድል ፣ ሁሉንም አይነት ግብይት፣ ታሪክ እና መዝናናት ..በቅርቡ ይጠብቁን !
Deebisanii misoomsuun Piyaassaa, Araadaa dhufanii wanti dhaban homaa hin jiraatu.Carraa hojii bal'aa,gabaa akaakuu hundaa,seenaa fi bashannana....yeroo dhihootti nu eegaa!
See less
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተጠኑ ጥናቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደው የዉይይት መድረክ በምስል:-
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልገሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተጠኑ ጥናቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የዉይይት መድረክ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በውጤታማነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሚረዱ እና የአሰራር ስርአትን ለማጠናከር የሚያግዙ በበጀት አመቱ ያከናወናቸዉን አራት ጥናቶች ላይ ከሚመለከታቸዉ ባለድረሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ የዉይይት መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩም በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደስ እንደተናናገሩት በጽ/ ቤቱ በበጀት አመቱ እንዲካሄዱ የተደረጉት ጥናቶች የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣን፣ ቀልጣፋና የዘመነ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው መሆኑን ጠቅሰዉ በዚህ ረገድ አራቱም ጥናትቶች ላይ ግብአት ለማሰባሰብ የተዘጋጀው የባለድርሻ አካላት መድረክ በቀጣይ ወደ ተግባር ለመግባት አቅም የሚፈጥር እንደሆነ ገልጸዋል።
በዚሁ ወቅት ጽ/ቤቱ የከተማውን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በበላይነት የመምራት፣ የማስተባበር፣ የመደገፍና የመከታተል ተልእኮውን በአግባቡ ለመወጣት በተጠሪ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ለማዘመንና የሚሰጡ አገልግሎቶችን የህብረተሰቡን እርካታ መጠን ለማረጋገጥ እንዲሁም ውጤታማነትን በጥናትና ምርምር ላይ ተመስርቶ በመፈተሽ የተገልጋዩን እርካታን ለማረጋገጥና ተግባረዊ ለማድረግ አቅምን የሚያጎለብቱ እንዲሁም ዉጤታማ አሰራሮችን ለመዘርጋት፣ መፍትሄም አመላካች ጥናቶች መካሄዳቸው ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንመሆኑንም አስገንዝበዋል።
አክለውም በጥናቶቹ ላይ የተሰጠዉ ሀሳብ በመዲናችን ባሉት ተቋማቶቻችን ከህብረተሰቡ የሚኑሱ አንዳንድ ቅሬታዎችን እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ ክፍቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ አቅም ነዉ ሲሉ ገልፀው የተነሱ ሀሳቦችን እንደግብአት በመዉሰድ እና ጥናቱ ከጥናትነት አልፎ መፍተሔ ሰጪ እንዲሆኑ በትኩረት በመስራት ወደ ተግባር ማስገባት ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል።
በዚሁ መድረክ በከተማ በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በውስጥ አቅም ተጠንተው ግብአት ለማሰባሰብ የቀረቡ ጥናቶች "የተጠሪ ተቋማት የሪፎርም ስራ አፈፃፀም፣በተጠሪ ተቋማት ለ3ኛ አካል(outsourcing) የተሰጡ የማዘጋጃ ቤታዊአገልግሎቶች አፈፃፀምና ቀጣይ ዳሰሳ ጥናት፣የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በ3ኛ አካል የተጠኑ ጥናቶች አተገባበር፣በተጠሪ ተቋማት የቅንጅታዊ አሰራር" ላይ የተካሄዱ ጥናቶች ቀርበዋል።
በግብዓት ማሰባሰቡ መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤቴዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣የተቋማት ተወካዮች፣የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጆች፣ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በየደረጃው ያሉ የተጠሪ ተቋማት ተወካዮች አመራሮች፣ዳይሬክተሮች፣ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
