Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
የቅድመ አደጋ ጥንቃቄ መልእክት..
በሠው ልጅ ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ከሚያደርሱት አደጋዎች አብዛኞቹ በጥንቃቄ ጉድለት የሚከሰቱ ናቸው።
በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ለመከላከል አለመቻል፤ የአካልና የንብረት ጉዳት ያስከትላል! ለሞት ሊዳርግም ይችላል!
ቅድሚያ ለደህንነትዎ በመስጠት የኤሌክትሪክ አደጋን ይከላከሉ!ለህይወት መጥፋት እና ንብረት መውደም ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉ የአሰራር እና አጠቃቀም ግድፈቶችን በማስወገድ ህይወትን እና ንብረትን ይታደጉ።
በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰሩ የተለያዩ መሳሪያዎች እና መሰኪያዎችን በአንድ ሶኬት ላይ ደራርበው ለረጅም ሰዓታት ከመጠቀም ይቆጠቡ።
የኤሌክትሪክ እሳት ቢነሳ ሀይሉን ከምንጩ ሳያቋርጡ በውሃ ለማጥፋት አይሞክሩ::
ልብ ይበሉ! የኤሌክትሪክ መስመር ሲበጠስ፣ ምሰሶ ሲወድቅ በእንጨት ወይም በብረት ለማንሳት መሞከር ከፍተኛ ጉዳት ስለሚያስከትል፤ ይህንን ከማድረግ ይቆጠቡ!
ለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ድንኳን ለመትከል ሲሉ ብረቱን ከኤሌክትሪክ ምሰሶና ሽቦ ጋር አያገናኙ!
በቤት ውስጥ የሚከናወን ማንኛውንም የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፤ በባለሙያ ብቻ ያከናውኑ!
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የመዲናዋ የኮሪደር ልማት ከከተማ ልማት ባለፈ ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ ተጋላጭ የነበሩ ዜጎችን የታደገ ነው
የመዲናዋ የኮሪደር ልማት ከከተማ ልማት ባለፈ ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ ተጋላጭ የነበሩ ዜጎችን የታደገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡
ኮሚሽኑ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን አስቀድሞ የመከላከል እና ከተከሰተም ፈጣን ምላሽ የመስጠት ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
በኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ወልደመስቀል፤ የእሳት ቃጠሎ፣ የመኪና አደጋ፣ የግንባታ መደርመስ፣ የመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ በመዲናዋ ከሚከሰቱ አደጋዎች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለዚህ ደግሞ የቤቶች ግንባታ ጥግግት፣ የመንገዶች ጥበት፣ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመዶች መደራረብ እና የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች መደፈን በምክንያትነት ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት በመዲናዋ በተለያዩ አደጋዎች የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 467 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ጠቅሰዋል።
በመሆኑም በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የመንገድ ኮሪደር ልማት ከከተማ ልማትም ባለፈ ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ ተጋላጭ የነበሩ ዜጎችን ከችግር የታደገ መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማቱ እና የመልሶ ግንባታ ስራው የአዲስ አበባን ገጽታ የሚያሳምርና የሚያጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተለይም የኮሪደር ልማት መርሃ ግብሩ ቤቶች በፕላን እንዲገነቡ፣ መንገዶች እንዲሰፉ፣ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች በጥራት እንዲሰሩ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
በርካታ አካባቢዎችን ከእሳት ቃጠሎ፣ ከጎርፍ መጥለቅለቅ፣ ከትራፊክ መጨናነቅና ሌሎች አደጋዎች የታደገ ሁነኛ መፍትሄ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የኮሪደር ልማቱ የአዲስ አበባን ታላቅነት የሚመጥን ስራ ለመስራትና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የተጀመረ የመልሶ ግንባታ ስራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
#ኢዜአ
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአግባቡ የተያዘ " ቆሻሻ ሃብት ነው " ስንል መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ገቢ ይፈጥራል ማለታችን ነው::ለመሆኑ ምን አይነት ቆሻሻዎችን ነው መልሶ ጥቅም ላይማዋል የሚቻለው?ለሚለው:-
• ብርጭቆ፡ ብርጭቆ ሙሉ በሙሉ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ቁሳቁስ ነው። ከጠርሙሶች፣መስኮቶች እና የብርጭቆ ዕቃዎች መስታወት ተመልሶ ወደ አዲስ መስታወት ሊቀየር ይችላል።
• ወረቀት እና ካርቶን፡- ወረቀት እና ካርቶን ወደ አዲስ የወረቀት ምርቶች እንደ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች እና የካርቶን ሳጥኖች ሊሠሩ ይችላሉ። ስለዚህ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ሳጥኖችን እና ወረቀቶችን እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል ይበረታታል.
• ፕላስቲክ፡- እንደ ፕላስቲክ የውሃ ጠርሙሶች፣ የመገበያያ ከረጢቶች እና ሌሎች የፕላስቲክ ማሸጊያዎች ያሉ ሊመለሱ የሚችሉ ብዙ የፕላስቲክ ዓይነቶች አሉ። ፕላስቲክ ተመልሶ ወደ አዲስ የፕላስቲክ ምርቶች ሊለወጥ ይችላል.
• ብረቶች፡- እንደ አሉሚኒየም፣ ብረት እና ብረት ያሉ ብረቶችን ከቆሻሻ ማገገሚያ እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል ሂደት ውስጥ ጠቃሚ እርምጃ ነው። ብረቶች ሊመለሱ እና ወደ አዲስ የማዕድን ምርቶች ሊቀየሩ ይችላሉ.
• ጎማዎች፡ ያገለገሉ ጎማዎች እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ እና እንደ የጎማ ወለል፣ ቱቦዎች እና የጎማ ጥበብ ያሉ አዳዲስ ምርቶችን ለማምረት ይችላሉ።
• ጨርቃጨርቅ፡- አንዳንድ የልብስና የጨርቃጨርቅ ዓይነቶችን መልሰው እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል እንደ የቤት ዕቃዎች እና እንደገና ጥቅም ላይ የዋሉ ጨርቆችን ለማምረት ይችላሉ።
• ባትሪዎች እና ኤሌክትሮኒክስ፡- ባትሪዎችን እና ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችም የድጋሚ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸው::
• ማዳበሪያ፡- ማዳበሪያ ተመልሶ ሊወጣና ወደ ኦርጋኒክ ማዳበሪያነት ሊለወጥ የሚችል ኦርጋኒክ ተረፈ ምርት ሊሆን ይችላል።
• ሊበላሹ የሚችሉ ቁሶች፡- እነዚህ ምግብ፣ የጓሮ አትክልት ቆሻሻ እና ሊበላሹ የሚችሉ እፅዋትን ያካትታሉ። ኦርጋኒክ ማዳበሪያን ለማምረት በኦርጋኒክ መበስበስ ሂደት ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ.
ቆሻሻን እንደገና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል አካባቢን ለመጠበቅ እና የተፈጥሮ ሀብቶችን ፍጆታ ለመቀነስ አስተዋፅኦ ያለው ጠቃሚ ሂደት መሆኑን ልብ ሊባል ይገባል. ስለዚህ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቆሻሻዎችን በማሰባሰብ እና በመለየት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ መደገፍ እና መበረታታት አለበት::
ሳምንታዊው የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚከናወነው ብሎክን መሠረት ያደረገው ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች የተካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ሾላ ገበያ በግ ተራው አካባቢ በድምቀት ተካሂዷል።
"እኔ አካባቢዬን ያለማንም ቀስቃሽ አፀዳለሁ እናንተስ!" በሚል መሪቃል ነው የተካሄደው።
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ቢሻው ግርማ በወረዳው 20 የሚሆኑ ብሎኮች መኖራቸውን ጠቁመው ከእነዚህም ወስጥ 18ቱን በፅዳታቸውና በውበታቸው ሞዴል ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።
አክለውም ስራ አስፈፃሚው አካባቢን ከማፅዳት ጎን ለጎን ቆሻሻን ወደ ሀብትነት ለመለወጥ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አሳስበዋል።
የየካ ክ/ከተማ ዋና አፈጉባኤ አቶ ብስራት ማጆሬ በበኩላቸው የአንድ ከተማ ዕድገትና ሰልጣኔ መገለጫ ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ፅዳትና ውበት መሆኑን ገልፀዋል። የከተማችንን ፅዳት ለመጠበቅ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት መድቦ እየሰራ ነው ለዚህ ደግሞ ሁላችንም ለከተማችን ፅዳትና ውበት በጋራ መስራት አለብን ብለዋል።
በፅዳት ስራው ላይም አመራሮችን ጨምሮ የፅዳት አምባሳደሮች : የፀጥታ አካላት : ወጣቶችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በፅዳት ስራችን፣ በምክክራችን በአብሮነታችን ትውልድን እንቀርፃለን" በሚል መልዕክት ሳምንታዊ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ መርሃ-ግብር ተካሄደ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር በዛሬው ዕለት የፅዳት ዘመቻ መርሃ-ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሄዷል።
በመርሃ-ግብሩ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገቡ ይስማውን ጨምሮ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች፤ የሀይማኖት አባቶች፤ እንዲሁም የወረዳው ነዋሪዎች እና የብሎክ አደረጃጀቶች ተሳትፈዋል።
በፅዳት ዘመቻው መርሃ-ግብር የወረዳ 2 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መለሰ ዋሴ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የአካባቢና የግል ንፅህና መጠበቅ ቀዳሚ ተግባር መሆን እንደሚገባ ጠቁመው፤ በወረዳው የተጀመረውን የፅዳት ንቅናቄ ተግባርም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የክ/ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መዝገቡ ይስማው በበኩላቸው የፅዳት ተግባር ከክረምት እስከ በጋ በየጊዜው የሚካሄድና አካባቢያችንን የማስዋብና የተዘጉ የውሃ መውረጃ ቱቦዎችንም የመክፈት ተግባር እንደሚጨምር ገልፀው፤ መሬት ስትፈጠር ንፁህ እና ውብ እንደነበረች ይህንን ንፅህናና ውበት በማስጠበቅ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ማፍራት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የከተማ ሥራ አስኪያጅ ጵህፈት ቤት ለሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሠራተኞች ስልጠና ሰጠ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ለሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ከማእከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ አጠቃላይ ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ
የሰልጠናው አላማም በአገልግሎት ስታንዳርድ ፣በቅንጅታው አስራር፣ በህትመት ስርጭትና ቁጥጥር ፣በአመለካከት ግንባታ እንዲሁም ተቋሙን በቅንጅታዊ አሰራር ለማሻሻል የሚሰችል አቅም መፍጠር እንደሆነ ተገልፆአል::
ሰልጠናው በ9 ዙር ለ1764 ሰልጠኞች
የሚሰጥ ሲሆን የአሁኑ ሰልጣኞች ለ5ኛው ዙር ሰልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
ለሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተጠሪነቱ ለከተማ ሥራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት መሆኑ ይታወቃል::
በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አገልግሎት አሰጣጡን ምቹ ለማድረግ እየተከናወነ ያለው ጥረት መሻሻል የታየበት እንደሆነ የተለያዩ ክ/ከተሞች ተገልጋዮች ገለፁ::
የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች በአዲስ ከተማ:-በቂርቆስና በአራዳ ክ/ ከተሞች ባሉ 6 ወረዳዎች ከተገልጋዮች ጋር በኤጀንሲው የተካሄደው ሪፎርም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያመጣውን ለውጥ አስመልክቶ ቃለ ሞልልስ አካሂደዋል::
በዚህም በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 13 እና ወረዳ 6 በቂርቆስ ክ/ከተማ ደግሞ ወረዳ 4 እና 5 አገልግሎት ሲያገኙ ከነበሩ ነዋሪዎች አንዳንዶች እንደገለጹት የቢሮ አደረጃጀትና ዘመናዊ የአሰራር ሰልቱ ለአገልግሎት አሰጣጥ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልጸው፤ በተለይ ሰራተኞች የሚያሳዩት ትህትና ምስጋና የሚገባው ነው ብለዋል።
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ፅ/ቤት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ተገልጋዮች ደግሞ የዲጂታል ወረፋ ማስጠበቂያ ስርአት ከመኖሩ ጀምሮ አገልግሎቱም በቴክኖሎጅ የታገዘ መሆኑ ተገልጋዮችን ከእንግልት ከመታደጉ በተጨማሪ ግልፅነት የተሞላበት አሰራር መዘርጋቱም አበረታች ለውጥ የታየበት እንደሆነ ገልፀዋል::
ውድ ተገልጋዮቻችን
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እየጨመረ የመጣውን የዲጂታል አገልግሎት ፍላጎት ለማሟላት የመረጃ ቋታችን የመረጃ ማከማቻ ማሻሻያ / Storage Upgrading / ለተከታታይ 54 ሰዓታት የሚያደርግ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎታችን ከዛሬ መጋቢት 20 ከረፋዱ 5:00 ጀምሮ እስከ እሁድ ሙሉ ለሙሉ የሚቋረጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ማሻሻያው ለዲጂታል አገልግሎታችን ቅልጥፍና ታስቦ እየተደረገ ያለ በመሆኑ በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እየጠየቅን ሰኞ መጋቢት 23 ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት የሚጀመር መሆኑን እንገልፃለን።
ውድ ተገልጋዮቻችን
* በዋና መስርያ ቤት እና ቅርንጫፍ ለሚሰጡ የማስረጃ ማረጋገጥ፣
* በወረዳ ጽ/ቤት የሚሰጡ የዲጂታል መታወቂያ ስርጭት ፣ በድብዳቤ የሚሰጡ እና ተያያዥ አገልግሎቶች እንዲሁም
* በጤና ተቋም የአንድ ማዕከል የልደት እና ሞት ምዝገባ አገልግሎትን መገልገል ለምትፈልጉ ቅዳሜን ጨምሮ ኤጀንሲያችን ለአገልግሎት ክፍት የሆነ መሆኑን እናሳውቃለን።
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የስነምግባር እና የፀረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ስልጠና ሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የስነምግባርና የፀረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ለጽ/ቤቱ ዳይሬክተሮች፣ለባለሙያዎች፣ለሰራተኞች የስነ ምግባር እና የመልካም አስተዳደር ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ መሰረታዊ የስነምግባር ምንነት፣የስነ ምግባር መርሆች፣የመልካም አስተዳደር ምንነት፣የመልካም አስተዳደር መርሆች በእነዚህ እና በሌሎች ርዕሶች ለሰልጣኞች እዉቀት ለማስጨበጥ የታለመ ነው።
በስልጠናው ላይ ሁሉም የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እና ዳይሬክተሮች ስልጠናዉ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን ስልጠናዉ ለሰልጣኞች በቂ እዉቅት እንደሚያሲዛቸዉ በስልጠናዉ ላይ ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የስራ የአቅም ማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የሰዉ ሀብት አስተዳደር ለዳይሬክተሮች፣ለባለሙያዎች፣ለሰራተኞች በፐብሊክ ሰርቪስ አዋጅና መመሪያ በተመለከተ የስራ ላይ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ መሰረታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሰራተኞች መመሪያ ደንብ፣አዋጅ፣መመሪያዎችን በእነዚህ እና በሌሎች ርዕሶች ለሰልጣኞች ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና በስራ ላይ ብቁ ባለሙያ ለማብቃት የታለመ ነው።
በስልጠናው ላይ ሁሉም የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እና ዳይሬክተሮች ስልጠናዉ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን ስልጠናዉ ሰልጣኞች የጎላ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ለግንዛቤዎ....
ደረቅ ቆሻሻ ከዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴያችን ጋር የተያያዘ የሰው ልጅ ፍላጎትን ከማሟላትና ከመጠቀም ጋር በቅርብ የተቆራኘና በዚህም ሳቢያ የሚፈጠር ነው፡፡
ሰዎች ለዕለት ፍጆታቸው የሚጠቀሙባቸው ምግቦች ማሸግያዎች፣ የዕቃ መጠቅለያዎች፣ ቁርጥራጭ ወረቀቶች፣ የውሃ ማሸጊያ ኘላስቲኮች፣ ተረፈ ምርቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና በአጠቃላይ አገልግሎት ሰጥተው ያበቁ አልባሳትን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶች በደረቅ ቆሻሻ ውስጥ ይመደባሉ፡፡
እነኚህ ቁሳቁሶች በአግባቡ ካልተወገዱ አካባቢን በመበከል በሰውም ሆነ በእንሰሳት ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡ በአግባቡ ከተከማቹና ከተያዙ ደግሞ መልሰው ጥቅም ላይ ሊውሉ ከመቻላቸውም በላይ ሀብት ሆነው ለሌሎች ወገኖች የስራ ዕድል መፍጠር ያስችላሉ፡፡
ደረቅ ቆሻሻ ከሚመነጭባቸው መንገዶች ውስጥ ከመኖሪያ ቤት፣ ከተቋማት፣ ከፋብሪካዎች፣ ከመንገድ ዳርቻዎች ፣ ከግንባታ ፍርስራሾች፣ ከህክምና ተቋማት ከግብርና እና ከኤሌክትሮኒክስ ወዘተ ከመሳሰሉት ሊመነጭ ይችላል፡፡ በአብዛኛው የሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ ግን ከመኖርያ ቤቶች ነው፡፡
ደረቅ ቆሻሻ በሶስት ይከፈላል
እነሱም፡-
1. የሚበሰብስ ቆሻሻ (Organic waste)
2. የማይበሰብስ ቆሻሻ (Non organic waste)
3. አደገኛ ቆሻሻ (Hazardous)
የሚበሰብስ ቆሻሻ ( Organic waste)
የሚበሰብስ ደረቅ ቆሻሻ ማለት የደረቅ ቆሻሻ ዓይነት ሆኖ በቀላሉ ሊበሰብስ የሚችሉ በአግባቡ ከተጠቀምንበት ቀልዝ (ኮምፖስት) ለመስራት የሚያገለግል ነው፡፡
ቆሻሻ በማለት ከምናስወግደው ከሚበሰብሱ ቆሻሻዎች ውስጥ ለምሳሌ የሽንኩርት ልጣጭ፣ የድንች ልጣጭ፣ የሙዝ ልጣጭ ወዘተ የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡
የማይበሰብስ ቆሻሻ (Non organic waste)
የማይበሰብሱ ደረቅ ቆሻሻዎች ማለት በቀላሉ ሊበሰብሱ የማይችሉ የቆሻሻ ዓይነቶች ማለት ሲሆን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው መልሶ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ናቸው፡- ለምሳሌ ብረታ ብረት ፣ ኘላስቲክ፣ ሀይላንድ ፣ ሚስማር ወዘተ የመሳሰሉትን ይይዛል፡፡
አደገኛ ቆሻሻ (Hazardous Waste)
አደገኛ ቆሻሻ የሚባሉት በአግባቡ ባለመያዛቸው እጽዋትን፣ እንስሳትን፣ ሰውን፣ አፈርን፣ አየርን፣ ውሃን የሚመርዙ በረዥምም ሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳት የሚያስከትሉ በአካባቢ ውስጥ ሳይሰባበሩ እና ሳይበሰብሱ ወይም ሳይሟሙ የሚቆዩ መርዛም ኬሚካሎች፣ ፈንጂዎች፣ ተቀጣጣይ መርዛማ የሆኑ በቀላሉ የመትነን ባህሪ ያላቸው ሬዲዮ አክቲቭ የሆኑና ከህክምና ተቋማት የሚወገዱ ቆሻሻዎችን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው ፡፡
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በአብዛኛው አካባቢዎች ዳግም ወደ ቦታው ተመልሷል
ዛሬ ከቀኑ 9:46 ጀምሮ የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አዲስ አበባን ጨምሮ በአብዛኛው አካባቢዎች ተመልሶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በዚህም ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት ስለጠበቃችሁ ምስጋና እያቀረብን፤ በቀሪ አካባቢዎችም አገልግሎቱን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ዳር መብራት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው::
ጥናቱ እየተካሄደ ያለው በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አስተባባሪነት ከአዲስ አበባ ኤሌክትሪክሪክ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል እና ከከተማው የመንገዶች ባለስልጣን በተውጣጡ ባለሙያዎች ነው::
የጥናት ውጤቱ በዛሬው እለት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እና የተቋሙ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተገኙበት ቀርቧል::
ለመንገድ ዳር መብራት ችግሮቹ ዙሪያ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየተካሄደ ያለው ይህ ጥናት ከአደረጃጀት:- ከህግ ማእቀፍ ከስታንደርድ ከጥገናና ከማልማት ስራዎች ጋር ተያይዞ አማራጭ ምክረ ሃሳቦች የቀረቡበት አንደሆነ ተመላክቷል::
በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተግባራዊ የተደረገው ተቋማዊ ሪፎርም የተገልጋዮችን እርካታ በማረጋገጥ ረገድ መሻሻል እንዳሳየና ለውጥ የመጣበት እንደሆነ የተለያዩ ክ/ከተሞች ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ::
የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ሰሞኑን በየክ/ከተሞች ባሉ ወረዳዎች ሪፎርሙ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያመጣውን ለውጥ አስመልክቶ ቦታው ላይ ተገኝተው የመስክ ምልከታ በማድረግ ከተገልጋዮች ጋር ቃለ ሞልልስ አካሂደዋል::
በተለይም በአቃቂ:በንፋስ ስልክ ላፍቶና በልደታ ክ/ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ላይ አገልግሎት ሲያገኙ ከነበሩ ነዋሪዎች አንዳንዶች እንደገለጹት በወረዳቸው በቴክኖሎጅ ታግዞ እየተሰጡ ያሉ የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች በፊት ከነበረው በተሻለ ፍጥነትና ቅልጥፍና አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን አመልክተዋል ፡፡
በላፍቶ ወረዳ 11 የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ፅ/ቤት ላይ ወሳኝ ኩነት አገልግሎት ለማግኘት በፅ/ ቤቱ የነበሩ ተገልጋዮች እንደገለፁት የቢሮ አደረጃጅቱ ለተገልጋይ ምቹና አስፈላጊው ቴክኖሎጅ የተዘረጋለት መሆኑ: አመራሩና ባለሙያዎቹም የተገልጋዮችን ችግር የሚፈታ ጠንካራ አሰራር መፍጠራቸው ለመጣው የአገልግሎት መሻሻል ተጠቃሽ መሆኑን ገልፀዋል::
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7ና በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ፅ/ቤት ካሉ ተገልጋዮች ከተገኘው አስተያየት መረዳት እንደተቻለው ደግሞ በጤና ጣቢያዎች የሁነት ምዘገባ ተግባራዊ መደረጉ:የወረፋ ማስጠበቂያ ስርአቱና መሰተንግዶው: እንዲሁም የሚሰጡ አገልግሎቶችንና ሊሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አስመልክቶ የጠዋት ገለፃ ለባለጉዳዮች የሚሰጥበት አሰራር መኖሩ ግልፅነትን በመፍጠርና ተገቢውን አገልግሎት በፍጥነት ለመስጠት በማስቻል ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል::
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ሥራ ሂደት ገምግመናል። ቀዳሚ አላማችን አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ኑሮ የተመቸች ሳቢ ከተማ ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት ማሳካት ነው። የማልማት ሥራ ሂደቱ በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚና በመንግሥት ብሎም አነስተኛ ገቢ ባላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እና የተለያዩ አካላት የተያዙና የተከራዩ ንብረቶችን የነካ ሊሆን ቢችልም ይህ ለረዥም ጊዜ ፋይዳ ትልም ይዞ የተነሳ ሥራ ሲጠናቀቅ ለሁሉም ባለድርሻ አካል ብሎም ለሰፊው ሕዝብ የሚሰጠው ጥቅም ትልቅ ነው። በተጨማሪም እየተስተዋለ ያለው አዲስ የሥራ ባህል ማቆጥቆጥ በመላው ሀገራችን ሊቀዳ እና ሊባዛ የሚገባው ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
