Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
ኤጀንሲው በቴክኖሎጅ ታግዞ እየሰጠ ያለውን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ግልፅነት የተላበሰ አገልግሎት በማጠናከር እንደ ከተማም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል ሆኖ መውጣት ይኖርበታል ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት የሪፎርም ቀንን ምክንያት በማድረግ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በቴክኖሎጅ የዘመነ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ ቤትን ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እና ሌሎች የከተማ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን አስመርቀዋል።
በዚሁ ወቅት ኢንጅነር ወንድሙ እንደተናገሩት የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በሪፎርሙ ባከናወናቸው ተግባራት ያስመዘገባቸው ውጤቶች እና በተለይም በቴክኖሎጅ የተደገፉ ስራዎች ለሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የተጣራ መረጃ ሞንጭ ወደ መሆን እየተሸጋገረ መሆኑ አበረታች ነው ሲሉ አድንቀዋል።
ተቋሙ ይህንን ተግባር በማጠናከር የከተማው ነዋሪዎች በአገልግሎት የሚረኩበት እና ወሳኝ እና ተፈላጊ ተቋም እንዲሆን እና እስካሁን ያስመዘገባቸውን አስደማሚ ለውጦች በማጠናከር እንደ ከተማም ሆነ በአገርአቀፍ ደረጃም ሞዴል ሆኖ መውጣት ይኖርበታል ሲሉ አስገንዝበዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.
ዘመናዊ ያልሆኑ አሰራሮችን በማዘመን የማህበረሰባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል፡፡
አቶ ሞገስ ባልቻ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት በአዲስ መልክ የታደሰውን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት መርቀዋል፡፡
ጳጉሜ ሁለት የኢትዮጵያ የሪፎርም ቀን እንዲሆን በማድረግ የተጀመረው ሪፎርማችን እንዲቀጥል ማድረግ ይገባናል ያልሉት የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ የቆዩ አሰራሮችን በማስተካከል ወደ ዘመናዊነት የመቀየር ሥራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ፓርቲያችን ብልፅግና ለህዝብ አገልግሎት መሻሻል በመንግስት በኩል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንን የሚያሳይ ተግባር ላይ መሆናችንን በዛሬው ዕለት ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል አቶ ሞገስ፡፡
አራዳ ክፍለ ከተማ እየለማች ያለች በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጣችንም ያልዘመነበት ሁኔታን የመለወጥ ስራው ከሁሉም በፊት ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ ነው ሲሉ አቶ ሞገስ ባልቻ አክለው ገልፀዋል፡፡
አቶ ጌታሁን አበራ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲሆኑ በክፍለ ከተማችን በዛሬው ዕለት የጳጉሜ 2 ቀንን ስናከብር የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መለወጥ ያለበትን ያልዘመነ አሰራር ለመለወጥ ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ፅህፈት ቤት የኤስ.ኤም.ኤስ ዲጂታል አገልግሎት በይፋ አስጀመረ
ጳግሜ 2/2016 ዓ.ም
ተቋሙ "ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት" በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረውን የፊፎርም ቀን ምክንያት በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡን የተሳለጠ እና የተቀላጠፈ ለማድረግ የሚያግዘውን የኤስ.ኤም.ኤስ ዲጂታል አገልግሎት የከተማ፣የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በይፋ አስጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ እንደገለፁት ተቋሙ ሁሉም ነዋሪ አገልግሎት ለማግኘት የሚመጣበት መሆኑን አንስተው የሚሰጡ አገልግሎቶች ዘመኑን የዋጀ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንግልትን ያስቀረ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ወረዳዎች የዲጂታል አገልግሎት በመስጠት ቀዳሚ በመሆኑ ምስጋና አቅርበዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው ጳግሜ 2 የሪፎርም ቀን መሆኑን በማንሳት የሪፎርም ዋና አላማም አገልግሎትን ማሳለጥ በመሆኑ በክፍለ ከተማው የሚሰጡ አገልግሎቶች ምቹ፣ቀልጣፋ እና ፈጣን ለማድረግ የክፍለ ከተማና የወረዳ ተቋማት ቢሮ የማዘመን እና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አንስተው በሁሉም ወረዳዎች የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ተቋማት የዲጂታል አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ገልፀዋል።
የኤስ.ኤም.ኤስ ዲጂታል አገልግሎቱ ተገልጋዮች በቤታቸው ሆነው አገልግሎቱን እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ለስራው መሳካት አስተዋፅኦ ስለነበራቸው አካላት እውቅና ተሰጥቷል።
Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዋሬ የተገነባው የመኖሪያ መንደር ብቻ ሳይሆን የሰውን ህይወት እና አኗኗር እንዲሁም አካባቢን እንደ አዲስ የመቀየረ ተግባር ሲሆን የአዋሬ የጋራ መኖሪያ መንደር 275 መኖሪያ ቤቶችን፣ 130 ሱቆችን፣ 3 ሰፋፊ እና አካፋይ መንገዶችን፣ የወንዝ ዳርቻ ልማትን፣ የአረንጓዴ ቦታዎች ልማትን፣ የህፃናት መጫወቻን እንዲሁም የመኪና ማቆሚያዎችን ያካተተ ነው።
ለአዋሬ ተነሺዎች ለተገነቡት አምስት ባለ 11 ወለል ህንፃዎች ግንባታ እና አርዓያነት ያለው የመሪነት ሚና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን በከተማችን ነዋሪዎች ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ኮሚሽን መ/ቤቱ አገልግሎቱን ለማዘመን በሙከራ ትግበራ ላይ ያዋላቸው የቴክኖሎጂ ስራዎች በከተማ አስተዳደሩ የስራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ፡፡
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂው ለማዘመን የሚያስችለው የቴክኖሎጂ የሙከራ ትግበራ ስራ በአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ተጎብኝቷል ፡፡
በጉብኝት መርሀ ገብሩ ላይ በቢሮ ሃላፊ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተፈራ ሞላ እና በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ስራ አሰኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ፣ ኮሚሸነር ፍቅሬ ግዛው፣ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አቶ ሰለሞን አማረ የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ተገኝተዋል።
በጉብኝቱ በሙከራ ላይ የሚገኘው የቴክኖሎጂ ትግበራ አደጋ በደረሰበት ቦታ የሚደረግ በረራንና በአደጋው ቦታ ያለውን የአደጋ ሁኔታ በቀጥታ በቪዲዮ የሚያስመለከት እንደሆነ በሙከራ ትግበራዉ እንዲታይ ተደርጓል ፡፡
በሌላ በኩልም ለኮሚሽኑ ሰራተኞች አገልግሎት እየሰጠ ያለው ክሊኒክ ከወረቀት አሰራር ነጻ የሆነ ቴክኖሎጂን ለመተግበር በሙከራ ስራ ላይ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
አመራሮቹ ከጉብኝቱ በኃላ በሰጡት አስተያየት አዲስ አበባ ከተማ አሁን ከደረሰችበት ዕድገት አንጻር አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ማከናወን መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቀሰው በዚህ መነሻም የኮሚሽን መ/ቤቱ የሪፎርም አካል በሆነው በቴክኖጂዉ ዘርፍ እያከናወናወኑ ያሉ ተግባራት ለውጥ ማምጣቸውን ጠቅሰው ቀሪ ስራዎች ተጠናቀዉ በፍጥነት ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባም አሳስበዋል ፡፡
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
አዋሬን ለሰው ልጅ ክብር ምቹ አድርጎ ወደ ህያውነት የመለወጥ ትልማችን እና ጥረታችን እውን ሆኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
10000000_380756961737744_7523393244771119431_n.mp4.crdownload24.97 MB
ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት!
በሪፎርም ጀምረን ትልቅ ውጤት ካስመዘገብንባቸው ስራዎች አንዱ የሆነው እና ለረዥም ጊዜያት የህዝባችን የቅሬታ ምንጭ የነበረው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በ119 ወረዳዎች ዲጂታላይዝ አድርገን የዜጎቻችንን እንግልት መቀነስ የሚያስችል ደረጃ ላይ በማምጣታችን በጣም ደስ ብሎናል::
የሪፎርማችን ውጤታማነት የሚለካው ለህዝባችን ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት በመሆኑ አገልግሎትን የሚያቀላጥፍ እና የህዝቡን እንግልት የሚቀንስ የሪፎርም ስራዎችን ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ በሁሉም ተቋሞቻችን ላይ በከፍተኛ ተነሳሽነት በመስራት ላይ እንገኛለን::
ዛሬ ያስመረቅነው የዲጂታላይዜሽን ስራ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ ያለውን የቴክኖሎጂ መስመር በአዲስ አሰራር የቀየረ፣ 119ኙም የተቋሙ ጽ/ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ በቀጥታ በካሜራ ቁጥጥር የሚደረግበት (Command Center) ያቀፈ፣ በአይነቱ በሃገራችን የመጀመርያ የሆኑ የዘርፉ መፍትሄዎችን የያዘ እንዲሁም በከተማችን የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አብዮት በጎውን ከክፉው አጃምሎ ጠርጎብናል። ተሻጋሪ ተቋሞች ለመገንባት አላስቻለንም። ለዚህ ነው ሪፎርምን የመረጥነው። እየመዘንን፣ እያነጠርን፣ እየመረመርን የሚበጀንን እንወስዳለን፤ የማይበጀንን እንጥላለን።
በዚህ ዕሳቤ ታላላቅ ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው። የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ ዘርፍ፣ የሕግ፣ የግብርና፣ የትምህርት፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሞችን እያሳካን በመጓዝ ላይ ነን። በትብብር ከሠራን የማናሳካው ሪፎርም፤ የማይደረስበት ብልጽግና አይኖርም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
