Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
አዲስ አበባ በአለም የከተሞች ቱሪዝም ፌደሬሽን ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነዉ
አዲስ አበባ ከተማ የአለም የከተሞች ቱሪዝም ፌደሬሽን አባል የሆነችበት የ2025 የአለም ከተሞች ቱሪዝም ፌደሬሽን ዓመታዊ ጉባዔን በቻይና ሆንግ ኮንግ እየተሳተፈች ነው።
በጉባዔው የአባል ከተሞች ከንቲባዎች እና የዘርፉ ኃላፊዎች፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ክቡር ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና የአዲስ አበባ ከተማ የባህል፣ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ኂሩት ካሳው( ዶ/ር) እንዲሁም የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እየተሳተፉ ነው።
ሀረር ከተማ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023 የዓለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆኗ መመዝገቧን ተከትሎ ዘንድሮ በተካሄደው ጉባኤ የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል መሆን መቻሏን የቢሮው ኃላፊ ኂሩት ካሳው (ዶ/ር)በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሳውቀዋል፡፡
ክቡር ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና ክቡር ኦርዲን በድሪ በአባል ከተሞች የከንቲባዎች ፎረም መክፈቻ ላይ ሁለቱን ከተሞች በጉባዔው ለተሳተፉ ከንቲባዎች ማስተዋወቃቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ አፍሪቃዊቷ መልኅቅ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
Femmes d’Afrique" መጽሔት በጥበበኛ ሴቶች አመራር ላይ ያተኮረ ፓን-አፍሪካዊ ወርሃዊ መጽሔት ! መጀመሪያው የአዲስ አበባ ሴት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አሁን በሞሮኮ የመጀመሪያው ዲጂታል የዜና መስመር በሆነው በካፕሊን እና በአካባቢዎ በሚገኙ የጋዜጣ መሸጫዎች ላይ ይገኛል።
በወቅታዊ ጉዳዮች እና በልዩ የአፍሪካ ሴቶች አስደናቂ ስኬቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገው መጽሔቱ፤
በሽፋን ታሪክ፡- *የአዲስ አበባ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ* ከሆኑት ከወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጋር የተደረገ ልዩ ቃለ መጠይቅ ይዞ ወጥቷል::
የከንቲባዋን አስደናቂ ጉዞ እና እየመሯት ያለችው የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የወደፊት ዕጣ ፈንታን በተመለከተ ያላቸው ጽኑ ራዕይ ላይ ትኩረቱ ያደርጋል! በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ፡- ማህበረሰብ እና የህዝብ ድጋፍ በአፍሪካ አህጉር አቀፍ የሴቶች መብት ቀንን ማክበር ፤ የአንጎላ ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ እስፔራንሳ ዳ ኮስታ፤ የጋቦን ቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ ሴልማ ዚታ ኦሊጊ ንጉኤማ፤ የቶጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ወ/ሮ ቪክቶር ቶሜጋህ-ዶግቤ እና ሌሎች ብዙ አነቃቂ ሴቶችን ያካትታል።
ፖለቲካ እና አመራር በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይም በ29ኛው የቀዳማዊ እመቤቶች ጉባኤ ላይ ያተኩራል።
የሴራሊዮን የቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ ፋቲማ ማዳ ባዮ የኦፒዲኤድ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡ ሲሆን፣ የአንጎላዋ ወ/ሮ አና ዲያስ ሎሬንሶ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል። እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ውስጥ ታዋቂ ሰዎች የሆኑት ስለ ወ/ሮ ሰልማ ማሊካ ሀዳዲ፣ ወ/ሮ አማ ትውም-አሞአ እና ወ/ሮ ሌራቶ ዶሮቲ ማታቦጌ ግንዛቤዎችን ያቀርባል።
የስፖርት ትኩረት፡- ለዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የተመረጡ የመጀመሪያዋ ዚምባቡዌዊት ሴት ክሪስቲ ኮቨንትሪ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመንገድ ዳር የተተከሉ ዘመናዊ የመብራት ምሶሶዎች እና አገልግሎታቸው
AMN-Addis Media Network
ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በከተማው በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ክንውን 64,075 የተወለዱ ህፃናትን በ90 ቀን ውስጥ የልደት ምዝገባ ማደረግ መቻሉ ተገለፀ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጠቅላላ ካውንስል የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የስራ አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡
በዘጠኝ ወራቱ አፈፃፀም:
ከሲቪል ምዝገባ ዘርፍ አኳያ
* ከኩነት ምዝገባ እኳያ በጥቅሉ የወቅታዊ ምዝገባ ሽፋን 109.63 በመቶ አፈፃፀም የተመዘገበ ሲሆን የልደት ምዝገባ የፍቺ ምዝገባ እንዲሁም የጉዲፈቻ መሆኑ የተገመገመ ሲሆን ይህም በከተማው የተዘረጋው የጤና ማዕከላት እና የፍርድ ቤቶች የአንድ ማዕከል የኩነት ምዝገባ አገልግሎት ስርዓት ውጤት መሆኑ ታይቷል።
* በከተማችን 58,342 ህፃናትን በተወለዱ በ90 ቀናት ውስጥ በወቅቱ የልደት ምዝገባ ለማድረግ ታቅዶ 64,075 ምዝገባ በማድረግ ከ100% በላይ መፈፀም የተቻለ ሲሆን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር 71.15% ብልጫ አሳይቷል።
* በድምሩ 341,674 ወሳኝ ኩነቶችን ( የልደት፣ ጉዲፈቻ፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ሞት ) በወቅቱ፣ በዘገየ እና ጊዜ ገደቡ ባለፈ መዝግቦ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 308,289 በመመዘገብ የእቀዱን 90.23 በመቶ ማከናወን የተቻለ ቢሆንም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1.52% ቅናሽ ያሳይል። ቅናሽ ካሳዩ ምዝገባዎች ጋብቻ ሲሆን ፍቺ በንፅፅር ብልጫ አሳይቷል።
የፍቺ እና ጉዲፈቻ ምዝገባ ከአምናው የምዝገባ ስርዓት ለውጥ የተደረገበት ሲሆን ልክ እንደ ጤና ተቋማት ሁሉ በፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት በመቻሉ አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
በአሁኑ ወቅት ጤና ተቋማት ፣ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በድምሩ 170 ማዕከላት ከመደበኛ ቢሮ ውጭ የወሳኝ ኩነት የአንድ ማዕከል ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከላት ናቸው።
ከነዋሪነት አገልግሎት ዘርፍ አንፃር:
* 509,938 ነዋሪዎችን ወደ ዲጂታል ምዝገባ ለማስገባት ታቅዶ ክንውን 528,495 (104%) ሲሆን ከአምናው 22.54% ብልጫ አለው፡፡ ይህም በዋናነት በ2016ዓ.ም በማንዋል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 14 ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል በመሸጋገራቸው የመጣ አብላጫ ነው።
* 473, 924 የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በአዲስ ፣ በእድሳት፣ በእርማት እና በምትክ ለመስጠት ታቅዶ 339,048 በመስጠት የእቅዱ 71.54 በመቶ ተከናውኗል። ከዚህም ውስጥ 97.03 በመቶ ዲጅታል መታወቂያ የተሰጣቸው ሲሆን ቀሪው ለአቅመ ደካሞች እና ታማሚዎች የቤት ለቤት አገልግሎት ፣ የጣት አሻራቸው ለተጓዳ እንዲሁም አሻራ መስጠት ለማይችሉ አካል ጉዳተኞች የተሰጠ ነው።
ተጠያቂነትን በተመለከተ:
* 188 የአሰራር ጥሰት የፈፀሙ፣ አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ የሞከሩ፣ የስራ ቦታ ስነ- ምግረር ያላከበሩ እና በሃሰተኛ መረጃ አገልግሎት ለማግኘት ጥረት ያደረጉ አመራር፣ ፈፃፀሚ እና ባለጉዳይ ተጠያቂ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ከተጠቀሰው ውስጥ የተገልጋይ ቁጥር 33 መሆኑ ተነግሯል።
በዕለቱ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክቶሬት አቶ ዮናስ አለማየሁ በጥሩ አፈፃፀም የታዩት እንደተጠበቀ ሆኖ በጉድለቶች ላይ መስራት እንዲቻል የቀጣይ ቀሪ ወራት አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን ከተሰጠው አግልግሎት ቁጥር ባሻገር የተገልጋይ እርካታ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስብዋል።
ለበለጠ መረጃ በነፃ መስመር 7533 ወይም 9779 ይደውሉ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
አዲስ አበባ በአለም የከተሞች ቱሪዝም ፌደሬሽን ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነዉ
አዲስ አበባ ከተማ የአለም የከተሞች ቱሪዝም ፌደሬሽን አባል የሆነችበት የ2025 የአለም ከተሞች ቱሪዝም ፌደሬሽን ዓመታዊ ጉባዔን በቻይና ሆንግ ኮንግ እየተሳተፈች ነው።
በጉባዔው የአባል ከተሞች ከንቲባዎች እና የዘርፉ ኃላፊዎች፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ክቡር ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና የአዲስ አበባ ከተማ የባህል፣ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ኂሩት ካሳው( ዶ/ር) እንዲሁም የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እየተሳተፉ ነው።
ሀረር ከተማ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023 የዓለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆኗ መመዝገቧን ተከትሎ ዘንድሮ በተካሄደው ጉባኤ የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል መሆን መቻሏን የቢሮው ኃላፊ ኂሩት ካሳው (ዶ/ር)በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሳውቀዋል፡፡
ክቡር ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና ክቡር ኦርዲን በድሪ በአባል ከተሞች የከንቲባዎች ፎረም መክፈቻ ላይ ሁለቱን ከተሞች በጉባዔው ለተሳተፉ ከንቲባዎች ማስተዋወቃቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ አፍሪቃዊቷ መልኅቅ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
"Femmes d’Afrique" መጽሔት በጥበበኛ ሴቶች አመራር ላይ ያተኮረ ፓን-አፍሪካዊ ወርሃዊ መጽሔት ! መጀመሪያው የአዲስ አበባ ሴት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አሁን በሞሮኮ የመጀመሪያው ዲጂታል የዜና መስመር በሆነው በካፕሊን እና በአካባቢዎ በሚገኙ የጋዜጣ መሸጫዎች ላይ ይገኛል።
በወቅታዊ ጉዳዮች እና በልዩ የአፍሪካ ሴቶች አስደናቂ ስኬቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገው መጽሔቱ፤
በሽፋን ታሪክ፡- *የአዲስ አበባ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ* ከሆኑት ከወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጋር የተደረገ ልዩ ቃለ መጠይቅ ይዞ ወጥቷል::
የከንቲባዋን አስደናቂ ጉዞ እና እየመሯት ያለችው የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የወደፊት ዕጣ ፈንታን በተመለከተ ያላቸው ጽኑ ራዕይ ላይ ትኩረቱ ያደርጋል! በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ፡- ማህበረሰብ እና የህዝብ ድጋፍ በአፍሪካ አህጉር አቀፍ የሴቶች መብት ቀንን ማክበር ፤ የአንጎላ ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ እስፔራንሳ ዳ ኮስታ፤ የጋቦን ቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ ሴልማ ዚታ ኦሊጊ ንጉኤማ፤ የቶጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ወ/ሮ ቪክቶር ቶሜጋህ-ዶግቤ እና ሌሎች ብዙ አነቃቂ ሴቶችን ያካትታል።
ፖለቲካ እና አመራር በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይም በ29ኛው የቀዳማዊ እመቤቶች ጉባኤ ላይ ያተኩራል።
የሴራሊዮን የቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ ፋቲማ ማዳ ባዮ የኦፒዲኤድ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡ ሲሆን፣ የአንጎላዋ ወ/ሮ አና ዲያስ ሎሬንሶ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል። እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ውስጥ ታዋቂ ሰዎች የሆኑት ስለ ወ/ሮ ሰልማ ማሊካ ሀዳዲ፣ ወ/ሮ አማ ትውም-አሞአ እና ወ/ሮ ሌራቶ ዶሮቲ ማታቦጌ ግንዛቤዎችን ያቀርባል።
የስፖርት ትኩረት፡- ለዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የተመረጡ የመጀመሪያዋ ዚምባቡዌዊት ሴት ክሪስቲ ኮቨንትሪ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመንገድ ዳር የተተከሉ ዘመናዊ የመብራት ምሶሶዎች እና አገልግሎታቸው
AMN-Addis Media Network
ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የተቋማዊ ባህል ምንነት ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለሠራተኞቹ ሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ የተቋማዊ ባህል ምንነት እና ግንባታ ላይ ያተኮረ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለፅ/ቤቱ ባለሙያዎች ሰጥቷል።
ስልጠናዉን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት አማካሪ አቶ ይብሬ ኢስማኤል ናቸው።
የስልጠናው ዋና አላማ የተቋማዊ ባህል እሴቶች ግንባታ አስፈላጊነት፣ ጠንካራ የተቋማዊ ባህል እና የስራ ውጤታማነት፣ የተቋም ባህል የመሪነት ሚናና እና ግኑኝነቶች፣በተቋም ባህል የመሪነት ሚናና ማእቀፎች እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለተቋሙ ባለሙያዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖሯቸው እና በጠንካራ የተቋም ባህል ግንባታ ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማድረግ ያለመ መሆኑን የጽ/ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጥ የስልጠና ቡድን መሪ ተወካይ የሆኑት አቶ ደስታ ፈንታ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪዎች እየተሰጠ ያለው አገልግሎት በቴክኖሎጅ የዘመነ እና መጉላላትን የቀነሰ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን በማዘመን ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘገባ ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የፋይዳ ልዩ ቁጥር በማጋራት የሚፈጠር ስርቆት አይኖርም
ባለ 12 አሀዝ የፋይዳ ልዩ ቁጥር በህይወት ዘመን አብሮ የሚቆይ የማይቀየር ቁጥር ሲሆን የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (16 አሀዝ) ቁጥር የሚባለው ደግሞ በተወሰነ ጊዜ የሚቀየር ቁጥር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር አንድ ግለሰብ ትክክለኛት ለማረጋገጥ አገልግሎት የሚያገለግል ነው፡፡
ነገር ግን ይህ ቁጥር በባዮሜትሪክ መረጃ የተደገፈ ልዮነትን የሚገልፅ በመሆኑ የአንድን ሰው ፋይዳ ልዩ ቁጥር በማጋራት የሚመጣ ምንም አይነት የማንነት ስርቆት ወይም ሌላ አገልግሎት ተመሳስሎ የሚገለገልበት አግባብ አለመኖሩን ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ 2017 የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም መገምገም ጀምረናል። በግምገማችን የሚቀጥሉትን ሶስት ወራት ሥራዎቻችንን እቅድ ለማጠናከር የሚረዱ ውይይቶችን እናካሂዳለን። እስካሁን ያሳካነው የሥራ ውጤት ሰፊ ቢሆንም ስኬታችን ሳያዘናጋን ለበለጠ ከፍታ የሚያነሳሳን ሊሆን ይገባል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
