Addis Ababa City Manager Office
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
1 474
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
" የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም "
አካባቢን በማፅዳትና ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ አምራች ዜጋ ፣ ጤናማና ሰላሙ የተጠበቀ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚቻል ተገለፀ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት " የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም " በሚል መሪ ቃል ወረዳ 7 ልዩ ቦታው በርታ አካባቢ በርካታ ነዋሪ የተሳተፈበት የክረምት የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል።
በፅዳት ንቅናቄው የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ ፣ የክ/ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ ፣ የወረዳ 07 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ነፃነት ያዛቸው ፣ የፀጥታ አካላት ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ አካባቢው ለጎርፍ ተጋላጭ በመሆኑ ማህበረሰቡ የቅድመ መከላከል ስራዎችን በስፋት ሊሰራ እንደሚገባና የፅዳት ንቅናቄዎች ዓላማ በማህበረሰቡ ዘንድ ግንዛቤ በመፍጠር ያለ ማንም ቀስቃሽ አካባቢው በየጊዜው የሚያፀዳ ዜጋ ያለመ ለመፍጠር መሆኑን ገልፀው አካባቢን በማፅዳት ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ ከተቻለ አምራች ዜጋን ፣ ጤናማ መህበረሰብን መፍጠር ፣ ሰላሙ የተጠበቀ እንዲሁም ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር የሚቻል መሆኑን ተናግረዋል።
የወረዳ 07 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ነፃነት ያዛቸው በበኩላቸው ከተማዋን እንደ ስምዋ ውብ ፅዱ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ አንስተው በወረዳው የሚገኙ ብሎኮችን ፅዱ በማድረግ ሞዴል አካባቢን ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝ ለዚህም የሁሉም አካላት ርብርብ የሚፈልግ መሆኑን ተናግረዋል ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ በበኩላቸዉ በክፍለ ከተማው የፅዳት ስራዎችን በበጋና በክረምት ወቅት በመከፉፈል ፅዱና ውብ አካባቢን መፍጠር መቻሉን አንስተው መጪው ወቅት ክረምት እንደመሆኑ በተደፈኑ ቱቦዎችና በቆሻሻዎች ምክንያት የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት አካባቢውን ማፅዳትና የተደፈኑ ቱቦዎችን መክፈት እንደሚገባ ጠቅሰዉ ለማህበረሰቡ በስፋት ግንዛቤን መፍጠር እንደሚገባ ነገር ግን ቆሻሻን ያለ አግባቡ በሚጥሉ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል ።
Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ክረምት በመጣ ቁጥር በርካታ ጉዳት ሲያደርሱባቸው የነበሩ ወንዞች ላይ ድልድይ በመሰራቱ እፎይታ ያገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ነዋሪዎች
AMN - ግንቦት 22/2017 ዓ.ም
የመዲናዋን የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት ስጋት ለመቅረፍ እየተሰራ ያለውን ስራ በተመለከተ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የሰጡት ማብራሪያ
AMN - ግንቦት 22/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መቀመጫውን ጋና ካደረገውና በዘመናዊ የቆሻሻ አወጋገድ የካበተ ልምድ ካለው ጆስፖንግ ግሩፕ ኩባንያ ጋር በመዲናዋ የሚመነጨውን ቆሻሻ በውጤታማነት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ መዲናችን ደረቅ ቆሻሻን መልሶ የመጠቀም አገልግሎት ጋር በተያያዘ እያስመዘገበች ያለውን ውጤት በተሻለ ደረጃ ለማስቀጠል እንደሚረዳ ገልፀዋል።
አክለውም በመዲናችን አዲስ አበባ በቆሻሻ አሰባሰብ የተመዘገበውን ውጤታማ አፈፃፀም ቆሻሻን ከምንጩ በመለዬት እና ለኮምፖስት እና ለኤሌክትሪክ ሃይል ምንጭነት በመጠቀም ረገድ ያለውን አፈፃፀም ይበልጥ በውጤታማነት ለማጠናከር ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው አስገንዝበዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አክለውም በመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ መሠረት በቀጣይ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚካሄዱ ገልፀው ይህም ከተማዋን ለነዋሪዎች ጽዱ፣ ምቹ፣ ውብ እና ለነዋሪዎች ተስማሚ የማድረግ ራእይን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አመልክተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶች በከተማችን እየተከናወኑ ያሉ ግዙፍ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል ። ከጉብኝት በኋላ በፅህፈት ቤታችን ተቀብለን በተለያዩ ከተማ አቀፍ ጉዳዮች እና የጋራ ስራዎች ዙሪያ ተወያይተናል።
ብፁዓን አባቶቻችን ከለውጡ ጀምሮ በከተማችን መንግሥት ያከናወናቸውን የልማት ስራዎች በመጐብኛት ለተሰሩት ስራዎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸው፣ በቀጣይ ጊዜያትም ፈጣሪ ክንውንን እንዲሰጠን በፀሎት እና በቡራኬ እንደማይለዩን ገልጸውልናል።
እኛም የሀገራችን ብቻ ሳይሆን የአህጉራችን መዲና እና የዓለም አቀፉ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ መናገሻ የሆነች አዲስ አበባችንን ይበልጥ ለመለወጥ ያለንን ቁርጠኝነት እየገለጽን፣ አባቶቻችን በምክር እና ጸሎት ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ስላሉ እና ስላበረታቱን ከልብ እናመሰግናለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 46ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን 2018-2022 የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ ማዕቀፉ የመንግስትን ገቢ መሠረት በማስፋት ወጪ ለመሸፈንና የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ፣ ከመንግስት ገቢ አሰባሰብ እና ሀብት አመዳደብ አኳያ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማመላከት ለቀጣይ በጀት አመት የበጀት ዝግጅት መነሻ ሆኖ እንዲያገለግል ማዕቀፉ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው ከአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት እና ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር ጋር በተፈረሙ ሁለት የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ ከአረብ ባንክ የተገኘው 49,550,000 የአሜሪካ ዶላር ከግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር በማስተሳሰር ለወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ሲሆን አነስተኛ ወለድ የሚከፈልበት እና የ5 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ20 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር የተገኘው 45,100,000 ኤስ ዲ አር የሴቶች እና የልጃገረዶች ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሚውል ሲሆን ከወለድ ነጻ፣ 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልበት እና 6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ምክር ቤቱም ብድሮቹ ከአገራችን የብድር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
3. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን የወጣ ደንብ ላይ ነው፡፡ ተቋሙ በዚህ ረገድ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያወጣውን ወጪ ሸፍኖ የውስጥ ገቢውንም ለማሳደግ እንዲችል የተገልጋዩን የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የአገልግሎት ክፍያ ለመወሰን ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
4. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በውጭ አገር ለስራ የሚሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች መብታቸው፤ ደህንነታቸው እና ክብራቸው በዘላቂነት መጠበቁን ለማረጋገጥ እንዲሁም ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም ለማስጠበቅ እንዲያስችል ሆኖ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
5. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የዕፅዋት ጥበቃና ኳራንቲን ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የተባይ አሰሳ እና ማስጠንቀቂያ ስርዓት ለመዘርጋት፤ ዕፅዋትን፣ የዕፅዋት ውጤትንና ሌላ ቁጥጥር የሚደረግበትን ቁስ በዓለም አቀፍ የዕፅዋት ጥበቃ ስምምነት መሰረት ተቆጣጥሮ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ወደ ውጭ ለመላክ እንዲሁም ቁጥጥር የሚደረግበት ተባይ ከውጭ አገር ከገባ እንዳይስፋፋና እንዳይሰራጭ ለማድረግ እንዲያስችል ሆኖ ረቅቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
//
ተረፈ ምርትን ወደ አገልግሎት
መዲናዋ የምታመነጨውን ተረፈ ምርት በተሻለ ሁኔታ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ…
መጪውን የክረምት ወራት ታሳቢ ያደረገ በርካታ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ለዝርዝር ዘገባው ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ👉
ከክረምት መቃረብ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑና ስጋት ያለባቸው ተብለው በተለዩ ክፍለ ከተሞች ያለው የአደጋ ዝግጁነት ምን ይመስላል?
ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉
AMN-Addis Media Network
በመዲናችን አዲስ አበባ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች ላይ አደጋዉን አስቀድሞ ለመከላከል በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተከናወኑ ስራዎች ላይ የተካሄደውን የመስክ ምልከታ አስመልክቶ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬት ዘገባን በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉
መጪውን የክረምት ወራት ታሳቢ ያደረገ በርካታ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ለዝርዝር ዘገባው ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
